ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
አጀል

ክፍል አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

6፥2 እርሱ ያ ከጭቃ የፈጠራችሁ ከዚያም ጊዜን የወሰነ ነው፥ እርሱም ዘንድ የተወሰነ ጊዜ አለ፡፡ هُوَ الَّذِي خَلَقَكُم مِّن طِينٍ ثُمَّ قَضَىٰ أَجَلًا ۖ وَأَجَلٌ مُّسَمًّى عِندَهُ

"አጀል" أَجَل የሚለው ቃል "አጀለ" أَجَّلَ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ጊዜ" ማለት ነው፦
2፥282 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ በዕዳ በተዋዋላችሁ ጊዜ ጻፉት፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا تَدَايَنتُم بِدَيْنٍ إِلَىٰ أَجَلٍ مُّسَمًّى فَاكْتُبُوهُ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ጊዜ" ለሚለው የገባው ቃል "አጀል" أَجَل መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል። አጀል በሁለት ይከፈላል፥ አንደኛው "አጀሉል ሙአለቅ" ሲሆን ሁለተኛ "አጀሉል ሙሠማ" ነው። እነዚህን ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦
6፥2 እርሱ ያ ከጭቃ የፈጠራችሁ ከዚያም ጊዜን የወሰነ ነው፥ እርሱም ዘንድ የተወሰነ ጊዜ አለ፡፡ هُوَ الَّذِي خَلَقَكُم مِّن طِينٍ ثُمَّ قَضَىٰ أَجَلًا ۖ وَأَجَلٌ مُّسَمًّى عِندَهُ

ሰውን ከፈጠረ በኃላ "ሱመ" ثُمَّ የሚለው ቅድመ ተከተል መቀመጡ የጊዜ ቅድመ ተከተልን ያሳያል፥ "ቀዷ" قَضَىٰ የሚለው ቃል "ቀዶ" قَضَى ማለትም "ወሰነ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ውሳኔ" ማለት ነው። ሰው ከተፈጠረ በኃላ ያለው ውሳኔ "ቀዷ ሙአለቅ" قَضَىٰ مُعَلَّق ሲሆን መልአክ መጥቶ "አጀሉል ሙአለቅ" أَجَل المُعَلَّق የሚጽፈው ነው፥ "ሙዐለቅ" مُعَلَّق ማለት "የተንጠለጠለ" ማለት ሲሆን መልአኩ መጥቶ ከሚጽፈው አራት ነገሮች አንዱ አጀሉል ሙአለቅ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 59 ሐዲስ 19
"ከዚያም አሏህ መልአክ ይልክና አራት ቃላትን ሲሳዩን፣ ጊዜውን፣ ሥራውን እና ሐዘኑን ወይም ደስታው እንዲጽፍ ይታዘዛል"። ثُمَّ يَبْعَثُ اللَّهُ مَلَكًا، فَيُؤْمَرُ بِأَرْبَعِ كَلِمَاتٍ، وَيُقَالُ لَهُ اكْتُبْ عَمَلَهُ وَرِزْقَهُ وَأَجَلَهُ وَشَقِيٌّ أَوْ سَعِيدٌ‏

ይህ አጀሉል ሙአለቅ ግለሰቡ በሚያሳየው ነጻ ፈቃድ አሏህን ሊያብሰው ወይም ሊያጸድቀው የሚችል ነገር ነው፦
13፥39 አላህ የሚሻውን ያብሳል፤ ያጸድቃልም፡፡ የመጽሐፉ መሠረትም እርሱ ዘንድ ነው፡፡ يَمْحُو اللَّهُ مَا يَشَاءُ وَيُثْبِتُ ۖ وَعِندَهُ أُمُّ الْكِتَابِ

ከልደት እስከ ሞት እስከሚመጣበት ጊዜ ድረስ ያለው አጀሉል ሙአለቅ ሶደቃህ በመስጠት፣ ወላጆችን በማክበር፣ የጎረቤት ሐቅ በመጠበቅ እንዲሁ ዝምድናን በመቀጠል ዕድሜ ይረዝማል፦
አደቡል ሙፍረድ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 22
ሠህል ኢብኑ ሙዓዝ ከአባቱ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ወላጆቹን የሚያከብር ለእርሱ መልካም ነው፥ አሏህ ዐዘ ወጀል ዕድሜውን ያረዝመዋል"። عَنْ سَهْلِ بْنِ مُعَاذٍ، عَنْ أَبِيهِ قَالَ‏:‏ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم‏:‏ مَنْ بَرَّ وَالِدَيْهِ طُوبَى لَهُ، زَادَ اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ فِي عُمْرِهِ‏.‏
አደቡል ሙፍረድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 12
ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ "ማንም ጌታውን የሚፈራ እና ዝምድናውን የሚቀጥል ዕድሜው ይረዝማል"። عَنِ ابْنِ عُمَرَ قَالَ‏:‏ مَنِ اتَّقَى رَبَّهُ، وَوَصَلَ رَحِمَهُ، نُسِّئَ فِي أَجَلِهِ
የሰው ዕድሜ ማጠር እና መርዘም አንደኛ በከይፊያህ ሁለተኛ በከሚያህ ደረጃ ሊሆን ይችላል፥ "ከይፊያህ" كَيْفِيَّة ማለት "ዓይነት"quality" ማለት ሲሆን አንድ ሰው በሚሠራው መልካም ሥራ የዕድሜው ከይፊያህ በመብቃቃት ይረዝማል፥ ለምሳሌ፦ አንድ ዓመት 12 ወር ነው፥ ለይለቱል ቀድር በዓመት አንዴ ስትሆን ከ 1000 ወር በላጭ ናት። 1000 ወር 83 ዓመት (1000÷12=83) ይሆናል፥ ለምሳሌ፦ አንድ ሰው 10 ዓመት ሙሉ ተከታትሎ ለይለቱል ቀድርን ያገኘ 830 ዓመት (83×10=830) በላይ እንደኖረ ይሆናል፦
97፥2 *መወሰኛይቱም ሌሊተ ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ?* وَمَا أَدْرَاكَ مَا لَيْلَةُ الْقَدْرِ
97፥3 *መወሰኛይቱ ሌሊት ከሺሕ ወር በላጭ ናት*፡፡ لَيْلَةُ الْقَدْرِ خَيْرٌ مِّنْ أَلْفِ شَهْرٍ
ሙወጧእ ማሊክ መጽሐፍ 19, ሐዲስ 706
ማሊክ ከታመኑ አህለል ዒልም ሰው ሰምቶ እንደተናገረው፦ "የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” ከእሳቸው በፊት የነበሩት ሕዝቦች የሕይወት ቆይታ እና አሏህ ያንን ቆይታ እንዴት እንደፈቀደ አጤኑ። ከእሳቸው በፊት የነበሩት ሕዝቦች ረጅም ዕድሜያቸውን ማከናወን የቻሉትን ያህል ሌሎች በጎ ተግባሮችን መሥራት እንዲችሉ የእርሳቸው ኡማህ በጣም አጭር እንደነበሩ ሆኖ ነበር፡፡ “መወሰኛይቱ ሌሊት ከሺሕ ወር በላጭ ናት” ብሎ አሏህ ለይለቱል ቀድርን ሰጣቸው”። عَنْ مَالِكٍ، أَنَّهُ سَمِعَ مَنْ، يَثِقُ بِهِ مِنْ أَهْلِ الْعِلْمِ يَقُولُ إِنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم أُرِيَ أَعْمَارَ النَّاسِ قَبْلَهُ أَوْ مَا شَاءَ اللَّهُ مِنْ ذَلِكَ فَكَأَنَّهُ تَقَاصَرَ أَعْمَارَ أُمَّتِهِ أَنْ لاَ يَبْلُغُوا مِنَ الْعَمَلِ مِثْلَ الَّذِي بَلَغَ غَيْرُهُمْ فِي طُولِ الْعُمْرِ فَأَعْطَاهُ اللَّهُ لَيْلَةَ الْقَدْرِ خَيْرٌ مِنْ أَلْفِ شَهْرٍ ‏.‏

የረመዷን ሠላሳ ቀን እና የሸዋል ስድስት ቀን መፆም አንድ ዓመት እንደፆምን የሚታሰበው አንድ መልካም ሥራ ምንዳው በአሥር እጥፍ ስለሆነ ነው፦
6፥160 በመልካም ሥራ የመጣ ሰው ለእርሱ ዐሥር ብጤዎችዋ አሉት፡፡ مَن جَاءَ بِالْحَسَنَةِ فَلَهُ عَشْرُ أَمْثَالِهَا
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 78
አቢ አዩብ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ማንም ረመዷንን የጾመ ከዚያም ከሸዋል ወር ስድስት ቀናትን ያስከተለ ዋጋው ዓመቱን ሙሉ እንደጾመ ነው"። عَنْ أَبِي أَيُّوبَ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ مَنْ صَامَ رَمَضَانَ ثُمَّ أَتْبَعَهُ سِتًّا مِنْ شَوَّالٍ فَذَلِكَ صِيَامُ الدَّهْرِ ‏

አንድ መልካም ሥራ አሥር ብጤዎች ካሉት የረመዷን አንድ ወር የያዘው 30 ቀናት መጾም የአሥር ወር ምንዳ አለው፥ 30×10= 300 ቀን ወይም 10 ወር ይሆናል።
እንዲሁ የሸዋል ስድስት ቀን መጾም የስድሳ ቀን ምንዳ አለው፥ 6×10= 60 ቀን ወይም 2 ወር ይሆናል።
በጥቀሉ 360 ቀን ወይም 12 ወር ከሆነ መልካም ሥራ በከይፊያህ ሲረዝም ይህንን ይመስላል። ጊዜ ጸጋ ነውና በአግባብ መጠቀም ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 36, ሐዲስ 1
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ከሰዎች ብዙዎች በአግባቡ የማይጠቀሙባቸው ሁለት ጸጋዎች ጤንነት እና ጊዜ ናቸው"። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ نِعْمَتَانِ مَغْبُونٌ فِيهِمَا كَثِيرٌ مِنَ النَّاسِ الصِّحَّةُ وَالْفَرَاغُ ‏"‏

"ከሚያህ" كَمِّيَّة ማለት ደግሞ "መጠን"quantity" ማለት ሲሆን የሰው ዕድሜ መጠን በመልካም ሥራ፣ የህክምና ሰበብ በማድረስ፣ ጥንቃቄ በማድረግ ሊረዝም አሊያም መጥፎ ሥራ በመሥራት፣ በግድየለሽነት፣ በዝርክርክነት ሊያጥር ይችላል፥ "ሐዘር" حَذَر ማለት "ጥንቃቄ"discretion" ማለት አምላካችን አሏህ የራሳችን ጥንቃቄ እንድንይዝ ነግሮናል፦
4፥71 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጥንቃቄአችሁን ያዙ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا خُذُوا حِذْرَكُمْ

አምላካችን አሏህ መልአኩ በሚከትበው ኪታብ ላይ ለመልአኩ የተወሰነ የዕድሜ ቁጥር እንዲጽፍ ይሰጠው እና ያ ቁጥር በመልካም ሥራ ሊረዝም ወይም በመጥፎ ሥራ ሊያጥር ይችላል፥ መልአኩ የጻፈው ኪታብ ላይ ሊጨምረው ሊቀንሰው የሚችል ነገር ስለሆነ ሙአለቅ ነው። ኢንሻሏህ ስለ አጀሉል ሙሠማ በክፍል ሁለት እናጠናቅቃለን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የዛሬው የኢትዮጵያ ትርምስ የትላንቱ የኦርቶዶክስ መምህራን፦
መምህር አባይነህ ካሴ
መምህር ምህረተ አብ
መምህር ታሪኩ አበራ
መምህር ዮርዳኖስ አበበ
መምህር ዘመድኩን በቀለ
የዘሩት የጥላቻ ንግግር ነው።

ሁላችንም በየግሩፑ፣ በየፔጁ እና በየኮሜንቱ ሼር ማድረግ አንርሳ!
ፋና

ቀንድ ያለው ዝንጀሮ
የሚራገጥ ዶሮ፤
የሚያገሳ ጉንዳን
የሚታዘል ዝሆን፤
የሚጥሚጣ ንፍሮ
ይህ ነው የኛ ኑሮ፤
እያለ የሚደሰኩር በዜና
በጥራቃው የአገራችን ፋና።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom
አጀል

ክፍል ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

3፥145 "ለማንኛይቱም ነፍስ በአላህ ውሳኔ ቢኾን እንጂ ልትሞት አይገባትም፥ ጊዜውም ተወስኖ ተጽፏል፡፡ وَمَا كَانَ لِنَفْسٍ أَن تَمُوتَ إِلَّا بِإِذْنِ اللَّهِ كِتَابًا مُّؤَجَّلًا

"አጀሉል ሙአለቅ" أَجَل المُعَلَّق ማለት "የተጠለጠለ ጊዜ" ማለት እንደሆነ፣ ይህም ጊዜ መልአኩ በማኅፀን የጻፈው ሊሻር ወይም ሊሻሻል እንደሚችል እና መልአኩ የጻፈውን ጊዜ ሰው በመልካም ሥራው የሚረዝም እና በመጥፎ ሥራ የሚያጥር እንደሆነ አይተን ነበር፥ በመቀጠል አሏህ ስለ "አጀሉል ሙሠማ" أَجَل المُّسَمًّى እንዲህ በማለት ይናገራል፦
6፥2 እርሱ ያ ከጭቃ የፈጠራችሁ ከዚያም ጊዜን የወሰነ ነው፥ እርሱም ዘንድ የተወሰነ ጊዜ አለ፡፡ هُوَ الَّذِي خَلَقَكُم مِّن طِينٍ ثُمَّ قَضَىٰ أَجَلًا ۖ وَأَجَلٌ مُّسَمًّى عِندَهُ

"ጊዜን የወሰነ ነው" ሲል አጀሉል ሙአለቅ ካመለከተ በኃላ "እርሱም ዘንድ የተወሰነ ጊዜ አለ" ሲል ደግሞ አጀሉል ሙሠማን ያሳያል፥ "የተወሰነ ጊዜ" ለሚለው የገባው ቃል "አጀሉ ሙሠማ" وَأَجَلٌ مُّسَمّ ሲሆን ይህም የተወሰነ ጊዜ የተከተበው እርሱ ዘንድ ባለው በለውሐል መሕፉዝ የተጻፈው ነው፦
13፥39 አላህ የሚሻውን ያብሳል፤ ያጸድቃልም፡፡ የመጽሐፉ መሠረትም እርሱ ዘንድ ነው፡፡ يَمْحُو اللَّهُ مَا يَشَاءُ وَيُثْبِتُ ۖ وَعِندَهُ أُمُّ الْكِتَابِ

ስለ አጀሉል ሙአለቅ "አላህ የሚሻውን ያብሳል፤ ያጸድቃልም" በማለት ከነገረን በኃላ እርሱ ዘንድ ስላለው ስለ ለውሐል መሕፉዝ "ኡሙል ኪታብ" أُمِّ الْكِتَاب በማለት ነገረን፥ ነገር ሁሉ በኡሙል ኪታብ የተጻፈ ነው፦
78፥29 ነገር ሁሉ የተጻፈ ሲኾን አጠቃለልነው፡፡ وَكُلَّ شَيْءٍ أَحْصَيْنَاهُ كِتَابًا
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 79
አቢ ሁረይራህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "አሏህ ፍጥረትን በወሰነ ጊዜ ከዐርሽ በላይ እርሱ ዘንድ ጻፈ"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ "‏ لَمَّا قَضَى اللَّهُ الْخَلْقَ كَتَبَ عِنْدَهُ فَوْقَ عَرْشِهِ

እዚህ ሐዲስ ላይ "ወሰነ" ለሚለው የገባው ቃል "ቀዶ" قَضَى ሲሆን ይህ ቀዷ "ቀዷ ሙብረም" قَضَىٰ مُبْرَم ነው፥ "ሙብረም" مُبْرَم ማለት "የተቆረጠረ" ማለት ነው። አጀሉል ሙአለቅ መንስኤ ሲሆን የመጨረሻው ሞት ሲመጣ ደግሞ ውጤት ነው፥ ይህ ውጤት አጀሉል ሙሠማ በጥብቁ ሰሌዳ ከፍጥረት በፊት ተጽፏል፦
3፥145 "ለማንኛይቱም ነፍስ በአላህ ውሳኔ ቢኾን እንጂ ልትሞት አይገባትም፥ ጊዜውም ተወስኖ ተጽፏል፡፡ وَمَا كَانَ لِنَفْسٍ أَن تَمُوتَ إِلَّا بِإِذْنِ اللَّهِ كِتَابًا مُّؤَجَّلًا
35፥11 ዕድሜው ከሚረዘምም አንድም አይረዘምም ከዕድሜውም አይጎደልም በመጽሐፉ ውስጥ ያለ ቢኾን እንጂ፡፡ ይህ በአላህ ላይ ገር ነው፡፡ وَمَا يُعَمَّرُ مِن مُّعَمَّرٍ وَلَا يُنقَصُ مِنْ عُمُرِهِ إِلَّا فِي كِتَابٍ ۚ إِنَّ ذَٰلِكَ عَلَى اللَّهِ يَسِيرٌ

ሞት ከመጣ በኃላ አጀሉል ሙሠማን ማርዘምም ማሳጠር የማይቻል ሲሆን ይህ ዕውቀት አሏህ ዘንድ በመጽሐፉ ውስጥ ያለውን ነው፥ ይህ አጀል ሲመጣ አንዲትን ሰዓት አይረዝምም አያጥርም፦
7፥34 ለሕዝብም ሁሉ የተወሰነ ጊዜ አላቸው፡፡ ጊዜያቸውም በመጣ ወቅት አንዲትን ሰዓት አይቆዩም አይቀደሙምም፡፡ وَلِكُلِّ أُمَّةٍ أَجَلٌ ۖ فَإِذَا جَاءَ أَجَلُهُمْ لَا يَسْتَأْخِرُونَ سَاعَةً ۖ وَلَا يَسْتَقْدِمُونَ
63፥11 ማንኛይቱም ነፍስ የሞት ጊዜዋ በመጣበት ጊዜ አላህ በፍጹም አያቆያትም፡፡ وَلَن يُؤَخِّرَ اللَّهُ نَفْسًا إِذَا جَاءَ أَجَلُهَا
2፥180 አንዳችሁን ሞት በመጣበት ጊዜ ሀብትን ቢተው ለወላጆችና ለቅርብ ዘመዶች በበጎ መናዘዝ በእናንተ ላይ ተጻፈ፡፡ كُتِبَ عَلَيْكُمْ إِذَا حَضَرَ أَحَدَكُمُ الْمَوْتُ إِن تَرَكَ خَيْرًا الْوَصِيَّةُ لِلْوَالِدَيْنِ وَالْأَقْرَبِينَ بِالْمَعْرُوفِ

አምላካችን አሏህ መጨረሻችንን በላ ኢላሀ ኢለል ሏህ ያሳምርልን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የተጻፈው ሞት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

3፥145 "በአላህ ፈቃድ ቢኾን እንጅ ለማንኛይቱም ነፍስ ልትሞት አይገባትም፥ ጊዜውም ተወስኖ ተጽፏል፡፡ وَمَا كَانَ لِنَفْسٍ أَن تَمُوتَ إِلَّا بِإِذْنِ اللَّهِ كِتَابًا مُّؤَجَّلًا

