ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.9K subscribers
68 photos
70 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ኮሮና ወረርሽኝ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

26፥80 *”በታመምኩም ጊዜ እርሱ ያሽረኛል”*፡፡ وَإِذَا مَرِضْتُ فَهُوَ يَشْفِينِ

"ጧዑን" طَّاعُون ማለት "መቅሰፍት" "ወረርሽ" "በሽታ" ማለት ነው። ነቢያችን"ﷺ" በመጨረሻ ዘመን የሚመጣ መቅሰፍት እንዳለ ተናግረዋል። ይህ መቅሰፍት መዲና አይገባም፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 92, ሐዲስ 81
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦*"በመዲና ተራሮች ላይ ጠባቂ መላኢካዎች አሉ። መቅሰፍትም ሆነ አድ-ደጃል ወደ ወደዚያ መግባት አይችሉም"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ عَلَى أَنْقَابِ الْمَدِينَةِ مَلاَئِكَةٌ، لاَ يَدْخُلُهَا الطَّاعُونُ وَلاَ الدَّجَّالُ

እዚህ ሐዲስ ላይ የተጠቀመው "ጧዑን" طَّاعُون በተለየ መልኩ "ሙፈሰል" مُفَصَّل ሲሆን "መውታን" مَوْتَان "ሙታን" مُوتَان ማለትም "መቅሰፍት" ማለት ነው። ይህ በመጨረሻ ዘመን የሚመጣው መቅሰፍት መዲና አይገባም።
ነገር ግን "ጧዑን" طَّاعُون በጥቅል መልኩ “ሙጅመል” مُجّمَل ሆኖ በየጊዜው የሚመጣውን ማንኛውንም ወረርሽ ለማመልከት አገልግሎት ላይ ውሏል። ሙጅመል ከሆኑት ጧዑን ማንኛውም ከአላህ ዘንድ ለበደላችን ቅጣት ሲሆን ለንጹሓን የአላህ ባሮች ደግሞ ምሕረት እና ሰማዕትነት ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 56, ሐዲስ 46
አነሥ ኢብኑ ማሊክ"ረ.ዐ" እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *“ወረርሽኝ ለሁሉም ሙሥሊም ሰማዕትነት ነው”"* عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ ـ رضى الله عنه ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ الطَّاعُونُ شَهَادَةٌ لِكُلِّ مُسْلِمٍ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 76, ሐዲስ 49
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *"የአላህን መልእክተኛ"ﷺ" ስለ ወረርሽኝ ጠየኳቸው። እርሳቸውም፦ *"አላህ ለሚሻው ሰው ይልክበታል፥ ለአማኞች ግን ምሕረት ነው። በአንድ አካባቢ ወረርሽኝ መከሰቱን ከሰማችሁ ወደ ከተማዋ አትግቡ! በከተማዋ ውስጥ ከሆናችሁ ደግሞ አላህ ምሕረቱን እስኪያመጣ እና የሰማዕትነት አጅር እኪሰጣችሁ ከከተማዋ አትውጡ!" አሉ"*። عَنْ عَائِشَةَ، زَوْجِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم أَنَّهَا أَخْبَرَتْنَا أَنَّهَا سَأَلَتْ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم عَنِ الطَّاعُونِ فَأَخْبَرَهَا نَبِيُّ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ أَنَّهُ كَانَ عَذَابًا يَبْعَثُهُ اللَّهُ عَلَى مَنْ يَشَاءُ، فَجَعَلَهُ اللَّهُ رَحْمَةً لِلْمُؤْمِنِينَ، فَلَيْسَ مِنْ عَبْدٍ يَقَعُ الطَّاعُونُ فَيَمْكُثُ فِي بَلَدِهِ صَابِرًا، يَعْلَمُ أَنَّهُ لَنْ يُصِيبَهُ إِلاَّ مَا كَتَبَ اللَّهُ لَهُ، إِلاَّ كَانَ لَهُ مِثْلُ أَجْرِ الشَّهِيدِ ‏

በጥቅል ከተገለጹት ወረርሽኝ አንዱ ኮሮና ወረርሽኝ"Corona virus" ያለ አንዳች ከላይ በፍጥነት እየተዛመተ ያለ ቫይረስ ነው። ይህ ፈተና ነው፥ ይህ ፈተና የበደለውንም ያልበደለውን ሳይለኝ የሚያጠቃ ፈተና ነው። የዚህ በሽታ ምሕረቱ ከአላህ ዘንድ ነው፥ ህመምን የሚያሽር አላህ ነው፦
8፥25 *ከእናንተም ውስጥ እነዚያን የበደሉትን ብቻ ለይታ የማትነካን ፈተና ተጠንቀቁ፡፡ አላህም ቅጣቱ ብርቱ መኾኑን እወቁ*፡፡ وَاتَّقُوا فِتْنَةً لَّا تُصِيبَنَّ الَّذِينَ ظَلَمُوا مِنكُمْ خَاصَّةً ۖ وَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ
26፥80 *”በታመምኩም ጊዜ እርሱ ያሽረኛል”*፡፡ وَإِذَا مَرِضْتُ فَهُوَ يَشْفِينِ

አላህ ምሕረቱ ያምጣልን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሸሃዳህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

57፥19 *እነዚያም በአላህ እና በመልክተኞቹ ያመኑት እነዚያ እነርሱ በጣም እውነተኞቹ በጌታቸውም ዘንድ መስካሪዎቹ ናቸው*፡፡ ለእነርሱ ምንዳቸው ብርሃናቸውም አልላቸው፡፡ እነዚያም የካዱት በአንቀጾቻችንም ያስተባበሉት እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው፡፡ وَالَّذِينَ آمَنُوا بِاللَّهِ وَرُسُلِهِ أُولَـٰئِكَ هُمُ الصِّدِّيقُونَ ۖ وَالشُّهَدَاءُ عِندَ رَبِّهِمْ لَهُمْ أَجْرُهُمْ وَنُورُهُمْ ۖ وَالَّذِينَ كَفَرُوا وَكَذَّبُوا بِآيَاتِنَا أُولَـٰئِكَ أَصْحَابُ الْجَحِيمِ

"ሸሃዳህ” شَهَادَة‎ የሚለው ቃል “ሸሂደ” شَهِدَ ማለትም “መሰከረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ምስክርነት” ማለት ነው፥ ሻሂድ شَاهِد አሊያም “ሸሂድ” شَهِيد ደግሞ “ምስክር” ማለት ሲሆን የሻሂድ ብዙ ቁጥር “ሹሀዳእ” شُهَدَاء ነው። አንድ ሰው ወደ ዲኑል ኢሥላም የሚገባበት “ቃለ-ምስክርነት” ሸሃዳህ ይባላል። ይህም ቃለ-ምስክርነት “ላ ኢላሀ ኢለሏህ ሙሐመዱን ረሱሉሏህ” لَا إِلَٰهَ إِلَّا ٱللَّٰهُ مُحَمَّدٌ رَسُولُ ٱللَّٰه ማለትም “ከአላህ በስተቀር አምላክ የለም፥ ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ ነው” የሚል ነው። በእያንዳንዱ ዘመን የተለያዩ መልእክተኛ ስላሉ በዛ ዘመን ባለው መልእክተኛ ለምሳሌ በዒሣ ከሆነ “ዒሣ ረሱሉሏህ” ብለው ይቀበሉ ነበር። ለምሳሌ አላህ በዒሣ ዘመን “በእኔ እና በመልክተኛዬ እመኑ” በማለት ወሕይ አውርዷል፦
5፥111 ወደ ሐዋርያትም *«በእኔ እና በመልክተኛዬ እመኑ»* በማለት ባዘዝኩ ጊዜ አስታውስ፡፡ «አመንን፤ እኛ ሙሥሊሞች መኾናችንን መስክር» አሉ፡፡ وَإِذْ أَوْحَيْتُ إِلَى الْحَوَارِيِّينَ أَنْ آمِنُوا بِي وَبِرَسُولِي قَالُوا آمَنَّا وَاشْهَدْ بِأَنَّنَا مُسْلِمُونَ

በአላህ እና በመልክተኞቹ ማመን ወደ ዱኑል ኢሥላም የሚያስገባ ቁልፍ ነው። እነዚያ ያመኑት መስካሪዎች ናቸው፦
57፥19 *እነዚያም በአላህ እና በመልክተኞቹ ያመኑት እነዚያ እነርሱ በጣም እውነተኞቹ በጌታቸውም ዘንድ መስካሪዎቹ ናቸው*፡፡ ለእነርሱ ምንዳቸው ብርሃናቸውም አልላቸው፡፡ እነዚያም የካዱት በአንቀጾቻችንም ያስተባበሉት እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው፡፡ وَالَّذِينَ آمَنُوا بِاللَّهِ وَرُسُلِهِ أُولَـٰئِكَ هُمُ الصِّدِّيقُونَ ۖ وَالشُّهَدَاءُ عِندَ رَبِّهِمْ لَهُمْ أَجْرُهُمْ وَنُورُهُمْ ۖ وَالَّذِينَ كَفَرُوا وَكَذَّبُوا بِآيَاتِنَا أُولَـٰئِكَ أَصْحَابُ الْجَحِيمِ

አላህ እራሱ፣ መላእክቶች እና የዕውቀት ባለቤቶችም "ላ ኢላሀ ኢለሏህ" ብለው መስክረዋል፦
3፥18 *አላህ በማስተካከል አስተናባሪ ሲኾን ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የሌለ መኾኑን መሰከረ፡፡ መላእክቶችና የዕውቀት ባለቤቶችም እንደዚሁ መሰከሩ፡፡ ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ አሸናፊው ጥበበኛው ነው*፡፡ شَهِدَ اللَّهُ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ وَالْمَلَائِكَةُ وَأُولُو الْعِلْمِ قَائِمًا بِالْقِسْطِ ۚ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ

ነቢያችን"ﷺ" ረሱል መሆናቸውን አላህ "መስክሩ" ብሏል፦
3፥81 *«እንግዲያስ መስክሩ፤ እኔም ከእናንተ ጋር ከመስካሪዎቹ ነኝ» አላቸው*፡፡ قَالَ فَاشْهَدُوا وَأَنَا مَعَكُم مِّنَ الشَّاهِدِينَ

“ላ ኢላሀ ኢለሏህ ሙሐመዱን ረሱሉሏህ” لَا إِلَٰهَ إِلَّا ٱللَّٰهُ مُحَمَّدٌ رَسُولُ ٱللَّٰه የሚለው ቁርኣን ውስጥ አለ፥ "ላ ኢላሀ ኢለሏህ" لَا إِلَٰهَ إِلَّا ٱللَّٰه እዚህ አንቀጽ ላይ አለ፦
47፥19 እነሆ *ከአላህ ሌላ አምላክ አለመኖሩንም* ዕወቅ!፡፡ فَاعْلَمْ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّهُ

"ሙሐመዱን ረሱሉሏህ" مُحَمَّدٌ رَسُولُ ٱللَّٰه የሚለው ደግሞ እዚህ አንቀጽ ላይ አለ፦
48፥29 የአላህ መልክተኛ ሙሐመድ እነዚያም ከእርሱ ጋር ያሉት ወዳጆቹ በከሓዲዎቹ ላይ ብርቱዎች በመካከላቸው አዛኞች ናቸው፡፡ አጎንባሾች፣ ሰጋጆች ኾነው ታያቸዋለህ፡፡ ከአላህ ችሮታንና ውዴታን ይፈልጋሉ፡፡ ምልክታቸው ከስግደታቸው ፈለግ ስትኾን በፊቶቻቸው ላይ ናት፡፡ مُّحَمَّدٌ رَّسُولُ اللَّهِ ۚ وَالَّذِينَ مَعَهُ أَشِدَّاءُ عَلَى الْكُفَّارِ رُحَمَاءُ بَيْنَهُمْ ۖ تَرَاهُمْ رُكَّعًا سُجَّدًا يَبْتَغُونَ فَضْلًا مِّنَ اللَّهِ وَرِضْوَانًا ۖ سِيمَاهُمْ فِي وُجُوهِهِم مِّنْ أَثَرِ السُّجُودِ

አንድ ላይ በአንድ አንቀጽ ላይ፦ "ላ ኢላሀ ኢሏ ሁወ፥ አኒ ረሱሉሏህ" لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ إِنِّي رَسُولُ اللَّهِ በል ተብሎ ተቀምጧል፦
7፥158 በላቸው፡- «እናንተ ሰዎች ሆይ! እኔ ወደ እናንተ ወደ ሁላችሁም *የአላህ መልክተኛ ነኝ፡፡ እርሱም ያ የሰማያትና የምድር ንግሥና ለእርሱ ብቻ የኾነ ነው፡፡ እርሱ እንጂ ሌላ አምላክ የለም*፡፡ ሕያው ያደርጋል፥ ያሞታል። قُلْ يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنِّي رَسُولُ اللَّهِ إِلَيْكُمْ جَمِيعًا الَّذِي لَهُ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ يُحْيِي وَيُمِيتُ

ነቢያችን"ﷺ" በሐዲሳቸው፦ “ኣላ ኢላሀ ኢለሏህ ሙሐመዱን ረሱሉሏህ” لَا إِلَٰهَ إِلَّا ٱللَّٰهُ مُحَمَّدٌ رَسُولُ ٱللَّٰه ከኢሥላም መሠረት አንዱ እንደሆነ ነግረውናል፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 40, ሐዲስ 4
ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ኢሥላም በአምስቱ መሠረቶች ላይ ተገንብቷል፤ እነርሱም፦ “ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፥ ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ ነው” በሚል ምስክርነት፣ ሶላትን በመቆም፣ ዘካህን በመስጠት፣ ረመዷንን በመፆም እና የአላህ በይት በመጎብኘት”*። عَنِ ابْنِ عُمَرَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ بُنِيَ الإِسْلاَمُ عَلَى خَمْسٍ شَهَادَةُ أَنْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللَّهِ وَإِقَامُ الصَّلاَةِ وَإِيتَاءُ الزَّكَاةِ وَصَوْمُ رَمَضَانَ وَحَجُّ الْبَيْتِ

መመስከር ማለት ዐውቄአለው፣ ዐምኛለው፣ እናገራለው፣ እተገብራለው ማለት ነው። አምላካችን አላህ ሹሀዳእ ከሚላቸው ባሮቹ ያርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
እሳት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

104፥6 *የተነደደችው የአላህ እሳት ናት*፡፡ نَارُ اللَّهِ الْمُوقَدَةُ

"አን-ናር" النَّار ማለት "እሳት" ማለት ሲሆን "ሙቀት"heat" እና "ነበልባል"flame" ነው፥ እሳት የተፈጠረው ከሰው በፊት በስድስት ቀናት ውስጥ ነው፦
50፥38 *"ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ በእርግጥ ፈጠርን"*፡፡ ድካምም ምንም አልነካንም፡፡ وَلَقَدْ خَلَقْنَا السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ وَمَا مَسَّنَا مِن لُّغُوبٍ

አደም የተፈጠረው በጁሙዓህ ቀን ሲሆን ጂኒዎች የተፈጠሩት ከአደም በፊት ከእሳት ነበልባል ነው፦
15፥27 ጃንንም ከሰው በፊት *ከእሳት ነበልባል ፈጠርነው*፡፡ وَالْجَانَّ خَلَقْنَاهُ مِن قَبْلُ مِن نَّارِ السَّمُومِ
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 7, ሐዲስ 26
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"መልካም ቀን ፀሐይ ከወጣችበት የጁሙዓህ ቀን ነው፥ በዚያ ቀን አደም ተፈጠረ። በዚያ ቀን ወደ ጀነት ገብቷል፥ ከጀነት በዚያ ቀን ወጥቷል"*። أَنَّهُ سَمِعَ أَبَا هُرَيْرَةَ، يَقُولُ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ خَيْرُ يَوْمٍ طَلَعَتْ عَلَيْهِ الشَّمْسُ يَوْمُ الْجُمُعَةِ فِيهِ خُلِقَ آدَمُ وَفِيهِ أُدْخِلَ الْجَنَّةَ وَفِيهِ أُخْرِجَ مِنْهَا

ስለዚህ ጂኒዎች የተፈጠሩበት እሳት የተፈጠረው ከሰው በፊት በስድስት ቀናት ውስጥ ነው፥ ግን በመጀመርያ ቀን ይሁን፣ በሁለተኛው ቀን ይሁን፣ በሦስተኛው ቀን ይሁን ወዘተ.. ዐናውቅም። "ነበልባል" ለሚለው የገባው ቃል "ሠሙም" سَمُوم ሲሆን በጀሀነም ላለው ፍጥረት ቅጣት "መርዝ" ነው፦
52፥27 «አላህም በእኛ ላይ ለገሰ፡፡ *የመርዛም እሳት* ቅጣትንም ጠበቀን፡፡ فَمَنَّ اللَّهُ عَلَيْنَا وَوَقَانَا عَذَابَ السَّمُومِ

"ሠሙም" سَمُوم የሚለው ቃል "ሠመ" سَمَّ ማለትም "መረዘ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን የእሳት "ነበልባል" ለሰው ሰውነት ስሚያቃጥል መርዝ ነው፥ "ሡም" سُمّ ማለት እራሱ ቅጽል ሲሆን "መርዛም" ማለት ነው። "ጀሀነም" جَهَنَّم‎ የሚለው ቃል ትርጉም ሁለት እይታ አለ፥ አንዱ እይታ "ጀሀነም" የሚለው ቃል "ሙሽተቅ” مُشتَق ማለትም "ከዐረቢኛ ቃል የሚረባ ቃል" ሲሆን "ጀሒም" ከሚለው የስም መደብ የመጣ ነው። "ጀሒም" جَحِيم የሚለው ቃል "ጀሑመ" جَحُمَ ማለትም "አቃጠለ" ነደደ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ማቀጣጠያ" "ማንደጃ" ማለት ነው፦
81፥12 *"ገሀነምም በተነደደች ጊዜ"*። وَإِذَا الْجَحِيمُ سُعِّرَتْ

"እዚህ አንቀጽ ላይ "ገሀነም" ለሚለው ቃል የገባው "ጀሒም" جَحِيم መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። "ነዒም" نَعِيم ማለት "ጸጋ" ማለት ሲሆን የጀሒም" ተቃራኒ ነው። ሁለተኛው እይታ "ጀሀነም" የሚለው ቃል “ጃሚድ” جامِد ማለትም "ከዐረቢኛ ቃል የማይረባ ቃል" ሲሆን "ጌሄኑም" ከሚል ሴማዊ ዳራ የመጣ ሙዐረብ ነው፥ “ሙዐረብ” مُعَرَّب ማለትም “ዐረቢኛ ውስጥ ገብቶ ዐረቢኛ የሆነ" ማለት ነው። እዚህ ዓለም ላይ ያለው እሳት እራሱ ከሰባው የጀሀነም እሳት አንዱ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 59, ሐዲስ 75
አቢ ሁረይራህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"የእናንተ እሳት ከሰባው የጀሀነም እሳት ክፍል ነው። አንዱም፦ "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ይህ ለቅጣት በቂ ነውን? አለ፥ እርሳቸውም፦ "እሳቱ ከተለመደው እሳት የበለጠ ስድሳ ዘጠኝ ክፍሎች አሉት፥ እያንዳንዱ የእሳት ክፍል ልክ እንደዚህ ጠንካራ ነው" አሉት*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ نَارُكُمْ جُزْءٌ مِنْ سَبْعِينَ جُزْءًا مِنْ نَارِ جَهَنَّمَ ‏"‌‏.‏ قِيلَ يَا رَسُولَ اللَّهِ، إِنْ كَانَتْ لَكَافِيَةً‏.‏ قَالَ ‏"‏ فُضِّلَتْ عَلَيْهِنَّ بِتِسْعَةٍ وَسِتِّينَ جُزْءًا، كُلُّهُنَّ مِثْلُ حَرِّهَا ‏

ከሰባው አንዱ የእሳት ክፍል ምድራችን ውስጥ ይገኛል። የምድርን 20% የያዘው የመሬት አስኳል"core" እራሱ 8653 መጠን(tonne) ድኝ"sulphur" ነው። ውስጣዊ አስኳሉ"inner core" እራሱ ጠጣር እሳት ነው፥ ይዞታው በራዲየስ እስከ 1220 ኪሎ ሜትር ሲሆን የሙቀቱ መጠን ደግሞ 5,400 ድግሪ ሴሊሽየስ °C ወይም 9,800 ዲግሪ ፋረንሃይት °F ነው። ውጫዊ አስኳሉ"outer core" እራሱ ፈሳሽ እሳት ነው፥ ይዞታው በራዲየስ እስከ 2,890 ኪሎ ሜትር ሲሆን የሙቀቱ መጠን ደግሞ 4,400 ድግሪ ሴሊሽየስ °C ወይም 7,952 ዲግሪ ፋረንሃይት °F ነው። ይህ የምድራችን የእሳት ሙቀት በክረምት እና በበጋ ይመጣል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 5, ሐዲስ 237
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"እሳት ወደ ጌታዋ በቅሬታ፦ "ጌታ ሆይ! የእኔ አንዱ ክፍል ሌላውን ክፍል በላ" አለች። ለእርሷም ሁለት መተንፈሻዎች ተደረገላት፥ አንደኛው መተንፈሻ በክረምት ሲሆን ሌላይኛው መተንፈሻ ደግሞ በበጋ ነው። ለዛ ነው ጽንፍ ሙቀት እና ቅዝቃዜ የምታገኙት"*። أَنَّهُ سَمِعَ أَبَا هُرَيْرَةَ، يَقُولُ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ اشْتَكَتِ النَّارُ إِلَى رَبِّهَا فَقَالَتْ يَا رَبِّ أَكَلَ بَعْضِي بَعْضًا ‏.‏ فَأَذِنَ لَهَا بِنَفَسَيْنِ نَفَسٍ فِي الشِّتَاءِ وَنَفَسٍ فِي الصَّيْفِ فَهُوَ أَشَدُّ مَا تَجِدُونَ مِنَ الْحَرِّ وَأَشَدُّ مَا تَجِدُونَ مِنَ الزَّمْهَرِيرِ
ሰሜናዊ ንፍቀ-ክበብ"Northern Hemisphere" ከታህሳስ እስከ መጋቢት ክረምት ሲሆን ከሰኔ እስከ መስከረም በጋ ነው። በተቃራኒው ደቡባዊ ንፍቀ-ክበብ"Southern Hemisphere" ከታህሳስ እስከ መጋቢት በጋ ሲሆን ከሰኔ እስከ መስከረም ክረምት ነው።
የሙቀት መጠን በሰሜናዊ ንፍቀ-ክበብ ከሰኔ እስከ መስከረም ባለው የበጋ ጊዜ ሲመጣ በደቡባዊ ንፍቀ-ክበብ ከሰኔ እስከ መስከረም ያለውን የክረምት ጊዜ ያመጣል፥ በተቃራኒው በደቡባዊ ንፍቀ-ክበብ ከታህሳስ እስከ መጋቢት ባለው የበጋ ጊዜ ሲመጣ በሰሜናዊ ንፍቀ-ክበብ ከታህሳስ እስከ መጋቢት ያለውን የክረምት ጊዜ ያመጣል።
ስለዚህ በሰሜናዊ ንፍቀ-ክበብ በበጋ ጊዜ የሚመጣው ሙቀት በደቡባዊ ንፍቀ-ክበብ ባለው የክረምት ጊዜ ነው፥ በደቡባዊ ንፍቀ-ክበብ በበጋ ጊዜ የሚመጣው ሙቀት በሰሜናዊ ንፍቀ-ክበብ ባለው የክረምት ጊዜ ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 39, ሐዲስ 2796
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"እሳት ወደ ጌታዋ በቅሬታ፦ "ጌታ ሆይ! የእኔ አንዱ ክፍል ሌላውን ክፍል በላ" አለች። ለእርሷም ሁለት መተንፈሻዎች ተደረገላት፥ አንደኛው መተንፈሻ በክረምት ሲሆን ሌላይኛው መተንፈሻ ደግሞ በበጋ ነው። በክረምት ማስተንፈሻዋ ዘምሀሪር ሲባል፥ በበጋ ማስተንፈሻዋ ደግሞ ሠሙም ይባላል"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ اشْتَكَتِ النَّارُ إِلَى رَبِّهَا وَقَالَتْ أَكَلَ بَعْضِي بَعْضًا فَجَعَلَ لَهَا نَفَسَيْنِ نَفَسًا فِي الشِّتَاءِ وَنَفَسًا فِي الصَّيْفِ فَأَمَّا نَفَسُهَا فِي الشِّتَاءِ فَزَمْهَرِيرٌ وَأَمَّا نَفَسُهَا فِي الصَّيْفِ فَسَمُومٌ ‏

ሰው እራሱ ከምድር አፈር ስለተሠራ በውስጡ ሙቀት አለው። "ሰው" የሚለው ቃል በግዕዝ “ሰብእ” ማለት ሲሆን "ሰባት" ማለት ነው። ሦስቱ ባሕርያተ-ነፍስ ማለትም የነፍስ ባሕርያት ልብ፣ ነቢብ እና ሕያው ነው፥ አራቱ ባሕርያተ-ስጋ ማለትም የስጋ ጥንታዊ ንጥረ-ነገር"classical element" ውኃ፣ እሳት፣ አፈር እና ነፋስ ነው። ውኃ እርጥበት፣ እሳት ሙቀት፣ አፈር ደረቅነት፤ ነፋስ ቅዝቃዜ አላቸው። ሰው ሙቀት ያለው በውስጡ የእሳት ባሕርይ ስላለው ነው፥ የሰውነት ሙቀት ከ 37.5 ድግሪ ሴሊሽየስ °C ወይም 99.5 ዲግሪ ፋረንሃይት °F በላይ ሲሆን ትኩሳት"fever" ይባላል። "አል-ሑማ" الْحُمَّى ማለት "ትኩሳት" ማለት ነው፥ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ"፦ "ትኩሳት ከእሳት ነው፥ በውኃ አብርዱት" ብለውናል፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 28, ሐዲስ 2216
ራፊዕ ኢብኑ ኻሊድ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ትኩሳት ከእሳት ነው፥ በውኃ አብርዱት"*። رَافِعِ بْنِ خَدِيجٍ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ الْحُمَّى فَوْرٌ مِنَ النَّارِ فَأَبْرِدُوهَا بِالْمَاءِ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 59, ሐዲስ 73
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችውም፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ትኩሳት ከእሳት ሙቀት ነው፥ በውኃ አብርዱት"*። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ الْحُمَّى مِنْ فَيْحِ جَهَنَّمَ، فَأَبْرِدُوهَا بِالْمَاءِ ‏

እሳት በነበልባል ደረጃ ሳይደርስ በሙቀት ደረጃ ያለው እራሱ የእሳት ክፍል ነው። እንግዲህ እዚህ ዓለም ላይ ያለው እሳት እራሱ ከሰባው የጀሀነም እሳት አንዱ ሲሆን የተቀሩት ስድሳ ዘጠኝ የእሳት ክፍሎት ለከሓዲዎችም መቀጣጫ የእሳት ቅጣት ናቸው፥ ይህቺ የተነደደችው የአላህ እሳት ናት። እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እራሳችሁን እና ቤተሰቦቻችሁን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጋዮች ከኾነች እሳት ጠብቁ፦
8፥14 *ይህ ቅጣታችሁ ነው ቅመሱትም፡፡ ለከሓዲዎችም "የእሳት ቅጣት" በእርግጥ አለባቸው*፡፡ ذَٰلِكُمْ فَذُوقُوهُ وَأَنَّ لِلْكَافِرِينَ عَذَابَ النَّارِ
104፥6 *የተነደደችው "የአላህ እሳት" ናት*፡፡ نَارُ اللَّهِ الْمُوقَدَةُ
66፥6 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እራሳችሁን እና ቤተሰቦቻችሁን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጋዮች ከኾነች እሳት ጠብቁ"*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا قُوا أَنفُسَكُمْ وَأَهْلِيكُمْ نَارًا وَقُودُهَا النَّاسُ

አላህ ከእሳት ቅጣት ይጠብቀን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዱዓችን ምላሽ የማያገኝበት አምስት ምክንያት አሉ። እነርሱም፦
1ኛ.ዱዓእ ያደረግነው ነገር ሐላል ሳትሆን ሐራም ከሆነ፣
2ኛ. ዱዓእ ያደረግነው ነገር መጥቶ የሚጎዳን ከሆነ፣
3ኛ. ዱዓእ ያደረግነው ነገር በኢማን ካልሆነ፣
4ኛ. አላህ ዱዓእ ካደረግነው ነገር የተሻለ አስቦልን፣
5ኛ. አላህ ትእግስትን እና ጽናትን ሊያስተምረን፣

አላህ ዱዓችንን በኢማን እና በኢኽላስ ይቀበለን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ተማሪው ነቢይ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥48 *"መጽሐፍንና ጥበብንም ተውራትንና ኢንጂልንም ያስተምረዋል"*፡፡ وَيُعَلِّمُهُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَالتَّوْرَاةَ وَالْإِنجِيلَ

"ተዕሊም" تَعْلِيم የሚለው ቃል "ዐለመ" عَلَّمَ ማለትም "አስተማረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ትምህርት" ማለት ነው። አምላካችን አላህ "ሙዐሊም" مُعَلِّم ማለትም "አስተማሪ" "ዐዋቂ" ነው፥ ዒሣ ደግሞ አላህ ያስተማረው "ሙዐለም" مُعَلَّم ማለትም "ተማሪ" ነው፦
3፥48 *"መጽሐፍንና ጥበብንም ተውራትንና ኢንጂልንም ያስተምረዋል"*፡፡ وَيُعَلِّمُهُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَالتَّوْرَاةَ وَالْإِنجِيلَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ያስተምረዋል" ለሚለው የገባው ግስ "ዩዐለሙ-ሁ" يُعَلِّمُهُ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። አንድ ማንነትና ምንነት ከሌላ ኑባሬ ከተማረ ፊሽካው ተነፋ፥ ያ ማንነትና ምንነት "ሁሉን ዐዋቂ" አይደለም። በባይብልም ከሔድን ኢየሱስን የላከው ማንነት እንዳስተማረው እራሱ አበክሮና አዘክሮ ተናግሯል፦
ዮሐንስ 8፥28 *"አባቴም "እንዳስተማረኝ" እነዚህን እናገር ዘንድ እንጂ ከራሴ አንዳች እንዳላደርግ በዚያን ጊዜ ታውቃላችሁ*"።
ዮሐንስ 7፥15-17 አይሁድም፦ *"ይህ ሰው ሳይማር መጻሕፍትን እንዴት ያውቃል? ብለው ይደነቁ ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው፦ "ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ አይደለም። ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ ይህ ትምህርት ከእግዚአብሔር ቢሆን ወይም እኔ ከራሴ የምናገር ብሆን ያውቃል*።

ምን ትፈልጋለህ? የላከው ካስተማረው ውጪ የራሱ ዕውቅት የሌለው አካል እንዴት ይመለካል? "ራስ"own self" የሚለው ድርብ ተውላጠ-ስም ነው፥ "ራሴ" የሚለው ማንነት "እግዚአብሔር" ከተባለው ማንነት በመደብ ተውላጠ-ስም መለየቱ በራሱ ያስተማረው እግዚአብሔር እና ተማሪው ኢየሱስ ሁለት መሆናቸውን ፍንትውና ቁልጭ አርጎ ያሳያል። ከራሱ ምንም ማድረግ የማይችል እና ከተማረው ውጪ ከራሱ ምንም የማይናገር ኢየሱስ የጥበብ፣ የማስተዋል፣ የምክር፣ የኃይል፣ የእውቀት መንፈስ ስላረፈበት በሰዎች ያለውን ነገር ያውቅ ነበር፦
ኢሳይያስ 11፥2 *የእግዚአብሔር መንፈስ፥ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፥ የምክርና የኃይል መንፈስ፥ የእውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል*።

ፈጣሪ አንድ ነብይ ሲያስነሳ እውቀትን፣ ጥበብን፣ ማስተዋልን ይሰጠዋል፥ በዚህም የሩቅ ሚስጥራትን ያውቃል እንጂ በራሱ ሁሉን ዐዋቂ አይደለም። አንድ ነብይ ከሰው በላይ የሆነ ዕውቀት እንዳለው ከአይሁዳውያን መረዳት ይቻላል፦
ሉቃስ 7፥39 የጠራው ፈሪሳዊም አይቶ፦ *"ይህስ ነቢይ ቢሆን፥ ይህች የምትዳስሰው ሴት ማን እንደ ሆነች እንዴትስ እንደ ነበረች ባወቀ ነበር"* አለ።
ዮሐንስ 4፥17-19 ሴቲቱ መልሳ፦ ባል የለኝም አለችው። ኢየሱስ፦ *ባል የለኝም በማለትሽ መልካም ተናገርሽ፥ አምስት ባሎች ነበሩሽና፥ አሁን ከአንቺ ጋር ያለው ባልሽ አይደለም። በዚህስ እውነት ተናገርሽ" አላት። ሴቲቱም፦ *ጌታ ሆይ! አንተ ነቢይ እንደ ሆንህ አያለሁ*"።

አይሁዳውያን አንድ ሰው መጥቶ በልባቸውን ያለውን ቢነግራቸው "ፈጣሪ ነህ" ሳይሆን የሚሉት፥ "ነቢይ ነህ" የሚሉት። ምክንያቱም የልብን የሚያውቅ ፈጣሪ ስለሆነ ያ ሰው ነቢይ ካልሆነ የልብን ማወቅ አይችልም። ኢየሱስ ደግሞ ከራሱ ሳይሆን ከፈጣሪ እየሰማ የሚናገር ሰው ነበረ፥ አክሎም፦ "የሰማሁትን ሁሉ ለእናንተ አስታውቄአችኋለሁና" ማለቱ በራሱ ዕውቀቱ ሁሉ ከፈጣሪ የሰማው ነው፦
ዮሐንስ 12፥49 *"እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፥ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ*"።
ዮሐንስ 5፥30 *እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ "እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ"*።
ዮሐንስ 8፥26 *"የላከኝ እውነተኛ ነው እኔም "ከእርሱ የሰማሁትን" ይህን ለዓለም እናገራለሁ" አላቸው*።
ዮሐንስ 15፥15 *"ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ለእናንተ አስታውቄአችኋለሁና"*።
ዮሐንስ 8፥40 ነገር ግን አሁን *ከእግዚእብሔር የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን ሰው* ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ?

መቼም "እግዚአብሔር ከእግዚአብሔር እየሰማ ሲናገር ነበር" ብላችሁ ዓይናችሁ በጨው አጥባችሁ እንደማታሞኙን ቅቡል ነው። ከእግዚአብሔር እየሰማ የሚናገረው ኢየሱስ ግን እዚሁ አንቀጽ ላይ "ሰው" ነው" ተብሏል። "ነቢይ" የሚለው የግዕዝ ቃል እራሱ "ነበየ" ማለትም "ተናገረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ነባቢ" "ተናጋሪ" ማለት ነው፥ ከፈጣሪ የሚመጣለት ንግግር ደግሞ "ነቢብ" ይባላል። ኢየሱስ ደግሞ ነቢይ ነው፦
ማርቆስ 6፥4 ኢየሱስም፦ *"ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ዘመዶቹ ከገዛ ቤቱም በቀር ሳይከበር አይቀርም* አላቸው።
ማቴዎስ 21፥11 ሕዝቡም፦ *ይህ ከገሊላ ናዝሬት የመጣ ነቢዩ ኢየሱስ ነው* አሉ።
ሉቃስ 24፥19 *በእግዚአብሔር እና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በሥራና በቃል ብርቱ ነቢይ ስለ ነበረው ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ"*።
ዮሐንስ 9፥17 አንተ ዓይኖችህን ስለ ከፈተ ስለ እርሱ ምን ትላለህ? ደግሞ አሉት። እርሱም፦ *"ነቢይ ነው* አለ።

ይህ አፍጦና አፋጦ፥ አግጦና አንጋጦ የሚታይ እውነት ነው። የናዝሬቱ ኢየሱስ በእግዚአብሔር እና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በሥራና በቃል ብርቱ ነቢይ ነው፥ ከገሊላ ናዝሬት የመጣ ነቢዩ ኢየሱስ ተማሪ ነው። መቼም ይህንን ስትሰሙ ቆሌ ተገፎና ቆሽት አሮ፦ "ሰማይ ተንዶ ሊናጫነኝ ነው፥ ምድር ተከፍቶ ሊውጠኝ ነው" እንደምትሉ እሙን ነው። የክርስትና ደርዛዊ ሥነ-መለኮትን በዘመናዊነት ማዘመን መላላጫና መጋጋጫ በሌለው እፉቅቅ እና እንብርክክ እየተጎተቱ መሔድ ነው። አላህ ሂዳያ ይስጣችሁ፥ ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አርባ አራቱ ታቦት

ድሮ ድሮ አርባ አራቱ ታቦት ሲባል አርባ አራት ቅዱሳን ይመስሉኝ ወይም አርባ አራት ታቦታት ያሉ ይመስለኝ ነበር። ቅሉ ግን አርባ አራቱ ታቦት እያሉ የሚጠሯቸው በጎንደር ከተማ ያሉትን አርባ አራት ታቦታት ነው፥ በእነዚህ አርባ አራቱ ታቦታት መሃላ ይፈጽማሉ። አርባ አራቱ ታቦታት ስም ዝርዝር የሚከተለው ናቸው፦
1) ፊት ሚካኤል
2) ፊት አቦ
3) አደባባይ ኢየሱስ
4) ግምጃ ቤት ማርያም
5) እልፍኝ ጊዬርጊስ
6) መድኃኔዓለም
7) ቅዱስ ገብርኤል
8) ጠዳ እግዚአብሔር አብ
9) አባ እንጦንዮስ
10) ደብረብርሃን ሥላሴ
11) አደባባይ ተክለሃይማኖት
12) ሠለስቱ ምእት
13) ልደታ ለማርያም
14) አጣጣሚ ሚካኤል
15) አቡነ ኤውሰጣቴዎስ
16) ቅዱስ ሩፋኤል
17) ደፈጫ ኪዳነምህረት
18) ቁስቋም ደብረ ፀሐይ
19) መጥምቁ ዬሐንስ
20) በኣታ ለማርያም
21) ቅዱስ ቂርቆስ
22) ዬሐንስ ወልደ ነጎድጓድ
23) አባ ጃሌ ተክለሃይማኖት
24) ፈንጥር ልደታ
25) ደብረ ምጥማቅ ማርያም
26) አባ ዐቢየ እግዚእ
27) ቅዱስ ፋሲለደስ
28) ሐዋርያት
29) ቀሃ ኢየሱስ
30) አርባዕቱ እንሰሳት
31) ጎንደሮች ጊዮርጊስ
32) ጎንደሮች ማርያም
33) አበራ ጊዮርጊስ
34) ብላጅግ ቅዱስ ሚካኤል
35) አባ ሳሙኤል
36) አይራ ሚካኤል
37) ጓራ ዮሐንስ
38) ወረንግቦ ጊዮርጊስ
39) አሮጌ ልደታ
40) አዘዞ ተክለሃይማኖት
41) ምንዝሮ ተክለሃይማኖት
42) ሰራራ ማርያም
43) ዳሞት ጊዮርጊስ
44) ጫጭቁና ማርያም

መሳቅ አይቻልም እዘንላቸው። አላህ ሂዳያህ ይስጣቸው! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ነቢይ እና ረሡል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

22፥52 *”ከመልእክተኛ እና ከነቢይም”* ከአንተ በፊት አንድንም አልላክንም፥ ባነበበ ና ዝም ባለ ጊዜ፣ ሰይጣን በንባቡ ላይ ማጥመሚያን ቃል የሚጥል ቢሆን እንጂ። وَمَا أَرْسَلْنَا مِنْ قَبْلِكَ مِنْ رَسُولٍ وَلَا نَبِيٍّ إِلَّا إِذَا تَمَنَّىٰ أَلْقَى الشَّيْطَانُ فِي أُمْنِيَّتِهِ

"ወሕይ" وَحْى የሚለው ቃል “አውሓ” أَوْحَىٰٓ ማለትም “ገለጠ” ወይም “አወረደ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ግልጠተ-መለኮት” ወይም “ግህደተ-መለኮት”Revelation” ማለት ነው። አምላካችን አላህ ወደ ነቢያት ወሕይ ስለሚያወርድ “አውሐይና” أَوْحَيْنَا ማለትም “አወረድን” ብሎ ይናገራል፦
4፥163 *"እኛ ወደ ኑሕ እና ከእርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነቢያት እንዳወረድን፥ ወደ አንተም አወረድን፡፡ ወደ ኢብራሂምም፣ ወደ ኢስማዒልም፣ ወደ ኢስሓቅም፣ ወደ ያዕቆብም፣ ወደ ነገዶቹም፣ ወደ ዒሳም፣ ወደ አዩብም፣ ወደ ዩኑስም፣ ወደ ሃሩን እና ወደ ሱለይማንም አወረድን፡፡ ለዳውድም ዘቡርን ሰጠነው*፡፡ إِنَّا أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ كَمَا أَوْحَيْنَا إِلَىٰ نُوحٍ وَالنَّبِيِّينَ مِن بَعْدِهِ ۚ وَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَعِيسَىٰ وَأَيُّوبَ وَيُونُسَ وَهَارُونَ وَسُلَيْمَانَ ۚ وَآتَيْنَا دَاوُودَ زَبُورًا

አምላካችን አላህ ወደ ነቢያት ወሕይ የሚያወርደው በሦስት አይነት መንገድ ነው፥ አንደኛው መንገድ በራእይ፣ ሁለተኛ መንገድ ከግርዶ ወዲያ፣ ሦስተኛው መንገድ መልአክን በመላክ ነው፦
42፥51 *ለሰው አላህ “በራእይ”፣ ወይም “ከግርዶ ወዲያ”፣ ወይም “መልክተኛን መልአክን” የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን “የሚያወርድለት” ቢሆን እንጅ በገሃድ “ሊያናግረው” ተገቢው አይደለም”*፥ እርሱ የበላይ ጥበበኛ ነውና። وَمَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُكَلِّمَهُ ٱللَّهُ إِلَّا وَحْيًا أَوْ مِن وَرَآئِ حِجَابٍ أَوْ يُرْسِلَ رَسُولًۭا فَيُوحِىَ بِإِذْنِهِۦ مَا يَشَآءُ ۚ إِنَّهُۥ عَلِىٌّ حَكِيمٌۭ

እነዚህ ወሕይ የሚወርድላቸው ሰዎች በሁለት ይከፈላሉ፥ እነርሱም "ነቢይ" እና "ረሡል" ይባላሉ። ይህን እሳቤ ነጥብ በነጥብ፥ ጥንልልና ጥንፍፍ አርገን እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
"ነቢይ"
"ነቢይ" نَبِيّ የሚለው ቃል "ነበአ” نَبَّأَ ማለትም "አወራ" ወይም "ተናገረ" ከሚል ሥርወ-ቃል ሲሆን "አውሪ" ወይም "ተናጋሪ" ማለት ነው፥ የነቢይ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ነቢዩን" نَبِيُّون ወይም "አንቢያእ" أَنْبِيَاء ነው። አንድ ሰው ከአላህ ዘንድ "ነበእ" نَبَأ ማለትም "የሩቅ ወሬ" ወይም "የሩቅ ንግግር" ሲወርድለት ነቢይ ይሰኛል፦
66፥3 *”ነቢዩ ከሚስቶቹ ወደ አንዷ ወሬን በመሰጠረ ጊዜ አስታውስ፡፡ እርሱንም በነገረች እና አላህ እርሱን ማውራትዋን ባሳወቀው ጊዜ ከፊሉን አስታወቀ፤ ከፊሉንም ተወ፡፡ በእርሱም ባወራት ጊዜ «ይህን ማን ነገረህ?» አለች፡፡ «ዐዋቂው ፥ውስጠ ዐዋቂው ነገረኝ» አላት”*። وَإِذْ أَسَرَّ ٱلنَّبِىُّ إِلَىٰ بَعْضِ أَزْوَٰجِهِۦ حَدِيثًۭا فَلَمَّا نَبَّأَتْ بِهِۦ وَأَظْهَرَهُ ٱللَّهُ عَلَيْهِ عَرَّفَ بَعْضَهُۥ وَأَعْرَضَ عَنۢ بَعْضٍۢ ۖ فَلَمَّا نَبَّأَهَا بِهِۦ قَالَتْ مَنْ أَنۢبَأَكَ هَٰذَا ۖ قَالَ نَبَّأَنِىَ ٱلْعَلِيمُ ٱلْخَبِيرُ

በዚህ አንቀጽ ውስጥ “ማን ነገረህ” ለሚለው ቃል የገባው “መን አንበአከ” مَنْ أَنْبَأَكَْ ሲሆን መልሱ “ነበአኒየ” نَبَّأَنِيَ ማለትም “ነገረኝ” ማለት ነው። “አንበአከ” أَنْبَأَكَْ ሆነ “ነበአኒየ” نَبَّأَنِيَ የሁለቱም ግስ ርቢ “ነበአ” نَبَّأَ ነው። ስለዚህ “ነቢይ” ማለት ሁሉን ዐዋቂው፥ ውስጠ ዐዋቂው አላህ የሚያናግረው እና የሚነግረው ማለት ነው። ከዚያም ባሻገር መመሪያው እራሱ በራሱ የነቢይነት መደብ ውስጥ ነው፦
15፥49 *”ባሮቼን እኔ ይቅርባዩ መሓሪው እኔው ብቻ መኾኔን ንገራቸው”*፡፡ نَبِّئْ عِبَادِي أَنِّي أَنَا الْغَفُورُ الرَّحِيمُ

“ንገራቸው” نَبِّئْ ለሚለው ትእዛዛዊ ግስ አሁንም “ነበእ” نَبِّئْ ሲሆን “ነበአ” نَبَّأَ ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ነው። አንድ ነቢይ ለአማንያን በመልካም ለማዘዝ እና በመጥፎ ለመከልከል ያስጠነቅቃል፥ ለራሱም ዒባዳህ ምን ምን ማድረግ እንዳለበት አላህ ይነግረዋል።

ነጥብ ሁለት
"ረሡል"
"ረሡል" رَسُول የሚለው ቃል "አርሠለ" أَرْسَلَ ማለትም "ላከ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መልእክተኛ" ማለት ነው፥ የረሡል ብዙ ቁጥር ደግሞ "ሩሡል" رُسُل ነው። አንድ ነቢይ ሕግ ያለበት "ሪሣላህ" رِسَالَة ማለትም "መልእክት" ሲወርድለት ረሡል" ይሆናል፦
5፥48 ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭና በእርሱ ላይ ተጠባባቂ ሲኾን በእውነት አወረድን፡፡ በመካከላቸውም *”አላህ ባወረደው ሕግ ፍረድ”*፡፡ እውነቱም ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌዎቻቸውን አትከተል፡፡ *”ከእናንተ ለሁሉም ሕግን እና መንገድን አደረግን”*፡፡ وَأَنزَلْنَآ إِلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَمُهَيْمِنًا عَلَيْهِ ۖ فَٱحْكُم بَيْنَهُم بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَآءَهُمْ عَمَّا جَآءَكَ مِنَ ٱلْحَقِّ ۚ لِكُلٍّۢ جَعَلْنَا مِنكُمْ شِرْعَةًۭ وَمِنْهَاجًۭا

"ከእናንተ ለሁሉም ሕግን እና መንገድን አደረግን" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። "እናንተ" የተባሉት መልእክተኞቹ ናቸው፥ እዚህ አንቀጽ ላይ “ሕግ” ለሚለው ቃል የገባው “ሺርዓህ” شِرْعَة መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። “መንገድ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሚንሃጅ” مِنْهَاج ሲሆን “መንሃጅ” مَنْهَج ማለት ነው። አምላካችን አላህ”ﷻ” ለሁሉም መልእክተኞች በዘመናቸው ሸሪዓህ እና መንሃጅ ማድረጉን ያሳያል። ረሡል ለአማንያን እና ለከሃድያን ለማስጠንቀቅ በሸሪዓህ ይላካል፦
22፥52 *”ከመልእክተኛ እና ከነቢይም”* ከአንተ በፊት አንድንም አልላክንም፥ ባነበበ ና ዝም ባለ ጊዜ፣ ሰይጣን በንባቡ ላይ ማጥመሚያን ቃል የሚጥል ቢሆን እንጂ። وَمَا أَرْسَلْنَا مِنْ قَبْلِكَ مِنْ رَسُولٍ وَلَا نَبِيٍّ إِلَّا إِذَا تَمَنَّىٰ أَلْقَى الشَّيْطَانُ فِي أُمْنِيَّتِهِ
እዚህ አንቀጽ ላይ "ነቢይ" نَبِيّ እና "ረሡል" رَسُول በሚሉት የማዕረግ ስሞች መካከል “ወ” وَ ማለትም “እና” የሚል መስተጻምር አለ፥ ይህም ነቢይ እና ረሡል ሁለት የተለያየ ደረጃ መሆኑን ቁልጭና ፍንትው አድርጎ ያሳያል። በተጨማሪም “አልላክንም” የሚለው አጽንዖታዊ ቃል “ቢሆን እንጂ” በሚል አፍራሽ ቃል በመምጣቱ ነብይ በመልካም እንዲያዝ በመጥፎ እንዲከለክል ለአማንያን እንደተላከ ሁሉ መልእክተኛ ደግሞ ለአማንያንና ለከሃድያን ለማስጠንቀቅና ለማብሰር ይላካል። መልእክተኛ መልክተኛ ለመሆን ነቢይነትን አሳልፎ ስለሆነ መልእክተኛ ሁሉ ነቢይ ነው፥ ነቢይ ሁሉ ግን መልእክተኛ አይደለም። ምክንያቱም ሪሣላ ሳይወርድለት ነቢይ ብቻ ሆኖ የሚቀር አለ፥ ለምሳሌ አደም የመጀመሪያው ነቢይ ሲሆን ኑሕ ደግሞ የመጀመሪያው ረሡል ነው፦
ኢማም አሕመድ መጽሐፍ 5, ሐዲስ 1781
አቡ ዘር እንደተረከው፦ *”የአላህ ነቢይ”ﷺ” ሆይ የመጀመሪያው ነቢይ ማን ነው? ብሎ አለ። እርሳቸውም፦ “አደም ነው” አሉ። እርሱም፦ “እርሱ ነቢይ ነበርን? ብሎ አለ። እርሳቸውም፦ “አዎ” አሉ”*። عَن أَبُو ذَرٍّ قُلْتُ : يَا نَبِيَّ اللَّهِ، فَأَيُّ الْأَنْبِيَاءِ كَانَ أَوَّلَ. قَالَ : ” آدَمُ “. قَالَ : قُلْتُ : يَا نَبِيَّ اللَّهِ، أَوَنَبِيٌّ كَانَ آدَمُ ؟ قَالَ : ” نَعَمْ،
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 4476
አነሥ እንደተረከው፦ "ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *"......(አደምም)፦ “ኑህ ጋር ሂዱ! እርሱ በምድር ላይ የተላከ የመጀመሪያው መልእክተኛ ነው፥ ወደ ምድር ባለቤቶች አላህ ልኮታል” ይላቸዋል"*። ائْتُوا نُوحًا فَإِنَّهُ أَوَّلُ رَسُولٍ بَعَثَهُ اللَّهُ إِلَى أَهْلِ الأَرْضِ‏.‏

ነጥብ ሦስት
"መደምደሚያ"
ነቢያችን”ﷺ” የነቢያት መደምደሚያ ናቸው። ከነቢያችን”ﷺ” በኃላ ነቢይ ብቻ ሳይሆን ረሡልም አይመጣም። ነቢይነት እና መልእክተኝነት በእርሳቸው ተደምድሟል፦
33:40 ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንድንም ሰው አባት አይደለም። ነገር ግን የአላህ መልክተኛ እና *”የነቢያት መደምደሚያ” ነው"*፥ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው። مَا كَانَ مُحَمَّدٌ أَبَا أَحَدٍ مِنْ رِجَالِكُمْ وَلَٰكِنْ رَسُولَ اللَّهِ وَخَاتَمَ النَّبِيِّينَ وَكَانَ اللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمًا
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 2272
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”በእርግጥም መልእክተኛነት እና ነቢይነት ተዘግቷል። ከእኔ በኃላ መልእክተኛም ነቢይም የለም*። حَدَّثَنَا أَنَسُ بْنُ مَالِكٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ” إِنَّ الرِّسَالَةَ وَالنُّبُوَّةَ قَدِ انْقَطَعَتْ فَلاَ رَسُولَ بَعْدِي وَلاَ نَبِيَّ

ታዲያ "ነብይ እና ረሱም ከነቢያችን”ﷺ” በኃላ የለም" ከተባለ “ነብይ ነኝ” ወይም “መልእክተኛ ነኝ” ብለው የተነሱት ሚርዛ ጉላም አሕመድ የቃዲያኒይ መስራች፣ ሚርዛ ሑሤን ዐሊይ የባሃኢያህን መስራች፣ ዶክተር ራሺድ ኸሊፋክ የቁርኣንያህ መስራች ምንድን ናቸው? ሲባል ኃሣዌ ነብይ እና መልእክተኛ ናቸው። “አድ-ደጃል” الدَّجَّال የሚለው ቃል “ደጀለ” دَجَلَ ማለትም “አጭበረበረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “አጭበርባሪ” ወይም “ሐሳዌ” ማለት ነው። እነዚህ ወደ ሠላሳ የሚቃረቡ ደጃሎች “እኔ የአላህ መልእክተኛ ነኝ” ወይም “እኔ የአላህ ነብይ ነኝ” ብለው ይነሳሉ፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 54, ሐዲስ 108
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው ነብዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “የመጨረሻይቱ ሰአት አትቆምም *ሠላሳ የሚቃረቡ ደጃሎች ቀጣፊዎች ተነስተውስ፦ “እኔ የአላህ መልእክተኛ ነኝ” ብለው ቢናገሩ ቢሆን እንጂ”*። عَنْ أَبِي، هُرَيْرَةَ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ” لاَ تَقُومُ السَّاعَةُ حَتَّى يُبْعَثَ دَجَّالُونَ كَذَّابُونَ قَرِيبٌ مِنْ ثَلاَثِينَ كُلُّهُمْ يَزْعُمُ أَنَّهُ رَسُولُ اللَّهِ
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 13
የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *ከእኔ ዑማ ውስጥ ሠላሳ የሚያህሉ ቀጣፊዎች፦ “ነቢይ ነኝ” ብለው ይነሳሉ፥ ነገር ግን እኔ የነቢያት መደምደሚያ ነኝ። ከእኔ በኃላ ነቢይ የለም”*። وَحَتَّى تَعْبُدَ قَبَائِلُ مِنْ أُمَّتِي الأَوْثَانَ وَإِنَّهُ سَيَكُونُ فِي أُمَّتِي كَذَّابُونَ ثَلاَثُونَ كُلُّهُمْ يَزْعُمُ أَنَّهُ نَبِيٌّ وَأَنَا خَاتَمُ النَّبِيِّينَ لاَ نَبِيَّ بَعْدِي

"አሏሁ አዕለም" اَللّٰهُ أَعْلَم‎

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
መለከት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

39፥68 *በቀንዱም ይነፋል፥ በሰማያት ውስጥ ያለው ፍጡር እና በምድርም ውስጥ ያለው ፍጡር ሁሉ አላህ የሻው ሲቀር በድንጋጤ ይሞታል፡፡ ከዚያም በእርሱ ሌላ መንነፋት ይነፋል፥ ወዲያውም እነርሱ የሚሠራባቸውን የሚጠባበቁ ኾነው ቋሚዎች ይኾናሉ*፡፡ وَنُفِخَ فِي الصُّورِ فَصَعِقَ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَمَن فِي الْأَرْضِ إِلَّا مَن شَاءَ اللَّهُ ۖ ثُمَّ نُفِخَ فِيهِ أُخْرَىٰ فَإِذَا هُمْ قِيَامٌ يَنظُرُونَ

“ሱር” صُّور የሚለው ቃል “ሶወረ” صَوَّرَ ማለትም “ቀረፀ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ቅርፅ" ማለት ነው፥ ይህ ቅርፅ ነጋሪት የሚጎሰምበት የመለከት ቀንድ ነው። "ቀርን" قَرْن ማለት "ቀንድ" ማለት ሲሆን ለመለከት የሚቀረጽ ቀንድ ነው፦
ሡነን አቢዳውድ መጽሐፍ 42, ሐዲስ 147
ዐብደሏህ ኢብኑ ዐምር እንደተረከው፦ "ነቢዩም አሉ፦ *"ሱር የሚነፋበት ቀንድ ነው"*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ "‏ الصُّورُ قَرْنٌ يُنْفَخُ فِيهِ ‏"‏

በፍርድ ቀን ጠሪው መልአክ ወደ አስደንጋጭ ነገር በቀንዱ በሚጠራበትን ቀን በሰማያት ውስጥ ያለው ፍጡር እና በምድርም ውስጥ ያለው ፍጡር ሁሉ አላህ የሻው ሲቀር በድንጋጤ ይሞታል፦
53፥6 ከእነርሱም ዙር፡፡ *ጠሪው መልአክ ወደ አስደንጋጭ ነገር የሚጠራበትን ቀን አስታውስ*፡፡ فَتَوَلَّ عَنْهُمْ ۘ يَوْمَ يَدْعُ الدَّاعِ إِلَىٰ شَيْءٍ نُّكُرٍ
39፥68 *በቀንዱም ይነፋል፥ በሰማያት ውስጥ ያለው ፍጡር እና በምድርም ውስጥ ያለው ፍጡር ሁሉ አላህ የሻው ሲቀር በድንጋጤ ይሞታል፡፡ ከዚያም በእርሱ ሌላ መንነፋት ይነፋል፥ ወዲያውም እነርሱ የሚሠራባቸውን የሚጠባበቁ ኾነው ቋሚዎች ይኾናሉ*፡፡ وَنُفِخَ فِي الصُّورِ فَصَعِقَ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَمَن فِي الْأَرْضِ إِلَّا مَن شَاءَ اللَّهُ ۖ ثُمَّ نُفِخَ فِيهِ أُخْرَىٰ فَإِذَا هُمْ قِيَامٌ يَنظُرُونَ

"አስ-ሶዕቃህ" الصَّعْقَةُ የሚለው ቃል "ሶዒቀ" صَعِقَ ማለት "እራሱ ሳተ" ወይም "ምንም ሆነ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "እራስን መሳት" ወይንም "ምንም መሆን" ማለት ነው። ፍጥረት በትንሳኤ ቀን ፊተኛው መነፋት ሲነፋ እራስን ይስታል ወይም ምንም ይሆናል፦
ሡነን አቢ ዳዉድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 658
አውሥ ኢብኑ አውሥ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ከቀናችሁ በላጩ ቀን የጁሙዓህ ቀን ነው፥ በዚያ ቀን አደም ተፈጠረ፥ በዚያ ቀን ሞተ። በዚያ ቀንም መለከት ይነፋል፥ ሁሉ በድንጋጤ ይሞታል”*። عَنْ أَوْسِ بْنِ أَوْسٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ إِنَّ مِنْ أَفْضَلِ أَيَّامِكُمْ يَوْمَ الْجُمُعَةِ فِيهِ خُلِقَ آدَمُ وَفِيهِ قُبِضَ وَفِيهِ النَّفْخَةُ وَفِيهِ الصَّعْقَةُ

"አኽራ" أُخْرَىٰ ማለት "ሌላ" ማለት ሲሆን "ሌላ መንነፋት" የሚለው ሁለተኛውን መነፋት ነው፥ በሁለቱ ማለትም በፊተኛው መነፋት እና በኃለኛው መነፋት መካከል ያለው ክፍተት አርባ ነው፦
ኢማም ቡኻሪ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 4814
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"በሁለቱ መነፋት ያለው ክፍተት አርባ ነው"*። قَالَ سَمِعْتُ أَبَا هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ بَيْنَ النَّفْخَتَيْنِ أَرْبَعُونَ ‏"‌‏

ይህ አርባ ቀን ይሁን ወይም ወር አሊያም ዓመት ምንም አልተገለጸም። በሁለተኛው መነፋት የሚሠራባቸውን የሚጠባበቁ ኾነው ቋሚዎች ይኾናሉ፥ “ቂያማህ” قِيَٰمَة የሚለው ቃል “ቃመ” قَامَ ማለትም “ተነሣ” “ቆመ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ትንሣኤ” ማለት ነው። ጠሪው መልአክ በሚጠራበት ቀን ከመቃብራቸው ይወጣሉ፦
50፥41 *"የሚነገርህን አዳምጥም፡፡ ጠሪው ከቅርብ ስፍራ በሚጠራበት ቀን ከመቃብራቸው ይወጣሉ*፡፡ وَاسْتَمِعْ يَوْمَ يُنَادِ الْمُنَادِ مِن مَّكَانٍ قَرِيبٍ
50፥42 *ጩኸቲቱን በእውነት የሚሰሙበት ቀን ያ ከመቃብር የመውጫው ቀን ነው*፡፡ يَوْمَ يَسْمَعُونَ الصَّيْحَةَ بِالْحَقِّ ۚ ذَٰلِكَ يَوْمُ الْخُرُوجِ
36፥51 *"በቀንዱም ይነፋል፥ ወዲያውኑም እነርሱ ከመቃብሮቻቸው ወደ ጌታቸው በፍጥነት ይገሰግሳሉ*፡፡ وَنُفِخَ فِي الصُّورِ فَإِذَا هُم مِّنَ الْأَجْدَاثِ إِلَىٰ رَبِّهِمْ يَنسِلُونَ
ይህ በመለከት ሁለቱን መነፋት የሚነፋው መልአክ "የመለከት ባለቤት" ነው፥ "ሷሒብ" صَاحِب ማለት "ጓድ" ወይም "ባለቤት" ማለት ነው፥ ዩኑስ "ሷሒቡል ሑት" صَاحِب الْحُوت ሲባል "የዓሣው ባለቤት" እንደሚባል ሁሉ ይህ መልአክ "ሷሒቡ አስ-ሱር" صَاحِب الصُّور ማለት "የመለከት ባለቤት" ተብሏል፦
ሡነን አቢ ዳዉድ መጽሐፍ 32, ሐዲስ 31
አቢ ሠዒድ አል-ኹድሪይ እንደተረከው፦ *"የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" "ሷሑበል ሱርን" አውስተዋል። በቀኙ ጂብሪል፥ በግራው ሚካኢል መሆናቸውን ተናግረዋል"*። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ قَالَ ذَكَرَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم صَاحِبَ الصُّورِ فَقَالَ ‏ "‏ عَنْ يَمِينِهِ جِبْرَائِلُ وَعَنْ يَسَارِهِ مِيكَائِلُ ‏"‏

ይህ ሷሒቡ አስ-ሱር በሌላ ሐዲስ "ኢሥራፊል" ተብሏል፥ “ኢሥራፊል” إِسْرَافِيل ማለት “ሩፋኤል” ማለት ሲሆን ከአራቱ የመላእክት አለቃ አንዱ ነው፦
ሡነን አን-ነሣኢ መጽሐፍ 50 , ሐዲስ 92
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ ይሉ ነበር፦ *"አላህ ሆይ! የጂብሪል እና የሚካኢል ጌታ፣ የኢሥራፊል ጌታ በአንተ ከእሳት ቅጣት እና ከቀብር ቅጣት እጠበቃለው"*። عَنْ عَائِشَةَ، أَنَّهَا قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ اللَّهُمَّ رَبَّ جِبْرَائِيلَ وَمِيكَائِيلَ وَرَبَّ إِسْرَافِيلَ أَعُوذُ بِكَ مِنْ حَرِّ النَّارِ وَمِنْ عَذَابِ الْقَبْرِ

ይህ አቧራ የሚያስነሳ ጥያቄ አልነበረም። በባይብልም ቢሆን ወይም በትውፊት በፍርድ ቀን ሰባት የመላእክት አለቆች ሚካኤል፣ ገብርኤል፣ ሩፋኤል፣ ኡራኤል፣ ራጉኤል፣ ፋኑኤል(ጀርምኤል)፣ ሳቁኤል(ሰራኤል) ሰባት መለከት ተሰቷቸው ነጋሪት እንደሚነፉ ይናገራል፦
ማቴዎስ 24፥31 *"መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፥ ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ"*።
ራእይ 8፥2 *"በእግዚአብሔርም ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ፥ ሰባትም መለከት ተሰጣቸው*።
ራእይ 8፥6 *"ሰባቱንም መለከት የያዙ ሰባቱ መላእክት ሊነፉ ተዘጋጁ"*።
ዳንኤል 10፥13 *"ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ"*።
ኤፌሶን 3፥10 *"በሰማያዊ ስፍራ ውስጥ ላሉት "አለቆች" እና ሥልጣናት ትታወቅ ዘንድ"*።

ሚካኤል ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ነው፥ ሌሎች የመላእክት ስላሉ "ዋነኞቹ አለቆች" ብሎ አስቀምጦታል። "አለቆች" የሚለው የግሪኩ ቃል "አርኬስ" ἀρχαῖς ሲሆን "አርኬ" ἄρχω ማለትም "አለቃ" ለሚለው ብዙ ቁጥር ነው፥ በመላእክት አለቃ ድምፅ የፈጣሪ መለከት ሲነፋ ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ፦
1ኛ ቆሮንቶስ 15፥52 *"መለከት ይነፋልና ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ"*፥ እኛም እንለወጣለን።
1 ተሰሎንቄ 4፥16 ጌታ ራሱ በትእዛዝ *"በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ*።

መልአክ በበድን አካል ላይ መንፋቱ ስትገረሙበት ነፋስ በበድን ላይ እፍ ብሎ እንደሚነፋ መነገሩ ተደመሙበት፦
ሕዝቅኤል 37፥9 እርሱም፦ *የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገር፥ ለነፋስ ትንቢት ተናገር! ለነፋስም፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ነፋስ ሆይ! ከአራቱ ነፋሳት ዘንድ ና፥ እነዚህም የተገደሉት በሕይወት ይኖሩ ዘንድ እፍ በልባቸው፡ በል! አለኝ*።

ነፋስ በተገደሉት በድን ላይ "እፍ" የሚለው እንዴት ነው? ይህንን መመለስ ከቻላችሁ ኢሥራፊል እንዴት እንደሚነፋ መረዳት ቀላል ነው። አላህ ሂዳያ ይስጣችሁ፥ ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አልገደሉትም

@ገቢር አንድ

http://bit.ly/2HWzE0a

@ገቢር ሁለት

http://bit.ly/2HUcLuz

@ገቢር ሦስት

http://bit.ly/2HSQxJa

@ገቢር አራት

http://bit.ly/2HYIDOy

@ገቢር አምስት

http://bit.ly/2HWJ3Fd
የመጨረሻው ቀን

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

33፥21 ለእናንተ *አላህን እና "የመጨረሻውን ቀን" የሚከጅል ለሆነ ሰው፣ አላህንም በብዙ ለሚያወሳ በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አላችሁ*፡፡ لَّقَدْ كَانَ لَكُمْ فِي رَسُولِ اللَّهِ أُسْوَةٌ حَسَنَةٌ لِّمَن كَانَ يَرْجُو اللَّهَ وَالْيَوْمَ الْآخِرَ وَذَكَرَ اللَّهَ كَثِيرًا

“ዱንያ” دُّنْيَا ማለት “ቅርቢቱ” ማለት ሲሆን የምንኖርበት ይህንን ዓለም ያመለክታል፥ “አኺራህ” آخِرة ማለት “መጨረሻይቱ” ማለት ሲሆን የሚቀጥለውን ዓለም ያመለክታል። የዚህ ዓለም የሚያበቃበት ቀን "የመጨረሻው ቀን ነው። "የመጨረሻው ዘመን ጥናት”Eschatology” በኢሥላም “አል-አኺሩ አዝ-ዘማን” الْآخِر الْزَمَان ይባላል፥ በቁርኣን "የውመል አኺር" يَوْم الْآخِر ማለትም "መጨረሻው ቀን" ተብሎ ብዙ ቦታ ተጠቅሷል፥ ከስድስቱ አርካኑል ኢማን መካከልም አንዱ "በመጨረሻው ቀን" ማመን ነው፦
33፥21 ለእናንተ *አላህን እና "የመጨረሻውን ቀን" የሚከጅል ለሆነ ሰው፣ አላህንም በብዙ ለሚያወሳ በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አላችሁ*፡፡ لَّقَدْ كَانَ لَكُمْ فِي رَسُولِ اللَّهِ أُسْوَةٌ حَسَنَةٌ لِّمَن كَانَ يَرْجُو اللَّهَ وَالْيَوْمَ الْآخِرَ وَذَكَرَ اللَّهَ كَثِيرًا
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 40, ሐዲስ 5
ዑመር ኢብኑ ኽጣብ እንዳስተላለፈው፦ “አንድ በጣም ነጭ ልብስ የለበሰና በጣም ጥቁር ጸጉር ያለው ሰው በመጣ ጊዜ ከአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ጋር ነበርን፤ ወደ እርሳቸው ሲጓዝ አይታይም ነበር፤ ወደ ነብዩ”ﷺ” እስከሚደርስ ድረስ ከእኛ መካከል ማንም ዐላወቀውም፤ ጉልበቱን በእራሳቸው ጉልበት ተቃራኒ አድርጎ ከዚያም እንዲህ አለ፦ *”ሙሐመድ ሆይ! ኢማን ምንድን ነው? እርሳቸውም፦ “በአላህ ማመን፣ በመላእክቱ ማመን፣ በመጽሐፍቱ ማመን፣ በነቢያቱ ማመን፣ በመጨረሻው ቀን ማመን እና በሰናይ እና እኩይ ቀደር ማመን ነው” አሉ*። ‏ قَالَ عُمَرُ بْنُ الْخَطَّابِ كُنَّا عِنْدَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَجَاءَ رَجُلٌ شَدِيدُ بَيَاضِ الثِّيَابِ شَدِيدُ سَوَادِ الشَّعَرِ لاَ يُرَى عَلَيْهِ أَثَرُ السَّفَرِ وَلاَ يَعْرِفُهُ مِنَّا أَحَدٌ حَتَّى أَتَى النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم فَأَلْزَقَ رُكْبَتَهُ بِرُكْبَتِهِ ثُمَّ قَالَ يَا مُحَمَّدُ مَا الإِيمَانُ قَالَ ‏”‏ أَنْ تُؤْمِنَ بِاللَّهِ وَمَلاَئِكَتِهِ وَكُتُبِهِ وَرُسُلِهِ وَالْيَوْمِ الآخِرِ وَالْقَدَرِ خَيْرِهِ وَشَرِّهِ

"የውም" يَوْم ማለት "ቀን" ማለት ሲሆን መአልት እና ሌሊት ያቀፈ የሀያ አራት ሰዓት እርዝማኔ ብቻ ሳይሆን ፍርድ የሚከናወንበት አንድ ሺህ ዓመት ያመለክታል፦
22፥47 አላህም ቀጠሮውን በፍጹም የማይጥስ ሲሆን በቅጣት ያቻኩሉሃል፡፡ *"እጌታህም ዘንድ አንዱ ቀን ከምትቆጥሩት ቀን እንደ ሺሕ ዓመት ነው"*፡፡ وَيَسْتَعْجِلُونَكَ بِالْعَذَابِ وَلَن يُخْلِفَ اللَّهُ وَعْدَهُ ۚ وَإِنَّ يَوْمًا عِندَ رَبِّكَ كَأَلْفِ سَنَةٍ مِّمَّا تَعُدُّونَ
32፥5 *"ነገሩን ሁሉ ከሰማይ ወደ ምድር ያዘጋጃል፡፡ ከዚያም ከምትቆጥሩት ዘመን ልኩ ሺህ ዓመት በሆነ ቀን ውስጥ ወደ እርሱ ይወጣል"*፡፡ يُدَبِّرُ الْأَمْرَ مِنَ السَّمَاءِ إِلَى الْأَرْضِ ثُمَّ يَعْرُجُ إِلَيْهِ فِي يَوْمٍ كَانَ مِقْدَارُهُ أَلْفَ سَنَةٍ مِّمَّا تَعُدُّونَ

ይህ የመጨረሻ ቀን፦
"የውመል መውዑድ" يَوْم الْمَوْعُودِ
"የውሙል ሐቅ" يَوْمُ الْحَقّ
"የውሙል ኹሩጅ" يَوْمُ الْخُرُوج
"የውመል ቂያማህ" يَوْمَ الْقِيَامَة
"የውሚ አድ-ዲን" يَوْمِ الدِّين
"የውመል ፈትሕ" يَوْمَ الْفَتْح
"የውመል ጀምዕ" يَوْمِ الْجَمْع
"የውሙል ፈስል" يَوْمُ الْفَصْل
"የውመ አት-ተላቅ" يَوْمَ التَّلَاق
"የውሚል ሒሣብ" يَوْمِ الْحِسَاب
"የውመ አት-ተናድ" يَوْمَ التَّنَاد
"የውሙል ወዒድ" يَوْمُ الْوَعِيد
"የውመል ሐሥራህ" يَوْمَ الْحَسْرَة
"የውሙም መሽሁድ" يَوْمٌ مَّشْهُود
"የውሙል ኹሉድ" يَوْمُ الْخُلُود ተብሏል።
ይህንን ጥርስ እና ምላሱን እየነቀስን ኢንሻላህ ነጥብ በነጥብ እናያለን፦
ነጥብ አንድ
"የውመል መውዑድ"
"የውመል መውዑድ" يَوْم الْمَوْعُودِ ማለት "የተቀጠረው ቀን" ማለት ነው፦
85፥2 *"በተቀጠረው ቀንም እምላለው"*። وَالْيَوْمِ الْمَوْعُودِ

አላህ ፍጥረትን ወሮታና አጸፌታ፥ ምንዳና ትሩፋት የሚከፍበትን ቀን ቀጥሯል። ይህ ቀጠሮ መጪ ነው፥ በዚያ ቀን ሰማዩ ተሰንጣቂ ነው፥ ቀጠሮው ተፈጻሚ ነው። ከሃድያን ቢዚያ ቀን፦ "ይህ ያ አዛኙ ጌታ በእርሱ የቀጠረን መልክተኞቹም እውነትን የነገሩን ነው" ይላሉ፦
29፥5 *የአላህን መገናኘት ተስፋ የሚያደርግ ሰው ይዘጋጅ፡፡ የአላህ ቀጠሮ በእርግጥ መጪ ነውና*፡፡ እርሱም ሰሚው ዐዋቂው ነው፡፡ مَن كَانَ يَرْجُو لِقَاءَ اللَّهِ فَإِنَّ أَجَلَ اللَّهِ لَآتٍ ۚ وَهُوَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ
34፥30 *«ለእናንተ ከእርሱ አንዲትንም ሰዓት የማትዘገዩበት የማትቀድሙበትም የቀጠሮ ቀን አላችሁ» በላቸው*፡፡ قُل لَّكُم مِّيعَادُ يَوْمٍ لَّا تَسْتَأْخِرُونَ عَنْهُ سَاعَةً وَلَا تَسْتَقْدِمُونَ
73፥18 *"ሰማዩ በእርሱ በዚያ ቀን ተሰንጣቂ ነው፡፡ ቀጠሮው ተፈጻሚ ነው*፡፡ السَّمَاءُ مُنفَطِرٌ بِهِ ۚ كَانَ وَعْدُهُ مَفْعُولًا
36፤52 *«ወይ ጥፋታችን! ከመኝታችን ማን ቀሰቀሰን? ይህ ያ አዛኙ ጌታ በእርሱ የቀጠረን መልክተኞቹም እውነትን የነገሩን ነው» ይላሉ*፡፡ قَالُوا يَا وَيْلَنَا مَن بَعَثَنَا مِن مَّرْقَدِنَا ۜ ۗ هَـٰذَا مَا وَعَدَ الرَّحْمَـٰنُ وَصَدَقَ الْمُرْسَلُونَ

ነጥብ ሁለት
"የውሙል ሐቅ"
"የውሙል ሐቅ" يَوْمُ الْحَقّ ማለት "የተረጋገጠ ወይም የእውነት ቀን" ማለት ነው፦
78፥39 *ይህ የተረጋገጠው ቀን ነው፡፡ የሻም ሰው ወደ ጌታው መመለስን ይይዛል*፡፡ ذَٰلِكَ الْيَوْمُ الْحَقُّ ۖ فَمَن شَاءَ اتَّخَذَ إِلَىٰ رَبِّهِ مَآبًا

“አል-የቂን” الْيَقِين ማለት “እርግጠኝነት” ማለት ሲሆን በሦስት ይከፈላል፥ እርሱም፦
“ዒልመል የቂን” عِلْمَ الْيَقِين ማለትም "እርግጠኛ ዕውቀት"
“ዐይነል የቂን” عَيْنَ الْيَقِين ማለትም "እርግጠኛ ማየት"
“ሐቁል የቂን” حَقُّ الْيَقِين ማለትም "እርግጠኛ እውነት" ነው።
አማንያን ጀነት ውስጥ ያለው ጸጋ መቅመስ፥ ከሃድያን ጀሃነም ውስጥ ያለው ቅጣት መቅመስ ሐቁል የቂን ነው፦
77፥43 *«ትሠሩት በነበራችሁት ዋጋ የምትደሰቱ ኾናችሁ ብሉ፣ ጠጡም፤» ይባላሉ*፡፡ كُلُوا وَاشْرَبُوا هَنِيئًا بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ
46፥34 *እነዚያም የካዱት ሰዎች በእሳት ላይ በሚቀረቡ ቀን «ይህ እውነት አይደለምን?» ይባላሉ፡፡ «እውነት ነው፤ በጌታችን ይኹንብን» ይላሉ፡፡ አላህም «ትክዱ በነበራችሁት ምክንያት ቅጣቱን ቅመሱ» ይላቸዋል”*፡፡ وَيَوْمَ يُعْرَضُ الَّذِينَ كَفَرُوا عَلَى النَّارِ أَلَيْسَ هَـٰذَا بِالْحَقِّ ۖ قَالُوا بَلَىٰ وَرَبِّنَا ۚ قَالَ فَذُوقُوا الْعَذَابَ بِمَا كُنتُمْ تَكْفُرُونَ

ኢንሻሏህ ይቀጥላል.....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የመጨረሻው ቀን

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

50፥42 *ጩኸቲቱን በእውነት የሚሰሙበት ቀን ያ ከመቃብር "የመውጫው ቀን" ነው*፡፡ يَوْمَ يَسْمَعُونَ الصَّيْحَةَ بِالْحَقِّ ۚ ذَٰلِكَ يَوْمُ الْخُرُوجِ

ነጥብ ሦስት
"የውሙል ኹሩጅ"
"የውሙል ኹሩጅ" يَوْمُ الْخُرُوج ማለት "የመውጫው ቀን ነው" ማለት ነው፥ ጠሪው መልአክ በሚጠራበት ቀን ሰዎች ከመቃብራቸው ይወጣሉ፦
53፥6 ከእነርሱም ዙር፡፡ *ጠሪው መልአክ ወደ አስደንጋጭ ነገር የሚጠራበትን ቀን አስታውስ*፡፡ فَتَوَلَّ عَنْهُمْ ۘ يَوْمَ يَدْعُ الدَّاعِ إِلَىٰ شَيْءٍ نُّكُرٍ
50፥41 *"የሚነገርህን አዳምጥም፡፡ ጠሪው ከቅርብ ስፍራ በሚጠራበት ቀን ከመቃብራቸው ይወጣሉ*፡፡ وَاسْتَمِعْ يَوْمَ يُنَادِ الْمُنَادِ مِن مَّكَانٍ قَرِيبٍ
50፥42 *ጩኸቲቱን በእውነት የሚሰሙበት ቀን ያ ከመቃብር "የመውጫው ቀን" ነው*፡፡ يَوْمَ يَسْمَعُونَ الصَّيْحَةَ بِالْحَقِّ ۚ ذَٰلِكَ يَوْمُ الْخُرُوجِ
30፥25 *ሰማይና ምድርም በትዕዛዙ መቆማቸው እና ከዚያም *ከምድር ጥሪን በጠራችሁ ጊዜ እናንተ ወዲያውኑ የምትወጡ መሆናችሁ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው*፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ أَن تَقُومَ السَّمَاءُ وَالْأَرْضُ بِأَمْرِهِ ۚ ثُمَّ إِذَا دَعَاكُمْ دَعْوَةً مِّنَ الْأَرْضِ إِذَا أَنتُمْ تَخْرُجُونَ

"የምትወጡ" ለሚለው የገባው ቃል "ተኽሩጁነ" تَخْرُجُونَ መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል። ጠሪው መልአክ የሚጣራበት የመጀመሪያው መነፋት ወደ አስደንጋጭ ነገር የሚጠራበትን ሲሆን ሁለተኛው መነፋት ሰዎች ከመቃብራቸው የሚወጡበት ነው፦
39፥68 *በቀንዱም ይነፋል፥ በሰማያት ውስጥ ያለው ፍጡር እና በምድርም ውስጥ ያለው ፍጡር ሁሉ አላህ የሻው ሲቀር በድንጋጤ ይሞታል፡፡ ከዚያም በእርሱ ሌላ መንነፋት ይነፋል፥ ወዲያውም እነርሱ የሚሠራባቸውን የሚጠባበቁ ኾነው ቋሚዎች ይኾናሉ*፡፡ وَنُفِخَ فِي الصُّورِ فَصَعِقَ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَمَن فِي الْأَرْضِ إِلَّا مَن شَاءَ اللَّهُ ۖ ثُمَّ نُفِخَ فِيهِ أُخْرَىٰ فَإِذَا هُمْ قِيَامٌ يَنظُرُونَ
36፥51 *"በቀንዱም ይነፋል፥ ወዲያውኑም እነርሱ ከመቃብሮቻቸው ወደ ጌታቸው በፍጥነት ይገሰግሳሉ*፡፡ وَنُفِخَ فِي الصُّورِ فَإِذَا هُم مِّنَ الْأَجْدَاثِ إِلَىٰ رَبِّهِمْ يَنسِلُونَ

ይህ በመለከት ሁለቱን መነፋት የሚነፋው መልአክ "ሷሒቡ አስ-ሱር" صَاحِب الصُّور ማለት "የመለከት ባለቤት" የመላእክት አለቃ ኢሥራፊል ነው።

ነጥብ አራት
"የውመል ቂያማህ"
“ቂያማህ” قِيَٰمَة የሚለው ቃል “ቃመ” قَامَ ማለትም “ተነሣ” ወይም “ቆመ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ትንሣኤ” ማለት ነው። "የውመል ቂያማህ" يَوْمَ الْقِيَامَة ማለት "የትንሣኤ ቀን" ማለት ነው፥ አምላካችን አላህ ስለ ትንሳኤ አጽንዖትና አንክሮት ለመስጠት በትንሣኤ ቀን ምሏል፦
75፥1 *"ነገሩ ከሓዲዎች እንደሚሉት አይደለም፡፡ *"በትንሣኤ ቀን እምላለሁ"*፡፡ لَا أُقْسِمُ بِيَوْمِ الْقِيَامَةِ
23፥16 *"ከዚያም እናንተ "በትንሣኤ ቀን" ትቀሰቀሳላችሁ"*፡፡ ثُمَّ إِنَّكُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ تُبْعَثُونَ
39፥68 *"ከዚያም በእርሱ ሌላ መንነፋት ይነፋል፥ ወዲያውም እነርሱ የሚሠራባቸውን የሚጠባበቁ ኾነው "ቋሚዎች" ይኾናሉ*፡፡ ثُمَّ نُفِخَ فِيهِ أُخْرَىٰ فَإِذَا هُمْ قِيَامٌ يَنظُرُونَ

"ቃኢም" قَآئِم ማለት "ቃሚ" ማለት ነው፥ የቃኢም ብዙ ቁጥር ደግሞ "ቂያም" قِيَام ማለት ሲሆን "ቋሚዎች" ማለት ነው። ትንሳኤ እንዳለ በዕውቀት ያወቁ እና በእምነት ያመኑ የዕውቀት እና የእምነት ባለቤቶች እነዚያ የካዱትን በትንሳኤ ቀን፦ "ይህም የካዳችሁት የትንሣኤ ቀን ነው፡፡ ግን እናንተ የማታውቁ ነበራችሁ" ይሏቸዋል፥ እነዚያ የካዱት በትንሣኤ ቀን ሙስሊሞች በኾኑ ኖሩ በብዛት ይመኛሉ። እነርሱ "ከአላህ ሌላ አምላክ የለም" በተባሉ ጊዜ ይኮሩ ነበሩ፦
30፥56 *እነዚያንም ዕውቀትንና እምነትን የተሰጡት «በአላህ መጽሐፍ (ፍርድ) እስከ ትንሣኤ ቀን በእርግጥ ቆያችሁ፡፡ ይህም የካዳችሁት የትንሣኤ ቀን ነው፡፡ ግን እናንተ የማታውቁ ነበራችሁ» ይሏቸዋል*፡፡ وَقَالَ الَّذِينَ أُوتُوا الْعِلْمَ وَالْإِيمَانَ لَقَدْ لَبِثْتُمْ فِي كِتَابِ اللَّهِ إِلَىٰ يَوْمِ الْبَعْثِ ۖ فَهَـٰذَا يَوْمُ الْبَعْثِ وَلَـٰكِنَّكُمْ كُنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ
15፥2 *"እነዚያ የካዱት በትንሣኤ ቀን ሙስሊሞች በኾኑ ኖሩ በብዛት ይመኛሉ"*፡፡ رُّبَمَا يَوَدُّ الَّذِينَ كَفَرُوا لَوْ كَانُوا مُسْلِمِينَ
37፥35 *እነርሱ "ከአላህ ሌላ አምላክ የለም" በተባሉ ጊዜ ይኮሩ ነበሩ*፡፡ إِنَّهُمْ كَانُوا إِذَا قِيلَ لَهُمْ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّهُ يَسْتَكْبِرُونَ
ነጥብ አምስት
"የውሚድ ዲን"
“ዲን” دِين የሚለው ቃል “ዳነ” دَانَ ማለትም “ፈረደ” “በየነ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ሃይማኖት” “ፍትሕ” “ፍርድ” “ሕግ” “መርሕ” ማለት ነው። "የውሚድ ዲን" يَوْمِ الدِّين ማለት "የፍርዱ ቀን" ማለት ነው፦
1፥4 *"የፍርዱ ቀን" ባለቤት ለኾነው"*፡፡ مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ
37፥20 *«ዋ ጥፋታችን! ይህ "የፍርዱ ቀን" ነው» ይላሉም*፡፡ وَقَالُوا يَا وَيْلَنَا هَـٰذَا يَوْمُ الدِّينِ
56፥6 *"ፍርድን ማግኘትም የማይቀር ነው"*፡፡ وَإِنَّ الدِّينَ لَوَاقِعٌ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ፍርድ" ለሚለው ቃል የገባው በአመልካች መስተአምር "አድ-ዲን" الدِّين መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። “ዲን” دِين ሦስት ደረጃ አለው፥ እርሱም፦
“ኢሥላም” إِسْلَٰم
“ኢማን” إِيمَٰن
“ኢሕሣን” إِحْسَٰن ናቸው።
ዲን ለአላህ ብቻ በማጥራት አላህን ማምለክ ነው፦
39፥11 በል «እኔ *አላህን ሃይማኖትን ለእርሱ ያጠራሁ ኾኜ እንዳመልከው ታዘዝኩ"*፡፡ قُلْ إِنِّي أُمِرْتُ أَنْ أَعْبُدَ اللَّهَ مُخْلِصًا لَّهُ الدِّينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ያጠራ" ለሚለው ቃል የገባው "ሙኽሊስ" مُخْلِص ነው። "ኢኽላስ" إِخْلَاص የሚለው ቃል "ኸለሰ" خَلَصَ ማለትም "ጠራ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን ከእዩልኝ እና ከስሙልኝ፥ ከወቀሳ እና ከሙገሳ ነጻ ሆኖ ዲንን ለአላህ ብቻ "ማጥራት" ማለት ነው። ዒባዳን በኢኽላስ የሚሠራ ሙሥሊም "ሙኽሊስ" مُخْلِص ይባላል። አላህ ዘንድ ዲን ኢሥላም ብቻ ነው፥ ከኢሥላም ዲን ሌላ ዲንን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከእርሱ ተቀባይ የለውም፡፡ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው፦
3፥19 *አላህ ዘንድ ሃይማኖት ኢሥላም ብቻ ነው*፡፡ إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ
3፥85 *ከኢሥላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከእርሱ ተቀባይ የለውም፡፡ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው*፡፡ وَمَن يَبْتَغِ غَيْرَ الْإِسْلَامِ دِينًا فَلَن يُقْبَلَ مِنْهُ وَهُوَ فِي الْآخِرَةِ مِنَ الْخَاسِرِينَ

ነጥብ ስድስት
"የውመል ፈትሕ"
"የውመል ፈትሕ" يَوْمَ الْفَتْح ማለት "የፍርድ ቀን" ማለት ነው፥ በቁርኣን ከተገለጹ የአላህ ስሞች መካከል "አል-ፈታሕ" الْفَتَّاح ማለትም "ፈራጁ" ነው፦
32፥29 *«"በፍርድ ቀን" እነዚያን የካዱትን ሰዎች እምነታቸው አይጠቅማቸውም፡፡ እነርሱም ጊዜን አይሰጡም»* በላቸው፡፡ قُلْ يَوْمَ الْفَتْحِ لَا يَنفَعُ الَّذِينَ كَفَرُوا إِيمَانُهُمْ وَلَا هُمْ يُنظَرُونَ
34፥26 *«ጌታችን በመካከላችን ይሰበስባል፡፡ ከዚያም በመካከላችን በእውነት ይፈርዳል፡፡ እርሱም በትክክል ፈራጁ ዐዋቂው ነው»* በላቸው፡፡ قُلْ يَجْمَعُ بَيْنَنَا رَبُّنَا ثُمَّ يَفْتَحُ بَيْنَنَا بِالْحَقِّ وَهُوَ الْفَتَّاحُ الْعَلِيمُ

"ፈትሕ" فَتْح የሚለው ቃል "ፈተሐ" فَتَحَ ማለትም "ከፈተ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መክፈት" ማለት ነው፥ "መፋቲሕ" مَفَاتِح ማለት እራሱ "መክፈቻ" ማለት ነው። ቁርኣን ላይ ተመሳሳይ ቃል ቢኖረው እንኳን ተመሳሳይ አሳብና ትርጉም አለው ማለት አይደለም፥ የአንድን ቃል አማራጭ ትርጉም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ ቅቡል ነው። መታየት ያለበት ቃሉ ሳይሆን ቃሉ የወከለው አሳብ ነው፥ እዚህ ዐውድ ላይ "ፈትሕ" فَتْح ማለት "ፍርድ" ማለት ነው፦
26፥118 *«በእኔ እና በእነርሱም መካከል ፍርድን "ፍረድ"! አድነኝም!፡፡ ከእኔ ጋር ያሉትን ምእምናንም፡፡»* فَافْتَحْ بَيْنِي وَبَيْنَهُمْ فَتْحًا وَنَجِّنِي وَمَن مَّعِيَ مِنَ الْمُؤْمِنِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ፍረድ" ለሚለው ግስ የገባው ቃል "ኢፍተሕ" افْتَحْ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። በፍርድ ቀን ለካፊር ይፈረድበታል፥ ለሙእሚን ይፈረድለታል።
ኢንሿላህ ይቀጥላል......

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የመጨረሻው ቀን

ገቢር ሦስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

42፥7 እንደዚሁም የከተሞች እናት የኾነችውን እና በአካባቢዋ ያሉትንም ልታስጠነቅቅ *የመሰብሰቢያውንም ቀን በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲኾን ልታስጠነቅቅ ዐረብኛ የኾነን ቁርኣን ወደ አንተ አወረድን*፡፡ وَكَذَٰلِكَ أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لِّتُنذِرَ أُمَّ الْقُرَىٰ وَمَنْ حَوْلَهَا وَتُنذِرَ يَوْمَ الْجَمْعِ لَا رَيْبَ فِيهِ

ነጥብ ሰባት
"የውሙል ጀምዕ"
"የውመል ጀምዕ" يَوْم الْجَمْع ማለት "የመሰብሰቢያውንም ቀን" ማለት ነው፦
42፥7 እንደዚሁም የከተሞች እናት የኾነችውን እና በአካባቢዋ ያሉትንም ልታስጠነቅቅ *የመሰብሰቢያውንም ቀን በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲኾን ልታስጠነቅቅ ዐረብኛ የኾነን ቁርኣን ወደ አንተ አወረድን*፡፡ وَكَذَٰلِكَ أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لِّتُنذِرَ أُمَّ الْقُرَىٰ وَمَنْ حَوْلَهَا وَتُنذِرَ يَوْمَ الْجَمْعِ لَا رَيْبَ فِيهِ

“አሐድ” أحَد ማለት “አንድ” ማለት ነው፣
“ኢስነይን” اِثْنَيْن‎ ማለት “ሁለት” ማለት ነው፣
“ሱላሳእ” ثُّلَاثَاء ማለት “ሦስት” ማለት ነው፣
“አርቢዓእ” أَرْبِعَاء ማለት “አራት” ማለት ነው፣
“ኸሚሥ” خَمِيس ማለት “አምስት” ማለት ነው፣
“ጁሙዓህ” جُمُعَة ማለት ደግሞ “ስብስብ” ማለት ነው፥ "የውሙል ጁሙዓህ" يَوْمُ الْجُمُعَة ማለት እራሱ "የስብስብ ቀን" ማለት ነው። አደም የተፈጠረው በጁሙዓህ ቀን ነው፥ ቂያማህ የሚቆመውም በጁሙዓህ ቀን ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 4, ሐዲስ 1
አቡ ሁራይራህ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"መልካም ቀን ፀሐይ ከወጣችበት የጁሙዓህ ቀን ነው፥ በዚያ ቀን አደም ተፈጠረ፣ በዚያ ቀን ወደ ጀነት ገብቷል፥ ከጀነት በዚያ ቀን ወጥቷል፣ ሰዓቲቱ በጁሙዓህ ቀን እንጂ አትቆምም"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ خَيْرُ يَوْمٍ طَلَعَتْ فِيهِ الشَّمْسُ يَوْمُ الْجُمُعَةِ فِيهِ خُلِقَ آدَمُ وَفِيهِ أُدْخِلَ الْجَنَّةَ وَفِيهِ أُخْرِجَ مِنْهَا وَلاَ تَقُومُ السَّاعَةُ إِلاَّ فِي يَوْمِ الْجُمُعَةِ ‏"‏

አምላካችን አላህ በመሰብሰቢያውንም ቀን ሰውን ሁሉ ሰብሳቢ ነው፥ ጌታችን በመካከላችን ይሰበስባል፡፡ ከዚያም በመካከላችን በእውነት ይፈርዳል፦
3፥9 «ጌታችን ሆይ! *አንተ በእርሱ ለመምጣቱ ጥርጥር የሌለበት በኾነ ቀን ሰውን ሁሉ ሰብሳቢ ነህ*፡፡ ምንጊዜም አላህ ቀጠሮውን አያፈርስምና፡፡» رَبَّنَا إِنَّكَ جَامِعُ النَّاسِ لِيَوْمٍ لَّا رَيْبَ فِيهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ لَا يُخْلِفُ الْمِيعَادَ
34፥26 *«ጌታችን በመካከላችን ይሰበስባል፡፡ ከዚያም በመካከላችን በእውነት ይፈርዳል፡፡ እርሱም በትክክል ፈራጁ ዐዋቂው ነው»* በላቸው፡፡ قُلْ يَجْمَعُ بَيْنَنَا رَبُّنَا ثُمَّ يَفْتَحُ بَيْنَنَا بِالْحَقِّ وَهُوَ الْفَتَّاحُ الْعَلِيمُ

ትክክለኛ ፈራጅ እርሱ ብቻ ስለሆነ በዚያ ቀን ለፍርድ ይሰበስባል፥ ያ ቀን መምጣቱ ጥርጥር የለበትም፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች ዐያውቁም፦
4፥26 *«አላህ ሕያው ያደርጋችኋል፥ ከዚያም ያሞታል። ከዚያም ወደ ትንሣኤ ቀን ይሰበስባችኋል፥ በእርሱ ጥርጥር የለበትም፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች ዐያውቁም»* በላቸው፡፡ قُلِ اللَّهُ يُحْيِيكُمْ ثُمَّ يُمِيتُكُمْ ثُمَّ يَجْمَعُكُمْ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ لَا رَيْبَ فِيهِ وَلَـٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ
4፥87 አላህ ከእርሱ በስተቀር አምላክ የለም፡፡ *"ወደ ትንሣኤ ቀን በእርሱ ጥርጥር የሌለበት ሲኾን በእርግጥ ይሰበስባችኋል"*፡፡ በንግግርም ከአላህ ይበልጥ እውነተኛ ማነው? اللَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ لَيَجْمَعَنَّكُمْ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ لَا رَيْبَ فِيهِ ۗ وَمَنْ أَصْدَقُ مِنَ اللَّهِ حَدِيثًا

ነጥብ ስምንት
"የውሙል ፈስል"
"የውሙል ፈስል" يَوْمُ الْفَصْل ማለት የመለያው ቀን" ማለት ነው፥ የመለያው ቀን ለሁሉም ቀጠሯቸው ነው፦
44፥40 *"የመለያው ቀን" ለሁሉም ቀጠሯቸው ነው"*፡፡ إِنَّ يَوْمَ الْفَصْلِ مِيقَاتُهُمْ أَجْمَعِينَ

አምላካችን አላህ በመለያው ቀን አማንያንን ወደ ጀነት በማስገባት፥ ከሃድያንን ወደ እሳት በማስገባት በፍርድ ይለያል፦
32፥25 *ጌታህ እርሱ በዚያ በእርሱ ይለያዩበት በነበሩት ነገር በትንሣኤ ቀን በመካከላቸው በፍርድ ይለያል*፡፡ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ يَفْصِلُ بَيْنَهُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ فِيمَا كَانُوا فِيهِ يَخْتَلِفُونَ
22፥17 *እነዚያ ያመኑት፣ እነዚያም ይሁዳውያን የሆኑ፣ ሳቢያኖችም፣ ክርስቲያኖችም፣ መጁሶችም፣ እነዚያም ያጋሩ አላህ በትንሣኤ ቀን በመካከላቸው በፍርድ ይለያል*፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ በእርግጥ ዐዋቂ ነውና፡፡ إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَالَّذِينَ هَادُوا وَالصَّابِئِينَ وَالنَّصَارَىٰ وَالْمَجُوسَ وَالَّذِينَ أَشْرَكُوا إِنَّ اللَّهَ يَفْصِلُ بَيْنَهُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ شَهِيدٌ

ከሃድያን አስተባባዮች ስለሆኑ "ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉ የነበራችሁት "የመለያው ቀን" ነው" ይባላሉ፦
77፥14 *የመለያውም ቀን ምን እንደኾነ ምን አሳወቀህ?* وَمَا أَدْرَاكَ مَا يَوْمُ الْفَصْلِ
77፥15 ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ وَيْلٌ يَوْمَئِذٍ لِّلْمُكَذِّبِينَ
37፥21 *«ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉ የነበራችሁት "የመለያው ቀን" ነው»* ይባላሉ፡፡ هَـٰذَا يَوْمُ الْفَصْلِ الَّذِي كُنتُم بِهِ تُكَذِّبُونَ
ነጥብ ዘጠኝ
"የውመት ተላቅ"
"የውመት ተላቅ" يَوْمَ التَّلَاق ማለት "የመገናኛውን ቀን" ማለት ነው፦
40፥15 *"እርሱ ደረጃዎችን ከፍ አድራጊ የዐርሹ ባለቤት ነው፡፡ "የመገናኛውን ቀን" ያስጠነቅቅ ዘንድ ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ ከትዕዛዙ መንፈስን ያወርዳል*፡፡ رَفِيعُ الدَّرَجَاتِ ذُو الْعَرْشِ يُلْقِي الرُّوحَ مِنْ أَمْرِهِ عَلَىٰ مَن يَشَاءُ مِنْ عِبَادِهِ لِيُنذِرَ يَوْمَ التَّلَاقِ

ሰው አላህን ተገናኝቶ በሠራው ሰናይ ሥራ ወይም በሠራው እኩይ ሥራ ከጌታው ይተሳሰባል፦
84፥6 *"አንተ ሰው ሆይ! አንተ "ጌታህን እስከምትገናኝ" ድረስ ልፋትን ለፊ ነህ፥ "ተገናኚውም" ነህ"*፡፡ يَا أَيُّهَا الْإِنسَانُ إِنَّكَ كَادِحٌ إِلَىٰ رَبِّكَ كَدْحًا فَمُلَاقِيهِ

ሶላት መስገድ ጌታቸውን የሚገናኙ መኾናቸውን በዕውቀት የሚያረጋግጡ በኾኑት ላይ ቀላል ናት፥ ግን አላህን አግኝቼ ይተሳሰበኛል ብሎ እርግጠኛ ባልሆነ ላይ ግን ከባድ ናት፦
2፥46 *(ሶላት) እነዚያ "ጌታቸውን የሚገናኙ እነርሱም ወደ እርሱ ተመላሾች መኾናቸውን የሚያረጋግጡ በኾኑት ላይ እንጅ ከባድ ናት*፡፡ الَّذِينَ يَظُنُّونَ أَنَّهُم مُّلَاقُو رَبِّهِمْ وَأَنَّهُمْ إِلَيْهِ رَاجِعُونَ

እኩያን ለእነርሱ፦ "ስገዱም" በተባሉ ጊዜ አይሰግዱም ነበር፥ ቅጣቱን ሲቀምሱ፦ ”ከሰጋጆቹ አልነበርንም" ይላሉ፦
77፥48 *"«ለእነርሱ ስገዱም» በተባሉ ጊዜ አይሰግዱም"*፡፡ وَإِذَا قِيلَ لَهُمُ ارْكَعُوا لَا يَرْكَعُونَ
74፥43 እነርሱም ይላሉ፦ *”ከሰጋጆቹ አልነበርንም”*፡፡ قَالُوا لَمْ نَكُ مِنَ الْمُصَلِّين

ነጥብ አስር
"የውሚል ሒሣብ"
"የውሚል ሒሣብ" يَوْمِ الْحِسَاب ማለት "የመተሳሰቢያ ወይም የምርመራ ቀን" ማለት ነው፦
38፥52 *"ይህ ለምርመራው ቀን የምትቀጠሩት ተስፋ ነው"*፡፡ هَـٰذَا مَا تُوعَدُونَ لِيَوْمِ الْحِسَابِ

"ሒሣብ" حِسَاب የሚለው ቃል "ሐሢበ" حَسِبَ ማለትም "መረመረ" "ተቆጣጠረ" ተሳሰበ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ምርመራ" "ቁጥጥር" "መተሳሰብ" "ማወራረድ" ማለት ነው። በቁርኣን ከተገለጹ የአላህ ውብ ስሞች መካከል "አል-ሐሢብ" الْحَسِيب ሲሆን "ተቆጣጣሪ" "መርማሪ" "ተሳሳቢ" ማለት ነው፦
4፥86 በሰላምታ በተከበራችሁም ጊዜ ከእርሷ ይበልጥ ባማረ ሰላምታ አክብሩ፡፡ ወይም እርሷኑ መልሷት፡፡ *"አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ተቆጣጣሪ ነውና"*፡፡ وَإِذَا حُيِّيتُم بِتَحِيَّةٍ فَحَيُّوا بِأَحْسَنَ مِنْهَا أَوْ رُدُّوهَا ۗ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ حَسِيبًا
2፥284 *በሰማያት ውስጥና በምድርም ውስጥ ያለው ሁሉ የአላህ ነው፡፡ በራሳችሁ ውስጥ ያለውን ብትገልጹ ወይም ብትደብቁት አላህ በእርሱ ይቆጣጠራችኋል*፡፡ لِّلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۗ وَإِن تُبْدُوا مَا فِي أَنفُسِكُمْ أَوْ تُخْفُوهُ يُحَاسِبْكُم بِهِ اللَّهُ

"ይቆጣጠራችኋል" ለሚለው የገባው ቃል "ዩሓሢብኩም" يُحَاسِبْكُم መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። በራሳችን ውስጥ ያለውን ብንገልጽ ወይም ብንደብቅ አምላካችን አላህ በእርሱ ማለትም በችሎታው ይቆጣጠረናል። እንዲሁ የፍርዱ ቀን ሰዎች የሠሩት ኸይር ሥራ፥ ወይም ሸር ሥራ ይተሳሰባል።
ኢንሿላህ ይቀጥላል......

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የመጨረሻው ቀን

ገቢር አራት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

50፥20 *"በቀንዱም ውስጥ ይነፋል፥ ያ ቀን የዛቻው ቀን ነው"*፡፡ وَنُفِخَ فِي الصُّورِ ۚ ذَٰلِكَ يَوْمُ الْوَعِيدِ

ነጥብ አሥራ አንድ
"የውመት ተናድ"
"የውመት ተናድ" يَوْمَ التَّنَاد ማለት "የመጠራሪያን ቀን" ማለት ነው፦
40፥32 *«ሕዝቦቼ ሆይ! እኔ በእናንተ ላይ የመጠራሪያን ቀን እፈራለሁ»* አላቸው። وَيَا قَوْمِ إِنِّي أَخَافُ عَلَيْكُمْ يَوْمَ التَّنَادِ

"እፈራለው" ያለው በመጠራሪያን ቀን የሚኖረውን የመጨረሻውን ቀን ቅጣት ነው፥ "የመጨረሻውንም ቀን ፍሩ" ተብሏል፦
11፥103 *"በዚህ ውስጥ የመጨረሻውን ቀን ቅጣት ለሚፈሩ ሁሉ መገሰጫ አለ"*፡፡ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لِّمَنْ خَافَ عَذَابَ الْآخِرَةِ
29፥36 ወደ መድየንም ወንድማቸውን ሹዐይብን ላክን፦ *«ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን አምልኩ! "የመጨረሻውንም ቀን" ፍሩ! በምድርም ውስጥ የምታጠፉ ሆናችሁ አታበላሹ»* አላቸውም፡፡ وَإِلَىٰ مَدْيَنَ أَخَاهُمْ شُعَيْبًا فَقَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ وَارْجُوا الْيَوْمَ الْآخِرَ وَلَا تَعْثَوْا فِي الْأَرْضِ مُفْسِدِينَ

"በእናንተ ላይ የመጠራሪያን ቀን" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። ሕዝቦቼ በክህደት ከቀጠሉ እና የእሳት ሰዎች ከሆኑ የጀነት ሰዎች የእሳትን ሰዎችን፦ "ጌታችን ቃል የገባልንን እውነት ኾኖ አገኘን፥ ጌታችሁ የዛተባችሁንስ እውነት ኾኖ አገኛችሁትን? ሲሉ ይጣራሉ፦
7፥44 *"የገነትም ሰዎች የእሳትን ሰዎችን «ጌታችን ቃል የገባልንን እውነት ኾኖ አገኘን፥ ጌታችሁ የዛተባችሁንስ እውነት ኾኖ አገኛችሁትን?» ሲሉ "ይጣራሉ"*፡፡ «አዎን አገኘን» ይላሉ፡፡ በመካከላቸውም «የአላህ ርግማን በበደለኞች ላይ ይኹን» ሲል ለፋፊ ይለፍፋል፡፡ وَنَادَىٰ أَصْحَابُ الْجَنَّةِ أَصْحَابَ النَّارِ أَن قَدْ وَجَدْنَا مَا وَعَدَنَا رَبُّنَا حَقًّا فَهَلْ وَجَدتُّم مَّا وَعَدَ رَبُّكُمْ حَقًّا ۖ قَالُوا نَعَمْ ۚ فَأَذَّنَ مُؤَذِّنٌ بَيْنَهُمْ أَن لَّعْنَةُ اللَّهِ عَلَى الظَّالِمِينَ

"ይጣራሉ" የሚለው ይሰመርበት። በጀነት ሰዎች እና በእሳትን ሰዎች መካከል ግርዶች አለ፥ ይህ ቦታ "አዕራፍ" أَعْرَاف ይባላል። በዚህ ቦታ ሰናይና እኩይ ሥራቸው በሚዛን እኩል የሆኑት ሰዎች "አስሓቡል አዕራፍ" أَصْحَابُ الْأَعْرَاف ይባላሉ፥ የጀነት ሰዎች የአዕራፍ ሰዎችን፦ "ሰላም ለእናንተ ይኹን" በማለት ይጣራሉ፦
7፥46 በመካከላቸውም ግርዶሽ አልለ፡፡ በአዕራፍም ላይ ሁሉንም በምልክታቸው የሚያውቁ ሰዎች አሉ፡፡ የገነትንም ሰዎች ሰላም ለእናንተ ይኹን በማለት ይጣራሉ፡፡ እነርሱም የአዕራፍ ሰዎች የሚከጅሉ ሲኾኑ ገና አልገቧትም፡፡ وَبَيْنَهُمَا حِجَابٌ ۚ وَعَلَى الْأَعْرَافِ رِجَالٌ يَعْرِفُونَ كُلًّا بِسِيمَاهُمْ ۚ وَنَادَوْا أَصْحَابَ الْجَنَّةِ أَن سَلَامٌ عَلَيْكُمْ ۚ لَمْ يَدْخُلُوهَا وَهُمْ يَطْمَعُونَ

ነጥብ አሥራ ሁለት
"የውሙል ወዒድ"
"የውሙል ወዒድ" يَوْمُ الْوَعِيد ማለት "የዛቻው ቀን" ማለት ነው፦
50፥20 *"በቀንዱም ውስጥ ይነፋል፥ ያ ቀን የዛቻው ቀን ነው"*፡፡ وَنُفِخَ فِي الصُّورِ ۚ ذَٰلِكَ يَوْمُ الْوَعِيدِ

በሃይማኖት ማስገደድ የለም፥ ቅኑ መንገድ ከጠማማው ተገልጧል። የሻም ሰው ይመን፥ የሻም ሰው ይካድ፦
2፥256 *በሃይማኖት ማስገደድ የለም፥ ቅኑ መንገድ ከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ*፡፡ لَا إِكْرَاهَ فِي الدِّينِ ۖ قَد تَّبَيَّنَ الرُّشْدُ مِنَ الْغَيِّ
18፥29 *«እውነቱም ከጌታችሁ ነው፡፡ የሻም ሰው ይመን፥ የሻም ሰው ይካድ»* በላቸው፡፡ وَقُلِ الْحَقُّ مِن رَّبِّكُمْ ۖ فَمَن شَاءَ فَلْيُؤْمِن وَمَن شَاءَ فَلْيَكْفُرْ

"የሻም ሰው ይመን፥ የሻም ሰው ይካድ" ማለት ዛቻ ነው። በግድ እምኑ በማለት በእነርሱ ላይ አስገዳጅ አይደለንም፥ የአላህ ዛቻ የሚፈራን ሰው በቁርኣን ማስታወስ ብቻ ነው፥ ከዚያም በዛቻው ቀን የገነትም ሰዎች የእሳትን ሰዎችን፦ ጌታችሁ "የዛተባችሁንስ" እውነት ኾኖ አገኛችሁትን? ሲሉ ይጣራሉ፦
50፥45 እኛ የሚሉትን ሁሉ ዐዋቂ ነን፡፡ *"አንተም በእነርሱ ላይ አስገዳጅ አይደለህም፡፡ ስለዚህ ዛቻዬን የሚፈራን ሰው በቁርኣን አስታውስ*፡፡ نَّحْنُ أَعْلَمُ بِمَا يَقُولُونَ ۖ وَمَا أَنتَ عَلَيْهِم بِجَبَّارٍ ۖ فَذَكِّرْ بِالْقُرْآنِ مَن يَخَافُ وَعِيدِ
7፥44 *"የገነትም ሰዎች የእሳትን ሰዎችን «ጌታችን ቃል የገባልንን እውነት ኾኖ አገኘን፥ ጌታችሁ "የዛተባችሁንስ" እውነት ኾኖ አገኛችሁትን?» ሲሉ "ይጣራሉ"*፡፡ «አዎን አገኘን» ይላሉ፡፡ በመካከላቸውም «የአላህ ርግማን በበደለኞች ላይ ይኹን» ሲል ለፋፊ ይለፍፋል፡፡ وَنَادَىٰ أَصْحَابُ الْجَنَّةِ أَصْحَابَ النَّارِ أَن قَدْ وَجَدْنَا مَا وَعَدَنَا رَبُّنَا حَقًّا فَهَلْ وَجَدتُّم مَّا وَعَدَ رَبُّكُمْ حَقًّا ۖ قَالُوا نَعَمْ ۚ فَأَذَّنَ مُؤَذِّنٌ بَيْنَهُمْ أَن لَّعْنَةُ اللَّهِ عَلَى الظَّالِمِينَ

አላህ በቁርኣን ዝቶበት የነበረው ቀን ሲመጣ ያ ቀን የዛቻው ቀን ነው። ካፊሮች አንዱ ሌላውን በመውቀስ ሲጨቃጨቁ አላህ፦ "ወደ እናንተ ዛቻን በእርግጥ ያስቀደምኩ ስኾን እኔ ዘንድ አትጨቃጨቁ" ይላቸዋል፥ ቀድሞውኑ አላህ፦ "እኛ ለበደለኞች አጥሯ በእነርሱ የከበበ የኾነችውን እሳት አዘጋጅተናል፥ ከጥም እርዳታንም ቢፈልጉ እንደ ዘይት ዝቃጭ ባለ ፊቶችን በሚጠብስ ውሃ ይረዳሉ፡፡ መጠጡ ከፋ፥ መደገፊያይቱም ምንኛ አስከፋች" ብሎ ተናግሯል፦
50፥28 *"አላህ «ወደ እናንተ ዛቻን በእርግጥ ያስቀደምኩ ስኾን እኔ ዘንድ አትጨቃጨቁ» ይላቸዋል*፡፡ قَالَ لَا تَخْتَصِمُوا لَدَيَّ وَقَدْ قَدَّمْتُ إِلَيْكُم بِالْوَعِيدِ
18፥29 *«እውነቱም ከጌታችሁ ነው፡፡ የሻም ሰው ይመን፤ የሻም ሰው ይካድ» በላቸው፡፡ እኛ ለበደለኞች አጥሯ በእነርሱ የከበበ የኾነችውን እሳት አዘጋጅተናል፥ ከጥም እርዳታንም ቢፈልጉ እንደ ዘይት ዝቃጭ ባለ ፊቶችን በሚጠብስ ውሃ ይረዳሉ፡፡ መጠጡ ከፋ፥ መደገፊያይቱም ምንኛ አስከፋች*። وَقُلِ الْحَقُّ مِن رَّبِّكُمْ ۖ فَمَن شَاءَ فَلْيُؤْمِن وَمَن شَاءَ فَلْيَكْفُرْ ۚ إِنَّا أَعْتَدْنَا لِلظَّالِمِينَ نَارًا أَحَاطَ بِهِمْ سُرَادِقُهَا ۚ وَإِن يَسْتَغِيثُوا يُغَاثُوا بِمَاءٍ كَالْمُهْلِ يَشْوِي الْوُجُوهَ ۚ بِئْسَ الشَّرَابُ وَسَاءَتْ مُرْتَفَقًا