ሁለቱ ወንጌላት
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
2፥79 ለነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉ እና ከዚያም በእርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው፡፡ فَوَيْلٌ لِّلَّذِينَ يَكْتُبُونَ الْكِتَابَ بِأَيْدِيهِمْ ثُمَّ يَقُولُونَ هَـٰذَا مِنْ عِندِ اللَّهِ لِيَشْتَرُوا بِهِ ثَمَنًا قَلِيلًا ۖ
በባይብልም አምላክ ለኢየሱስ የሰጠውን ቃል ወንጌል ይለዋል፥ ይህንን የአምላክ ወንጌል ኢየሱስ ሲሰብከው ነበረ፦
ዮሐንስ 17፥8 "የሰጠኸኝን ቃል" ሰጥቻቸዋለሁና።
ዮሐንስ 17፥14 እኔ "ቃልህን" ሰጥቻቸዋለሁ።
ሉቃስ 4፥18 ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና።
ማርቆስ 1፥14 ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የአምላክን ወንጌል እየሰበከ ወደ ገሊላ መጣ። Καὶ μετὰ τὸ παραδοθῆναι τὸν Ἰωάνην ἦλθεν ὁ Ἰησοῦς εἰς τὴν Γαλιλαίαν κηρύσσων τὸ εὐαγγέλιον τοῦ Θεοῦ
ኢየሱስ አምላኩ የሰጠውን የአምላክ ወንጌል ለአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ሰጥቶ እነርሱም ይህን ወንጌልን ሰበኩ፥ ይህ ወንጌል ለእስራኤል ቤት እንጂ ለአሕዛብ እና ለሳምራውያን አልመጣም፦
ሉቃስ 9፥6 ወጥተውም "ወንጌልን እየሰበኩ" እና በስፍራው ሁሉ እየፈወሱ በየመንደሩ ያልፉ ነበር።
ማቴዎስ 10፥5-6 እነዚህን አሥራ ሁለቱን ኢየሱስ ላካቸው፥ አዘዛቸውም፥ እንዲህም አለ፦ "በአሕዛብ መንገድ አትሂዱ፥ ወደ ሳምራውያንም ከተማ አትግቡ፥ ይልቅስ የእስራኤል ቤት ወደሚሆኑ ወደ ጠፉት በጎች ሂዱ እንጂ"።
"መሢሕ ይመጣል" ብለው የሚጠብቁት አይሁዳውያን እንጂ አሕዛብ ስላልሆነ የመሢሑ ወንጌል ትርጉም ያለው ለእስራኤል ቤት ብቻ ነው፥ ኢየሱስ ከአብ የተላከው ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች ሲሆን በተመሳሳይ ኢየሱስ ሐዋርያትን የላከው የእስራኤል ቤት ወደሚሆኑ ወደ ጠፉት በጎች ብቻ ነው፦
ማቴዎስ 15፥24 እርሱም መልሶ፦ "ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላክሁም" አለ።
ዮሐንስ 20፥21 ኢየሱስም ዳግመኛ፦ ሰላም ለእናንተ ይሁን፤ አብ እንደ ላከኝ እኔ ደግሞ እልካችኋለሁ" አላቸው።
"አብ እንደ ላከኝ እኔ ደግሞ እልካችኋለሁ" የሚለው ይሰማርበት! በ 70 ድኅረ ልደት ጀነራል ጢጦስ ኢየሩሳሌም እና ቤተ መቅደሱን በእሳት ሲያጋይ የእስራኤል ቤት ተበተኑ፦
ያዕቆብ 1፥1 የእግዚአብሔር እና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ያዕቆብ "ለተበተኑ ለአሥራ ሁለቱ ወገኖች" ሰላም ለእናንተ ይሁን።
የተበተኑት ቅድሚያ በአሶር፣ ቀጥሎ በባቢሎን፣ ለጥቆ በሮማውያን ነው። የእስራኤል ቤት አሥራ ሁለቱ ነገዶች ሲኖሩት በኢየሱስ የተሾሙት ወንጌሉን ለእስራኤል ቤት የሚናገሩት ሐዋርያትም አሥራ ሁለት ብቻ እና ብቻ ናቸው፦
ማቴዎስ 19፥28 እናንተ ደግሞ በአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ስትፈርዱ በአሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ።
ወንጌሉን ካሰሙ በኃላ የፍርድ ቀን በአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ለመፍረድ በአሥራ ሁለት ዙፋን ላይ የሚቀመጡት አሥራ ሁለቱ ሐዋርያ ብቻ ናቸው። የእስራኤል ቤት የተገረዙ አይሁዳውያን ሲሆኑ የአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ዋና መሪ ጴጥሮስ ከኢየሱስ ለተገረዙት የሆነ ሐዋርያ ሲሆን ጳውሎስ ደግሞ እራሱን "ለአሕዛብ ሐዋርያ" በማድረግ እራሱን ሾሟል፦
ገላትያ 2፥8 "ለተገረዙት ሐዋርያ" እንዲሆን ለጴጥሮስ የሠራለት፥ ለእኔ ደግሞ "ለአሕዛብ ሐዋርያ" እንድሆን ሠርቶአልና።
በዚህም ምክንያት ጴጥሮስ "ለተገረዙት የሆነው ወንጌል" ከኢየሱስ አደራ እንደተሰጠው ጳውሎስ ደግሞ "ላልተገረዙት የሆነው ወንጌል" አደራ እንደተሰጠው በማመላከት ሁለት ወንጌሎች ማለትም "ለተገረዙት የሆነው ወንጌል" እና "ላልተገረዙት የሆነው ወንጌል" እንዳለት ጳውሎስ ተናግሯል፦
ገላትያ 2፥7 ተመልሰው ግን ጴጥሮስ "ለተገረዙት የሆነው ወንጌል" አደራ እንደ ተሰጠው እንዲሁ ለእኔ "ላልተገረዙት የሆነው ወንጌል" አደራ እንደ ተሰጠኝ አዩ።
ጳውሎስ ለአሕዛብ(ለግሪካውያን እና ለሮማውያን) የሰበከው የኢየሱስን ወንጌል እና የትንሳኤውን ወንጌል በመቀላቀል ነው፦
የሐዋርያት ሥራ 17፥18 ሌሎችም የኢየሱስን እና የትንሣኤውን ወንጌል ስለ ሰበከላቸው፦ "አዲሶችን አማልክት የሚያወራ ይመስላል" አሉ።
ጳውሎስ በግሪክ አቴና ከኤፊቆሮስ ወገን እና ኢስጦኢኮች ከተባሉት ፈላስፎች ሲገናኝ "የትንሳኤውን ወንጌል" ሲሰብክላቸው "አዲሶችን አማልክት የሚያወራ ይመስላል" ያሉት ምክንያት አዲሶቹ አማልክት የተባሉት ሞተው የተነሱት አማልክት"Dying-and-rising deitys" ሲሆኑ እነርሱም "አቲስ" Ἄττις የሚባለው አምላክ፣ "ዛግሩስ" Ζαγρεύς የሚባለው አምላክ፣ "ዲኦንይሱስ" Διόνυσος የሚባለው አምላክ ናቸው።
ለዚህ ነው ከ 100-165 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረው ዐቃቢ ክርስትና እና የሄለናዊ ፈላስፋ ዮስጦስ ሰማዕቱ"Justin Martyr" የኢየሱስ ስቅለት፣ ሞት እና ትንሳኤ የጂፒተር ልጆችን ግሪካውያን ከሚያምኑበት ጋር ተመሳሳይ እንጂ የተለያየ ነገር እንዳልሆነ የተናገረው፦
እንዲሁ የአምላክ በኵር የሆነው ቃል ያለ ተራክቦ መገኘት እና መምህራችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቀለ፣ ሞተ እና ተነሳ ስንል እናንተ የጂፒተር ልጆችን ከምታምኑባቸው ጋር ተመሳሳይን እንጂ የተለያየ ነገር አላመጣንም።
The Ante-Nicene Fathers: The first Apology of justin chapter 21

ጳውሎስ ይህ ላልተገረዙት የሆነ የትንሳኤ ወንጌል ከኢየሱስ እግር ሥር እንደ ሐዋርያቱ የሰማው ሳይሆን "ኢየሱስ ክርስቶስ ገልጦልኛል" በማለት በመገለጥ እንዳገኘው ይናገራል፦
ገላትያ 1፥11 ወንድሞች ሆይ፥ በእኔ የተሰበከ ወንጌል እንደ ሰው እንዳይደለ አስታውቃችኋለሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ገልጦልኛል እንጂ እኔ ከሰው አልተቀበልሁትም አልተማርሁትምም።
ሄለናዊ ግሪክ ለሆኑት ለገላቲያ ሰዎች ጳውሎስ የሰበከው ላልተገረዙት የሆነ የትንሳኤ ወንጌል ሲሆን እርሱ ከሚሰብከው ላልተገረዙት ከሆነው ወንጌል ሌላ የተገረዙት ለሆኑት የሆነውን ወንጌል የሰበከ እርግማን እንዳለበት ተናግሯል፦
ገላትያ 1፥8 ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ "ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን" ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን።
ጳውሎስ "ተገለጠልኝ" የሚለው ይህን የአሕዛብ ወንጌል ለዋኖቹ ለአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት እንደነገራቸው፣ ለእነዚህ ዋነኞች አለቆች ግድ እንደማይሰጠው እና ኬፋን(ጴጥሮስን) እንደተቃወመው ሊፈረድበት እንደሚገባ ተናግሯል፦
ገላትያ 2፥2 ዋኖች ግን መስለው ለሚታዩ ለብቻቸው አስታወቅኋቸው።
ገላትያ 2፥6 አለቆች የመሰሉት ግን በፊት ማን እንደ ነበሩ አይገደኝም፤ እግዚአብሔር የሰውን ፊት አይቶ አያደላም፤ አለቆች የመሰሉት አንዳች እንኳ አልጨመሩልኝምና፥
ገላትያ 2፥11 ነገር ግን ኬፋ ወደ አንጾኪያ በመጣ ጊዜ ፊት ለፊት ተቃወምሁት፥ ይፈረድበት ዘንድ ይገባ ነበርና።
ገላትያ 2፥9 "አዕማድ መስለው የሚታዩ ያዕቆብ፣ ኬፋ እና ዮሐንስ እኛ ወደ አሕዛብ እነርሱም ወደ ተገረዙት ይሄዱ ዘንድ ለእኔ እና ለበርናባስ ቀኝ እጃቸውን ሰጡን።
"አምድ" ማለት "ምሰሶ" "መሠረት" ማለት ነው፥ የአምድ ብዙ ቁጥር "አዕማድ" ሲሆን "ምሰሶዎች" "መሠረቶች" ማለት ነው። አዕማድ የሆኑትን ያዕቆብን፣ ኬፋን እና ዮሐንስን "አዕማድ መስለው የሚታዩ" ብሎ መወረፍ አግባብ አይደለም፥ የወረፈበት ምክንያት ኢየሱስ ባዘዛቸው መሠረት ወደ ተገረዙት ስለሄዱ ነው። ለኤክሌሲያ አሥራ ሁለት መሠረቶች ነበሩአት፥ እነርሱም አሥራ ሁለቱ የኢየሱስ ሐዋርያት ብቻ እና ብቻ ናቸው፦
ራእይ 21፥14 ለከተማይቱም ቅጥር አሥራ ሁለት መሠረቶች ነበሩአት፥ በእነርሱም ውስጥ የአሥራ ሁለቱ የበጉ ሐዋርያት ስሞች ተጽፈው ነበር።
ጳውሎስ ሄለናዊ ግሪክ ለሆኑት ለቆሮንቶስ ሰዎች ከሰበከው ኢየሱስ እና ከተቀበሉት የአሕዛብ ወንጌል ሌላ የሐዋርያቱ ኢየሱስ እና ወንጌል መጥቶ ቢሰበክ እንዳይቀበሉ አስጠንቅቋል፦
2ኛ ቆሮንቶስ 11፥4 የሚመጣውም ያልሰበክነውን ሌላ ኢየሱስ ቢሰብክ፥ ወይም ያላገኛችሁትን ልዩ መንፈስ ወይም ያልተቀበላችሁትን ልዩ ወንጌል ብታገኙ፥ በመልካም ትታገሡታላችሁ።
በመቀጠል ዐውዱ ከላይ ከጳውሎስ የተለየ ወንጌል የሚሰብኩትን "እነዚህ" በማለት ዋኖቹ ሐዋርያት እንደሆኑ ጠቅሷል፦
2ኛ ቆሮንቶስ 11፥5 "ከ-"እነዚህ" ከዋነኞቹ ሐዋርያት በአንድ ነገር እንኳ እንደ ጎደልሁ ራሴን አልቆጥርም።
እነዚህን ዋነኞቹን ሐዋርያት ያዕቆብን፣ ኬፋን እና ዮሐንስን "ውሸተኞች ሐዋርያት እና ተንኮለኞች ሠራተኞች ናቸውና" በማለት ይዘልፋቸዋል፦
2ኛ ቆሮንቶስ 11፥13 እንደ እነዚህ ያሉ ሰዎች የክርስቶስን ሐዋርያት እንዲመስሉ ራሳቸውን እየለወጡ፥ ውሸተኞች ሐዋርያት እና ተንኮለኞች ሠራተኞች ናቸውና።
አዲስ ኪዳን ላይ ካሉት ሦስት አራተኛ የሆኑት አሥራ ሦስት ደብዳቤዎች የጳውሎስ ደብዳቤዎች ናቸው፥ እነዚህን ደብዳቤዎች የአሕዛብ ወንጌል ሲሆኑ እነዚህን መጽሐፍት በእጆቻቸው ለሚጽፉ እና ከዚያም በእርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «የፈጣሪ ንግግር ነው» ለሚሉ ወዮላቸው፦
2፥79 ለነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉ እና ከዚያም በእርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው፡፡ فَوَيْلٌ لِّلَّذِينَ يَكْتُبُونَ الْكِتَابَ بِأَيْدِيهِمْ ثُمَّ يَقُولُونَ هَـٰذَا مِنْ عِندِ اللَّهِ لِيَشْتَرُوا بِهِ ثَمَنًا قَلِيلًا ۖ
አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።
✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም

የጳውሎስ ስህተት
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
2፥79 ለነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉ እና ከዚያም በእርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው፡፡ فَوَيْلٌ لِّلَّذِينَ يَكْتُبُونَ الْكِتَابَ بِأَيْدِيهِمْ ثُمَّ يَقُولُونَ هَـٰذَا مِنْ عِندِ اللَّهِ لِيَشْتَرُوا بِهِ ثَمَنًا قَلِيلًا ۖ
ኢየሱስ ሲመጣ በሙሴ በኩል ከአምላክ የተሰጠውን ሕግ እና በነቢያት የተነገረውን ትንቢት ሊሽር ሳይሆን ሊፈጽም መጥቷል፦
ማቴዎስ 5፥17 እኔ ሕግን እና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም።
"ልፈጽም" ሲል "ላሟላ" "ልተገብር" ማለቱ ነው፥ በሙሴ የተነገረውን ሕግ ሊተገብር እና በነቢያት የተነገረውን ትንቢት ፍጻፌ በማድረግ ሊያሟላ ነው። ሰማይ እና ምድር እስኪያልፍ ድረስ ከሙሴ ሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም፦
ማቴዎስ 5፥18 እውነት እላችኋለሁ ሰማይ እና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፥ ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም፥ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ።
ነገር ግን ከእነዚህ ከሁሉ ካነሱት ትእዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም እንዲሁ የሚያስተምር ማንም ሰው በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ "ታናሽ" ይባላል፦
ማቴዎስ 5፥19 እንግዲህ ከእነዚህ ከሁሉ ካነሱት ትእዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም እንዲሁ የሚያስተምር ማንም ሰው በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ "ታናሽ" ይባላል።
የጳውሎስ ስሙ "ሳውል" ነው፥ ነገር ግን "ሕግ ተሽሯል" ብሎ ሲያስተምር "ጳውሎስ" ተባለ። "ፓውሎስ" Παῦλος ማለት "ታናሽ" ማለት ነው፥ የፈጣሪን ሕግ የማይረባ እና ደካማ ብሎ በመንቀፍ "ተሽራለች" ያለው ጳውሎስ ነው፦
ዕብራውያን 7፥18 ስለዚህም የምትደክም የማትጠቅምም ስለሆነች የቀደመች ትእዛዝ "ተሽራለች"።
ኤፌሶን 2፥14 በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ..።
2፥14 በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው።
ሕጉን በአዋጅ ያስነገረው እራሱ ፈጣሪ ነው፥ በትእዛዝም ያጻፈው እራሱ ፈጣሪ ነው። ነገር ግን ጳውሎስ "ተሽራል" "የዕዳ ጽሕፈት ነው" "ተደምስሷል" ይለናል፥ ይህ የጳውሎስ ስህተቱ ነው።
የጳውሎስ ሌላው ስህተቱ ፈጣሪ "ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም" ሲል ጳውሎስ በተቃራኒው "ሰው እንዲህ(ነጠላ) ሆኖ ቢኖር መልካም ነው" ይለናል፦
ዘፍጥረት 2፥18 ያህዌህ አምላክም አለ፦ "ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ረዳት ልፍጠርለት"። וַיֹּ֙אמֶר֙ יְהוָ֣ה אֱלֹהִ֔ים לֹא־טֹ֛וב הֱיֹ֥ות הָֽאָדָ֖ם לְבַדֹּ֑ו אֶֽעֱשֶׂהּ־לֹּ֥ו עֵ֖זֶר כְּנֶגְדֹּֽו׃
1ኛ ቆሮንቶስ 7፥26-27 እንግዲህ ስለ አሁኑ ችግር ይህ መልካም ይመስለኛል፤ "ሰው እንዲህ ሆኖ ቢኖር መልካም ነው"። በሚስት ታስረህ እንደ ሆንህ መፋታትን አትሻ፤ "በሚስት አልታሰርህ እንደ ሆንህ ሚስትን አትሻ"።
"በሚስት አልታሰርህ እንደ ሆንህ ሚስትን አትሻ" ምን ዓይነት ምክር ነው? ስለ ደናግል በተናገረበት ዐውድ ላይ "የአሁኑ ጊዜ ችግር" የሚለው መጋባትን ነው፥ የምነና እና የብትህውና ትምህርት ጠንሳሹ አባ እንጦስ ሳይሆን ጳውሎስ ነው፦
1 ቆሮንቶስ 7፥ 8 ላላገቡ እና ለመበለቶች ግን እላለሁ፦ "እንደ እኔ ቢኖሩ ለእነርሱ መልካም ነው"።
"እንደ እኔ (ሳያገቡ) ቢኖሩ ለእነርሱ መልካም ነው" እና "ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም" እርስ በእርሱ ይጣረሳል።
ጳውሎስ የሚቃረነው ከፈጠረው ፈጣሪ ጋር ብቻ ሳይሆን እከተለዋለው ከሚለው ከኢየሱስ ጋርም ነው፥ ኢየሱስ "ያለ ዝሙት ምክንያት ሚስቱን ፈትቶ ሌላዪቱን የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል" ሲል ጳውሎስ ደግሞ "ሚስትም ከባልዋ ብትለያይ ግን ሳታገባ ትኑር" በማለት ይቃረናል፦
ማቴዎስ 19፥9 "እኔ ግን እላችኋለሁ "ያለ ዝሙት ምክንያት ሚስቱን ፈትቶ ሌላዪቱን የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል"፥ የተፈታችውንም የሚያገባ ያመነዝራል" አላቸው።
1ኛ ቆሮንቶስ 7፥10 ሚስትም ከባልዋ አትለያይ፥ ብትለያይ ግን ሳታገባ ትኑር ወይም ከባልዋ ትታረቅ።
የጳውሎስ ሌላው ስህተቱ ከግሪካውያን ሥነ ተረት"mythology" ይቀዳ ነበር። በግሪካውያን “አምላክ አንድ ነው” ብለው ስለማያምኑ “እኛ የአምላክ ዘር ነን” ብለው ያምናሉ፥ ለምሳሌ፦ ከ 315-310 ቅድመ ልደት ይኖር የነበረው ባለ ቅኔው አራተስ”Aratus” እራሱ ይህንን ይናገር ነበር፦
የሐዋርያት ሥራ 17፥28 “ከእናንተ ከባለ ቅኔዎች አንዳንዶች ደግሞ፦ “እኛ ደግሞ ዘሩ ነንና” ብለው እንደ ተናገሩ። τινες τῶν καθ’ ὑμᾶς ποιητῶν εἰρήκασιν Τοῦ γὰρ καὶ γένος ἐσμέν.
ጳውሎስ ከባለ ቅኔዎች መጥቀሱ ያጅባል። “ጌኑስ” γένος ማለት “ዘር” “ውሉድ”offspring” ማለት ሲሆን ጳውሎስ ከአራተስ ጠቅሶ “የአምላክ ዘር ከሆንን” በማለት አጽድቆላቸዋል፦
የሐዋርያት ሥራ 17፥29 እንግዲህ የአምላክ ዘር ከሆንን..። γένος οὖν ὑπάρχοντες τοῦ Θεοῦ
ጳውሎስ እስር ቤት ሆኖ ለአሥር አጥቢያ እና ለሦስት ግለሰቦች አሥራ አራት ደብዳቤዎችን ያጽፍ እና ይጽፍ ነበር፦
ሮሜ 16፥22 "ይህን መልእክት የጻፍሁ እኔ ጤርጥዮስ" በጌታ ሰላምታ አቀርብላችኋለሁ።
የሮሜ ደብዳቤ የጳውሎስ ብቻ ሳይሆን የተማሪው የጤርጥዮስም ጭምር ነው፥ "ይህን መልእክት የጻፍሁ እኔ ጤርጥዮስ" የሚለው በቂ ማሳያ ሲሆን ይህ የፈጣሪ ቃል ነውን? "በርኖሱን እና መጻሕፍቱን ይልቁንም በብራና የተጻፉትን አምጣልኝ" የሚለው ጳውሎስ እንጂ ፈጣሪ አይደለም፦
2ኛ ጢሞቴዎስ 4፥13 ስትመጣ በጢሮአዳ ከአክርጳ ዘንድ የተውሁትን በርኖሱን እና መጻሕፍቱን ይልቁንም በብራና የተጻፉትን አምጣልኝ።
ስለዚህ የጳውሎስ ደብዳቤዎች በገዛ እጁ የጻፋቸው የእርሱ ሰላምታዎች እንጂ የአምላክ ቃል በፍጹም አይደሉም፦
1ኛ ቆሮንቶስ 16፥21 እኔ ጳውሎስ ይህን ሰላምታ በገዛ እጄ ጽፌአለሁ።
ቆላስይስ 4፥18 በገዛ እጄ የተጻፈ የእኔ የጳውሎስ ሰላምታ ይህ ነው። እስራቴን አስቡ።
2ኛ ተሰሎንቄ 3፥17 በገዛ እጄ የተጻፈ የእኔ የጳውሎስ ሰላምታ ይህ ነው፤ የመልእክቴ ሁሉ ማስረጃ ይህ ነው፤ እንዲህ እጽፋለሁ።
እነዚህን ደብዳቤዎች በእጆቻቸው ለሚጽፉ እና ከዚያም በእርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «የፈጣሪ ንግግር ነው» ለሚሉ ወዮላቸው፦

የጳውሎስ ኩረጃ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
3፥71 «የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! እውነቱን በሐሰት ለምን ትቀላቅላላችሁ? እውነቱንም እናንተ የምታውቁ ስትኾኑ ለምን ትደብቃላችሁ?» يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لِمَ تَلْبِسُونَ الْحَقَّ بِالْبَاطِلِ وَتَكْتُمُونَ الْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ
ጥንት የነበሩት የፈጣሪ ነቢያት በአምላክ ተልከው ትንቢት ሲመጣላቸው የሚናገሩት በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ነበር፦
2ኛ ጴጥሮስ 1፥21ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፥ ዳሩ ግን በአምላክ ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።
"በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ" እንጂ "በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ጻፉ" አይልም፥ ብዙ ሰዎች ጳውሎስ የጻፋቸውን አሥራ አራት ደብዳቤዎች"letters" "በመንፈስ ቅዱስ ተነድቶ ነው" ይላሉ። ቅሉ ግን በመንፈስ ቅዱስ ተነድቶ የተጻፈ ጽሑፍ የለም፥ ባይሆን በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው የተናገሩት ንግግር አለ። ይህም ከአምላክ ተልከው ትንቢት እንጂ ታሪክ አይደለም፥ ከመነሻው ይህ ጥቅስ ስለ ነቢያት እንጂ ስለ እነ ጳውሎስ ሽታው የለውም።
ጳውሎስ ብዙ ጊዜ ከጥንት ነቢያት ሲጠቅስ ስለሚሳሳት የሚጽፈው በመንፈስ ቅዱስ በጭራሽ አይደለም፦
1ኛ ቆሮንቶስ 2፥9 ነገር ግን፦ "ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው አምላክ ለሚወዱት ያዘጋጀው" ተብሎ እንድተጻፈ፥ እንዲህ እንናገራለን።
በብሉይ ኪዳን "ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው" ተብሎ የተጻፈ በባትሪ ብትፈልጉ አታገኙም፥ ጥቅሱን የወሰደበት ቦታ አምላክ ስላዘጋጀው ነገር ሳይሆን አሐዳውያን ባዕድ አምላክን መስማት፣ መቀበል እና ማየት እንዳልፈለጉ የሚያስጨብጥ ነው፦
ኢሳይያስ 64፥4 ሰዎች ከጥንት ጀምሮ ለሚጠብቁህ ከምትሠራላቸው ከአንተ በቀር ሌላ አምላክን አልሰሙም በጆሮአቸውም አልተቀበሉም ዓይንም አላየችም።
ጳውሎስ ሲኮርጅ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ቢሆን ኖሮ በትክክል ማስቀመጥ ያቅተዋልን? እንቀጥል! ጳውሎስ ከኢሳይያስ ጠቅሶ እንዲህ ይሳሳታል፦
ሮሜ 11፥26 እንደዚሁም እስራኤል ሁሉ ይድናል፤ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፦ "መድኃኒት ከጽዮን ይወጣል፥ ከያዕቆብም ኃጢአተኛነትን ያስወግዳል።
ኢሳይያስ 59፥20 ለጽዮን ታዳጊ ይመጣል፥ በያዕቆብም ዘንድ ከኃጢአት ለሚርቁ፥ ይላል ያህዌህ። וּבָ֤א לְצִיֹּון֙ גֹּואֵ֔ל וּלְשָׁבֵ֥י פֶ֖שַׁע בְּיַֽעֲקֹ֑ב נְאֻ֖ם יְהוָֽה
"ለጽዮን ታዳጊ ይመጣል" ማለት እና "መድኃኒት ከጽዮን ይወጣል" ማለት ሁለት የተለያየ ቃላት ነው፥ "በያዕቆብም ዘንድ ከኃጢአት ለሚርቁ" ማለት እና "ከያዕቆብም ኃጢአተኛነትን ያስወግዳል" ማለት ሁለት የተለያየ ቃላት ነው። መንፈስ ቅዱስ ይህ ጠፍቶት ነው? ጳውሎስ የኮረጀው ከዕብራይስጡ ሳይሆን ከግሪክ ሰፕቱጀንት ነው፦
καὶ ἥξει ἕνεκεν Σιὼν ὁ ῥυόμενος καὶ ἀποστρέψει ἀσεβείας ἀπὸ ᾿Ιακώβ.
ግሪክ ሰፕቱጀንት የዕብራይስጥ ቅጂ ሳይሆን ከዕብራይስጥ ወደ ግሪክ የትርጉም ሥራ ነው፥ ጳውሎስ ከትርጉም ሥራ ላይ እየኮረጀ "የአምላክ መገለጥ ነው" ብሎ መቅጠፉ ጥሩ አይደለም። ጳውሎስ እንዲህ ዓይነት የኩረጃ ስህተቶችን የተሳሳተባቸው በቁና ማቅረብ ይቻል ነበር፥ ቅሉ እና ጥቅሉ ግን አንባቢያንን ማሰልቸት ነው።
የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! ከአምላክ የመጣውን እውነት ከኩረጃ ንግግር ጋር ለምን ትቀላቅላላችሁ? ይህ ሥራ ዋጋ ያስከፍላል፦

ቅዱሳን መናፍስት
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
16፥102 እነዚያን ያመኑትን ለማረጋጋት እና ሙሥሊሞቹን ለመምራት እና ለማብሰር ቁርኣንን ቅዱሱ መንፈስ (ጂብሪል) እውነተኛ ሲኾን ከጌታህ አወረደው" በላቸው፡፡ قُلْ نَزَّلَهُ رُوحُ الْقُدُسِ مِن رَّبِّكَ بِالْحَقِّ لِيُثَبِّتَ الَّذِينَ آمَنُوا وَهُدًى وَبُشْرَىٰ لِلْمُسْلِمِينَ
"ቅዱሳን" የሚለው ቃል "ቅዱስ" ለሚለው ቃል ብዜት ሲሆን መላእክት "ቅዱሳን" ተብለዋል፦
ዘዳግም 33፥2 ከአእላፋትም "ቅዱሳኑ" መጣ፤
በስተ ቀኙም የእሳት ሕግ ነበረላቸው። וְאָתָ֖ה מֵרִבְבֹ֣ת קֹ֑דֶשׁ מִֽימִינֹ֕ו [אֵשְׁדָּת כ] (אֵ֥שׁ ק) (דָּ֖ת ק) לָֽמֹו׃
"በስተ ቀኙም የእሳት ሕግ ነበረላቸው" የሚለው ይሰመርበት! ሕግ የተነገረው እና የተሰጠው በመላእክት ሥርዓት ነው፥ እነዚህ ጥቅስን፦ የሐዋርያት ሥራ 7፥53 ዕብራውያን 2፥2 ተመልከት!
መላእክት ብዙ ቦታ "ቅዱሳን" ተብለዋል፦
ኢዮብ 15፥15 እነሆ "በቅዱሳኑ" ስንኳ አይታመንም፤ ሰማያትም በፊቱ ንጹሐን አይደሉም።
ዳንኤል 8፥13: ከቅዱሳኑም አንዱ ሲናገር ሰማሁ ለተናገረው ለቅዱሱም ሁለተኛው ቅዱስ፦
ዳንኤል 4፥13 "አንድ ቅዱስ ጠባቂ" ከሰማይ ወረደ።
ዳንኤል 4፥17 ይህ ነገር "የጠባቂዎች ትእዛዝ"፥ ይህም ፍርድ "የቅዱሳን ቃል" ነው።
"መንፈስ" "ረቂቅ" "ምጡቅ" ማለት ሲሆን የመንፈስ ብዙ ቁጥር ደግሞ "መናፍስት" ነው፥ መላእክት "መናፍስት" ተብለዋል፦
ዕብራውያን 1፥14 ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ "የሚላኩ" እና የሚያገለግሉ "መናፍስት" አይደሉምን?
እዚህ አንቀጽ ላይ "መናፍስት" የተባሉት መላእክት እንደሆኑ እሙን እና ቅቡል ነው። "ቄስ" ተብሎ ብዜቱ "ቀሳውስት" እንደሆነ፣ "ቅዱስ" ተብሎ ብዜቱ "ቅዱሳን" እንደሆነ፣ "አምላክ" ተብሎ ብዜቱ "አማልክት" እንደሆነ ሁሉ "መንፈስ" ተብሎ ብዜቱ "መናፍስት" ነው። ነገር ግን "መንፈሶች" "ቄሶች" "ቅዱሶች" "አምላኮች" ጸያፍ ርቢ ናቸው፥ መላእክት "ቅዱሳን መናፍስት" ከሆኑ አንድ ነጠላ መልአክ "ቅዱስ መንፈስ" ሊባል ይችላል። ስለዚህ በቁርኣን ጂብሪል "ቅዱስ መንፈስ" መባሉ ስትሰሙ የሚያውረገርጋችሁ ማላመጫው እና ማዳመጫው ከተቀላቀለበት የሚመጣ ክፉኛ መረዳት ነው፦
16፥102 እነዚያን ያመኑትን ለማረጋጋት እና ሙሥሊሞቹን ለመምራት እና ለማብሰር ቁርኣንን ቅዱሱ መንፈስ (ጂብሪል) እውነተኛ ሲኾን ከጌታህ አወረደው በላቸው፡፡ قُلْ نَزَّلَهُ رُوحُ الْقُدُسِ مِن رَّبِّكَ بِالْحَقِّ لِيُثَبِّتَ الَّذِينَ آمَنُوا وَهُدًى وَبُشْرَىٰ لِلْمُسْلِمِينَ
"ከጌታህ አወረደው" የሚለው ይሰመርበት! ጂብሪል ቁርኣንን ከአሏህ ማውረዱ ስሙር እና እሙር ነው፦
2፥97 "ለጂብሪል ጠላት የኾነ ሰው በቁጭት ይሙት በላቸው"፡፡ እርሱ ቁርኣኑን ከበፊቱ ለነበሩት አረጋጋጭ ለምእመናን መሪ እና ብስራት ሲኾን "በአላህ ፈቃድ በልብህ ላይ አውርዶታልና"፡፡ قُلْ مَن كَانَ عَدُوًّا لِّجِبْرِيلَ فَإِنَّهُ نَزَّلَهُ عَلَىٰ قَلْبِكَ بِإِذْنِ اللَّهِ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَهُدًى وَبُشْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ
አምላካችን አሏህ ለጂብሪል እልቅና በመስጠት ወደራሱ በማስጠጋት "መንፈሳችን" በማለት ይናገራል፦
19፥7 ከእነሱም መጋረጃን አደረገች፡፡ መንፈሳችንም (ጂብሪልን) ወደ እርሷ ላክን፡፡ ለእርሷም ትክክለኛ ሰው ሆኖ ተመሰለላት፡፡ فَاتَّخَذَتْ مِن دُونِهِمْ حِجَابًا فَأَرْسَلْنَا إِلَيْهَا رُوحَنَا فَتَمَثَّلَ لَهَا بَشَرًا سَوِيًّا
ይህ እኮ አያስገርምም። ባይብል ላይ ሰባቱ የመላእክት ሊቃውንት የእግዚአብሔር መናፍስት ተብለዋል፥ "ሊቅ" ማለት "አለቃ" ማለት ሲሆን "ሊቃውንት" ደግሞ "አለቆች" ማለት ነው፦
ዳንኤል 10፥13 ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ። וְהִנֵּ֣ה מִֽיכָאֵ֗ל אַחַ֛ד הַשָּׂרִ֥ים הָרִאשֹׁנִ֖ים בָּ֣א לְעָזְרֵ֑נִי
ራእይ 5፥6 እነርሱም ወደ ምድር ሁሉ የተላኩ "የእግዚአብሔር መናፍስት" ናቸው።
መላእክት "የእግዚአብሔር መናፍስት" መባላቸው ስትሰሙ ፍግም እና ክልትው ከማለት ይልቅ ከአፉ እስከ ገደፉ ጢቅ አርጎ ማንበብ ይበጃል። እነርሱም ወደ ምድር ሁሉ የተላኩ "የእግዚአብሔር መናፍስት" ሰባቱ የመላእክት አለቆች ሲሆኑ በትውፊት ሚካኤል፣ ገብርኤል፣ ሩፋኤል፣ ራጉኤል፣ ዑራኤል፣ ፋኑኤል፣ ሳቁኤል ናቸው፥ እነዚህ ሰባቱ መላእክት በዙፋኑ ፊት የሚቆሙ ሰባቱ መላእክት፣ ሰባት የእሳት መብራቶች፣ ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት፣ የእግዚአብሔር ዓይኖች ተብለዋል፦
ራእይ 8፥2 በእግዚአብሔርም ፊት የሚቆሙትን "ሰባቱን መላእክት" አየሁ፥
ራእይ 4፥5 በዙፋኑም ፊት "ሰባት የእሳት መብራቶች" ይበሩ ነበር፥ እነርሱም "ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት" ናቸው።
ዘካርያስ 4፥2 "ሰባትም መብራቶች" ነበሩበት፤
ዘካርያስ 4፥10 "እነዚህ ሰባቱ" ደስ ብሎአቸው በዘሩባቤል እጅ ቱንቢውን ያያሉ፤ "እነዚህም" በምድር ሁሉ የሚዘዋወሩ "የእግዚአብሔር ዓይኖች" ናቸው።
ስለዚህ መላእክት "ቅዱሳን መናፍስት" እና "የእግዚአብሔር መናፍስት" ሲባሉ ጎብለል፣ ዘንጎል፣ ደንጎል እያላችሁ በእምነት ከተቀበላችሁ እንግዲያውስ ከመላእክት አንዱ ገብርኤል በነጠላ "ቅዱስ መንፈስ" እና "መንፈሳችን" ሲባል ክች እና ምንክች አትበሉ። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ዳይሞንዮስ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
5፥90 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የሚያሰክር መጠጥ፣ ቁማር፣ ጣዖታት፣ አዝላም ከሰይጣን ሥራ የኾኑ እርኩስ ብቻ ናቸው፡፡ እርኩስን ራቁትም ልትድኑ ይከጀላልና፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّمَا الْخَمْرُ وَالْمَيْسِرُ وَالْأَنصَابُ وَالْأَزْلَامُ رِجْسٌ مِّنْ عَمَلِ الشَّيْطَانِ فَاجْتَنِبُوهُ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ
በዕብራይስጥ "ጊሉል" גִּלּוּל እና በግሪክ ሰፕቱጀንት "ኤዴሎስ" εἰδώλοις ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ምስል" "ጣዖት" ማለት ሲሆን እስራኤላውያን ልጆቻቸውን ለጣዖቶቻቸው ሠዉ፦
ሕዝቅኤል 23፥39 ልጆቻቸውንም "ለ-ጣዖቶቻቸው" ሠዉ። וּֽבְשַׁחֲטָ֤ם אֶת־בְּנֵיהֶם֙ לְגִלּ֣וּלֵיהֶ֔ם
መዝሙር 106፥37 ወንዶች ልጆቻቸውን እና ሴቶች ልጆቻቸውን "ለ-ሼዲም" ሠው። וַיִּזְבְּח֣וּ אֶת־בְּ֭נֵיהֶם וְאֶת־בְּנֹֽותֵיהֶ֗ם לַשֵּֽׁדִים׃
"ሼድ" שֵׁד ማለት "ሐሰተኛ አምላክ" ማለት ሲሆን "ሼዲም" שֵּֽׁדִים ደግሞ የሼድ ብዙ ቁጥር ነው፥ "ሼዲም" שֵּֽׁדִים ማለት እስራኤላውያን የማያውቋቸውም አማልክት፣ በቅርብ ጊዜ የተነሡ አዲሶች፣ አባቶቻቸውም ያልፈሩአቸው አምላክት ሲሆኑ መሥዋዕት ሰዉላቸው፦
ዘዳግም 32፥17 አምላክ ላልሆኑ ሼዲም፥ ለማያውቋቸውም አማልክት፥ በቅርብ ጊዜ ለተነሡ ለአዲሶች፣ አባቶቻቸውም ላልፈሩአቸው "አማልክት ሠዉ"። יִזְבְּח֗וּ לַשֵּׁדִים֙ לֹ֣א אֱלֹ֔הַ אֱלֹהִ֖ים לֹ֣א יְדָע֑וּם חֲדָשִׁים֙ מִקָּרֹ֣ב בָּ֔אוּ לֹ֥א שְׂעָר֖וּם אֲבֹתֵיכֶֽם׃
"ዳይሞን" δαίμων ማለት በግሪክ ኮይኔ "አምላክ" ማለት ነው፥ የዳይሞን ብዙ ቁጥር ደግሞ "ዳይሞንዮን" δαιμονίων ወይም "ዳይሞንዮስ" δαιμονίοις ሲሆን "አማልክት" ማለት ነው። "ሼዲም" שֵּֽׁדִים ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ዳይሞንዮስ" δαιμονίοις ሲሆን የአሕዛብ ጣዖታት ናቸው፦
1ኛ ዜና መዋዕል 16፥26 የአሕዛብ አማልክት ሁሉ ጣዖታት ናቸው፥ ያህዌህ ግን ሰማያትን ሠራ። כִּ֤י ׀ כָּל־אֱלֹהֵ֣י הָעַמִּ֣ים אֱלִילִ֑ים וַֽ֝יהוָ֗ה שָׁמַ֥יִם עָשָֽׂה׃
መዝሙር 96፥5 የአሕዛብ አማልክት ሁሉ ጣዖታት ናቸው፥ ያህዌህ ግን ሰማያትን ሠራ። כִּ֤י ׀ כָּל־אֱלֹהֵ֣י הָעַמִּ֣ים אֱלִילִ֑ים וַֽ֝יהוָ֗ה שָׁמַ֥יִם עָשָֽׂה׃
በዐማርኛ "አጋንንት" ብለው ያስቀመጡት "ኤሊሊም" אֱלִילִ֑ים ሲሆን "ጣዖታት" ማለት ነው። ብሉይ ላይ "በቅርብ ጊዜ ለተነሡ ለአዲሶች" የተባሉት ወደ አዲስ ኪዳን ስንመጣን "አዲሶችን አማልክት" ተብለዋል፦
የሐዋርያት ሥራ 17፥18 "አዲሶችን አማልክት" የሚያወራ ይመስላል" Ξένων δαιμονίων δοκεῖ καταγγελεὺς εἶναι·
ኢስጦኢኮች ከተባሉት ፈላስፎች "አማልክት" ለሚለው የተጠቀሙበት ቃል "ዳይሞንዮን" δαιμονίων እንደሆነ ልብ አድርግ! ዳይሞንዮን የተባሉት ጣዖታት ሲሆኑ የጣዖቶቹ አለቃ ብዔል ዜቡል እራሱ ጣዖት ነው፦
ማቴዎስ 12፥24 ፈሪሳውያን ግን ሰምተው፦ "ይህ በአማልክት አለቃ በብዔል ዜቡል ካልሆነ በቀር አማልክትን አያወጣም" አሉ። οἱ δὲ Φαρισαῖοι ἀκούσαντες εἶπον Οὗτος οὐκ ἐκβάλλει τὰ δαιμόνια εἰ μὴ ἐν τῷ Βεελζεβοὺλ ἄρχοντι τῶν δαιμονίων.

እዚህ አንቀጽ ላይ በዐማርኛ "አጋንንት" ብለው ያስቀመጡት ቃል "ዳይሞንዮን" δαιμονίων ሲሆን "አማልክት" ማለት ነው፥ የአማልክቱ አለቃ ብዔል ዜቡል እራሱ የአቃሮናውያን ጣዖት ነው። አቃሮናውያን የሚያመልኩት ጣዖት ብዔልዜቡል በትክክል ስሙ "በኣል-ዘቡብ" בַּעַל זְבוּב ነው፦
2 ነገሥት 1፥3 የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ትጠይቁ ዘንድ የምትሄዱት በእስራኤል ዘንድ አምላክ ስለሌለ ነውን? לְכ֣וּ דִרְשׁ֗וּ בְּבַ֤עַל זְבוּב֙ אֱלֹהֵ֣י עֶקְרֹ֔ון אִם־אֶחְיֶ֖ה מֵחֳלִ֥י זֶֽה׃ ס
"በኣል" בַּעַל ማለት "ጌታ" ማለት ሲሆን "ዘቡብ" זְבוּב ማለት ደግሞ "ዝንብ" ማለት ነው፥ "በኣል-ዘቡብ" בַּעַל זְבוּב ማለት "የዝንብ ጌታ" ማለት ነው። ጣዖታውያን ጣዖቶቻቸውን "ቅዱሳን አማልክት" ብለው ይጠሯቸዋል፦
ዳንኤል 5፥11 "የቅዱሳን አማልክት" መንፈስ ያለበት ሰው በመንግሥትህ ውስጥ አለ።
ዳንኤል 4፥8 በመጨረሻም "የቅዱሳን አማልክት መንፈስ" ያለበት እንደ አምላኬ ስም ብልጣሶር የሚባለው ዳንኤል በፊቴ ገባ።
እነዚህ ጣዖታት ውስጣቸው "መንፈስ አለ" ብለው ስለሚያምኑ "የቅዱሳን አማልክት መንፈስ" የሚሉት ለዛ ነው፥ የእነዚህ አማልክት መናፍስት "ቅዱሳን አማልክት" ሳይሆኑ "ርኵሳን መናፍስት" ናቸው፦
ራእይ 16፥13 ከዘንዶውም አፍ፣ ከአውሬው አፍ እና ከሐሰተኛውም ነቢይ አፍ ጓጕንቸሮች የሚመስሉ ሦስት "ርኵሳን መናፍስት" ሲወጡ አየሁ።
ራእይ 16፥14 ምልክት እያደረጉ "የአማልክት መናፍስት ናቸውና"። εἰσὶν γὰρ πνεύματα δαιμονίων ποιοῦντα σημεῖα,
እዚህ አንቀጽ ላይ በዐማርኛ "አጋንንት" ብለው ያስቀመጡት ቃል "ዳይሞንዮን" δαιμονίων ሲሆን ባይብል ስለ አጋንንት ግልጽ ትምህርት የለውም፥ ጋኔን ማለት ደግሞ ጂን ማለት አይደለም። ክርስቲያኖች "ቤልሆር ጋኔን ወይም ሰይጣን" ነው" ብለው ያስባሉ፥ ይህ ስህተት ነው፦
2ኛ ቆሮንቶስ 6፥15 ክርስቶስስ "ከ-"ቤልሆር" ጋር ምን መስማማት አለው? τίς δὲ συμφώνησις Χριστοῦ πρὸς Βελιάρ,
በዐማርኛ "ቤልሆር" ተብሎ የተቀመጠው ቃል በዕብራይስጥ "ቤሊያል" בְּלִיַּעַל በግሪክ "ቤሊአል" Βελιάρ ሲሆን ትርጉሙ "ምናምንቴ" ማለት ነው እንጂ "ሰይጣን" ወይም "ጋኔን" ማለት አይደለም፦
ምሳሌ 6፥12 "ምናምንቴ" ሰው የበደለኛም ልጅ፡
በጠማማ አፍ ይሄዳል። אָדָ֣ם בְּ֭לִיַּעַל אִ֣ישׁ אָ֑וֶן הֹ֝ולֵ֗ךְ עִקְּשׁ֥וּת פֶּֽה׃
1ኛ ሳሙኤል 2፥12 የዔሊም ልጆች "ምናምንቴዎች" ነበሩ፤ ያህዌህን አያውቁም ነበር። וּבְנֵ֥י עֵלִ֖י בְּנֵ֣י בְלִיָּ֑עַל לֹ֥א יָדְע֖וּ אֶת־יְהוָֽה׃
በቁርኣን ደግሞ ጣዖታት "አንሷብ" أَنْصَاب ይባላሉ፥ "ኑስብ" نُصْب ማለት "ሐውልት" "ምስል" "ጣዖት" ማለት ሲሆን የኑስብ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ኑሱብ" نُصُب ወይም "አንሷብ" أَنْصَاب ነው፦
5፥90 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የሚያሰክር መጠጥ፣ ቁማር፣ ጣዖታት፣ አዝላም ከሰይጣን ሥራ የኾኑ እርኩስ ብቻ ናቸው፡፡ እርኩስን ራቁትም ልትድኑ ይከጀላልና፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّمَا الْخَمْرُ وَالْمَيْسِرُ وَالْأَنصَابُ وَالْأَزْلَامُ رِجْسٌ مِّنْ عَمَلِ الشَّيْطَانِ فَاجْتَنِبُوهُ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ
እዚህ አንቀጽ ላይ "ጣዖታት" ለሚለው የገባው ቃል "አንሷብ" أَنْصَاب ሲሆን አንሷብ ከሰይጣን ሥራ የኾኑ እርኩስ ብቻ ናቸው፡፡ አምላካችን አሏህ ከጣዖት እርኩሰት ይጠብቀን! አሚን።

መናፍስት ጠሪ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
7፥194 እነዚያ ከአሏህ ሌላ የምትጠሯቸው እንደ እናንተ አምላኪዎች ናቸው፥ እውነተኞችም እንደሆናችሁ ጥሩዋቸው እና ለእናንተ ይመልሱላችሁ አይችሉም። إِنَّ ٱلَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ عِبَادٌ أَمْثَالُكُمْ ۖ فَٱدْعُوهُمْ فَلْيَسْتَجِيبُوا۟ لَكُمْ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
"ሩሓህ" רוּחַ የሚለው የዕብራይስጥ ቃል እና "ፕኒውማ" πνεῦμα የሚለው የግሪክ ቃል "መንፈስ" ማለት ሲሆን መንፈስ ማለት እራሱ "ረቂቅ" "ምጡቅ" ማለት ነው፥ የመንፈስ ብዙ ቁጥር "መናፍስት" ነው፦
ዘኍልቍ 27፥16 የሥጋ ሁሉ መናፍስት አምላክ ያህዌህ በማኅበሩ ላይ ይሹመው። יִפְקֹ֣ד יְהוָ֔ה אֱלֹהֵ֥י הָרוּחֹ֖ת לְכָל־בָּשָׂ֑ר אִ֖ישׁ עַל־הָעֵדָֽה׃
ዘኍልቍ 16፥22 እነርሱም በግምባራቸው ወድቀው፦ አምላክ ሆይ! አንተ የሥጋ ሁሉ መናፍስት አምላክ፥ አንድ ሰው ኃጢአት ቢሠራ አንተ በማኅበሩ ሁሉ ላይ ትቈጣለህን?" አሉ። וַיִּפְּל֤וּ עַל־פְּנֵיהֶם֙ וַיֹּ֣אמְר֔וּ אֵ֕ל אֱלֹהֵ֥י הָרוּחֹ֖ת לְכָל־בָּשָׂ֑ר הָאִ֤ישׁ אֶחָד֙ יֶחֱטָ֔א וְעַ֥ל כָּל־הָעֵדָ֖ה תִּקְצֹֽף׃ פ
እነዚህ አናቅጽ ላይ "መናፍስት" ለሚለው የገባው ቃል "ሩሑት" רוּחֹ֖ת ሲሆን "ሩሓህ" רוּחַ ለሚለው ብዜት ነው፥ እነዚህ አናቅጽ ላይ "መናፍስት" የሚለው መላእክትን ወይም የዳይሞንዮስ መናፍስት ሳይሆን ሰዎች በውስጣቸው ያለው ውሳጣዊ ተፈጥሮ የሚያሳይ ነው። አምላክ የሥጋ ሁሉ መናፍስት አስገኚ ስለሆነ "የመናፍስት አባት" ተብሏል፦
ዕብራውያን 12፥9 እንዴትስ ይልቅ "ለመናፍስት" አባት አብልጠን ልንገዛ እና በሕይወት ልንኖር በተገባን? καὶ ἐνετρεπόμεθα· οὐ πολὺ μᾶλλον ὑποταγησόμεθα τῷ Πατρὶ τῶν πνευμάτων καὶ ζήσομεν;
እዚህ አንቀጽ ላይ "መናፍስት" ለሚለው የገባው ቃል "ፕኒውማቶን" πνευμάτων ሲሆን "ፕኒውማ" πνεῦμα ለሚለው ብዙ ቁጥር ነው። በነቢያት ውስጥ ያለው የነቢያት ውስጣዊ ተፈጥሮ "መናፍስት" ተብሏል፥ አንዱ አምላክ የነቢያትም መናፍስት አምላክ ነው፦
1ኛ ቆሮንቶስ 14፥32 "የነቢያትም መናፍስት" ለነቢያት ይገዛሉ። καὶ πνεύματα προφητῶν προφήταις ὑποτάσσεται·
ራእይ 22፥6 "የነቢያትም መናፍስት ጌታ አምላክ" በቶሎ ሊሆን የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ እንዲያሳይ መልአኩን ላከ። καὶ ὁ Κύριος ὁ Θεὸς τῶν πνευμάτων τῶν προφητῶν ἀπέστειλεν τὸν ἄγγελον αὐτοῦ δεῖξαι τοῖς δούλοις αὐτοῦ ἃ δεῖ γενέσθαι ἐν τάχει.
"አንትሮፖስ" ἄνθρωπος ማለት "ሰው" ማለት ሲሆን የሰው ውጫዊ ክፍል አካል "ውጫዊ ሰው"outward man" እንደተባለ ሁሉ የሰው ውስጣዊ ክፍል የሰው መንፈስ እራሱ "ውስጣዊ ሰው"inward man " ተብሏል፦
2ኛ ቆሮንቶስ 4፥16 ነገር ግን የውጭው ሰውነታችን ቢጠፋ እንኳ የውስጡ ሰውነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል። ἀλλ’ εἰ καὶ ὁ ἔξω ἡμῶν ἄνθρωπος διαφθείρεται, ἀλλ’ ὁ ἔσω ἡμῶν ἀνακαινοῦται ἡμέρᾳ καὶ ἡμέρᾳ.
የሰው ውጫዊ ክፍል ሥጋ አፈር ነውና ወደ አፈር ይመለሳል፥ የሰው ውስጣዊ ክፍል መንፈስ ደግሞ ወደ ሰጠው ወደ አምላክ ይመለሳል፦
መክብብ 12፥7 አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ፥ "መንፈስም" ወደ ሰጠው ወደ አምላክ ሳይመለስ። וְיָשֹׁ֧ב הֶעָפָ֛ר עַל־הָאָ֖רֶץ כְּשֶׁהָיָ֑ה וְהָר֣וּחַ תָּשׁ֔וּב אֶל־הָאֱלֹהִ֖ים אֲשֶׁ֥ר נְתָנָֽהּ׃
ወደ ፈጣሪ ከሚመለሱት መናፍስት አንዱ የጻድቃን መንፈሶች ናቸው፥ "መንፈሶች" የመንፈስ ጸያፍ እርቢ ነው፦
ዕብራውያን 12፥23 ፍጹማንም ወደ ሆኑት ወደ ጻድቃን "መንፈሶች" ደርሳችኃል። καὶ πνεύμασι δικαίων τετελειωμένων,
"ጠልሰም" ማለት ቋንቋዊ ትርጉሙ "ማስዋብ" ማለት ሲሆን ሃይማኖታዊ ትርጉሙ "መንፈሳዊ ጥበብ" ማለት ነው፥ ይህ ጠልሰም የሚባለው ትምህርት በየገዳማቱ በብራናዎች ተጽፎ ይገኛል። በተለይ ሰሜን ሸዋ በሚገኘው የደብረ ሊባኖስ ገዳም፣ ቢሾፍቱም በቤተ ሩፋኤል ገዳም፣ ትግራይ በደብረ ዳሞ ገዳም፣ ላሊበላ በይምርሃነ ክርስቶስ ገዳም፣ ጐጃም ጣና ቂርቆስ ገዳም፣ ወሎ በአቡነ ይምርሃነ ክርስቶስ ገዳም ውስጥ በስፋት ትምህርቱ ይሰጣል። በጠልሰም ትምህርት ውስጥ የሞቱ ቅዱሳን ማናገር "ምስሓበ ቅዱሳን" እና "ምስሓበ መናፍስት" ትምህርት ዐቢይ ትምህርት ነው፥ ነገር ግን ፈጣሪ መናፍስትንም መጥራት እና የሞቱ ሙታንን መሳብ ከልክሎታል፦
ዘዳግም 18፥11 አስማተኛም፥ መተተኛም፥ በድግምት የሚጠነቍልም፥ መናፍስትንም የሚጠራ፥ ጠንቋይም፥ ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ።
ዘዳግም 18፥12 ይህንም የሚያደርግ ሁሉ በያህዌህ ፊት የተጠላ ነው።
በተጨማሪ ዘሌዋውያን 19፥31 ዘሌዋውያን 20፥27 ተመልከት! የሞቱ ሰዎች ከሞቱ በኃላ ከዚህ ዓለም ጋር ግንኙነት የሚያደርጉበት ዓይን፣ ጆሮ፣ ጭንቅላት ወዘተ ይፈራርሳል፥ የምንናገረውን አይሰሙም፣ የምንሠራውን ዓያዩም፣ የምናስበውን አያውቁም፦
ኢሳይያስ 8፥19 እነርሱም፦ "የሚጮኹትንና ድምፃቸውን ዝቅ አድርገው የሚናገሩትን መናፍስት ጠሪዎችን እና ጠንቋዮችን ጠይቁ" ባሉአችሁ ጊዜ ሕዝቡ ከአምላኩ መጠየቅ አይገባውምን? ወይስ ለሕያዋን ሲሉ ሙታንን ይጠይቃሉን?
የሙታን መናፍስት መጥራት በጥብቅ የተከለከለ ነው፥ በጸሎት ሊጠየቅ የሚችል አምላክ እያለ ሙታንን መጠየቅ አግባብ አይደለም። የሞቱ ጻድቃንንን፣ ሰማዕታትን፣ ነቢያት በሌሉበት መጥራት ሆነ መለማመን ሺርክ ነው፥ ምክንያቱም የሁላችንንም ጸሎት ሰምቶ የሚመልስ አንድ አምላክ ብቻ እና ብቻ ነው። እነዚያ ከአሏህ ሌላ የምትጠሯቸው እንደ እናንተ አምላኪ ሰዎች ናቸው፥ ብትጠሯቸው መልስ መስጠት አይችሉም፦

ሁሉንም መስማት፣ ማየት፣ ማወቅ የሚችል አንድ አምላክ አሏህ ሆኖ ሳለ ወደ ፍጡራንን ዱዓእ በማድረግ ከሚደረግ ሺርክ አሏህ ይጠብቀን! አሚን።

እግዚአብሔር አብ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
6፥98 እርሱም ያ ከአንዲት ነፍስ ያስገኛችሁ ነው፡፡ وَهُوَ الَّذِي أَنشَأَكُم مِّن نَّفْسٍ
በዕብራይስጥ ለአንዱ አምላክ "አብ" אָ֑ב ማለት "አስገኚ" "ምንጭ" ማለት ነው፥ አንዱ አምላክ ሰውን ጭቃ አርጎ ስለ ሠራ "አብ" אָ֑ב ተብሏል፦
ኢሳይያስ 64፥8 ያህዌህ ሆይ! አንተ አባታችን ነህ፤ እኛ ጭቃ ነን አንተም ሠሪያችን ነህ፥ እኛም ሁላችን የእጅህ ሥራ ነን። יְהוָ֖ה אָבִ֣ינוּ אָ֑תָּה אֲנַ֤חְנוּ הַחֹ֙מֶר֙ וְאַתָּ֣ה יֹצְרֵ֔נוּ וּמַעֲשֵׂ֥ה יָדְךָ֖ כֻּלָּֽנוּ׃
እዚህ አንቀጽ ላይ አንዱ አምላክ "አብ" אָ֑ב ሲባል ሰዎች "ጭቃ" ተብለዋል፥ ጭቃው የእጁ ሥራ ሲሆን "አባት" የሚለው "ሠሪ" ማለት ስለሆነ "አባታችን" የሚለው "ሠሪያችን" በሚል ተለዋዋጭ ቃል መጥቷል። "ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? ሲልም "ለሁላችን አንድ ሠሪ" መኖሩን የሚያሳይ ነው፦
ሚልክያስ 2፥10 ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን? הֲלֹ֨וא אָ֤ב אֶחָד֙ לְכֻלָּ֔נוּ הֲלֹ֛וא אֵ֥ל אֶֽחָ֖ד בְּרָאָ֑נוּ
ዮሐንስ 8፥41 አንድ አባት አለን፥ እርሱም አምላክ ነው። ἕνα Πατέρα ἔχομεν τὸν Θεόν.
ኤፌሶን 4፥6 አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ። εἷς Θεὸς καὶ Πατὴρ πάντων,
"አባት" ለአንዱ አምላክ ሲቀጸል በራሱ "አስገኚ" ማለት እንጂ "የባሕርይ አባት" ማለት አይደለም።
"ሆ ቴዎስ ሆ ፓትሮስ" Ο Θεός ο Πατρὸς ማለት "እግዚአብሔር አብ"God the Father" ማለት ሲሆን 13 ጊዜ ተጠቅሷል፥ እነዚህን አናቅጽ ተመልከት፦
ዮሐንስ 6፥27 ገላትያ 1፥1 ኤፌሶን 6፥23 ፊልጵስዩስ 2፥11 ቆላስይስ 3፥17 1ኛ ተሰሎንቄ 1፥1 2ኛ ጢሞቴዎስ 1፥2 ቲቶ1፥4 1ኛ ጴጥሮስ 1፥1 2ኛ የጴጥሮስ 1፥17 2ኛ ዮሐንስ 1፥3 ያዕቆብ 1፥27 ይሁዳ 1፥1
ኢየሱስ እግዚአብሔር የማይሆንበት ምክንያት አብ አለመሆኑ ነው፥ ምክንያቱም "አብ" ወይም "አባታች" የሚል ማዕረግ ያለው አንዱ እግዚአብሔር ብቻ እና ብቻ ነው፦
2ኛ ጢሞቴዎስ 1፥2 ከእግዚአብሔር አብ እና ከጌታችን ከክርስቶስ ኢየሱስ ጸጋ እና ምሕረት ሰላምም ይሁን። ἔλεος, εἰρήνη ἀπὸ Θεοῦ Πατρὸς καὶ Χριστοῦ Ἰησοῦ τοῦ Κυρίου ἡμῶν.
1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥2 ከእግዚአብሔር አባታችን እና ከክርስቶስ ኢየሱስ ከጌታችን ጸጋ እና ምሕረት ሰላምም ይሁን። χάρις, ἔλεος, εἰρήνη ἀπὸ Θεοῦ πατρὸς καὶ Χριστοῦ Ἰησοῦ τοῦ κυρίου ἡμῶν.
"እግዚአብሔር አብ" የሚለው "እግዚአብሔር አባታችን" በሚል ተለዋዋጭ ቃል ከመጣ እግዚአብሔር እና ኢየሱስ ሁለት የተለያዩ ምንነት እና ማንነት ናቸው። እግዚአብሔር "አብ" የተባለው "አባታችን" ስለተባለ ነው፥ ኢየሱስ ግን "አብ" ወይም "አባታችን" የተባለበት ጥቅስ የለም።
"ሆ ቴዎስ ሆ ሁዮስ" Ο Θεός ο γιος ማለት "እግዚአብሔር ወልድ"God the Son" ማለት ሲሆን ይህ ስም የተሰየመው በ325 ድኅረ ልደት በኒቂያ ጉባኤ ነው፥ "ሆ ቴዎስ ሆ ኑማ ቶ ሐጊዎን" Ο Θεός ο Πνεῦμα τὸ Ἅγιον ማለት "እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ"God the Holy Spirit" ማለት ሲሆን ይህ ስም የተሰየመው በ381 ድኅረ ልደት በቆስጠንጢኒያ ጉባኤ ነው።
ስለዚህ "አብ" የሚባለው የኢየሱስ አስገኚ የሆነው "እግዚአብሔር" ነው፦
ቆላስይስ 1፥3 የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አባት እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እናመሰግናለን። Εὐχαριστοῦμεν τῷ Θεῷ Πατρὶ τοῦ Κυρίου ἡμῶν Ἰησοῦ Χριστοῦ.
በተጨማሪ የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር እንደሆነ እነዚህን አናቅጽ ተመልከት፦ ዮሐንስ 5፥18 ሮሜ 15፥6 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥24
እግዚአብሔር አንድ ነው። ከእግዚአብሔር ውጪ "አብ" የለም፥ ከአብ ውጪ "እግዚአብሔር" የለም፦
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 79 ቁጥር 21
"ከእግዚአብሔር በስተቀር አባቴ የሚለው ማንን ነው?
መጽሐፈ ምሥጢር ምዕራፍ 29 ቁጥር 53
"አብ" ከዘላለም እስከ ዘላለም "እግዚአብሔር" ይባላል፥ ለአብ ከእግዚአብሔር ሌላ ስም አላገኘንለትም"
ሥርዓተ ቅዳሴ ምዕራፍ 5 ቁጥር 36
"የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር አንድ ነው"
ሥርዓተ ቅዳሴ ምዕራፍ 5 ቁጥር 33
"የኢየሱስ ክርስቶስ አባት በሚሆን ፍጥረቱን ሁሉ በፈጠረ በአንድ አምላክ እናምናለን"
"ሆ ሁዮስ ቱ ቴዉ" ὁ υἱός τοῦ Θεοῦ, ማለት "የእግዚአብሔር ልጅ"The Son of God" ማለት ነው፥ እግዚአብሔር "የኢየሱስ አባት" እንደተባለ ሁሉ ኢየሱስ "የእግዚአብሔር ልጅ" ተብሏል። ኢየሱስ እግዚአብሔር ቢሆን ኖሮ አብ "የእግዚአብሔር አባት ነው" የሚል ይገኝ ነበር። ክርስቲያኖችን "የኢየሱስ አባት ማን ነው? ስንላቸው "እግዚአብሔር" ይሉናል፥ ኢየሱስ ራሱ የራሱ አባት ካልሆነ እና አባቱ እግዚአብሔር ከሆነ ኢየሱስ እግዚአብሔር አይደለም።
አምላካችን አሏህ በቁርኣን የተገለጹ ዘጠና ዘጠኝ ባሕርያቱን የሚገልጹ የተዋቡ ስሞች አሉት። ከስሞቹ አንዱ "አል ባሪእ" ነው፥ "አል ባሪእ" الْبَارِئ የሚለው ቃል "በረአ" بَرَأَ ማለትም "ተገኘ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "አስገኚው" ማለት ነው፦
59፥24 እርሱ አሏህ ፈጣሪው፣ "አስገኚው"፣ ቅርጽን አሳማሪው ነው፡፡ ለእርሱ መልካሞች ስሞች አሉት፡፡ هُوَ اللَّهُ الْخَالِقُ الْبَارِئُ الْمُصَوِّرُ ۖ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ
እዚህ አንቀጽ ላይ "አስገኚው" ለሚለው የገባው ቃል "አል ባሪእ" الْبَارِئ ነው፥ አምላካችን አሏህ ሰዎችን ሁሉ በማስገኘቱ የሁላችንም አስገኚ ነው፦

"አብ" የሚለው ማዕረግ "አስገኚ" የሚለው ባሕርይን ለመቀጸል ከመጣ እንግዲያውስ እኛ ሙሥሊሞች "አብ" ብለን ሳንቀጽል ቁርኣን እና ሐዲስ በግልጽ በወሰፈበት ወስፍ "አል ባሪእ" الْبَارِئ ብለን አንዱ አምላካችንን አሏህን እንጠራዋለው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከሁለቱ የሚመጣው
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
5፥111 ወደ ሐዋርያትም «በእኔ እና በመልእክተኛዬ እመኑ» በማለት ባዘዝኩ ጊዜ አስታውስ፡፡ وَإِذْ أَوْحَيْتُ إِلَى الْحَوَارِيِّينَ أَنْ آمِنُوا بِي وَبِرَسُولِي
አምላካችን አሏህ ለዒሣ በሰጠው ወሕይ በኢንጂል ለሐዋርያት፦ "በእኔ እና በመልእክተኛዬ እመኑ" ብሎ አዟቸው ነበር፦

እዚህ አንቀጽ "ባዘዝኩ" ለሚለው የገባው ቃል "አውሐይት" أَوْحَيْتُ የግሥ መደብ ሲሆን የስም መደቡ "ወሕይ" وَحْي ማለትም "ግልጠተ መለኮት"revelation" ነው።
በአሏህ አምላክነት በመልእክተኛው በኢየሱስ ነቢይነት ማመን የአርካኑል ኢማን ክፍል ሆኖ ሳለ ክርስቲያን ሚሽነሪዎች እራሳቸውን የሚያስጠጉበትን ጳውሎስ የተናገረውን ንግግር ተንተርሰው ሙግት ለማዋቀር እና ለማደራጀት ይደክማሉ፦
1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥2 ከእግዚአብሔር አባታችን እና ከክርስቶስ ኢየሱስ ከጌታችን ጸጋ፣ ምሕረት እና ሰላም ይሁን። χάρις, ἔλεος, εἰρήνη ἀπὸ Θεοῦ πατρὸς καὶ Χριστοῦ Ἰησοῦ τοῦ κυρίου ἡμῶν.
ጳውሎስ በደብዳቤዎቹ ውስጥ 10 ቦታ ላይ "ከእግዚአብሔር አባታችን እና ከክርስቶስ ኢየሱስ ከጌታችን ጸጋ፣ ምሕረት እና ሰላም ይሁን" ይላል፥ እነዚህ ጥቅሳትን ተመልከት፦ ሮሜ 1፥7 1ኛ ቆሮ 1፥3 2ኛ ቆሮ 1፥2 ገላትያ 1፥3 ኤፌሶን 1፥2 ፊልጲስዩስ 1፥2 ቆላስይስ 1፥2 2ኛ ተሰሎንቄ 1፥2 2ኛ ጢሞቴዮስ 1፥2 ፊልሞና 1፥3
እነዚህ አናቅጽ ላይ "ጸጋ፣ ምሕረት እና ሰላም" ከአንዱ አምላክ እና ከኢየሱስ "ይሁን" ስለተባለ ውድድር እና ድርድር የሚወዱ ሚሽነሪዎች ኢየሱስ የአንዱን አምላክ መለኮት እንደሚጋራ አድርገው ለመረዳት ይቃጣሉ፥ ወለዱም ወደዱም ይህ ሙግት ውኃ የሚቋጥር እና የሚያነሳ ሙግት አይደለም። ምክንያቱም "ጸጋ እና ሰላም ይሁን" የተባለው ከአንዱ አምላክ እና ከኢየሱስ ብቻ ሳይሆን ከሰባቱ መላእክትም ጭምር ነው፦
ራእይ 1፥4 ካለውና ከነበረው "ከ-"ሚመጣውም፥ በዙፋኑም ፊት ካሉት "ከ-"ሰባቱ መናፍስት፥ ከታመነውም ምስክር ከሙታንም በኵር የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነ "ከ-ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እና ሰላም ለእናንተ ይሁን። χάρις ὑμῖν καὶ εἰρήνη ἀπὸ ὁ ὢν καὶ ὁ ἦν καὶ ὁ ἐρχόμενος, καὶ ἀπὸ τῶν ἑπτὰ Πνευμάτων ἃ ἐνώπιον τοῦ θρόνου αὐτοῦ, καὶ ἀπὸ Ἰησοῦ Χριστοῦ, ὁ μάρτυς ὁ πιστός, ὁ πρωτότοκος τῶν νεκρῶν καὶ ὁ ἄρχων τῶν βασιλέων τῆς γῆς.
ጸጋ እና ሰላም ከሦስት ምንነቶች እንደመጣ ይህ ጥቅስ ያስረዳል፦
፨አንደኛ "ያለው፣ የነበረው እና የሚመጣው" ከተባለው ከአብ፣
፨ሁለተኛ "ሰባቱ መናፍስት" ከተባሉት መላእክት፣
፨ሥስተኛ "ታማኝ ምስክር" ከሆነው ከኢየሱስ ነው።
"አፖ" ἀπὸ ማለት "ከ" ማለት ሲሆን ይህ መስተዋድድ "ያለው፣ የነበረው እና የሚመጣው" ከሚለው ቃል በፊት፣ "ሰባቱ መናፍስት" ከሚለው ቃል በፊት እና "ከታማኙ ምስክር" በፊት መግባቱ ሦስቱን ሃልዎቶች ለይቷቸዋል።
በተጨማሪ "ያለው፣ የነበረው እና የሚመጣው" የተባለውን ምንነት ከሰባቱ መናፍስት ምንነት እና ከኢየሱስ ምንነት ለመለየት "ካይ" καὶ ማለትን "እና" በሚል መስተጻምር መምጣቱ የሦስቱንም ምንነት ያሳያል። እነዚህ ሰባቱ መላእክት በእግዚአብሔር ወይም በዙፋኑ ፊት የሚቆሙትን እና የሚበሩት ሰባቱን መላእክት ናቸው፦
ራእይ 8፥2 በእግዚአብሔርም ፊት የሚቆሙትን "ሰባቱን መላእክት" አየሁ።
ራእይ 4፥5 በዙፋኑም ፊት "ሰባት የእሳት መብራቶች" ይበሩ ነበር፥ እነርሱም "ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት" ናቸው።
ራእይ 5፥6 እነርሱም ወደ ምድር ሁሉ የተላኩ "የእግዚአብሔር መናፍስት" ናቸው።
በተጨማሪ እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 990 ድኅረ ልደት የግሪክ ኤጲስ ቆጶስ ኦኩሜኑስ ራእይ 1፥4 ባብራራው ግራጫ የሆነ ማብራሪያ "ሰባቱ መናፍስት ሰባቱ መላእክት ናቸው" ብሏል። ታዲያ ጸጋ እና ሰላም ከሰባቱ መላእክት ስለሚሆን ሰባቱ መላእክት ከአንዱ አምላክ ጋር መለኮትን ይጋራሉን? እንቀጥል፦
ምሳሌ 24፥21 ልጄ ሆይ! ያህዌህን እና ንጉሥን ፍራ። יְרָֽא אֶת־ יְהוָ֣ה בְּנִ֣י וָמֶ֑לֶךְ
ምሳሌ 24፥22 መከራቸው ድንገት ይነሣልና፥
ከሁለቱ የሚመጣውን ጥፋት ማን ያውቃል? כִּֽי־פִ֭תְאֹם יָק֣וּם אֵידָ֑ם וּפִ֥יד נֵיהֶ֗ם מִ֣י יֹודֵֽעַ׃ ס
እዚህ ዐውድ ላይ “ንጉሥ” የተባለው በፍርድ ወንበር የሚቀመጥ ማንኛውም ንጉሥ ያመለክታል፥ ምሳሌ 20፥8 ተመልከት! ያህዌህ እና ንጉሥን “ፍሩ” ተብሎ የገባው የግሥ መደብ “ዩራ” יְרָֽא־ ሲሆን ሥርወ-ቃሉ “ያረ” יָרֵא ነው። ከያህዌህ እና ከንጉሥ የሚመጣው ጥፋት ድንገት ነው፥ እናማ ንጉሡ ከአንዱ አምላክ ጋር መለኮትን ይጋራልን? ዘርፈ ብዙ፣ መጠነ ሰፊ፣ ፈርጀ ጥልቅ፣ ደርዘ ምጥቅ የዕውቀት አንጡራ ሀብት ሲመጣ ሐሰት ከቦታው ገለል ይላል፥ አየህ ውሸት በእውነት ፊት እሳት የነካው ሰም፣ ፀሐይ ያየው ቅቤ፣ ነፋስ የጎበኘው አቧራ ነው። እኛ ሙሥሊሞች ከፈጣሪ ውጪ ሐጃችንን ይሞላልላን ብለን የምመገንበት መገን እና የምመጀንበት መጀን የለንም። እናንተንም አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ኢየሱስ አብ ነውን?
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
59፥24 እርሱ አላህ ፈጣሪው፣ "አስገኚው"፣ ቅርጽን አሳማሪው ነው፡፡ ለእርሱ መልካሞች ስሞች አሉት፡፡ هُوَ اللَّهُ الْخَالِقُ الْبَارِئُ الْمُصَوِّرُ ۖ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ
አምላካችን አሏህ በቁርኣን ከተገለጹ ዘጠና ዘጠኝ ስሞቹ አንዱ "አል ባሪእ" الْبَارِئ ማለትም "አስገኚው" ነው፦
59፥24 እርሱ አላህ ፈጣሪው፣ "አስገኚው"፣ ቅርጽን አሳማሪው ነው፡፡ ለእርሱ መልካሞች ስሞች አሉት፡፡ هُوَ اللَّهُ الْخَالِقُ الْبَارِئُ الْمُصَوِّرُ ۖ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ
በዕብራይስጥ ለአንዱ አምላክ "አብ" אָ֑ב ማለት "አስገኚ" "ምንጭ" ማለት ነው፥ አንዱ አምላክ ሰውን ጭቃ አርጎ ስለ ሠራ "አብ" אָ֑ב ተብሏል፦
ኢሳይያስ 64፥8 ያህዌህ ሆይ! አንተ አባታችን ነህ፤ እኛ ጭቃ ነን አንተም ሠሪያችን ነህ፥ እኛም ሁላችን የእጅህ ሥራ ነን። יְהוָ֖ה אָבִ֣ינוּ אָ֑תָּה אֲנַ֤חְנוּ הַחֹ֙מֶר֙ וְאַתָּ֣ה יֹצְרֵ֔נוּ וּמַעֲשֵׂ֥ה יָדְךָ֖ כֻּלָּֽנוּ׃
እዚህ አንቀጽ ላይ አንዱ አምላክ "አብ" אָ֑ב ሲባል ሰዎች "ጭቃ" ተብለዋል፥ ጭቃው የእጁ ሥራ ሲሆን "አባት" የሚለው "ሠሪ" ማለት ስለሆነ "አባታችን" የሚለው "ሠሪያችን" በሚል ተለዋዋጭ ቃል መጥቷል። "ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? ሲልም "ለሁላችን አንድ ሠሪ" መኖሩን የሚያሳይ ነው፦
ሚልክያስ 2፥10 ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን? הֲלֹ֨וא אָ֤ב אֶחָד֙ לְכֻלָּ֔נוּ הֲלֹ֛וא אֵ֥ל אֶֽחָ֖ד בְּרָאָ֑נוּ
ዮሐንስ 8፥41 አንድ አባት አለን፥ እርሱም አምላክ ነው። ἕνα Πατέρα ἔχομεν τὸν Θεόν.
ኤፌሶን 4፥6 አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ። εἷς Θεὸς καὶ Πατὴρ πάντων,
"አባት" ለአንዱ አምላክ ሲቀጸል በራሱ "አስገኚ" ማለት እንጂ "የባሕርይ አባት" ማለት አይደለም። ይህ ሆኖ ሳለ የሐዋርያት ቤተክርስቲያን በተለምዶው ኢየሱስ ብቻ"only Jesus" የሚባሉት "ኢየሱስ አብ ነው" ብለው ይህንን ጥቅስ ይጠቅሳሉ፦
ዮሐንስ 14፥10 ነገር ግን በእኔ የሚኖረው አብ እርሱ ሥራውን ይሠራል። ὁ δὲ Πατὴρ ἐν ἐμοὶ μένων ποιεῖ τὰ ἔργα αὐτοῦ.
ይህ ጥቅስ ጭራሽ "እኔ" የሚለው ማንነት እና "እኔ" በሚለው የሚኖረው አብ ሁለት ማንነት እንደሆኑ ቁልጭ አርጎ ያሳያል፥ እዚህ አንቀጽ ላይ "የሚኖር" ለሚለው የገባው ቃል "ሜኖን" μένων ነው። አብ በኢየሱስ መኖሩ ኢየሱስን አብ ካሰኘውማ በፍቅር የሚኖር ሰው አምላክ ሊሆን ነው፦
1ኛ ዮሐንስ 4፥16 በፍቅርም የሚኖር በአምላክ ይኖራል፥ "አምላክ በእርሱ ይኖራል"። καὶ ὁ μένων ἐν τῇ ἀγάπῃ ἐν τῷ Θεῷ μένει καὶ ὁ Θεὸς ἐν αὐτῷ μένει.
እዚህ አንቀጽ ላይ "ይኖራል" ለሚለው የገባው ቃል "ሜኔይ" μένει ሲሆን ከላይ ካለው ጋር በተመሳሳይ መሠረቱ "ሜኖ" μένω ነው፥ ታዲያ በፍቅር የሚኖር ሰው አምላክ ነውን? በመቀጠል "ኢየሱስ አብ ነው" ብለው ይህንን ጥቅስ ይጠቅሳሉ፦
ዮሐንስ 14፥11 እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ። πιστεύετέ μοι ὅτι ἐγὼ ἐν τῷ Πατρὶ καὶ ὁ Πατὴρ ἐν ἐμοί·
"እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ" ማለቱ ኢየሱስን አብ አብን ኢየሱስ ካደረገው ሐዋርያት ኢየሱስ ወይም ኢየሱስ ሐዋርያት ይሆኑ ነበር፦
ዮሐንስ 14፥20 እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ። ἐν ἐκείνῃ τῇ ἡμέρᾳ γνώσεσθε ὑμεῖς ὅτι ἐγὼ ἐν τῷ Πατρί μου καὶ ὑμεῖς ἐν ἐμοὶ κἀγὼ ἐν ὑμῖν.
"እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ" ማለቱ ሐዋርያት ከኢየሱስ ጋር ያላቸውን ግኑኝነት የሚያሳይ እንጂ ሐዋርያትን ኢየሱስ ካላደረገ እንግዲያውስ "እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ" ማለቱ አብ ከኢየሱስ ጋር ያለውን ግኑኝነት የሚያሳይ እንጂ ኢየሱስን አብ አያደርገውም። በነገራችን ላይ ሥላሴአውያን ለኢየሱስ አምላክነት ከሚጠቅሷቸው ተወዳጆች ጥቅስ አንዱ ነውና ሙግቱ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ነው፥ ስለዚህ ኢየሱስ አብ ወይም አምላክ ሳይሆን የአምላክ መልእክተኛ ነው። እናንተንም አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

በቅርብ ቀን በቪድዮ ተከታታይ ትምህርት በዚህ ዩቱብ ቻናል ይለቀቃል። ሰብስክራይብ፣ ሼር እና ላይክ በማድረግ ተደራሽነቱን ይወጡ! https://youtube.com/@Wahidislamicapologist
የጳውሎስ ቅጥፈት
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
3፥71 «የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! እውነቱን በሐሰት ለምን ትቀላቅላላችሁ? እውነቱንም እናንተ የምታውቁ ስትኾኑ ለምን ትደብቃላችሁ?» يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لِمَ تَلْبِسُونَ الْحَقَّ بِالْبَاطِلِ وَتَكْتُمُونَ الْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ
የአዲስ ኪዳን ምሁራን እንደሚያትቱት የማቴዎስ ወንጌል የተጻፈው በ 60 ወይም በ 70 አሊያም 85 ድኅረ ልደት ነው፣ የማርቆስ ወንጌል የተጻፈው በ 60 ድኅረ ልደት ነው፣ የሉቃስ ወንጌል የተጻፈው በ 85 ድኅረ ልደት ነው፣ የዮሐንስ ወንጌል የተጻፈው ከ 90 እስከ 100 ድኅረ ልደት ነው።
እነዚህ አራት ወንጌላት ከመጻፋቸው በፊት ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች ከ 53 እስከ 54 ድኅረ ልደት ሲጽፍ፦ "መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ በሦስተኛው ቀን ተነሣ" በማለት ተናግሯል፦
1ኛ ቆሮንቶስ 15፥3 እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ እንዲህ ብዬ፦ መጽሐፍ እንደሚል "ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም"፥ መጽሐፍም እንደሚል "በሦስተኛው ቀን ተነሣ"።
ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች ከ 53 እስከ 54 ድኅረ ልደት ሲጽፍ አራቱ ወንጌል ካልነበሩ "መጽሐፍ" የሚለው የብሉይ ኪዳንን መጻሕፍት ነው፥ ካልሆነ ሌላ የአዲስ ኪዳን መጽሐፍ የነበረ እና የጠፋ ይኖር ይሆን? ቅሉ እና ጥቅሉ ግን ብሉይ ኪዳን ላይ "መሢሑ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ በሦስተኛው ቀን ተነሣ" የሚል የለምና ጳውሎስ ቀጥፏል፥ በተለይ "በሦስተኛው ቀን ተነሣ" የሚለው ስለ ሕዝብ የሚናገረውን አጣሞ ነው፦
ሆሴዕ 6፥1-2 ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ፤ እርሱ ሰብሮናልና፥ እርሱም ይፈውሰናል፤ እርሱ መትቶናል፥ እርሱም ይጠግነናል። ከሁለት ቀን በኋላ ያድነናል፤ "በሦስተኛውም ቀን ያስነሣናል"፥ በፊቱም በሕይወት እንኖራለን።
"በሦስተኛውም ቀን ያስነሣናል" አለ እንጂ በሦስተኛውም ቀን ያስነሳዋል" አላለም። ቅጥፈቱ በዚህ አያበቃም፥ ጳውሎስ ተነስቶ ከወንጌላውያን ተስተካክሎ ወንጌል ጽፎ ነበር፦
ተአምረ ማርያም 113፥26 ጳውሎስ ተነስቶ ከእነርሱ ተስተካክሎ ወንጌል ጻፈ፣ ጴጥሮስም ሌላ ወንጌል ጻፈ፣ ማቴዎስም በበኩሉ ጻፈ፣ ዮሐንስም እንደ እነርሱው ወንጌል ጻፈ።
ታዲያ የጳውሎስ ወንጌል የት ገባ? ጳውሎስም የራሱን ወንጌል ለሉቃስ ሰጠውና ሉቃስ በስሙ ሰየመው፦
ተአምረ ማርያም 113፥27 ጴጥሮስም የጻፈውን ወንጌል ለማርቆስ ሰጠው፥ በስሙም ሰየመው፣ ጳውሎስም ለሉቃስ ሰጠውና በስሙ ሰየመው።
ለቃስ ከጳውሎስ ከተቀበለ ዘንዳ ሉቃስ ላይ ኢየሱስ፦ "ክርስቶስ መከራ ይቀበላል በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ይነሣል፥ በስሙም ንስሐና የኃጢአት ስርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል" ተብሎ ተጽፎአል ብሎ እንደተናገረ አስዋሽተውታል፦
ሉቃስ 24፥46-47 እንዲህም አላቸው፦ "ክርስቶስ መከራ ይቀበላል በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ይነሣል፥ በስሙም ንስሐና የኃጢአት ስርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል" ተብሎ እንዲሁ ተጽፎአል።
ብሉይ ኪዳን ላይ የትኛውም መጽሐፍ ላይ "ክርስቶስ መከራ ይቀበላል በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ይነሣል፥ በስሙም ንስሐና የኃጢአት ስርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል" የሚል የለም፥ በተለይ "ክርስቶስ መከራ ይቀበላል በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ይነሣል" የሚል ሽታው የለም። ከአዲስ ኪዳን ውስጥ 14 ደብዳዎችን የጻፈው ይህ ሰው እውነትን በቅጥፈት ቀላቅሏል፥ ጳውሎስ እንዲህ ዓይነት ቅጥፈት ቀጥፎ ማስቀጠፉ በራሱ እውነትን በሐሰት መቀላቀል ነው፦

አምላካችን አሏህ ከዚህ ቅጥፈት አውጥቶ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

የአማልክት አምላክ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
21፥22 በሁለቱ (በሰማያት እና በምድር) ውስጥ ከአሏህ ሌላ አማልክት በነበሩ ኖሮ በተበላሹ ነበር፡፡ የዐርሹ ጌታ አሏህም ከሚሉት ሁሉ ጠራ፡፡ لَوْ كَانَ فِيهِمَا آلِهَةٌ إِلَّا اللَّهُ لَفَسَدَتَا ۚ فَسُبْحَانَ اللَّهِ رَبِّ الْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ
በባይብል "አምላክ" የሚለው ስያሜ በሁለት መልኩ ይመጣል፥ አንዱ የባሕርይ ስያሜ"ontological term" ሆኖ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የግብር ስያሜ"functional term" ሆኖ ነው። አንዱ አምላክ አምላክነቱ የባሕርይ ገንዘቡ ሲሆን ከእርሱ በቀር በሐቅ የሚመለክ ማንም የለም፦
1 ቆሮንቶስ 8፥4 ከአንዱም በቀር ማንም አምላክ እንደሌለ እናውቃለን።
"ማንም" የሚለው ቃል "ማንነትን" የሚያሳይ ሲሆን ከአንድ ማንነት ውጪ ሌላ ምንነት አምላክ አይደለም፥ ይህም አንድ ነጠላ ማንነት "እኔ" እያለ የሚናገር ብቻውን ተመላኪ ነው፦
ኢሳይያስ 45፥5 እኔ ያህዌህ ነኝ ከእኔም ሌላ ማንም የለም፤ ከእኔም በቀር አምላክ የለም፤
ኢሳይያስ 45፥6 እኔ ያህዌህ ነኝ፥ ከእኔም ሌላ ማንም የለም።
ኢሳይያስ 45፥21 እኔ ያህዌህ አይደለሁምን? ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም።
ኢሳይያስ 45፥22 እኔ አምላክ ነኝና፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለምና ወደ እኔ ዘወር በሉ ትድኑማላችሁ።
ኢሳይያስ 46፥9 እኔ አምላክ ነኝና፥ ሌላም የለምና የቀድሞውን የጥንቱን ነገር አስቡ፤ እኔ ያህዌህ ነኝ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም።
"እኔ" ለአንድ ነጠላ ቅዋሜ ማንነት"person" የምንጠቀምበት ተውላጠ ስም ነው፥ ይህ አንድ እኔነት ከእርሱ በቀር ማንም ማንነት አምላክነት የለውም። ነገር ግን በሰማይ መላእክት እንዲሁ በምድር ነቢያት አማልክት ተብለዋል፦
1 ቆሮንቶስ 8፥5-6 ነገር ግን በሰማይ ሆነ በምድርም ሆነ አማልክት የተባሉ ምንም ቢኖሩ ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ አለን።
በሰማይ ሆነ በምድርም ሆነ አማልክት የተባሉ ምንም ቢኖሩ የእነርሱ አምላክነት የጸጋ ሲሆን የባሕርይ አምላክነት ያለው አንድ አምላክ አብ ብቻውን አለ። በሰማይ ያሉት መላእክት "አማልክት" ተብለዋል፦
መዝሙር 138፥1 "በአማልክትም" ፊት እዘምርልሃለሁ። אֹודְךָ֥ בְכָל־לִבִּ֑י נֶ֖גֶד אֱלֹהִ֣ים אֲזַמְּרֶֽךָּ׃
መዝሙር 8፥5 "ከአማልክትን" እጅግ ጥቂት አሳነስኸው"። וַתְּחַסְּרֵ֣הוּ מְּ֭עַט מֵאֱלֹהִ֑ים
በዕብራይስጥ "ኤሎሃ" אלוהּ ማለት "አምላክ" ማለት ነው፥ የኤሎሃ ብዜት ደግሞ "ኤሎሂም" אלהים ሲሆን "አማልክት" ማለት ነው። በምድር ላይ ደግሞ ነቢያት እራሳቸው የአምላክ እንደራሴ ሆነው ስለሚናገሩ "አምላክ" ተብለዋል፦
ዮሐንስ 10፥34 ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፦ እኔ፦ አማልክት ናችሁ አልሁ" ተብሎ በሕጋችሁ የተጻፈ አይደለምን?
ዮሐንስ 10፥35 መጽሐፉ ሊሻር አይቻልምና እነዚያን የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን "አማልክት" ካላቸው። .
ነቢያትን "አማልክት ናችሁ" ያላቸው "ከእኔ በቀር አምላክ ማንም የለም" "ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ" ብሎ የተናገረው አንዱ አምላክ ነው፦
ዘጸአት 20፥3 ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ።
መዝሙር 82፥6 እኔ ግን፦ "አማልክት ናችሁ"፥ ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ" አልሁ።
መጽሐፈ ምሥጢር ምዕራፍ 4 ቁጥር 25
ስለ ነቢያትም፦ "እናንተ አማልክት ናችሁ፥ ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ" እኔ አልሁ"።
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ "እናንተ አማልክት ናችሁ" የሚለው ስለ ነቢያት እንደሆነ አስረግጠው ነግረውናል። ነገር ግን በሰማይ ሆነ በምድርም ሆነ አማልክት የተባሉ ምንም ቢኖሩ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ፥ ፍጥረት ለእርሱ የሆነ አንድ አምላክ አብ አለ። አብ ከሁሉ በላይ የሚሆን አንድ አምላክ ነው፦
1ኛ ቆሮንቶስ 8፥6 ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ አለን።
ኤፌሶን 4፥6 "ከሁሉ በላይ" የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ።
አንዱ አምላክ አብ በሰማይ አማልክት የተባሉት የመላእክት እና በምድር ላይ አማልክት የተባሉት የነቢያት ሁሉ አምላክ ስለሆነ "የአማልክት አምላክ" ተብሏል፦
መዝሙር 50፥1 "የአማልክት አምላክ" ያህዌህ ተናገረ።
ኢያሱ 22፥22 "የአማልክት አምላክ" ያህዌህ፥ "የአማልክት አምላክ" ያህዌህ እርሱ አውቆታል።
መዝሙር 136፥2 "የአማልክትን አምላክ" አመስግኑ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
ለአምላክ አምላክ ካለው አምላክ ያለው አምላክ አምላክነቱ የግብር ስያሜ እንጂ ተመላኪ አንዱ አምላክ ማለት አይደለም፥ አምላክ በግብር ስያሜ የአንዱ አምላክ እንደራሴ፣ ቃል አቀባይ፣ አፈ ቀላጤ፣ ወኪል ማለት ነው። የግብር አምላክ ተጠሪነቱ ለባሕርይ አምላክ ስለሆነ "አምላክ" መባሉ የጸጋን እንጂ በራስ መብቃቃትን አያሳይም፦
መዝሙር 45፥6 "አምላክ" ሆይ! ዙፋንህ ለዘላለም ነው፥ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው።
መዝሙር 45፥7 ከባልንጀሮችህ ይልቅ
አምላክ አምላክህ በደስታ ዘይትን ቀባህ። מְשָׁחֲךָ֡ אֱלֹהִ֣ים אֱ֭לֹהֶיךָ שֶׁ֥מֶן שָׂשֹׂ֗ון מֵֽחֲבֵרֶֽיךָ׃
ንጉሥ ሰሎሞን "አምላክ" መባሉ በጸጋ ያገኘው ስለሆነ አባቱ ዳዊት፦ "አምላክ አምላክህ በደስታ ዘይትን ቀባህ" በማለት የንጉሡ አምላክነት አምላክ እንዳለው ተናግሯል። "አምላክ ሆይ! አምላክ አምላክህ" የሚለው ኃይለ ቃል የሚያሳየው አምላክ ያለው አምላክን ስለሆነ "አምላክ ሆይ" መባሉ ግብርን እንጂ ባሕርይን አያሳይም፥ ምክንያቱም ለባሕርይ አምላክ አምላክ የለውምና። "አምላክ አምላክህ በደስታ ዘይትን ቀባህ" የሚለው ጥቅስ ለንጉሥ ሰሎሞን የሚያመለክት ቢሆንም የዕብራውያን ጸሐፊ ድርብ ንግግር አርጎ ለኢየሱስ ተጠቅሞበታል፦
ዕብራውያን 1፥8 ስለ ልጁ ግን፦ አምላክ ሆይ! ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው።
ዕብራውያን 1፥9 አምላክ አምላክህ ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ" ይላል። ἔχρισέν σε, ὁ Θεός, ὁ Θεός σου ἔλαιον ἀγαλλιάσεως παρὰ τοὺς μετόχους σου.
ስለዚህ እዚህ አንቀጽ ላይ ኢየሱስ አምላክ የተባለበት ንጉሥ ሰሎሞን በተባለበት ስሌት እና ቀመር የግብር እንጂ የባሕርይ አይደለም፥ ይህ እንግዲህ የባይብል እሳቤ ነው። ቅሉ እና ጥቅሉ ግን ቁርኣን ሲወርድ በሰማያት እና በምድር ውስጥ ከአሏህ ሌላ አማልክት እንደሌሉ እና የዐርሹ ጌታ አሏህም ከሚሉት ሁሉ እንደጠራ ይናገራል፦

የቱን ትመርጣላችሁ? የተወሳሰበው ትምህርት ወይስ ጥልል እና ጥንፍፍ ያለው የተውሒድ ትምህርት? አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ዘላለማዊ ምንምነት
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
4፥56 እነዚያን በተአምራታችን የካዱትን በእርግጥ እሳትን እናገባቸዋለን፡፡ ስቃይን እንዲቀምሱ ቆዳዎቻቸው በተቃጠሉ ቁጥር ሌሎችን ቆዳዎች እንለውጥላቸዋለን፡፡ إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا بِآيَاتِنَا سَوْفَ نُصْلِيهِمْ نَارًا كُلَّمَا نَضِجَتْ جُلُودُهُم بَدَّلْنَاهُمْ جُلُودًا غَيْرَهَا لِيَذُوقُوا الْعَذَابَ ۗ
በኢሥላም ተስተምህሮት ሰው በአሏህ ላይ ላሻረከው የሺርክ ወንጀል በጀሀነም ይኖራል፥ ከዚያ ወዲህ ላለው ወንጀል እንደ ሥራው መጠን ይቀጣል፥ ቅጣቱን እስከሚጨርስ ድረስ ቆዳዎቹ በተቃጠሉ ቁጥር ሌሎች ቆዳዎች ይለወጥለታል፦
4፥56 እነዚያን በተአምራታችን የካዱትን በእርግጥ እሳትን እናገባቸዋለን፡፡ ስቃይን እንዲቀምሱ ቆዳዎቻቸው በተቃጠሉ ቁጥር ሌሎችን ቆዳዎች እንለውጥላቸዋለን፡፡ አሏህ አሸናፊ ጥበበኛ ነውና፡፡ إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا بِآيَاتِنَا سَوْفَ نُصْلِيهِمْ نَارًا كُلَّمَا نَضِجَتْ جُلُودُهُم بَدَّلْنَاهُمْ جُلُودًا غَيْرَهَا لِيَذُوقُوا الْعَذَابَ ۗ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَزِيزًا حَكِيمًا
ወደ ባይብል ስንሄድም የማያምኑ የሚቀጡበት ቅጣት ዘውታሪ ቅጣት ለመሆኑ እኵሌቶቹ ወደ እፍረት እና ወደ ዘላለም ጕስቍልና እንደሚሄዱ፣ ቀን እና ሌሊት ዕረፍት እንደሌላቸው፣ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ቀን እና ሌሊት እንደሚሰቃዩ ይናገራል፦
ዳንኤል 12፥2 በምድርም ትቢያ ውስጥ ካንቀላፉቱ ብዙዎች ይነቃሉ፤ እኵሌቶቹ ወደ ዘላለም ሕይወት፥ እኵሌቶቹም ወደ እፍረት እና ወደ ዘላለም ጕስቍልና።
ራእይ 14፥11 ለአውሬው እና ለምስሉም የሚሰግዱ የስሙንም ምልክት የሚቀበል ሁሉ ቀን እና ሌሊት ዕረፍት የላቸውም።
ራእይ 20፥10 ለዘላለምም እስከ ዘላለም ቀን እና ሌሊት ይሣቀያሉ።
ኢሳይያስ 66፥24 ወጥተውም በእኔ ያመፁብኝን ሰዎች ሬሳቸውን ያያሉ፤ ትላቸው አይሞትምና፥ እሳታቸውም አይጠፋምና።
ኤርምያስ 23፥40 የዘላለምንም ስድብ ከቶም ተረስቶ የማይጠፋውን የዘላለምን እፍረት አመጣባችኋለሁ።
እሳቱ የማይጠፋ እና የማይጠፋውን የዘላለም እፍረት ካለ የዘላለም ምንምነት"eternal annihilation" የሚባለው ትምህርት ስህተት ነው፥ "የዘላለም ምንምነት" ማለት ወንጀለኛው በእሳት ተቃጥሎ እንደ ዐመድ ከመፈጠሩ በፊት ወደነበረበት ምንም የሚሆንበት እንጂ ስቃይ እና ህመም የማይሰማበት ሁኔታ ነው" ተብሎ የሚሰጥ ትምህርት ነው። ይህንን የዘላለም ምንምነት ከሚያስተምሩ የቤተክርስቲያን አበው መካከል የአንጾኪያ አግናጢዮስ፣ ዮስጦስ ሰማዕቱ፣ የሰርምኔሱ ኢራኒየስ እና የሮሙ አንብሮስ ናቸው። በዘመናችንም ከፕሮቴስታንት አንግሊካን፣ እንዲሁ አድቬንቲስት እና የይሆዋ ምስክሮች በዘላለማዊ ምንምነት ያምናሉ፥ የዘላለም ምንምነት ከሚጠቀሱ ጥቅሳት መካከል ለናሙና አንዱን እንመልከት፦
ማቴዎስ 10፥28 ይልቅስ ነፍስን እና አካልን በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ። φοβεῖσθε δὲ μᾶλλον τὸν δυνάμενον καὶ ψυχὴν καὶ σῶμα ἀπολέσαι ἐν γεέννῃ.
እዚህ ጥቅስ ላይ "ነፍስን እና አካልን በገሃነም ሊያጠፋ" ስለሚል ነፍስ እና አካል በእሳት ተቃጥለው ወደ ምንምነት ይሆናሉ አይልም፥ ከዚያ ይልቅ ከአምላክ መራቅን እና በዘላለም ጥፋት ይቀጣሉ፦
2ኛ ተሰሎንቄ 1፥9 ከጌታ ፊት እና ከኃይሉ ክብር ርቀው በዘላለም ጥፋት ይቀጣሉ። οἵτινες δίκην τίσουσιν ὄλεθρον αἰώνιον ἀπὸ προσώπου τοῦ Κυρίου καὶ ἀπὸ τῆς δόξης τῆς ἰσχύος αὐτοῦ,
ደግሞም "ሊያጠፋ" ለሚለው የግሥ መደብ ሥርወ ቃሉ "አፓሉሚ" ἀπόλλυμι ሲሆን መራቅን ወይም ከእይታ መሰወርን ለማመልከት መጥቷል፦
ሉቃስ 5፥24 ይህ ልጄ ሞቶ ነበር እና ደግሞም ሕያው ሆኖአል፥ "ጠፍቶም" ነበር ተገኝቶአልም። ደስም ይላቸው ጀመር። ὅτι οὗτος ὁ υἱός μου νεκρὸς ἦν καὶ ἀνέζησεν, ἦν ἀπολωλὼς καὶ εὑρέθη. καὶ ἤρξαντο εὐφραίνεσθαι.
"ጠፍቶ ነበር" ማለት "ምንም ሆኖ ነበር" ማለት ሳይሆን ከአባቱ እቅፍ አለመኖሩን እና መራቁን የሚያሳይ ነው፥ በግ ከእረኛው እንዲሁ ድሪም ከባለድሪም ሲጠፋ ከእይታ ተሰወሩ እንጂ ፍጹም ምንም"complete destruction" እንደማይሆኑ ሁሉ ወንጀለኛም "ይጠፋል" ማለት "ምንም" ይሆናል ማለት አይደለም፦
ሉቃስ 15፥4 መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ "ቢጠፋ" ዘጠና ዘጠኙን በበረሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ "ሊፈልገው" የማይሄድ ከእናንተ ማን ነው?
ሉቃስ 15፥8 ወይም አሥር ድሪም ያላት አንድ ድሪም "ቢጠፋባት" መብራት አብርታ ቤትዋንም ጠርጋ "እስክታገኘው" ድረስ አጥብቃ የማትፈልግ ሴት ማን ናት?
መጥፋት ምንምነት ቢሆን ኖሮ መፈለጉ ትርጉም የለውም፥ ምክንያቱም የሌለ ነገር አይፈለግም። አሏህ ከተሳሳተ ትምህርት ይጠብቀን! አሚን።

ትምህርት በዩቱብ ቪድዮ ተለቋል። መልእክቱ ተደራሽነት እንዲኖረው ላይክ፣ ሼር እና ሰብስክራይብ በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ እንሁን። ወጀዛኩሙላህ ኸይራ!
https://youtu.be/VsdOTeybj40
https://youtu.be/VsdOTeybj40
ሐጅ በባይብል
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
22፥27 አልነውም፦ "በሰዎችም ውስጥ በሐጅ ትእዛዝ ጥራ!፡፡ وَأَذِّن فِي النَّاسِ بِالْحَجِّ يَأْتُوكَ رِجَالًا
"ሐጅ" حَجّ የሚለው ቃል "ሐጀ" حَجَّ ማለትም "ጎበኘ" ከሚል ሥርወ-ቃል የተገኘ ሲሆን "ጉብኝት" ማለት ነው፥ አምላካችን አሏህ ለኢብራሂም፦ "በሰዎችም ውስጥ በሐጅ ትእዛዝ ጥራ" አለው፦

በባይብል ደግሞ "ኸግ" חַג የሚለው ቃል "ኸገግ" חָגַג ማለትም "ጎበኘ" "ከበበ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ጉብኝት" ማለት ነው፦
ዘጸአት 10፥9 "ሙሴም፦ "ለያህዌህ "ኸግ" ልናደርግ ስለሆነ ወጣቶቻችንን እና ሽማግሌዎቻችንን፣ ወንዶች እና ሴቶች ልጆቻችን፣ በጎቻችንን እና ከብቶቻችንን ይዘን እንሄዳለን" አለ። וַיֹּ֣אמֶר מֹשֶׁ֔ה בִּנְעָרֵ֥ינוּ וּבִזְקֵנֵ֖ינוּ נֵלֵ֑ךְ בְּבָנֵ֨ינוּ וּבִבְנֹותֵ֜נוּ בְּצֹאנֵ֤נוּ וּבִבְקָרֵ֙נוּ֙ נֵלֵ֔ךְ כִּ֥י חַג־יְהוָ֖ה לָֽנוּ׃
ዘጸአት 12፥14 ይህም ቀን መታሰቢያ ይሁናችሁ፥ ለያህዌህ "ኸግ" ታደርጉታላችሁ፤ ለልጅ ልጃችሁ ሥርዓት ሆኖ ለዘላለም ታደርጉታላችሁ። וְהָיָה֩ הַיֹּ֨ום הַזֶּ֤ה לָכֶם֙ לְזִכָּרֹ֔ון וְחַגֹּתֶ֥ם אֹתֹ֖ו חַ֣ג לַֽיהוָ֑ה לְדֹרֹ֣תֵיכֶ֔ם חֻקַּ֥ת עֹולָ֖ם תְּחָגֻּֽהוּ׃
በብዙ ትርጉም ላይ "በዓል"feast" ተብሎ የተቀመጠው ቃል በዕብራይስጡ "ጉብኝነት"pilgrim" ነው፥ "ኹግ" חוּג ማለት እራሱ "ኸገግ" חָגַג ማለትም "ከበበ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ክበብ" ማለት ነው። ጥንት ለዘላለም የተሰጣቸው የጉብኝነት በዓል በመዞር ያረጉት ነበር፥ በአይሁዳውያን በዓመት ሦስት ጊዜ የዳስ በዓል፣ በዓለ ኃምሳ እና ፋሲካ ሊያከብሩ ሲሉ በወሩ ከ 15 እስከ 21 ለሥድስት ወይም ለሰባት ቀን ሲጎበኙ ይዞራሉ። "ሱካህ" סוכה ማለትም "ድንኳን" ማለት ሲሆን ድንኳኑን የሚዞሩት ዙረት "ሐካፋህ" ይባላል። "ሐካፋህ" הקפה ማለት "ዙረት" ማለት ሲሆን የሚዞሩት ሰባት ጊዜ ስለሆነ "ሐካፉት" הקפות ይሉታል፥ ይህም በሚንሃግ፣ በሚድራሽ እና በባቢሎን ታልሙድ ተዘግቧል። አሏህ ሐጅ ከሚያደርጉት ሑጃጆች ያድርገን! አሚን።

ኢየሱስ
"ነገረ ክርስቶስ"Christology"
ትምህርት በዩቱብ ቪድዮ ተለቋል። መልእክቱ ተደራሽነት እንዲኖረው ላይክ፣ ሼር እና ሰብስክራይብ በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ እንሁን። ወጀዛኩሙላህ ኸይራ!
https://youtu.be/7oao4CB_JSk

ዩቱብ ቀጥታ ለመግባት ይህንን ሊንክ ያስፈንጥሩ፦ https://youtube.com/@Wahidislamicapologist
ተጠየቅ ዘኦርቶዶክስ አዋልድ
እውን ጌታ ዕውር ነውን? ዕውር ሆኖ ከዕውር ጋር ጉድጓድ ይገባልን?
የአቡነ ሀብተ ማርያም ገድል ገጽ 163
"ጌታም፦ "ኃይል የምሰጥ እኔ ነኝ፤ ዕውር ዕውርን ቢከተል ሁለቱም ከጉድጓድ እንዲወድቁ #እኔ #ዕውር #ነኝ፤ በሰላም ወደ እውነተኛ መንገድ የምመራ አይደለሁም፤ ስሜ ብርሃን ነው።
ማቴዎስ 15፥14 ተዉአቸው፤ ዕውሮችን የሚመሩ ዕውሮች ናቸው፤ #ዕውርም #ዕውርን #ቢመራው #ሁለቱም #ወደ #ጉድጓድ #ይወድቃሉ፡ አለ።