በባይብል ፈጣሪ ነገርን ሁሉ በ-"ጊዜ" ውብ አድርጎ ሠርቶታል፥ ከሰማይ በታች ለሆነ ነገር ሁሉ "ጊዜ" አለው። ለመወለድ "ጊዜ" እንዳለው ሁሉ ለመሞትም "ጊዜ" አለው፦
መክብብ 3፥11 ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው።
መክብብ 3፥1 ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው።
መክብብ 3፥2 ለመወለድ ጊዜ አለው፥ ለመሞትም ጊዜ አለው።

የሰውን ሩሕ(መንፈስ) በማውጣት ሰውን የሚያሞት፣ ወደ መቃብር የሚያወርድ እና ከመቃብር የሚያወጣ እራሱ ፈጣሪ ነው፦
1ኛ ሳሙኤል 2፥6 ያህዌህ ያሞታል ያድናልም፤ ወደ መቃብር ያወርዳል ያወጣል። יְהוָ֖ה מֵמִ֣ית וּמְחַיֶּ֑ה מֹורִ֥יד שְׁאֹ֖ול וַיָּֽעַל׃
ዘዳግም 32፥39 አሁንም እኔ ብቻዬን እኔ እንደ ሆንሁ፥ ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ እዩ፤ እኔ አሞታለው፥ አድንማለሁ። רְא֣וּ ׀ עַתָּ֗ה כִּ֣י אֲנִ֤י אֲנִי֙ ה֔וּא וְאֵ֥ין אֱלֹהִ֖ים עִמָּדִ֑י אֲנִ֧י אָמִ֣ית וַאֲחַיֶּ֗ה מָחַ֙צְתִּי֙ וַאֲנִ֣י אֶרְפָּ֔א וְאֵ֥ין מִיָּדִ֖י מַצִּֽיל׃
መዝሙር 104፥29 መንፈሳቸውን ታወጣለህ ይሞታሉም፥ ወደ አፈራቸውም ይመለሳሉ። תֹּסֵ֣ף ר֭וּחָם יִגְוָע֑וּן וְֽאֶל־עֲפָרָ֥ם יְשׁוּבֽוּן׃

በጊዜ የሚያሞት እና ሕያው የሚያደርግ ፈጣሪ እንደሆነ ካየን ዘንዳ ሰው ከፍጥረት በፊት የተወሰኑለት የሕይወት ዕድሜ በመጽሐፍ ተጽፏል፦
መዝሙር 139፥16 ለእኔ የተወሰኑልኝ ዘመናት ገና አንዳቸውም ወደ መኖር ሳይመጡ በመጽሐፍህ ተመዘገቡ። (አዲሱ መደበኛ ትርጉም) גלמי ראו עיניך ועל ספרך כלם יכתבו ימים יצרו ולא אחד בהם׃

እዚህ አንቀጽ ላይ የአዲሱ መደበኛ ትርጉም ላይ "መጽሐፍ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል በዕብራይስጡ "ሰፈር" סֵפֶר ሲሆን ይህም መጽሐፍ ሰው ወደ መኖር ከመምጣቱ በፊት ተወስኖ የተጻፈበት መጽሐፍ ነው፥ ይህንን የአዲሱ መደበኛ ትርጉም የግርጌ ማስታወሻ፦ "የሰው የሕይወት ዘመን በእግዚአብሔር የተወሰነ ነው፥ "በመጽሐፍህ" የእግዚአብሔር ውሳኔዎች ሁሉ የተጻፉበት የሰማይ መዝገብ ነው" በማለት ያትታል። የ 1954 እትም ደግሞ የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ ሳይፈጠሩ በመጽሐፍ እንደተጻፉ ይናገራል፦
መዝሙር 139፥16 የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ
አንድ ስንኳ ሳይኖር በመጽሐፍህ ተጻፉ። καὶ ἐπὶ τὸ βιβλίον σου πάντες γραφήσονται· ἡμέρας πλασθήσονται καὶ οὐθεὶς ἐν αὐτοῖς.

እዚህ አንቀጽ ላይ በግሪክ ሰፕቱአጀንት ላይ "መጽሐፍ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ቢብሊዮን" βιβλίον ነው፥ "አንድ ስንኳ ሳይኖር" ማለት "ምንም ነገር ሳይኖር" ማለት ሲሆን ምንም ነገር ሳይፈጠር የሰዎች ዕድሜ በአምላክ መጽሐፍ ተጽፏል። ይህንን ኤጲፋንዮስ በቅዳሴ ላይ፦ "ሁሉ በመጽሐፉ የተጻፈ ነው" በማለት ይናገራል፦
የኤጲፋንዮስ ቅዳሴ 14፥15 "ከእርሱ የሚሰወር የለም፣ ሁሉ በእርሱ ዘንድ የተገለጠ ነው፣ በዓይኖቹ ፊት ሁሉ የተዘረጋ ነው፣ ሁሉ በመጽሐፉ የተጻፈ ነው"።

ኢየሱስ ሲያስተምር፦ "ወደ ላከኝም እሄዳለሁ" በማለት ስለማረጉ ይናገራል፦
ዮሐንስ 7፥33 ኢየሱስም፦ ገና ጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር እቆያለሁ ወደ ላከኝም እሄዳለሁ።
ዮሐንስ 16፥5 አሁን ግን ወደ ላከኝ እሄዳለሁ ከእናንተም፦ ወዴት ትሄዳለህ? ብሎ የሚጠይቀኝ የለም።

ኢየሱስ ከማረጉ በፊት ስለማረጉ አስቀድሞ ተወስኖ ተጽፎለት ነበር፦
ሉቃስ 22፥22 የሰው ልጅስ እንደ ተወሰነው ይሄዳል።
ማቴዎስ 26፥24 የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሄዳል።

"መወሰን" እና "መጻፍ" ተለዋዋጭ ሆኖ መምጣቱ በራሱ ከፍጥረት አስቀድሞ ተወስኖ የሚጻፍበት መጽሐፍ እንዳለ አመላካች ነው። የሰው ዕድሜ ሁሉ ፍጥረት ሳይኖር በመጽሐፍ ከተጻፈ "ዕድሜህ እንዲረዝም አባትህንና እናትህን አክብር" ወይም "ዕድሜአችሁ እንዲረዝም አምላካችሁ ባዘዛችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ" የሚለው ቃል ትርጉሙ ግልጽ አይደለም፦
ዘጸአት 20፥12 አባትህንና እናትህን አክብር፤ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም።
ዘዳግም 5፥33 በሕይወት እንድትኖሩ፥ መልካምም እንዲሆንላችሁ፥ በምትወርሱአትም ምድር ዕድሜአችሁ እንዲረዝም ያህዌህ አምላካችሁ ባዘዛችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ።

ወይ እንደ ኢሥላም አስተምህሮት አጀሉል ሙአለቅ እና አጀሉል ሙሠማ የሚባል ትምህርት ስለሌላችሁ የተጻፈው ዕድሜ እንዴት እንደሚረዝም ግልጽ ትምህርት የላችሁም። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
1ኛ ዙር የሙቃረናህ ደርሥ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ!

"ሙቃረናህ" مُقَارَنَة ማለት "የሃይማኖት ንጽጽር"Comparative Religion" ማለት ሲሆን በእሥልምና እና በክርስትና መካከል ያለው የሥነ-መለኮት አንድነት እና ልዩነት እየተነጻጸረ የሚቀርብበት ጥናት ነው፥ ተማሪዎች በድምጽ እና በጽሑፍ የታገዘውን ይህ ጥናት ለስድስት ወር ያክል በሁለት ተርም በማጠናቀቃቸው በመካቴ እሥልምና ወይም በዐቅብተ እሥልምና ውስጥ ዐቃቤ እሥልምና ወይም ዐቃቢት እሥልምና"islamic apologist" ሆነው ዛሬ 54 ተማሪዎች ተመርቀዋል።
በድጋሚ እንኳን ደስ ያላችሁ!

እነዚህ ተማሪዎች በመሬት ሆነ በኦንላይን አብረው ከእኛ ጋር ለመሥራት እና የኢሥላምን ብርሃን በኩፍር ጨለማ ላሉት ለማብራት ቃል ገብተዋል።
ለኢሥላም ዘብ እና አበጋዝ የሆኑ ዐቃቢያነ ኢሥላም እንዲመረቁ ቀን ከሌሊት ደፋ ቀና ያላችሁ የደርሡ ቦርድ እና አድሚናት አምላካችን አሏህ መልካም ሥራችሁን ሁሉ በኢኽላስ ይቀበላችሁ! አሚን።
يَا مُقَلِّبَ الْقُلُوبِ ثَبِّتْ قَلْبِي عَلَى دِينِكَ
አሚር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

9፥71 ምእመናን እና ምእምናት ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ በደግ ነገር ያዛሉ፤ ከክፉም ይከለክላሉ፡፡ وَالْمُؤْمِنُونَ وَالْمُؤْمِنَاتُ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَاءُ بَعْضٍ ۚ يَأْمُرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَوْنَ عَنِ الْمُنكَرِ

"አምር" أَمْر የሚለው ቃል "አመረ" أَمَرَ ማለትም "አዘዘ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ትእዛዝ" ማለት ነው፥ በመልካም የሚያዙ አዛዥ "አሚር" أَمِير ሲባሉ የሚታዘዙ ታዛዥ ደግሞ "መእሙር" مَأْمُور ይባላሉ፦
3፥104 ከእናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ በመልካም ሥራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ፡፡ እነዚያም እነርሱ የሚድኑ ናቸው፡፡ وَلْتَكُن مِّنكُمْ أُمَّةٌ يَدْعُونَ إِلَى الْخَيْرِ وَيَأْمُرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَوْنَ عَنِ الْمُنكَرِ ۚ وَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ
9፥71 ምእመናን እና ምእምናት ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ በደግ ነገር ያዛሉ፤ ከክፉም ይከለክላሉ፡፡ وَالْمُؤْمِنُونَ وَالْمُؤْمِنَاتُ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَاءُ بَعْضٍ ۚ يَأْمُرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَوْنَ عَنِ الْمُنكَرِ

በደግ ነገር በማዘዝ እና በክፉ ነገር በመከልከል የምታዝ ሴት አማኝ "አሚራህ" أَمِيرَة ትባላለች፥ አሏህ በከለከለው መጥፎ ነገር የሚከለክል እና ባዘዘው መልካም ነገር የሚያዝ አሚርን መታዘዝ ግዴታ ነው፦
4፥59 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገዙ! መልእክተኛውን እና ከእናንተ የትእዛዝ ባለቤቶችን ታዘዙ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَطِيعُوا اللَّهَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ وَأُولِي الْأَمْرِ مِنكُمْ ۖ

"ከ" የሚለው መስተዋድድ ያለበት "እናንተ" የሚለው ተውላጠ ስም የሚያመለክተው ምእመናንን ብቻ ሲሆን "ኡውሊል አምር" أُولِي الْأَمْر የተባሉት አሚራት ከምእመናን ብቻ መሆናቸውን ቁልጭ አርጎ ያሳያል። አሚራትን መታዘዝ በእርግጥ ነቢያችንን"ﷺ" መታዘዝ ነው፥ አሚራትን ማመጽ ነቢያችንን"ﷺ" ማመጽ ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 33, ሐዲስ 46
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "እኔን የሚታዘዝ በእርግጥ አሏህን ታዘዘ፥ እኔን የሚያምጽ በእርግጥ አሏህን አመጸ። አሚር የሚታዘዝ በእርግጥ እኔን ታዘዘ፥ አሚርን የሚያምጽ በእርግጥ እኔን አመጸ"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ مَنْ أَطَاعَنِي فَقَدْ أَطَاعَ اللَّهَ وَمَنْ يَعْصِنِي فَقَدْ عَصَى اللَّهَ وَمَنْ يُطِعِ الأَمِيرَ فَقَدْ أَطَاعَنِي وَمَنْ يَعْصِ الأَمِيرَ فَقَدْ عَصَانِي ‏"‏

አምላካችን አሏህ አሚራትን የምንታዘዝ ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የሰሞኑ ተግዳሮት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

110፥2 ሰዎችንም ጭፍሮች እየኾኑ በአላህ ሃይማኖት ውስጥ ሲገቡ ባየህ ጊዜ አስታውስ! وَرَأَيْتَ ٱلنَّاسَ يَدْخُلُونَ فِى دِينِ ٱللَّهِ أَفْوَاجًۭا

ሰሞኑን ሰዎች ወደ ዲኑል ኢሥላም በገፍ እየገቡ ይገኛሉ። አል-ኃምዱ ሊሏህ! ይህ የኢሥላም መጠነ ሰፊ የእድገት መርሐ ግብር በመላው ዓለም ላይ እየተናወጠ ነው፥ ኢሥላም እያንዳንዱን ቤት በማንኳኳት እየገባ ነው። "ሰዎችንም ጭፍሮች እየኾኑ በአላህ ሃይማኖት ውስጥ ሲገቡ ባየህ ጊዜ አስታውስ" የሚለው ትንቢት የሚያጅብ ነው፦
110፥2 ሰዎችንም ጭፍሮች እየኾኑ በአላህ ሃይማኖት ውስጥ ሲገቡ ባየህ ጊዜ አስታውስ! وَرَأَيْتَ ٱلنَّاسَ يَدْخُلُونَ فِى دِينِ ٱللَّهِ أَفْوَاجًۭا

የኢሥላም መስፋፋት"expansion" ማሻሏህ ይሁን የሚያስብል ሲሆን የማጠናከር"consolidation" ሥራው ላይ ግን ችላ ብለናል፥ ወደ ዲኑ የሚገቡትን ሰዎች በትምህርት፣ በአሳብ፣ በጉልበት፣ በንዋይ መደገፍ የሁላችንም አላፍትና ነው። የሠለሙትን ልጆች መከታተል"follow-up" ትልቅ ተግዳሮት ነው። በዚህ ሥራ ላይ ተፍ ተፍ የምትሉ አሏህ ሥራችሁን በኢኽላስ ይቀበላችሁ! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሳላመቻምች ከአሏህ እንደወረደበት
እንደዛው እንዳለ እንደተቀራበት
ይህ ነው መንሀጄ እኔ የማምንበት

ሌላው ለስሜት ሲደምር ሲቀንስ
ባይብሉን በረዘው በስሜት ፈረስ

ለስሜቱ እንዲመች ሲሰርዝ ሲደልዝ
የነቢያት ትምህርት አስሉን ሲበልዝ

የቁርኣኑ ጠባቂ ግን አንድ ነው
እርሱም የዓለማቱ ጌታ ነው።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom
ሂዳያህ እና ዶላላህ

ክፍል አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥26 በእርሱ ብዙዎችን ያጠማል፥ በእርሱም ብዙዎችን ያቀናል፡፡ በእርሱም አመጸኞችን እንጅ ሌላን አያጠምም፡፡ يُضِلُّ بِهِ كَثِيرًا وَيَهْدِي بِهِ كَثِيرًا ۚ وَمَا يُضِلُّ بِهِ إِلَّا الْفَاسِقِينَ

አንድ ሰው ቁርኣንን ከሰማ ጊዜ ጀምሮ ሑጃህ ይቆምበታል፥ "ሑጃህ" حُجَّة ማለት "አስረጅ" ማለት ነው። ቁርኣን የተሟላ የአሏህ ሑጃህ ነው፦
6፥149 «የተሟላው አስረጅ የአላህ ነው፥ በሻም ኖሮ ሁላችሁንም ባቀናችሁ ነበር» በላቸው”፡፡ قُلْ فَلِلَّهِ الْحُجَّةُ الْبَالِغَةُ ۖ فَلَوْ شَاءَ لَهَدَاكُمْ أَجْمَعِينَ

አሏህ ሰውን አስገድዶ ለሁሉም ሂዳያህ መስጠት ቢፈልግ ችሎታው አለው፥ ቅሉ ግን የሰውን ነጻ ፈቃድ የሚጻረር ስለሆነ አሏህ ቁርኣንን ሑጃህ አርጎ አውርዷል። ቁርኣን ወደዚያች እርሷ ቀጥተኛ ወደ ኾነችው መንገድ ይመራል፥ ቁርኣን ካመንክበት ሂዳያህ የምትወፈቅበት ሑጃህ ይሆንልካል ወይም ከካድከው ደላላህ የምታገኝበት ሑጃህ ይሆንብካል፦
17፥9 ይህ ቁርኣን ወደዚያች እርሷ ቀጥተኛ ወደ ኾነችው መንገድ ይመራል፡፡ إِنَّ هَـٰذَا الْقُرْآنَ يَهْدِي لِلَّتِي هِيَ أَقْوَمُ وَيُبَشِّرُ الْمُؤْمِنِينَ
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 2, ሐዲስ 1
አቡ ማሊክ አል-አሽዐሪይ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ቁርኣን አስረጅ ይሆልካል ወይ አስረጅ ይሆንብካል”። عَنْ أَبِي مَالِكٍ الأَشْعَرِيِّ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ” الْقُرْآنُ حُجَّةٌ لَكَ أَوْ عَلَيْكَ “

"ሂዳያህ" هِدَايَة የሚለው ቃል "ሀዳ" هَدَى ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ምሪት"guidance" ማለት ነው፥ "ሃዲያህ" هَدِيَّة የሚለው ቃል እራሱ "ስጦታ" ማለት ሲሆን ሂዳያህ ከአሏህ የሚሰጥ ተውፊቅ ነው። "ዶላላህ" ضَلَّة የሚለው ቃል "ዶለ" ضَلَّ ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ጥመት"misguidance" ማለት ነው፥ ዶላላህ ከአሏህ የሆነ ቅጣት ሲሆን ኪሳራ ነው። አምላካችን አሏህ በቁርኣን ብዙዎችን ያጠማል፥ በቁርኣን ብዙዎችን ያቀናል። የሚያቀናው የቁርኣንን መልእክት ተቀብለው የሚታዘዙትን ሲሆን የሚያጠመው ደግሞ የቁርኣንን መልእክት የሚያስተባብሉትን አመጸኞች ነው፦
39፥23 ይህ የአላህ መምሪያ ነው፡፡ በእርሱ የሚሻውን ሰው ይመራበታል፡፡ አላህም የሚያጠመው ሰው ለእርሱ ምንም አቅኚ የለውም፡፡ ذَٰلِكَ هُدَى اللَّهِ يَهْدِي بِهِ مَن يَشَاءُ ۚ وَمَن يُضْلِلِ اللَّهُ فَمَا لَهُ مِنْ هَادٍ
2፥26 በእርሱ ብዙዎችን ያጠማል፥ በእርሱም ብዙዎችን ያቀናል፡፡ በእርሱም አመጸኞችን እንጅ ሌላን አያጠምም፡፡ يُضِلُّ بِهِ كَثِيرًا وَيَهْدِي بِهِ كَثِيرًا ۚ وَمَا يُضِلُّ بِهِ إِلَّا الْفَاسِقِينَ
63፥6 አላህ አመጸኞችን ሕዝቦች አይመራምና፡፡ إِنَّ اللَّهَ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الْفَاسِقِينَ

"ማጥመም" ማለት "አለማቅናት" ማለት ከሆነ ቁርኣን ለሑጃህ ሲነበብ የተመራም ሰው የሚመራው ለራሱ ብቻ ነው፥ የጠመመም ሰው የሚጠመው ጉዳቱ በራሱ ላይ ነው፦
27፥92 ቁርኣንንም እንዳነብ ታዝዣለሁ፡፡ የተመራም ሰው የሚመራው ለራሱ ብቻ ነው፡፡ የጠመመ ሰውን «እኔ ከአስጠንቃቂዎች ነኝ እንጅ ሌላ አይደለሁም» በለው፡፡ وَأَنْ أَتْلُوَ الْقُرْآنَ ۖ فَمَنِ اهْتَدَىٰ فَإِنَّمَا يَهْتَدِي لِنَفْسِهِ ۖ وَمَن ضَلَّ فَقُلْ إِنَّمَا أَنَا مِنَ الْمُنذِرِينَ
10፥108 «እናንተ ሰዎች ሆይ! እውነቱ ከጌታችሁ በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ በእርሱ የተመራም ሰው የሚመራው ለራሱ ነው፡፡ የጠመመም ሰው የሚጠመው ጉዳቱ በራሱ ላይ ነው፡፡ እኔም በእናንተ ላይ ተጠባበቂ አይደለሁም» በላቸው፡፡ قُلْ يَا أَيُّهَا النَّاسُ قَدْ جَاءَكُمُ الْحَقُّ مِن رَّبِّكُمْ ۖ فَمَنِ اهْتَدَىٰ فَإِنَّمَا يَهْتَدِي لِنَفْسِهِ ۖ وَمَن ضَلَّ فَإِنَّمَا يَضِلُّ عَلَيْهَا ۖ وَمَا أَنَا عَلَيْكُم بِوَكِيلٍ

ከጌታችን የመጣው እውነት ቁርኣን ሲሆን ይህንን እውነት ያስተባበለ ሰው ይጠማል፥ የተቀበለ ሰው ይቀናል። ቁርኣን ተነቦለት አሻፈረኝ ካለ ነቢያች"ﷺ" በእርሱ ላይ ተጠባባቂ አይደሉም፥ እርሳቸው ከአስጠንቃቂ መልእክተኞች አንዱ እንጂ ሌላ አይደሉም። አምላካችን አሏህ መልእክተኛን እስከሚልክ ድረስ ማንንም አይቀጣም፦
17፥15 የተመራ ሰው የሚመራው ለራሱ ብቻ ነው፥ የጠመመም ሰው የሚሚጠመው ጉዳቱ በእርሷ ላይ ነው፡፡ ተሸካሚም ነፍስ የሌላይቱን ነፍስ ኃጢኣት አትሸከምም፡፡ መልእክተኛንም እስከምንልክ ድረስ የምንቀጣ አይደለንም፡፡ مَّنِ اهْتَدَىٰ فَإِنَّمَا يَهْتَدِي لِنَفْسِهِ ۖ وَمَن ضَلَّ فَإِنَّمَا يَضِلُّ عَلَيْهَا ۚ وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٌ وِزْرَ أُخْرَىٰ ۗ وَمَا كُنَّا مُعَذِّبِينَ حَتَّىٰ نَبْعَثَ رَسُولًا
"ዐድል" عَدْل ማለት "ፍትሕ" ማለት ሲሆን የቁርኣንን መልእክት ሰምቶ ያስተባለለውን አመጸኛ በዱንያህ አሏህ የሚቀጣው ቅጣት ማጥመም ሲሆን ፍትሕ ነው፥ "ፈድል" فَضْل ማለት "ችሮታ" ማለት ሲሆን የቁርኣንን መልእክት ሰምቶ ያመነው አማኝ በዱንያህ አሏህ የሚወፍቀው ስጦታ ፈድል ነው፦
22፥54 አላህም እነዚያን ያመኑትን ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ "መሪ" ነው፡፡ وَإِنَّ اللَّهَ لَهَادِ الَّذِينَ آمَنُوا إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ

አሏህ በስም መደብ "ሃዲ" هَادِ ማለትም "መሪ" ተብሏል እንጂ በስም መደብ "ሙዲል" مُضِلّ ማለትም "አጥማሚ" አልተባለም፥ አሏህ ማቅናቱ ባሕርይው ሲሆን ማጥመሙ ግን ቅጣቱ ነው። አሏህ እነዚያን ያመኑትን ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ይመራል፥ ፍላጎት ያለው ሰው አምኖ የጌታውን መንገድ ይይዛል። አሏህም ወደ እርሱ በንስሓ የሚመለሰውን ሰው ይመራል፦
76፥29 ይህቺ መገሠጫ ናት፡፡ የሻም ሰው ወደ ጌታው መንገድን ይይዛል፡፡ إِنَّ هَـٰذِهِ تَذْكِرَةٌ ۖ فَمَن شَاءَ اتَّخَذَ إِلَىٰ رَبِّهِ سَبِيلًا
13፥27 «አላህ የሚሻውን ያጠምማል፥ የተመለሰውንም ሰው ወደ እርሱ ይመራል» በላቸው፡፡ قُلْ إِنَّ اللَّهَ يُضِلُّ مَن يَشَاءُ وَيَهْدِي إِلَيْهِ مَنْ أَنَابَ

እውነትትን ካወቁ በኋላ ከእውነት መዞር ጥመት እንጂ ሌላ ምንም የለም፥ እውነት ከመጣ በኃላ የፈለገ ማመን የፈለገ መካድ ይችላል፦
10፥32 እርሱ እውነተኛ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ከእውነትም በኋላ ጥመት እንጂ ሌላ ምን አለ? ከእውነት እንዴት ትዞራላችሁ?። فَذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمُ الْحَقُّ ۖ فَمَاذَا بَعْدَ الْحَقِّ إِلَّا الضَّلَالُ ۖ فَأَنَّىٰ تُصْرَفُونَ
18፥29 «እውነቱም ከጌታችሁ ነው፡፡ የሻም ሰው ይመን፤ የሻም ሰው ይካድ» በላቸው፡፡ وَقُلِ الْحَقُّ مِن رَّبِّكُمْ ۖ فَمَن شَاءَ فَلْيُؤْمِن وَمَن شَاءَ فَلْيَكْفُرْ
4፥170 እናንተ ሰዎች ሆይ! መልክተኛው እውነትን ከጌታችሁ አመጣላችሁ፡፡ እመኑም ለእናንተ የተሻለ ይኾናል፡፡ ብትክዱም በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነውና፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ قَدْ جَاءَكُمُ الرَّسُولُ بِالْحَقِّ مِن رَّبِّكُمْ فَآمِنُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ وَإِن تَكْفُرُوا فَإِنَّ لِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ

ማመን ለአማኙ የተሻለ ነው፥ መካድ ግን እራሱ ከሃዲውን እንጂ አሏህን ምንም አይጎዳም። ከእምነታቸው፣ መልክተኛውም እውነት መኾኑን ከመሰከሩ እና የተብራሩ አንቀጾችም ከመጡላቸው በኋላ የካዱን ሕዝቦች አሏህ አያቀናም(ያጠማል)፦
3፥86 ከእምነታቸው፣ መልክተኛውም እውነት መኾኑን ከመሰከሩ እና የተብራሩ አንቀጾችም ከመጡላቸው በኋላ የካዱን ሕዝቦች አላህ እንዴት ያቀናል? አላህ በዳዮችንም ሕዝቦች አያቀናም፡፡ كَيْفَ يَهْدِي اللَّهُ قَوْمًا كَفَرُوا بَعْدَ إِيمَانِهِمْ وَشَهِدُوا أَنَّ الرَّسُولَ حَقٌّ وَجَاءَهُمُ الْبَيِّنَاتُ ۚ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الظَّالِمِينَ

እውነትን ዐውቀው እና የተብራሩ አንቀጾች ከመጡላቸው በኃላ ቢያስተባብሉ በደለኞች ናቸው፥ በደለኞች በግልጽ ጥመት ውስጥ ናቸው፦
31፥11 በእውነቱ በዳዮቹ በግልጽ ጥመት ውስጥ ናቸው፡፡ بَلِ الظَّالِمُونَ فِي ضَلَالٍ مُّبِينٍ

አሏህ በሕዝቦች ዘንድ ያለውን ጸጋ እና ኹኔታ እስከሚለውጡ ድረስ ማንንም አያጠምም፥ ከእውነት በተዘነበሉም ጊዜ ግን ልቦቻቸውን በማጥመም አዘነበላቸው፦
13፥11 አላህ በሕዝቦች ዘንድ ያለውን ጸጋ በራሳቸው ያለውን ኹኔታ እስከሚለውጡ ድረስ አይለውጥም፡፡ إِنَّ اللَّهَ لَا يُغَيِّرُ مَا بِقَوْمٍ حَتَّىٰ يُغَيِّرُوا مَا بِأَنفُسِهِمْ
61፥5 ከእውነት በተዘነበሉም ጊዜ አላህ ልቦቻቸውን አዘነበላቸው፡፡ አላህም አመጸኞችን ሕዝቦች አያቀናም፡፡ فَلَمَّا زَاغُوا أَزَاغَ اللَّهُ قُلُوبَهُمْ ۚ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الْفَاسِقِينَ

ኢንሻሏህ ስለ ሂዳያህ እና ዶላላህ በክፍል ሁለት እንቋጫለን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሂዳያህ እና ዶላላህ

ክፍል ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥175 እነዚያ ጥመትን በቅንነት ቅጣትንም በምሕረት የገዙ ናቸው፡፡ በእሳት ላይም ምን ታጋሽ አደረጋቸው! أُولَـٰئِكَ الَّذِينَ اشْتَرَوُا الضَّلَالَةَ بِالْهُدَىٰ وَالْعَذَابَ بِالْمَغْفِرَةِ ۚ فَمَا أَصْبَرَهُمْ عَلَى النَّارِ

አምላካችን አሏህ በቁርኣን ውስጥ ከምሳሌው ሁሉ ለሰዎች ገልጿል፥ እርሱ ትንሿን ትንኝን ኾነ ከበላይዋ ያለ ትልቅ ነገር ምሳሌ ለማድረግ አያፍርም፦
17፥89 በዚህም ቁርኣን ውስጥ ከምሳሌው ሁሉ ለሰዎች በእርግጥ መላለስን፡፡ አብዛኞቹም ሰዎች ክህደትን እንጂ ሌላን እምቢ አሉ፡፡ وَلَقَدْ صَرَّفْنَا لِلنَّاسِ فِي هَـٰذَا الْقُرْآنِ مِن كُلِّ مَثَلٍ فَأَبَىٰ أَكْثَرُ النَّاسِ إِلَّا كُفُورًا
2፥26 አላህ ማንኛውንም ነገር ትንኝን ኾነ ከበላይዋ የኾነንም ምሳሌ ለማድረግ አያፍርም፡፡ إِنَّ اللَّهَ لَا يَسْتَحْيِي أَن يَضْرِبَ مَثَلًا مَّا بَعُوضَةً فَمَا فَوْقَهَا

እነዚያ ያመኑት ቁርኣን ከጌታቸው የመጣ እውነት መኾኑን ያውቃሉ፥ እነዚያም የካዱትማ «አላህ በዚህ ምንን ምሳሌ ሽቷል» ይላሉ፡፡ በቁርኣን ብዙዎችን ያጠማል፥ በቁርኣን ብዙዎችን ያቀናል፡፡ በእርሱም አመፀኞችን እንጅ ሌላን አያጠምም፦
2፥26 እነዚያ ያመኑትማ እርሱ ከጌታቸው የመጣ እውነት መኾኑን ያውቃሉ፡፡ እነዚያም የካዱትማ «አላህ በዚህ ምንን ምሳሌ ሽቷል» ይላሉ፡፡ በእርሱ ብዙዎችን ያጠማል፥ በእርሱም ብዙዎችን ያቀናል፡፡ በእርሱም አመፀኞችን እንጅ ሌላን አያጠምም፡፡ فَأَمَّا الَّذِينَ آمَنُوا فَيَعْلَمُونَ أَنَّهُ الْحَقُّ مِن رَّبِّهِمْ ۖ وَأَمَّا الَّذِينَ كَفَرُوا فَيَقُولُونَ مَاذَا أَرَادَ اللَّهُ بِهَـٰذَا مَثَلًا ۘ يُضِلُّ بِهِ كَثِيرًا وَيَهْدِي بِهِ كَثِيرًا ۚ وَمَا يُضِلُّ بِهِ إِلَّا الْفَاسِقِينَ

ቀጣዩ አንቀጽ "አመጸኞች" የሚለውን ቃል ለማመልከት "እነዚያ" የሚል አመልካች ተውላጠ ስም በመጠቀም እነዚያ አመጸኞች የአሏህን ቃል ኪዳን ከአጠበቀባቸው በኋላ የሚያፈርሱ፣ እንዲቀጠል በእርሱ ያዘዘውን ነገር የሚቆርጡ እና በምድርም ላይ የሚያበላሹ እንደሆኑ ይናገራል፥ እነዚያ እነርሱ ከሳሪዎቹ ናቸው፦
2፥27"እነዚያ" የአላህን ቃል ኪዳን ከአጠበቀባቸው በኋላ የሚያፈርሱ፣ እንዲቀጠል በእርሱ ያዘዘውን ነገር የሚቆርጡ እና በምድርም ላይ የሚያበላሹ ናቸው። እነዚያ እነርሱ ከሳሪዎቹ ናቸው፡፡ الَّذِينَ يَنقُضُونَ عَهْدَ اللَّهِ مِن بَعْدِ مِيثَاقِهِ وَيَقْطَعُونَ مَا أَمَرَ اللَّهُ بِهِ أَن يُوصَلَ وَيُفْسِدُونَ فِي الْأَرْضِ ۚ أُولَـٰئِكَ هُمُ الْخَاسِرُونَ

አሏህ በቁርኣን ውስጥ ከገለጸው ምሳሌ የእነዚያም የካዱት ምሳሌ እንደዚያ ድምጽን እና ጥሪን በስተቀር ሌላን በማይሰማ እንስሳ ላይ እንደሚጮህ ብጤ ነው፦
2፥171 የእነዚያም የካዱት ምሳሌ እንደዚያ ድምጽን እና ጥሪን በስተቀር ሌላን በማይሰማ እንስሳ ላይ እንደሚጮህ ብጤ ነው፡፡ እነርሱም ደንቆሮዎች፣ ዲዳዎች፣ ዕውሮች ናቸው፤ ስለዚህ እነርሱ አያውቁም፡፡ وَمَثَلُ الَّذِينَ كَفَرُوا كَمَثَلِ الَّذِي يَنْعِقُ بِمَا لَا يَسْمَعُ إِلَّا دُعَاءً وَنِدَاءً ۚ صُمٌّ بُكْمٌ عُمْيٌ فَهُمْ لَا يَعْقِلُونَ

ከእነዚያ እውነትን እያወቁ ከካዱት በተቃራኒው እውነትን ለማወቅ በአሏህ መንገድ እየታገሉ የሚፍጨረጨሩትን አሏህ የልባቸውን እሾት ስለሚያውቅ ሂዳያህ ይወፍቃቸዋል፥ "የትኛው ሰው በልቡ ቅን ነው" የሚለውን አሏህ ዐዋቂ ነው፦
29፥69 እነዚያም በእኛ መንገድ የታገሉ መንገዳችንን በእርግጥ እንመራቸዋለን፡፡ وَالَّذِينَ جَاهَدُوا فِينَا لَنَهْدِيَنَّهُمْ سُبُلَنَا
28፥56 አንተ የወደድከውን ሰው ፈጽሞ አታቀናም፡፡ ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያቀናል፥ እርሱም ቅኖቹን ዐዋቂ ነው፡፡ إِنَّكَ لَا تَهْدِي مَنْ أَحْبَبْتَ وَلَـٰكِنَّ اللَّهَ يَهْدِي مَن يَشَاءُ ۚ وَهُوَ أَعْلَمُ بِالْمُهْتَدِينَ
68፥7 ጌታህ እርሱ ከመንገዱ የጠመመውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም ተመሪዎቹን ዐዋቂ ነው፡፡ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعْلَمُ بِمَن ضَلَّ عَن سَبِيلِهِ وَهُوَ أَعْلَمُ بِالْمُهْتَدِينَ

"ሙህተድ" مُهْتَد ማለት "ተመሪ" "ቅን" ማለት ነው። አሏህ ሙህተዲንን ዐዋቂ ነው። እኛ ግን ሂዳያህ ሰጪም ነሺም አይደለንም፥ ማን ሂዳያህ እንደሚገባው ያውቃል። አምላካችን አሏህ አሸናፊ እና ጥበበኛ ስለሆነ የሚሻውን በቁርኣን ያጠማል፥ የሚሻውን በቁርኣን ያቀናል፦
14፥4 አላህም የሚሻውን ያጠማል፥ የሚሻውንም ያቀናል፡፡ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡ فَيُضِلُّ اللَّهُ مَن يَشَاءُ وَيَهْدِي مَن يَشَاءُ ۚ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ

"አላህም የሚሻውን ያጠማል፥ የሚሻውንም ያቀናል" የሚለው ኃይለ-ቃል "ዓም" ሆኖ የመጣ ነው፥ "ዓም" عَامّ ማለት "ጥቅል"general" ማለት ነው። ለምሳሌ፦ "ለሚሻውም ሰው ይምራል፥ የሚሻውንም ሰው ይቀጣል" የሚለው ኃይለ-ቃል "ዓም" ሆኖ የመጣ ነው፦
2፥284 ለሚሻውም ሰው ይምራል፥ የሚሻውንም ሰው ይቀጣል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡ فَيَغْفِرُ لِمَن يَشَاءُ وَيُعَذِّبُ مَن يَشَاءُ ۗ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

ነገር ግን "ለሚሻውም ሰው ይምራል፥ የሚሻውንም ሰው ይቀጣል" የሚለው ዓም በሌሎች አናቅጽ "ኻስ" ሆኖ ይመጣል፥ "ኻስ" خَاصّ ማለት "ተናጥል"specifical" ማለት ነው። ምሕረት እና ቅጣት በማመን እና በመካድ እንደሆነ "ኻስ" ሆኖ መጥቷል፦
5፥9 እነዚያንም ያመኑትንና በጎ ሥራዎችን የሠሩትን አላህ (ገነትን) ተስፋ አደረገላቸው፡፡ ለእነርሱ ምሕረትና ታላቅ ምንዳ አላቸው፡፡ وَعَدَ اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ ۙ لَهُم مَّغْفِرَةٌ وَأَجْرٌ عَظِيمٌ
67፥6 ለእነዚያም በጌታቸው ለካዱት የገሀነም ቅጣት አልላቸው፡፡ መመለሻይቱም ከፋች! وَلِلَّذِينَ كَفَرُوا بِرَبِّهِمْ عَذَابُ جَهَنَّمَ ۖ وَبِئْسَ الْمَصِيرُ
4፥147 ብታመሰግኑ እና ብታምኑ አላህ እናንተን በመቅጣት ምን ያደርጋል? አላህም ወሮታን መላሽ ዐዋቂ ነው፡፡ مَّا يَفْعَلُ اللَّهُ بِعَذَابِكُمْ إِن شَكَرْتُمْ وَآمَنتُمْ ۚ وَكَانَ اللَّهُ شَاكِرًا عَلِيمًا
4፥48 አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም፡፡ ከዚህ ሌላ ያለውንም ኀጢአት ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ إِنَّ اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن يَشَاءُ ۚ
እንግዲያውስ አሏህ የሚሻውን በማመኑ እንደሚምር እና የሚሻውን በመካዱ የሚቀጣ ከሆነ በተመሳሳይም የሚሻውን በማመኑ ያቀናዋል፥ የሚሻውን በመካዱ ያጠመዋል። ምሪት እና ጥመት በማመን እና በመካድ እንደሆነ "ኻስ" ሆኖ መጥቷል፦
22፥54 አላህም እነዚያን ያመኑትን ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ "መሪ" ነው፡፡ وَإِنَّ اللَّهَ لَهَادِ الَّذِينَ آمَنُوا إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ
13፥27 «አላህ የሚሻውን ያጠምማል፥ የተመለሰውንም ሰው ወደ እርሱ ይመራል» በላቸው፡፡ قُلْ إِنَّ اللَّهَ يُضِلُّ مَن يَشَاءُ وَيَهْدِي إِلَيْهِ مَنْ أَنَابَ
3፥86 አላህ በዳዮችንም ሕዝቦች አያቀናም፡፡ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الظَّالِمِينَ
31፥11 በእውነቱ በዳዮቹ በግልጽ ጥመት ውስጥ ናቸው፡፡ بَلِ الظَّالِمُونَ فِي ضَلَالٍ مُّبِينٍ

ስለዚህ "የሚሻው" የሚለው ቃል በጥቅሉ ሠበብ እና መሥቡብ ሁሉ በአሏህ መሺኣህ ሥር መሆኑን አመላካች ነው፥ ጥመት እና ቅጣት ዐድል ሆነው መምጣታቸው እንዲሁ ምሪት እና ምሕረት ፈድል ሆነው መምጣታቸው በራሱ ከሑጃህ በኃላ ያሉ ወሮታ እና አጸፌታ፣ ምንዳ እና ትሩፋት፣ ስርጉት እና ትርሲት መሆናቸውን ቁልጭ እና ፍንትው አርጎ ያሳያል፦
2፥175 እነዚያ ጥመትን በቅንነት ቅጣትንም በምሕረት የገዙ ናቸው፡፡ በእሳት ላይም ምን ታጋሽ አደረጋቸው? أُولَـٰئِكَ الَّذِينَ اشْتَرَوُا الضَّلَالَةَ بِالْهُدَىٰ وَالْعَذَابَ بِالْمَغْفِرَةِ ۚ فَمَا أَصْبَرَهُمْ عَلَى النَّارِ

"እነዚያ" የሚለው አመልካች ተውላጠ ስም የሚያመለክተው እውነትን ያስተባበሉ ከሓድያን ሲሆን እነርሱም ጥመትን በቅንነት ቅጣትንም በምሕረት የገዙ ናቸው። አሏህ ፍትኸኛ፣ ጥበበኛ እና ዐዋቂ እንጂ እንደ ፍጡራን በዘፈቀደ የሚፈርድ አይደለም፥ ልብን የሚያውቅ፣ የሚቆጣጠር እና የሚመረምር አምላክ ፍርደ ገምድል በፍጹም አይደለም። አሏህ ቅንጣት ታክል ማንንም አይበድልም፥ ነገር ግን ሰው እራሱን የሚበድነው ማመን እና መታዘዝ ሲችል በመካድ እና በማመጽ ነው፦
18፥49 ጌታህም አንድንም አይበድልም፡፡ وَلَا يَظْلِمُ رَبُّكَ أَحَدًا
4፥40 አላህ የብናኝን ክብደት ያህል አይበድልም፡፡ إِنَّ اللَّهَ لَا يَظْلِمُ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ
10፥44 አላህ ሰዎችን ምንም አይበድልም፡፡ ግን ሰዎች እራሳቸውን ይበድላሉ፡፡ إِنَّ اللَّهَ لَا يَظْلِمُ النَّاسَ شَيْئًا وَلَـٰكِنَّ النَّاسَ أَنفُسَهُمْ يَظْلِمُونَ

አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይወፍቀን! ከደላላህ ቅጣት ይጠብቀን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የክርስትና ጦም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

28፥50 እሺ ባይሉህም የሚከተሉት ዝንባሌዎቻቸውን ብቻ መኾኑን ዕወቅ! ከአላህ የኾነ መመሪያ ሳይኖረው ዝንባሌውን ከተከተለ ሰው ይበልጥ የጠመመ አንድም የለም፡፡ فَإِن لَّمْ يَسْتَجِيبُوا لَكَ فَاعْلَمْ أَنَّمَا يَتَّبِعُونَ أَهْوَاءَهُمْ ۚ وَمَنْ أَضَلُّ مِمَّنِ اتَّبَعَ هَوَاهُ بِغَيْرِ هُدًى مِّنَ اللَّهِ

አምላካችን አሏህ ከሶላቱ መግሪብ ጀምሮ እስከ ሶላቱል ፈጅር ድረስ ማንኛውም ሐላል ምግብ እንድንበላ እና ሐላል መጠጥ እንድንጠጣ ፈቅዶልናል፦
2፥187 ከጎህ የኾነው ነጩ ክርም ከጥቁሩ ክር ለእናንተ እስከሚገልጽላችሁ ድረስ ብሉ፥ ጠጡም፡፡ ከዚያም ጦምን እስከ ሌሊቱ ድረስ ሙሉ፡፡ وَكُلُوا وَاشْرَبُوا حَتَّىٰ يَتَبَيَّنَ لَكُمُ الْخَيْطُ الْأَبْيَضُ مِنَ الْخَيْطِ الْأَسْوَدِ مِنَ الْفَجْرِ ۖ ثُمَّ أَتِمُّوا الصِّيَامَ إِلَى اللَّيْلِ ۚ

ከዚያ ከሶላቱል ፈጅር ስለ ሶላቱል መግሪብ ድረስ ከምንም ዓይነት ምግብ እንዳንበላ እና ከምንም ዓይነት መጠጥ እንዳንጠጣ አዞናል። "ጦም" የሚለው የግዕዙ ቃል "ጦመ" ማለትም "ተወ" "ታቀበ" "ታረመ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን ከምግብ እና ከመጠጥ "መተው" "መታቀብ" "መታረም" ማለት ነው፥ ጦም ማለት ከምግብ እና ከመጠጥ መተው፣ መታቀብ፣ መታረም እንጂ ከሥጋ እና ከሥጋ ተዋእፆ ከሆኑት እንቁላል፣ ወተት፣ አይብ እየተቆጠቡ ነገር ግን በእጅ አዙር የሥጋ፣ የእንቁላል፣ የወተት ምትክ የሆኑትን ባቄላ፣ አተር፣ በቆሎ፣ ገብስ የመሳሰሉት በሳይክል ተዙሮ የማያልቀውን ቡፌ መብላት አይደለም። ይህ ሠው ሠራሽ ጦም እንጂ ባይብል ላይ የለም፦
ዳንኤል 10፥3 ማለፊያ እንጀራም አልበላሁም፥ ሥጋና ጠጅም በአፌ አልገባም፥ ሦስቱም ሳምንት እስኪፈጸም ድረስ ዘይት አልተቀባሁም።

ዳንኤል ጦም ሲጦም እንጀራ እና ሥጋ ባለመብላት እና ጠጅ ባለመጠጣት ከሁሉ ነገር ይታቀብ ነበር እንጂ እንደ ኦርቶዶክስ ጦም ከሥጋ ተቆጥቦ እንጀራ አይበላም ነበር፥ ኦርቶዶክሳውያን በጦም ወቅት ቅዳሴ እንዳለቀ በተለይ ዲያቆናት፣ ቀሳውስት፣ ደብተራዎች ደጀ ሰላም ውስጥ ገብተው ሥጋ የሚተኩ ምግቦች ከርሳቸው እስኪወጠር ሲያግበሰብሱ እና ጠላ፣ ጠጅ፣ ፊልተር እንዲሁ ሀብታም ለተዝካር ያመጣውን ውስኪ እና አረቄ ሲጋቱ እና ሲሰክሩ ማየት የአደባባይ ጉድ ነው። ከኦርቶዶክስ ጦም በተቃራኒው ሙሴ ሲጦም እንጀራ ባለመብላት እና ውኃም ባለመጠጣት ነበር፥ ኢየሱስ ሲጦም ምንም አልበላም ነበር፦
ዘጸአት 34፥28 በዚያም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከከያህዌህ ጋር ነበረ፤ እንጀራም አልበላም፥ ውኃም አልጠጣም።
ማቴዎስ 4፥2 አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ።
ሉቃስ 4፥2 አርባ ቀን ከዲያብሎስ ተፈተነ። በነዚያም ቀኖች ምንም አልበላም፥ ከተጨረሱም በኋላ ተራበ።

ስለዚህ ከሥጋ እና ከሥጋ ተዋእፆ ከሆኑት እንቁላል፣ ወተት፣ አይብ እየተቆጠቡ ነገር ግን በእጅ አዙር የሥጋ፣ የእንቁላል፣ የወተት ምትክ የሆኑትን ባቄላ፣ አተር፣ በቆሎ፣ ገብስ መብላት ሰው ሠራሽ ጦም ነው፥ ይህንን ሰው ሠራሽ ጦም ይዛችሁ የኢሥላምን ጦም ለመተቸት ሞራሉ ሆነ ዐቅሙ የላችሁም።
"ሁዳድ" ማለት "ሰፊ" ማለት ሲሆን "ሁዳዴ"lent" እራሱ 40 ቀናት የነበረ ሲሆን ቅዳሜ እና እሑድ ተተስቶ 15 ቀናት በ 40 ቀናት ሲጨመር 8 ሳምንት ወይም 55 ቀናት በማድረግ የሚጦሙት "ሶውሙል ከቢር" صَوْم ٱلْكَبِير ማለትም "ዐብይ ጦም" ይባላል። ይህንን ሁዳዴ "ጡሙ" ብሎ የደነገገው በ 339 ድኅረ-ልደት አትናቴዎስ ሲሆን በውጪው ዓለም ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክ እና ጥቂት የፕሮቴስታንት አንጃዎች ይጦሙታል፥ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ያሉት አጥማዋት ማለትም ፅጌ፣ ገና፣ ነነዌ፣ ሁዳዴ፣ ሰኔ፣ ፍልሰታ የቤተክርስቲያን መሪዎች ቀስ በቀስ እና በጊዜ ሂደት የደነገጓቸው ሰው ሠራሽ ሕግ እንጂ የመለኮት ትእዛዞች አይደሉም።
የነነዌ ጦምም ለነነዌ ሰዎች ለሥስት ቀን የተሰጠ እንጂ አማኞች እንዲጦሙ የታዘዘበት አንቀጽ በባይብል ሽታውን አናገኝም።
አምላካችን አሏህ ካፈጠርን በኃላ ከሐላል ጥንዳችን ጋር ተራክቦ ማድረግን ሐላል አድርጓልናል፦
2፥187 በጾም ሌሊት ወደ ሴቶቻችሁ መድረስ ለእናንተ ተፈቀደላችሁ፡፡ أُحِلَّ لَكُمْ لَيْلَةَ الصِّيَامِ الرَّفَثُ إِلَىٰ نِسَائِكُمْ

በባይብል ግን አንድ ሰው ከትዳር አጋሩ ጋር በጦም ጊዜ ተራክቦ ማድረግ "ክልክል ነው" የሚል ፍንጭ ይቅርና ሽታው የለም።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ስለ ጦም ያለው መመሪያ ፍትሐ ነገሥት ላይ ይገኛል፥ ፍትሐ ነገሥት በ1240 ድኅረ-ልደት በግብጽ አገር ውስጥ አቡል ፋዳዒል ኢብኑል አሣል ጠጅ እየጠጣ በዐረቢኛ የጻፈው ድርሰት ነው። ይህ መጽሐፍ ወደ ግዕዝ የተተረጎመው በ 1450 ድኅረ-ልደት በአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ሲሆን በቤተ ክህነት እና በቤተ መንግሥት ሕጉ መዋል የጀመረው በ 1455 ድኅረ-ልደት በበአጼ ሠርጸ ድንግል ዘመን ነው። ይህንን መመሪያ የጻፉት በግልጠተ መለኮት ሳይሆን ዝንባሌአቸውን በመከተል ነው፦
28፥50 እሺ ባይሉህም የሚከተሉት ዝንባሌዎቻቸውን ብቻ መኾኑን ዕወቅ! ከአላህ የኾነ መመሪያ ሳይኖረው ዝንባሌውን ከተከተለ ሰው ይበልጥ የጠመመ አንድም የለም፡፡ فَإِن لَّمْ يَسْتَجِيبُوا لَكَ فَاعْلَمْ أَنَّمَا يَتَّبِعُونَ أَهْوَاءَهُمْ ۚ وَمَنْ أَضَلُّ مِمَّنِ اتَّبَعَ هَوَاهُ بِغَيْرِ هُدًى مِّنَ اللَّهِ

አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ማኅተቤን አልበጥስም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥256 በሃይማኖት ማስገደድ የለም፡፡ ቅኑ መንገድ ከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ፡፡ لَا إِكْرَاهَ فِي الدِّينِ ۖ قَد تَّبَيَّنَ الرُّشْدُ مِنَ الْغَيِّ

በአንድ ወቅት ስለ ኢትዮጵያ መፍረስ ማንም በአእምሮ ውልብ ሳይልበት ዶክተር ዐቢይ፦ "ኢትዮጵያ አትፈርስም" እያሉ ሕዝቡን ሽብር ይነዙት ነበር፥ ጅብ አህያ ፊት ቆሞ፦ "አልበላሽም" ሲላት እርሷ፦ "አልበላሽም ምን አመጣው? አለች አሉ። ብዙ ጊዜ አዲስ አጀንዳ የሚቀይሱ ሰዎች ሰዎች ያላሰቡትን እንዳሰቡ አርጎ በሰው ኅሊና ላይ መሳል የሥነ ልቦና ጨዋታቸው ነው፥ መምህር ምሕረተ አብ ከአራት ዓመት ወዲህ በየጉባኤው፦ "ማኅተቤን አልበጥስም" የሚል ስብከት እና መዝሙር እንደ በቀቀን መደጋገሙ ሙሥሊሙ ማኅተብ በጣሽ ክርስቲያኑ ማኅተቡን ተበጣሽ አርድጎ ለመሳል የሚዳዳው ነው። በተለይ በማንቂያ ደውል "ማኅተቤን አልበጥስም" የሚለው የዘወትር መፎክሩ በብዙኃን ዘንድ፦ "ይህ ሰው መቼ ይሆን ባይብልን የሚሰብከው? የሚል ጥያቄ ማስነሳቱ አልቀረም፥ በእርግጥ መምህሩ የኢሥላም ብርሃን እያንዳንዱ ቤት ዘው እያለ እየገባ መሆኑን መመከት እንዳቃተው አካሄዱ ያሳብቅበታል። እሥልምና ሰው አስገድዶ ከማሥለም ይልቅ "የፈቀደ ሰው ይመን፤ የፈቀደ ሰው ይካድ" በማለት ሰው ነጻ ምርጫ እንዳለው ያመላክታል፦
18፥29 «እውነቱም ከጌታችሁ ነው፡፡ የፈቀደ ሰው ይመን፤ የፈቀደ ሰው ይካድ» በላቸው፡፡ وَقُلِ الْحَقُّ مِن رَّبِّكُمْ ۖ فَمَن شَاءَ فَلْيُؤْمِن وَمَن شَاءَ فَلْيَكْفُر

አምላካችን አሏህ ሰዎች ሁሉ አማኝ እንዲሆኑ ቢፈልግ ኖሮ በማስገደድ አማኝ ያረጋቸው ነበር፥ ቅሉ ግን ለሰው ነጻ ፈቃድ ስለተሰጠው ሰዎችን አማኞች እንዲኾኑ ማስገደድ ሐራም ነው። እውነቱ ከጌታችን ስለመጣ ቅኑ መንገድ ከጠማማው በእርግጥ ተገለጧልና በሃይማኖት ማስገደድ የለም፦
10፥99 ጌታህም በሻ ኖሮ በምድር ያሉት ሰዎች ሁሉም የተሰበሰቡ ሆነው ባመኑ ነበር፡፡ ታዲያ አንተ ሰዎችን አማኞች እንዲኾኑ ታስገድዳለህን?። وَلَوْ شَآءَ رَبُّكَ لَـَٔامَنَ مَن فِى ٱلْأَرْضِ كُلُّهُمْ جَمِيعًا ۚ أَفَأَنتَ تُكْرِهُ ٱلنَّاسَ حَتَّىٰ يَكُونُوا۟ مُؤْمِنِينَ
2፥256 በሃይማኖት ማስገደድ የለም፡፡ ቅኑ መንገድ ከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ፡፡ لَا إِكْرَاهَ فِي الدِّينِ ۖ قَد تَّبَيَّنَ الرُّشْدُ مِنَ الْغَيِّ ۚ

ከአርካኑል ዒባዳህ አንዱ መሐባህ ሲሆን አሏህን ማምለክ ያለብን አፍቅረነው እንጂ ተገደን በፍጹም ስላልሆነ እኛ በእነርሱ ላይ አስገዳጅ አይደለንም፦
50፥45 “እኛ የሚሉትን ሁሉ ዐዋቂ ነን፡፡ አንተም በእነርሱ ላይ አስገዳጅ አይደለህም፡፡ ስለዚህ ዛቻየን የሚፈራን ሰው በቁርኣን አስታውስ!”፡፡ نَّحْنُ أَعْلَمُ بِمَا يَقُولُونَ ۖ وَمَا أَنتَ عَلَيْهِم بِجَبَّارٍ ۖ فَذَكِّرْ بِالْقُرْآنِ مَن يَخَافُ وَعِيدِ

ሲጀመር ተገዶ የሠለመ እራሱ እሥልምናው መቼ መቅቡል ይሆንና? ጎትጉተን እና ጎትተን ብናመጣው ልቡ ላይ ኢማን ከሌለውስ ምን ይፈይድልናል? ይህንን ልናረግላቸው ሆነ ልናረግባቸው አምላካችን አሏህ አላዘዘንም። የሚያጅበው ነገር አንዳንድ አካባቢ በዘር የተነሳ መፈናቀል እና መገደል ሲኖር የተፈናቀለው እና የተገደለው ኦርቶዶክስ ከሆነ በሃይማኖቱ ሙሥሊም ከሆነ በዘሩ የሚሉት ነገር ሁሌም ፈገግ ያረገኛል፥ አፈናቃዩ እና ገዳዩ በሃይማኖት ከሆነ ተመሳሳይ ሃይማኖትን ለምን ያፈናቅናል? ለምን ይገላል? የኦርቶዶክስ መምህራን እነ መምህር ምሕረተ አብ፣ መምህር ዓባይነህ፣ መምህር ዮርዳኖስ፣ መምህር ዘመድኩን፣ ቀሲስ ኤፍሬም ቀን ከሌሊት ስለ እሥልምና አሉታዊ ነገር በመናገር እንዲሁ እርር እና ምርር በማለት የሚንጨረጨሩት እና የሚንተከተኩት፦
አንደኛ የእሥልምናን ሥነ መለኮታዊ እሳቤ መቋቋም ስላቃታቸው ነው።
ሁለተኛ ስለ ክርስትና የሚያስተምሩት ትምህርት ስላለቀባቸው ነው።
ሦስተኛ የገዛ አማኞቻቸው በጉያቸው እያፈተለኩ ወደ ዲኑል ኢሥላም እየገቡ ስለሆነ ነው።

እርግጥ ነው የሙሥሊሞች አስተማሪዎች ማኅተም አስበጣሽ ናቸው፥ ብዙ ክርስቲያኖችን በፍቅር፣ በትህትና፣ በአክብሮት፣ በጥበብ እና በዕውቀት እያስተማሩ ማኅተም አስበጣሽ ሆነዋል። የሰው ማኅተም መበጠስ በሃይማኖት ማስገደድ ነውና በዚህ ድርጊት ውስጥ ሙሥሊሙ የለበትም፥ በትምህርት ግን ማስበጠሱን ግን ኢንሻሏህ ይቀጥላል።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም