ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ነጥብ አንድ
"ቀደር ከውኒይ"
"ከውኒይ" كَوْنِيّ የሚለው ቃል “ከወነ” كَوَّنَ‎ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ኹነት" ማለት ነው፥ አምላካችን አሏህ በቃሉ "ኩን" كُن የሚለው ነገር ሁሉ ይኾናል፦
16፥40 ለማንኛውም ነገር መኾኑን በሻነው ጊዜ ቃላችን ለእርሱ “ኹን” ማለት ብቻ ነው፥ ወዲውም ይኾናል፡፡ إِنَّمَا قَوْلُنَا لِشَيْءٍ إِذَا أَرَدْنَاهُ أَن نَّقُولَ لَهُ كُن فَيَكُونُ

አምላካችን አሏህ እንዲሆን በቀደረው ላይ የሰው ምርጫ ሆነ ፈቃድ የለበትም፥ ለምሳሌ ፍጡራን ሴት ሆነ ወንድ ለመሆን፣ ለመወለድ ሆነ ለመሞት፣ አጭር ሆነ ረጅም ለመሆን ምርጫ የላቸውም፦
28፥68 ጌታህም የሚሻውን ይፈጥራል፤ ይመርጣልም፡፡ ለእነርሱ ለፍጡራን ምርጫ የላቸውም፡፡ وَرَبُّكَ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ وَيَخْتَارُ ۗ مَا كَانَ لَهُمُ الْخِيَرَة

አንድ ሰው ወፈፌ ከሆነ ወደ ዐቅሉ እስኪመለስ ድረስ እና የተኛ ሰው እስኪነሳ ድረስ የሚሠራውን እኩይ ሥራ ፈልጎ ስላልሆነ መላእክት አይመዘግቡበትም፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 40, ሐዲስ 48
ዓኢሻህ “ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ “የአላህ መልዕክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ብዕር ከሦስት ሰዎች ተነስቷል፥ እነርሱም፦ የተኛ ሰው እስኪነሳ ድረስ፣ ዕብደ ወደ ዐቅሉ እስኪመለስ ድረስ እና ልጅ እስኪጎሎብት ድረስ”። عَنْ عَائِشَةَ، رضى الله عنها أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ رُفِعَ الْقَلَمُ عَنْ ثَلاَثَةٍ عَنِ النَّائِمِ حَتَّى يَسْتَيْقِظَ وَعَنِ الْمُبْتَلَى حَتَّى يَبْرَأَ وَعَنِ الصَّبِيِّ حَتَّى يَكْبَرَ ‏

ባለማወቅ የሚሠራ መጥፎ ሥራ “ስህተት” ሲባል በመርሳት የማይሠራ መልካም ሥራ “ግድፈት” ይባላል፥ ስህተት ሆነ ግድፈት አያስቀጣም፦
2፥286 “ጌታችን ሆይ! ”ብንረሳ ወይም ብንስት አትቅጣን” በሉ፡፡ رَبَّنَا لَا تُؤَاخِذْنَا إِن نَّسِينَا أَوْ أَخْطَأْنَ
33፥5 በእርሱ በተሳሳታችሁበትም ነገርም በእናንተ ላይ ኃጢአት የለባችሁም፥ ግን ልቦቻችሁ ዐዉቀው በሠሩት ኃጢአት አለባችሁ”። አላህም መሃሪ አዛኝ ነው። وَلَيْسَ عَلَيْكُمْ جُنَاحٌۭ فِيمَآ أَخْطَأْتُم بِهِۦ وَلَٰكِن مَّا تَعَمَّدَتْ قُلُوبُكُمْ ۚ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورًۭا رَّحِيمًا

“ብንረሳ” ማለት መሥራቱ ግዴታ የሆነ መልካም ሥራ በመርሳት መግደፍ ሲሆን “ብንስት” ማለት መሥራቱ ክልክል የሆነ መጥፎ ሥራ ባለማወቅ መሳሳት ነው። በተሳሳትንበት ነገር በእኛ ላይ ኃጢአት የለብንም፥ ቅሉ ግን ልባችን እያወቀው በሠራነው መጥፎ ሥራ ኃጢአት አለበት። ሰው ድርሻው በሌለበት እና ጣልቃ ገብ ባልሆነበት የአሏህ ሥራ ተገዶ ነውና የተገደዱበት ነገር አያስጠይቅም አያስቀጣም፦
2፥173 ሽፍታ እና ወሰን አላፊ ሳይኾን ለመብላት የተገደደ ሰውም በእርሱ ላይ ኃጢኣት የለበትም፥ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ فَمَنِ اضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَلَا إِثْمَ عَلَيْهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
16፥115 አመጸኛም ወይም ወሰን አላፊ ሳይኾን ለመብላት የተገደደ ሰው ይፈቀድለታል፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ فَمَنِ اضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَإِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
6፥145 አመጸኛ እና ወሰን ያለፈ ሳይኾንም የተገደደ ሰው ከተወሱት ቢበላ ኃጢአት የለበትም፡፡ ጌታህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ فَمَنِ اضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَإِنَّ رَبَّكَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 10, ሐዲስ 2123
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ ”አላህ በኡማዬ ላይ ስህተት፣ መርሳት እና የገተደዱበትን ነገር አንስቷል”። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، عَنِ النَّبِيِّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏ “‏ إِنَّ اللَّهَ وَضَعَ عَنْ أُمَّتِي الْخَطَأَ وَالنِّسْيَانَ وَمَا اسْتُكْرِهُوا عَلَيْهِ

ሰው ይህንን የአሏህን ውሳኔ በመቀበል አጅር ሲያገኝ በተቃራኒው ሲያስተባብል ቅጣት ያገኘዋል እንጂ ወንድ ወይም ሴት፣ አጭር ወይም ረጅም፣ መወለድ ወይም መሞት አያስቀጣም አያሸልምም።
ስለ "ቀደር ከውኒይ" قَدَر كَوْنِيّ በቅጡ ያለተረዳው አል ጀዕድ ኢብኑ ዲርሀም 715 ድኅረ ልደት ላይ፦ "ሰው በአሏህ ዕውቀት፣ ፈቃድ እና ምርጫ ብቻ የሚኖር ነጻ ፈቃድ የሌለው ፍጡር"necessitarian" ነው" የሚል ፍልስፍና ነበረው፥ ይህ ፍልስፍናው "ጀብሪያህ" جَبْرِيَّة ይባላል፥ "ጀብር" جَبْر የሚለው ቃል "ጀበረ" جَبَرَ ማለትም "ተገደደ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መገደድ" ማለት ነው። ይህ ጽንፍ በኢሥላም ውድቅ ሆኗል፥ ምክንያቱም ሰው ነጻ ፈቃድ እንዳለው ሸሪዓዊ፣ ሥነ-አመክኗዊ እና ተፈጥሯዊ ማስረጃዎች ስላሉም ጭምር ነው። የጀብሪያ ፍልስፍና ውድቅ የሚሆንበትን ምክንያት በክፍል ሁለት ስለ ቀደር ሸርዒይ ኢንሻሏህ እንዳስሳለን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አቅሣሙል ቀደር

ክፍል ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

54፥49 እኛ ሁሉን ነገር በልክ ፈጠርነው፡፡ إِنَّا كُلَّ شَيْءٍ خَلَقْنَاهُ بِقَدَرٍ

ነጥብ ሁለት
"ቀደር ሸርዒይ"
"ሸርዒይ" شَرْعِيّ የሚለው ቃል "ሸረዐ" شَرَعَ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ድንጋጌ" "ሕግ" "መርሕ" ማለት ነው፦
45፥18 ከዚያም ከትእዛዝ "በትክክለኛይቱ ሕግ" ላይ አደረግንህ፡፡ ثُمَّ جَعَلْنَاكَ عَلَىٰ شَرِيعَةٍ مِّنَ الْأَمْرِ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ትክክለኛይቱ ሕግ" ለሚለው የገባው ቃል "ሸሪዓህ" شَرِيعَة እንደሆነ ልብ አድርግ! አምላካችን አሏህ ሰዎች የሚዳኙበት ሕግ እና መንገድ አድርጓል፦
5፥48 ከእናንተ ለሁሉም ሕግን እና መንገድን አደረግን"። ۚ لِكُلٍّۢ جَعَلْنَا مِنكُمْ شِرْعَةًۭ وَمِنْهَاجًۭا

ይህም ሕግ ስለ ፈርድ፣ ሙስተሐብ፣ ሙባሕ፣ መክሩህ እና ሐራም የሚዘረዝሩ አሕካም ናቸው፥ ሰው በእነዚህ አሕካም መሥኡሉል ዐደብ አለበት። "መሥኡል" مَسْؤُول ማለት "ተጠያቂነት" ማለት ሲሆን "ዐደብ" اَدَب‎ ማለት ደግሞ "ግብረገብ" ማለት ነው፥ በጥቅሉ "መሥኡሉል ዐደብ" مَسْؤُول الاَدَب‎ ማለት "ግብረገባዊ ተጠያቂነት"moral accountability" ማለት ሲሆን ሰው በሚሠራው ሥራ ይጠየቃል፦
16፥93 ትሠሩት ከነበራችሁትም ሁሉ በእርግጥ ትጠየቃላችሁ፡፡ وَلَتُسْأَلُنَّ عَمَّا كُنتُمْ تَعْمَلُون
102፥8 ከዚያም ከጸጋችሁ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ። ثُمَّ لَتُسْأَلُنَّ يَوْمَئِذٍ عَنِ النَّعِيمِ

"ነዒም" نَّعِيم ማለት "ጸጋ" ማለት ሲሆን ይህ የተሰጠን ጸጋ አድርግ የተባለውን የመታዘዝዝና ያለመታዘዝ፥ አታድርግ የተባለውን የመከልከልና ያለመከልከል ነጻ ፈቃድ"free will" ነው። አሏህ በሠራው እና በሚሠራው ሥራ አይጠየቅም፥ ሰዎች ግን በሚሠሩት ሰናይ ሆነ እኩይ ሥራ ግብረገባዊ ተጠያቂነት ስላለባቸው በፍርዱ ቀን ይጠየቃሉ፦
21፥23 ከሚሠራው ሁሉ አይጠየቅም፡፡ እነርሱ ግን ይጠየቃሉ፡፡ لَا يُسْأَلُ عَمَّا يَفْعَلُ وَهُمْ يُسْأَلُونَ

ሰዎች በተሰጣቸው ነጻ ፈቃድ ይሠሩት የነበሩትን መልካም ነገር ይመነዳሉ፥ በተቃራኒው ይሠሩት የነበሩትን መጥፎ ነገር ይቀጣሉ፦
18፥180 “ይሠሩት የነበሩትን ነገር በእርግጥ ይመነዳሉ”፡፡ سَيُجْزَوْنَ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ
6፥120 “እነዚያ ኃጢአትን የሚሠሩ ይሠሩት በነበሩት ነገር በእርግጥ ይቀጣሉ”፡፡ نَّ الَّذِينَ يَكْسِبُونَ الْإِثْمَ سَيُجْزَوْنَ بِمَا كَانُوا يَقْتَرِفُونَ

ሰው የሚሠራው መልካም ሆነ መጥፎ ሥራ ከመሥራቱ በፊት አሏህ ስለሚያውቀው በጥብቁ ሰሌዳ ከትቦታል፥ ስለሚሆን የቀደረው ቀደር የራሱ ዕውቀት ሲሆን "ቀደር ሸርዒይ" قَدَر شَرْعِيّ ይባላል። ቀደር ሸርዒይ የተከተበው ስለሚሆን እንጂ እንዲሆን አይደለም፥ በተጨማሪም ለሰው አድርግ እና አታድርግ የተባለው ሕግ የማድረግ እና ያለማድረግ የሚችልበትን ነጻ ፈቃድ መሰጠቱ በራሱ የአሏህ ውሳኔ ስለሆነ ቀደር ነው። በዚህ የሰው ምርጫ ውስጥ አሏህ ምንም ነገር አያስገድድም፥ አሏህ ቢያስገድድ ኖሮ ሁሉም ሰው ቅን እና አማኝ ይሆን ነበር። ግን በነጻ ፈቃዳቸው እንጂ በማስገደድ ቅን እና አማኝ ማረግ አልፈለገም፦
6፥149 «የተሟላው ማስረጃ የአላህ ነው፡፡ በሻም ኖሮ ሁላችሁንም ባቀናችሁ ነበር» በላቸው፡፡ قُلْ فَلِلَّهِ الْحُجَّةُ الْبَالِغَةُ ۖ فَلَوْ شَاءَ لَهَدَاكُمْ أَجْمَعِينَ
10፥99 ጌታህም በሻ ኖሮ በምድር ያሉት ሰዎች ሁሉም የተሰበሰቡ ሆነው ባመኑ ነበር፡፡ ታዲያ አንተ ሰዎችን አማኞች እንዲኾኑ ታስገድዳለህን? وَلَوْ شَاءَ رَبُّكَ لَآمَنَ مَن فِي الْأَرْضِ كُلُّهُمْ جَمِيعًا ۚ أَفَأَنتَ تُكْرِهُ النَّاسَ حَتَّىٰ يَكُونُوا مُؤْمِنِينَ

ቅሉ ግን ሰው የማመን እና የመካድ ነጻ ፈቃድ ስላለው ቀደር ሸርዒይ ውስጥ ጣልቃ ገብ እና ባለ ድርሻ ነው፥ አሏህም "ቅኑ መንገድ ይህ ነው" በማለት አማኝ እንዲሆን እና "ጠማማ መንገድ ይህ ነው" በማለት ከሃዲ እንዳይሆን ሁለቱንም መንገዶች ገልጾልናል። የፈለገ ቅኑን መንገድ በመከተል ማመን አሊያም የፈለገ ጠማማውን መንገድ በመከተል መካድ የግለሰቡ ምርጫ ነው፦
2፥256 በሃይማኖት ማስገደድ የለም፡፡ ቅኑ መንገድ ከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ፡፡ لَا إِكْرَاهَ فِي الدِّينِ ۖ قَد تَّبَيَّنَ الرُّشْدُ مِنَ الْغَيِّ
90፥10 ሁለት መንገዶችም አልመራነውምን? وَهَدَيْنَٰهُ ٱلنَّجْدَيْنِ
76፥3 እኛ አመስጋኝ ወይም ከሐዲ ሲሆን መንገዱን መራነዉ። إِنَّا هَدَيْنَٰهُ ٱلسَّبِيلَ إِمَّا شَاكِرًۭا وَإِمَّا كَفُورًا
18፥29 «እውነቱም ከጌታችሁ ነው፡፡ የሻም ሰው ይመን፤ የሻም ሰው ይካድ» በላቸው፡፡ وَقُلِ الْحَقُّ مِن رَّبِّكُمْ ۖ فَمَن شَاءَ فَلْيُؤْمِن وَمَن شَاءَ فَلْيَكْفُرْ

"አድርግ" ተብሎ የታዘዘው ሙፍረዳት "አታድርግ" ተብሎ የተከለከለው ሙሐረማት፣ ተስፋ እና ዛቻ፣ ሽልማት እና ቅጣት፣ ጀነት እና ጀሀነም ሰው በነጻ ፈቃዱ ስለሚሠራው እና ስለሚያደርገው የተጻፉ መሆኑን ቁልጭ እና ፍንትው ያለ ማሳያ ነው።
ስለ "ቀደር ሸርዒይ" قَدَر شَرْعِيّ በቅጡ ያለተረዳው ከ1077–1166 ድኅረ-ልደት ይኖር የነበረ ሰው ዐብዱል ቃዲር አል-ጂላኒይ፦ "ሰው ያለ አሏህ ዕውቀት፣ ምርጫ እና ፈቃድ ብቻውን በራሱ ነጻ ፈቃድ ያለው ፍጡር"libriterian" ነው" የሚል ፍልስፍና ነበረው። ይህ ፍልስፍና "ቀደሪያህ" قَدَرِيَّة ይባላል፥ "ቀደሪያህ" የሚለው ስም "ዐብዱል ቃዲር" ከሚለው ስም ቁልምጫ ሆኖ የተሰየመ ነው።
ሁለቱን ሙቀደራት ቀደር ከውኒይ እና ቀደር ሸርዒይ ጥልል እና ጥንፍፍ አርጎ ማጥለል እና ማጠንፈፍ የአሏህ ውሳኔ እና የሰውን ነጻ ፈቃድ በቅጡ ለመረዳት ጉልኅ ሚና አለው። አሏህ በቀደር ከሚያምኑ ሙእሚን ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
መራቲቡል ቀደር

ክፍል አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

15፥45 አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡ وَكَانَ اللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ مُّقْتَدِرًا

"ቀደር" قَدَر የሚለው ቃል "ቀደረ" قَدَرَ ማለትም "ቻለ" "ወሰነ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ውሳኔ" "ችሎት" ማለት ነው፥ "ቁድራህ" قُدْرَة ማለት "ችሎታ" ማለት ሲሆን የአሏህ ባሕርይ ነው። አምላካችን አሏህ ነገርን ሁሉ በቀድር የሚፈጥር "አል-ሙቅተዲር" الْمُّقْتَدِر ነው፦
15፥45 አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡ وَكَانَ اللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ مُّقْتَدِرًا

"ሙረተብ" مُرَتِّب የሚለው ቃል "ረተበ" رَتَّبَ ማለትም "ደረጀ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ደረጃ" ማለት ነው፥ "መርተባህ" مَرْتَبَة ደግሞ የሙረተብ አንስታይ መደብ ነው። የመርተባህ ብዙ ቁጥር "መራቲብ" مَراتِب ወይም "ሙርተባት" مُرَتَّبَات ነው፥ በጥቅሉ "መራቲቡል ቀደር" مَراتِب القَدَر ማለት "የቀደር ደረጃዎች" ማለት ነው። መራቲቡል ቀደር በአራት ይከፈላሉ፥ እነርሱም፦
"መርተበቱል ዒልም" مَرْتَبَة العِلْم
"መርተበቱል ኪታብ" مَرْتَبَة الكِتَاب
"መርተበቱል መሺኣህ" مَرْتَبَة المَشِئَة
"መርተበቱል ኸልቅ" مَرْتَبَة الخَلْق ናቸው።

ነጥብ አንድ
"መርተበቱል ዒልም"
"ዒልም" عِلْم ማለት "ዕውቀት" ማለት ሲሆን ቦታ ሳይፈጠር እና ጊዜ ሳይቆጠር በፊት አምላካችን አሏህ ሁሉን ነገር ያውቃል፥ በቁርኣን ከተገለጹት መልካም ስሞቹ አንዱ "አል-ዐሊም" الْعَلِيم ሲሆን "ሁሉን ዐዋቂ" ማለት ነው፦
33፥54 አላህ ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው። فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمًا

"ዒልም" عِلْم የአሏህ የራሱ ባሕርይ ሲሆን "ሸይእ" شَيْء ደግሞ ፍጡር ነው፥ "ሸይእ" شَيْء ማለት "ነገር" ማለት ሲሆን ይህም ነገር ጊዜ እና ቦታ ነው። አምላካችን አሏህ አላፊ ጊዜ፣ አሁናዊ ጊዜ፣ መጻኢ ጊዜ በዕውቀቱ ያካበበ ነው
19፥64 በፊታችን ያለው፣ በኋላችንም ያለው እና በዚህም መካከል ያለው ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ ጌታህም ረሺ አይደለም፡፡ لَهُ مَا بَيْنَ أَيْدِينَا وَمَا خَلْفَنَا وَمَا بَيْنَ ذَٰلِكَ ۚ وَمَا كَانَ رَبُّكَ نَسِيًّا

ጂብሪል "በፊታችን ያለው" ሲል አላፊ ጊዜን፣ "በኋላችንም ያለው" ሲል መጻኢ ጊዜን፣ "በዚህም መካከል ያለው ሁሉ" ሲል አሁናዊ ጊዜን ያመለክታል፥ አሏህ በዕውቀቱ ትላንትን፣ ዛሬን እና ነገን ያካበበ ነው። በተመሳሳይ ርዝመታዊ ቦታ፣ ቁመታዊ ቦታ፣ ስፋታዊ ቦታ ስለማያካብቡት ከፍጥረት በኃላ የሚሆነውን ነገር ሁሉ ከፍጥረት በፊት ያውቃል፥ እንዲሆን ያለውን ነገር እና ስለሚሆን ያለውን ነገር ሁሉ ያውቃል። አሏህ ምንም "ነገር" ሳይኖር ብቻውን ነበረ፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 59, ሐዲስ 2
ዒምራም ኢብኑ ሑሰይን እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" አሉ፦ "ምንም ነገር ሳይኖር አሏህ ነበረ"። عَنْ عِمْرَانَ بْنِ حُصَيْنٍ، قَالَ إِنِّي عِنْدَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم كَانَ اللَّهُ وَلَمْ يَكُنْ شَىْءٌ غَيْرُهُ

አሏህ ምንም "ነገር" ሳይኖር ብቻውን ሲኖር የማወቅ ባሕርይም ነበረው፥ ነገርን ከፈጠረ በኃላም በዕውቀቱ ጊዜ እና ቦታን ያካበበ ነው፦
32፥54 ንቁ! እርሱ(አላህ) በነገሩ ሁሉ ከባቢ ነው፡፡ أَلَا إِنَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ
65፥12 አላህም በነገሩ ሁሉ በዕውቀት ያካበበ መኾኑን ታወቁ ዘንድ ይህንን አሳወቃችሁ፡፡ وَأَنَّ اللَّهَ قَدْ أَحَاطَ بِكُلِّ شَيْءٍ عِلْمًا

ሰው አንድን ነገር ለማወቅ ያ የሚያውቀው ነገር ከዕውቀቱ ቀድሞ መገኘት አለበት፥ ለምሳሌ፦ እኔ ልጄን ለማወቅ ቅድሚያ ልጄ መኖር አለበት። ልጄ ሳይኖር ልጄ ዐላውቀውም፥ እኔ ልጄን ለማወቅ ልጄ መንስኤ"cause" ሲሆን ስለ ልጄ የማውቀው ዕውቀት ደግሞ ውጤት"effect" ነው። አምላካችን አሏህ ዘንድ ግን አንድን ነገር ለማወቅ የሚታወቀው ነገር መኖር መስፈርት አይደለም፥ አሏህ ፍጥረትን ከመፍጠሩ በፊት ፍጥረቱን ያውቀዋል። የአሏህ ዕውቀት የፍጥረት መንስኤ ሲሆን ፍጥረት ግን ውጤት ነው፥ አንድ ሰው ዐዋቂ ለመባል ታዋቂ ነገር እንደሚያስፈልገው አሏህን ግን ዐዋቂ ለመባል ታዋቂ ነገር አያስፈልገውም። አሏህ ልክ እንደ ሰው በታዋቂ ነገር ላይ ጥገኛ ሳይሆን ከሚታወቅ ነገር ታብቃቂ ነው፦
29፥6 አላህ ከዓለማት በእርግጥ ተብቃቂ ነውና፡፡ إِنَّ اللَّهَ لَغَنِيٌّ عَنِ الْعَالَمِينَ
3፥97 የካደም ሰው አላህ ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ነው፡፡ وَمَن كَفَرَ فَإِنَّ اللَّهَ غَنِيٌّ عَنِ الْعَالَمِينَ

"ዐሊም" عَلِيم ማለት "ዐዋቂ" ማለት ሲሆን "መዕሉም" مَعْلُوم ማለት ደግሞ "ታዋቂ" ማለት ነው፥ አምላካችን አሏህ ከሚታወቁ ነገራቶች ሁሉ የተብቃቃ ነው። "ዓለም" عَالَم ማለት "ጽንፈ ዓለም" ማለት ነው፥ የዓለም ብዙ ቁጥር ደግሞ "ዓለሚን" عَالَمِين ወይም "ዓለሙን" عَالَمُون ሲሆን "ጽንፈ ዐለማት" ማለት ነው። ዐሊም ፋዒል ሲሆን መዕሉም መፍዑል ነው፥ በሰው ከሄድን ሰው ጥገኛ ስለሆነ ዐሊም ለመባል መዕሉም ያስፈልገዋል። አሏህ ግን የተብቃቃ ስለሆነ መዕሉም የሆኑ ጽንፈ ዐለማት ከመፈጠራቸው በፊትም ዐሊም ነው፥ አላህ ጽንፈ ዐለማትን ስለሚያውቃቸው እርሱ ዐሊም የተባለበት ሰው በተባለበት ስሌት እና ቀመር አይደለም።
ቀደሪያዎች እና የይሆዋ ምስክሮች፦ "ፈጣሪ ሁሉን ነገር ማወቅ ከፈለገ ይችላል እንጂ ፈጣሪ ሁሉን ዐዋቂ አይደለም፥ ሰው በነጻ ፈቃዱ ምን እንደሚሠራ ቀድሞውኑን ፈጣሪ ምንም አያውቅም። የእርሱ ዕውቀት አንጻራዊ ዕውቀትconditional knowledge" እንጂ ፍጹማዊ ዕውቀት"absolute knowledge አይደለም" የሚል ዋልታ ረገጥ ፍልስፍና አላቸው፥ እንግዲህ ከቁርኣን እና ከሐዲስ አንጻር በግልጽ እና በማያሻማ መልኩ አሏህ ሁሉን ዐዋቂ እንደሆነ ተገልጿል።
ኢንሻሏህ ስለ መርተበቱል ኪታብ በክፍል ሁለት እንዳስሳለን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
መራቲቡል ቀደር

ክፍል ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

52፥2 በተጻፈው መጽሐፍ እምላለው፡፡ وَكِتَابٍ مَّسْطُورٍ

ነጥብ ሁለት
"መርተበቱል ኪታብ"
"ኪታብ" كِتَاب ማለት "መጽሐፍ" ማለት ሲሆን አምላካችን አሏህ የራሱን ዕውቀት በኪታብ ላይ ጽፎታል፦
20፥52 ሙሳም፦ "ዕውቀትዋ እጌታዬ ዘንድ በመጽሐፍ የተመዘገበ ነው፡፡ ጌታዬ አይሳሳትም አይረሳምም" አለው፡፡ قَالَ عِلْمُهَا عِندَ رَبِّي فِي كِتَابٍ ۖ لَّا يَضِلُّ رَبِّي وَلَا يَنسَى
22፥70 አላህ በሰማይና በምድር ውስጥ ያለን ሁሉ በእርግጥ የሚያውቅ መኾኑን አታውቅምን? ይህ በመጽሐፍ ውስጥ የተመዘገበ ነው፡፡ ይህ በአላህ ላይ ገር ነው፡፡ أَلَمْ تَعْلَمْ أَنَّ اللَّهَ يَعْلَمُ مَا فِي السَّمَاءِ وَالْأَرْضِ ۗ إِنَّ ذَٰلِكَ فِي كِتَابٍ ۚ إِنَّ ذَٰلِكَ عَلَى اللَّهِ يَسِيرٌ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ይህ" የሚለው አመልካች ተውላጠ ስም "አላህ በሰማይና በምድር ውስጥ ያለን ሁሉ የሚያውቀው" የሚለውን ዕውቀት ሲሆን ይህም ዕውቀት በመጽሐፍ ውስጥ የተመዘገበ ነው፥ ይህ ዕውቀት በመጽሐፍ ውስጥ መመዝገብ ለአሏህ ቀላል ነው። አሏህ ይህ ዕውቀት በመጽሐፍ ውስጥ የጻፈው ያ የሚጻፈው "ነገር" ከመፈጠሩ አስቀድሞ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 179
አቢ ሁረይራህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ "አሏህ ፍጥረትን ከመፍጠሩ በፊት በመጽሐፍ ጻፈ"። سَمِعَ أَبَا هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ يَقُولُ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ "‏ إِنَّ اللَّهَ كَتَبَ كِتَابًا قَبْلَ أَنْ يَخْلُقَ الْخَلْقَ

ከፍጥረት እስከ ፍርድ ቀን ድረስ የሚሆኑትን ነገር ሁሉ የያዘ ይህ መጽሐፍ፦
"ለውሐል መሕፉዝ" لَوحَ المَّحْفُوظ
"ኪታቡል መክኑን" كِتَابٍ الْمَّكْنُون
"ኪታቡል መሥጡር" المَّسْطُور
"ኡሙል ኪታብ" أُمِّ الْكِتَاب
"ኪታቡል ሙቢን" كِتَاب المُّبِين ተብሏል፦
85፥22 የተጠበቀ በኾነ ሰሌዳ ውስጥ ነው፡፡ فِي لَوْحٍ مَّحْفُوظٍ
56፥78 በተጠበቀ መጽሐፍ ውስጥ ነው፡፡ فِي كِتَابٍ مَّكْنُونٍ
52፥2 በተጻፈው መጽሐፍ እምላለው፡፡ وَكِتَابٍ مَّسْطُورٍ
43፥4 እርሱም በመጽሐፎቹ እናት ውስጥ እኛ ዘንድ በእርግጥ ከፍተኛ ጥበብ የተመላ ነው፡፡ وَإِنَّهُ فِي أُمِّ الْكِتَابِ لَدَيْنَا لَعَلِيٌّ حَكِيمٌ
10፥61 በምድርም ሆነ በሰማይ የብናኝ ክብደት ያክል ከጌታህ ዕውቀት አይርቅም፡፡ ከዚያም ያነሰ የተለቀም የለም፤ በግልጹ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈ ቢሆን እንጂ፡፡ وَمَا يَعْزُبُ عَن رَّبِّكَ مِن مِّثْقَالِ ذَرَّةٍ فِي الْأَرْضِ وَلَا فِي السَّمَاءِ وَلَا أَصْغَرَ مِن ذَٰلِكَ وَلَا أَكْبَرَ إِلَّا فِي كِتَابٍ مُّبِينٍ

ከሥነ-አመክንዮ ባሻገር የሚያጅበው አሏህ ከፍጥረት በፊት ከመጻፉ ይልቅ ማወቁ ነው፥ አሏህ ሰዎች የሚሠሩትን እና የሚያደርጉትን ከመሥራታቸው እና ከማወቃቸው በፊት ካወቀ ዘንዳ ያንን የሚሠሩትን እና የሚያደርጉትን ሥራ እና ድርጊት መጻፉ ለመረዳት ቀላል ነው። ሰዎች የሚሠሩት እና የሚያደርጉትን ሥራ መልካም ሆነ ክፉ ሥራ የተጻፈው ስለሚሠሩት እንጂ እንዲሠሩት አይደለም፥ ስለሚያደርጉት እንጂ እንዲያደርጉት አይደለም።
ለምሳሌ፦ አንድ የኬምስትሪ ባለሙያ መድኃኒት ሠርቶ ውጤቱ ኤክስፓየርድ ማድረግ ቢሆን በተመሳሳይ የፋርማሲ ባለሙያ ስለ መድኃኒቱ አጥንቶ መድኃኒቱ በዚህ ቀን ኤክስፓየርድ ያረጋል" ብሎ ኤክስፓየርድ ከማድረጉ በፊት በመግለጫው ላይ ቢጽፍ እና መድኃኒቱ ኤክስፓየርድ ቢያደርግ መድኃኒቱ ኤክስፓየርድ እንዲያደርግ ተጠያቂው የኬምስትሪ ባለሙያ እንጂ ፋርማሲስቱ አይደደለም፥ ባይሆን የፋርማሲ ባለሙያ ባላ ዕውቀት መሆኑን እንጂ ለመድኃኒቱ ሥሪት አላፍትናው ያለበት የኬምስትሪ ባለሙያ እንደሆነ ሁሉ ሰዎች ለሚሠሩት ሥራ አላፊነቱ የሰዎች ሲሆን አሏህ ሥራቸውን ቀድሞውኑ በመጽሐፍ መጽሐፉ የእርሱን ዐዋቂነት ያሳያል።
ሰው ግብረ ገባዊ ተጠያቂነት ያለው ፍጡር ስለሆነ እንደ እንስሳ ልቅ ሆኖ እንዳይተው ጌታችን አሏህ ሙሐከማትን የሚያስተምር መልእክተኛ ልኳል። አምላካችን አሏህ ፍትሓዊ አምላክ ነው፥ መልእክተኛ ልኮ የላከውን መልእክት ሰዎች እስካልሰሙ ድረስ ደግሞ አይቀጣቸውም፦
75፥36 ሰው ልቅ ኾኖ መተውን ያስባልን? أَيَحْسَبُ الْإِنسَانُ أَن يُتْرَكَ سُدًى
17፥15 መልእክተኛን እስከምንልክ ድረስ የምንቀጣ አይደለንም፡፡ وَمَا كُنَّا مُعَذِّبِينَ حَتَّىٰ نَبْعَثَ رَسُولًا

"ሑጃህ" حُجَّة ማለት "አስረጅ" ማለት ሲሆን ሰዎች መልእክቱን ከሰሙ በኃላ ሲያስተባብሉ በፍርድ ቀን አልሰማንም እንዳይሉ አሏህ በጀነት የሚያበስሩ እና በጀሀነም የሚያስጠነቅቁ መልእክተኞችን ልኳል፦
17፥165 ከመልክተኞቹ በኋላ ለሰዎች በአላህ ላይ አስረጅ እንዳይኖር አብሳሪዎችና አስጠንቃቂዎች የኾኑን መልክተኞች ላክን፡፡ አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው፡፡ رُّسُلًا مُّبَشِّرِينَ وَمُنذِرِينَ لِئَلَّا يَكُونَ لِلنَّاسِ عَلَى اللَّهِ حُجَّةٌ بَعْدَ الرُّسُلِ ۚ وَكَانَ اللَّهُ عَزِيزًا حَكِيمًا
20፥134 እኛም ከእርሱ በፊት በቅጣት ባጠፋናቸው ኖሮ «ጌታችን ሆይ! ከመዋረዳችን እና ከማፈራችን በፊት አንቀጾችህን እንከተል ዘንድ ወደ እኛ መልእክተኛን አትልክም ነበርን?» ባሉ ነበር፡፡ وَلَوْ أَنَّا أَهْلَكْنَاهُم بِعَذَابٍ مِّن قَبْلِهِ لَقَالُوا رَبَّنَا لَوْلَا أَرْسَلْتَ إِلَيْنَا رَسُولًا فَنَتَّبِعَ آيَاتِكَ مِن قَبْلِ أَن نَّذِلَّ وَنَخْزَىٰ
አሏህ መልእክተኛ መላኩን እና ማስተባበላቸውን የሚያውቁ በዳዮች የፍርዱ ቀን "አንቀጾችህን እንከተል ዘንድ ወደ እኛ መልእክተኛን አትልክም ነበርን" ከማለት ይልቅ "ጌታችን ሆይ! ወደ ቅርበ ጊዜ ድረስ አቆየን፡፡ ጥሪህን እንቀበላለንና መልክተኞቹንም እንከተላለን" ይላሉ፥ አሏህም፦ "ከአሁን በፊት በምድረ ዓለም "ለእናንተ ምንም መወገድ የላችሁም" በማለት የማላችሁ አልነበራችሁምን" ይላቸዋል፦
14፥44 ሰዎችንም ቅጣቱ የሚመጣባቸውን ቀን አስጠንቅቃቸው! እነዚያም የበደሉት «ጌታችን ሆይ! ወደ ቅርበ ጊዜ ድረስ አቆየን፡፡ ጥሪህን እንቀበላለንና መልክተኞቹንም እንከተላለንና» ይላሉ፡፡ «ከአሁን በፊት በምድረ ዓለም ለእናንተ ምንም መወገድ የላችሁም በማለት የማላችሁ አልነበራችሁምን» ይባላሉ፡፡ وَأَنذِرِ النَّاسَ يَوْمَ يَأْتِيهِمُ الْعَذَابُ فَيَقُولُ الَّذِينَ ظَلَمُوا رَبَّنَا أَخِّرْنَا إِلَىٰ أَجَلٍ قَرِيبٍ نُّجِبْ دَعْوَتَكَ وَنَتَّبِعِ الرُّسُلَ ۗ أَوَلَمْ تَكُونُوا أَقْسَمْتُم مِّن قَبْلُ مَا لَكُم مِّن زَوَالٍ

የጀሃነም ዘበኞች የሆኑ መላእክት ለከሓድያን፦ "ከእናንተ የኾኑ መልእክተኞች የጌታችሁን አንቀጾች በእናንተ ላይ የሚያነቡላችሁ እና የዚህንም ቀን መገናኘት የሚያስጠነቅቋችሁ አልመጡላችሁምን? ሲሏቸው "መጥተውልናል" በማለት ይጸጸታሉ፦
39፥71 እነዚያ የካዱትም የተከፋፈሉ ጭፍሮች ኾነው ወደ ገሀነም ይነዳሉ፡፡ በመጧትም ጊዜ ደጃፎችዋ ይከፈታሉ፡፡ ዘበኞችዋም «ከእናንተ የኾኑ መልእክተኞች የጌታችሁን አንቀጾች በእናንተ ላይ የሚያነቡላችሁ እና የዚህንም ቀን መገናኘት የሚያስጠነቅቋችሁ አልመጡላችሁምን?» ይሏቸዋል፡፡ «የለም መጥተውልናል፤ ግን የቅጣቲቱ ቃል በከሓዲዎች ላይ ተረጋገጠች» ይላሉ፡፡ وَسِيقَ الَّذِينَ كَفَرُوا إِلَىٰ جَهَنَّمَ زُمَرًا ۖ حَتَّىٰ إِذَا جَاءُوهَا فُتِحَتْ أَبْوَابُهَا وَقَالَ لَهُمْ خَزَنَتُهَا أَلَمْ يَأْتِكُمْ رُسُلٌ مِّنكُمْ يَتْلُونَ عَلَيْكُمْ آيَاتِ رَبِّكُمْ وَيُنذِرُونَكُمْ لِقَاءَ يَوْمِكُمْ هَـٰذَا ۚ قَالُوا بَلَىٰ وَلَـٰكِنْ حَقَّتْ كَلِمَةُ الْعَذَابِ عَلَى الْكَافِرِينَ

የእሳት ሰዎች ለቅጣት የዳረጋቸው ነገር ምን እንደሚሠሩ ቀድሞ መጻፉ እንደሆነ የፍርድ ቀን አንድ ጊዜም ምክንያት ሰተው አያውቁም፥ "በሰቀር ውስጥ ምን አገባችሁ? ሲባሉ "ከሙሶሊን አልነበርንም" በማለት ምላሽ ይሰጣሉ፦
74፥42 «በሰቀር ውስጥ ምን አገባችሁ?» ይሏቸዋልም مَا سَلَكَكُمْ فِي سَقَرَ
74፥43 እነርሱም፦ «ከሙሶሊን አልነበርንም» ይላሉ፡፡ قَالُوا لَمْ نَكُ مِنَ الْمُصَلِّينَ

"ሙሶሊን" مُصَلِّين ማለት ሶላትን ደንቡን ጠብቀው የሚቆሙ፣ የሚያጎነብሱ እና የሚሰግዱ ናቸው፥ አሏህ፦ "አንቀጾቼ በእናንተ ላይ የሚነበቡላችሁ እና በእነርሱ የምታስተባብሉ አልነበራችሁምን? ሲላቸው፦ "ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ መናጢነታችን አሸነፈችን፥ ጠማማዎችም ሕዝቦች ነበርን" "የምንሰማ ወይም የምንረዳ በነበርንም ኖሮ በነዳጅ እሳት ጓዶች ውስጥ ባልኾን ነበር" ይላሉ፦
23፥105 «አንቀጾቼ በእናንተ ላይ የሚነበቡላችሁ እና በእነርሱ የምታስተባብሉ አልነበራችሁምን» ይባላሉ፡፡ أَلَمْ تَكُنْ آيَاتِي تُتْلَىٰ عَلَيْكُمْ فَكُنتُم بِهَا تُكَذِّبُونَ
23፥106 ይላሉ «ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ መናጢነታችን አሸነፈችን፥ ጠማማዎችም ሕዝቦች ነበርን፡፡ قَالُوا رَبَّنَا غَلَبَتْ عَلَيْنَا شِقْوَتُنَا وَكُنَّا قَوْمًا ضَالِّينَ
67፥10 «የምንሰማ ወይም የምንረዳ በነበርንም ኖሮ በነዳጅ እሳት ጓዶች ውስጥ ባልኾን ነበር» ይላሉ፡፡ وَقَالُوا لَوْ كُنَّا نَسْمَعُ أَوْ نَعْقِلُ مَا كُنَّا فِي أَصْحَابِ السَّعِيرِ

አምላካችን አሏህ ፍትሓዊ አምላክ ሰለሆነ ማንንም አይበድልም፥ "ዘራህ" ذَرَّة ማለት "ቅንጣት"atom" ማለት ሲሆን አሏህ ቅንጣት ታክል ማንንም አይበድልም። ነገር ግን ሰው እራሱን የሚበድነው ማመን እና መታዘዝ ሲችል በመካድ እና በማመጽ ነው፦
18፥49 ጌታህም አንድንም አይበድልም፡፡ وَلَا يَظْلِمُ رَبُّكَ أَحَدًا
4፥40 አላህ የብናኝን ክብደት ያህል አይበድልም፡፡ إِنَّ اللَّهَ لَا يَظْلِمُ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ
10፥44 አላህ ሰዎችን ምንም አይበድልም፡፡ ግን ሰዎች እራሳቸውን ይበድላሉ፡፡ إِنَّ اللَّهَ لَا يَظْلِمُ النَّاسَ شَيْئًا وَلَـٰكِنَّ النَّاسَ أَنفُسَهُمْ يَظْلِمُونَ

አሏህ ማንንም የማይበድል ከሆነ በጥብቁ ሰሌዳ የተጻፈው የአሏህ ዕውቀት መሆኑን ተረድተን እና የተጻፈው ምን እንደሆነ ስለማናውቅ ከእኛም የሚጠበቅብን ሠበቡን ማድረስ ብቻ ነው።
ኢንሻሏህ ስለ መርተበቱል መሺአህ በክፍል ሦስት እንዳስሳለን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
መራቲቡል ቀደር

ክፍል ሦስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

24፥45 አላህ የሚሻውን ሁሉ ይፈጥራል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና*፡፡ يَخْلُقُ اللَّهُ مَا يَشَاءُ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِير

ነጥብ ሦስት
"መርተበቱል መሺኣህ"
"መሺኣህ" مَشِئَة የሚለው ቃል "ሻአ" شَاءَ ማለትም "ፈቀደ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ፈቃድ" ማለት ነው፥ አምላካችን አሏህ የሚሻውን ሁሉ ይፈጥራል፦
24፥45 አላህ የሚሻውን ሁሉ ይፈጥራል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና፡፡ يَخْلُقُ اللَّهُ مَا يَشَاءُ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِير

አሏህ ሁሉን ነገር በማድረግ ከሃሊ ኩሉ ስለሆነ እዚህ አንቀጽ ላይ "ቀዲር" قَدِير ተብሏል፥ በፍጥረቱ ውስጥ የሚሻውን ይጨምራል። ለሚሻው ሰው ሴቶችን ይሰጣል፥ ለሚሻውም ሰው ወንዶችን ይሰጣል፦
35፥1 በፍጥረቱ ውስጥ የሚሻውን ይጨምራል፤ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና፡፡ يَزِيدُ فِي الْخَلْقِ مَا يَشَاءُ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
42፥49 የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ ለሚሻው ሰው ሴቶችን ይሰጣል፥ ለሚሻውም ሰው ወንዶችን ይሰጣል፡፡ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ يَهَبُ لِمَن يَشَاءُ إِنَاثًا وَيَهَبُ لِمَن يَشَاءُ الذُّكُورَ
28፥68 ጌታህም የሚሻውን ይፈጥራል፥ ይመርጣልም፡፡ ለእነርሱ ለፍጡራን ምርጫ የላቸውም*፡፡ وَرَبُّكَ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ وَيَخْتَارُ ۗ مَا كَانَ لَهُمُ الْخِيَرَة

አንድ ሰው መቼና የት እንደሚወለድ፣ መቼና የት እንደሚሞት፣ ፆታው ወንድ ወይም ሴት፣ ቁመቱ አጭር ወይም ረጅም ለመሆን ምርጫ የለውም፥ አሏህ የሚሻውን ይፈጥራል። "የሚሻውን" ለሚለው የገባው ቃል "የሻኡ" يَشَاءُ ሲሆን "የፈቀደውን" ማለት ነው። ይህ ፈቃድ እንዲሆን የፈቀደው ብቻ ነው፥ ስለሚሆን የፈቀደው ነገር ደግሞ እርሱ የሚወደው መልካም ነገር እና የጠላው ክፉ ነገር ያመለክታል። "ሰዎች የሚያስቡት ትክክል እና ስህተት፣ የሚናገሩት እውነት እና ውሸት፣ የሚተገብሩት መልካም እና ክፉ ነገር የሚሆነው አሏህ ፈቅዶ ነው" ብሎ መቀበል መርተበቱል መሺኣህ ነው፥ ይህም ስለሚሆን የፈቀደው ነው። የሰው ነጻ ፈቃድ እራሱ በአሏህ ፈቃድ ሥር ነው፦
81፥29 የዓለማት ጌታ አላህ ካልፈቀደ አትፈቅዱም፡፡ وَمَا تَشَاءُونَ إِلَّا أَن يَشَاءَ اللَّهُ رَبُّ الْعَالَمِينَ
76፥30 አላህም ካልፈቀደ በስተቀር አትፈቅዱም፡፡ አላህ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና*፡፡ وَمَا تَشَاءُونَ إِلَّا أَن يَشَاءَ اللَّهُ ۚ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَلِيمًا حَكِيمًا

ይህ የአሏህ ፈቃድ"Permission" ጉዳዩ መውደድ እና መጥላት፣ መስማማት እና አለመስማማት፣ መቀበል እና አለመቀበል ያካትታል፥ ሰዎች አድርጉ የተባሉትን የማድረግ ወይም ያለማድረግ እና አታድርጉ የተባሉትን የማድረግ ወይም ያለማድረግ ነጻ ፈቃድ ፈቅዶ የሰጠው አሏህ ነው። አምላካችን አሏህ ለሰው በኢህላም አመጽ ምን እንደሆነ እና አሏህ መፍራት ምን እንደሆነ አሳውቆታል፦
91፥8 አመጽዋን እና ፍርሃትዋንም ባሳወቃት፡፡ فَأَلْهَمَهَا فُجُورَهَا وَتَقْوَاهَا

እዚህ አንቀጽ ላይ "ባሳወቀ" ለሚለው የገባው ቃል "አልሀመ" أَلْهَمَ መሆኑን ልብ በል! "ኢልሃም" إِلْهَام የሚለው ቃል እራሱ "አልሀመ" أَلْهَمَ ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ውሳጣዊ ግንዛቤ ወይም ዕውቀ-ልቦና”intuition” ማለት ነው፦
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 91፥8 ኢብኑ ዐባሥ “አመጽዋን እና ፍርሃትዋንም ባሳወቃት” የሚለውን ሲናገር፦ “ለእርሷ መልካም እና ክፉን ገልጾላታል”። ሙጃሂድ፣ ቀታዳህ፣ ሶሓክ እና ሰውሪይ ተመሳሳይ ነገር ብለዋል፥ ሠዒድ ኢብኑ ጁበይር፦ “መልካም እና ክፉን ባሳወቃት” ብሏል”።
قال ابن عباس : ( فألهمها فجورها وتقواها ) بين لها الخير والشر . وكذا قال مجاهد ، وقتادة ، والضحاك ، والثوري . وقال سعيد بن جبير : ألهمها الخير والشر .

"ፉጁር" فُجُور ማለት "አመጽ" ማለት ሲሆን ይህም አመጽ አሏህ ያዘዘውን መልካም ነገር ባለማድረግ እና የከለከለውን መጥፎ ነገር በማድረግ ማመጽ ነው፥ "ተቅዋ" تَقْوَا ማለት ደግሞ "አሏህን መፍራት" ማለት ሲሆን ይህም ፍርሃት አሏህ ያዘዘውን መልካም ነገር በማድረግ እና የከለከለውን መጥፎ ነገር ባለማድረግ መታዘዝ ነው። ስለዚህ ሰው ሲፈጠር በነጻ ፈቃዱ መታዘዝ እና ማመጽ የሚችልበትን ችሎታ ተሰቶት ነው፦
23፥62 ማንኛይቱንም ነፍስ ችሎታዋን እንጂ አናስገድዳትም፡፡ وَلَا نُكَلِّفُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا
6፥152 ነፍስን ችሎታዋን እንጂ አናስገድድም፡፡ لَا نُكَلِّفُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا
2፥233 ነፍስ ችሎታዋን እንጂ አትገደድም፡፡ لَا تُكَلَّفُ نَفْسٌ إِلَّا وُسْعَهَا

"ውሥዕ" وُسْع ማለት "ችሎታ" ማለት ሲሆን ሰው አሏህ "አድርግ" ብሎ ያዘዘውን የማድረግ እና "አታድርግ" ብሎ የከለከውን ያለማድረግ ችሎታ እና ዐቅም ያሳያል፥ መልካም ሥራ ለመሥራት እና ክፉ ሥራ ለመታቀብ ብለን አሏህን የምንፈራው እንኳን ያቅማችንን ያክል ነው። ይህም ተገቢ ፍርሃት ነው፦
65፥16 አላህንም የቻላችሁትን ያክል ፍሩት። فَاتَّقُوا اللَّهَ مَا اسْتَطَعْتُمْ
3፥102 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገቢውን መፍራት ፍሩት፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ حَقَّ تُقَاتِهِ

አምላካችን አሏህ፦ "በጎ ሥራን ሥሩ" እና "ወሰንንም አትለፉ" ማለቱ በራሱ ሰው በጎ ሥራን የመሥራት እና ያለመሥራት ወይም ወሰን ማለፍ እና አለማለፍ ዐቅም እንዳለው የሚያሳይ ነው፦
2፥195 በጎ ሥራን ሥሩ! አላህ በጎ ሠሪዎችን ይወዳልና፡፡ وَأَحْسِنُوا ۛ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُحْسِنِينَ
5፥87 ወሰንንም አትለፉ፡፡ አላህ ወሰን አላፊዎችን አይወድምና፡፡ وَلَا تَعْتَدُوا ۚ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْمُعْتَدِينَ
ሰው ነጻ ፈቃድ ባይኖረው ኖሮ መሥራት እና አለመሥራት ዐቅም እና ችሎታ የሌለውን ነገር "ሥራ" እና "አትሥራ" የሚል ሙሐከማት መስጠቱ ትርጉም አይኖረውም ነበር፥ አሏህ በጎ ሠሪዎችን የሚወደው በሚሠሩት በጎ ሥራ ሲሆን እና ወሰን አላፊዎችን የሚጠላው ደግሞ በሚተላለፉት መጥፎ ሥራ ነው። ሰው በተሰጠው የማድረግ እና ያለማድረግ ነጻ ፈቃድ በዱንያህ ይፈተናል፦
102፥8 ከዚያም ከጸጋችሁ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ። ثُمَّ لَتُسْأَلُنَّ يَوْمَئِذٍ عَنِ النَّعِيمِ
6፥165 እርሱም ያ በምድር ምትኮች ያደረጋችሁ በሰጣችሁም ጸጋ ሊፈትናችሁ ከፊላችሁን ከከፊሉ በላይ በደረጃዎች ከፍ ያደረገ ነው፡፡ وَهُوَ الَّذِي جَعَلَكُمْ خَلَائِفَ الْأَرْضِ وَرَفَعَ بَعْضَكُمْ فَوْقَ بَعْضٍ دَرَجَاتٍ لِّيَبْلُوَكُمْ فِي مَا آتَاكُمْ ۗ إِنَّ رَبَّكَ سَرِيعُ الْعِقَابِ وَإِنَّهُ لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ

"ነዒም" نَّعِيمِ ማለት "ጸጋ" ማለት ሲሆን ይህ የተሰጠን ጸጋ አድርግ የተባለውን የመታዘዝዝና ያለመታዘዝ፥ አታድርግ የተባለውን የመከልከልና ያለመከልከል ፈተና ስለሆነ "በሰጣችሁም ጸጋ ሊፈትናችሁ" ይለናል፥ አምላካችን አሏህ በከለከለን ክፉ ነገር እና ባዘዘን መልካም ነገር ይፈትነናል፦
21፥35 ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፡ ለመፈተንም በክፉም በበጎም እንፈትናችኋለን፡፡ ወደ እኛም ትመለሳላችሁ፡፡ كُلُّ نَفْسٍ ذَائِقَةُ الْمَوْتِ ۗ وَنَبْلُوكُم بِالشَّرِّ وَالْخَيْرِ فِتْنَةً ۖ وَإِلَيْنَا تُرْجَعُونَ

"አምር" أَمْر ማለት "ትእዛዝ" ማለት ሲሆን ሙፍረዳትን ያመለክታል፥ "ነህይ" نَهْي ማለት "ዕቀባ" ማለት ሲሆን ሙሐረማትን ያመለክታል። እንስሳ አምር እና ነህይ ስለሌላቸው ልቅ ናቸው፥ ሰው ግን ነጻ ፈቃድ ስላለው በሚሠራው መልካም ሥራ ስለሚነዳ እና በሚሠራው ክፉ ሥራ ስለሚቀጣ ልቅ ሆኖ አልተተወም፦
75፥36 ሰው ልቅ ኾኖ መተውን ያስባልን? أَيَحْسَبُ الْإِنسَانُ أَن يُتْرَكَ سُدًى

ሰው አማኝ እና ከሃዲ፣ ታዛዥ እና አመጸኛ፣ ሙሥሊም እና ሙሽሪክ መሆኑ በራሱ ሰው በገዛ ነጻ ፈቃዱ የሚወስን ፍጡር መሆኑ አመላካችን ነው፦
2፥35 «አደም ሆይ! አንተ ከነሚስትህ በገነት ተቀመጥ፤ ከርሷም በፈለጋችሁት ስፍራ በሰፊው ተመገቡ፤ ግን ይህችን ዛፍ አትቅረቡ፤ ከበደለኞች ትኾናላችሁና» አልንም፡፡ وَقُلْنَا يَا آدَمُ اسْكُنْ أَنتَ وَزَوْجُكَ الْجَنَّةَ وَكُلَا مِنْهَا رَغَدًا حَيْثُ شِئْتُمَا وَلَا تَقْرَبَا هَـٰذِهِ الشَّجَرَةَ فَتَكُونَا مِنَ الظَّالِمِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "በፈለጋችሁት" ለሚለው የገባው ቃል "ሺእቱማ" شِئْتُمَا ሲሆን "በፈቀዳችሁ" ማለት ነው፥ አደም እና ሐዋህ "ፈቃድ" እንዳላቸው አመላካች ነው።"በሰፊው" ለሚለው የገባው ቃል "ረገድ" رَغَد ሲሆን "ነጻ" ማለት ነው፥ መመገብ እና አለመመገብ ነጻ ፈቃድ እንዳላቸው አመላካች ነው። "ተመገቡ" ለሚለው የገባው ቃል "ኩላ" كُلَا ሲሆን "ሲጋቱል አምር" صِيغَة اَلْأَمْر ማለት "ትእዛዛዊ ግሥ"imperative verb" ነው። "አትቅረቡ" ለሚለው የገባው ቃል "ላ ተቅረባ" لَا تَقْرَبَا ሲሆን "ተሕሪም" تَحْرِيم ማለት "ክልከላ" '"ዕቀባ" ነው።
ስለዚህ በሰው የሚሆነው መልካም እና ክፉ ነገር ሁሉ አሏህ ፈቅዶ ነው፥ ሰው የማመን ሆነ የመካድ ነጻ ፈቃድ አለው፦
18፥29 «እውነቱም ከጌታችሁ ነው፡፡ የፈቀደ ሰው ይመን፤ የፈቀደ ሰው ይካድ» በላቸው፡፡ وَقُلِ الْحَقُّ مِن رَّبِّكُمْ ۖ فَمَن شَاءَ فَلْيُؤْمِن وَمَن شَاءَ فَلْيَكْفُر

"ፈቀደ" ለሚለው የግሥ መደብ የገባው ቃል "ሻአ" شَاءَ ሲሆን ሰው እንደ እንስሳ ደመነፍስ ወይም እንደ ቁስ ግዑዝ ነገር ሳይሆን በአሏህ ፈቃድ ሥር ነጻ ፈቃድ ያለው ፍጡር መሆኑን ያሳያል፦
10፥100 ለማንኛዋም ነፍስ በአላህ ፈቃድ ቢሆን እንጂ ልታምን ችሎታ የላትም፡፡ وَمَا كَانَ لِنَفْسٍ أَن تُؤْمِنَ إِلَّا بِإِذْنِ اللَّهِ
25፥57 «በእርሱ ላይ ዋጋን በፍጹም አልጠይቃችሁም፡፡ ግን ወደ ጌታው መልካም መንገድን ለመያዝ "የፈቀደ" ሰው ይሥራ» በላቸው፡፡ قُلْ مَا أَسْأَلُكُمْ عَلَيْهِ مِنْ أَجْرٍ إِلَّا مَن شَاءَ أَن يَتَّخِذَ إِلَىٰ رَبِّهِ سَبِيلًا
76፥29 ይህቺ መገሠጫ ናት፡፡ "የፈቀደ" ሰው ወደ ጌታው መንገድን ይይዛል፡፡ إِنَّ هَـٰذِهِ تَذْكِرَةٌ ۖ فَمَن شَاءَ اتَّخَذَ إِلَىٰ رَبِّهِ سَبِيلًا

አሁንም ሁለቱም አናቅጽ ላይ "ፈቀደ" ለሚለው የግሥ መደብ የገባው ቃል "ሻአ" شَاءَ ሲሆን ሰው እንዲያምን ሆነ እንዲክድ አሏህ መፍቀዱን ያሳያል፥ ሰው የራሱ ፍላጎት አለው። በፍላጎቱ አኺራን ወይም ዱንያን መምረጥ ይችላል፦
42፥20 በሥራው የኋለኛይቱን ዓለም አዝመራ የሚፈልግ የኾነ ሰው ለእርሱ በአዝመራው ላይ እንጨምርለታለን፡፡ የቅርቢቱንም ዓለም አዝመራ የሚፈልግ የኾነ ሰው ከእርሷ የተወሰነለትን ብቻ እንሰጠዋለን፡፡ ለእርሱም በኋለኛይቱ ዓለም ምንም ፋንታ የለውም፡፡ مَن كَانَ يُرِيدُ حَرْثَ الْآخِرَةِ نَزِدْ لَهُ فِي حَرْثِهِ ۖ وَمَن كَانَ يُرِيدُ حَرْثَ الدُّنْيَا نُؤْتِهِ مِنْهَا وَمَا لَهُ فِي الْآخِرَةِ مِن نَّصِيبٍ

"አጅር" أَجْر ማለት "ሽልማት" "ትሩፋት" "ምንዳ" ማለት ሲሆን "ዐዛብ" عَذَاب ማለት ደግሞ "ቅጣት" "ክስረት" "ፍዳ" ማለት ነው፥ አሏህ የፍርዱ ቀን በአምስቱ አሕካም የሽልማት እና የቅጣት ዋጋ እንዲሁ የምንዳ እና የፍዳ ዋጋ ለሰው የሚከፍለው ሰው ነጻ ፈቃድ ስላለው ነው። "ጀዛ" جَزَى ማለት "ዋጋ" ማለት ሲሆን ፍጥረትን ፈጥሮ እና አምስቱን አሕካም ሰጥቶ የሚያስተናብረው ጌታ በፍርዱ ቀን ለሁሉም ዋጋ የሚሰጠው ፍትኸኛ ስለሆነ ነው፦
76፥22 «ይህ በእርግጥ ለእናንተ ዋጋ ኾነ፡፡ ሥራችሁም ምስጉን ኾነ» ይባላሉ፡፡ إِنَّ هَـٰذَا كَانَ لَكُمْ جَزَاءً وَكَانَ سَعْيُكُم مَّشْكُورًا
9፥95 ይሠሩትም በነበሩት ዋጋ መኖሪያቸው ገሀነም ነው፡፡ وَمَأْوَاهُمْ جَهَنَّمُ جَزَاءً بِمَا كَانُوا يَكْسِبُونَ

ኢንሻሏህ ስለ መርተበቱል ኸልቅ በክፍል አራት እንዳስሳለን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
መራቲቡል ቀደር

ክፍል አራት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

39፥62 አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው፡፡ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ

ነጥብ አራት
"መርተበቱል ኸልቅ"
"ሸይእ" شَيْء ማለት "ነገር"thing" ማለት ሲሆን "ዘመካን" زَمَكَان ነው፥ "ዘማን" زَمَان ማለት "ጊዜ"time" ማለት ሲሆን "መካን" مَكَان ማለት ደግሞ "ቦታ"space" ማለት ነው። አምላካችን አሏህ ምንም ነገር ሳይኖር ነበረ፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 59, ሐዲስ 2
ዒምራም ኢብኑ ሑሰይን እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" አሉ፦ "ምንም ነገር ሳይኖር አሏህ ነበረ"። عَنْ عِمْرَانَ بْنِ حُصَيْنٍ، قَالَ إِنِّي عِنْدَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم كَانَ اللَّهُ وَلَمْ يَكُنْ شَىْءٌ غَيْرُهُ

"ኸልቅ" خَلْق የሚለው ቃል "ኸለቀ" خَلَقَ ማለትም "ፈጠረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መፍጠር" ማለት ነው፦
7፥54 ንቁ! መፍጠር እና ማዘዝ የእርሱ ብቻ ነው፡፡ የዓለማት ጌታ አላህ ክብሩ ላቀ፡፡ أَلَا لَهُ الْخَلْقُ وَالْأَمْرُ ۗ تَبَارَكَ اللَّهُ رَبُّ الْعَالَمِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "መፍጠር" ለሚለው የገባው ቃል "ኸልቅ" خَلْق እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል። አሏህ "ኻሊቅ" خَالِق‎ ማለትም "ፈጣሪ" ሲሆን ነገር ሁሉ "መኽሉቅ" مَخْلُوق‎ ማለትም "ፍጡር" ነው፦
39፥62 አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው፡፡ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ

"ሲፍር" صِفْر የሚለው ቃል "ሶፊረ" صَفِرَ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "አልቦ ነገር" "ምንም ነገር"nothing" ማለት ነው፥ አምላካችን አሏህ "ነገርን" እምኀበ አልቦ ኀበቦ ማለትም ካለመኖር ወደ መኖር "ኩን" كُن እያለ ፈጠረው፦
16፥40 ለማንኛውም "ነገር" መኾኑን በሻነው ጊዜ ቃላችን ለእርሱ "ኹን" ማለት ብቻ ነው፥ ወዲውም ይኾናል፡፡ إِنَّمَا قَوْلُنَا لِشَيْءٍ إِذَا أَرَدْنَاهُ أَن نَّقُولَ لَهُ كُن فَيَكُونُ

"ዐመል" عَمَل ማለት "ሥራ"action" ማለት ሲሆን አሏህ የፈጠረው ሰውን ብቻ ሳይሆን ሰው የሚሠራውን ሥራ ጭምር ነው። "ዐመል" عَمَل አራት ነገር ያቅፋል፥ እርሱም፦ መሺኣህ፣ ማዳህ፣ መካን እና ዘማን ናቸው።
1ኛ. "መሺኣህ"
አንድ ሰው መልካምም ይሁን ክፉ ሥራ ሢሠራ "መሺኣህ" مَشِئَة ማለትም "ነጻ ፈቃድ"free will" አለው፥ ይህንን መሺዓህ የፈጠረው አሏህ ነው።
2ኛ. "ማዳህ"
አንድ ሰው መልካምም ይሁን ክፉ ሥራ የሚሠራበት "ማዳህ" مَادَّة ማለትም "ቁስ"matter" አለው፥ ለምሳሌ አንድ ሰው በጥፊ ሲማታ የመታበት እጅ ወይም በእርግጫ ሲራገጥ የተራገጠበት እግር ቁስ ሲሆን የፈጠረው አሏህ ነው።
3ኛ. "መካን"
አንድ ሰው መልካምም ይሁን ክፉ ሥራ የሚሠራበት "መካን" مَكَان ማለትም "ቦታ"space" አለው፥ ይህንን ቦታ የፈጠረው አሏህ ነው።
4ኛ. "ዘማን"
አንድ ሰው መልካምም ይሁን ክፉ ሥራ የሚሠራበት "ዘማን" زَمَان ማለትም "ጊዜ"time" አለው፥ ይህንን ጊዜ የፈጠረው አሏህ ነው።
አምላካችን አሏህ የፈጠረው እኛንም ሥራችንንም ነው፦
37፥96 አላህ እናንተን እና የምትሠሩትን የፈጠረ ሲኾን፡፡ وَاللَّهُ خَلَقَكُمْ وَمَا تَعْمَلُونَ

"የምትሠሩትን የፈጠረ" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! "የምትሠሩትን" ለሚለው የገባው ቃል "ተዕመሉነ" تَعْمَلُونَ መሆኑ በራሱ ዐመልን የፈጠረ አሏህ መሆኑን ያሳያል። አምላካችን አሏህ ኑሕን፦ "መርከቢቱን ሥራ" ብሎ ካዘዘው በኃላ ኑሕ የሠራውን መርከብ "ፈጠርንላቸው" በማለት ሰው የሚሠራው ሥራ እርሱ እንደፈጠረ ይናገራል፦
11፥37 በጥበቃችን እና በትእዛዛችንም ሆነህ መርከቢቱን ሥራ፡፡ وَاصْنَعِ الْفُلْكَ بِأَعْيُنِنَا وَوَحْيِنَا
36፥42 ከመሰሉም በእርሱ የሚሳፈሩበትን ለእነርሱ ፈጠርንላቸው፡፡ وَخَلَقْنَا لَهُم مِّن مِّثْلِهِ مَا يَرْكَبُونَ
የዘመናችን መጓጓዣ"transport" የሆኑትን የአየር መጓጓዣ አይሮፕላን፣ የየብስ መጓጓዣ አውቶ ሞቢል መኪና እና የባሕር መጓጓዣ ባለ ሞተር"engine" መርከብ የሠሩት ሰዎች ሆነው ሳለ አምላካችን አሏህ በወደፊት ግሥ፦ "የማታውቁትንም ድንቅ ነገር ይፈጥራል" በማለት ሰዎች የሠሩትን እንደሚፈጥር ይናገራል፦
16፥8 ፈረሶችንም፣ በቅሎዎችንም፣ አህዮችንም ልትጓዙበት እና ልታጌጡባቸው ፈጠረላችሁ፡፡ የማታውቁትንም ድንቅ ነገር ይፈጥራል፡፡ وَالْخَيْلَ وَالْبِغَالَ وَالْحَمِيرَ لِتَرْكَبُوهَا وَزِينَةً ۚ وَيَخْلُقُ مَا لَا تَعْلَمُونَ

"ይፈጥራል" ለሚለው የገባው ቃል "የኽሉቁ" يَخْلُقُ ሲሆን የወደፊት ግሥ ሙሥተቅበል ነው፥ የአየር መጓጓዣ አይሮፕላን የተሠራው እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 1799 ድኅረ-ልደት የንስር ወፍ ንድፍ ታይቶ ነው፣ የየብስ መጓጓዣ አውቶ ሞቢል መኪና የተሠራውበ 1768 ድኅረ-ልደት የፈረስ ንድፍ ታይቶ ሲሆን በተመሳሳይ ባቡር የተሠራው በ 1550 ድኅረ-ልደት የአባጨጓሬ ንድፍ ታይቶ ነው፣ የባሕር መጓጓዣ ባለ ሞተር መርከብ የተሠራው 1805 ድኅረ-ልደት የዶልፊን ዓሣ ንድፍ ታይቶ ነው። የሰው መልካም ሥራ ያለ ኢማን ከተሠራ በፍርዱ ቀን ምንዳ አያስመነዳም፥ የሰው ክፉ ሥራው ባለማወቅ ከተሠራ "ዑዝር ቢል-ጀህል" عُذْر بِالجَهْل ነውና በፍርዱ ቀን ቅጣት አያስቀጣም፦
14፥18 የእነዚያ በጌታቸው የካዱት ሰዎች ምሳሌ መልካም ሥራዎቻቸው በነፋሻ ቀን ነፋስ በእርሱ እንደ በረታችበት አመድ ነው፡፡ በሠሩት ሥራ በምንም ላይ ሊጠቀሙ አይችሉም፡፡ ይህ እርሱ ሩቅ ጥፋት ነው፡፡ مَّثَلُ الَّذِينَ كَفَرُوا بِرَبِّهِمْ ۖ أَعْمَالُهُمْ كَرَمَادٍ اشْتَدَّتْ بِهِ الرِّيحُ فِي يَوْمٍ عَاصِفٍ ۖ لَّا يَقْدِرُونَ مِمَّا كَسَبُوا عَلَىٰ شَيْءٍ ۚ ذَٰلِكَ هُوَ الضَّلَالُ الْبَعِيدُ
33፥5 በእርሱ በተሳሳታችሁበትም ነገርም በእናንተ ላይ ኃጢአት የለባችሁም፥ ግን ልቦቻችሁ ዐዉቀው በሠሩት ኃጢአት አለባችሁ”። አላህም መሃሪ አዛኝ ነው። وَلَيْسَ عَلَيْكُمْ جُنَاحٌۭ فِيمَآ أَخْطَأْتُم بِهِۦ وَلَٰكِن مَّا تَعَمَّدَتْ قُلُوبُكُمْ ۚ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورًۭا رَّحِيمًا

ከሓድያን በሠሩት መልካም ሥራ የፍርዱ ቀን መጠቀም የማይችሉት ኢማን ስለሌላቸው ሲሆን የሚሳሳቱት ደግሞ የሚሠሩት መጥፎ ሥራ ኃጢአት ሆኖ የማይቆጠርባቸው ያለ ማወቅ ስለሠሩት ነው፥ "ኃጢአት" ማለት አሏህ "አታድርጉ" ያለውን መጥፎ ሥራ ሰምቶ እና ዐውቆ መተላለፍ ነው። የሰው መልካም ሥራ የሚያስመነዳው እና መጥፎ ሥራው የሚያስቀጣው በኒያ በተሠራው ሥራ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 47
ዑመር እንደተረከው፦ "የአሏህ መልክተኛ"ﷺ" እንዲህ ብለዋል፦ "ሥራ የሚለካው በኒያህ ነው፥ ማንኛውምንም ሰው የነየተውን ያገኛል። عَنْ عُمَرَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ الأَعْمَالُ بِالنِّيَّةِ، وَلِكُلِّ امْرِئٍ مَا نَوَى

"ኒያህ" نِيَّة የሚለው ቃል "ነዋ" نَوَى ማለትም "ወጠነ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ውጥን"intention" ማለት ነው፥ ኒያህ በልብ ውስጥ የሚቀመጥ እና አሏህ ብቻ የሚያውቀው ጉዳይ ነው። የፍርዱ ቀን ሰዎች ተቀስቅሰው ምንዳ እና ፍዳ የሚበየንባቸው በነየቱት ኒያህ ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 4370
አቢ ሁራይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ሰዎች ተቀስቅሰው የሚበየንባቸው በነየቱት ነው"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏:‏ ‏ “‏ إِنَّمَا يُبْعَثُ النَّاسُ عَلَى نِيَّاتِهِمْ

አምላካችን አሏህ በመልካም ኒያህ ነይተው መልካም ሥራ በመሥራት ከሚመነዱት ያድርገን! አሚን። ይህንን ተከታታይ የቀደር ትምህርት ያገኘነው ከኡሥታዛችን ሷዲቅ(አቡ ሃይደር) ነውና መልካም ሥራውን ሁሉ በኢኽላስ ይቀበለው! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የተለያዩ ትምህርቶችን በድምጽ ማግኘት ከፈለጋችሁ ይህንን ሊንክ አስፈንጥሩ፦ https://tttttt.me/abuhyder
ተሀጁድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

73፥2 ሌሊቱን ሁሉ ጥቂት ሲቀር ቁም። قُمِ اللَّيْلَ إِلَّا قَلِيلًا

"ተሀጁድ" تَّهَجُّد የሚለው ቃል "ተሀጀደ" تَهَجَّدَ ማለትም "ተነሳ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መነሳት" ማለት ነው፥ ተሀጁድ በቁርኣን ውስጥ ተጨማሪ ሶላት ነው፦
17፥79 ከሌሊትም ለአንተ ተጨማሪ የኾነችን ሶላት በእርሱ በቁርኣን ስገድ፡፡ ጌታህ ምስጉን በኾነ ስፍራ በእርግጥ ያቆምሃል፡፡ وَمِنَ اللَّيْلِ فَتَهَجَّدْ بِهِ نَافِلَةً لَّكَ عَسَىٰ أَن يَبْعَثَكَ رَبُّكَ مَقَامًا مَّحْمُودًا

እዚህ አንቀጽ ላይ "ስገድ" ለሚለው የገባው ቃል "ተሀጀድ" تَهَجَّدْ ሲሆን "ተነስ" ማለት ነው፥ "ተሀጁድ" تَّهَجُّد የሚለው ቃል በግልጽ በሐዲስ ላይ መጥቷል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 19, ሐዲስ 17
ሑዘይፋህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" ከሌሊት ተሀጁድ በሚቆሙበት ጊዜ በሢዋክ ጥሳቸውን ያነጹ ነበር"። عَنْ حُذَيْفَةَ ـ رضى الله عنه ـ أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم كَانَ إِذَا قَامَ لِلتَّهَجُّدِ مِنَ اللَّيْلِ يَشُوصُ فَاهُ بِالسِّوَاكِ‏.‏

"ቂያሙል ለይል" قِيَام اللَّيْل አጠቃላይ የሌሊት ሶላት የሚያመለክት ሲሆን ሌሊቱን ጥቂት ሲቀር የሚቆም ነው፥ ቂያሙል ለይል ሶላትን መቆም፣ ቁርኣን መቅራት እና ዚክር ማድረግ የሚይዝ ነው። የሌሊት መነሳት እርሷ ሕዋሳትን እና ልብን ለማስማማት በጣም ብርቱ ናት፥ ለማንበብም ትክክለኛ ናት፦
73፥2 ሌሊቱን ጥቂት ሲቀር ቁም። قُمِ اللَّيْلَ إِلَّا قَلِيلًا
73፥3 ግማሹን ቁም ወይም ከእርሱ ጥቂትን ቀንስ፡፡ نِّصْفَهُ أَوِ انقُصْ مِنْهُ قَلِيلًا
73፥4 ወይም በእርሱ ላይ ጨምር፡፡ ቁርኣንንም በዝግታ ማንበብን አንብብ፡፡ أَوْ زِدْ عَلَيْهِ وَرَتِّلِ الْقُرْآنَ تَرْتِيلًا
73፥6 የሌሊት መነሳት እርሷ ሕዋሳትን እና ልብን ለማስማማት በጣም ብርቱ ናት፡፡ ለማንበብም ትክክለኛ ናት፡፡ إِنَّ نَاشِئَةَ اللَّيْلِ هِيَ أَشَدُّ وَطْئًا وَأَقْوَمُ قِيلًا

ሙተቂን የሚባሉት የአሏህ ባሮች በጀነት ውስጥ የሚሆኑት ሙሕሢኒን ስለሆኑ ነው። ሙተቂን ከሌሊቱ ጥቂትን ብቻ ይተኙ ነበሩ፥ በሌሊቱ መጨረሻዎችም እነርሱ ምሕረትን ይለምናሉ፦
51፥15 አላህን ፈሪዎቹ በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡ إِنَّ الْمُتَّقِينَ فِي جَنَّاتٍ وَعُيُونٍ
51፥16 ያንን ጌታቸው የሰጣቸውን ተቀባዮች ኾነው በገነት ውስጥ ይኾናሉ፡፡ እነርሱ ከዚህ በፊት መልካም ሠሪዎች ነበሩና፡፡ آخِذِينَ مَا آتَاهُمْ رَبُّهُمْ ۚ إِنَّهُمْ كَانُوا قَبْلَ ذَٰلِكَ مُحْسِنِينَ
51፥17 ከሌሊቱ ጥቂትን ብቻ ይተኙ ነበሩ፡፡ كَانُوا قَلِيلًا مِّنَ اللَّيْلِ مَا يَهْجَعُونَ
51፥18 በሌሊቱ መጨረሻዎችም እነርሱ ምሕረትን ይለምናሉ፡፡ وَبِالْأَسْحَارِ هُمْ يَسْتَغْفِرُونَ

የአልረሕማንም ባሮች በቂያሙል ለይል ለጌታቸው በግንባራቸው ተደፊዎችና ቋሚዎች ኾነው የሚያድሩት ናቸው፦
25፥63 የአልረሕማንም ባሮች እነዚያ በምድር ላይ በዝግታ የሚኼዱት እና ባለጌዎችም በክፉ ባነጋገሩዋቸው ጊዜ ሰላም የሚሉት ናቸው፡፡ وَعِبَادُ الرَّحْمَـٰنِ الَّذِينَ يَمْشُونَ عَلَى الْأَرْضِ هَوْنًا وَإِذَا خَاطَبَهُمُ الْجَاهِلُونَ قَالُوا سَلَامًا
25፥64 እነዚያም ለጌታቸው በግንባራቸው ተደፊዎች እና ቋሚዎች ኾነው የሚያድሩት ናቸው፡፡ وَالَّذِينَ يَبِيتُونَ لِرَبِّهِمْ سُجَّدًا وَقِيَامًا
ቂያሙል ለይል ከመተኛታችን በፊት እና ተኝተን ከተነሳንበት ያለውን ሶላት ሊያመለክት ይችላል፥ ተሀጁድ ግን ከእንቅልፋችን ተነስተን ሌሊቱን የምንቆመው ሶላት ነው። "ተራዊሕ" تَرَاوِيح ደግሞ በረመዷን ከዒሻእ በኃላ ከሌሊቱ የመጀመሪያው ክፍል የሚሰገድ ሲሆን ቂያሙል ረመዷን ነው፥ ተሀጁድ ከሌሊቱ ግማሽ ወይም መጨረሻ ሲሰገድ "ሶላቱል ለይል" صَلاَةُ اللَّيْل ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 48 ሐዲስ 210
አቡ ኡማህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ ዐምር ኢብኑ ዐበሣህ ነቢዩ"ﷺ" ሲናገሩ ሰምቶ እንደነገረኝ እርሳቸው እንዲህ አሉ፦ "በሌሊቱ የመጨረሻ ክፍል ጌታ ለአምላኪው ቅርብ ነው"። قَالَ سَمِعْتُ أَبَا أُمَامَةَ، رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ يَقُولُ حَدَّثَنِي عَمْرُو بْنُ عَبَسَةَ، أَنَّهُ سَمِعَ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ "‏ أَقْرَبُ مَا يَكُونُ الرَّبُّ مِنَ الْعَبْدِ فِي جَوْفِ اللَّيْلِ الآخِرِ ‏
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 5, ሐዲስ 517
ዑመር እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ሶላቱል ለይል ሁለት ሁለት ነው"። عَنِ ابْنِ عُمَرَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏ "‏ صَلاَةُ اللَّيْلِ مَثْنَى مَثْنَى ‏"‏ ‏.‏

ሶላቱል አት-ተሀጁድ ላይ "ሶላቱ አሽ-ሸፍዕ" صَلاَةُ الشَّفْع ሁለት ሁለት ረክዓህ ሲሆን "ሶላቱል ዊትር" صَلاَةُ الوِتْر ደግሞ አንድ ረክዓህ ነው፥ "ሸፍዕ" شَّفْع ማለት "ጥንድ"even" ማለት ሲሆን "ዊትር" وِتْر ማለት ደግሞ "ነጠላ"odd" ማለት ነው።
፨ሶላቱ አሽ-ሸፍዕ የመጀመሪያው ረክዓህ ሱረቱል ፋቲሓህ ተቀርቶ ሱረቱል ኢኽላስ እና ሱረቱ አን-ናስ ሲቀራ ሁለተኛው ረክዓህ ደግሞ ሱረቱል ፋቲሓህ ተቀርቶ ሱረቱል ኢኽላስ እና ሱረቱል ፈለቅ ይቀራል፥ ከዚያ ሁለት ሁለት እያለ እስከ ስምንት ወይም አሥር መሄድ ይችላል።
፨ሶላቱል ዊትር ሱረቱል ፋቲሓህ ተቀርቶ፣ ሱረቱል ኢኽላስ ሦስት ጊዜ ተቀርቶ ከዚያ ሱረቱል ፈለቅ እና ሱረቱ አን-ናስ ይቀራል፥ ሶላቱል ዊትር የተሀጁድ መዝጊያ ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 6, ሐዲስ 184
ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "የሌሊት የመጨረሻ ሶላታችሁን በዊትር አድርጉ"። عَنِ ابْنِ عُمَرَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ اجْعَلُوا آخِرَ صَلاَتِكُمْ بِاللَّيْلِ وِتْرًا ‏"‏ ‏.‏
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 6, ሐዲስ 158
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ከሌሊቱ እስከ መጨረሻው ሶላቱል ዊትር ድረስ ይሰግዱ ነበር"። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يُصَلِّي مِنَ اللَّيْلِ حَتَّى يَكُونَ آخِرَ صَلاَتِهِ الْوِتْرُ ‏.‏

ሶላቱል አት-ተሀጁድ ከፍተኛ ረክዓህ አሥራ ሦስት ረክዓህ የሚሆነው ሁለት ረከዓህ ከዚያ ሁለት ሁለት ሁለት ሁለት ሁለት እያለ አሥር ሲሆን እና በዊትር ሲቋጭ ነው፥ አነስተኛው ደግሞ ሁለት ረክዓህ ከዚያ ሁለት ሲሆን እና በዊትር ሲቋጭ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 19, ሐዲስ 19
ኢብኑ ዐባሥ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "በለይል የነቢዩ"ﷺ" ሶላት አሥራ ሦስት ረክዓህ ነበር"። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ كَانَ صَلاَةُ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم ثَلاَثَ عَشْرَةَ رَكْعَةً‏.‏ يَعْنِي بِاللَّيْلِ‏.‏
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 19, ሐዲስ 21
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ "ነቢዩ"ﷺ" ከሌሊቱ አሥራ ሦስት ረክዓህ ዊትርን ጨምሮ ይሰግዱ ነበር"። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ قَالَتْ كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم يُصَلِّي مِنَ اللَّيْلِ ثَلاَثَ عَشْرَةَ رَكْعَةً مِنْهَا الْوِتْرُ.‏
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 19, ሐዲስ 18
ዐብደሏህ ኢብኑ ዑመር"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "አንድ ሰውም፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" ሆይ! ሶላቱል ለይል እንዴት ነው? አላቸው፥ እርሳቸውም፦ "ሁለት ረክዓህ በሁለት ረክዓህ ይከተላል፥ ጎህ በተቃረብክ ጊዜ በዊትር ቋጭ"። أَنَّ عَبْدَ اللَّهِ بْنَ عُمَرَ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ إِنَّ رَجُلاً قَالَ يَا رَسُولَ اللَّهِ، كَيْفَ صَلاَةُ اللَّيْلِ قَالَ ‏ "‏ مَثْنَى مَثْنَى، فَإِذَا خِفْتَ الصُّبْحَ فَأَوْتِرْ بِوَاحِدَةٍ ‏"‌‏.‏

አምላካችን አሏህ ሶላቱል አት-ተሀጁድ ከሚቆሙ ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የኢሥላም ትንሳኤ

"ትንሳኤ" ማለት በፍካሬአዊ አነጋገር አንድ የተዳከመ ነገር ተመልሶ ማንሰራራት ነው፥ የኢሥላም ትንሳኤ ማለት ያ ተዳክሞ የነበረው የኺላፋው ጊዜ፣ ያ የወርቃማው ጊዜ፣ ያ የሸሪዓው ጊዜ ተመልሶ ማንሰራራት ነው። ኢሥላም ሁሉንም ዘር፣ ብሔር፣ ዘውግ፣ አገር ዐቃፊ እና አካታች እንጂ ነቃፊ እና አግላይ አይደለም፥ ሙሥሊም የአንድ ብሔር ወይም የአንድ ዘውግ አሊያም የአንድ አገር ትንሳኤ ተስፋ በፍጹም አያረግም። እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ፥ ነገር ግን ከሌላው ኬንያዊ፣ ሱማሌያዊ፣ ህንዳዊ፣ ኤርትራዊ ወዘተ.. አልበልጥም። እንግዲያውስ ዘረኝነት ማለት የራስን አተልቆ የሌላውን ዘር፣ ብሔር፣ ዘውግ፣ አገር ማሳነስ ነው፥ ሙሥሊም በዘረኝነት ግማት ከጠነባ የምር የአሏህ ገመድ ከእጁ አፈትልኳል። ኢሥላም ዓለም ዐቀፍ ሃይማኖት እንደመሆኑ መጠን ሁሉንም የሰው ልጆች በሐቅ እና በፍትሕ የሚጠቀልልበት ጊዜ ኢንሻሏህ ቅርብ ነው።

ደውለቱ አሽ-ሸሪዓህ ባቂያህ!

አሏህ በቴኦክራሲ የሚመራውን ሸሪዓዊ መንግሥት በማምጣት ነስሩን ያቅርብልን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom
ዘካቱል ፊጥር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

41፥7 ለእነዚያ ዘካን ለማይሰጡት እነርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም እነርሱ ከሓዲዎች ለኾኑት ወዮላቸው፡፡ الَّذِينَ لَا يُؤْتُونَ الزَّكَاةَ وَهُم بِالْآخِرَةِ هُمْ كَافِرُونَ

“ዘካህ” زَكَاة ጥቅላዊ የግዴታ ምፅዋት ማለት ሲሆን የዘካህ ብዙ ቁጥር “ዘካት” زَكَوَات ሲሆን በተናጥል ዘካት በሁለት ይከፈላል፥ እነርሱም “ዘካቱል ማል” زَكَاة المَال እና “ዘካቱል ፊጥር” زَكَاة الفِطْر ናቸው። “ፊጥር” فِطْر ማለት “ፆም መግደፊያ” ማለት ሲሆን የፊጥር ብዙ ቁጥር ደግሞ “ፉጡር” فُطُور ነው፥ የረመዷን ፆም ማብቂያ በዓል እራሱ “ዒዱል ፊጥር” عِيدُ ٱلْفِطْر ይባላል። “ዘካቱል ፊጥር” زَكَاة الفِطْر ደግሞ ለመሣኪን በዒዱል ፊጥር ቀን ለማስፈጠሪያነት የሚውል ገንዘብ ነው፥ “መሣኪን” مَسَاكِين ማለት የዕለት ጉርስ የዓመት ልብስ የሌላቸው “ነዳያን” ማለት ነው። “ለግው” لَّغْو ማለት “ውድቅ ንግግር” ማለት ሲሆን “ረፈስ” رَّفَث ማለት ደግሞ “ስሜት ቀስቃሽ ንግግር” ማለት ነው፥ ዘካቱል ፊጥር ለፆመኛ ውድቅ ንግግር እና ስሜት ቀስቃሽ ንግግር ማፅጃ እንዲሁ ለመሣኪን መብል ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 45
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” ዘካቱል ፊጥርን ለፆመኛ ለግው እና ረፈስ ማፅጃ እንዲሁ ለመሣኪን መብል እንዲሆን ግዴታ አድርገዋል”። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ فَرَضَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ زَكَاةَ الْفِطْرِ طُهْرَةً لِلصَّائِمِ مِنَ اللَّغْوِ وَالرَّفَثِ وَطُعْمَةً لِلْمَسَاكِينِ .‏

“ግዴታ አድርገዋል” ለሚለው የገባው የግስ መደብ “ፈረዶ” فَرَضَ መሆኑ በራሱ ዘካቱል ፊጥር ፈርድ መሆኑ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፥ “ፈርድ” فَرْض የሚለው ቃል እራሱ “ፈረዶ” فَرَضَ ማለትም “ግዴታ አደረገ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ግዴታ” ማለት ነው። ነዳያን ሲቀሩ ይህ ገንዘብ ወደ ሶላቱል ዒድ ከመሄዳችን በፊት መክፈል በሁሉም ሙሥሊም ላይ የተጣለ ፈርድ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 24, ሐዲስ 109
አቢ ዑመር”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “ነቢዩ”ﷺ” ዘካቱል ፊጥርን ሰዎች ወደ ዒድ ሶላት ከመሄዳቸው በፊት እንዲከፈል አዘዋል”። عَنِ ابْنِ عُمَرَ ـ رضى الله عنهما ـ أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم أَمَرَ بِزَكَاةِ الْفِطْرِ قَبْلَ خُرُوجِ النَّاسِ إِلَى الصَّلاَةِ‏.‏
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 24, ሐዲስ 104
አቢ ዑመር”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” ከሙሥሊም በሁሉም ተገልጋይ ሆነ አገልጋይ አሊያም ወንድ ሆነ ሴት ላይ ከተምር አንድ ሷዕ ወይም ከገብስ አንድ ሷዕ ዘካቱል ፊጥር እንዲከፈል ግዴታ አድርገዋል”። عَنِ ابْنِ عُمَرَ ـ رضى الله عنهما ـ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَرَضَ زَكَاةَ الْفِطْرِ صَاعًا مِنْ تَمْرٍ، أَوْ صَاعًا مِنْ شَعِيرٍ، عَلَى كُلِّ حُرٍّ أَوْ عَبْدٍ، ذَكَرٍ أَوْ أُنْثَى، مِنَ الْمُسْلِمِينَ‏.‏

በሐዲሱ “ሷዕ” صَاع ማለት እና በቁርኣኑ 12፥72 ላይ “ሡዋዕ” صُوَاع ማለት “የእህል መስፈሪያ” ማለት ነው፥ አንድ ሷዕ በክብደት ከ 2.04 እስከ 2.5 kg የሚመዝን ወይም በመጠን በሁለት እጆች 4 እፍኞች ሲሆን ወደ ዓለም ዓቀፍ የመለኪያ ሥርዓት”metric system” ገንዘብ ሲቀየር 5.5 ፓውንድ ይሆናል። በሸቀጥ ገንዘብ ግብይት ዘካቱል ማል የሚወጣው ከብር፣ ከወርቅ እና ከቤት እንስሳት ሲሆን ዘካቱል ፊጥር ደግሞ ከእህል ዓይነት ነው። ዘካን የማይሰጥ “በመጨረሻይቱ ዓለም ከአሏህ ዘንድ መተሳሰብ የለም” ብሎ የሚክድ ሰው ነው፦
41፥7 ለእነዚያ ዘካን ለማይሰጡት እነርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም እነርሱ ከሓዲዎች ለኾኑት ወዮላቸው፡፡ الَّذِينَ لَا يُؤْتُونَ الزَّكَاةَ وَهُم بِالْآخِرَةِ هُمْ كَافِرُونَ

ዘካን ካለመስጠት ከሚያስቀጣ ቅጣት አሏህ ይጠብቀን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አጀል

ክፍል አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

6፥2 እርሱ ያ ከጭቃ የፈጠራችሁ ከዚያም ጊዜን የወሰነ ነው፥ እርሱም ዘንድ የተወሰነ ጊዜ አለ፡፡ هُوَ الَّذِي خَلَقَكُم مِّن طِينٍ ثُمَّ قَضَىٰ أَجَلًا ۖ وَأَجَلٌ مُّسَمًّى عِندَهُ

"አጀል" أَجَل የሚለው ቃል "አጀለ" أَجَّلَ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ጊዜ" ማለት ነው፦
2፥282 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ በዕዳ በተዋዋላችሁ ጊዜ ጻፉት፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا تَدَايَنتُم بِدَيْنٍ إِلَىٰ أَجَلٍ مُّسَمًّى فَاكْتُبُوهُ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ጊዜ" ለሚለው የገባው ቃል "አጀል" أَجَل መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል። አጀል በሁለት ይከፈላል፥ አንደኛው "አጀሉል ሙአለቅ" ሲሆን ሁለተኛ "አጀሉል ሙሠማ" ነው። እነዚህን ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦
6፥2 እርሱ ያ ከጭቃ የፈጠራችሁ ከዚያም ጊዜን የወሰነ ነው፥ እርሱም ዘንድ የተወሰነ ጊዜ አለ፡፡ هُوَ الَّذِي خَلَقَكُم مِّن طِينٍ ثُمَّ قَضَىٰ أَجَلًا ۖ وَأَجَلٌ مُّسَمًّى عِندَهُ

ሰውን ከፈጠረ በኃላ "ሱመ" ثُمَّ የሚለው ቅድመ ተከተል መቀመጡ የጊዜ ቅድመ ተከተልን ያሳያል፥ "ቀዷ" قَضَىٰ የሚለው ቃል "ቀዶ" قَضَى ማለትም "ወሰነ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ውሳኔ" ማለት ነው። ሰው ከተፈጠረ በኃላ ያለው ውሳኔ "ቀዷ ሙአለቅ" قَضَىٰ مُعَلَّق ሲሆን መልአክ መጥቶ "አጀሉል ሙአለቅ" أَجَل المُعَلَّق የሚጽፈው ነው፥ "ሙዐለቅ" مُعَلَّق ማለት "የተንጠለጠለ" ማለት ሲሆን መልአኩ መጥቶ ከሚጽፈው አራት ነገሮች አንዱ አጀሉል ሙአለቅ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 59 ሐዲስ 19
"ከዚያም አሏህ መልአክ ይልክና አራት ቃላትን ሲሳዩን፣ ጊዜውን፣ ሥራውን እና ሐዘኑን ወይም ደስታው እንዲጽፍ ይታዘዛል"። ثُمَّ يَبْعَثُ اللَّهُ مَلَكًا، فَيُؤْمَرُ بِأَرْبَعِ كَلِمَاتٍ، وَيُقَالُ لَهُ اكْتُبْ عَمَلَهُ وَرِزْقَهُ وَأَجَلَهُ وَشَقِيٌّ أَوْ سَعِيدٌ‏

ይህ አጀሉል ሙአለቅ ግለሰቡ በሚያሳየው ነጻ ፈቃድ አሏህን ሊያብሰው ወይም ሊያጸድቀው የሚችል ነገር ነው፦
13፥39 አላህ የሚሻውን ያብሳል፤ ያጸድቃልም፡፡ የመጽሐፉ መሠረትም እርሱ ዘንድ ነው፡፡ يَمْحُو اللَّهُ مَا يَشَاءُ وَيُثْبِتُ ۖ وَعِندَهُ أُمُّ الْكِتَابِ

ከልደት እስከ ሞት እስከሚመጣበት ጊዜ ድረስ ያለው አጀሉል ሙአለቅ ሶደቃህ በመስጠት፣ ወላጆችን በማክበር፣ የጎረቤት ሐቅ በመጠበቅ እንዲሁ ዝምድናን በመቀጠል ዕድሜ ይረዝማል፦
አደቡል ሙፍረድ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 22
ሠህል ኢብኑ ሙዓዝ ከአባቱ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ወላጆቹን የሚያከብር ለእርሱ መልካም ነው፥ አሏህ ዐዘ ወጀል ዕድሜውን ያረዝመዋል"። عَنْ سَهْلِ بْنِ مُعَاذٍ، عَنْ أَبِيهِ قَالَ‏:‏ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم‏:‏ مَنْ بَرَّ وَالِدَيْهِ طُوبَى لَهُ، زَادَ اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ فِي عُمْرِهِ‏.‏
አደቡል ሙፍረድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 12
ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ "ማንም ጌታውን የሚፈራ እና ዝምድናውን የሚቀጥል ዕድሜው ይረዝማል"። عَنِ ابْنِ عُمَرَ قَالَ‏:‏ مَنِ اتَّقَى رَبَّهُ، وَوَصَلَ رَحِمَهُ، نُسِّئَ فِي أَجَلِهِ
የሰው ዕድሜ ማጠር እና መርዘም አንደኛ በከይፊያህ ሁለተኛ በከሚያህ ደረጃ ሊሆን ይችላል፥ "ከይፊያህ" كَيْفِيَّة ማለት "ዓይነት"quality" ማለት ሲሆን አንድ ሰው በሚሠራው መልካም ሥራ የዕድሜው ከይፊያህ በመብቃቃት ይረዝማል፥ ለምሳሌ፦ አንድ ዓመት 12 ወር ነው፥ ለይለቱል ቀድር በዓመት አንዴ ስትሆን ከ 1000 ወር በላጭ ናት። 1000 ወር 83 ዓመት (1000÷12=83) ይሆናል፥ ለምሳሌ፦ አንድ ሰው 10 ዓመት ሙሉ ተከታትሎ ለይለቱል ቀድርን ያገኘ 830 ዓመት (83×10=830) በላይ እንደኖረ ይሆናል፦
97፥2 *መወሰኛይቱም ሌሊተ ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ?* وَمَا أَدْرَاكَ مَا لَيْلَةُ الْقَدْرِ
97፥3 *መወሰኛይቱ ሌሊት ከሺሕ ወር በላጭ ናት*፡፡ لَيْلَةُ الْقَدْرِ خَيْرٌ مِّنْ أَلْفِ شَهْرٍ
ሙወጧእ ማሊክ መጽሐፍ 19, ሐዲስ 706
ማሊክ ከታመኑ አህለል ዒልም ሰው ሰምቶ እንደተናገረው፦ "የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” ከእሳቸው በፊት የነበሩት ሕዝቦች የሕይወት ቆይታ እና አሏህ ያንን ቆይታ እንዴት እንደፈቀደ አጤኑ። ከእሳቸው በፊት የነበሩት ሕዝቦች ረጅም ዕድሜያቸውን ማከናወን የቻሉትን ያህል ሌሎች በጎ ተግባሮችን መሥራት እንዲችሉ የእርሳቸው ኡማህ በጣም አጭር እንደነበሩ ሆኖ ነበር፡፡ “መወሰኛይቱ ሌሊት ከሺሕ ወር በላጭ ናት” ብሎ አሏህ ለይለቱል ቀድርን ሰጣቸው”። عَنْ مَالِكٍ، أَنَّهُ سَمِعَ مَنْ، يَثِقُ بِهِ مِنْ أَهْلِ الْعِلْمِ يَقُولُ إِنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم أُرِيَ أَعْمَارَ النَّاسِ قَبْلَهُ أَوْ مَا شَاءَ اللَّهُ مِنْ ذَلِكَ فَكَأَنَّهُ تَقَاصَرَ أَعْمَارَ أُمَّتِهِ أَنْ لاَ يَبْلُغُوا مِنَ الْعَمَلِ مِثْلَ الَّذِي بَلَغَ غَيْرُهُمْ فِي طُولِ الْعُمْرِ فَأَعْطَاهُ اللَّهُ لَيْلَةَ الْقَدْرِ خَيْرٌ مِنْ أَلْفِ شَهْرٍ ‏.‏

የረመዷን ሠላሳ ቀን እና የሸዋል ስድስት ቀን መፆም አንድ ዓመት እንደፆምን የሚታሰበው አንድ መልካም ሥራ ምንዳው በአሥር እጥፍ ስለሆነ ነው፦
6፥160 በመልካም ሥራ የመጣ ሰው ለእርሱ ዐሥር ብጤዎችዋ አሉት፡፡ مَن جَاءَ بِالْحَسَنَةِ فَلَهُ عَشْرُ أَمْثَالِهَا
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 78
አቢ አዩብ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ማንም ረመዷንን የጾመ ከዚያም ከሸዋል ወር ስድስት ቀናትን ያስከተለ ዋጋው ዓመቱን ሙሉ እንደጾመ ነው"። عَنْ أَبِي أَيُّوبَ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ مَنْ صَامَ رَمَضَانَ ثُمَّ أَتْبَعَهُ سِتًّا مِنْ شَوَّالٍ فَذَلِكَ صِيَامُ الدَّهْرِ ‏

አንድ መልካም ሥራ አሥር ብጤዎች ካሉት የረመዷን አንድ ወር የያዘው 30 ቀናት መጾም የአሥር ወር ምንዳ አለው፥ 30×10= 300 ቀን ወይም 10 ወር ይሆናል።
እንዲሁ የሸዋል ስድስት ቀን መጾም የስድሳ ቀን ምንዳ አለው፥ 6×10= 60 ቀን ወይም 2 ወር ይሆናል።
በጥቀሉ 360 ቀን ወይም 12 ወር ከሆነ መልካም ሥራ በከይፊያህ ሲረዝም ይህንን ይመስላል። ጊዜ ጸጋ ነውና በአግባብ መጠቀም ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 36, ሐዲስ 1
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ከሰዎች ብዙዎች በአግባቡ የማይጠቀሙባቸው ሁለት ጸጋዎች ጤንነት እና ጊዜ ናቸው"። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ نِعْمَتَانِ مَغْبُونٌ فِيهِمَا كَثِيرٌ مِنَ النَّاسِ الصِّحَّةُ وَالْفَرَاغُ ‏"‏

"ከሚያህ" كَمِّيَّة ማለት ደግሞ "መጠን"quantity" ማለት ሲሆን የሰው ዕድሜ መጠን በመልካም ሥራ፣ የህክምና ሰበብ በማድረስ፣ ጥንቃቄ በማድረግ ሊረዝም አሊያም መጥፎ ሥራ በመሥራት፣ በግድየለሽነት፣ በዝርክርክነት ሊያጥር ይችላል፥ "ሐዘር" حَذَر ማለት "ጥንቃቄ"discretion" ማለት አምላካችን አሏህ የራሳችን ጥንቃቄ እንድንይዝ ነግሮናል፦
4፥71 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጥንቃቄአችሁን ያዙ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا خُذُوا حِذْرَكُمْ

አምላካችን አሏህ መልአኩ በሚከትበው ኪታብ ላይ ለመልአኩ የተወሰነ የዕድሜ ቁጥር እንዲጽፍ ይሰጠው እና ያ ቁጥር በመልካም ሥራ ሊረዝም ወይም በመጥፎ ሥራ ሊያጥር ይችላል፥ መልአኩ የጻፈው ኪታብ ላይ ሊጨምረው ሊቀንሰው የሚችል ነገር ስለሆነ ሙአለቅ ነው። ኢንሻሏህ ስለ አጀሉል ሙሠማ በክፍል ሁለት እናጠናቅቃለን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የዛሬው የኢትዮጵያ ትርምስ የትላንቱ የኦርቶዶክስ መምህራን፦
መምህር አባይነህ ካሴ
መምህር ምህረተ አብ
መምህር ታሪኩ አበራ
መምህር ዮርዳኖስ አበበ
መምህር ዘመድኩን በቀለ
የዘሩት የጥላቻ ንግግር ነው።

ሁላችንም በየግሩፑ፣ በየፔጁ እና በየኮሜንቱ ሼር ማድረግ አንርሳ!
ፋና

ቀንድ ያለው ዝንጀሮ
የሚራገጥ ዶሮ፤
የሚያገሳ ጉንዳን
የሚታዘል ዝሆን፤
የሚጥሚጣ ንፍሮ
ይህ ነው የኛ ኑሮ፤
እያለ የሚደሰኩር በዜና
በጥራቃው የአገራችን ፋና።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom
አጀል

ክፍል ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

3፥145 "ለማንኛይቱም ነፍስ በአላህ ውሳኔ ቢኾን እንጂ ልትሞት አይገባትም፥ ጊዜውም ተወስኖ ተጽፏል፡፡ وَمَا كَانَ لِنَفْسٍ أَن تَمُوتَ إِلَّا بِإِذْنِ اللَّهِ كِتَابًا مُّؤَجَّلًا

"አጀሉል ሙአለቅ" أَجَل المُعَلَّق ማለት "የተጠለጠለ ጊዜ" ማለት እንደሆነ፣ ይህም ጊዜ መልአኩ በማኅፀን የጻፈው ሊሻር ወይም ሊሻሻል እንደሚችል እና መልአኩ የጻፈውን ጊዜ ሰው በመልካም ሥራው የሚረዝም እና በመጥፎ ሥራ የሚያጥር እንደሆነ አይተን ነበር፥ በመቀጠል አሏህ ስለ "አጀሉል ሙሠማ" أَجَل المُّسَمًّى እንዲህ በማለት ይናገራል፦
6፥2 እርሱ ያ ከጭቃ የፈጠራችሁ ከዚያም ጊዜን የወሰነ ነው፥ እርሱም ዘንድ የተወሰነ ጊዜ አለ፡፡ هُوَ الَّذِي خَلَقَكُم مِّن طِينٍ ثُمَّ قَضَىٰ أَجَلًا ۖ وَأَجَلٌ مُّسَمًّى عِندَهُ

"ጊዜን የወሰነ ነው" ሲል አጀሉል ሙአለቅ ካመለከተ በኃላ "እርሱም ዘንድ የተወሰነ ጊዜ አለ" ሲል ደግሞ አጀሉል ሙሠማን ያሳያል፥ "የተወሰነ ጊዜ" ለሚለው የገባው ቃል "አጀሉ ሙሠማ" وَأَجَلٌ مُّسَمّ ሲሆን ይህም የተወሰነ ጊዜ የተከተበው እርሱ ዘንድ ባለው በለውሐል መሕፉዝ የተጻፈው ነው፦
13፥39 አላህ የሚሻውን ያብሳል፤ ያጸድቃልም፡፡ የመጽሐፉ መሠረትም እርሱ ዘንድ ነው፡፡ يَمْحُو اللَّهُ مَا يَشَاءُ وَيُثْبِتُ ۖ وَعِندَهُ أُمُّ الْكِتَابِ

ስለ አጀሉል ሙአለቅ "አላህ የሚሻውን ያብሳል፤ ያጸድቃልም" በማለት ከነገረን በኃላ እርሱ ዘንድ ስላለው ስለ ለውሐል መሕፉዝ "ኡሙል ኪታብ" أُمِّ الْكِتَاب በማለት ነገረን፥ ነገር ሁሉ በኡሙል ኪታብ የተጻፈ ነው፦
78፥29 ነገር ሁሉ የተጻፈ ሲኾን አጠቃለልነው፡፡ وَكُلَّ شَيْءٍ أَحْصَيْنَاهُ كِتَابًا
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 79
አቢ ሁረይራህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "አሏህ ፍጥረትን በወሰነ ጊዜ ከዐርሽ በላይ እርሱ ዘንድ ጻፈ"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ "‏ لَمَّا قَضَى اللَّهُ الْخَلْقَ كَتَبَ عِنْدَهُ فَوْقَ عَرْشِهِ

እዚህ ሐዲስ ላይ "ወሰነ" ለሚለው የገባው ቃል "ቀዶ" قَضَى ሲሆን ይህ ቀዷ "ቀዷ ሙብረም" قَضَىٰ مُبْرَم ነው፥ "ሙብረም" مُبْرَم ማለት "የተቆረጠረ" ማለት ነው። አጀሉል ሙአለቅ መንስኤ ሲሆን የመጨረሻው ሞት ሲመጣ ደግሞ ውጤት ነው፥ ይህ ውጤት አጀሉል ሙሠማ በጥብቁ ሰሌዳ ከፍጥረት በፊት ተጽፏል፦
3፥145 "ለማንኛይቱም ነፍስ በአላህ ውሳኔ ቢኾን እንጂ ልትሞት አይገባትም፥ ጊዜውም ተወስኖ ተጽፏል፡፡ وَمَا كَانَ لِنَفْسٍ أَن تَمُوتَ إِلَّا بِإِذْنِ اللَّهِ كِتَابًا مُّؤَجَّلًا
35፥11 ዕድሜው ከሚረዘምም አንድም አይረዘምም ከዕድሜውም አይጎደልም በመጽሐፉ ውስጥ ያለ ቢኾን እንጂ፡፡ ይህ በአላህ ላይ ገር ነው፡፡ وَمَا يُعَمَّرُ مِن مُّعَمَّرٍ وَلَا يُنقَصُ مِنْ عُمُرِهِ إِلَّا فِي كِتَابٍ ۚ إِنَّ ذَٰلِكَ عَلَى اللَّهِ يَسِيرٌ

ሞት ከመጣ በኃላ አጀሉል ሙሠማን ማርዘምም ማሳጠር የማይቻል ሲሆን ይህ ዕውቀት አሏህ ዘንድ በመጽሐፉ ውስጥ ያለውን ነው፥ ይህ አጀል ሲመጣ አንዲትን ሰዓት አይረዝምም አያጥርም፦
7፥34 ለሕዝብም ሁሉ የተወሰነ ጊዜ አላቸው፡፡ ጊዜያቸውም በመጣ ወቅት አንዲትን ሰዓት አይቆዩም አይቀደሙምም፡፡ وَلِكُلِّ أُمَّةٍ أَجَلٌ ۖ فَإِذَا جَاءَ أَجَلُهُمْ لَا يَسْتَأْخِرُونَ سَاعَةً ۖ وَلَا يَسْتَقْدِمُونَ
63፥11 ማንኛይቱም ነፍስ የሞት ጊዜዋ በመጣበት ጊዜ አላህ በፍጹም አያቆያትም፡፡ وَلَن يُؤَخِّرَ اللَّهُ نَفْسًا إِذَا جَاءَ أَجَلُهَا
2፥180 አንዳችሁን ሞት በመጣበት ጊዜ ሀብትን ቢተው ለወላጆችና ለቅርብ ዘመዶች በበጎ መናዘዝ በእናንተ ላይ ተጻፈ፡፡ كُتِبَ عَلَيْكُمْ إِذَا حَضَرَ أَحَدَكُمُ الْمَوْتُ إِن تَرَكَ خَيْرًا الْوَصِيَّةُ لِلْوَالِدَيْنِ وَالْأَقْرَبِينَ بِالْمَعْرُوفِ

አምላካችን አሏህ መጨረሻችንን በላ ኢላሀ ኢለል ሏህ ያሳምርልን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም