ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
69 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
አምላክን ማየት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥75 የመርየም ልጅ አልመሢሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ

"እኔን ያየ አብን አይቶአል" የሚለውን ኃይለ-ቃል ይዘው የሐዋርያት ቤተክርስቲያን በተለምዶ ኢየሱስ ብቻ"only Jesus" የሚባሉት፦ "ኢየሱስ አብ ነው" ሲሉ ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክ፣ አንግሊካን እና ፕሮቴስታንት ደግሞ፦ "ኢየሱስ አምላክ ነው" የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል፥ እውን ይህ ኃይለ-ቃል "ኢየሱስ አብ ነው" ወይም "ኢየሱስ አምላክ ነው" ለሚለው ዶክትሪን ድምዳሜ ላይ ያደርሳልን? ጥቅሱን በሰከነ እና በሰላ አእምሮ እንመልከተው፦
ዮሐ14፥7 እኔንስ ብታውቁኝ አባቴን ደግሞ ባወቃችሁ ነበር። ከአሁንም ጀምራችሁ ታውቁታላችሁ አይታችሁትማል አለው።
ዮሐ14፥8 ፊልጶስ ጌታ ሆይ፥ አብን አሳየንና ይበቃናል አለው። ኢየሱስም አለው።
ዮሐ14፥9 አንተ ፊልጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቶአል።

"እኔን ያየ አብን አይቶአል" ማለት እና "እኔ አብ ነኝ ወይም እኔ አምላክ ነኝ" ማለት አንድ የሚሆነው በምን ሒሣብ ታሥቦ ነው? ኢየሱስ፦ "እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል" ብሏል፥ እና ሐዋርያት ኢየሱስ ናቸውን? ተመሳሳይ ሰዋስው ነው፦
ማቴዎስ 10፥40 እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።

"እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል" ማለት "ሐዋርያትን መቀበል ኢየሱስን እንደ መቀበል ነው" ማለት ከሆነ እንግዲያውስ "እኔን ያየ አብን አይቶአል" ማለት "ወልድን ማየት አብን እንደ ማየት ነው" ማለት ነው፥ "እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል" ማለት "ወልድን መቀበል አብን እንደ መቀበል ነው" ማለት ከሆነ "ወልድን ማየት አብን እንደ ማየት ነው" ማለት ነው። ተመሳሳይ ሙግት እንመልከት፦
ሉቃ10፥16 እናንተንም የጣለ እኔን ይጥላል፤ እኔንም የጣለ የላከኝን ይጥላል።

"እናንተንም የጣለ እኔን ይጥላል" ማለት "ሐዋርያትን መጣል ኢየሱስን እንደ መጣል ነው" ማለት ከሆነ እንግዲያውስ "እኔን ያየ አብን አይቶአል ማለት ወልድን ማየት አብን እንደ ማየት ነው" ማለት ነው፥ "እኔንም የጣለ የላከኝን ይጥላል" ማለት "ወልድን መጣል አብን እንደ መጣል ነው" ማለት ከሆነ "ወልድን ማየት አብን እንደማየት ነው" ማለት ነው። እንቀጥል፦
ዮሐንስ 5፥46 ሙሴንስ ብታምኑት እኔን ባመናችሁ ነበር።

"ሙሴንስ ብታምኑት እኔን ባመናችሁ ነበር" ማለት ሙሴ ኢየሱስ ነውን? ወይስ "ሙሴን ማመን ኢየሱስ እንደ ማመን ነው" ማለት ነው? እንዲሁ ኢየሱስን ማየት አብን እንደ ማየት ነው፣ ኢየሱስን ማወቅ አብን እንደ ማወቅ ነው፣ ኢየሱስን መጥላት አብን እንደ መጥላት ነው፦
ዮሐንስ 12፥45 እኔንም የሚያይ የላከኝን ያያል።
ዮሐንስ 14፥7 እኔንስ ብታውቁኝ አባቴን ደግሞ ባወቃችሁ ነበር።
ዮሐንስ 15፥23 እኔን የሚጠላ አባቴን ደግሞ ይጠላል።

"እኔን" አንደኛ ማንነት "የላከኝ ወይም አባቴ" ሁለተኛ ማንነት፥ ስለዚህ ሁለት ማንነቶችን ቀልጭ አርጎ ያሳያል፦
ዮሐንስ 15፥24 አሁን ግን እኔንም አባቴንም አይተውማል ጠልተውማል።

ያዩት እና የጠሉት ሁለት ማንነት ነው፥ "እኔን" አንድ "አባቴን" ሁለት። አብን ታውቁታላችሁ አይታችሁትማል፦
ዮሐንስ 14፥7 ከአሁንም ጀምራችሁ ታውቁታላችሁ አይታችሁትማል" አለው።

"ማየት" ማለት በእማሬአዊ አብን በሥጋ ዓይን መመልከት ሳይሆን በመልእክተኛው ማንነት ውስጥ በፍካሬአዊ "መገንዘብ" ማለት ነው፦
ዮሐንስ 6፥46። አብን ያየ ማንም የለም፥ ከእግዚአብሔር ከሆነ በቀር እርሱ አብን አይቶአል።

"ከሆነ" የሚለው ቃል በቅጡ ይሰመርበት! "ከ"-እግዚአብሔር የሆነ መንፈሳዊ ሰው እርሱ አብን አይቷል፥ በሥጋ ዓይን ግን አብን ያየ ማንም የለም፦
ዮሐንስ 5፥37 የላከኝ አብም እርሱ ስለ እኔ መስክሮአል። ድምፁን ከቶ አልሰማችሁም፥ “መልኩንም አላያችሁም”፤
ዮሐንስ 1፥18 መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም።
1ኛ ዮሐንስ 4፥12 እግዚአብሔርን ማንም ከቶ አላየውም።
1ኛ ጢሞቴዎስ 6፥16 አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም።

ከኢየሱስ እርገት በኃላ "እግዚአብሔርን ማንም ከቶ አላየውም" ሲባል ኢየሱስ "አብን አይታችሁትማል" ከሚለው ጋር ለማስማማት የሚቻለው "ወልድን ማየት አብን እንደ ማየት ነው" በሚል ቀመር ብቻ ነው። ብሉይ ኪዳን ላይ መላእክት ሲገለጡ ሰዎች "እግዚአብሔር አይተናል" ይሉ ነበር።

ናሙና አንድ፦
ዘፍጥረት 16፥7 "የእግዚአብሔር መልአክም" በውኃ ምንጭ አጠገብ በበረሀ አገኛት።
ዘፍጥረት 16፥13 እርስዋም ይናገራት የነበረውን የእግዚአብሔርን ስም ኤልሮኢ ብላ ጠራች፤ የሚያየኝን በውኑ እዚህ ደግሞ አየሁትን? ብላለችና።

ናሙና ሁለት፦
ሆሴዕ 12፥4 "ከመልአኩም" ጋር ታግሎ አሸነፈ፤ አልቅሶም ለመነው።
ዘፍጥረት 32፥24 ያዕቆብ ግን ለብቻው ቀረ፤ አንድ "ሰውም" እስከ ንጋት ድረስ ይታገለው ነበር።
ዘፍጥረት 32፥30 ያዕቆብም፦ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፥ ሰውነቴም ድና ቀረች" ሲል የዚያን ቦታ ስም ጵኒኤል ብሎ ጠራው።

ናሙና ሦስት፦
መሣፍንት 13፥21 ያን ጊዜም ማኑሄ "የእግዚአብሔር መልአክ" መሆኑን አወቀ።
መሣፍንት 13፥22 ማኑሄም ሚስቱን፦ እግዚአብሔርን አይተናልና ሞት እንሞታለን" አላት።

መላእክት መልእክተኞች ሲሆኑ በመላእክት የአምላክ መታየት "አስተርዮተ አምላክ"theophany" ሲሆን ይህም መታየት ፍካሬአዊ እንጂ እማሬአዊ አይደለም፦
ዘጸአት 33፥20 ደግሞም፦ ሰው አይቶኝ አይድንምና ፊቴን ማየት አይቻልህም፡ አለ።

መላእክትን ማየት እግዚአብሔር ማየት ከሆነ መልእክተኛውን "ኢየሱስን ማየት እግዚአብሔር ማየት ነው" ብሎ መረዳት እንጂ መልእክተኛው እራሱ አብ ወይም አምላክ ነው" ብሎ መደምደም የሾቀ ድምዳሜ ነው። የመርየም ልጅ አልመሢሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፦
5፥75 የመርየም ልጅ አልመሢሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ

ኢየሱስን የላከውን አንዱን አምላክ አሏህ እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። አሏህን ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አንዋዑል ዒባዳህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

21፥92 ይህች አንዲት መንገድ ስትሆን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት፡፡ እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ፡፡ إِنَّ هَـٰذِهِ أُمَّتُكُمْ أُمَّةً وَاحِدَةً وَأَنَا رَبُّكُمْ فَاعْبُدُونِ

ቁርኣን ውስጥ "ኢሥቲንባጥ" اِسْتِنْبَاطْ ሲደረግ የዒባዳህ ዓይነቶች ፍንትው እና ቁልጭ ብለው ይወጣሉ። "ነውዕ" نَوْع የሚለው ቃል "ናዐ" نَاعَ‎ ማለትም "መደበ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ምድብ" "ዓይነት" ማለት ነው፥ የነውዕ ብዙ ቁጥር ደግሞ "አንዋዕ" أنْوَاع ሲሆን "ዓይነቶች" ማለት ነው። በጥቅሉ "አንዋዑል ኢባዳህ" أنْوَاعُ العِبَادَة ማለት "የአምልኮ ዓይነቶች" ማለት ነው፥ አንዋዑል ኢባዳህ የሚባሉት ዒባደቱል ቀልቢያህ፣ ዒባደቱል ቀውሊያህ እና ዒባደቱል ዐመሊያህ ናቸው። እነዚህን ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
"ቀልቢያህ"
"ዒባደቱል ቀልቢያ" عِبَادَة القَلْبِيَّة ማለት "የኃልዮ አምልኮ" ማለት ነው፥ "ቀልብ" قَلْب የሚለው ቃል "ቀለበ" قَلَبَ ማለትም "ለበወ" "ኀለየ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ልብ" "ኃልዮ" ማለት ነው። በልብ የሚፈጸሙ አምልኮ ዒልሚያህ፣ ኢማንያህ፣ ኢኽላስ፣ ኢሕሣን፣ ተወኩል፣ ተቅዋእ፣ ሶብር እና መሐባህ ናቸው፦

፨"ዒልሚያህ" عِلْمِيَّة ማለት "ዕውቀት" ማለት ሲሆን ይህም የዕውቀት ቁንጮ "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" لَا إِلٰهَ إِلَّا اللّٰه የሚለውን ዐቂዳህ ማወት ነው።

፨"ኢማንያህ" ِإِيمَانِيَّة ማለት "እምነት" ማለት ነው፥ ኢማን ከሰባ ወይም ከስልሳ በላይ ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን ትልቁ ቅርንጫፍ "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" لَا إِلٰهَ إِلَّا اللّٰه የሚለው ቃል ነው።

፨"ኢኽላስ" إِخْلَاص‎ ማለት እውነት ለማንገሥ ሐሠትን ለማርከሥ የሚደረግ "መተናነስ" ወይም ከሙገሳ እና ከወቀሳ ነጻ ሆኖ ለአሏህ ውዴታ የሚደረግ "ማጥራት" ማለት ነው።

፨"ኢሕሣን" ማለት "አሏህን እንደምታየው አርገህ ማምለክ፥ አሊያም አሏህ እንደሚያይህ አርገህ ማምለክ" ማለት ነው።

፨"ተወኩል" تَوَكُّل ማለት "አሏህን መጠጊያ፣ መመኪያ፣ መሸሸጊያ አድርገን የምንይዝበት ዐቅም" ማለት ነው።

፨"ተቅዋእ" تَقْوَا ማለት "አሏህ ሁሉን ዐዋቂ ነው” በልቤ የማስበውን ያውቃል፣ “አሏህ ሁሉን ነገር ሰሚ ነው” መስጥሬ የምናገረውን ይሰማል፣ “አሏህ ሁሉን ተመልካች ነው” ተደብቄ የማደርገውን ያያል ብሎ መጥፎ ከማሰብ፣ ከመናገር፣ ከማድረግ እድንቆጠብ የሚያደርገን ስሜት ነው።

፨"ተዋዱዕ تَوَاضُع ማለት "መተናነስ"humility" ማለት ሲሆን ለአሏህ የሚደረግ መጎባደድ ነው።

፨"ሶብር" صَّبْر ማለት "ሙሲባህ ሲመጣ ኢሥቲርጃዕ በማድረግ የምናሳልፍበትን ዐቅም የሚሰጥ ስሜት ነው።

፨"መሐባህ" مَحَبَّة አሏህን በፍጹም እና በሙሉ ሁለንተና ማፍቀር ነው።
ነጥብ ሁለት
"ቀውልያ"
"ዒባደቱል ቀውልያ" عِبَادَة القَوْلِيَّة ማለት "የነቢብ አምልኮ" ማለት ነው፥ "ቀውል" قَوْل የሚለው ቃል "ቀወለ" قَوَّلَ ማለትም "ነበበ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ነቢብ" "አንደበት" ማለት ነው። በአንደበት የሚፈጸሙ አምልኮ ሸሃዳህ፣ ተውባህ፣ ዱዓእ፣ ደዕዋህ፣ ዚክር እና ቂርኣት ናቸው፦

፨"ሸሃዳህ" شَهَادَة‎ ማለት "አሽሀዱ አነ ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" أَشْهَدُ أَنْ لَا إِلٰهَ إِلَّا ٱلله እና "አሽሀዱ አነ ሙሐመደን ረሡሉሏህ" أَشْهَدُ أَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ ٱلله በማለት በአፍ የምናውጀው ቃለ-ምስክርነት ነው።

፨"ተውባህ" تَوْبَة ማለት ከልብ አሏህን ይቅርታ በመጠየቅ "ይቅር በለኝ" ብሎ መማጸን ነው።

፨"ዱዓእ" دُعَآء ማለት አሏህን በተለያዩ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ስሙን በመጥራት እየለመንን የምንጠይቀው ነው።

፨"ደዕዋህ" دَعْوَة ሰዎችን ከሺርክ፣ ከኩፍር፣ ከቢድዓህ፣ ከፈሣድ ወደ አሏህ የምንጠራበት አስተምህሮት ነው።

፨"ዚክር" ذِكْر የአሏህ ስም በተህሊል፣ በተክቢር፣ በተሕሚድ፣ በተሥቢሕ፣ በተምጂድ፣ በኢሥቲግፋር፣ በኢሥቲዓዛህ፣ በበስመሏህ፣ በሐስበላህ፣ በኢሥቲርጃህ እየጠራን የምንዘክረው ነው።

፨"ቂርኣት" قِرْاءَت ማለት ቁርኣንን በሙጀወድ ወይም በሙረተል ደንቡን ጠብቆ መቅራት ነው።

ነጥብ ሦስት
"ዐመል"
"ዒባደቱል ዐመልያ" عِبَادَة العَمَلِيَّة ማለት "የገቢር አምልኮ" ማለት ነው፥ "ዐመል"عَمَل የሚለው ቃል "ዐሚለ" عَمِلَ ማለትም "ገበረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ገቢር" "ድርጊት" ማለት ነው። በድርጊት የሚፈጸሙ አምልኮ ሶላት፤ ሶውም፣ ዘካህ፣ ሐጅ እና ጂሃድ ናቸው፦

፨"ሶላት" صَّلَات ማለት ቂያም፣ ሩኩዕ፣ ሡጁድ የያዘ "ጸሎት" ነው።

፨"ሶውም" صَوْم ማለት ከፈጅር እስከ መግሪብ ከምግብ እና ከመጠጥ ተከልክሎ ተቅዋእ መቀበያ ነው።

፨"ዘካህ" زَكَاة ማለት አሏህ ከሰጠን ሲሳይ ላይ መጥራራት ለማግኘት ለድኾች፣ ለምስኪኖችም፣ ለባለ ዕዳዎችም ወዘተ የሚሰጥ ምጽዋት ነው።

፨"ሐጅ" حَجّ ማለት የአሏህ ቤት በደንቡ መጎብኘት ነው።

፨"ጂሃድ" جِهَاد ማለት እውነት ለማንገሥ እና ሐሠትን ለማርከሥ ተብሎ በአሏህ መንገድ የሚደረግ ትግል ነው።

ስንጠቀልለው በቀልብ፣ በቀውል እና በዐመል የሚፈጸሙ የዒባዳህ ዓይነቶች አንዱ ከሌላው ጋር የተሰናሰነ እና የተሳሰረ ነው፥ ለምሳሌ ኢማንያህ ዒባደቱል ቀልቢያህ ቢሆንም በቀውል የምንመከክረው እና በዐመል የምንተገብረው ነው፣ ጂሃድ ዒባደቱል ዐመልያ ቢሆንም በቀውል የምናገረው እና በቀልብ የምናስበው ነው፣ ተውባህ ዒባደቱል ቀውልያ ቢሆንም በቀልብ የምንጸጸተው እና በዐመል መጥፎ ድርጊቱን የምንተወው ነው።
አምላካችን አሏህ በኢማን፣ በኢኽላስ፣ በኢትባዕ የምናመልከው ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የረመዷን ወር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

2፥185 እንድትጦሙ የተጻፈባችሁ ያ በእርሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድ እና እውነትን ከውሸት ከሚለዩም ገላጮች አንቀጾች ሲኾን ቁርኣን የተወረደበት የረመዳን ወር ነው፡፡ ከእናንተም ወሩን ያገኘ ሰው ይጡመው፡፡ شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَاتٍ مِّنَ الْهُدَىٰ وَالْفُرْقَانِ ۚ فَمَن شَهِدَ مِنكُمُ الشَّهْرَ فَلْيَصُمْهُ

"ሸህር" شَهْر የሚለው ቃል "ሸሀረ" شَهَرَ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ወር" ማለት ነው፥ "ሸህር" شَهْر የሚለው ቃል በቁርኣን ውስጥ በነጠላ የመጣው 12 ጊዜ ነው። የሚያጅበው የወሮች ቁጥር አሏህ ዘንድ በአሏህ መጽሐፍ አሥራ ሁለት ነው፥ እነዚህም፦
1ኛው ወር "ሙሐረም" مُحَرَّم
2ኛው ወር "ሶፈር" صَفَر
3ኛው ወር "ረቢዑል-አወል" رَبِيع ٱلْأَوَّل
4ኛው ወር "ረቢዑ አስ-ሳኒይ" رَبِيع ٱلثَّانِي
5ኛው ወር "ጁማዱል-አወል" جُمَادَىٰ ٱلْأَوَّل
6ኛው ወር። ጀማዱ አስ-ሳኒይ" جُمَادَىٰ ٱلثَّانِي
7ኛው ወር "ረጀብ" رَجَب
8ኛው ወር "ሸዕባን" شَعْبَان
9ኛው ወር "ረመዷን" رَمَضَان
10ኛው ወር "ሸዋል" شَوَّال
11ኛው ወር "ዙል-ቀዕዳህ" ذُو ٱلْقَعْدَة
12ኛው ወር "ዙል-ሒጃህ" ذُو ٱلْحِجَّة ናቸው፦
9፥36 የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን ዐሥራ ሁለት ወር ነው፡፡ ከእነርሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው፡፡ إِنَّ عِدَّةَ الشُّهُورِ عِندَ اللَّهِ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا فِي كِتَابِ اللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65 ሐዲስ 4662
አቡበከር”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ ”ዘመን አላህ ሰማያትን እና ምድር በፈጠረበት ቀን የቀድሞ ሁኔታ ይመለሳል። አንድ ዓመት ዐሥራ ሁለት ወር ነው፥ ከእነርሱም አራቱ የተከበሩ ናቸው። ሦስቱ ተከታታይ ዙል-ቀዒዳህ፣ ዙል-ሒጃህ፣ ሙሐረም ናቸው፥ አራተኛው በጀማዱ-ሣኒ እና በሻዕባን መካከል ያለው ረጀብ ነው። عَنْ أَبِي بَكْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ إِنَّ الزَّمَانَ قَدِ اسْتَدَارَ كَهَيْئَتِهِ يَوْمَ خَلَقَ اللَّهُ السَّمَوَاتِ وَالأَرْضَ، السَّنَةُ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا مِنْهَا، أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ، ثَلاَثٌ مُتَوَالِيَاتٌ، ذُو الْقَعْدَةِ وَذُو الْحِجَّةِ وَالْمُحَرَّمُ وَرَجَبُ مُضَرَ الَّذِي بَيْنَ جُمَادَى وَشَعْبَانَ
“ረመዷን” رَمَضَان የሚለው ቃል "ረመዶ" رَمَضَ ማለትም "ደረቀ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ድርቀት” ወይም “ሞቃት” ማለት ነው፥ ረመዷን የወር ስም እንጂ የጦም ስም አይደለም። የተቆጠሩ ቀኖች የያዘው ረመዷን 9ኛው ወር ሲሆን ይህ ወር የሚጦምበት ምክንያት ቁርኣን ከጥብቁ ሰሌዳ ወደ ቅርቢቱ ሰማይ የወረደበት ወር ስለሆነ ነው፦
2፥185 እንድትጦሙ የተጻፈባችሁ ያ በእርሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድ እና እውነትን ከውሸት ከሚለዩም ገላጮች አንቀጾች ሲኾን ቁርኣን የተወረደበት የረመዳን ወር ነው፡፡ ከእናንተም ወሩን ያገኘ ሰው ይጡመው፡፡ شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَاتٍ مِّنَ الْهُدَىٰ وَالْفُرْقَانِ ۚ فَمَن شَهِدَ مِنكُمُ الشَّهْرَ فَلْيَصُمْهُ

እዚህ አንቀጽ ላይ "የረመዷን ወር" ለሚለው የገባው ቃል “ሸህሩ ረመዷን” شَهْرُ رَمَضَان መሆኑን ልብ አድርግ! ይህ ወር የጸጋ ወር ስለሆነ በዒባዳህ ለሚዘወተሩ የጀነት ደጆች ክፍት የሆነበት፥ በተቃራኒው የእሳት ደጆች የሚዘጉበት ነው። እንዲሁ ማሪድ የሚባሉት ኩፋሩል ጂን የሚባሉት ሸያጢን የሚታሰሩበት ነው፦
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 30, ሐዲስ 9
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው የአላህም መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ”የረመዷን ወር ሲጀመር የሰማይ ደጆች ይከፈታሉ፣ የጀሃነም ደጆች ይዘጋሉ፣ ሰይጣናትም ይታሰራሉ”። سَمِعَ أَبَا هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ يَقُولُ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ إِذَا دَخَلَ شَهْرُ رَمَضَانَ فُتِّحَتْ أَبْوَابُ السَّمَاءِ، وَغُلِّقَتْ أَبْوَابُ جَهَنَّمَ، وَسُلْسِلَتِ الشَّيَاطِينُ ‏”‌‏

“የሰማይ ደጆች ይከፈታሉ፥ የጀሃነም ደጆች ይዘጋሉ” ማለት "በዚህ ወር የሚሞት ሁሉ እሳት አይገባም፥ ሁሉም ጀነት ይገባል" ማለት ሳይሆን የወሩን ድባብ ታላቅነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፥ በዚህ ወር “የሰማይ ደጆች ይከፈታሉ” ማለት "ሌላውን 11 ወራት ዝግ ነበር" ማለት እንዳልሆነ ሁሉ፥ ሙእሚን ዘርፈ-ብዙ እና መጠነ-ሰፊ የአምልኮ ተግባራትን በማከናወን ወደ አሏህ የሚቀርቡበትን የጸጋ ወር ለማመልከት የተገለጸ ፈሊጣዊ አገላለጽ ነው። ለምሳሌ ሙሥሊም በሳምንት ውስጥ ሁለት ቀናት የሡናህ አጥዋማት ይፆማል፥ እነርሱም ሰኞ እና ሐሙስ ናቸው። ሰኞ እና ሐሙስ የጀነት ደጃፎች በአሏህ ላይ ምንም ነገር ላላሻረከ ሁሉ ይከፈታል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 45, ሐዲስ 43
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም እንዲህ አሉ፦ ”የጀነት ደጃፎች በአላህ ላይ ምንም ነገር ላላሻረከ ሁሉ ሰኞ ቀን እና ሐሙስ ቀን ይከፈታል፥ አንድ ሰው በውስጡ መራራነት በወንድሙ ላይ ካለበት በስተቀር”። እንዲህም ይባላል፦ “በሁለቱ መካከል ዕርቅ እስኪሆን ድረስ አጢኑ፣ በሁለቱ መካከል ዕርቅ እስኪሆን ድረስ አጢኑ፣ በሁለቱ መካከል ዕርቅ እስኪሆን ድረስ አጢኑ”። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏”‏ تُفْتَحُ أَبْوَابُ الْجَنَّةِ يَوْمَ الاِثْنَيْنِ وَيَوْمَ الْخَمِيسِ فَيُغْفَرُ لِكُلِّ عَبْدٍ لاَ يُشْرِكُ بِاللَّهِ شَيْئًا إِلاَّ رَجُلاً كَانَتْ بَيْنَهُ وَبَيْنَ أَخِيهِ شَحْنَاءُ فَيُقَالُ أَنْظِرُوا هَذَيْنِ حَتَّى يَصْطَلِحَا أَنْظِرُوا هَذَيْنِ حَتَّى يَصْطَلِحَا أَنْظِرُوا هَذَيْنِ حَتَّى يَصْطَلِحَا

የጀነት ደጃፎች ሰኞ ቀን እና ሐሙስ ቀን ክፍት የሆነው ቂም ወይም ጥላቻ በሙሥሊም ወንድሙ ላይ በልቡ ላልቋጠረ ሙሥሊም ነው። ሰኞ እና ሐሙስ ሳምንታዊ መጠነ-ሰፊ የአምልኮ ጊዜ ለማመልከት እንጂ ሌላውን የአዘቦት ቀናት ሥራዎች አይቀርቡም ወይም አሏህ ይቅር አይልም አሊያም የጀነት ደጃፎች አይከፈቱም ማለትን እንደማያሲዝ ሁሉ በረመዷን ወር “የሰማይ ደጆች ይከፈታሉ” ማለት "ሌላውን 11 ወራት ዝግ ነበር" ማለት አይደለም፥ የሚያሳየው የወሩን ድባብ ታላቅነት ነው።

“አሏሁ አዕለም” اَللّٰهُ أَعْلَم‎

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የረመዷን ስጦታ

በስምንት አርስት የተሰደረ አርስት በረመዷን ወር እንካችሁ ብለናል። ሊንኩን በማስፈንጠር ያግኙት!

1. የረመዷን ወር፦
https://tttttt.me/Wahidcom/3107

2. የጨረቃ አቆጣጠር፦
https://tttttt.me/Wahidcom/2717

3. ጨረቃ እና ኮከብ፦
https://tttttt.me/Wahidcom/2360

4. የሚታሰሩ ሰይጣናት፦
https://tttttt.me/Wahidcom/2724

5. ሡሑር፦
https://tttttt.me/Wahidcom/2726

6. ተራዊህ፦
https://tttttt.me/Wahidcom/833

7. ኢዕቲካፍ፦
https://tttttt.me/Wahidcom/2286

8. ለይለቱል ቀድር፦
https://tttttt.me/Wahidcom/2289

ሁሉም ቦታ ለሁሉም ሰው እንዲዳረስ አሰራጩ!

ወጀዛኩሙሏህ ኸይራ!
በዕል እና ሁበል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

37፥125 በዕልን ትገዛላችሁን? ከሰዓሊዎቹ ሁሉ ይበልጥ በጣም አሳማሪ የሆነውንም አምላክ ትተዋላችሁን? أَتَدْعُونَ بَعْلًا وَتَذَرُونَ أَحْسَنَ الْخَالِقِينَ

ነቢዩ ኢልያሥ ለሕዝቦቹ፦ “አላህን አትፈሩምን? በዕልን ትገዛላችሁን? ከሰዓሊዎቹ ሁሉ ይበልጥ በጣም አሳማሪ የሆነውንም አምላክ ትተዋላችሁን? አሏህን ጌታችሁን እና የቀድሞዎቹ አባቶቻችሁን ጌታ ትተዋላችሁን? አላቸው፦
37፥124 ለሕዝቦቹ፦ “አላህን አትፈሩምን?” ባለ ጊዜ አስታውስ። إِذْ قَالَ لِقَوْمِهِ أَلَا تَتَّقُونَ
37፥125 በዕልን ትገዛላችሁን? ከሰዓሊዎቹ ሁሉ ይበልጥ በጣም አሳማሪ የሆነውንም አምላክ ትተዋላችሁን? أَتَدْعُونَ بَعْلًا وَتَذَرُونَ أَحْسَنَ الْخَالِقِينَ
37፥126 አላህን ጌታችሁን እና የቀድሞዎቹ አባቶቻችሁን ጌታ ትተዋላችሁን? اللَّهَ رَبَّكُمْ وَرَبَّ آبَائِكُمُ الْأَوَّلِينَ

"በዕል" بَعْل ማለት በቋንቋ ደረጃ "ባል" "ባለቤት" "ጌታ" "አባወራ" ማለት ነው፥ "በዕል" بَعْل የመራባት አምላክ ተብሎ የሚጠራ ጣዖት ሲሆን ይህም ጣዖት በሞዓብ "በኣል" በግሪክ "ዘዩስ" በሮም "ጁፒተር" በግብጽ "ሴት"በሰናዖር "ሐዳድ" ይባላል።
"ሁበል"هُبَل የሚለው ቃል ደግሞ የሁለት ቃላት ውቅር ነው፥ "ሁ" هُ ማለት "ሁወ" هُوَ ማለት ሲሆን "በል" بَل ማለት ደግሞ "በዕል" بَعْل ማለት ነው። በጥቅሉ "ሁበል"هُبَل ማለት "ሁወል በዕል" هُوَ الْبَعْل ማለትም "እርሱ በኣል ነው" ማለት ነው፥ ሁበል የሚባለውን ጣዖት "በአል ነው" ብሎ ከሞዓባውያን ሶሪያ ወደ መካህ ያመጣው ዐምር ኢብኑ ሉሃይ ነው። “ኑስብ” نُصْب ማለት “ሐውልት” ማለት ሲሆን የኑስብ ብዙ ቁጥር ደግሞ “ኑሱብ” نُصُب ወይም “አንሷብ” أَنْصَاب ነው፥ ነቢያችን”ﷺ” ነቢይ ሆነው ሲላኩ መካህ ውስጥ በአሏህ ቤት ዙሪያ ከድንጋይ የተሠሩ ኑሱብ ነበሩ። እነዚህን 360 የሚደርሱ ጣዖታት ነቢያችን”ﷺ” ከመዲና ስደት በኃላ ወደ መካህ ድል አርገው ሲገቡ ከሰባበሯቸው አንዱ ሁበል ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 64, ሐዲስ 320
ዐብደላህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ ”ነቢዩ”ﷺ” በመክፈት ቀን ወደ መካህ በገቡ ጊዜ ሦስት መቶ ስድሳ ኑሱብ በአላህ ቤት ዙሪያ ነበሩ። እርሳቸውም እነርሱን በእጃቸው መስበሪያ በመሰባበር ሲጀምሩ፦ “እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና” አሉ”። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ دَخَلَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم مَكَّةَ يَوْمَ الْفَتْحِ وَحَوْلَ الْبَيْتِ سِتُّونَ وَثَلاَثُمِائَةِ نُصُبٍ، فَجَعَلَ يَطْعُنُهَا بِعُودٍ فِي يَدِهِ وَيَقُولُ ‏ “‏ جَاءَ الْحَقُّ وَزَهَقَ الْبَاطِلُ، جَاءَ الْحَقُّ، وَمَا يُبْدِئُ الْبَاطِلُ وَمَا يُعِيدُ ‏”‌‏.‏

እዚህ ድረስ ስለ በዕል እና ሁበል በኢሥላም ያለውን ምልከታ ከተረዳን ዘንድል በመቀጠል ወደ ባይብል በመሄድ ማየት ይቻላል። በባይብል "በኣል" בַּעַל ማለት "ባለቤት"owner" ማለት ነው፦
ዘጸአት 21፥28 የበሬው "ባለቤት" ግን ንጹሕ ነው። וּבַ֥עַל הַשֹּׁ֖ור נָקִֽי

እዚህ አንቀጽ ላይ የበሬው ባለቤት "በኣል" בַּעַל ተብሏል። በሌላ አንቀጽ "በኣል" בַּעַל ማለት ደግሞ "ባል"husband" በሚል መጥቷል፦
ምሳሌ 12፥4 ልባም ሚስት ለ-ባል-ዋ ዘውድ ናት። אֵֽשֶׁת־חַ֭יִל עֲטֶ֣רֶת בַּעְלָ֑הּ

እዚህ አንቀጽ ላይ የሚስት ባል "በኣል" בַּעַל ተብሏል። ፈጣሪ "በኣል" בַּעַל ተብሎ በባይብል ተጠቅሷል፦
ኢሳይያስ 54፥5 ፈጣሪሽ ባልሽ ነው። כִּ֤י בֹעֲלַ֙יִךְ֙ עֹשַׂ֔יִךְ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ባል" ለሚለው የገባው ቃል "ቡዓለ" בֹעֲלַ ሲሆን የግስ መደብ ነው፥ "ቡዓለ" בֹעֲלַ ማለት "ገዛ" ማለት ሲሆን "በዓሉ" בְּעָל֥וּ ማለት "ገዙ" ማለት ነው፦
ኢሳይያስ 26፥13 ያህዌህ አምላካችን ሆይ! ከአንተ በቀር ሌሎች ጌቶች ገዝተውናል። יְהוָ֣ה אֱלֹהֵ֔ינוּ בְּעָל֥וּנוּ אֲדֹנִ֖ים זֽוּלָתֶ֑ךָ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ገዝተውናል" ለሚለው የገባው ቃል "በዓሉ-ኑ" בְּעָל֥וּנוּ እንደሆነ ልብ አድርግ! ስለዚህ "ፈጣሪ "በኣል" בַּעַל ነው" ሲባል "ገዥ ነው" "ባለቤት ነው" "ጌታ ነው" ማለት እንጂ "ባል ነው" ማለት አይደለም፥ ምክንያቱም እርሱ ፆታ እና ሚስት የሌለው ማንነት እና ምንነት ነውና። "በኣል" בַּעַל ከነዓናውያን የመራባት አምላክ ብለው የሚያመልኩት የጣዖት ስም ነው፦
መሣፍንት 2፥13 ያህዌህን ትተው "በኣልን" እና አስታሮትን አመለኩ። וַיַּעַזְב֖וּ אֶת־יְהוָ֑ה וַיַּעַבְד֥וּ לַבַּ֖עַל וְלָעַשְׁתָּרֹֽות׃
1 ነገሥት 16፥32 በሰማርያም በሠራው በ-"በኣል" ቤት ውስጥ ለ-"በኣል" መሠዊያ አቆመ። וַיָּ֥קֶם מִזְבֵּ֖חַ לַבָּ֑עַל בֵּ֣ית הַבַּ֔עַל אֲשֶׁ֥ר בָּנָ֖ה בְּשֹׁמְרֹֽון

አቃሮናውያን የሚያመልኩት ጣዖት ብዔልዜቡል በትክክል ስሙ "በኣል-ዘቡብ" בַּעַל זְבוּב ነው፦
2 ነገሥት 1፥3 የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ትጠይቁ ዘንድ የምትሄዱት በእስራኤል ዘንድ አምላክ ስለሌለ ነውን? לְכ֣וּ דִרְשׁ֗וּ בְּבַ֤עַל זְבוּב֙ אֱלֹהֵ֣י עֶקְרֹ֔ון אִם־אֶחְיֶ֖ה מֵחֳלִ֥י זֶֽה׃ ס

"ዘቡብ" זְבוּב ማለት "ዝንብ" ማለት ነው፥ "በኣል-ዘቡብ" בַּעַל זְבוּב ማለት "የዝንብ ጌታ" ማለት ነው። ሞዓባውያን የሚያመልኩት ጣዖት ብዔልፌጎር በትክክል ስሙ "በኣል-ፌዑር" בַּעַל זְבוּב ነው፦
ዘኍልቍ 25፥3 እስራኤልም ብዔልፌጎርን ተከተለ፤ የእግዚአብሔርም ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ። וַיִּצָּ֥מֶד יִשְׂרָאֵ֖ל לְבַ֣עַל פְּעֹ֑ור וַיִּֽחַר־אַ֥ף יְהוָ֖ה בְּיִשְׂרָאֵֽל׃

"ፌዑር" פְעוֹר በሞዓብ ምድር የነበረ የተራራ ስም ነው፥ "በኣል-ፌዑር" בַּעַל פְעוֹר ማለት "የፌዑር ጌታ" ማለት ነው። "ያህ" יָהּ የሚለው ቃል "ያህዌህ" יְהוָֹה ለሚለው ቃል ምጻረ-ቃል ነው፥ "በኣል-ያህ" וּבְעַלְיָ֣ה ማለት "ያህዌህ በኣል ነው" ማለት ሲሆን ይህም ስም ከሠላሳ የቀስተኞች አለቃ የአንዱ ነበር፦
1 ዜና መዋዕል 12፥5 ኤሉዛይ፥ ኢያሪሙት፥ "በኣል-ያህ" ሰማራያህ፥ ሀሩፋዊው ሰፋጥያስ። אֶלְעוּזַ֤י וִירִימֹות֙ וּבְעַלְיָ֣ה וּשְׁמַרְיָ֔הוּ וּשְׁפַטְיָ֖הוּ [הַחֲרִיפִי כ] (הַחֲרוּפִֽי׃ ק)

በቁርኣን እና በሐዲስ "በዕል" بَعْل ወይም "ሁበል" هُبَل የሚለው ቃል ለዓለማቱ ጌታ ለአሏህ ግልጋሎት ላይ በፍጹም አልዋለውም፥ ከዚያ ይልቅ አሏህ "ጌታ" መሆኑን ለማመልከት የገባው ቃል "ረብ" رَبّ ነው።
አሏህ ቀጥተኛውም መንገድ ለሁሉም ይምራቸው! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዓሣ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

16፥14 እርሱም ያ ባሕርን ከእርሱ እርጥብ ሥጋን ልትበሉ እና ከእርሱም የምትለብሱትን ጌጣጌጥ ታወጡ ዘንድ ያገራ ነው፡፡ وَهُوَ الَّذِي سَخَّرَ الْبَحْرَ لِتَأْكُلُوا مِنْهُ لَحْمًا طَرِيًّا وَتَسْتَخْرِجُوا مِنْهُ حِلْيَةً تَلْبَسُونَهَا

"ደም" دَّم ማለት "ደም" ማለት ሲሆን ደም በአብዛኛው የቀይ ቀለም ያለው የአካል ፈሳሽ ሲሆን በተለያዩ የአካል ክፍሎች በመሰራጨት ለሕዋሳት ምግብ እና ኦክስጅን የሚያደርስ ነው፥ "መይታህ" مَيْتَة ማለት "ያለ እርድ የሞተ ሥጋ" ማለት ሲሆን በአገራች ቋንቋ "በክት" ይባላል። አምላካችን አሏህ ደምን መብላት እና የሞተ ሥጋን መብላት ሐራም አድርጓል፦
2፥173 በእናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትን፣ ደምን፣ የአሳማ ሥጋን እና በእርሱ ማረድ ከአላህ ስም ሌላ የተነሳበትን ነገር ብቻ ነው፡፡ إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيْكُمُ الْمَيْتَةَ وَالدَّمَ وَلَحْمَ الْخِنزِيرِ وَمَا أُهِلَّ بِهِ لِغَيْرِ اللَّهِ
16፥115 በእናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትን፣ ደምን፣ የአሳማን ሥጋ እና ያንን በመታረድ ጊዜ በእርሱ ከአላህ ስም ሌላ የተነሳበትን ብቻ ነው፡፡ إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيْكُمُ الْمَيْتَةَ وَالدَّمَ وَلَحْمَ الْخِنزِيرِ وَمَا أُهِلَّ لِغَيْرِ اللَّهِ بِهِ
6፥145 በላቸው፡- «ወደ እኔ በተወረደው ውስጥ በክት፣ ወይም ፈሳሽ ደም፣ ወይም የአሳማ ሥጋ እርሱ ርኩስ ነውና፣ ወይም በአመጽ ከአላህ ስም ሌላ በእርሱ ላይ የተወሳበት ካልኾነ በስተቀር በሚመገበው ተመጋቢ ላይ እርም የኾነን ነገር አላገኝም፡፡ قُل لَّا أَجِدُ فِي مَا أُوحِيَ إِلَيَّ مُحَرَّمًا عَلَىٰ طَاعِمٍ يَطْعَمُهُ إِلَّا أَن يَكُونَ مَيْتَةً أَوْ دَمًا مَّسْفُوحًا أَوْ لَحْمَ خِنزِيرٍ فَإِنَّهُ رِجْسٌ أَوْ فِسْقًا أُهِلَّ لِغَيْرِ اللَّهِ بِهِ

"ሐረመ" حَرَّمَ ማለት "የተከለከለ" ማለት ነው፥ ይህ ክልከላ እኛን ስለሚጎዳን እንጂ አንድ ሰው በረሃብ አሊያም በጥማት ምክንያት ሞት አፋፍ ላይ ቢሆን ደም እና የሞተ ሥጋ መብላቱ ሙባሕ ነው። ለመብላት የተገደደ ሰውም በእርሱ ላይ ኃጢኣት የለበትም፥ አምላካችን አሏህ ለነቢያችን”ﷺ ኡማህ ካነሳው ሦስት ነገሮች አንዱ የገተደዱበትን ነገር ነው፦
2፥173 ሽፍታ እና ወሰን አላፊ ሳይኾን ለመብላት የተገደደ ሰውም በእርሱ ላይ ኃጢኣት የለበትም፥ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ فَمَنِ اضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَلَا إِثْمَ عَلَيْهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
16፥115 አመጸኛም ወይም ወሰን አላፊ ሳይኾን ለመብላት የተገደደ ሰው ይፈቀድለታል፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ فَمَنِ اضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَإِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
6፥145 አመጸኛ እና ወሰን ያለፈ ሳይኾንም የተገደደ ሰው ከተወሱት ቢበላ ኃጢአት የለበትም፡፡ ጌታህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ فَمَنِ اضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَإِنَّ رَبَّكَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 10, ሐዲስ 2123
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ ”አላህ በኡማዬ ላይ ስህተት፣ መርሳት እና የገተደዱበትን ነገር አንስቷል”። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، عَنِ النَّبِيِّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏ “‏ إِنَّ اللَّهَ وَضَعَ عَنْ أُمَّتِي الْخَطَأَ وَالنِّسْيَانَ وَمَا اسْتُكْرِهُوا عَلَيْهِ

ነገር ግን በማንኛውም ወቅት እና ሁኔታ ሁለት ዓይነት የሞተ ሥጋ እና ሁለት ዓይነት ደም መብላት ሐላል ነው፥ ሁለት ዓይነት የሞተ ሥጋ ዓሣ እና አንበጣ ሲሆኑ ሁለት ዓይነት ደም ደግሞ ጉበት እና ጣፊያ ናቸው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 29, ሐዲስ 64
ዐብደሏህ ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ሁለት ዓይነት የሞተ ሥጋ እና ሁለት ዓይነት ደም ለእኛ ተፈቅዶልናል፥ ሁለት ዓይነት የሞተ ሥጋ ዓሣ እና አንበጣ ሲሆን ሁለት ዓይነት ደም ደግሞ ጉበት እና ጣፊያ ነው"። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عُمَرَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏ "‏ أُحِلَّتْ لَنَا مَيْتَتَانِ وَدَمَانِ فَأَمَّا الْمَيْتَتَانِ فَالْحُوتُ وَالْجَرَادُ وَأَمَّا الدَّمَانِ فَالْكَبِدُ وَالطِّحَالُ ‏"‏ ‏.‏

ዓሣ እና አንበጣ የማይታረዱ ሥጋ ሲሆኑ በተለይ የአንበጣ ሐላል መሆን የሚያንገሸግሻቸው አንበጣ በባይብል ሐላል መሆኑን ስለማያውቁ ነው፥ ራሱም ዮሐንስ ምግቡ አንበጣ ነበረ፦
ዘሌዋውያን 11፥22 ከእነርሱም እነዚህን "ትበላላችሁ"፤ አራቱን ዓይነት "አንበጣዎች" በየወገናቸው።
ማቴዎስ 3፥4 ራሱም ዮሐንስ የግመል ጠጉር ልብስ ነበረው፥ በወገቡም ጠፍር ይታጠቅ ነበር፤ "ምግቡም አንበጣ" እና የበረሀ ማር ነበረ።

"ጦሪይ" طَرِيّ ማለት "እርጥብ" "ትኩስ" "ስስ" "ለስላሳ" "ገር" ማለት ሲሆን ከባሕር የሚገኘውን ሥጋ ለማመልከት መጥቷል፥ ይህም እርጥብ፣ ትኩስ፣ ስስ፣ ለስላሳ፣ ገር ሥጋ ዓሣ ነው፦
16፥14 እርሱም ያ ባሕርን ከእርሱ እርጥብ ሥጋን ልትበሉ እና ከእርሱም የምትለብሱትን ጌጣጌጥ ታወጡ ዘንድ ያገራ ነው፡፡ وَهُوَ الَّذِي سَخَّرَ الْبَحْرَ لِتَأْكُلُوا مِنْهُ لَحْمًا طَرِيًّا وَتَسْتَخْرِجُوا مِنْهُ حِلْيَةً تَلْبَسُونَهَا

እንዲህ ጥያቄ ለመጠየቅ ቅንነቱ ካለ መተናነሱ ይታከልበታል፥ መተናነስ ደግሞ ከትህትና ወደ ልዕልና፣ ከእርደት ወደ እርገት፣ ከቀንበር ወደ መንበር የሚያሸጋግር መጓጓዣ ነው። ዛሬ ብዙ ወደ ኢሥላም የመጡ ሺ በክንፉ ሺ በአክናፉ የተባለላቸው ኅሩያን እና ንዑዳን የከፍታቸው ምሥጢር በመተናነስ መጠየቃቸው ነውና በቅንነት ጠይቁ!

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሪባ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥278 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ “ከአራጣም የቀረውን ተዉ”፡፡ አማኞች እንደኾናችሁ ተጠንቀቁ”፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَذَرُوا مَا بَقِيَ مِنَ الرِّبَا إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ

"ሪባ" رِّبَا የሚለው ቃል "ረበየ" رَبَّيَ ማለትም “አነባበረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “የተነባበረ” ማለት ነው፦
41፥39 አንተ ምድርን ደረቅ ኾና ማየትህም ከምልክቶቹ ነው፡፡ በእርሷም ላይ ውሃን ባወረድን ጊዜ በቡቃያዎችዋ ትላወሳለች፥ ትነፋለችም፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ أَنَّكَ تَرَى الْأَرْضَ خَاشِعَةً فَإِذَا أَنزَلْنَا عَلَيْهَا الْمَاءَ اهْتَزَّتْ وَرَبَتْ ۚ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ትነፋለችም” ለሚለው አንስታይ ግሥ የገባው ቃል “ረበት” رَبَتْ ሲሆን የስም መደቡ "ሪባ" رِّبَا ነው፥ ይህ ቋንቋዊ ፍቺው ሲሆን ሃይማኖታዊ ፍቺው "ሪባ" رِّبَا ማለት "ወለድ"interest" ወይም “አራጣ”Usury” ማለት ነው። አምላካችን አሏህ፦ "ሪባን የተነባበሩ እጥፎች ሲኾኑ አትብሉ" ብሎ ከልክሎናል፦
3፥130 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! "ሪባን የተነባበሩ እጥፎች ሲኾኑ አትብሉ"፡፡ ትድኑም ዘንድ አላህን ፍሩ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَأْكُلُوا الرِّبَا أَضْعَافًا مُّضَاعَفَةً ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ

"ወለድ" ማለት አበዳሪ አካል በጭማሬ ንዋይ ለተበዳሪ አካል የሚያበድረው ተረፈ-እሴት ነው። ወለዱ የሚሰላው በዓመት ከመቶ እጅ ነው፥ በዚህ ስሌት ለወር ወይም ለሦስት ወር አሊያም ለመንፈቅ ተስተልቶ የሚከፈል ብድርና ዕዳ ነው።
ይህም ወለድ ሁለት አይነት ነው፥ አንደኛው የብድር ወለድ ሲሆን ሌላው የዕዳ ወለድ ነው። እነዚህን እንመልከት፦

፨የብድር ወለድ”Simple interest” ሆኖ ሲጀመር መርሑ “P” × “R” × “N” = “S” ነው፥ ይህ መርሕ ሲተነተን፦
1. “P” ማለት “ዋና ገንዘብ”Principal Amount” ማለት ነው።
2. “R” ማለት “የወለድ ልኬት”Interest Rate” ማለት ነው።
3. “N” ማለት “የብድር ጊዜ”Term of the loan”​ ማለት ነው።
4. “S” ማለት “የብድር ወለድ”Simple interest” ማለት ነው።

ለምሳሌ፦ 100,000 ዋና ገንዘብ ቢሆን፣ 0.05% የወለድ ልኬት ቢሆን፣ 3 ዓመት የብድር ጊዜ ቢሆን የብድር ወለዱ 15,000 ይሆናል። በዓመት ከ 100,000 ላይ 5% እየተወሰደ ለ 3 ዓመት ከተከፈለ የሚከፍለው ወለድ 15,000 ይመጣል፥ 100,000 x 0.05 x 3 =15,000 ይሆናል።
ይህ የብድር ወለድ በተባለው ሦስት ዓመት ካልተከፈለ የዕዳ ወለድ ይሆናል።

፨የዕዳ ወለድ"Compound interest" የብድሩ መክፈያ ወቅት ደርሶ ተበዳሪው በቃሉ መሠረት መክፈል ሳይችል ሲቀር በብድሩ መጠን ላይ የሚደረግ ጭማሪ ነው፡፡ በዓመት ከ 100,000 ላይ 5% እየተወሰደ ለ 3 ዓመት የሚከፍለው ወለድ፦
4ኛ ዓመት ላይ 10%
5ኛ ዓመት ላይ 15%
6ኛ ዓመት 20% እያለ ዕዳው እየጨመረ ይመጣል።
4ኛ ዓመት ላይ 100,000 x 0.10 x 3 =30,000 ይሆናል።
5ኛ ዓመት ላይ 100,000 x 0.15 x 4 =60,000 ይሆናል።
6ኛ ዓመት ላይ 100,000 x 0.20 x 5 =100,000 ይሆናል።
እንዲህ እያለ እስከ በብድር ላይ ወለድ በልቶ ከኪሳራው እጁን ለማውጣት ማስያዣ”collateral” የቤት ካርታ፣ የሰው ዋስ እና የቋሚ ቅጥር ማስረጃ ድረስ ይሞለጭፉታል። ወለድ ወለድን ሲወልድ ዕዳው እልፍ፣ አእላፍ፣ አእላፋት፣ ትእልፊት፣ ምእልፊት እያለ ይቀጥላል። ወለድ እየተነባበረ ሲመጣ በረከትን ያጠፋል፥ ከወለድ በሰዎች ገንዘቦች ውስጥ ይጨመር ዘንድ የሚሰጠው አሏህ ዘንድ ኪሳራ እንጂ አይጨምርም፦
2፥276 ”አላህ ሪባን በረከቱን ያጠፋል፡፡ ምጽዋቶችንም ያፋፋል፡፡ አላህም ኃጠኢተኛ ከሓዲን ሁሉ አይወድም፡፡ يَمْحَقُ اللَّهُ الرِّبَا وَيُرْبِي الصَّدَقَاتِ ۗ وَاللَّهُ لَا يُحِبُّ كُلَّ كَفَّارٍ أَثِيمٍ
30፥39 ”ከሪባም በሰዎች ገንዘቦች ውስጥ ይጨመር ዘንድ የምትሰጡት አላህ ዘንድ አይጨምርም”*ም፡፡ ከምጽዋትም የአላህን ፊት የምትሹ ሆናችሁ የምትሰጡት እነዚያ ሰጪዎች አበርካቾች እነርሱ ናቸው፡፡ وَمَآ ءَاتَيْتُم مِّن رِّبًۭا لِّيَرْبُوَا۟ فِىٓ أَمْوَٰلِ ٱلنَّاسِ فَلَا يَرْبُوا۟ عِندَ ٱللَّهِ ۖ وَمَآ ءَاتَيْتُم مِّن زَكَوٰةٍۢ تُرِيدُونَ وَجْهَ ٱللَّهِ فَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْمُضْعِفُونَ

በጥንት ጊዜ “ወለድ” እራሱ ከብድር ወለድ ወደ ዕዳ ወለድ ሲሸጋገር “አራጣ” ይባላል። ነገር ግን ምዕራባውያን ለማምታታት “ወለድ” ማለት በተቋም የሚያበድር ሕጋዊ አካል ሲሆን “አራጣ” ማለት ግን በግለሰብ የሚያበድር ሕገወጥ አካል አርገው ነው ያስቀመጡት። በተቋም ደረጃ በወለድ የሚያበድር አካል ሆነ በግለሰብ ደረጃ በወለድ የሚያበድር አካል ልዩነታቸው ሕጋዊ ሌብነት እና ሕገወጥ ሌብነት ብቻ ነው። አምላካችም አሏህ፦ “ገንዘቦቻችሁን በመካከላችሁ “ያለ አግባብ” ማለትም “በቁማር፣ በሪባ፣ በጉቦ፣ በስርቆት” አትብሉ” ብሎ ከልክሎናል፦
2፥188 ”ገንዘቦቻችሁንም በመካከላችሁ ያለ አግባብ አትብሉ፡፡ እናንተም የምታውቁ ስትኾኑ ከሰዎች ገንዘቦች ከፊልን በኃጢኣት ትበሉ ዘንድ ወደ ዳኞች አትጣሏት”፡፡ وَلَا تَأْكُلُوا أَمْوَالَكُم بَيْنَكُم بِالْبَاطِلِ وَتُدْلُوا بِهَا إِلَى الْحُكَّامِ لِتَأْكُلُوا فَرِيقًا مِّنْ أَمْوَالِ النَّاسِ بِالْإِثْمِ وَأَنتُمْ تَعْلَمُون

ሚሽነሪዎች፦ "ሪባ" ማለት "አራጣ" እንጂ "ወለድ" ማለት አይደለም፥ ስለዚህ "ወለድ" ክልክል የሆነበት ጥቅስ የለም" የሚሉት አንደኛ ስለ ወለድ እና አራጣ እሳቦቱ በቅጡ ስላልተረዱ እና ጥራዝ ነጠቅ ዕውቀት ስላላቸው ነው፥ ሁለተኛ ወለድ ሐርም ስለመሆኑ ከባይብሉ በጥሞና ስላናበቡ እና ጥራዝ ጠለቅ ዕውቀት ስለሌላቸው ነው። በባይብል በወለድ ማበደር ሐራም ነው፦
ዘሌዋውያን 25፥37 ብርህን በወለድ አታበድረው። وَلَا تَأْخُذْ مِنْ ذَلِكَ الشَّخصِ رِبًا
ዘዳግም 23፥19 ለወንድምህ በወለድ አታበድር፤ የብር ወይም የእህል ወይም የማናቸውንም ነገር ሁሉ ወለድ አትውሰድ። لَا تَفْرِضُوا الرِّبَا عَلَى أحَدٍ مِنْ بَنِي إسْرَائِيلَ يَقْتَرِضُ مِنْكُمْ مَالًا أوْ طَعَامًا أوْ أيَّ شَيءٍ آخَرَ

ሁለቱም አናቅጽ ላይ "ወለድ" ለሚለው የገባው ቃል "ሪባ" رِبًا መሆኑን ልብ አድርጉ! ቅሉ ግን ይህ ሕግ የሚሠራው ለአይሁዳውያን እንጂ አይሁዳውያን ከአይሁዳውያን ውጪ ያሉትን በወለድ ማበደር ሐላል ነው፦
ዘዳግም 23፥20 ለእንግዳው በወለድ አበድረው!

በኢሥላም ሸሪዓህ ግን ለማንም በወለድ ማበደር ሆነ ከማንም በወለድ መበደር ሐራም ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ተእዊል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

12፥6 «እንደዚሁም እንዳየኸው ጌታህ ይመርጥሃል፡፡ *ከንግግሮችም ትርጉምን ያስተምርሃል"*፡፡ وَكَذَٰلِكَ يَجْتَبِيكَ رَبُّكَ وَيُعَلِّمُكَ مِن تَأْوِيلِ الْأَحَادِيثِ

"ተእዊል" تَأْوِيل የሚለው ቃል "አወለ" أَوَّلَ ማለትም "ተሮጎመ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ትርጉም"interpretation" ማለት ነው፥ በሌላ መልኩ "ተእዊል" تَأْوِيل የሚለው ቃል "አወለ" أَوَّلَ ማለትም "ጨረሰ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መጨረሻ" ማለት ነው፦
4፥59 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ መልክተኛውን እና ከእናንተም የስልጣን ባለቤቶችን ታዘዙ፡፡ *”በማንኛውም ነገር ብትከራከሩ በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ብትኾኑ የተከራከራችሁበትን ነገር ወደ አላህ እና ወደ መልክተኛው መልሱት፡፡ ይህ የተሻለ "መጨረሻውም" ያማረ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَطِيعُوا اللَّهَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ وَأُولِي الْأَمْرِ مِنكُمْ ۖ فَإِن تَنَازَعْتُمْ فِي شَيْءٍ فَرُدُّوهُ إِلَى اللَّهِ وَالرَّسُولِ إِن كُنتُمْ تُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ ۚ ذَٰلِكَ خَيْرٌ وَأَحْسَنُ تَأْوِيلًا

እዚህ አንቀጽ ላይ "መጨረሻው" ለሚለው ቃል የገባው ቃል "ተእዊላ" تَأْوِيلًا መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። ቁርኣን ላይ ተመሳሳይ ቃል ቢኖረው እንኳን ተመሳሳይ አሳብና ትርጉም አለው ማለት አይደለም። የአንድን ቃል አማራጭ ትርጉም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ ቅቡል ነው። መታየት ያለበት ቃሉ ሳይሆን ቃሉ የወከለው አሳብ ነው። ነቢያችን"ﷺ" በቁርኣን ከተሰጣቸው አንዱ አንድ ቃላት ሰፊ ትርጉም ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 21, ሐዲስ 7
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"በነቢያት ላይ በስድስት ነገር ከብሬአለው፥ እርሱም፦ "ጀዋሚዓል ከሊም ተሰቶኛል፣ በጠላት ልብ ውስጥም ፍርሀት እንዲጣል በመደረግ ተረዳኹኝ፣ የምርኮ ገንዘብ ሐላል ሆነውልኛል፣ ምድር በጠቅላላ ጡሀራና የመስገጃ ክልል ተደረገልኝ፣ ለፍጡራን ሁሉ ተላኩኝ፣ የነቢያት መደምደሚያ ሆንኩኝ"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ فُضِّلْتُ عَلَى الأَنْبِيَاءِ بِسِتٍّ أُعْطِيتُ جَوَامِعَ الْكَلِمِ وَنُصِرْتُ بِالرُّعْبِ وَأُحِلَّتْ لِيَ الْغَنَائِمُ وَجُعِلَتْ لِيَ الأَرْضُ مَسْجِدًا وَطَهُورًا وَأُرْسِلْتُ إِلَى الْخَلْقِ كَافَّةً وَخُتِمَ بِيَ النَّبِيُّون

"ጀዋሚዓል ከሊም" جَوَامِعَ الْكَلِم የሁለት ቃላት ውቅር ነው፥ የጀዋሚዕ እና የከሊም ነው። "ጀዋሚዕ" جَوَامِع ማለት "ብዛት" ማለት ሲሆን በነጠላ "ጃሚዕ" جَامِع ሲሆን ደግሞ "ብዙ" ማለት ነው። "ከሊም" كَلِم ወይም "ከሊማት" كَلِمَات ማለት "ቃላት" ማለት ሲሆን በነጠላ "ከሊማህ" كَلِمَة ሲሆን ደግሞ "ቃል" ማለት ነው። "ጀዋሚዓል ከሊም" ማለት "አንድ ቃል ሆኖ ብዛት ቃላት ያለው ትርጉም" ማለት ነው። ይህንን ከተረዳን ዘንዳ እዚህ አርስት ላይ "ተእዊል" تَأْوِيل የሚለው ቃል የምናየው "ትርጉም"interpretation" በሚለው እሳቤ ነው፦
3፥7 *"እርሱ ያ በአንተ ላይ መጽሐፉን ያወረደ ነው፡፡ ከእርሱ ከመጽሐፉ ግልጽ የኾኑ አንቀጾች አሉ፡፡ እነርሱ የመጽሐፉ መሠረቶች ናቸው፡፡ ሌሎችም ምሳሌአዊ አንቀጾች አሉ፡፡ እነዚያማ በልቦቻቸው ውስጥ ጥመት ያለባቸው ሰዎች ማሳሳትን ለመፈለግ እና ትርጉሙን ለመፈለግ ከእርሱ ሙተሻቢውን ይከታተላሉ፡፡ ፍቺውን አላህ እና በዕውቀትም የጠለቁት ብቻ እንጅ ሌላ አያውቀውም፡፡ እነርሱም፦ «በእርሱ አምነናል፤ ሁሉም ከጌታችን ዘንድ ነው» ይላሉ፡፡ የአእምሮ ባለቤቶችም እንጅ ሌላው አይገሰጽም"*፡፡ هُوَ الَّذِي أَنزَلَ عَلَيْكَ الْكِتَابَ مِنْهُ آيَاتٌ مُّحْكَمَاتٌ هُنَّ أُمُّ الْكِتَابِ وَأُخَرُ مُتَشَابِهَاتٌ ۖ فَأَمَّا الَّذِينَ فِي قُلُوبِهِمْ زَيْغٌ فَيَتَّبِعُونَ مَا تَشَابَهَ مِنْهُ ابْتِغَاءَ الْفِتْنَةِ وَابْتِغَاءَ تَأْوِيلِهِ ۗ وَمَا يَعْلَمُ تَأْوِيلَهُ إِلَّا اللَّهُ ۗ وَالرَّاسِخُونَ فِي الْعِلْمِ يَقُولُونَ آمَنَّا بِهِ كُلٌّ مِّنْ عِندِ رَبِّنَا ۗ وَمَا يَذَّكَّرُ إِلَّا أُولُو الْأَلْبَابِ

ከላይ ያቀረብኩት ከዐረቢኛው ጋር ተቀራራቢ ትርጉም ያለውን የሻኪር ትርጉም ነው። "ሙሕከማት" مُّحْكَمَات ማለት "ግልጽ"clear" ማለት ነው፥ የመጽሐፉ መሠረት የሆኑት የኢሥላም እና የኢማን መሠረት ግልጾች አናቅጽ ናቸው። "ሙተሻቢያት" مُتَشَابِهَات ማለት "ምሳሌአዊ"allegorical" ማለት ነው፥ ምሳሌአዊ አናቅጽን ትርጉም አላህ እና በዕውቀትም የጠለቁት እንጂ ሌላ ማንም ዐያውቀውም። ለምሳሌ ዩሱፍ ለአባቱ፡- «አባቴ ሆይ! እኔ ዐስራ አንድ ከዋክብትን ፀሐይንና ጨረቃንም በሕልሜ አየሁ፡፡ ለእኔ ሰጋጆች ሆነው አየኋቸው» ብሏል፦
12፥4 *"ዩሱፍ ለአባቱ፡- «አባቴ ሆይ! እኔ ዐስራ አንድ ከዋክብትን ፀሐይንና ጨረቃንም በሕልሜ አየሁ፡፡ ለእኔ ሰጋጆች ሆነው አየኋቸው» ባለ ጊዜ አስታውስ"*፡፡ إِذْ قَالَ يُوسُفُ لِأَبِيهِ يَا أَبَتِ إِنِّي رَأَيْتُ أَحَدَ عَشَرَ كَوْكَبًا وَالشَّمْسَ وَالْقَمَرَ رَأَيْتُهُمْ لِي سَاجِدِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ የተቀመጡት ከዋክብት የዩሱፍ ወንድሞች፣ ፀሐይ አባቱ፣ ጨረቃ እናቱ ናቸው፦
12፥6 «እንደዚሁም እንዳየኸው ጌታህ ይመርጥሃል፡፡ *"ከንግግሮችም ትርጉምን ያስተምርሃል"*፡፡ وَكَذَٰلِكَ يَجْتَبِيكَ رَبُّكَ وَيُعَلِّمُكَ مِن تَأْوِيلِ الْأَحَادِيثِ
12፥100 *"ወላጆቹንም በዙፋኑ ላይ አወጣቸው፡፡ ለእርሱም ሰጋጆች ኾነው ወረዱለት፡፡ «አባቴም ሆይ! ይህ ፊት ያየኋት ሕልሜ ትርጉም ነው፡፡ ጌታ በእርግጥ እውነት አደረጋት"*፡፡ وَرَفَعَ أَبَوَيْهِ عَلَى الْعَرْشِ وَخَرُّوا لَهُ سُجَّدًا ۖ وَقَالَ يَا أَبَتِ هَـٰذَا تَأْوِيلُ رُؤْيَايَ مِن قَبْلُ قَدْ جَعَلَهَا رَبِّي حَقًّا

"ትርጉም" ለሚለው ቃል ሁለቱም አናቅጽ ላይ "ተእዊል" تَأْوِيل መሆኑን ልብ በል። ከዋክብት፣ ፀሐይ፣ ጨረቃ ትርጉም ይዞ መምጣቱ አንባቢ ልብ ይለዋል። ልክ እንደዚሁ በምሳሌአዊ አነጋገር ነቢያችን"ﷺ" በራእይ ወተት እና ልብስ አይተው ነበር፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 62, ሐዲስ 31
የሐምዛህ አባት እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ተኝቼ ሳለ የሚጠጣ ነገር አየሁኝ፥ ከጣቶቼ በሚፈልቁት ወተት በማየት እየረካው ነበር። ከዚያም ለዑመር ሰጠሁት። ባልደረቦቻቸውም፦ "ትርጉሙ ምንድን ነው? ብለው ጠየቁ፥ እርሳቸውም፦ "ዕውቀት ነው" አሉ"*። قَالَ أَخْبَرَنِي حَمْزَةُ، عَنْ أَبِيهِ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ بَيْنَا أَنَا نَائِمٌ شَرِبْتُ ـ يَعْنِي اللَّبَنَ ـ حَتَّى أَنْظُرُ إِلَى الرِّيِّ يَجْرِي فِي ظُفُرِي أَوْ فِي أَظْفَارِي، ثُمَّ نَاوَلْتُ عُمَرَ ‏"‌‏.‏ فَقَالُوا فَمَا أَوَّلْتَهُ قَالَ ‏"‏ الْعِلْمَ ‏"‌‏.‏
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 44, ሐዲስ 20
አቢ ሠዒድ አል-ኹድሪይ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ተኝቼ ሳለ ሰዎች ወደ እኔ ቀርበው፥ ልብስ ለብሰዋል። አንዳንዶቹ እስከ ደረታቸው፥ አንዳንዶቹ ከዚያ ባሻገር ለብሰዋል። ከዚያ ወደ ዑመር ኢብኑል ኸጧብ አለፈ፥ የእርሱ ልብስ ግን የተለቀቀ ነው። ባልደረቦቻቸውም፦ "ትርጉሙ ምንድን ነው? ብለው ጠየቁ፥ እርሳቸውም፦ "ዲን ነው" አሉ"*። بْنُ سَهْلٍ أَنَّهُ سَمِعَ أَبَا سَعِيدٍ الْخُدْرِيَّ، يَقُولُ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ بَيْنَا أَنَا نَائِمٌ رَأَيْتُ النَّاسَ يُعْرَضُونَ وَعَلَيْهِمْ قُمُصٌ مِنْهَا مَا يَبْلُغُ الثُّدِيَّ وَمِنْهَا مَا يَبْلُغُ دُونَ ذَلِكَ وَمَرَّ عُمَرُ بْنُ الْخَطَّابِ وَعَلَيْهِ قَمِيصٌ يَجُرُّهُ ‏"‏ ‏.‏ قَالُوا مَاذَا أَوَّلْتَ ذَلِكَ يَا رَسُولَ اللَّهِ قَالَ ‏"‏ الدِّينَ ‏"‏ ‏.‏

ወተቱ ዕውቀት፥ ልብሱ ዲን መሆኑን ከተረዳን የተእዊል እሳቤ ከሞላ ጎደል ይህንን ይመስላል። ይህ አተረጓጎም የቁርኣንን መሠረትና ውቅር፣ ዋልታና ማገር፣ ጥልቀትና ስፋት፣ ድርና ማግ በቅጡ በማወቅ የጠለቁት ያውቁታል። ለምሳሌ አላህ ኢብኑ ዐባሥ የቁርኣንን ትርጉም አስተምሮታል፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 171
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ያዙኛና እንዲህ አሉ፦ *"አላህ ሆይ! ጥበብን እና የመጽሐፉ ትርጉም አስተምረው"*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ ضَمَّنِي رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ إِلَيْهِ وَقَالَ ‏ "‏ اللَّهُمَّ عَلِّمْهُ الْحِكْمَةَ وَتَأْوِيلَ الْكِتَابِ

"ትርጉም" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ተእዊል" تَأْوِيل ነው። ቁርኣን ሁሌም ያጅባል፥ አንድ መጽሐፍ ሆኖ ውስጡ ግን ቢያስተነትኑት የማያልቅ ብዙ መጽሐፍት ይዟል። የአእምሮዎች ባለቤቶች በውስጡ ያሉትን አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑ እና እንዲገሰጹ አላህ አውርዶታል፦
98፥3 *"በውስጧ ቀጥተኛ የኾኑ መጽሐፍት ያሉባት የኾነችን"*፡፡ فِيهَا كُتُبٌ قَيِّمَةٌ
38፥29 *"ይህ ወደ አንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሐፍ ነው፥ የአእምሮዎች ባለቤቶችም አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑ እና እንዲገሰጹ አወረድነው"*፡፡ كِتَابٌ أَنزَلْنَاهُ إِلَيْكَ مُبَارَكٌ لِّيَدَّبَّرُوا آيَاتِهِ وَلِيَتَذَكَّرَ أُولُو الْأَلْبَابِ

"መጽሐፍት ያሉባት" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። “እንዲያስተነትኑ” ለሚለው ቃል የገባው “ሊየደበሩ” لِيَدَّبَّرُوا መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። “ተደቡር” تَدَبُر ማለት “ማስተንተን” ማለት ነው፥ “ዱቡር” دُبُر ማለት እራሱ “ጀርባ” ማለት ሲሆን ከቁርኣን ሑሩፍ በስተ-ጀርባ ያለውን ዕውቀት መረዳት ተደቡር ይባላል። አላህ አንቀጾቹን ከሚያስተነትኑና ከሚገሰጹ የአእምሮዎች ባለቤቶች ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ጦመኛ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

33፥35 "ጦመኛ ወንዶች እና ጦመኛ ሴቶችም፣ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች ወንዶች እና ጠባቂ ሴቶችም፣ አላህን በብዙ አውሺዎች ወንዶች እና አውሺዎች ሴቶችም አላህ ለእነርሱ ምሕረትን እና ታላቅን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል"፡፡ وَالصَّائِمِينَ وَالصَّائِمَاتِ وَالْحَافِظِينَ فُرُوجَهُمْ وَالْحَافِظَاتِ وَالذَّاكِرِينَ اللَّهَ كَثِيرًا وَالذَّاكِرَاتِ أَعَدَّ اللَّهُ لَهُم مَّغْفِرَةً وَأَجْرًا عَظِيمًا

በትንሣኤ ቀን የሚያገኙት ምንዳ ምን ያክል እንደሆነ ያልተገለጸ እና ምንዳቸው ያለ ግምት የሚከፈላቸው ሦስት ሰዎች፦
1ኛ. ትዕግሥተኛ፦
39፥10 "ታጋሾቹ ምንዳቸውን የሚያገኙት ያለግምት ነው"፡፡ إِنَّمَا يُوَفَّى الصَّابِرُونَ أَجْرَهُم بِغَيْرِ حِسَابٍ

2ኛ. ይቅር ባይ፦
42፥40 "ይቅርም ያለ እና ያሳመረ ሰው ምንዳው በአላህ ላይ ነው"፡፡ فَمَنْ عَفَا وَأَصْلَحَ فَأَجْرُهُ عَلَى اللَّهِ

3ኛ. ጦመኛ፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 33, ሐዲስ 167
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "የአደም ልጅ ማንኛውም ሥራው በአሥር እና በሰባት መቶ መካከል ሐሠናህ ይበዛለታል፥ አሏህ ሡብሓነሁ እንዲህ አለ፦ "ጦም ሲቀር። ጦም ለእኔ ነው፥ ምንዳውንም እኔ እከፍለዋለው"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ "‏ كُلُّ عَمَلِ ابْنِ آدَمَ يُضَاعَفُ لَهُ الْحَسَنَةُ بِعَشْرِ أَمْثَالِهَا إِلَى سَبْعِمِائَةِ ضِعْفٍ ‏.‏ قَالَ اللَّهُ سُبْحَانَهُ إِلاَّ الصَّوْمَ فَإِنَّهُ لِي وَأَنَا أَجْزِي بِهِ ‏"‏ ‏.‏

ናቸው። በተጨማሪም ሦስት ሰዎች ልመናቸው ተመላሽ አይሆንም፥ እነርሱም፦ “እስኪያፈጥር ድረስ ያለ ጦመኛ፣ ፍትሐዊ መሪ እና የተበዳይ ልመና ናቸው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 48, ሐዲስ 229
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ሦስት ሰዎች ልመናቸው ተመላሽ አይሆንም፥ እነርሱም፦ “እስኪያፈጥር ድረስ ያለ ጦመኛ፣ ፍትሐዊ መሪ እና የተበዳይ ልመና ናቸው”። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ ثَلاَثَةٌ لاَ تُرَدُّ دَعْوَتُهُمُ الصَّائِمُ حَتَّى يُفْطِرَ وَالإِمَامُ الْعَادِلُ وَدَعْوَةُ الْمَظْلُومِ “‏

ጦመኛን ያስፈጠረ ጦመኛው ከሚያገኘውን ምንዳ ምንም ሳይቀነስ ጦመኛው ሊያገኘው የሚችለውን ምንዳ ያገኛል፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 7, ሐዲስ 109
ዘይድ ኢብኑ ኻሊድ አል ጁሀኒይ እንደተረከው፦ የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ጦመኛን ያስፈጠረ ጦመኛው ከሚያገኘውን ምንዳ ምንም ሳይቀነስ ጦመኛው ሊያገኘው የሚችለውን ምንዳ ያገኛል"። عَنْ زَيْدِ بْنِ خَالِدٍ الْجُهَنِيِّ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ "‏ مَنْ فَطَّرَ صَائِمًا كَانَ لَهُ مِثْلُ أَجْرِهِمْ مِنْ غَيْرِ أَنْ يَنْقُصَ مِنْ أُجُورِهِمْ شَيْئًا ‏"‏ ‏.‏

በተለይ መሳኪኖች፣ ድውያንን እና ለዲናቸው ሲሉ ከቤታቸው የተባረሩ ሠለምቴዎችን ማስፈጠር አንርሳ! አምላካችን አሏህ ጦመኛ ወንድ ባሪያውን "ሷኢም" صَّائِم ሲለው ጦመኛ ሴት ባሪያውን ደግሞ "ሷኢማህ" صَّائِمَة ይላታል፥ ለእነርሱ ምሕረትን እና ታላቅን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል፦
33፥35 "ጦመኛ ወንዶች እና ጦመኛ ሴቶችም፣ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች ወንዶች እና ጠባቂ ሴቶችም፣ አላህን በብዙ አውሺዎች ወንዶች እና አውሺዎች ሴቶችም አላህ ለእነርሱ ምሕረትን እና ታላቅን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል"፡፡ وَالصَّائِمِينَ وَالصَّائِمَاتِ وَالْحَافِظِينَ فُرُوجَهُمْ وَالْحَافِظَاتِ وَالذَّاكِرِينَ اللَّهَ كَثِيرًا وَالذَّاكِرَاتِ أَعَدَّ اللَّهُ لَهُم مَّغْفِرَةً وَأَجْرًا عَظِيمًا

አሏህ "ሷኢሚን" صَّآئِمِين እና "ሷኢማት" صَّآئِمَٰت ከሚላቸው ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የጁሙዓህ ፈርድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

62፥9 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በጁሙዓህ ቀን ለሶላት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا نُودِيَ لِلصَّلَاةِ مِن يَوْمِ الْجُمُعَةِ فَاسْعَوْا إِلَىٰ ذِكْرِ اللَّهِ

"ፈርድ" فَرْض የሚለው ቃል "ፈረደ" فَرَضَ ማለትም "ተገደደ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ግዴታ"obligatory" ማለት ነው፥ አንድን ነገር በማድረግ ምንዳ የሚያስገኝ በተቃራኒው ባለማድረግ ፍዳን የሚያስገኝ መርሕ ፈርድ ይባላል። ፈርድ በሁለት ይከፈላል፥ እርሱም "ፈርዱል ዐይን" فَرْض العَيْن እና "ፈርዱል ኪፋያህ" فَرْض الكِفَايَة ናቸው።
"ዐይን" عَيْن የሚለው ቃል "ዓነ" عَانَ‎ ማለትም "ነጠለ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ተናጥል" ማለት ነው። "ፈርዱል ዐይን” فَرْض العَيْن ማለት "የተናጥል ግዴታ" ማለት ነው፥ ፈርዱል ዐይን የሚባሉት ለምሳሌ ሶላት፣ ሐጅ፣ ዘካህ፣ ፆም ወዘተ ናቸው።
"ኪፋያህ" كِفَايَة የሚለው ቃል "ከፋ" كَفَى ማለትም "ጠቀለለ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ጥቅል" ማለት ነው። "ፈርዱል ኪፋያህ" فَرْض الكِفَايَة ማለት "የጥቅል ግዴታ" ማለት ነው፥ ፈርዱል ኪፋያህ የሚባሉት ለምሳሌ "ደዕዋህ" دَعْوَة እና "ሶላቱል ጀናዛህ" صَّلَات الجَنَازَة ናቸው።
"ሶላቱል ጁሙዓህ” صَّلَات الْجُمُعَة ግን "ፈርዱል ዐይን” فَرْض العَيْن ነው፥ ለዚህም አምላካችን አሏህ፦ "በጁሙዓህ ቀን ለሶላት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ" በማለት አዞናል፦
62፥9 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በጁሙዓህ ቀን ለሶላት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا نُودِيَ لِلصَّلَاةِ مِن يَوْمِ الْجُمُعَةِ فَاسْعَوْا إِلَىٰ ذِكْرِ اللَّهِ

ጁሙዓህ መታደም ምንዳ የሚያስገኝ በተቃራኒው ባለማድረግ ፍዳን የሚያስገኝ ፈርዱል ዐይን ሲሆን እሩቅ ሳንሄድ ማንም በስንፍና ሦስት ተከታታይ ጁሙዓህ የተወ አሏህ በልቡ ላይ ያትምበታል፦
ሡነን አቢ ዳድው መጽሐፍ 2, ሐዲስ 663
አቢ አል-ጀዕድ አድ-ዶምሪይ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ማንም በስንፍና ሦስት ተከታታይ ጁሙዓህ የተወ አሏህ በልቡ ላይ ያትምበታል"። عَنْ أَبِي الْجَعْدِ الضَّمْرِيِّ، - وَكَانَتْ لَهُ صُحْبَةٌ - أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ مَنْ تَرَكَ ثَلاَثَ جُمَعٍ تَهَاوُنًا بِهَا طَبَعَ اللَّهُ عَلَى قَلْبِهِ ‏"‏ ‏.‏

የጁሙዓህ ፈርድ በሙሥሊም ሴት ላይ፣ በባርነት ቀንበር ውስጥ ላለ አገልጋይ ላይ፣ ለአቅመ አደም ላልደረሰ ልጅ ላይ፣ በጉዞ ላይ ላለ ሙሣፊር ላይ፣ በሽታ በያዘው ህመምተኛ ላይ፣ በድውይ ለተጠቃ ሰው ላይ እና በድካም ላለ አረጋዊ ላይ ግዳጅ አይደለም፡፡ አምላካችን አሏህ ለሁላችንም ጁሙዓን የምንታደምበትን ቁዋ ይወድቀን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሶላት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

4፥103 ሶላት በምእምናን ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናትና፡፡ إِنَّ الصَّلَاةَ كَانَتْ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ كِتَابًا مَّوْقُوتًا

"ሩክን" رُكْن ማለት "ምሰሶ" "ዐምድ" "ማዕዘን" ማለት ሲሆን የሩክን ብዙ ቁጥር ደግሞ "አርካን" أَرْكَان ሲሆን "ምሰሶች" "አዕማድ" "ማዕዘናት" ማለት ነው፥ በጥቅሉ "አርካኑል ኢሥላም" أَرْكَان الْإِسْلَٰم ማለት "የኢሥላም ምሰሶች" "የኢሥላም አዕማድ" "የኢሥላም ማዕዘናት" ማለት ነው። ከአርካኑል ኢሥላም አንዱ ሶላት ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 40, ሐዲስ 4
ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ”ኢሥላም በአምስቱ መሠረቶች ላይ ተገንብቷል፤ እነርሱም፦ “ከአሏህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፥ ሙሐመድም የአሏህ መልእክተኛ ነው” በሚል ምስክርነት፣ ሶላትን በመቆም፣ ዘካህን በመስጠት፣ ረመዷንን በመፆም እና የአላህ በይት በመጎብኘት”። عَنِ ابْنِ عُمَرَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ بُنِيَ الإِسْلاَمُ عَلَى خَمْسٍ شَهَادَةُ أَنْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللَّهِ وَإِقَامُ الصَّلاَةِ وَإِيتَاءُ الزَّكَاةِ وَصَوْمُ رَمَضَانَ وَحَجُّ الْبَيْتِ

"ሶላት" صَلَاة የሚለው ቃል "ሶላ" صَلَّىٰ ማለትም "ጸለየ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ጸሎት" ማለት ነው፥ "ሶላት" صَلَاة በውስጡ ሦስት ዐበይት ክፍሎች ያቅፋል። እነርሱም፦
1ኛ. "ቂያም" قِيَام ማለትም "መቆም"
2ኛ. "ሩኩዕ" رُكوع ማለትም "ማጎንበስ"
3ኛ. "ሡጁድ" سُّجُود ማለትም "ስግደት" ናቸው፦
22፥77 እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ! በስግደታችሁ አጎንብሱ፣ በግንባራችሁም ተደፉ፣ ጌታችሁንም አምልኩ፣ በጎንም ነገር ሥሩ፣ ልትድኑ ይከጀልላችኋልና፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا ارْكَعُوا وَاسْجُدُوا وَاعْبُدُوا رَبَّكُمْ وَافْعَلُوا الْخَيْرَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ ۩

ሶላትን ደንቡን ጠብቀው የሚቆሙ፣ የሚያጎነብሱ እና የሚሰግዱ "ሙሶሊን" مُصَلِّين ይባላሉ፥ አመጸኞች በሰቀር ውስጥ ሆነው ለምን በሰቀር ውስጥ ገባችሁ? ሲባሉ፦ "ከሙሶሊን አልነበርንም" የሚል መልስ ይሰጣሉ፦
74፥43 እነርሱም፦ «ከሙሶሊን አልነበርንም» ይላሉ። قَالُوا لَمْ نَكُ مِنَ الْمُصَلِّينَ

ሙሰሊን በቂያም "ሙቂሚን" مُّقِيمِين ሲባሉ፣ በሩኩዕ "ራኪዒን" رَّاكِعِين ሲባሉ፣ በሱጁድ ደግሞ "ሣጂዲን" سَاجِدِين ይባላሉ። ሶላት በምእምናን ላይ በአምስት ወቅት ጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናት፥ ኢማን እና ኩፍርን ለይቶ በመካከል ያለው ግድግዳ ሶላት ነው፦
4፥103 ሶላት በምእምናን ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናትና፡፡ إِنَّ الصَّلَاةَ كَانَتْ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ كِتَابًا مَّوْقُوتًا
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 40, ሐዲስ 13
ጃቢር እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "በኢማን እና በኩፍር መካከል የሚለየው ሶላት ነው"። عَنْ جَابِرٍ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ بَيْنَ الْكُفْرِ وَالإِيمَانِ تَرْكُ الصَّلاَةِ

ከነቢያችን”ﷺ” በፊት በነበሩት ነቢያት በቀን አምስት ጊዜ ሶላት ላይቆሙ ይችላሉ፥ ወይ ያንሳል አሊያም ይበዛ ይሆናል። ነገር ግን አሏህ ሶላትን መስገድ ወደ እነርሱ አውርዷል፦
21፥73 ”ወደ እነርሱም መልካም ሥራዎችን መሥራትን፣ ሶላትንም መስገድን፣ ዘካንም መስጠትን አወረድን”፡፡ وَأَوْحَيْنَآ إِلَيْهِمْ فِعْلَ ٱلْخَيْرَٰتِ وَإِقَامَ ٱلصَّلَوٰةِ وَإِيتَآءَ ٱلزَّكَوٰة

"ፈሕሻእ" فَحْشَاء ማለት "መጥፎ ቃላት" ማለት ሲሆን "ሙንከር" مُنكَر ደግሞ "መጥፎ ሥራ" ነው፥ ሁለቱም የሸይጧን እርምጃዎች ናቸው። ሶላት ግን በኢማን፣ በኢኽላስ እና በኢትባዕ ከተፈጸመች ከፈሕሻእ እና ከሙንከር ነገር ሁሉ ትከለክላለች፦
24፥21 እርሱ በመጥፎ እና በሚጠላ ነገር ያዛልና፡፡ فَإِنَّهُ يَأْمُرُ بِالْفَحْشَاءِ وَالْمُنكَرِ
29፥45 ሶላት ከመጥፎ እና ከሚጠላ ነገር ሁሉ ትከለክላለችና፡፡ አላህንም ማውሳት ከሁሉ ነገር በላጭ ነው። إِنَّ الصَّلَاةَ تَنْهَىٰ عَنِ الْفَحْشَاءِ وَالْمُنكَرِ ۗ وَلَذِكْرُ اللَّهِ أَكْبَرُ

ሶላት በዱንያህ የምታስረዳ እና አሏህ በሚፈሩት ላይ ቀላት ናት፥ በአኺራ ደግሞ የጀናህ ቁልፍ ናት፦
2፥45 በመታገስ እና በሶላትም ተረዱ! እርሷም (ሶላት) በፈሪዎች ላይ እንጅ በሌላው ላይ በእርግጥ ከባድ ናት፡፡ وَاسْتَعِينُوا بِالصَّبْرِ وَالصَّلَاةِ ۚ وَإِنَّهَا لَكَبِيرَةٌ إِلَّا عَلَى الْخَاشِعِينَ
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 4
ሙጃሂድ እና ጃቢር ኢብኑ ዐብደሏህ"ረ.ዐ." የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ሶላት የጀናህ ቁልፍ ናት፥ ውዱእ ደግሞ የሶላት ቁልፍ ነው"። عَنْ مُجَاهِدٍ، عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ، رضى الله عنهما قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ مِفْتَاحُ الْجَنَّةِ الصَّلاَةُ وَمِفْتَاحُ الصَّلاَةِ الْوُضُوءُ ‏"‏ ‏

አሏህ ሙሶሊን ከሚላቸው ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዘካህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

2፥277 እነዚያ ያመኑ፣ መልካም ሥራዎችንም የሠሩ፣ ሶላትንም ያስተካከሉ፣ ”ዘካንም የሰጡ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው፡፡ በእነርሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም እነርሱም አያዝኑም”፡፡ إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ وَآتَوُا الزَّكَاةَ لَهُمْ أَجْرُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ وَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ

“ዘካህ” زَكَاة የሚለው ቃል “ዘካ” زَكَىٰ ማለትም “ጠራ” ከሚል የግስ መደብ የመጣ ሲሆን “መጥራራት” ማለት ነው፦
20፥76 ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው የመኖሪያ ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ አሏቸው፡፡ ይህም “የተጥራራ” ሰው ምንዳ ነው፡፡ جَنَّاتُ عَدْنٍ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا ۚ وَذَٰلِكَ جَزَاءُ مَن تَزَكَّىٰ

“የተጥራራ” ለሚለው ግስ የገባው ቃል “ተዘካ” تَزَكَّىٰ ሲሆን የስም መደቡ “ዘካህ” زَكَوٰة ነው። ይህ ቋንቋዊ ፍቺው ሲሆን ሸሪዓዊ ፍቺው ደግሞ “የግዴታ ምጽዋት” ማለት ነው፥ አምላካችን አሏህ ከሰጠን ሲሳይ ላይ የምንለግሰው ልግስና ዘካህ ይባላል፦
2፥277 እነዚያ ያመኑ፣ መልካም ሥራዎችንም የሠሩ፣ ሶላትንም ያስተካከሉ፣ ”ዘካንም የሰጡ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው፡፡ በእነርሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም እነርሱም አያዝኑም”፡፡ إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ وَآتَوُا الزَّكَاةَ لَهُمْ أَجْرُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ وَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ
8፥3 እነዚያ ሶላትን ደንቡን አሟልተው የሚሰግዱ ”ከሰጠናቸውም ሲሳይ የሚለግሱ ናቸው”፡፡ الَّذِينَ يُقِيمُونَ الصَّلَاةَ وَمِمَّا رَزَقْنَاهُمْ يُنفِقُون

ዘካን የሚሰጡ አላህ ዘንድ ምንዳ አላቸው፥ በእነርሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም እነርሱም አያዝኑም። “ሪዝቅ” رِزْق ማለት “ሲሳይ” ማለት ሲሆን አምላካችን አሏህ ደግሞ “አር-ረዛቅ” الرَّزَّاق ማለትም “ሲሳይን ሰጪ” ነው። “ኢንፋቅ” إِنفَاق ማለት “ልግስና” ማለት ሲሆን “ሙንፊቂን” مُنفِقِين ደግሞ “ለጋሾች” ማለት ነው። አምላካችን አሏህ ከሰጠን ሲሳይ የምለግሰው ልግስና የበረከት ምንጭና ለአሏህ ውዴታ ያለን መገለጫ ነው። ዘካህ መስጠት በረከትን ያፋፋል፥ ነገር ግን መስጠት ያለብን የአሏህን ውዴታ ለመሻት እንጂ ትርፍ ፈልገን መሆን የበትም፦
2፥276 ”አላህ አራጣን በረከቱን ያጠፋል፡፡ ምጽዋቶችንም ያፋፋል”፡፡ አላህም ኃጠኢተኛ ከሓዲን ሁሉ አይወድም፡፡ يَمْحَقُ اللَّهُ الرِّبَا وَيُرْبِي الصَّدَقَاتِ ۗ وَاللَّهُ لَا يُحِبُّ كُلَّ كَفَّارٍ أَثِيمٍ
30፥39 ”ከሪባም በሰዎች ገንዘቦች ውስጥ ይጨመር ዘንድ የምትሰጡት አላህ ዘንድ አይጨምርም፡፡ ከምጽዋትም የአላህን ፊት የምትሹ ሆናችሁ የምትሰጡት እነዚያ ሰጪዎች አበርካቾች እነርሱ ናቸው”፡፡ وَمَا آتَيْتُم مِّن رِّبًا لِّيَرْبُوَ فِي أَمْوَالِ النَّاسِ فَلَا يَرْبُو عِندَ اللَّهِ ۖ وَمَا آتَيْتُم مِّن زَكَاةٍ تُرِيدُونَ وَجْهَ اللَّهِ فَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْمُضْعِفُونَ
74፥6 “ማብዛትንም የምትፈልግ ኾነህ አትለግስ”። وَلَا تَمْنُن تَسْتَكْثِرُ

ዘካህ ከጥንት ጀምሮ ነቢያት እስካሉ ድረስ የነበረ ከኢሥላም ምሰሶ አንዱ ነው፥ አሏህ ዘካንም ስለ መስጠት ትእዛዝ ከነቢያችን”ﷺ” በፊት ወደ ነበሩት ነቢያት አውርዷል፦
21፥73 ”ወደ እነርሱም መልካም ሥራዎችን መሥራትን፣ ሶላትንም መስገድን፣ ዘካንም መስጠትን አወረድን”፡፡ وَأَوْحَيْنَآ إِلَيْهِمْ فِعْلَ ٱلْخَيْرَٰتِ وَإِقَامَ ٱلصَّلَوٰةِ وَإِيتَآءَ ٱلزَّكَوٰة

ስለዚህ የኢሥላም ማዕዘን የሆነው ዘካህ ኢሥላም እስካለ ድረስ ከጥንት ጀምሮ አለ ማለት ነው። አምላካችን አሏህ ሙንፊቂን ከሚላቸው ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዘካቱል ማል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

104፥2 ለእዚያ ገንዘብን የሰበሰበ እና የቆጣጠረው ለኾነ ወዮለት፡፡ الَّذِي جَمَعَ مَالًا وَعَدَّدَهُ

“ዘካህ” زَكَاة ጥቅላዊ የግዴታ ምፅዋት ማለት ሲሆን የዘካህ ብዙ ቁጥር “ዘካት” زَكَوَات ሲሆን በተናጥል ዘካት በሁለት ይከፈላል፥ እነርሱም “ዘካቱል ማል” زَكَاة المَال እና “ዘካቱል ፊጥር” زَكَاة الفِطْر ናቸው። “ማል” مَال ማለት “ሀብት” ማለት ሲሆን የማል ብዙ ቁጥር ደግሞ “አምዋል” أَمْوَال ነው፥ ከተቀማጭ ሀብት ላይ ወይም ከትርፍ ላይ የሚሰጠው ዘካህ “ዘካቱል ማል” زَكَاة المَال ይባላል። ዘካቱል ማል ከነቢያችን”ﷺ” መላክ በፊት በነበሩት ነቢያት ጊዜ ከመቶ 2.5 % ላይሰጥ ይችል ይሆናል፥ ወይ ያንሳል አሊያም ይበዛ ይሆናል። ምናልባት ከመቶ 10 % አሥራት ሊሆን ይችል ይሆናል፥ ወሏሁ አዕለም። በነቢያችን”ﷺ” ሸሪዓህ ግን ዘካቱል ማል ከካፒታል ላይ ከመቶ 2.5 % የሚሰጥ ነው፥ ነቢያችን”ﷺ” ከሁለት መቶ ዲርሀም 5% ዘካህ እንደሚወጣ ተናግረዋል። ያ ማለት የዘካህ ሒሳብ በመቶ ዲርሀም 5፥2=2.5 ይሆናል፦
2፥219 ”ምንን እንደሚመጸውቱም መጠኑን ይጠይቁሃል፡፡ «ትርፍን መጽውቱ» በላቸው”፡፡ እንደዚሁ ታስተነትኑ ዘንድ አላህ ለእናንተ አንቀጾችን ይገልጽላችኋል፡፡ وَيَسْأَلُونَكَ مَاذَا يُنفِقُونَ قُلِ الْعَفْوَ ۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمُ الْآيَاتِ لَعَلَّكُمْ تَتَفَكَّرُونَ
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 9, ሐዲስ 18 ዐሊይ”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ”ሁለት መቶ ዲርሀም ለአንተ በሆነች ጊዜና ዓመት ከሞላች አምስት ደራሂም ይወጣል፥ በአንተ ምንም ነገር አይሆንም ሃያ ዲናር እስኪሆን ድረስ”። عَنْ عَلِيٍّ، – رضى الله عنه – عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم بِبَعْضِ أَوَّلِ هَذَا الْحَدِيثِ قَالَ ‏”‏ فَإِذَا كَانَتْ لَكَ مِائَتَا دِرْهَمٍ وَحَالَ عَلَيْهَا الْحَوْلُ فَفِيهَا خَمْسَةُ دَرَاهِمَ وَلَيْسَ عَلَيْكَ شَىْءٌ – يَعْنِي فِي الذَّهَبِ – حَتَّى يَكُونَ لَكَ عِشْرُونَ دِينَارًا

በዚህ ሐዲስ መሠረት የአንድ ሰው ካፒታል 20 ዲናር ወይም 200 ዲርሀም ሲሆን ዘካህ ይወጅበታል፥ በሸሪዓህ የዘካህ አነስተኛ የክፍያ መጠን “ኒሷብ” نِصاب ይባላል፥ ይህም ኒሷብ የሚለካው 20 ዲናር ወይም 200 ዲርሀም ሲሆን ነው። “ዲናር” دِينَار‎ ማለት “የወርቅ ሳንቲም”gold coin” ማለት ሲሆን “ዲርሀም” دِرْهَم‎ ማለት ደግሞ “የብር ሳንቲም”silver coin” ማለት ነው። ይህ በጥንት ጊዜ የሸቀጥ ገንዘብ”commodity money” ነው። “ዲናር” እና “ዲርሀም” የሚለኩት በሚስቃል ነው፥ “ሚስቃል” مِثْقَال የሚለው ቃል “ሰቀለ” ثَقَلَ ማለትም “ከበደ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ክብደት” ማለት ነው።
1 ሚስቃል ወርቅ 4.25 ግራም ነው፥ 20 ሚስቃል ወርቅ ደግሞ 4,25x 20 = 85 ግራም ወርቅ ይሆናል ማለት ነው።
1 ሚስቃል ብር 2.975 ግራም ነው፥ 200 ሚስቃል ብር ደግሞ 2.975x 200= 595 ግራም ብር ይሆናል ማለት ነው።

በዘካህ ላይ የሚወጅበው ኒሷብ 85 ግራም ወርቅ ወይም 595 ግራም ብር ነው።
አንድ ሙሥሊም ያስቀመጠው ካፒታል ዓመት ከሞላው እና ያም ካፒታል 85 ግራም ወርቅ ወይም 595 ግራም ብር ያክል ከሆነ ዘካህ ማውጣት ግዴታው ነው። እነዚህን ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
"የወርቅ ኒሷብ"
የወርቅ ኒሷብ ወደ ወረቀት ገንዘብ”Fiat money” ለመቀየር ወርቅን ዛሬ ባለው በ 24 ካራት የወቅቱ ግብይት ለናሙና ያክል መሥራት ይቻላል፦

1. በስውዲን አንድ 24 ካራት ግራም ወርቅ 601.97 ክራውን ነው፥ 601.97 ×85= 51,167.45 ክራውን ይሆናል።
2. በኢትዮጵያ አንድ 24 ካራት ግራም ወርቅ 3,249.1 ብር ነው፥ 3,249.1×85= 276,173.5 ብር ይሆናል።
3. በአሜሪካ አንድ 24 ካራት ግራም ወርቅ 63.457 ዶላር ነው፥ 63.457×85= 5,393.845 ዶላር ይሆናል።
ስለዚህ አንድ ሙሥሊም ያለው ካፒታል በገንዘብ ሲተመን፦
፨ በስውዲን 51,167.45 ክራውን ሲሆን፣
፨ በኢትዮጵያ 276,173.5 ብር ሲሆን፣
፨ በአሜሪካ 5,393.845 ዶላር ሲሆን ከዚያ ወዲህ ዘካህ ማውጣቱ ፈርድ ነው።
ለምሳሌ፦ አንድ ሰው በኢትዮ 276,173.5 ሺ ብር ካለው ከ 276,173.5 ሺ ብር ላይ 2.5% ዘካ ያወጣል፥ ያ ማለት የዘካው ብር 276,173.5×2.5÷100= ውጤቱ 6,904.3375 ብር ይሆናል ማለት ነው።
ነጥብ ሁለት
"የብር ኒሷብ"
የብር ኒሷብ ወደ ወረቀት ገንዘብ”Fiat money” ለመቀየር ብርን ዛሬ ባለው የወቅቱ ግብይት ለናሙና ያክል መሥራት ይቻላል፦

1. በስውዲን አንድ ግራም ብር 7.8 ክራውን ነው፥ 7.8×595= 6,981 ክራውን ይሆናል።
2. በኢትዮጵያ አንድ ግራም ብር 42.1 ብር ነው፥ 42.1×595= 25,049.5 ብር ይሆናል።
3. በአሜሪካ አንድ ግራም ብር 0.821 ዶላር ነው፥ 0.823×595= 736.585 ዶላር ይሆናል።
ስለዚህ አንድ ሙሥሊም ያለው ካፒታል በብር ገንዘብ ሲተመን፦
፨ በስውዲን 6,981 ክራውን ሲሆን፣
፨ በኢትዮጵያ 25,049.5 ብር ሲሆን፣
፨ በአሜሪካ 736.585 ዶላር ሲሆን ከዚያ ወዲህ ዘካህ ማውጣቱ ፈርድ ነው።
ለምሳሌ አንድ ሰው በኢትዮ 25,049.5 ሺ ብር ካለው ከ 25,049.5 ሺ ብር ላይ 2.5% ዘካ ያወጣል፥ ያ ማለት የዘካው ብር 25,049.5×2.5÷100= 626.2375 ብር ይሆናል ማለት ነው።

ይህ በጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር የ 2022 ድኅረ-ልደት ግብይት ነው፦
http://goldpricez.com/
ዘካቱል ማል የሚወጣበት አነስተኛ ዋጋ የብር ኒሷብ ስለሆነ አብላጫው ምሁራን የብር ኒሷብን መሠረት ባደረገ መልኩ ከዚያ እንዲወጣ ፈትዋ ሰተዋል፥ ስለዚህ አንድ ሰው ዓመት የተቀመጠ ኢትዮጵያ ውስጥ 25 ሺህ ብር እና ከዛ በላይ ካለው ዘካህ ማውጣት ግዴታ አለበት።
አምላካችን አሏህ የዘካቱል ማል ገንዘብ የሚውለው ለድኾች፣ ለምስኪኖችም፣ ዘካን በማሰጠት ለሚያስተባብሩ፣ ልቦቻቸውም በኢሥላም ለሚለማመዱት፣ በባርነት ተገዢዎችን ነጻ ለማውጣት፣ ለባለ ዕዳዎችም፣ በአሏህ መንገድም ለሚሠሩ እና ለመንገደኞች እንደሆነ ነግሮናል፦
9፥60 ግዴታ ምጽዋቶች የሚከፈሉት ለድኾች፣ ለምስኪኖችም፣ በርሷም ላይ ለሚሠሩ ሠራተኞች፣ ልቦቻቸውም በኢሥላም ለሚለማመዱት፣ በባርነት ተገዢዎችን ነጻ በማውጣት፣ በባለ ዕዳዎችም፣ በአላህ መንገድም በሚሠሩ፣ በመንገደኛም ብቻ ነው፡፡ ከአላህ የተደነገገች ግዴታ ናት”፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡ إِنَّمَا الصَّدَقَاتُ لِلْفُقَرَاءِ وَالْمَسَاكِينِ وَالْعَامِلِينَ عَلَيْهَا وَالْمُؤَلَّفَةِ قُلُوبُهُمْ وَفِي الرِّقَابِ وَالْغَارِمِينَ وَفِي سَبِيلِ اللَّهِ وَابْنِ السَّبِيلِ ۖ فَرِيضَةً مِّنَ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ

እንግዲህ አንድ ሙሥሊም ይህንን ዘካ ካላወጣ የትንሳኤ ቀን ገንዘቡ እንደ ሁለት አይኖቹ ላይ ጥቁር ነጥቦች የተጣሉበት ወንድ መላጣ እባብ ተመስሎ ይመጣና ማንገጭላውን አጥብቆ በመያዝ፦ “እኔ ገንዘብህ ነኝ፥ እኔ ድልብህ ነኝ” ይለዋል፦
3፥180 ”እነዚያም አላህ ከችሮታው በሰጣቸው ገንዘብ የሚነፍጉ እርሱ ለእነርሱ ደግ አይምሰላቸው፡፡ ይልቁንም እርሱ ለእነርሱ መጥፎ ነው፡፡ ያንን በእርሱ የነፈጉበትን በትንሣኤ ቀን እባብ ኾኖ ይጠለቃሉ”፡፡ وَلَا يَحْسَبَنَّ الَّذِينَ يَبْخَلُونَ بِمَا آتَاهُمُ اللَّهُ مِن فَضْلِهِ هُوَ خَيْرًا لَّهُم ۖ بَلْ هُوَ شَرٌّ لَّهُمْ ۖ سَيُطَوَّقُونَ مَا بَخِلُوا بِهِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 90, ሐዲስ 5
አቢ ሁራይራ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ”አላህ ገንዘብ ሰጥቶት የእሱን ዘካህ ያላወጣ የትንሳኤ ቀን ገንዘቡ እንደ ሁለት አይኖቹ ላይ ጥቁር ነጥቦች የተጣሉበት ወንድ መላጣ እባብ ተመስሎ ይመጣና ማንጋጭላውን አጥብቆ በመያዝ፦ “እኔ ገንዘብህ ነኝ፥ እኔ ድልብህ ነኝ ይለዋል”። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ يَكُونُ كَنْزُ أَحَدِكُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ شُجَاعًا أَقْرَعَ، يَفِرُّ مِنْهُ صَاحِبُهُ فَيَطْلُبُهُ وَيَقُولُ أَنَا كَنْزُكَ‏.‏ قَالَ وَاللَّهِ لَنْ يَزَالَ يَطْلُبُهُ حَتَّى يَبْسُطَ يَدَهُ فَيُلْقِمَهَا فَاهُ

ዘካን ካለመስጠት ከሚያስቀጣ ቅጣት አሏህ ይጠብቀን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሶላቱል ፈጅር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

4፥103 ሶላት በምእምናን ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናትና፡፡ إِنَّ الصَّلَاةَ كَانَتْ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ كِتَابًا مَّوْقُوتًا

"ፈጅር" فَجْر የሚለው ቃል "ፈጀረ" فَجَرَ ማለትም "ነጋ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ንጋት" "ጎህ" ማለት ነው፥ አምላካችን አሏህ ይህን የጎህ ወቅት በሶላት እንድንቆም ያዘናል፦
17፥78 ሶላትን ከፀሐይ መዘንበል እስከ ሌሊት ጨለማ ድረስ ስገድ፤ "የጎህ ሰላት ስገድ"፣ የጎህ ሶላት መላእክት የሚጣዱት ነውና። أَقِمِ الصَّلَاةَ لِدُلُوكِ الشَّمْسِ إِلَىٰ غَسَقِ اللَّيْلِ وَقُرْآنَ الْفَجْرِ ۖ إِنَّ قُرْآنَ الْفَجْرِ كَانَ مَشْهُودًا

"የጎህ ሰላት ስገድ" የሚለው ትእዛዛዊ ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! እዚህ አንቀጽ ላይ "ጎህ" ለሚለው የገባው ቃል "ፈጅር" فَجْر መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል። አምላካችን አሏህ እንቅጩን "ሶላቱል ፈጅር" صَلَاة الْفَجْر ብሎ ነግሮናል፦
24፥58 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያ እጆቻችሁ የጨበጧቸው እና እነዚያም ከእናንተ ለአካላ መጠን ያልደረሱት "ከጎህ ስግደት" በፊት፣ በቀትር ልብሶቻችሁን በምታወልቁ ጊዜ እና ከምሽት ስግደትም በኋላ ሦስት ጊዜያት ለመግባት ሲፈልጉ ያስፈቅዷችሁ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لِيَسْتَأْذِنكُمُ الَّذِينَ مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ وَالَّذِينَ لَمْ يَبْلُغُوا الْحُلُمَ مِنكُمْ ثَلَاثَ مَرَّاتٍ ۚ مِّن قَبْلِ صَلَاةِ الْفَجْرِ وَحِينَ تَضَعُونَ ثِيَابَكُم مِّنَ الظَّهِيرَةِ وَمِن بَعْدِ صَلَاةِ الْعِشَاءِ ۚ ثَلَاثُ عَوْرَاتٍ لَّكُم

እረ እንደውም ጌታችን አሏህ ሶላቱል ፈጅርን ለማመልከት፦ "በምታነጉ ጊዜ" "በማለዳም" "በምትንነሳ ጊዜ" "ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት" በማለት በአፅንኦትና በአንክሮት ይናገራል፦
30፥17 አላህንም በምታመሹ ጊዜ “በምታነጉም ጊዜ አጥሩት፡፡ فَسُبْحَانَ اللَّهِ حِينَ تُمْسُونَ وَحِينَ تُصْبِحُونَ
40፥55 በማታም "በማለዳም" ጌታህን ከማመስገን ጋር አጥራው፡፡ وَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ بِالْعَشِيِّ وَالْإِبْكَارِ
52፥48 ጌታህንም "በምትነሳ ጊዜ" ከማመስገን ጋር አወድሰው፡፡ وَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ حِينَ تَقُومُ
50፥39 ጌታህንም ከማመስገን ጋር "ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት" ከመግባቷም በፊት አወድሰው፡፡ وَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ قَبْلَ طُلُوعِ الشَّمْسِ وَقَبْلَ الْغُرُوبِ
20፥130 ጌታህንም "ፀሐይ ከመውጣትዋ በፊት" ከመግባትዋም በፊት የምታመሰግን ኾነህ አጥራው፡፡ وَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ قَبْلَ طُلُوعِ الشَّمْسِ

በእርግጥ አሏህ የነገረን ሶላት በምእምናን ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ መሆኗን ብቻ ሳይሆን ያቺ የሶላት ጊዜ ፈጅርም እንደሆነ ጭምር ነው፦
4፥103 ሶላት በምእምናን ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናትና፡፡ إِنَّ الصَّلَاةَ كَانَتْ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ كِتَابًا مَّوْقُوتًا

አሏህ ሶላቱል ፈጅርን ከሚቆሙ ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም