ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.3K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
በዐረብ አገር ያሉ ኢትዮጵያውያን!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥143 አላህ ለሰዎች በጣም ርኅሩኅ አዛኝ ነውና፡፡ إِنَّ اللَّهَ بِالنَّاسِ لَرَءُوفٌ رَّحِيمٌ

በዐረብ አገር ያሉ ኢትዮጵያዊ ወንድም እና እኅት የሚደርስባቸውን ፍትሕ አልባ መከራ፣ ስቃይ፣ እንግልት፣ ግርፊያ፣ ድብደባ፣ እስራት እና ግዞት አጥብቀን ልንቃወም ይገባል! ሰው ለሰው ለማዘን እና ለመራራት መስፈርቱ ሰው መሆን ብቻ ነው። አምላካችን አሏህ ለሰዎች በጣም ርኅሩኅ አዛኝ ነው፥ ለሰዎች የማያዝኑ አሏህ ለእነርሱ አያዝንላቸውም፦
2፥143 አላህ ለሰዎች በጣም ርኅሩኅ አዛኝ ነውና፡፡ إِنَّ اللَّهَ بِالنَّاسِ لَرَءُوفٌ رَّحِيمٌ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97 ሐዲስ 6
ጀሪር ኢብኑ ዐብደሏህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ *”ለሰዎች የማያዝኑ አሏህ ለእነርሱ አያዝንላቸውም”*። ظَبْيَانَ عَنْ جَرِيرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ لاَ يَرْحَمُ اللَّهُ مَنْ لاَ يَرْحَمُ النَّاسَ

ለእነዚህ የእናት እና የአባት ማጀት "እንሞላለን" ብለው ከቀዬአቸው የተሰደዱ ኢትዮጵያዊ ወንድሞቻችን እና እኅቶቻችን ላይ የሚደርሰውን መከራ፣ ስቃይ፣ እንግልት፣ ግርፊያ፣ ድብደባ፣ እስራት እና ግዞት ለማስቆም ከቻልን ለሚመለከተው አካል ስሞታ እና አቤቱታ ማቅረብ፣ ካልቻልን ደግሞ መመገናኛ ብዙኃን ተጠቅመን ተጽዕኖ መፍጠር፣ ያም ካልተቻለ ዱዓእ ወደ አሏህ በማድረግ መበርታት አለብን። አሏህ በዓለማችን ላይ ያለውን በደል እያየ እና እየሰማ የመታገሱ ባሕርይ የራሱ ጥበብ አለው፥ ቅሉ ግን ይዘገያል እንጂ ሰዎችን በዱንያ ያለ ፍትሕ የሚቀጡ አሏህ ይቀጣቸዋል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 45 ሐዲስ 157
ዑርዋህ ኢብኑ ዙበይር እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ *”እነዚያ ሰዎችን በዱንያ ያለ ፍትሕ የሚቀጡ አላህ ይቀጣቸዋል”*። عَنْ عُرْوَةَ، بْنِ الزُّبَيْرِ فَقَالَ مَا هَذَا إِنِّي سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ “‏ إِنَّ اللَّهَ يُعَذِّبُ الَّذِينَ يُعَذِّبُونَ النَّاسَ فِي الدُّنْيَا

አሏህ ነስሩን ለሁላችን ያቅርብልን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የሴት ደረጃ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

39፥34 “ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ የሚሹት ሁሉ አለላቸው፡፡ ይህ የበጎ አድራጊዎች ምንዳ ነው”፡፡ لَهُم مَّا يَشَاءُونَ عِندَ رَبِّهِمْ ۚ ذَٰلِكَ جَزَاءُ الْمُحْسِنِينَ

“ፈድል” فَضْل የሚለው ቃል “ፈዶለ” فَضَّلَ ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ስጦታ” “ችሮታ” “ጸጋ”Bounty” ማለት ነው፥ ሴትነት እና ወንድነት በተፈጥሮ ከአሏህ የተሰጠን ጸጋ ነው፦
4፥32 *”አላህም ከፊላችሁን በከፊሉ ላይ በእርሱ ያበለጠበትን ጸጋ አትመኙ! ለወንዶች ከሠሩት ሥራ እድል አላቸው፥ ለሴቶችም ከሠሩት ሥራ ዕድል አላቸው፡፡ وَلَا تَتَمَنَّوْا مَا فَضَّلَ اللَّهُ بِهِ بَعْضَكُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ ۚ لِّلرِّجَالِ نَصِيبٌ مِّمَّا اكْتَسَبُوا ۖ وَلِلنِّسَاءِ نَصِيبٌ مِّمَّا اكْتَسَبْنَ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ያበለጠ” ለሚለው ቃል የገባው “ፈዶለ” فَضَّلَ መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል! ወንድነት ለወንድ የተሰጠ ጸጋ ነው፥ ለወንዶች ከሠሩት ሥራ እድል አላቸው። ሴትነት ለሴት የተሰጠ ጸጋ ነው፥ ለሴቶችም ከሠሩት ሥራ ዕድል አላቸው። ለወንድ የተሰጠውን ጸጋ ሴት መመኘት የለባትም! ለሴት የተሰጠ ጸጋ ወንድ መመኘት የለበትም፥ ወንድ በሴት ላይ ሴት በወንድ ላይ የሚበላለጡት ጸጋ አለ እንጂ ወንድ ሴት አይደለም እንዲሁ ሴት ወንድ አይደለችም፦
3፥36 “ወንድም እንደ ሴት አይደለም”፡፡ وَلَيْسَ الذَّكَرُ كَالْأُنثَىٰ

አንድ ተባእት አምኖ መልካም ከሠራ መልካም ኑሮን በሚኖርበት መጠን አንድ እንስትም አምና መልካም ከሠራች መልካም ኑሮን ትኖራለች፦
16፥97 ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ በጎን የሠራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን፡፡ مَنْ عَمِلَ صَالِحًا مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَلَنُحْيِيَنَّهُ حَيَاةً طَيِّبَةً

አንድ ተባእት አምኖ መልካም ከሠራ ጀነት እንደሚገባ ሁሉ አንድ እንስትም አምና መልካም ከሠራች ጀነት ትገባለች፦
4፥124 ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ ከበጎ ሥራዎች አንዳችን የሚሠራም ሰው እነዚያ ገነትን ይገባሉ፡፡ وَمَن يَعْمَلْ مِنَ الصَّالِحَاتِ مِن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَأُولَـٰئِكَ يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ
40፥40 “እርሱ ምእመን ኾኖ ከወንድ ወይም ከሴት በጎን የሠራም ሰው እነዚያ ገነትን ይገባሉ፡፡ በእርሷ ውስጥ ያለ ቁጥጥር ይመገባሉ”፡፡ وَمَنْ عَمِلَ صَالِحًا مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَأُولَـٰئِكَ يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ يُرْزَقُونَ فِيهَا بِغَيْرِ حِسَابٍ
9፥72 “አላህ ምእምናንን እና ምእምናትን ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ በመኖሪያ ገነቶችም ውስጥ መልካም መኖሪያ ቤቶችን ቃል ገብቶላቸዋል”፡፡ وَعَدَ اللَّهُ الْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا وَمَسَاكِنَ طَيِّبَةً فِي جَنَّاتِ عَدْنٍ ۚ وَرِضْوَانٌ مِّنَ اللَّهِ أَكْبَرُ

ወንድ አማኞች “ሙእሚኒን” مُؤْمِنِين ሲባሉ ሴት አማኞች “ሙእሚናት” مُؤْمِنَات ይባላሉ፥ በጀነት ውስጥ ወንድ አማኞች እና ሴት አማኞችም የሚፈልጉት ነገር ሁሉ አለላቸው፦
25፥16 ለእነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ኾነው የሚፈልጉት ሁሉ አለላቸው፡፡ ይህም ተስፋ ከጌታህ ተለማኝ ተስፋ ነው፡፡ لَّهُمْ فِيهَا مَا يَشَاءُونَ خَالِدِينَ ۚ كَانَ عَلَىٰ رَبِّكَ وَعْدًا مَّسْئُولًا
39፥34 “ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ የሚሹት ሁሉ አለላቸው፡፡ ይህ የበጎ አድራጊዎች ምንዳ ነው”፡፡ لَهُم مَّا يَشَاءُونَ عِندَ رَبِّهِمْ ۚ ذَٰلِكَ جَزَاءُ الْمُحْسِنِينَ
43፥71 “በእርሷም ውስጥ ነፍሶች የሚከጅሉት እና ዓይኖችም የሚደሰቱበት ሁሉ አለ፥ እናንተም በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ናችሁ፡፡ وَفِيهَا مَا تَشْتَهِيهِ الْأَنفُسُ وَتَلَذُّ الْأَعْيُنُ ۖ وَأَنتُمْ فِيهَا خَالِدُونَ
41፥31 ለእናንተም በእርሷ ውስጥ ነፍሶቻችሁ የሚሹት ሁሉ አለላችሁ፡፡ ለእናንተም በእርሷ ውስጥ የምትፈልጉት ሁሉ አለላችሁ”፡፡ وَلَكُمْ فِيهَا مَا تَشْتَهِي أَنفُسُكُمْ وَلَكُمْ فِيهَا مَا تَدَّعُونَ
16፥31 “ለእነርሱም በወስጧ የሚሹት ሁሉ አላቸው፡፡ እንደዚሁ አላህ ጥንቁቆችን ይመነዳል”፡፡ لَهُمْ فِيهَا مَا يَشَاءُونَ ۚ كَذَٰلِكَ يَجْزِي اللَّهُ الْمُتَّقِينَ
“ተቅዋእ” تَقْوَى ማለት “አሏህ መፍራት” ማለት ሲሆን አሏህን የሚፈሩ ወንድ እና ሴት “ሙተቂን” مُتَّقِين ይባላሉ፥ ለሙተቂን በጀነት ውስጥ ከአሏህ የኾነ ውዴታ ጥንዶች አላቸው፦
3፥15 «ከዚህ ሁሉ ነገር የሚበልጥን ልንገራችሁን» በላቸው፡፡ እርሱም፦ «ለእነዚያ ለተጠነቀቁት ሰዎች በጌታቸው ዘንድ በሥራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች በውስጧ ሁልጊዜ ነዋሪዎች ሲኾኑ ንጹሕ የተደረጉ አዝዋጅ ከአላህም የኾነ ውዴታ አላቸው» قُلْ أَؤُنَبِّئُكُم بِخَيْرٍ مِّن ذَٰلِكُمْ ۚ لِلَّذِينَ اتَّقَوْا عِندَ رَبِّهِمْ جَنَّاتٌ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا وَأَزْوَاجٌ مُّطَهَّرَةٌ وَرِضْوَانٌ مِّنَ اللَّهِ

“ዘውጅ” زَوْج የሚለው ቃል “ዘወጀ” زَوَّجَ ማለትም “ተጠናዳ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ጥንድ” “ባል” “ሚስት” ማለት ነው፥ 58፥1 ላይ “ባልዋ” ለሚለው የገባው ቃል “ዘውጂሃ” زَوْجِهَا ሲሆን 7፥19 ላይ “ሚስትህ” ለሚለው የገባው ቃል ደግሞ “ዘውጁከ” َزَوْجُكَ ነው። የዘውጅ ብዙ ቁጥር ደግሞ “አዝዋጅ” أَزْوَاج ሲሆን “ጥንዶች” ማለት ነው፥ አምላካችን አሏህ በግስ መደብ “ዘወጅናሁም” زَوَّجْنَاهُم ማለትም “እናጠናዳቸዋለን” ብሎ ቃል ገብቷል፦
44፥54 ነገሩ እንደዚሁ ነው፥ ሁር ዒን እናጠናዳቸዋለን፡፡ كَذَٰلِكَ وَزَوَّجْنَاهُم بِحُورٍ عِينٍ

“አሕወር” أَحْوَر ማለት “ውብ” ማለት ሲሆን ተባታይ መደብ ነው፥ “ሐውራእ” حَوْرَاء‎ ማለት ደግሞ “ውቢት” ማለት ሲሆን አንስታይ መደብ ነው። “ሑር” حُور ማለት የሁለቱም ጾታ ብዜት ነው፥ “ዒን” عِين ማለት “ዓይናማ” ” ማለት ነው። “ሑረል ዒን” حُور العِين ማለት በጥቅሉ “ውብ ዓይናማ” ማለት ነው። በጀነት “ነፍሶች የሚከጅሉት እና ዓይኖችም የሚደሰቱበት ሁሉ አለ” እንደተባለው “ሑረል ዒን” አምላካችን አሏህ ለወንድ እና ለሴት ሙተቂን ባሮቹ ያዘጋቻቸው ናቸው፥ አምላካችን አሏህ ጥንድን ያጠናዳው ምድር ከምታበቅለው፣ ከራሳችን እና ከማናውቀው ነገር ነው፦
36፥36 ያ ምድር ከምታበቅለው፣ ከራሳቸውም እና “ከማያውቁትም ነገር" ጥንዶችን ሁሏንም የፈጠረ ጥራት ይገባው፡፡ سُبْحَانَ الَّذِي خَلَقَ الْأَزْوَاجَ كُلَّهَا مِمَّا تُنبِتُ الْأَرْضُ وَمِنْ أَنفُسِهِمْ وَمِمَّا لَا يَعْلَمُونَ
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 36፥36 "ከዚያም አለ፦ "ያ ምድር ከምታበቅለው ጥንዶችን ሁሏንም የፈጠረ ጥራት ይገባው" ማለት ሰብልን፣ ፍራፍሬን እና አታክልትን ማለት ነው። "ከራሳቸውም" ማለት ከወንድ እና ከሴት አደረገላቸው ማለት ነው። "ከማያውቁትም ነገር" ማለት የማይታወቁ የተለያዩ ፍጥረት ማለት ነው።
ثم قال : ( سبحان الذي خلق الأزواج كلها مما تنبت الأرض ) أي : من زروع وثمار ونبات . ( ومن أنفسهم ) فجعلهم ذكرا وأنثى ، ( ومما لا يعلمون ) أي : من مخلوقات شتى لا يعرفونها.

፨ አንደኛ "ምድር ከምታበቅለው" ማለት ከምድር ውስጧ ከፍሬዎች ሁሉ ሁለት ሁለት ጥንዶችን ያደረገ ነው፦
13፥3 እርሱም ያ ምድርን የዘረጋ በእሷም ተራራዎችን እና ወንዞችን ያደረገ በውስጧም ከፍሬዎች ሁሉ ሁለት ሁለት ጥንዶችን ያደረገ ነው፡፡ وَهُوَ الَّذِي مَدَّ الْأَرْضَ وَجَعَلَ فِيهَا رَوَاسِيَ وَأَنْهَارًا ۖ وَمِن كُلِّ الثَّمَرَاتِ جَعَلَ فِيهَا زَوْجَيْنِ اثْنَيْنِ

፨ ሁለተኛ "ከራሳቸውም" ማለት ከራሳችሁ ጥንዶችን ወደ እነርሱ ትረኩ ዘንድ ያደረገ ነው፦
30፥21 ለእናንተም ከራሳችሁ ጥንዶችን ወደ እነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፣ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً

፨ ሦስተኛ "ከማያውቁትም ነገር" ማለት ሑረል ዒን አዲስ ፍጥረት አድርጎ ለሙተቂን ከዓይኖች መርጊያ የተደበቀላቸውን ጸጋ ሲሆን ይህንን ጸጋ አሁን ላይ ማንኛይቱም ነፍስ ዐታውቅም፥ በጀነት ውስጥ ያለው ጸጋ ዓይን ዓይቶት የማያውቅ፣ ጆሮ ሰምቶት የማያውቅ እና በሰው ልብ ውልብ ብሎ የማያውቅ ነው፦
56፥35 እኛ አዲስ ፍጥረት አድርገን ለእነርሱ ፈጠርናቸው፡፡ إِنَّا أَنشَأْنَاهُنَّ إِنشَاءً
32፥17 ይሠሩትም በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለእነርሱ የተደበቀላቸውን ጸጋ ማንኛይቱም ነፍስ ዐታውቅም፡፡ فَلَا تَعْلَمُ نَفْسٌ مَّا أُخْفِيَ لَهُم مِّن قُرَّةِ أَعْيُنٍ جَزَاءً بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 302
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “የላቀው አሏህም እንዲህ አለ፦ “እኔ ለደጋግ ባሮቼ ዓይን ዓይቶት የማያውቅ፣ ጆሮ ሰምቶት የማያውቅ እና በሰው ልብ ውልብ ብሎ የማያውቅ ጸጋን አዘጋጅቻለው”። ከዚያም እርሳቸው፦ “ይሠሩትም በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለእነርሱ የተደበቀላቸውን ጸጋ ማንኛይቱም ነፍስ ዐታውቅም” የሚለውን አንቀጽ አነበቡ"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ يَقُولُ اللَّهُ تَعَالَى أَعْدَدْتُ لِعِبَادِي الصَّالِحِينَ مَا لاَ عَيْنٌ رَأَتْ، وَلاَ أُذُنٌ سَمِعَتْ، وَلاَ خَطَرَ عَلَى قَلْبِ بَشَرٍ، ذُخْرًا، بَلْهَ مَا أُطْلِعْتُمْ عَلَيْهِ ‏”‌‏.‏ ثُمَّ قَرَأَ ‏{‏فَلاَ تَعْلَمُ نَفْسٌ مَا أُخْفِيَ لَهُمْ مِنْ قُرَّةِ أَعْيُنٍ جَزَاءً بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ‏}‏

በተረፈ ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 238 ላይ ወይም ጃሚዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 22, ሐዲስ 46 ላይ አሊያም ጃሚዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 38, ሐዲስ 2760 ላይ “ሰባ ሁለት አዝዋጅ” የሚለውን ሙሐዲስ ሸይኽ አል-አልባኒይ ረሒመሁል ሏህ “ደረጃቸው ዶዒፍ ናቸው” ብለዋቸዋል፥ ዶዒፍ ደግሞ መቅቡል ሳይሆን መርዱድ ነው።

አሏህ በጀነት ያዘጋጀልንን ጸጋ ይወፍቀን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
‏اسلام عليكم ورحمته الله وبركاته

አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ።

የዶ/ር Dan Alan Brubaker መፅሀፍን ዳሰሳ ቀጣዩ ክፍል እነሆ! ዛሬ ደግሞ ክፍል -6 ይዘን ቀርበናል።በዚህ ክፍል ዶክተሩ ያቀረበውን ምሳሌ 5 -ላይ ምላሽ ተሰጥቶበታል።

🔰Like and Share

https://tttttt.me/Abuyusra3
የአሏህ ዐዋቂነት

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

65፥11 "አሏህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው"፡፡ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

አምላካችን አሏህ ሁሉንም "ነገር" ዐዋቂ ነው፥ "ሸይእ" شَيْء ማለት "ነገር" ማለት ሲሆን ይህም ነገር አጠቃላይ ፍጥረትን ሁሉ ያጠቃልላል፦
65፥11 "አሏህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው"፡፡ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

አሏህ አንድ ነገር ከመከሰቱ፣ ከመሆኑ፣ ከመደረጉ፣ ከመከናወኑ በፊት ያለውን ሩቅ ነገር እና አንድ ነገር ከተከሰተ፣ ከሆነ፣ ከተደረገ፣ ከተከናወነ በኃላ ያለውን ግልጹን ነገር ሁሉ ዐዋቂ ነው፦
64፥18 "ሩቁን ነገር ግልጹንም ሁሉ ዐዋቂው አሸናፊው ጥበበኛው ነው"፡፡ عَالِمُ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ

ይህ ሆኖ ሳለ ሚሽነሪዎች፦ "አሏህ ለማወቅ የሚታወቅ ነገር ያስፈልገዋል፥ የሚታወቅ ነገር ሳይኖር ዐያውቅም" በማለት ለመዘባበቻቸው ጀውጃዋ፣ ጀርጃራ እና ተጅረብራቢ በመሆን ይህንን አቀጽ ይጠቅሳሉ፦
2፥143 ያችንም በርሷ ላይ የነበርክባትን አቅጣጫ መልክተኛውን የሚከተለውን ሰው ወደ ክህደት ከሚመለሰው ሰው ”ልናውቅ” እንጅ ቂብላህ አላደረግናትም፡፡ وَمَا جَعَلْنَا الْقِبْلَةَ الَّتِي كُنتَ عَلَيْهَا إِلَّا لِنَعْلَمَ مَن يَتَّبِعُ الرَّسُولَ مِمَّن يَنقَلِبُ عَلَىٰ عَقِبَيْهِ

"ቂብላህ የተደረገበት ምክንያት መልክተኛውን የሚከተለውን ሰው ወደ ክህደት ከሚመለሰው ሰው ለማወቅ ከሆነ ያለ ቂብላህ መልክተኛውን የሚከተለውን ሰው ወደ ክህደት ከሚመለሰው ሰው ማወቅ አይችልምን? ብለው ይጠይቃሉ። ቁርኣን ላይ ተመሳሳይ ቃል ቢኖረው እንኳን ተመሳሳይ አሳብና ትርጉም አለው ማለት አይደለም፥ የአንድን ቃል አማራጭ ትርጉም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት አረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ ቅቡል ነው። መታየት ያለበት ቃሉ ሳይሆን ቃሉ የወከለው አሳብ ነው፥ ነቢያችን”ﷺ” በቁርኣን ከተሰጣቸው አንዱ ጥበብ አንድ ቃላት ሰፊ ትርጉም ነው። ይህም “ጀዋሚዓል ከሊም” جَوَامِعَ الْكَلِم ይባላል፥ ከዚህ አንጻር "ልናውቅ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ሊነዕለመ" لِنَعْلَمَ ሲሆን "ልንገልጽ" "ልንለይ" በማለት ይመጣል፦
3፥166 ሁለቱ ጭፍሮችም በተጋጠሙ ቀን የደረሰባችሁ በአላህ ፈቃድ ነው፥ ምእምናንንም "ሊገልጽ" ነው፡፡ وَمَا أَصَابَكُمْ يَوْمَ الْتَقَى الْجَمْعَانِ فَبِإِذْنِ اللَّهِ وَلِيَعْلَمَ الْمُؤْمِنِينَ
3፥167 እነዚያንም የነፈቁትን እና ለእነርሱ «ኑ! በአላህ መንገድ ተጋደሉ ወይም ተከላከሉ» የተባሉትን "ሊገልጽ" ነው፡፡ وَلِيَعْلَمَ الَّذِينَ نَافَقُوا ۚ وَقِيلَ لَهُمْ تَعَالَوْا قَاتِلُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ أَوِ ادْفَعُو

እነዚህ ዐውድ ላይ "ሊገልጽ" ለሚለው የገባው ቃል "ሊየዕለመ" لِيَعْلَمَ መሆኑን ልብ አድርግ! በአሏህ ፈቃድ ሁለቱ ጭፍሮችም በተጋጠሙ ቀን የደረሰባቸው መናፍቃን እና ምእመናንን ለመለየት እና ለመግለጽ ነው፥ ስለዚህ ቂብላህ የተደረገበት ምክንያት መልክተኛውን የሚከተለውን ሰው ወደ ክህደት ከሚመለሰው ሰው ለመለየት እና ለመግለጽ ነው።

እዚህ ድረስ ከተግባባን በተመሳሳይ ሰዋስው ባይብል ላይ የተቀመጡትን አንዳንድ አናቅጽ እንመልከት፦
ዘዳግም 8፥2 በልብህም ያለውን ትእዛዙን ትጠብቅ ወይም አትጠብቅ እንደሆነ "ያውቅ ዘንድ" ሊያስጨንቅህ በእነዚህ በአርባ ዓመታት በምድረ በዳ የመራህን መንገድ ሁሉ አስብ።

ያህዌህ በአርባ ዓመታት በምድረ በዳ የመራህን በልብህም ያለውን ትእዛዙን ትጠብቅ ወይም አትጠብቅ እንደሆነ "ያውቅ ዘንድ" ማለት ምን ማለት ነው? ከመምራቱ በፊት ዐያውቅምን? እንቀጥል፦
ዘዳግም 13፥3 "አምላካችሁን ያህዌህን በፍጹም ልባችሁ በፍጹምም ነፍሳችሁ ትወድዱት እንደ ሆነ "ያውቅ ዘንድ" አምላካችሁ ያህዌህ ሊፈትናችሁ ነው።

በመካከልህም ሐሠተኛ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ የሚነሳው አምላካችሁን ያህዌህን በፍጹም ልባችሁ በፍጹምም ነፍሳችሁ ትወድዱት እንደ ሆነ "ያውቅ ዘንድ" ለመፈተን ከሆነ ሳይፈትን በፊት በፍጹም ልባችሁ በፍጹምም ነፍሳችሁ መውደዳችሁህን ዐያውቅምን? እንቀጥል፦
2ኛ ዜና መዋዕል 32፥31 እግዚአብሔር ይፈትነውና በልቡ ያለውን ሁሉ "ያውቅ ዘንድ" ተወው።

በአንድ ወቅት አንዱን የሥነ መለኮት ተማሪ ስጠይቀው፦ "አይ ወሒድ "ማወቅ" የሚለው ቃል በተለያየ ዐውድ ምን ዐይነት ትርጉም ይዞ እንደሚመጣ ብታውቅ ኖሮ ይህንን አትጠይቅም ነበር" በማለት መለሰልኝ፦
ዘፍጥረት 4፥1 አዳምም ሚስቱን ሔዋንን "አወቀ" ፀነሰችም፥ ቃየንንም ወለደች።

እዚህ አንቀጽ ላይ "አወቀ" ማለት "ተራክቦ አደረገ" በሚል ከመጣ "ቂብላህ መልክተኛውን የሚከተለውን ሰው ወደ ክህደት ከሚመለሰው ሰው ”ልናውቅ” ማለት "ልንለይ" "ልንገልጽ" "ልንፈትን" ማለት ነው" ብሎ መረዳት እንዴት አቃታችሁ? ቁርኣንን ዶግ ዐመድ ለማድረግ እና ጥንብ እርኩሱን ለማውጣት ይህ ያህን መዳዳትስ ምንድን ነው? "ማወቅ" የሚለው ቃል "መምረጥ" በሚል ይመጣል፥ ፈጣሪ፦ "ዐውቄአችኋለሁ" ሲል "መርጬአችኋለሁ" ማለት ነው፦
አሞጽ 3፥2 እንዲህም ብሎአል፦ እኔ ከምድር ወገን ሁሉ እናንተን ብቻችሁን "ዐውቄአችኋለሁ"፤ ስለዚህ ስለ ኃጢአታችሁ ሁሉ እበቀላችኋለሁ።
ማቴዎስ 7፥23 የዚያን ጊዜም፦ ከቶ "አላወቅኋችሁም" እናንተ ዓመፀኞች ከእኔ ራቁ! ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።

"አላወቅኋችሁም" ማለት "አልተቀበልኳችሁም" "አልፈልጋችሁም" ማለት ከሆነ ቂብላህ መልክተኛውን የሚከተለውን ሰው ወደ ክህደት ከሚመለሰው ሰው ”ልናውቅ” ማለት "ልንለይ" "ልንገልጽ" "ልንፈትን" ማለት ነው" ብሎ መረዳት እንዴት ከበዳችሁ? ይህ ጥያቄ እንደ በቀቀን ወፍ ስንቴ ደገማችሁት? ከርሞ ጥጃ፣ አድሮ ቃሪያ እና ታጥቦ ጭቃ መሆንስ ምንድን ነው? ሆድ ወዶ፣ አፍ ክዶ፣ ክፉ ለምዶ አይሆንምና ከላይ ያለውን መልስ በቅጡ እና በጥሞና አንብቡት!

አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ማሻሏህ ዐለይኩም 30 ሺህ ገብታችኃል። ይህ የሚያሳየው የአንባቢያን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ነው። አል-ሓምዱ ሊሏህ!
ክርስቲያኖች ወደ ግሩፑ በገፍ እየተመማችሁ ነው፥ ደስ ይላል። ክርስቲያኖች ሆይ! አሏህ በምታነቡት ሂዳያህ እንዲሰጣችሁ እና እኛም በእናንተ ምክንያት አጅር እንድናገኝ ወደ አሏህ ኢንሻሏህ ዱዓእ እናደርጋለን!
ሙሥሊሞች ደግሞ ለሌሎች የሂዳያህ ሰበብ ከመሆን በተጓዳኝ ሰዎች ከሺርክ፣ ከኩፍር እና ከቢድዓህ ነጻ እንዲወጡ ይህንን ቻናል በየግሩፑ፣ በየፔጁ፣ በየኮሜንቱ እና በየቻናሉ ሼር በማድረግ ከአሏህ ዘንድ ሰዋብ አግኙ!

ወጀዛኩሙሏህ ኸይራ!
ኢሥቲርጃዕ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥156 እነዚያን መከራ በነካቻቸው ጊዜ «እኛ ለአላህ ነን፥ እኛም ወደ እርሱ ተመላሾች ነን» የሚሉትን አብስር፡፡ الَّذِينَ إِذَا أَصَابَتْهُم مُّصِيبَةٌ قَالُوا إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُونَ

"ኢሥቲርጃዕ" اِسْتِرْجَاع‎ ማለት "ኢና ሊሏሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን" إِنَّا لِلَّٰهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُون ማለት ነው፥ "ኢና ሊሏሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን" إِنَّا لِلَّٰهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُون ማለት "እኛ ለአሏህ ነን፥ እኛም ወደ እርሱ ተመላሾች ነን" ማለት ሲሆን ማንኛውም ሙሥሊም ሙሲባህ በነካችው ጊዜ፦ "ኢና ሊሏሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን" ማለቱ ሙስተሐብ ነው፦
2፥156 እነዚያን መከራ በነካቻቸው ጊዜ «እኛ ለአላህ ነን፥ እኛም ወደ እርሱ ተመላሾች ነን» የሚሉትን አብስር፡፡ الَّذِينَ إِذَا أَصَابَتْهُم مُّصِيبَةٌ قَالُوا إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُونَ
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 48, ሐዲስ 142
ዑመር ኢብኑ አቢ ሠለማህ ከእናቱ ከኡሙ ሠላማህ እንደተረከው፦ "የአሏህም መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ከእናንተ መካከል መከራ በነካው ጊዜ፦ "ኢና ሊሏሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን" ይበል!። عَنْ عَمْرِو بْنِ أَبِي سَلَمَةَ، عَنْ أُمِّهِ أُمِّ سَلَمَةَ، عَنْ أَبِي سَلَمَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ إِذَا أَصَابَ أَحَدَكُمْ مُصِيبَةٌ فَلْيَقُلْ ‏:‏ ‏(‏ إنَّا لِلَّهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُونَ ‏)‏

ሶላት አሏህ በሚፈሩት ፈሪዎች ላይ እና ወደ አሏህ ተመላሾች መኾናቸውን "ኢና ሊሏሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን" ብለው የሚያረጋግጡ በኾኑት ላይ ቀላል ስትሆን ከእነርሱ ውጪ በሌላው ላይ በእርግጥ ከባድ ናት፦
2፥45 በመታገስ እና በሶላትም ተረዱ! እርሷም ሶላት በፈሪዎች ላይ እንጅ በሌላው ላይ በእርግጥ ከባድ ናት፡፡ وَاسْتَعِينُوا بِالصَّبْرِ وَالصَّلَاةِ ۚ وَإِنَّهَا لَكَبِيرَةٌ إِلَّا عَلَى الْخَاشِعِينَ
2፥46 እነዚያ እነርሱ ጌታቸውን የሚገናኙ እነርሱም ወደ እርሱ ተመላሾች መኾናቸውን የሚያረጋግጡ በኾኑት ላይ እንጂ ከባድ ናት፡፡ الَّذِينَ يَظُنُّونَ أَنَّهُم مُّلَاقُو رَبِّهِمْ وَأَنَّهُمْ إِلَيْهِ رَاجِعُونَ

በሚነካን መከራ ትእግስት ይጠይቃል፥ እነዚያን መከራ በነካቻቸው ጊዜ፦ "እኛ ለአላህ ነን፥ እኛም ወደ እርሱ ተመላሾች ነን" የሚሉት "ሷቢሪን" صَّابِرِين በጀነት የተበሰሩ ናቸው፦
31፥17 በሚያገኝህም መከራ ላይ ታገስ!፡፡ وَاصْبِرْ عَلَىٰ مَا أَصَابَكَ
2፥155 ታጋሾችንም አብስር፡፡ وَبَشِّرِ الصَّابِرِينَ
2፥156 እነዚያን መከራ በነካቻቸው ጊዜ «እኛ ለአላህ ነን፥ እኛም ወደ እርሱ ተመላሾች ነን» የሚሉትን አብስር፡፡ الَّذِينَ إِذَا أَصَابَتْهُم مُّصِيبَةٌ قَالُوا إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُونَ

ዐውዱ ላይ "እነዚያ" የሚለው አመልካችን ተውላጠ ስም "ታጋሾች" የተባሉትን ነው። አምላካችን አሏህ እነዚያን መከራ በነካቻቸው ጊዜ፦ "እኛ ለአላህ ነን፥ እኛም ወደ እርሱ ተመላሾች ነን" ከሚሉት ታጋሾች ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አዳዲስ ለገባችሁ ወደ ላይ ያልተነበቡ የተለያዩ አርዕስት ስላሉ ወጣ ብላችሁ አንብቡ!
ጥቁር ሰው

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

30፥22 "ሰማያትንና ምድርንም መፍጠሩ፣ የቋንቋዎቻችሁ እና የመልኮቻችሁም መለያየት ከአስደናቂ ተአምራቱ ነው፥ በዚህ ውስጥ ለዐዋቂዎች ተአምራት አሉበት"፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ خَلْقُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَاخْتِلَافُ أَلْسِنَتِكُمْ وَأَلْوَانِكُمْ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّلْعَالِمِينَ

"ኻሪጅ" خَارِج ወይም "ኻሪጂይ" خَارِجِيّ የሚለው ቃል "ኻሪጀ" خَارِجَ ማለትም "አፈነገጠ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "አፈንጋጭ" ማለት ነው፥ የኻሪጅ ወይም የኻሪጂይ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ኻሪጁን" خَارِجُون ወይም "ኸዋሪጅ" خَوَارِج‎ ሲሆን "አፈንጋጮች" ማለት ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 173
ኢብኒ አቢ አውፋ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ኸዋሪጅ የጀሀነም ውሻ ናቸው"። عَنِ ابْنِ أَبِي أَوْفَى، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ "‏ الْخَوَارِجُ كِلاَبُ النَّارِ ‏"‏ ‏.‏

እነዚህ ከኢሥላም የሚያፈነግጡ ሕዝቦች ቁርኣንን ይቀራሉ ግን ከጉሮሮአቸው አልፎ አይወርድም፥ መነሻቸውም ዒራቅ ነው፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 88, ሐዲስ 16
ዩሠይር ኢብኑ ዐምር እንደተረከው፦ "እኔ ለሠህል ኢብኑ ሑነይፍ፦ "ነቢዩ"ﷺ" ስለ ኸዋሪጅ ነገር ሲናገሩ ሰምተሃልን? ብዬ ጠየኩት፥ እርሱም፦ "እርሳቸው በእጃቸው ወደ ዒራቅ በማመላከት፦ "ከእርሱም(ከዒራቅ) ሕዝቦች ቁርኣንን ይቀራሉ ግን ከጉሮሮአቸው አልፎ አይወርድም፥ ልክ ከደጋን ቀስት እንደሚወረወር ከኢሥላም ያፈነግጣሉ"። حَدَّثَنَا يُسَيْرُ بْنُ عَمْرٍو، قَالَ قُلْتُ لِسَهْلِ بْنِ حُنَيْفٍ هَلْ سَمِعْتَ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ فِي الْخَوَارِجِ شَيْئًا قَالَ سَمِعْتُهُ يَقُولُ ـ وَأَهْوَى بِيَدِهِ قِبَلَ الْعِرَاقِ ـ ‏ "‏ يَخْرُجُ مِنْهُ قَوْمٌ يَقْرَءُونَ الْقُرْآنَ لاَ يُجَاوِزُ تَرَاقِيَهُمْ، يَمْرُقُونَ مِنَ الإِسْلاَمِ مُرُوقَ السَّهْمِ مِنَ الرَّمِيَّةِ ‏"‌‏.‏

በአንደበቶቻቸው እውነትን የሚናገሩ ግን ከጉሮሮአቸው አልፎ ወደ ልቦናቸው የማይዘልቅ ከሆኑን አንዱ አሏህ ዘንድ ከፍጥረት እጅግ የተጠላው ሲሆን መልኩ ለምልክትነት ጥቁር እንደሆነ ተጠቅሷል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 12, ሐዲስ 205
ዑበይዲሏህ ኢብኒ አቢ ራፊዕ እንደተረከው፦ "ሐሩሪያህ ባፈነገጡ ጊዜ ነጻ የወጣ የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" አገልጋይ ከዐሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ"ረ.ዐ." ጋር ሆኖ እንዲህ አለ፦ "እነርሱም፦ "ፍርድ የአሏህ እንጂ የማንም አይደለም" አሉ፥ ዐሊይም፦ "ሐሰት የተፈለገባት እውነተኛ ንግግር ናት፥ የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" የእነርሱን ጠባይ ገልጸውታል። እኔም በእነዚህ ሰዎች ላይ ይህንን ጠባይ አይቼባቸዋለው፥ በአንደበቶቻቸው እውነትን የሚናገሩ ግን ከጉሮሮአቸው አልፎ ወደ ልቦናቸው የማይዘልቅ የሆኑ ናቸው፡፡ ከእነርሱ መካከል አሏህ ዘንድ ከፍጥረት እጅግ የተጠላው አንድ ጥቁር ሰው አለ፥ ይህም ሰው አንደኛው እጁ የበግ ወይም የፍየል ጡት የሚመስል ነው"። عَنْ عُبَيْدِ اللَّهِ بْنِ أَبِي رَافِعٍ، مَوْلَى رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم أَنَّ الْحَرُورِيَّةَ لَمَّا خَرَجَتْ وَهُوَ مَعَ عَلِيِّ بْنِ أَبِي طَالِبٍ - رضى الله عنه - قَالُوا لاَ حُكْمَ إِلاَّ لِلَّهِ ‏.‏ قَالَ عَلِيٌّ كَلِمَةُ حَقٍّ أُرِيدَ بِهَا بَاطِلٌ إِنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَصَفَ نَاسًا إِنِّي لأَعْرِفُ صِفَتَهُمْ فِي هَؤُلاَءِ ‏ "‏ يَقُولُونَ الْحَقَّ بِأَلْسِنَتِهِمْ لاَ يَجُوزُ هَذَا مِنْهُمْ - وَأَشَارَ إِلَى حَلْقِهِ - مِنْ أَبْغَضِ خَلْقِ اللَّهِ إِلَيْهِ مِنْهُمْ أَسْوَدُ إِحْدَى يَدَيْهِ طُبْىُ شَاةٍ أَوْ حَلَمَةُ ثَدْىٍ ‏"‏ ‏

"ሐሩሪያህ" حَرُورِيَّة የኸዋሪጅ ሌላ ስም ነው፥ እዚህ ሐዲስ ላይ "ጥቁር ሰው አሏህ ዘንድ ከፍጥረት እጅግ የተጠላው ነው" የሚል ሽታው እንኳን የለም። ባይሆን "አሥወድ" أَسْوَد የሚለው ቅጽል ሰውዬውን ለመለየት የገባ ገላጭ ቃል ነው፥ ዒራቅ ደግሞ የአፍሪካ አህጉር ስላልሆነ "አንድ ጥቁር ሰው አለ" የሚለው አፍሪካውያንን በፍጹም አያመለክትም። ለምሳሌ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለን አንድ ደግ ሰው ለመግለጽ "መቆዶንያ ውስጥ የሚሠራ ቢኒያም የሚባል አንድ ቀይ ሰው አለ" ብል "ቀይ" የሚለውን ቀለም የወሰድኩት ለምልክት እንጂ ልጁ "ቀዳማይ አሜሪካዊ የሆኑትን ቀይ ሕንድ ነው" ወይም "ቀይ ሰው ሁሉ ደግ ነው" እያኩኝ እንዳልሆነ ማንም ይረዳል፥ በተመሳሳይም ከኸዋሪጅ አንዱ አሏህ ዘንድ ከፍጥረት እጅግ የተጠላው ጥቁር በመሆኑ ሳይሆን ኻሪጅ በመሆኑ ነው። ከዚያ ይልቅ የሰው መልክ በቀለም መለያየት ከአስደናቂ የአሏህ ተአምራቱ ነው፥ በዚህ ውስጥ ለዐዋቂዎች ተአምራት አሉበት፦
30፥22 "ሰማያትንና ምድርንም መፍጠሩ፣ የቋንቋዎቻችሁ እና የመልኮቻችሁም መለያየት ከአስደናቂ ተአምራቱ ነው፥ በዚህ ውስጥ ለዐዋቂዎች ተአምራት አሉበት"፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ خَلْقُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَاخْتِلَافُ أَلْسِنَتِكُمْ وَأَلْوَانِكُمْ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّلْعَالِمِينَ
"አደም" آدَم የሚለው ቃል "አደመ" آدَمَ ማለትም "ጠቆረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ጥቁር" ማለት ነው፥ ጭቃ በባሕርይው የመድረቅ ባሕርይ አለው። ጭቃ ሲደርቅ ይጠቁራል፥ አደም የተፈጠረው ከጥቁር ጭቃ ነው፦
15፥26 ሰውንም ከሚቅጨለጨል ሸክላ ከሚገማ ጥቁር ጭቃ በእርግጥ ፈጠርነው፡፡ وَلَقَدْ خَلَقْنَا الْإِنسَانَ مِن صَلْصَالٍ مِّنْ حَمَإٍ مَّسْنُونٍ

የአደም ልጆች በጠቅላላ በአደም በኩል ከምድር አፈር የመጣን ነን፥ ብዙ ዓይነት የቀለም ልዩነት ያለብን አሏህ ከሁሉም የምድር ክፍል ወስዶ ስለፈጠረን ነው፦
71፥17 "አላህም ከምድር ማብቀልን አበቀላችሁ"። وَاللَّهُ أَنبَتَكُم مِّنَ الْأَرْضِ نَبَاتًا
20፥55 "ከእርሷ ከምድር ፈጠርናችሁ"። مِنْهَا خَلَقْنَاكُمْ
78፥7 "ብዙ ዓይነቶችም አድርገን ፈጠርናችሁ"፡፡ وَخَلَقْنَٰكُمْ أَزْوَٰجًۭا
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3213
አቡ ሙሣ እንደተረከው፥ የአላህ መልክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ከፍ ያለው አሏህ አደምን ከጭብጥ አፈር ፈጠረው፥ እርሱም ከሁሉም የምድር ክፍል ወስዶ ፈጠረው። ስለዚህ የአደም ልጆች አንዳንዶቹ ቀይ፣ ነጭ፣ ጥቁር፣ ጠይም ወዘተ ሆኑ"። عَنْ أَبِي مُوسَى الأَشْعَرِيِّ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ إِنَّ اللَّهَ تَعَالَى خَلَقَ آدَمَ مِنْ قَبْضَةٍ قَبَضَهَا مِنْ جَمِيعِ الأَرْضِ فَجَاءَ بَنُو آدَمَ عَلَى قَدْرِ الأَرْضِ فَجَاءَ مِنْهُمُ الأَحْمَرُ وَالأَبْيَضُ وَالأَسْوَدُ وَبَيْنَ ذَلِكَ وَالسَّهْلُ وَالْحَزْنُ وَالْخَبِيثُ وَالطَّيِّبُ ‏”‏

"አደም" آدَم የሚለው ስም 25 ጊዜ በቁርኣን የመጣ ሲሆን ዒሣ የሚለው ስም በተመሳሳይ የመጣው 25 ጊዜ ነው፥ አሏህ ዘንድ የዒሣ ምሳሌ እንደ አደም ብጤ ሲሆን ዒሣ የፊቱ ቀለም ጥቁር ነው፦
3፥59 "አላህ ዘንድ የዒሣ ምሳሌ እንደ አደም ብጤ ነው፡፡ ከዐፈር ፈጠረው፡፡ ከዚያም ለእርሱ «ኹን» አለው፥ ኾነም"፡፡ إِنَّ مَثَلَ عِيسَىٰ عِندَ اللَّهِ كَمَثَلِ آدَمَ ۖ خَلَقَهُ مِن تُرَابٍ ثُمَّ قَالَ لَهُ كُن فَيَكُونُ
ሙወጧኡል ኢማም መሊክ መጽሐፍ 49, ሐዲስ 1675
ዐብደሏህ ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "በከዕባህ ዘንድ በነበርኩ ጊዜ ራእይ አየው፥ ከጥቁር ሰዎች እናንተ ዐይታችሁ የማታውቁትን በጣም ቆንጆ ጥቁር ሰው አየሁ"፡፡ عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عُمَرَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ أَرَانِي اللَّيْلَةَ عِنْدَ الْكَعْبَةِ فَرَأَيْتُ رَجُلاً آدَمَ كَأَحْسَنِ مَا أَنْتَ رَاءٍ مِنْ أُدْمِ الرِّجَالِ "

ነቢያችንም"ﷺ"፦ ይህ ማን ነው? ብለው ሲጠይቁ፦ "የመርየም ልጅ መሢሑ ነው" ተብለዋል፦
ሙወጧኡል ኢማም መሊክ መጽሐፍ 49, ሐዲስ 1675
"እኔም ይህ ማን ነው? ብዬ ጠየኩኝ፥ "የመርየም ልጅ መሢሑ ነው" ተብሎ ተመለሰልኝ"። فَسَأَلْتُ مَنْ هَذَا قِيلَ هَذَا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

ስለዚህ "አፍሪካዊ ጥቁር አሏህ ዘንድ ከፍጥረት እጅግ የተጠላው ነው" የሚለው የሚሽነሪዎች ቅጥፈት እንዲህ ይጋለጣል፥ አምላካችን አሏህ ውጫዊ ነገራችንን የፈጠረው ለውበት እንጂ የሚመዝነው ሥራችንን እና ለሥራ የወጠንበትን ልብ ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 45, ሐዲስ 42
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ *"የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "አሏህ ወደ ልባችሁ እና ወደ ሥራችሁ እንጂ ወደ ቅርጻችሁ እና ወደ ገንዘባችሁ አይመለከትም"፡፡ عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ إِنَّ اللَّهَ لاَ يَنْظُرُ إِلَى صُوَرِكُمْ وَأَمْوَالِكُمْ وَلَكِنْ يَنْظُرُ إِلَى قُلُوبِكُمْ وَأَعْمَالِكُمْ ‏"‏

“ዐመል” عَمَل ማለት “ገቢር” ወይም “ድርጊት” አሊያም "ሥራ" ማለት ሲሆን የዐመል ብዙ ቁጥር ደግሞ "አዕማል" أَعْمَال ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ወንድ ወይስ ሰው?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

33፥4 አላህ ለአንድ ሰው በሆዱ ውስጥ ሁለትን ልቦች አላደረገም፡፡ مَّا جَعَلَ اللَّهُ لِرَجُلٍ مِّن قَلْبَيْنِ فِي جَوْفِهِ

ሴትን በቁልምጫ ስም "ሴትዮ" ስንል ወንድን ደግሞ "ሰውዬ" እንላለን፥ ነገር ግን "ሰውዬ" የሚለው የቀልምጫ ስም መነሻው "ሰው" ሲሆን "ሰው" የሚለው ቃል በተናጥል "ወንድ" የሚለው ቃል ለመተካት እና እንዲሁ በጥቅሉ "ወንድ እና ሴትን" ለማመልከት ይመጣል። በተመሳሳይም "ረጁል" رَجُل የሚለው ቃል "ወንድ" ማለት ሲሆን "ሰው" በሚል ይመጣል፦
33፥4 አላህ ለአንድ ሰው በሆዱ ውስጥ ሁለትን ልቦች አላደረገም፡፡ مَّا جَعَلَ اللَّهُ لِرَجُلٍ مِّن قَلْبَيْنِ فِي جَوْفِهِ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ሰው" ለሚለው የገባው ቃል "ረጁል" رَجُل መሆኑን አስተውል! "ረጁል" ልክ እንደ "ሰው" የሚለው ቃል ሁለት የተለያዩ ትርጉም ወክሎ ጥቅም ላይ የሚውል እና የሚገባ ቃል ነው፥ "ሰው" ለሴት እና ለወንድ የወል ስም ሆኖ ያገለግላል፦
4፥124 ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ ከበጎ ሥራዎች አንዳችን የሚሠራም ሰው እነዚያ ገነትን ይገባሉ፡፡ وَمَن يَعْمَلْ مِنَ الصَّالِحَاتِ مِن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَأُولَـٰئِكَ يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ
40፥40 “እርሱ ምእመን ኾኖ ከወንድ ወይም ከሴት በጎን የሠራም ሰው እነዚያ ገነትን ይገባሉ፡፡ በእርሷ ውስጥ ያለ ቁጥጥር ይመገባሉ”፡፡ وَمَنْ عَمِلَ صَالِحًا مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَأُولَـٰئِكَ يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ يُرْزَقُونَ فِيهَا بِغَيْرِ حِسَابٍ

እነዚህ አናቅጽ ላይ "ሰው" ለሚለው የገባው ቃል "ሁወ" هُوَ ሲሆን "እርሱ" ማለት ነው፥ እርሱ የተባለው ሰው "ወንድ እና ሴት" ስለሆነ "ዘከር" ذَكَر እና "ኡንሳ" أُنثَىٰ የሚለው ቃል ተቀምጧል። ስለዚህ "አላህ ለአንድ ሰው በሆዱ ውስጥ ሁለትን ልቦች አላደረገም" የሚለውን "አላህ ለአንድ ወንድ በሆዱ ውስጥ ሁለትን ልቦች አላደረገም" ተብሎ መተርጎም አለበት የሚለው ሙግት አይሠራም፥ "አላህ ለአንድ ወንድ በሆዱ ውስጥ ሁለትን ልቦች አላደረገም" ከተባለ "ሴት ሁለት ልብ አላት ማለት ነው፥ ያ ከሆነ እሥልምና ሴትን ዝቅ ያረጋል" የሚለው የክርስቲያን ፕሪንስ አንኮላ ስሑት ሙግት ፉርሽ ነው። "አንድ ቃልን ለሁለት የተለያዩ ነገሮችን የሚውለውን"two different things by the same word" አንድ ነገር አርጎ መውሰድ "አሻሚ ተፋልሶ"Fallacy of equivocation" ነው። ለምሳሌ፦
premise 1
Since only man is rational.
premise 2
And no woman is a man.
conclusion
Therefore, no woman is rational.

ብሎ መተርጎም አሻሚ ሕፀፅ ነው፥ በ 1ኛው ነጥብ "Man" የተባለው "ሰው"human" ሲሆን በ 2ኛው "Man" የተባለው "ወንድ"male" ነው፥ ስለዚህ አንድ ቃልን ለሁለት የተለያዩ ነገሮችን ወክሎ የሚውለውን በተቃራኒው "Man" የሚለውን "ወንድ" ብቻ ብለን ተርጉመን፦ "ወንድ ብቻውን ዐቅለኛ ነው፣ ሴት ወንድ አይደለችም፣ ስለዚህ ሴት ዐቅለኛ አይደለችም" ብሎ መረዳት በሥ-አመክንዮ ሙግት አሻሚ ሕፀፅ ነው፦
17፥70 የአደምንም ልጆች በእርግጥ አከበርናቸው፡፡ وَلَقَدْ كَرَّمْنَا بَنِي آدَمَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ልጆች" ለሚለው የገባው ቃል "በኒይ" بَنِي ሲሆን "ኢብን" اِبْن ለሚለው ቃል ብዜት ነው፥ "ኢብን" اِبْن ማለት "ወንድ ልጅ" ማለት ሲሆን "በኒይ" بَنِي ማለት ደግሞ "ወንድ ልጆች" ማለት ነው። ነገር ግን አምላካችን አሏህ፦ "የአደም ልጆች" ሲል የአደምን ወንድ እና ሴት ልጆች እንጂ ወንድ ልጆች ብቻ ለማለት አይደለም፦
18፥46 ገንዘብ እና ልጆች የቅርቢቱ ሕይወት ጌጦች ናቸው፡፡ الْمَالُ وَالْبَنُونَ زِينَةُ الْحَيَاةِ الدُّنْيَا
8፥28 ገንዘቦቻችሁ እና ልጆቻችሁም ፈተና ብቻ መኾናቸውን እና አላህ ዘንድ ታላቅ ምንዳ ያለው መኾኑን እወቁ፡፡ وَاعْلَمُوا أَنَّمَا أَمْوَالُكُمْ وَأَوْلَادُكُمْ فِتْنَةٌ وَأَنَّ اللَّهَ عِندَهُ أَجْرٌ عَظِيمٌ

እነዚህ አናቅጽ ላይ "በኑን" بَنُون የሚለው "ኢብን" اِبْن ለሚለው ብዙ ቁጥር ሲሆን አጠቃላይ ልጆችን ስለሚያመለክት "አውላድ" أَوْلَاد በሚል መጥቷል፥ "ወለድ" وَلَد ልጅ ማለት ሲሆን "አውላድ" أَوْلَاد ደግሞ "ልጆች" ማለት ነው። ይህ በነሕው ደርስ "ኢሥሙል ሙሽተሪክ" ይባላል፥ "ኢሥሙል ሙሽተሪክ" اِسْم المُشْتَرِك ማለት "ተመሳሳይ ቃል ግን የተለያየ ትርጉም ያለው አሳብ"Homonym" ነው።
እዚህ ድረስ ከተግባባን በተመሳሳይ ሰዋስው ባይብል ላይ የተቀመጡትን አንዳንድ አናቅጽ እንመልከት፦
ዘሌዋውያን 20፥27 "ሰው" ወይም "ሴት" መናፍስትን ቢጠሩ ወይም ጠንቋዮች ቢሆኑ ፈጽመው ይገደሉ!።
ዘኍልቍ 6፥2 ለእስራኤል ልጆች ንገራቸው፦ "ሰው" ወይም "ሴት" ለያህዌህ ራሱን የተለየ ያደርግ ዘንድ የናዝራዊነት ስእለት ቢሳል።

እነዚህ አናቅጽ ላይ "ሰው" የተባለው በተናጥል የሴት ተቃራኒ "ወንድ" ነው፥ ያ ማለት "ሰው" ክቡር ነው" ሲባል ወንድ ክቡር ነው ሴት ወራዳ ናት" ማለት ነው" ብሎ መደምደም ስሑት ሙግት ነው፦
መዝሙር 49፥12 "ሰው ግን ክቡር ሆኖ ሳለ አያውቅም"።

እዚህ አንቀጽ ላይ "ሰው" የተባለው በጥቅል ወንድ እና ሴት ማለት ነው" ካላችሁ እንግዲያውስ "ረጁል" የሚለውንም ቃል በጥቅል ለወንድ እና ለሴት፥ በተናጥል ለወንድ ግልጋሎት ላይ እንደሚውል ተረዱት!

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አምላክ ስንት ነው?

ባይብል፦
ዘዳግም 6፥4 እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው።

ቁርኣን፦
18፥110 «እኔ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ማለት ወደ እኔ የሚወረድልኝ፦ "አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው" ማለትን ነው፥ እኔን ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ፡፡ የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፤ መልካም ሥራን ይሥራ፡፡ በጌታውም መገዛት አንድንም አያጋራ» በላቸው፡፡

የዐበይት ክርስትና አንቀጸ-እምነት የያዘ ሃይማኖተ አበው፦
የአንጾኪያው ኤጲስ ቆጶስ ዲዮናስዮስ ወደ እስክንድርያው ኤጲስ ቆጶስ ወደ ሚናስ በላከው መልእክቱ፦ "አምላክ ሦስት ነው" ብሎ እንቅጩን ፍርጥ አርጎ ተናግሯል፦
ሃይማኖተ አበው ዘዲዮናስዮስ ምዕራፍ 99
"አምላክነስ ሥሉስ እንበለ ተሌልዮ"።
ትርጉም፦
"አምላካችን ያለ መለየት ሦስት ነው"።

የነቢያትን ትምህርት ጠብቆ የያዘ የትኛው ሃይማኖት ነው? ክርስትና ወይስ እሥልምና? መልሱ ለኅሊና!

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ተጋሪ የለውም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

43፥15 ከባሮቹም ለእርሱ ቁራጭን ልጅ አደረጉለት፡፡ ሰው በእርግጥ ግልጽ ከሓዲ ነው፡፡ وَجَعَلُوا لَهُ مِنْ عِبَادِهِ جُزْءًا ۚ إِنَّ الْإِنسَانَ لَكَفُورٌ مُّبِينٌ

የመርየም ልጅ መሢሑ ለአሏህ ባሪያ ከመኾን ፈጽሞ አይጠየፍም፥ አምላካችን አሏህ እርሱን ለእስራኤል ልጆች ተአምር ያደረገው ባሪያ እንጅ ሌላ አይደለም፦
4፥172 መሢሑ ለአላህ ባሪያ ከመኾን ፈጽሞ አይጠየፍም፡፡ لَّن يَسْتَنكِفَ الْمَسِيحُ أَن يَكُونَ عَبْدًا لِّلَّهِ
43፥59 እርሱ በእርሱ ላይ የለገስንለት እና ለእስራኤል ልጆች ተአምር ያደረግነው የኾነ ባሪያ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ إِنْ هُوَ إِلَّا عَبْدٌ أَنْعَمْنَا عَلَيْهِ وَجَعَلْنَاهُ مَثَلًا لِّبَنِي إِسْرَائِيلَ

ነገር ግን መሢሑ ከአሏህ ባሮች አንዱ ሆኖ ሳለ ዐበይት ክርስቲያኖች ከአብ ባሕርይ ባሕርይን ወስዶ፣ ከአካሉ አካልን ወስዶ እና አብን አህሎና መስሎ ከእርሱ ወጣ፣ ተወለደ፣ ተገኘ በማለት አሏህን ወላዲ መሢሑን ተወላዲ በማድረግ ለአሏህ ቁራጭን አደረጉለት፦
43፥15 ከባሮቹም ለእርሱ ቁራጭን ልጅ አደረጉለት፡፡ ሰው በእርግጥ ግልጽ ከሓዲ ነው፡፡ وَجَعَلُوا لَهُ مِنْ عِبَادِهِ جُزْءًا ۚ إِنَّ الْإِنسَانَ لَكَفُورٌ مُّبِينٌ

“አካል ዘእም-አካል፥ ባሕርይ ዘእም-ባሕርይ” ማለት “ከአካል አካልን ወስዶ፥ ከባሕርይ ባሕርይን ወስዶ” ማለት ነው፥ ወልድ ከአብ ማንነት(አካል) ማንነትን ወስዶ እና ከአብ ምንነት(ባሕርይ) ምንነትን ወስዶ ተወለደ የሚለው ትምህርታቸው ከባሮቹ ለአሏህ ቁራጭን ማድረግ ነው። አሏህ አንድ ነው፥ እርሱ ከማንነቱ እና ከምንነቱ ማንንም አልወለደም። ከእርሱ ማንነት እና ምንነት የተወለደ ማንም የለም፥ ከእርሱ የተወለደ ማንም አምላክ የለም፦
112፥1 በል «እርሱ አላህ አንድ ነው፡፡ قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ
112፥3 አልወለደም፤ አልተወለደምም፡፡ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ
23፥91 አላህ ምንም ልጅን አልወለደም፡፡ ከእርሱም ጋር አንድም አምላክ የለም፡፡ مَا اتَّخَذَ اللَّهُ مِن وَلَدٍ وَمَا كَانَ مَعَهُ مِنْ إِلَـٰهٍ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 496
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “ነቢዩ”ﷺ” አሏህ እንዲህ አሉ፦ “አሏህም አለ፦ “የአደም ልጅ እኔን አስዋሸ፥ እንዲህ ለማድረግ መብት አልነበረውም፡፡ ደግሞም ሰደበኝ፥ እንዲህ ለማድረግም መብት አልነበረውም፡፡ እኔን ማስዋሸቱ የሚያመለክተው፦ “መጀመሪያ ላይ እንደፈጠረኝ አድርጎ ዳግም አይሠራኝም” የሚለው ንግግሩ ነው፥ ለመሆኑ መጀመሪያ እርሱን መፍጠር ነው ወይስ ዳግም መሥራት ለእኔ ይበልጥ የሚቀል የነበረው? እኔን መሳደቡን የሚያመለክተው ደግሞ፦ “አሏህ ልጅ ወልዷል” ማለቱ ነው፥ እኔ አንድ ነኝ፣ የሁሉ መጠጊያ ነኝ፣ አልወለድኩም፣ አልተወለድኩም፣ ለእኔ አንድም ብጤ የለኝም”፡፡ عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ قَالَ اللَّهُ كَذَّبَنِي ابْنُ آدَمَ وَلَمْ يَكُنْ لَهُ ذَلِكَ، وَشَتَمَنِي وَلَمْ يَكُنْ لَهُ ذَلِكَ، فَأَمَّا تَكْذِيبُهُ إِيَّاىَ فَقَوْلُهُ لَنْ يُعِيدَنِي كَمَا بَدَأَنِي، وَلَيْسَ أَوَّلُ الْخَلْقِ بِأَهْوَنَ عَلَىَّ مِنْ إِعَادَتِهِ، وَأَمَّا شَتْمُهُ إِيَّاىَ فَقَوْلُهُ اتَّخَذَ اللَّهُ وَلَدًا، وَأَنَا الأَحَدُ الصَّمَدُ لَمْ أَلِدْ وَلَمْ أُولَدْ وَلَمْ يَكُنْ لِي كُفْأً أَحَدٌ ‏”‌‏.‏

አሏህ ከሚሉት ነገር ጥራት ይገባውና ከወለደ በአንድነቱ ላይ ብዝኃነት ሊመጣ ነው፥ ከተወለደ ደግሞ መነሾ እና ጅማሮ ሊኖረውን ነው። በእርግጥ፦ “አሏህ ልጅን ወለደ” ማለት ከባድ መጥፎ ንግግር ነው፥ ከዚህ ንግግር ሰማያት ሊቀደዱ፣ ምድርም ልትሰነጠቅ፣ ጋራዎችም ተንደው ሊወድቁ ይቃረባሉ፦
19፥88 «አልረሕማንም ልጅን ወለደ» አሉ፡፡ وَقَالُوا اتَّخَذَ الرَّحْمَـٰنُ وَلَدًا
19፥89 ከባድ መጥፎን ነገር በእርግጥ አመጣችሁ፡፡ لَّقَدْ جِئْتُمْ شَيْئًا إِدًّا
19፥90 ከዚህ ንግግር ሰማያት ሊቀደዱ፣ ምድርም ልትሰነጠቅ፣ ጋራዎችም ተንደው ሊወድቁ ይቃረባሉ፡፡ تَكَادُ السَّمَاوَاتُ يَتَفَطَّرْنَ مِنْهُ وَتَنشَقُّ الْأَرْضُ وَتَخِرُّ الْجِبَالُ هَدًّا
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 8
አቢ ሙሣ አል-አሽዐሪይ እንደተረከው፦ “ነቢዩ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “እንደ አሏህ መጥፎ ንግግር እየሰማ የሚታገስ ማንም የለም፥ ለእርሱ ልጅን ይመጥናሉ። እርሱ ግን ጤንነት ይሰጣቸዋል እንዲሁ ሲሳይ ይለግሳቸዋል”። عَنْ أَبِي مُوسَى الأَشْعَرِيِّ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَا أَحَدٌ أَصْبَرُ عَلَى أَذًى سَمِعَهُ مِنَ اللَّهِ، يَدَّعُونَ لَهُ الْوَلَدَ، ثُمَّ يُعَافِيهِمْ وَيَرْزُقُهُمْ ‏”‌‏.‏

ከዚህ ሁሉ የሚገርመው “ለአሏህ ልጅ አለው” ብለው ወደ ኩፍራቸው ይጣራሉ፥ ለአሏህ ልጅ መያዝ አይገባውም። በሰማያት እና በምድር ያለው ሁሉ በትንሣኤ ቀን ለአሏህ ባሪያ ኾነው የሚመጡ እንጂ ሌላ አይደሉም፦
19፥91 “ለአልረሕማን ልጅ አለው” ብለው ይጣራሉ፡፡ أَن دَعَوْا لِلرَّحْمَـٰنِ وَلَدًا
19፥92 ለአልረሕማን ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ وَمَا يَنبَغِي لِلرَّحْمَـٰنِ أَن يَتَّخِذَ وَلَدًا
19፥93 በሰማያት እና በምድር ያለው ሁሉ በትንሣኤ ቀን ለአልራሕማን ባሪያ ኾነው የሚመጡ እንጂ ሌላ አይደሉም፡፡ إِن كُلُّ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ إِلَّا آتِي الرَّحْمَـٰنِ عَبْدًا
“ወለድ” وَلَد የሚለው ቃል “ወለደ” وَلَدَ ማለትም “ወለደ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ወልድ” ወይም “ልጅ” ማለት ነው። የቤተክርስቲያን አበው ከሚባሉት አንዱ አርጌንስ፦ “አምላክ ከእርሱ ለተወለደው ለአንድያ ልጁ አባት ነው፥ ከእርሱ ምንነት ያለ ምንም ጅማሮ ተገኘ” “እርሱ(ወልድ) ዲዩቴሮስ ቴኦስ ነው” ብሎ ያስተምር ነበር። ዋቢ መጽሐፍት ይመልከቱ፦
1. Origen, De Principiis, Book 1:
2. Origen Against Celsus, 5.39 (PG 14:108-110; ANF 4: 561.)

“ዲዩቴሮስ ቴኦስ” δεύτερος Θεός ማለት “ሁለተኛ አምላክ” ማለት ነው፥ ነገር ግን ለአሏህ አንድም ቢጤ፣ አምሳያ፣ አቻ፣ እኩያ፣ ባልደረባ፣ ሞክሼ፣ ተጋሪ የለውም፦
112፥4 ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም፡፡ وَلَمْ يَكُن لَّهُ كُفُوًا أَحَدٌ
6፥163 «ለእርሱ ተጋሪ የለውም፡፡ በዚህም በማጥራት ታዘዝኩ፡፡ እኔም የሙሥሊሞች መጀመሪያ ነኝ» በል!፡፡ لَا شَرِيكَ لَهُ ۖ وَبِذَٰلِكَ أُمِرْتُ وَأَنَا أَوَّلُ الْمُسْلِمِينَ

በ 325 ድኅረ ልደት የኒቂያ ጉባኤ ላይ የአትናቴዎስ የእምነት መግለጫ ኢየሱስን፦ “ከአምላክ የተገኘ አምላክ” ሲሉት ከ 1225-1274 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረ ሃይማኖተኛ ፈላስፋ ቶማስ አኩናስ ደግሞ፦ “ከአምላክ በተገኘ አምላክ” ብሎታል። ዋቢ መጽሐፍ ይመልከቱ፦
Thomas Aquinas, Comm. On John, Chap 5, Lecture 2

አሏህ አምላክነቱን የሚጋራ ተጋሪ የለውም፥ ማንነቱን እና ምንነቱን የሚጋሩ ተጋሪ ከሌለው እርሱ ወላዲ ሆኖ የወለደው ተወላዲ በፍጹም የለም፦
6፥101 እርሱ ሰማያትንና ምድርን ያለ ብጤ ፈጣሪ ነው፡፡ ለእርሱ ሷሒባህ የሌሉት ሲኾን እንዴት ለእርሱ ልጅ ይኖረዋል? ነገርንም ሁሉ ፈጠረ፡፡ እርሱም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ بَدِيعُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ أَنَّىٰ يَكُونُ لَهُ وَلَدٌ وَلَمْ تَكُن لَّهُ صَاحِبَةٌ ۖ وَخَلَقَ كُلَّ شَيْءٍ ۖ وَهُوَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ
He is Beginner of the heavens and the earth. How would He have a child when He is without a “companion” and He created everything and He is Knowing of everything? Dr. Laleh Bakhtiar

“ሷሒብ” صَاحِب የሚለው ቃል “ሶሒበ” صَحِبَ ማለትም “ተጎዳኘ” “ተጎዳጀ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ጓድ” “ጓደኛ” “ባልደረባ”companion” ማለት ነው፦
18፥37 “ጓደኛው” እርሱ ለእርሱ የሚመላለሰው ሲኾን «በዚያ ከዐፈር፣ ከዚያም ከፍትወት ጠብታ ከፈጠረህ፣ ከዚያም ሰው ባደረገህ አምላክ ካድክን» አለው፡፡ قَالَ لَهُ صَاحِبُهُ وَهُوَ يُحَاوِرُهُ أَكَفَرْتَ بِالَّذِي خَلَقَكَ مِن تُرَابٍ ثُمَّ مِن نُّطْفَةٍ ثُمَّ سَوَّاكَ رَجُلًا

እዚህ አንቀጽ ላይ “ጓደኛ” ለሚለው የገባው ቃል “ሷሒብ” صَاحِب መሆኑ ልብ አድርግ! የሷሒብ ብዙ ቁጥር ደግሞ “አስሓብ” أَصْحَاب‎ ወይም “ሷሒባህ” صَاحِبَة ሲሆን “ጓዶች” “ጓደኞች” “ባልደረቦች” ማለት ነው። ለምሳሌ፦ “መልአክ” مَلْأَك የሚለው ቃል “ለአከ” لَأَكَ ማለትም “ላከ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ተላላኪ” ማለት ነው፥ የመለክ ብዙ ቁጥር ደግሞ “መላኢክ” مَلَائِك‎ ወይም “መላኢካህ” مَلَائِكَة‎ ነው። “ሷሒባህ” እና “መላኢካህ” مَلَائِكَة‎ በሚለው መድረሻ ቅጥያ ላይ ያለች “ታ” ة የምትባለው “ታእ-መርቡጧህ” تَاء مَرْبُوطَة ሙአነስ ናት፦
3፥39 እርሱም በጸሎት ማድረሻው ክፍል ቆሞ ሲጸልይ መላእክት ጠሩት፡፡ فَنَادَتْهُ الْمَلَائِكَةُ وَهُوَ قَائِمٌ يُصَلِّي فِي الْمِحْرَابِ
3፥42 መላእክትም ያሉትን አስታውስ፡፡ وَإِذْ قَالَتِ الْمَلَائِكَةُ

እነዚህ አናቅጽ ላይ “ጠሩ” ለሚለው የገባው ቃል “ናደት” َنَادَتْ ሲሆን “ያሉት” ለሚለው የገባው ቃል ደግሞ “ቃለት” قَالَت ነው፥ ግን “ናደት” َنَادَتْ ማለት “ጠራች” ማለት ሲሆን “ቃለት” قَالَت ደግሞ “አለች” ማለት ነው። እንዲሁ “ለም ተኩን” لَمْ تَكُن ማለት “የሌሉ” ማለት ሲሆን በአንስታይ መደብ “የሌለች” ማለት ነው።
እዚህ ድረስ ከተግባባን ልጅ ከወላጅ ሲወለድ በመልክ መስሎ እና በባሕርይ አህሎ ከወላጁ ምንነት ተጋሪ ይሆናል፥ ልጅ ከወላጅ በመልክ የሚመሳሰል እና በባሕርይ የሚስተካከል አቻ፣ ሞክሼ፣ ቢጤ፣ አምሳያ ነው። አሏህ ተጋሪ ጓደኞች እና ባልደረቦች ከሌሉት ልጅ መውለዱ ትርጉም የለውም፥ አሏህ የእርሱን ማንነት እና ምንነት የሚጋራ ተጋሪ ከሌለው እንዴት ልጅ ይኖረዋል? ስለዚህ አሏህ ተጋሪ ከሌለው “እንዴት ልጅ ይኖረዋል” ማለት “ልጅ የለውም” ማለት ነው።
ለአሏህ ለዚያ ልጅን ላልያዘው፥ ለእርሱ ተጋሪ ለሌለው ምስጋና ይገባው፦
17፥111 «ለአላህ ለዚያ ልጅን ላልያዘው፣ ለእርሱም በንግሥናው ተጋሪ ለሌለው፣ ለእርሱም ከድካም ረዳት ለሌለው ምስጋና ይገባው» በል! ማክበርንም አክብረው፡፡ وَقُلِ الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي لَمْ يَتَّخِذْ وَلَدًا وَلَمْ يَكُن لَّهُ شَرِيكٌ فِي الْمُلْكِ وَلَمْ يَكُن لَّهُ وَلِيٌّ مِّنَ الذُّلِّ ۖ وَكَبِّرْهُ تَكْبِيرًا

አምላካችን አሏህ እነዚያንም «አሏህ ልጅን ይዟል» ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት ቁርኣንን አወረደው። ለአሏህ ልጅን መውለድ ባሕርይው ስላልሆነ አይገባውም፥ ከጉድለት ሁሉ ጠራ። አሏህ ዒሣን ያለ አባት “ኹን” በሚል ቃል ከመርየም ፈጥሮታል፦
18፥4 እነዚያንም «አላህ ልጅን ይዟል» ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት አወረደው፡፡ وَيُنذِرَ الَّذِينَ قَالُوا اتَّخَذَ اللَّهُ وَلَدًا
19፥35 ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፥ ነገርን በሻ ጊዜ ለርሱ የሚለው «ኹን» ነው፥ ወዲያውም ይኾናል፡፡ مَا كَانَ لِلَّهِ أَن يَتَّخِذَ مِن وَلَدٍ ۖ سُبْحَانَهُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ
3፥47 “ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለእኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፥ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አንዳችን በሻ ጊዜ ለርሱ «ኹን» ይለዋል፥ ወዲውኑም ይኾናል” አላት፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
‏اسلام عليكم ورحمته الله وبركاته

አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ።

የዶ/ር Dan Alan Brubaker መፅሀፍን ዳሰሳ ቀጣዩ ክፍል እነሆ! ዛሬ ደግሞ ክፍል -7 ይዘን ቀርበናል።በዚህ ክፍል ዶክተሩ ያቀረበውን ምሳሌ 6 -ላይ ምላሽ ተሰጥቶበታል።

🔰Like and Share

https://tttttt.me/Abuyusra3
ነቢዩ ሃሩን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

19፥53 ከችሮታችንም ወንድሙን ሃሩንን ነቢይ አድርገን ሰጠነው፡፡ وَوَهَبْنَا لَهُ مِن رَّحْمَتِنَا أَخَاهُ هَارُونَ نَبِيًّا

አምላካችን አሏህ ሙሣን ነቢይ እና መልእክተኛ አርድጎ አስነስቶታል፥ ለእርሱም ተውራትን ሰቶታል፦
19፥51 በመጽሐፉ ውስጥ ሙሣንም አውሳ! እርሱ ምርጥ ነበርና፥ መልክተኛ ነቢይም ነበር፡፡ وَاذْكُرْ فِي الْكِتَابِ مُوسَىٰ ۚ إِنَّهُ كَانَ مُخْلَصًا وَكَانَ رَسُولًا نَّبِيًّا
2፥53 ሙሣንም መጽሐፍን እና ፉርቃንን ትመሩ ዘንድ በሰጠነው ጊዜ አስታውሱ!፡፡ وَإِذْ آتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ وَالْفُرْقَانَ لَعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ ለሙሣ የተሰጠው ተውራት መጽሐፍ እና ፉርቃን ተብሏል፥ "አል-ኪታብ" الْكِتَاب እና "አል-ፉርቃን" الْفُرْقَان በሚለው ቃላት መካከል "ወ" وَ የሚል አያያዥ መስተጻምር መኖሩ በራሱ ተውራት እራሱ ኪታብ እና ፉርቃን መሆኑን አመላካች ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 13, ሐዲስ 20
አል-በራእ ኢብኑ አዚብ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” ከአይሁድ ዐዋቂ አንድ ሰው ጠሩትና፦ "በዚያ ተውራትን ወደ ሙሣ ባወረደው በአሏህ አምልሃለው" አሉት"። عَنِ الْبَرَاءِ بْنِ عَازِبٍ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم دَعَا رَجُلاً مِنْ عُلَمَاءِ الْيَهُودِ فَقَالَ ‏ "‏ أَنْشُدُكَ بِاللَّهِ الَّذِي أَنْزَلَ التَّوْرَاةَ عَلَى مُوسَى ‏"‏ ‏.‏

አሏህ ለሙሣ ይህንን ሪሣላህ በማውረድ በደለኞች ወደ ሆኑ ሕዝቦች ወደ ፈርዖን ሕዝቦች፦ "ሂድ" አለው፦
26፥10-11 ጌታህም ሙሣን «ወደ በደለኞቹ ሕዝቦች ሂድ» በማለት በጠራው ጊዜ አስታውስ! «ወደ ፈርዖን ሕዝቦች ሂድ! አላህን አይፈሩምን?» አለው፡፡ وَإِذْ نَادَىٰ رَبُّكَ مُوسَىٰ أَنِ ائْتِ الْقَوْمَ الظَّالِمِينَ قَوْمَ فِرْعَوْنَ ۚ أَلَا يَتَّقُونَ

ሙሣም፦ "ጌታዬ ሆይ! እኔ ሊያስተባብሉኝ እፈራለሁ፣ ልቤም ይጠብባል፣ ምላሴም አይፈታም፡፡ ስለዚህ ወደ ሃሩን ላክ!" አለ፦
26፥12-13 ሙሣም አለ «ጌታዬ ሆይ! እኔ ሊያስተባብሉኝ እፈራለሁ፣ ልቤም ይጠብባል፣ ምላሴም አይፈታም፡፡ ስለዚህ ወደ ሃሩን ላክ!፡፡ قَالَ رَبِّ إِنِّي أَخَافُ أَن يُكَذِّبُونِ وَيَضِيقُ صَدْرِي وَلَا يَنطَلِقُ لِسَانِي فَأَرْسِلْ إِلَىٰ هَارُونَ

ሙሣ ወንድሙ ሃሩን እንዲረዳው አሏህ የጠየቀው ሙሣ ኮልታፋ ስለነበር እና ወንድሙ አንደበተ ርቱዕ ስለነበር ነው፥ ሙሣም ለአሏህ፦ "ሃሩንን ወንድሜን ከቤተሰቦቼም ለእኔ ረዳትን አድርግልኝ!" ብሎ በዱዓእ ጠየቀው፦
20፥129-30 ከቤተሰቦቼም ለእኔ ረዳትን አድርግልኝ! ሃሩንን ወንድሜን። وَاجْعَل لِّي وَزِيرًا مِّنْ أَهْلِي هَارُونَ أَخِي
28፥34 «ወንድሜም ሃሩን እርሱ ምላሱ ከእኔ የተባ ነው፡፡ እውነተኛነቴንም የሚያረጋግጥልኝ ረዳት ኾኖ ከእኔ ጋር ላከው፡፡ እኔ ሊያስተባብሉኝ እፈራለሁና፡፡» وَأَخِي هَارُونُ هُوَ أَفْصَحُ مِنِّي لِسَانًا فَأَرْسِلْهُ مَعِيَ رِدْءًا يُصَدِّقُنِي ۖ إِنِّي أَخَافُ أَن يُكَذِّبُونِ

"ከእኔ ጋር ላከው" የሚለው ይሰመርበት! አሏህም ለሙሣ ወንድሙን ሃሩንን ረዳት አደረገለት፥ ነቢይ አድርጎ ሰጠው፦
25፥35 በእርግጥም ለሙሣ መጽሐፍን ሰጠነው፡፡ ከእርሱም ጋር ወንድሙን ሃሩንን ረዳት አደረግንለት፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ وَجَعَلْنَا مَعَهُ أَخَاهُ هَارُونَ وَزِيرًا
19፥53 ከችሮታችንም ወንድሙን ሃሩንን ነቢይ አድርገን ሰጠነው፡፡ وَوَهَبْنَا لَهُ مِن رَّحْمَتِنَا أَخَاهُ هَارُونَ نَبِيًّا

አሏህ ለሙሣ ያወረደው ሪሣላህ ተውራት ሲሆን ይህንን ተውራት ሃሩን ከሙሣ ጋር እንዲላክ ተጋራው፦
20፥32 በነገሬም አጋራው፡፡ وَأَشْرِكْهُ فِي أَمْرِي

"አጋራ" ለሚለው የገባው ቃል "አሽሪክ" وَأَشْرِكْ ሲሆን ሃሩን የሙሣን ሪሣላህ ተውራትን መጋራቱን ያሳያል። አሏህ ተውራት ለሙሣ እና ለሃሩን ፉርቃን፣ ብርሃንን እና ለጥንቁቆች መገሰጫን አድርጎ ሰጣቸው፦
21፥48 ለሙሣ እና ለሃሩን ፉርቃን፣ ብርሃንን እና ለጥንቁቆች መገሰጫን በእርግጥ ሰጠናቸው፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَىٰ وَهَارُونَ الْفُرْقَانَ وَضِيَاءً وَذِكْرًا لِّلْمُتَّقِينَ

"ፉርቃን" فُرْقَان ማለት "እውነትን ከሐሠት መለያ ሚዛን" ማለት ነው። ሃሩን ለሙሣ የወረደለትን ሪሣላህ ከሙሣ ጋር ሆኖ እንዲናገር አሏህ በተአምራቱ እና በግልጽ አስረጅ ላካቸው፦
23፥45 ከዚያም ሙሣን እና ወንድሙን ሃሩንን በተአምራታችን እና በግልጽ አስረጅ ላክን፡፡ ثُمَّ أَرْسَلْنَا مُوسَىٰ وَأَخَاهُ هَارُونَ بِآيَاتِنَا وَسُلْطَانٍ مُّبِينٍ

ሃሩን ለሙሣ የወረደለት ሪሣላህ በመጋራት ወደ ፈርዖን ሄደው፦ "እኛ የዓለማት ጌታ መልክተኞች ነን" እንዲሉ አሏህ አዘዛቸው፦
26፥16 ወደ ፈርዖንም ሂዱ! በሉትም፦ "እኛ የዓለማት ጌታ መልክተኞች ነን"፡፡ فَأْتِيَا فِرْعَوْنَ فَقُولَا إِنَّا رَسُولُ رَبِّ الْعَالَمِينَ

አሏህ አንድን ሰው ወሕይ በማውረድ ሲያናግረው ያ ሰው ነቢይ ይባላል፥ በዚህ ረገድ አሏህ ሃሩንን ስላናገረው ሃሩን ነቢይ ነው። ነገር ግን ለራሱ እራሱን የቻለ ሪሣላህ ስላልወረደለት ረሡል አይደለም፥ ታዲያ ለምን ረሡል ተባለ? ሲባል የሙሣን ሪሣላህ እና መልእክተኝነት ተጋርቶ ወደ ፈርዖን እና ወደ ሕዝቡ ከሙሣ ጋር ስለተላከ ነው።

“አሏሁ አዕለም” اَللّٰهُ أَعْلَم‎

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የለበጣ ንግግር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥157 «የአሏህን መልእክተኛ የመርየምን ልጅ አል-መሢሕ ዒሣን ገደልን» በማለታቸውም ረገምናቸው፡፡ وَقَوْلِهِمْ إِنَّا قَتَلْنَا الْمَسِيحَ عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ رَسُولَ اللَّهِ

አይሁዳውያን፦ "ዒሣ የአሏህ መልእክተኛ እና መሢሑ ነው" ብለው አያምኑም፥ ቅሉ ግን በሽሙጥ እና በለበጣ ንግግር፦ "የአሏህን መልእክተኛ የመርየምን ልጅ አል-መሢሕ ዒሣን" በማለት ዒሣን "ገደልን" ብለዋል፦
4፥157 «የአሏህን መልእክተኛ የመርየምን ልጅ አል-መሢሕ ዒሣን ገደልን» በማለታቸውም ረገምናቸው፡፡ وَقَوْلِهِمْ إِنَّا قَتَلْنَا الْمَسِيحَ عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ رَسُولَ اللَّهِ

"የአሏህ መልእክተኛ እና አል-መሢሕ" የሚለው ቃል የለበጣ እና የሽሙጥ ንግግር ነው። ለምሳሌ ቁሬይሾች፦ "ለነቢያችን"ﷺ" ቁርኣን ከአሏህ ዘንድ ወርዶላቸዋል" ብለው አያምኑም ግን በሽሙጥ እና በለበጣ ንግግር፦ "አንተ ያ በእርሱ ላይ ቁርኣን የተወረደለት ሆይ" በማለት ነቢያችንን"ﷺ" "አንተ በእርግጥ ዕብድ ነህ" ብለዋል፦
15፥6 «አንተ ያ በእርሱ ላይ ቁርኣን የተወረደለት ሆይ! አንተ በእርግጥ ዕብድ ነህ» አሉም፡፡ وَقَالُوا يَا أَيُّهَا الَّذِي نُزِّلَ عَلَيْهِ الذِّكْرُ إِنَّكَ لَمَجْنُونٌ

በተመሳሳይ ባይብል ላይ አይሁዳውያን በሽሙጥ እና በለበጣ ንግግር ኢየሱስን፦ "የእስራኤል ንጉሥ ክርስቶስ" ብለዋል፦
ማርቆስ 15፥32፤ አይተን እናምን ዘንድ "የእስራኤል ንጉሥ ክርስቶስ" አሁን ከመስቀል ይውረድ" አሉ።

"ኽሪስቶስ" Χριστός በግሪክ ሲሆን በዕብራይስጥ "መሺአኽ" מָשִׁיחַ ነው። አይሁዳውን ኢየሱስ "የእስራኤል ንጉሥ እና ክርስቶስ(መሢሕ) ነው" ብለው አያምኑም፥ ይህ የለበጣ እና የሽሙጥ ንግግር ነው። ጭራሽ በሽሙጥ እና በለበጣ ንግግር፦ "ይህ ኢየሱስ የአይሁድ ንጉሥ ነው" የሚል የክሱን ጽሕፈት ከራሱ በላይ አኖሩ፦
ማቴዎስ 27፥37 "ይህ ኢየሱስ የአይሁድ ንጉሥ ነው" የሚል የክሱን ጽሕፈት ከራሱ በላይ አኖሩ።

ስለዚህ እንቶንይ ሮጀርስ እና ቡችሎቹ ቁርኣን፦ "አይሁዳውያን "ኢየሱስ መልእክተኛ እና መሢሕ ነው" ብለው እንደሚያምኑ አድርጎ አስቀምጧል" ለሚለው የሐሠት ክስ"false allegation" በሰፈው ቁና መሰፈሩ የእንቧይ ካብ ያደርገዋል፥ ከላይ ያለው የባይብል ተመሳሳይ ነጥብ አፍጦና አፋጦ፤ አግጦና አንጋጦ የሚታይ እውነት ነው። መቼም አይሁዳውያን ኢየሱስ "የእስራኤል ንጉሥ እና ክርስቶስ(መሢሕ) ነው" ብለው በለበጣ እና በሽሙጥ መናገራቸው ስትሰሙ ቆሌ ተገፎ እና ቆሽት አሮ፦ "ሰማይ ተንዶ ሊናጫነኝ ነው፥ ምድር ተከፍቶ ሊውጠኝ ነው" እንደምትሉ እሙን ነው። የክርስትና ደርዛዊ ሥነ-መለኮትን በዘመናዊነት ማዘመን መላላጫ እና መጋጋጫ በሌለው እፉቅቅ እና እንብርክክ እየተጎተቱ መሔድ ነው። አላህ ሂዳያ ይስጣችሁ፥ ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ወላዲተ ሰብእ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

19፥34 ይህ የመርየም ልጅ ዒሣ ነው፡፡ ያ ስለ እርሱ የሚከራከሩበት እውነተኛ ቃል ነው፡፡ ذَٰلِكَ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ ۚ قَوْلَ الْحَقِّ الَّذِي فِيهِ يَمْتَرُونَ

"አንትሮፖቶኮስ" ἄνθρωποτόκος ማለት "ወላዲተ ሰብእ" ማለት ነው፥ በግዕዝ "ሰብእ" ማለት "ሰው" ማለት ሲሆን "ወላዲተ ሰብእ" ማለት "የሰው ወላጅ" ማለት ነው። ማርያም "ወላዲተ ሰብእ" ወይም "እመ ሰብእ" ናት፥ ማርያም ፀንሳ የወለደችው ሰው ነው። ይህም ሰው ኢየሱስ ሲሆን ከእርሷ ሰው የሆነ ነው፦
ገላትያ 4፥4 ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር "ከ-ሴት የተወለደውን" ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ። ὅτε δὲ ἦλθεν τὸ πλήρωμα τοῦ χρόνου, ἐξαπέστειλεν ὁ Θεὸς τὸν Υἱὸν αὐτοῦ, γενόμενον ἐκ γυναικός, γενόμενον ὑπὸ νόμον,

"የተወለደው" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ጌኖሜኖን" γενόμενον ሲሆን "ጊኖማይ" γίνομαι ማለትም "ሆነ" ወይም "ተወለደ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "የሆነውን" ማለት ነው፥ ኢየሱስ ከማርያም ሰው መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። "ከ" የሚለው መስተዋድድ መነሻ ቅጥያ ሆኖ የገባበት "ሴት" ሌላ ጥቅስ ላይ "ዘር" ተብላለች፦
ሮሜ 1፥3 ይህም ወንጌል በሥጋ "ከ-ዳዊት ዘር ስለ ተወለደ" ..ስለ.. ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። περὶ τοῦ Υἱοῦ αὐτοῦ τοῦ γενομένου ἐκ σπέρματος Δαυεὶδ κατὰ σάρκα,

"ጌኖሜኖዩ" γενομένου ማለት "ስለ ተወለደ" "ስለ ሆነ" ማለት ነው። ፈጣሪ የሚያስሆን አድራጊ ሲሆን "ማስሆን" እና "ማድረግ" ደግሞ ገቢር ግሥ"active verb" ነው፥ ኢየሱስ የሚሆን ተደራጊ ሲሆን "መሆን" እና "መደረግ" ደግሞ ተገብሮ ግሥ"passive verb" ነው። ፈጣሪ ነገርን ሁሉ የሚያስሆን አድራጊ ከሆነ ፍጡር ሁሉ የሚሆን ተደራጊ ነው፥ ኢየሱስ ሰው "መሆኑ" በራሱ ፍጡሩነቱን ያሳያል።
"ሴት" በሚለው "የዳዊት ዘር" በሚል ተለዋዋጭ መምጣቱ በራሱ ማርያም የዳዊት ዘር መሆኗን እና ልጇ ከእርሷ ሰው መሆኑን እና መወለዱን ፍንትው አድርጎ ያሳያል። "ከ-ሴት የተወለደ" "ከ-ዳዊት ዘር የተወለደ" ተለዋዋጭ ቃል ናቸው፥ ኢየሱስ ከዳዊት ዘር የሆነ እና ከዳዊት ዘር የመጣ ሰው ነው፦
2 ጢሞቴዎስ 2፥8 ከዳዊት ዘርም "የሆነውን" ኢየሱስ ክርስቶስን አስብ!።
ዮሐንስ 7፥42 ክርስቶስ ከዳዊት ዘር ዳዊትም ከነበረባት መንደር ከቤተ ልሔም እንዲመጣ መጽሐፍ አላለምን? አሉ።
ሐዋ. ሥራ 13፥23 "ከ-ዚህም ሰው ዘር" እግዚአብሔር እንደ ተስፋው ቃል ለእስራኤል መድኃኒትን እርሱም ኢየሱስን "አመጣ"።

"ሰው" የተባለው ዳዊት ሲሆን ከዳዊት ዘር እግዚአብሔር ኢየሱስን ካለመኖር ወደ መኖር አመጣ፥ አምጪ አንድ እግዚአብሔር ሲሆን መጪ ኢየሱስ ነው። መጽሐፍ ክርስቶስ ከዳዊት ዘር እንዲመጣ ተናግሯል፥ ክርስቶስ ከማርያም የተጸነሰ የማኅፀኗ ፍሬ ነው፦
ማቴዎስ 1፥20 "ከ-"እርሷ የተፀነሰው" ከመንፈስ ቅዱስ ነውና።
ሉቃስ 1፥42 "የ-ማኅፀንሽም ፍሬ" የተባረከ ነው።

"ከ" የሚለው መስተዋድድ "እርሷ" በሚለው ላይ መነሻ ቅጥያ ሆኖ መምጣቱ ፅንሱ ከእርሷ መሆኑን ያስረዳል፥ "የ" የሚለው አገናዛቢ ዘርፍ "ማኅፀንሽ" በሚለው ቃል ላይ መነሻ ቅጥያ ሆኖ መምጣቱ ኢየሱስ ከእርሷ የተገኘው ፍሬ መሆኑን አመላካች ነው። ከቤተ ልሔም የወጣው እና የመጣው ይህ ፍሬ አወጣጡ ከአዳም ጀምሮ ነው፦
ሚክያስ 5፥2 ከአንቺ ግን አወጣጡ "ከቀድሞ ጀምሮ" ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።