የሙሴ አምላክ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
10፥3 *ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው*፡፡ ከዚያም ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብር ሲኾን በዐርሹ ላይ ተደላደለ፡፡ ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም፡፡ እነሆ! *”አላህ ጌታችሁ ነውና አምልኩት*፤ አትገሰጹምን? إِنَّ رَبَّكُمُ ٱللَّهُ ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ فِى سِتَّةِ أَيَّامٍۢ ثُمَّ ٱسْتَوَىٰ عَلَى ٱلْعَرْشِ ۖ يُدَبِّرُ ٱلْأَمْرَ ۖ مَا مِن شَفِيعٍ إِلَّا مِنۢ بَعْدِ إِذْنِهِۦ ۚ ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمْ فَٱعْبُدُوهُ ۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ
እኛ ሙስሊሞች ክርስቲያኖችን፦ “ኢየሱስ፦ እኔ አምላክ ነኝ፥ አምልኩኝ” ያለበት ጥቅስ ከባይብል አሳዩን ስላቸው፤ እንደዛ የሚልበት አንቀፅ እንደሌለ ሲያውቁት በእጅ አዙር ልከክልህ እከክልኝ በሚል ስሁት ሙግት አላህ፦ “እኔ እኔ አምላክ ነኝ፥ አምልኩኝ” ያለበት ጥቅስ ከቁርአን አሳዩን ብለው እህህና አሄሄ እያሉ ያለቃቅሳሉ፤ ቁርአን ላይ በቁና ጥቅስ አላህ፦ “እኔ አምላክ ነኝ፥ አምልኩኝ” ያለበት አናቅጽ ማቅረብ ይቻላል፤ ጥንትም ሙሳን ሲያናግር የነበረው የሙሳ አምላክ አላህ እራሱ ነው፤ አላህ ለሙሳ፦ “እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና አምልከኝ” ብሎታል፦
20፥14 *«እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና አምልከኝ*፡፡ ሶላትንም በእርሷ እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡ إِنَّنِىٓ أَنَا ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدْنِى وَأَقِمِ ٱلصَّلَوٰةَ لِذِكْرِىٓ
“ይህ እኮ ሙሳን ነው ያለው” የሚል ምላሽ ይሰጣል፤ ታዲያ እኮ ሙሳን ያናገረው አላህ እንደሆነ ቁርአን ይናገራል፤ የተፈለገው አላህ፦ “እኔ እኔ አምላክ ነኝ፥ አምልኩኝ” ያለበት ጥቅስ ነው፤ በተጨማሪም ሙሳን “እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና አምልከኝ” ብሎ የተናገረው ነብያችንን”ﷺ” የሚያናግር አላህ ለመሆኑ ሁለት ነጥቦችን ማየት እንችላለን፦
ነጥብ አንድ
“ተጠራ”
አላህ ለሙሳ፦ “እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና አምልከኝ” ብሎ ከማለቱ በፊት «ሙሳ ሆይ» በማለት ጠርቶታል፦
20፥11 በመጣም ጊዜ «ሙሳ ሆይ» በማለት *”ተጠራ*፡፡ فَلَمَّآ أَتَىٰهَا نُودِىَ يَٰمُوسَىٰٓ
ይህንን ጥሪ ጠርቶ ያነጋገረው እራሱ እንደሆነ በመጀመሪያ መደብ ለነብያችን”ﷺ”፦ “ጠራነው፤ ያነጋገርነውም ሲኾን አቀረብነው” በማለት ሙሴን የጠራው እርሱ እንደሆነ ይናገራል፦
19፥51 በመጽሐፉ ውስጥ *ሙሳንም አውሳ*፡፡ እርሱ ምርጥ ነበርና፡፡ መልክተኛ ነቢይም ነበር፡፡ وَٱذْكُرْ فِى ٱلْكِتَٰبِ مُوسَىٰٓ ۚ إِنَّهُۥ كَانَ مُخْلَصًۭا وَكَانَ رَسُولًۭا نَّبِيًّۭا
19፥52 ከጡር ቀኝ ጎን በኩልም *ጠራነው፤ ያነጋገርነውም* ሲኾን አቀረብነው፡፡ وَنَٰدَيْنَٰهُ مِن جَانِبِ ٱلطُّورِ ٱلْأَيْمَنِ وَقَرَّبْنَٰهُ نَجِيًّۭا
ነጥብ ሁለት
“የሚወረድልህንም”
አላህ ሙሳን፦ “እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና አምልከኝ” ብሎ ከማለቱ በፊት “የሚወረድልህንም ነገር አዳምጥ” ብሎታል፦
20፥13 «እኔም መረጥኩህ፤ *”የሚወረድልህንም”* ነገር አዳምጥ፡፡ وَأَنَا ٱخْتَرْتُكَ فَٱسْتَمِعْ لِمَا يُوحَىٰٓ
አላህ ከዚህ በፊት ለመልእክተኛ ምን ብሎ እንደሚያወርድ ሲናገር “ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ” በማለት እራሱ ወሕይ እንደሚያወርድ ለነብያችን”ﷺ” ይነግራቸዋል፦
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ *”ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ”* በማለት ወደ እርሱ *”የምናወርድለት”* ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ
ነጥብ ሶስት
“አምልኩኝ”
አላህ በመጀመሪያ መደብ “አዕቡዱኒ” َٱعْبُدُونِ “አምልኩኝ” ብሎ ይናገራል፤ በተጨማሪም በሶስተኛ መደብ ስለ እራሱ ሲናገር “አዕቡዱሁ” َٱعْبُدُوهُ “አምልኩት” ብሎ ይናገራል፦
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ *”እኔንም ብቻ አምልኩኝ”*፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ
21፥92 ይህች አንዲት መንገድ ስትሆን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት፤ *”እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ”*፡፡ إِنَّ هَٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمْ أُمَّةًۭ وَٰحِدَةًۭ وَأَنَا۠ رَبُّكُمْ فَٱعْبُدُونِ
6፥102 ይህ *”ጌታችሁ አላህ ነው፤ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፤ ነገርን ሁሉ ፈጣሪ ነው፤ ስለዚህ አምልኩት”*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው፡፡ ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمْ ۖ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ خَٰلِقُ كُلِّ شَىْءٍۢ فَٱعْبُدُوهُ ۚ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍۢ وَكِيلٌۭ
✍ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ወሰላሙ አለይኩም

አል-አወል ወል-አኺር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
57፥3 *"እርሱ ፊትም ያለ፣ ኋላም ቀሪ፣ ግልጽም፣ ስውርም ነው፡፡ እርሱም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው"*፡፡ هُوَ الْأَوَّلُ وَالْآخِرُ وَالظَّاهِرُ وَالْبَاطِنُ ۖ وَهُوَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ
"አል-አወል" الْأَوَّل ማለት "መጀመሪያ የሌለው ፊተኛ" ማለት ሲሆን "አል-አኺር" الْآخِر ማለት ደግሞ "መጨረሻ የሌለው ኃለኛ" ማለት ነው። አምላካችን አላህ ከፍጥረት በፊት ቀዳማይ ፊተኛ፥ ከፍጥረት በኃላም ደኃራይ ኃለኛ ነው፦

ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 48, ሐዲስ 112
አቢ ሁራይራ እንደተረከው፦ "ፋጢማህ ወደ ነቢዩ"ﷺ" ስለ አገልጋይ ጠየቀች፥ እርሷቸውም ለእርሷ፦ *"አላህ ሆይ! የሰባቱ ሰማያት እና የታላቁ ዙፋን ጌታ ነህ፥ የነገር ሁሉ ጌታ ጌታችን ሆይ! ተውራትን፣ ኢንጂልን፣ ቁርኣንን አውራጅ ነህ፥ ቅንጣትን እና የፍሬ አጥንትን ፈልቃቂ ነህ። አንተ አናትን የምትይዝ ስትሆን ከእኩይ ነገር ሁሉ በአንተ እጠበቃለው። አንተ ፊተኛ ነህ፥ ከአንተ በፊት ምንም ነገር የለም። አንተ ኃለኛ ነህ፥ ከአንተ በኃላ ምንም ነገር የለም። አንተ ግልጽ ነህ፥ ከአንተ በላይ ምንም ነገር የለም። አንተ ስውር ነህ፥ ከአንተ ባሻገር ምንም ነገር የለም" በይ አሏት"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ جَاءَتْ فَاطِمَةُ إِلَى النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم تَسْأَلُهُ خَادِمًا فَقَالَ لَهَا " قُولِي اللَّهُمَّ رَبَّ السَّمَوَاتِ السَّبْعِ وَرَبَّ الْعَرْشِ الْعَظِيمِ رَبَّنَا وَرَبَّ كُلِّ شَيْءٍ مُنْزِلَ التَّوْرَاةِ وَالإِنْجِيلِ وَالْقُرْآنِ فَالِقَ الْحَبِّ وَالنَّوَى أَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ كُلِّ شَيْءٍ أَنْتَ آخِذٌ بِنَاصِيَتِهِ أَنْتَ الأَوَّلُ فَلَيْسَ قَبْلَكَ شَيْءٌ وَأَنْتَ الآخِرُ فَلَيْسَ بَعْدَكَ شَيْءٌ وَأَنْتَ الظَّاهِرُ فَلَيْسَ فَوْقَكَ شَيْءٌ وَأَنْتَ الْبَاطِنُ فَلَيْسَ دُونَكَ شَيْءٌ
ከአላህ በፊት ምንም ነገር የለም፥ ከአላህ በኃላ ምንም ነገር የለም። "ሸይእ" شَيْء ማለት "ነገር" ማለት ሲሆን አጠቃላይ ፍጥረት ነው። ሁሉ ነገር ጠፊ ነው፥ ሁሉ ነገር ሲጠፋ ኃላ ቀሪ ኃለኛ አላህ ነው። ሁሉ ነገር ሳይኖር ፊትም ያለ ፊተኛ እርሱ ብቻ ነው፦
28፥88 ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አትግገዛ፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ *ነገሩ ሁሉ ከአላህ በቀር ጠፊ ነው*፡፡ ፍርዱ የእርሱ ብቻ ነው፡፡ ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ፡፡ وَلَا تَدْعُ مَعَ اللَّهِ إِلَـٰهًا آخَرَ ۘ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ كُلُّ شَيْءٍ هَالِكٌ إِلَّا وَجْهَهُ ۚ لَهُ الْحُكْمُ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 59, ሐዲስ 2
ዒምራም ኢብኑ ሑሰይን እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *”በመጀመሪያ ምንም ነገር ሳይኖር አላህ ነበረ"*፣ ከዚያ ዙፋኑን በውኃ ላይ ነበረ፣ ከዚያ ሁሉን ነገር ጻፈ፣ ከዚያ ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ። عَنْ عِمْرَانَ بْنِ حُصَيْنٍ، قَالَ إِنِّي عِنْدَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم كَانَ اللَّهُ وَلَمْ يَكُنْ شَىْءٌ غَيْرُهُ، وَكَانَ عَرْشُهُ عَلَى الْمَاءِ، وَكَتَبَ فِي الذِّكْرِ كُلَّ شَىْءٍ، وَخَلَقَ السَّمَوَاتِ وَالأَرْضَ
አላህ መጀመሪያ ከሌለው ከጊዜ በኃላ መነሻ ያለው ምንም አይነት ሲፋህ የለውም። “ሲፋህ” صِفَة ማለት "ባሕርይ"attribute" ማለት ነው፥ የሲፋህ ብዙ ቁጥር “ሲፋት” صِفَات ነው። የእርሱ ሲፋህ የእርሱ ምንነት መገለጫ ነው። እኔ መነሻ እስካለኝ ድረስ የእኔ ባሕርይ ጅማሬ አለው፥ አላህ ግን ጅማሬ ስለሌለው የእርሱ ባሕርይ ፍጥረታዊ ሳይሆን መለኮታዊ፤ ሰዋዊ ሳይሆን አምላካዊ ነው። እርሱ ከፍጥረት “ተብቃቂ” ነው፦
35፥15 እናንተ ሰዎች ሆይ! እናንተ ሁል ጊዜ ወደ አላህ ከጃዮች ናችሁ፡፡ *አላህም እርሱ “ተብቃቂው” ምስጉኑ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ أَنتُمُ الْفُقَرَاءُ إِلَى اللَّهِ ۖ وَاللَّهُ هُوَ الْغَنِيُّ الْحَمِيدُ
አላህ የማወቅ፣ የማፍቀር፣ የመስማት፣ የማየት ባሕርይ አለው፥ ይህ ባሕርይ መንስኤ የለውም። እኔ ለማወቅ የሚታወቅ ማንነትና ምንነት፣ ለማፍቀር የሚፈቀር ማንነትና ምንነት፣ ለመስማት የሚናገር ማንነትና ምንነት፣ ለማየት የሚታይ ማንነትና ምንነት ያስፈልገኛል። አላህ ግን ፍጥረት ሳይኖር ዐዋቂ፣ አፍቃሪ፣ ሰሚ፣ ተመልካች ነው። የእርሱ ባሕርይ ከማንም ከምንም ጋር አይመሳሰልም፦
42፥11 *”የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው”*፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ ۖ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ
"ምንም ነገር" የሚለው ይሰመርበት። አላህ ለመስማት እና ለማየት ጊዜና ቦታ አይገድበውም። እኔ ለማየት ብርሃን ያስፈልገኛል፥ በጨለማ ውስጥ ያለውን ማየት አልችልም። አላህ ግን ለማየት ብርሃን አያስፈልገውም፥ በጨለማ ውስጥ ያለውን ያያል። እኔ ለመስማት ሞገድ ያስፈልገኛል። አላህ ግን ለመስማት ሞገድ አያስፈልገውም፥ በአንድ ጊዜ ሁሉንም ነገር መስማት ይችላል። ሰው "ሰሚዕ" سَّمِيع ማለትም "ሰሚ" እና "በሲር" بَصِير ማለትም "ተመልካች" ተብሏል፦
76፥2 እኛ ሰዉን በሕግ ግዳጅ የምንፈትነው ስንሆን ቅልቅሎች ከሆኑ የፍትወት ጠብታ ፈጠርነዉ፥ *"ሰሚ ተመልካችም አደረግነዉ"*። إِنَّا خَلَقْنَا الْإِنسَانَ مِن نُّطْفَةٍ أَمْشَاجٍ نَّبْتَلِيهِ فَجَعَلْنَاهُ سَمِيعًا بَصِيرًا
ሰው ሰሚ እና ተመልካች የተባለበት አላህ ሰሚ እና ተመልካች በተባለበት ስሌትና ቀመር እንዳልሆነ ከተረዳን ዘንዳ፥ ሰው ዐዋቂ እና አፍቃሪ የተባለው አላህ ዐዋቂ እና አፍቃሪ በተባለበት መልክና ልክ አይደለም። ሰው አፍቃሪ ለመባል ተፈቃሪ ነገር ያስፈልገዋል፥ ዐዋቂ ለመባል ታዋቂ ነገር ያስፈልገዋል። አላህ ግን ምንም ፍጥረት ሳይኖር በባሕርይ ያለ ታዋቂ ዐዋቂ፣ ያለ ተፈቃሪ አፍቃሪ፣ ያለ ተፈጣሪ ፈጣሪ ነው።

በእርሱ ባሕርይ "ነው" እንጂ "ሆነ" አይባልም። "ሆነ" ጅማሬ ላለው ነገር ነው፥ ፈጣሪ ሆነ፣ ዐዋቂ ሆነ፣ አፍቃሪ ሆነ አይባልም። እርሱ የሚያስሆን እንጂ የሚሆን አይደለም፥ የሚያደርግ እንጂ የሚደረግ አይደለም። የእርሱ ዐዋቂነት፣ አፍቃሪነት፣ ፈጣሪነት መነሻ መዳረሻ የሌለው ከፍጡራን ጋር የማይመሳሰል ባሕርይ ነው። እርሱ እስካለ ድረስ የእርሱ ዐዋቂነት፣ አፍቃሪነት፣ ፈጣሪነት ከፍጥረት በፊት ነበረ። ያለ ፍጥረት ፈጣሪ የለም ካልን ከፍጥረት በፊት እግዚአብሔር አማንያንን መርጧል፥ ያውቃቸው ነበር" ማለት ትርጉም አይኖረውም፦
ኤፌሶን 1፥4 *"ዓለም ሳይፈጠር በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን"*።
1 ጴጥሮስ 1፥20 *"ዓለም ሳይፈጠር እንኳ አስቀድሞ ታወቀ"*፥
ያለ ተመራጭ መራጭ፥ ያለ ዐዋቂ ታዋቂ እንዴት ይኖራል? እኔ የሚመረጥ ነገር ሳይኖር መምረጥ ስለማልችልና የሚታወቅ ነገር ሳኖር ማወቅ ስለማልችል እግዚአብሔር የሚመረጥ ነገር ሳይኖር እንዴት ከፍጥረት በፊት መረጠ? የሚታወቅ ነገር ሳኖር እንዴት ዐወቀ? ምን ነካህ ወሒድ "የፈጣሪ ባሕርይ ከፍጡራን ጋር አይመሳሰልም" ከሆነ መልሱ እንግዲያውስ አላህ ከፍጥረት በፊት አፍቃሪ ለመባል ተፈቃሪ ነገር መኖር መስፈርት አይደለም። አይ "ሦስቱ አካላት እግዚአብሔር አብ፣ እግዚአብሔር ወልድ፣ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እርሱ በእርሳቸው ይፋቀሩ ስለነበር ነው" ካላችሁ ፈጣሪ ከጊዜ በኃላ የተገኘ ባሕርይ ከሌለው ይቅርባይቱ እና ፈጣሪነቱ አብሮት ከነበረ የሥላሴ አባላት እርስ በርሳቸው ይቅር ሲባባሉ እና ሲፈጣጠሩ ነው የኖሩት? እግዚአብሔር ዓለም ሳይፈጠር ንጉሥ ነበር፦
መዝሙር 74፥12 *"እግዚአብሔር ግን ከዓለም አስቀድሞ ንጉሥ ነው"*።
በማን ላይ ንጉሥ ነበር? አንደኛው እግዚአብሔር አብ በሌሎች እግዚአብሔር ላይ ነግሦባቸው ነበረን? ተነጋሽ ሳይኖር ነጋሽ አይታሰብም ከተባል ማለት ነው። ይህ አለሌ ጥያቄ መጽሐፍትን ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ስላልሆነ ስሁት ሙግት ነው። ፍልስፍና የተቆላ ገብስ ነው፤ ሲበሉት ይጣፍጣል፥ ግን ሲዘሩት አይበቅልም። ይህ ፍልስፍና ተገልብጦ እራሳቸውን እስር ቤት የሚከታቸው ጥያቄ ነው። አላህ ሂዳያህ ይስጣቸው፥ ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።
✍ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም

ስድብ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
49፥11 *"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ወንዶች ከወንዶች አይቀልዱ፡፡ ከእነርሱ የበለጡ ሊኾኑ ይከጀላልና፡፡ ሴቶችም ከሴቶች አይሳለቁ፡፡ ከእነርሱ የበለጡ ሊኾኑ ይከጀላልና፡፡ እራሳችሁንም አታነውሩ፡፡ በመጥፎ ስሞችም አትጠራሩ፡፡ ከእምነት በኋላ የማመጽ ስም ከፋ፡፡ ያልተጸጸተም ሰው እነዚያ እነርሱ በዳዮቹ ናቸው"*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا يَسْخَرْ قَوْمٌ مِّن قَوْمٍ عَسَىٰ أَن يَكُونُوا خَيْرًا مِّنْهُمْ وَلَا نِسَاءٌ مِّن نِّسَاءٍ عَسَىٰ أَن يَكُنَّ خَيْرًا مِّنْهُنَّ ۖ وَلَا تَلْمِزُوا أَنفُسَكُمْ وَلَا تَنَابَزُوا بِالْأَلْقَابِ ۖ بِئْسَ الِاسْمُ الْفُسُوقُ بَعْدَ الْإِيمَانِ ۚ وَمَن لَّمْ يَتُبْ فَأُولَـٰئِكَ هُمُ الظَّالِمُونَ
“በደል” ሦስት አይነት ነው፥ እርሱም፦ አላህን መበደል፣ ሰውን መበደል እና እራስን መበደል ነው። ሰውን መበደል ማንኛውም ሰው ሌላው ላይ የሚያደርሰው በደል ነው። ሰውን መበደል ማለት የሰው ሐቅ መንካት ነው፥ የሰው ሐቅ ተነክቶ የሚመለሰው በካሳ ወይም በይቅርታ ብቻ ነው። “ከፋራህ” كَفّارَة ማለት “ካሳ” መክፈል ማለት ሲሆን “ዐፉው” عَفُوّ ማለት ደግሞ “ይቅርታ” ማለት ነው። የበደልነውን ሰው በካሳ ወይም በይቅርታ ሐቁን ካልመለስን የትንሳኤ ቀን በአላህ ዘንድ ያስጠይቀናል። ሰውን መዝረፍ፣ ማማት፣ መስደብ፣ መማታት፣ መግደል ሰውን መበደል ነው። ዛሬ የምናየው ነጥብ ስለ ስድብ ነው፥ አምላካችን አላህ፦ "እራሳችሁንም አታነውሩ፡፡ በመጥፎ ስሞችም አትጠራሩ፡፡ ከእምነት በኋላ የማመጽ ስም ከፋ፡፡ ያልተጸጸተም ሰው እነዚያ እነርሱ በዳዮቹ ናቸው" ይለናል፦

"ቀውም" قَوْم ማለት "ሕዝብ" ማለት ነው፥ አንደኛው ሕዝብ በሌላ ሕዝብ ላይ መቀለድ ሐራም ነው። ለምሳሌ የኦሮሞ ሕዝብ በአማራ ሕዝብ፥ የአማራ ሕዝብ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ማለት ነው። አንደኛዋ ሴት በሌላ ሴት ላይ መሳለቅ ሐራም ነው። ቀልድና ስላቅ የስድብ አይነቶች ናቸው። "እራሳችሁን አታነውሩ" ማለት "እርስ በእርሳችሁ አትዘላለፉ" ማለት ነው፥ ትልቁ ነውር ስድብ ነው። በስድብ ሰው ማነወር ሐራም ነው፥ ማበሻቀጥ ሆነ ማብጠልጠል አሊያም መዝለፍ የስድብ አይነት ነው። "አታነውሩ" ለሚለው ቃል የገባው "ላ ተልሚዙ" لَا تَلْمِزُو ሲሆን "አትዝለፉ" ማለት ነው፥ "ሉመዛህ" لُّمَزَة ማለት በራሱ "ዘላፊ" "ተሳዳቢ" "አነዋሪ" ማለት ነው፦
104፥1 *"ለሃሜተኛ ለዘላፊ ሁሉ ወዮለት"*፡፡ وَيْلٌ لِّكُلِّ هُمَزَةٍ لُّمَزَةٍ
68፥11*"ሰውን አነዋሪን እና በማሳበቅ ኼያጅን አትታዘዝ"*፡፡ هَمَّازٍ مَّشَّاءٍ بِنَمِيمٍ
"አልቃብ" أَلْقَٰب ማለት "እኩይ ስም" ማለት ነው፥ በዚህ የመበሻሸቂያ ስም መጠራራት ከእምነት በኋላ የማመጽ ስም ነው፡፡ "በመጥፎ ስሞችም አትጠራሩ" የሚለው አንቀጽ የወረደበት ምክንያት ይህ ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3578
አቢ ጀቢራህ ኢብኑ አድ-ደሓክ እንደተረከው፦ *"አንድ ሰው ከመካከላችን በሁለት ወይም በሦስት ስም ይታወቃል፥ እርሱም ከሚጠላው በአንዱ ስም ተጠራ። ከዚያም፦ "በመጥፎ ስሞችም አትጠራሩ" የሚለው አንቀጽ ወረደ"*። يُحَدِّثُ عَنْ أَبِي جَبِيرَةَ بْنِ الضَّحَّاكِ، قَالَ كَانَ الرَّجُلُ مِنَّا يَكُونُ لَهُ الاِسْمَيْنِ وَالثَّلاَثَةَ فَيُدْعَى بِبَعْضِهَا فَعَسَى أَنْ يَكْرَهَ قَالَ فَنَزَلَتْ هَذِهِ الآيَةُ ( وَلاَ تَنَابَزُوا بِالأَلْقَابِ ) .
"መጥፎ ስም" ማለት ሰውዬው ቢጠራበት ደስ የማይለው እና ስሜቱ የሚጎዳበት ስም ነው። በእኩይ ስም ሰውን የሚጠራ እና በዚህ ድርጊቱ ያልተጸጸተም ሰው በደለኛ ነው። ይህ ሥራው ዓመፅ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 41
ዐብደሏህ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ሙሥሊምን መሳደብ ፉሡቅ ነው፥ መግደል ደግሞ ኩፍር ነው"*። فَقَالَ حَدَّثَنِي عَبْدُ اللَّهِ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ " سِبَابُ الْمُسْلِمِ فُسُوقٌ، وَقِتَالُهُ كُفْرٌ

"ፉሡቅ" فُسُوق ወይም ፊሥቅ" فِسْق የሚለው ቃል "ፈሠቀ" فَسَقَ ማለትም "ዓመፀ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ዓመፅ" ማለት ነው። አምላካችን አላህ በቁርኣኑ "እራሳችሁን አታነውሩ" ሲለን፥ ነቢያችን"ﷺ" ደግሞ "ሙሥሊምን መሳደብ ፉሡቅ ነው" ብለውናል። እርስ በእርስ መዘላለፍ ከተጀመረ ቀጣዩ ደረጃ እርስ በእርስ መገዳደል ነው፦
4፥29 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ገንዘቦቻችሁን በመካከላችሁ ያለ አግባብ አትብሉ፡፡ ግን ከእናንተ በመዋደድ የኾነችውን ንግድ ብሉ፡፡ *”እራሳችሁንም አትግደሉ”*፡፡ አላህ ለእናንተ አዛኝ ነውና፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَأْكُلُوا أَمْوَالَكُم بَيْنَكُم بِالْبَاطِلِ إِلَّا أَن تَكُونَ تِجَارَةً عَن تَرَاضٍ مِّنكُمْ ۚ وَلَا تَقْتُلُوا أَنفُسَكُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ كَانَ بِكُمْ رَحِيمًا
"እራሳችሁንም አትግደሉ" ማለት "እርስ በእርሳችሁ አትገዳደሉ" ማለት ነው። ይህ ደግሞ ከዓመፅ ወደ ክህደት ያመራል፥ ለዛ ነው ነቢያችን"ﷺ" "ሙሥሊምን መግደል ደግሞ ኩፍር ነው" ያሉት። በግል ደረጃ እንኳን እራስን ለመግደል መንስኤው እራስን ማነወር ነው። ሰው ራሱ ስለ ራሱ ጥሩ ካልተሰማው እራሱን ዝቅ አድርጎ ማነወር ይጀምራል፥ ይህ ሂደት ስር ሲሰድ እራስን ወደ መግደል እርምጃና ደረጃ ይደርሳል። ወደተነሳንበት ነጥብ ስንመለስ ስድብ ፈሳዱ ይህን ያክል አደገኛ ነው ማለት ነው፥ የራሳችን እምነት እንዳይሰደብ ከፈለግን የሌላውን እምነት መሳደብ የለብንም፦
6፥108 *"እነዚያንም ከአላህ ሌላ የሚገዙዋቸውን አትሳደቡ፡፡ ድንበርን በማለፍ ያለዕውቀት አላህን ይሳደባሉና"*፡፡ وَلَا تَسُبُّوا الَّذِينَ يَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ فَيَسُبُّوا اللَّهَ عَدْوًا بِغَيْرِ عِلْمٍ
ጣዖታውያን ከአላህ ሌላ የሚጠሯቸውን ማንነት ሆነ ምንነት ከዘለፍን እነርሱም ድንበርን በማለፍ ያለዕውቀት አላህን ይሳደባሉና። የሌላውን እምነት መዝለፍ እራሱ የሌላ ሰው ሐቅ መንካት ስለሆነ በደል ነው። ስድብ አሳብን በተሻለ አሳብ ማሸነፍ ሲያቅተን የምንጠቀምበት ዱላ ነው። ይህ ጽርፈት ሥር ከሰደደ የመግደል ስሜት ይፈጥራል። አላህ ከጽርፈት ይጠብቀን፥ ለሁላችንም ሂዳያህ ይስጠን! አሚን።

መልካም ንግግር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡
2፥263 *መልካም ንግግር እና ምሕረት ማድረግ ማስከፋት ከሚከተላት ምጽዋት በላጭ ነው*፡፡ አላህም ተብቃቂ ታጋሽ ነው፡፡ قَوْلٌ مَّعْرُوفٌ وَمَغْفِرَةٌ خَيْرٌ مِّن صَدَقَةٍ يَتْبَعُهَا أَذًى ۗ وَاللَّهُ غَنِيٌّ حَلِيمٌ
ከሥነ-ምግባር እሴት አንዱ መልካም ቃልን መናገር ነው፤ ሰይጣን መልካም ቃል በማይናገሩት በመካከላቸው ያበላሻል፤ አላህ መልካምን ቃልን ፍሬ በምትሰጥ መልካም ዛፍ ሲመስላት ክፉ ቃልን ደግሞ ፍሬ በማይሰጥ ክፉ ዛፍ ይመስለዋል፦
17፥53 ለባሮቼም በላቸው፦ ያችን እርሷ *“መልካም የሆነችውን ቃል ይናገሩ”፤ ሰይጣን በመካከላቸው ያበላሻልና*፤ ሰይጣን ለሰው ግልጽ ጠላት ነውና። وَقُل لِّعِبَادِى يَقُولُوا۟ ٱلَّتِى هِىَ أَحْسَنُ ۚ إِنَّ ٱلشَّيْطَٰنَ يَنزَغُ بَيْنَهُمْ ۚ إِنَّ ٱلشَّيْطَٰنَ كَانَ لِلْإِنسَٰنِ عَدُوًّۭا مُّبِينًۭا
14፥24 *አላህ መልካምን ቃል ሥርዋ በምድር ውስጥ የተደላደለች ቅርንጫፍዋም ወደ ሰማይ የረዘመች እንደሆነች መልካም ዛፍ አድርጎ ምሳሌን እንዴት እንደገለጸ አላየኽምን?* أَلَمْ تَرَ كَيْفَ ضَرَبَ اللَّهُ مَثَلًا كَلِمَةً طَيِّبَةً كَشَجَرَةٍ طَيِّبَةٍ أَصْلُهَا ثَابِتٌ وَفَرْعُهَا فِي السَّمَاءِ
14፥25 *ፍሬዋን በጌታዋ ፈቃድ በየጊዜው ትሰጣለች፡፡ አላህም ለሰዎች ይገሰጹ ዘንድ ምሳሌዎችን ይገልጻል*፡፡ تُؤْتِي أُكُلَهَا كُلَّ حِينٍ بِإِذْنِ رَبِّهَا ۗ وَيَضْرِبُ اللَّهُ الْأَمْثَالَ لِلنَّاسِ لَعَلَّهُمْ يَتَذَكَّرُونَ
14፥26 *የመጥፎም ቃል ምሳሌ ከምድር በላይ የተጎለሰሰች ለእርሷ ምንም መደላደል የሌላት እንደኾነች መጥፎ ዛፍ ነው*፡፡ وَمَثَلُ كَلِمَةٍ خَبِيثَةٍ كَشَجَرَةٍ خَبِيثَةٍ اجْتُثَّتْ مِن فَوْقِ الْأَرْضِ مَا لَهَا مِن قَرَارٍ
22፥24 *ከንግግርም ወደ መልካሙ ተመሩ*፡፡ ወደ ምስጉንም መንገድ ተመሩ፡፡ وَهُدُوا إِلَى الطَّيِّبِ مِنَ الْقَوْلِ وَهُدُوا إِلَىٰ صِرَاطِ الْحَمِيدِ
ምእመናን ከውድቅ ንግግር ራቂዎች ናቸው፤ መልካም ንግግር ማስከፋት ከሚከተላት ምጽዋት በላጭ ነው፦
23፥3 *እነዚያም እነርሱ ከውድቅ ንግግር ራቂዎች*፡፡ وَالَّذِينَ هُمْ عَنِ اللَّغْوِ مُعْرِضُونَ

35፥10 ማሸነፍን የሚፈልግ የኾነ ሰው አሸናፊነት ለአላህ ብቻ ነው፤ ማሸነፍን በመግገዛት ይፈልገው፡፡ *መልካም ንግግር ወደ እርሱ ይወጣል*፤ በጎ ሥራም ከፍ ያደርገዋል፡፡ مَن كَانَ يُرِيدُ الْعِزَّةَ فَلِلَّهِ الْعِزَّةُ جَمِيعًا ۚ إِلَيْهِ يَصْعَدُ الْكَلِمُ الطَّيِّبُ وَالْعَمَلُ الصَّالِحُ يَرْفَعُه
ነቢያችንም”ﷺ” በቅዱስ ንግግራቸው፦ “በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምን መልካም ይናገር አሊያም ዝም ይበል” ብለዋል፤ በተጨማሪም “መልካም ንግግር ሰደቃ ነው” ብለዋል፦
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 36, ሐዲስ 46
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ *”የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ “በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምን መልካም ይናገር አሊያም ዝም ይበል*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ “ مَنْ كَانَ يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الآخِرِ فَلْيَقُلْ خَيْرًا أَوْ لِيَسْكُتْ ”
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 12, ሐዲስ 72
አቢ ሀረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ ሰደቃህ በእያንዳንዱ የጸሐይ መውጫ ቀን በእያንዳንዱ የሰው መገጣጠሚያ ግዴታ ነው፤ በሁለት ወገን ፍትሕ ማድረግ ሰደቃ ነው፤ በእንስሳ ላይ የሚጋልብን ማማከር ወይም ሊጭን ሲል መርዳት ሰደቃ ነው፤ *”መልካም ንግግር ሰደቃ ነው”*፤ ወደ ሶላት ማንኛውም እርምጃ ማድረግ ሰደቃ ነው፤ ከመንገድ ላይ እኩይ ነገር ማስወገድ ሰደቃ ነው። وَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم “ كُلُّ سُلاَمَى مِنَ النَّاسِ عَلَيْهِ صَدَقَةٌ كُلَّ يَوْمٍ تَطْلُعُ فِيهِ الشَّمْسُ – قَالَ – تَعْدِلُ بَيْنَ الاِثْنَيْنِ صَدَقَةٌ وَتُعِينُ الرَّجُلَ فِي دَابَّتِهِ فَتَحْمِلُهُ عَلَيْهَا أَوْ تَرْفَعُ لَهُ عَلَيْهَا مَتَاعَهُ صَدَقَةٌ – قَالَ – وَالْكَلِمَةُ الطَّيِّبَةُ صَدَقَةٌ وَكُلُّ خَطْوَةٍ تَمْشِيهَا إِلَى الصَّلاَةِ صَدَقَةٌ وَتُمِيطُ الأَذَى عَنِ الطَّرِيقِ صَدَقَةٌ

ቅዱስ ቁርኣን
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
56፥77 እርሱ *የከበረ* ቁርኣን ነው። إِنَّهُۥ لَقُرْءَانٌۭ كَرِيمٌۭ
ቅዱስ ቁርኣን የምንልበት ምክንያት ቁርኣን "ከሪም" ስለተባለ ነው፤ "ከሪም" كَرِيم የሚለው ቃል "ቅዱስ" "ክቡር" "ብፁዕ" "ንኡድ" "ውዱስ" "ስቡህ" "እኩት" "እጹብ" የሚል ፍቺ አለው፦

"መጽሐፍ ቅዱስ" ማለት "ቅዱስ መጽሐፍ" ማለት ነው፤ የፈጣሪ ንግግር ብቻ ነው ቅዱስ እንጂ የሰው ንግግር ቅዱስ አይደለም። ባይብል የሰው ንግግር ስላለበት ቅዱስ መጽሐፍ አይባልም። ስለዚህ ባይብልን "መጽሐፍ ቅዱስ" በማለት ፋንታ "ባይብል" በሉት፤ "ባይብል" የሚለው የኢንግሊሹ ቃል "ቢብሊያ" βιβλία ከሚል የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙ "ጥቅሎች"scrolls" ማለት ነው፣ በነጠላ ደግሞ "ቢብሊኦን" βιβλίον ሲሆን "ጥቅል"scroll" ማለት ነው። ይህ ቃል ለማንኛውም መጽሐፍ ቃሉ ያገለግላል። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ቁርኣን ብቻ ነው፤ ምክንያቱም የቁርኣን ተናጋሪ ፈጣሪ ብቻ ስለሆነ ማለት ነው፤ በእግጥም ቁርኣን "ቅዱስ" "ክቡር" "ብፁዕ" "ንኡድ" "ውዱስ" "ስቡህ" "እኩት" "እጹብ" ነው።

ነቢያችን"ﷺ" አይመለኩም
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
48፥9 *"በአላህ እና በመልክተኛውም ልታምኑ፣ ልትረዱትም፣ ልታከብሩትም። አላህን በጧትና ከቀትር በኋላ ልታወድሱትም ላክነው"*፡፡ لِّتُؤْمِنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ وَتُعَزِّرُوهُ وَتُوَقِّرُوهُ وَتُسَبِّحُوهُ بُكْرَةً وَأَصِيلًا
በክርስትና የቀጥታ አምልኮ የሚያመልኩት ሦስት አካላትን እና የኢየሱስን ሰውነት ሲሆን፥ የተዛዋዋሪ አምልኮ የሚያመልኩት ደግሞ ቅዱሳን ሰዎችን እና ቅዱሳን መላእክትን ነው። ይህንን ግሳንግስ የአምልኮ እሳቤ ለመሸፈን፦ "እናንተ ሙሥሊሞች ነቢያችሁን ታመልካላችሁ" ብለው አረፉት። እዚህ ድምዳሜ ላይ አደረሰን ያሉትን አንቀጽ ጥልልና ጥንፍፍ አርገን እስቲ እንመልከት። ነቢያችን"ﷺ" የተላኩበት ዓላማ በአላህ አምላክነት እና በእርሳቸው ነቢይነት እንድናምን፣ እርሳቸውን ልንረዳና ልናከብር፣ አላህን በጧትና ከቀትር በኋላ እንድናወድሰው ነው፦

አላህ አንድ አምላክ እንደሆነ፥ ከእርሱም በቀር አምላክ እንደሌለ ማመን እና ነቢያችን"ﷺ" ከእርሱ የተላኩ መልእክተኛ መሆናቸውን ማመን ፈርድ ነው፦
48፥13 *"በአላህ እና በመልክተኛው ያላመነም ሰው እኛ ለከሓዲዎች እሳትን አዘጋጅተናል"*፡፡ وَمَن لَّمْ يُؤْمِن بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ فَإِنَّا أَعْتَدْنَا لِلْكَافِرِينَ سَعِيرًا
"ቱዐዘሩ" تُعَزِّرُو ማለት "ልትረዱ" ማለት ሲሆን "ቱዐዘሩ" تُعَزِّرُو በሚል ግስ ላይ "ሁ" هُ ማለትም "እርሱ" የሚል ተሳቢ ተውላጠ-ስም ነቢያችንን"ﷺ" ለማመልከት የገባ ነው፥ በተመሳሳይም "ቱወቀሩ" تُوَقِّرُو ማለት "ልታከብሩ" ማለት ሲሆን "ቱወቀሩ" تُوَقِّرُو በሚል ግስ ላይ "ሁ" هُ ማለትም "እርሱ" የሚል ተሳቢ ተውላጠ-ስም ነቢያችንን"ﷺ" ለማመልከት የገባ ነው። መርዳትና ማክበር በሌላ አንቀጽም ለነቢያችን"ﷺ" አገልግሎት ላይ ውሏል፦
7፥157 እነዚያም በእርሱ ያመኑ *"ያከበሩትም የረዱትም"* ያንንም ከእርሱ ጋር የተወረደውን ብርሃን የተከተሉ እነዚያ እነሱ የሚያድኑ ናቸው፡፡ فَالَّذِينَ آمَنُوا بِهِ وَعَزَّرُوهُ وَنَصَرُوهُ وَاتَّبَعُوا النُّورَ الَّذِي أُنزِلَ مَعَهُ ۙ أُولَـٰئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ
ቀጥሎ "ቱሠበሑሁ" تُسَبِّحُوهُ ማለት ግን "ልታጠሩት" ማለት ነው። “ሡብሓን” سُبْحَٰن የሚለው ቃል “ሠበሐ” سَبَّحَ ማለትም “አመሰገነ” ወይም “አጠራ” “አወደሰ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማህሌት” “ውዳሴ” “ስብሐት” ማለት ነው፥ “ተሥቢሕ” تَسْبِيح ማለት ደግሞ “ተስብሖት” ማለት ነው። በጧት በምናነጋ ጊዜ እና ከቀትር በኋላ በምናመሽ ጊዜ ተሥቢሕ የምናቀርበው ለአላህ ብቻ ነው፦
33፥42 *በቀኑ መጀመሪያና መጨረሻም አጥሩት*፡፡ وَسَبِّحُوهُ بُكْرَةً وَأَصِيلًا
30፥17 አላህንም በምታመሹ ጊዜ በምታነጉም ጊዜ አጥሩት”*፡፡ فَسُبْحَانَ اللَّهِ حِينَ تُمْسُونَ وَحِينَ تُصْبِحُونَ
"ሁ" هُ ማለትም "እርሱ" የሚለው ተውላጠ-ስም 48፥9 የአንቀጹ መነሻ ላይ "አላህ" اللَّه የሚለውን ስም ተክቶ የመጣ ነው፥ በተጨማሪም 30፥17 ላይ የምናጠራው አላህን እንደሆነ ተናግሯል። “አጥሩ” ለሚለው ቃል የገባው “ሡብሓነ” سُبْحَانَ ሲሆን ለአላህ የምናቀርበው ስብሐት ከላይ አንቀጹ ላይ እንደተቀመጠው “ሡብሓነ አሏህ” سُبْحَانَ اللَّه ነው። ስለዚህ "በጧትና ከቀትር በኋላ ልታወድሱትም" የተባለው ነቢያችን"ﷺ" ሳይሆኑ አላህ ነው። ምክንያቱም ተሥቢሕ እራሱ አምልኮ ነው፥ ነቢያችን"ﷺ" ደግሞ ይከበራሉ እንጂ አይመለኩም። "ቱሠበሑሁ" تُسَبِّحُوهُ የተባለው አላህ እንደሆነ የነቢያችን"ﷺ" ዘመድ እና ባልደረባ ኢብኑ ዐባሥ"ረ.ዐ." ተናግሯል፦
ተፍሢሩል ኢብኑ ዐባሥ ሱረቱል ፈትሕ 48፥9
*"ልታጠሩትም" ማለት "አላህ ልታጠሩት" ማለት ነው፥ "በጧትና ከቀትር በኋላ" ማለት "ጠዋትና ማታ" ማለት ነው"*።
{ وتسبحوه} أي تسبحون اللّه، { بكرة وأصيلاً} أي أول النهار وآخره،
አላህ እራሱ ነቢያችንን"ﷺ" "ሠበሕ" سَبِّح ማለትም "አሞግስ" ይላቸዋል፥ የሚሞገሰው ደግሞ ከሁሉ በላይ የኾነውን ጌታ ብቻ ነው። ሙሥሊሞች አላህ ስሙ እንዲወሳ ባዘዘው ቤቶች ውስጥ በጧት እና በማታ ለእርሱ ያጠራሉ፥ በአላህ ቤቶች በመስጊዶችም ውስጥ ከአላህ ጋር አንድንም ማንነትና ምንነት አይገዙም፦
87፥1 *"ከሁሉ በላይ የኾነውን ጌታህን ስም አሞግሥ"*፡፡ سَبِّحِ اسْمَ رَبِّكَ الْأَعْلَى
24፥36 *"አላህ እንድትከበር እና ስሙ በውስጧ እንዲወሳ ባዘዘው ቤቶች ውስጥ አወድሱት፡፡ በውስጧ በጧት እና በማታ ለእርሱ ያጠራሉ"*፡፡ فِي بُيُوتٍ أَذِنَ اللَّهُ أَن تُرْفَعَ وَيُذْكَرَ فِيهَا اسْمُهُ يُسَبِّحُ لَهُ فِيهَا بِالْغُدُوِّ وَالْآصَالِ
72፥18 *"እነሆ መስጊዶችም የአላህ ብቻ ናቸው፡፡ በውስጣቸው ከአላህ ጋር አንድንም አትገዙ" ማለትን ተወረደለኝ"*፡፡ وَأَنَّ الْمَسَاجِدَ لِلَّهِ فَلَا تَدْعُوا مَعَ اللَّهِ أَحَدًا
ስለዚህ "ሙሥሊሞች ነቢያችሁን ታመልካላችሁ" የሚለው ግንዛቤ ቁርኣኑን በትክክል ካለመረዳት እና ዳተኛና ቸልተኛ ከመሆን የሚመጣ የተውረገረገ፣ የተንሸዋረረ፣ የደፈረሰ፣ የተሳከረ ስሑት ግንባቤ ነው። ከጸለምተኛ ግንዛቤ ወጥታችሁ አብርኆተኛ እንድትሆኑ አላህ ይርዳችሁ! አሚን።

ዘረኝነት
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
30፥22 ሰማያትንና ምድርንም መፍጠሩ፣ *የቋንቋዎቻችሁ እና የመልኮቻችሁም መለያየት ከአስደናቂ ታምራቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለዐዋቂዎች ተዓምራቶች አሉበት*፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ خَلْقُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَاخْتِلَافُ أَلْسِنَتِكُمْ وَأَلْوَانِكُمْ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّلْعَالِمِينَ
“ዘረኝነት”racism” ማለት የራስን ቋንቋና ዘውግ አተልቆ የሌላውን ማሳነስ፣ ማግለል፣ መቃረን እና ማራከስ ነው። ዘረኝነት ትዳርን፣ ቤተሰብን፣ ጉርብትናን፣ ማህበረሰብን፣ ሃይማኖት፣ መንግሥትን፣ አገርን የሚበትን ክፉ በሽታ ነው። ዘረኝነት፣ ጎጠኝነት፣ ጠርዘኝነት፣ ቡድንተኝነት ምንጫቸው “ዝንባሌ”inclination” ነው። እኛ ሁላችንም የአንድ አባት የአደም፥ የአንድ እናት የሐዋ ልጆች ነን። ታዲያ የአንድ እናት እና አባት ልጆች ከሆንን አንዱን ዘር ማብለጥ ሌላውን ማሳነስ ጠባብነት አይደለምን? አማራ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ፣ ትግሬ ወዘተ ቋንቋ ነው፤ የቋንቋዎቻችን መለያየት ከአስደናቂ ታምራቶቹ ነው፤ በዚህ ውስጥ ለዐዋቂዎች ተዓምራቶች አሉበት፦

ቋንቋዎች ይዘውት የመጡት ታሪክ፣ ባህል፣ ልማድ፣ ትውፊት፣ ወግ፣ ክህሎት እና ሙዳየ-ቃላት “ዘውግ” ethnic” ሆኗል፤ ይህ እራሱ የቻለ ውበት ነው። ዘረኝነት ግን ከቋንቋ አሊያም ከቀለም የሚመጣ ሳይሆን የልብና የአስተሳሰብ በሽታ ነው። የቋንቋዎቻችሁ እና የመልኮቻችሁም መለያየት ከአስደናቂ ታምራቶቹ እንጂ መኩሪያ ወይም ማብጠልጠሊያ አይደለም፤ ዘረኝነት በዲንያ በአላህ ዘንድ ዋጋ የሚያሳጣ ሲሆን በአኺራም ደግሞ ለጀሃነም ይዳርጋል፦
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 344
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ *”አላህ ዐዘ ወጀል ከእናንተ የዘመነ-ጃሂሊያን ኩራት አስወግዷል፤ ይህም በዘር መኩራት ነው። ይህ ለጥንቁቁ አማኝም ወይም ለአደገኛው ካሃዲ አንድ ብቻ ነው። እናንተ የአደም ልጆች ናችሁ፤ አደም ከአፈር ነው የመጣው፤ ሰዎች በዘራቸው የሚኮሩ ከሆነ ጀሃነምን ይሞሏታል፤ ወይም አላህ ዘንድ ዋጋቸው ጥንዚዛ በአፍንጫው ከሚሽከረከር ጉድፍ ያነሰ ከሆኑት ይሆናል*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم “ إِنَّ اللَّهَ عَزَّ وَجَلَّ قَدْ أَذْهَبَ عَنْكُمْ عُبِّيَّةَ الْجَاهِلِيَّةِ وَفَخْرَهَا بِالآبَاءِ مُؤْمِنٌ تَقِيٌّ وَفَاجِرٌ شَقِيٌّ أَنْتُمْ بَنُو آدَمَ وَآدَمُ مِنْ تُرَابٍ لَيَدَعَنَّ رِجَالٌ فَخْرَهُمْ بِأَقْوَامٍ إِنَّمَا هُمْ فَحْمٌ مِنْ فَحْمِ جَهَنَّمَ أَوْ لَيَكُونُنَّ أَهْوَنَ عَلَى اللَّهِ مِنَ الْجِعْلاَنِ الَّتِي تَدْفَعُ بِأَنْفِهَا النَّتْنَ ”
የአደም ልጆች የአንድ አባት እና እናት ልጆች ነን ብሎ ማስተንተን መጠበብ ሲሆን በዘረኝነት አራንቋ መለከፍ መጥበብ ነው፦
ሱነን ነሳኢ መጽሐፍ 37 , ሐዲስ 150
ጁንደብ ኢብኑ ዐብደላህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ *”ማንም ሰው ግልጽ ባልሆነ ነገር፣ በዘረኝነት ጥብቅና፣ በዘረኝነት መንገድ የተጋደለ ግድያው የጃህሊያ ነው*። عَنْ جُنْدُبِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم “ مَنْ قَاتَلَ تَحْتَ رَايَةٍ عُمِّيَّةٍ يُقَاتِلُ عَصَبِيَّةً وَيَغْضَبُ لِعَصَبِيَّةٍ فَقِتْلَتُهُ جَاهِلِيَّةٌ ”
“ጃህሊያህ” جَاهِلِيَّةٌ ማለት “መሃይምነት” ማለት ነው፤ ቅድመ-ቁርኣን ያለው ጊዜ ዘመነ-ጃህሊያህ ይባላል፤ በእርግጥም በዘመነ-ጃህሊያህ ጊዜ የነበረችው ዘረኝነት ጥንብ ናት፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 45, ሐዲስ 81
ጃቢር ኢብኑ ዐብደላህ እንዳስተላለፈው፦ “በጉዞ ከነቢዩ”ﷺ” ጋር ነበርን፤ አንድ ሰው ከሙሃጅር ከአንሷር የሆነውን አንድ ሰው ጀርባውን መታው፤ አንሷሩም፦ “አንሷሪ ሆይ! አለ፤ ሙሃጅሩም፦ “ሙሃጅር ሆይ! አለ። ከዚያም የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” *”ይህ የጃህሊያህ አጠራር አይደለምን? አሉ፤ እነርሱም፦ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አንድ ሰው ከሙሃጅር ከአንሷር የሆነውን አንድ ሰው ጀርባውን መታው” አሉ፤ እርሳቸው፦ “እርሷን(ዘረኝነትን) ተዋት ጥንብ ናት” አሉ*። جَابِرَ بْنَ عَبْدِ اللَّهِ يَقُولُ كُنَّا مَعَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم فِي غَزَاةٍ فَكَسَعَ رَجُلٌ مِنَ الْمُهَاجِرِينَ رَجُلاً مِنَ الأَنْصَارِ فَقَالَ الأَنْصَارِيُّ يَا لَلأَنْصَارِ وَقَالَ الْمُهَاجِرِيُّ يَا لَلْمُهَاجِرِينَ . فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ” مَا بَالُ دَعْوَى الْجَاهِلِيَّةِ ” . قَالُوا يَا رَسُولَ اللَّهِ كَسَعَ رَجُلٌ مِنَ الْمُهَاجِرِينَ رَجُلاً مِنَ الأَنْصَارِ . فَقَالَ ” دَعُوهَا فَإِنَّهَا مُنْتِنَةٌ
“ሙሃጅር” مُهَاجِر ማለት “ስደተኛ” ማለት ሲሆን ከመካ የተሰደዱትን ሶሓብይን ያመለክታል፤ “አንሷር” أَنْصَارٍ ማለት “ረዳት” ማለት ሲሆን ከመካ የተሰደዱት የተቀበሉ የመዲና ሶሓብይን ያመለክታል። አንዱ ዘር ተነስቶ ሌላውን ዘር ሲበድል የተበደለው ያልበደለውን በዘሩ ብቻ በቁርሾ ለመበቀል መነሳት ጠባብነት ነው፤ በኢስላም የቀደሙት ትውልድ በሰሩት ወንጀል የአሁኑን ትውልድ መጠየቅ ወይም መቅጣት እራሱ ሕግ መተላለፍ ነው፦
ሱነን ነሳኢ መጽሐፍ 37 , ሐዲስ 162
ዐብደላህ እንደተረከው ነብዩም”ﷺ” አሉ፦.. *ሰው በአባቱ ወይም በወንድሙ ወንጀል አይቀጣም*። وَلاَ يُؤْخَذُ الرَّجُلُ بِجَرِيرَةِ أَبِيهِ وَلاَ بِجَرِيرَةِ أَخِيهِ ”

በተጨማሪም አንድ ሰው ባጠፋው ብዙኃኑን ዘር ማንቋሸሽ ወይም ማዋረድ ሐራም ነው፦
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 33, ሐዲስ 106
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ከሰዎች መካከል ትልቁ ውሸታም ሌላው ሰው ማንቋሸሽ እና መላውን ዘር ማዋረድ ነው*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ “ إِنَّ أَعْظَمَ النَّاسِ فِرْيَةً لَرَجُلٌ هَاجَى رَجُلاً فَهَجَا الْقَبِيلَةَ بِأَسْرِهَا
እረ እሩቅ ሳንሄድ ወደ ዘረኝነት የሚጣራ፣ በዘረኝነት መንገድ የሚታገል፣ በዘረኝነት መንገድ ሲከተል የሞተ ሰው ከነብያችን”ﷺ” ሱናህ ውጪ ነው፦
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 349
ጁበይር እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ወደ ዘረኝነት የሚጣራ ከእኛ አይደለም። በዘረኝነት መንገድ የሚታገኝ ከእኛ አይደለም። በዘረኝነት መንገድ ሲከተል የሞተ ከእኛ አይደለም*። عَنْ جُبَيْرِ بْنِ مُطْعِمٍ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ “ لَيْسَ مِنَّا مَنْ دَعَا إِلَى عَصَبِيَّةٍ وَلَيْسَ مِنَّا مَنْ قَاتَلَ عَلَى عَصَبِيَّةٍ وَلَيْسَ مِنَّا مَنْ مَاتَ عَلَى عَصَبِيَّةٍ ”
በድንበር፣ በክልል፣ በወሰን የከፋፈሉን ሰዎች ናቸው። ምድር እኮ የአላህ ናት። እንግዲህ ዲኑል ኢሥላምን የመሰለ ሰውን የሚያስተሳስር የአላህ ገመድ እያለ በዘረኝነት፣ በጎጠኝነት፣ በጠርዘኝነት፣ በቡድንተኝነት መለያየት “አትለያዩ” ያለን አላህ አለመታዘዝ ነው። ዛሬ በመሃይምነት አራንቋ ተጠቅተን በማህበራዊ ሚድያ ዘረኝነትን ስናራግብ እንውላለን፤ ኢስላም ዓለም-ዐቀፍ ሆኖ ሳለ ምነው ጠበብንሳ? ምነው ይህ ያህል ኢማናችን ወረደሳ? የኢሥላም ልዕልና ከዘር፣ ከብሔር፣ ከቋንቋ፣ ከቀለም፣ ከፓለቲካ በላይ ነው። አላህ ሁላችንም ያስተካክለን፥ ሂዳያ ይስጠን፣ ከጥንቧ ዘረኝነት ይጠብቀን! አሚን።

አል-ሑሩፉል ሙቀጧዓት
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
10፥1 *"አሊፍ ላም ሯ"* ይህቺ ጥበብ ከተመላው መጽሐፍ አንቀጾች ናት፡፡ الر ۚ تِلْكَ آيَاتُ الْكِتَابِ الْحَكِيمِ
ነቢያችን"ﷺ" በቁርኣን ከተሰጣቸው አንዱ አንድ ቃላት ሰፊ ትርጉም ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 21, ሐዲስ 7
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"በነቢያት ላይ በስድስት ነገር ከብሬአለው፥ እርሱም፦ "ጀዋሚዓል ከሊም ተሰቶኛል፣ በጠላት ልብ ውስጥም ፍርሀት እንዲጣል በመደረግ ተረዳኹኝ፣ የምርኮ ገንዘብ ሐላል ሆነውልኛል፣ ምድር በጠቅላላ ጡሀራና የመስገጃ ክልል ተደረገልኝ፣ ለፍጡራን ሁሉ ተላኩኝ፣ የነቢያት መደምደሚያ ሆንኩኝ"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ " فُضِّلْتُ عَلَى الأَنْبِيَاءِ بِسِتٍّ أُعْطِيتُ جَوَامِعَ الْكَلِمِ وَنُصِرْتُ بِالرُّعْبِ وَأُحِلَّتْ لِيَ الْغَنَائِمُ وَجُعِلَتْ لِيَ الأَرْضُ مَسْجِدًا وَطَهُورًا وَأُرْسِلْتُ إِلَى الْخَلْقِ كَافَّةً وَخُتِمَ بِيَ النَّبِيُّون
"ጀዋሚዓል ከሊም" جَوَامِعَ الْكَلِم የሁለት ቃላት ውቅር ነው፥ የጀዋሚዕ እና የከሊም ነው። "ጀዋሚዕ" جَوَامِع ማለት "ብዛት" ማለት ሲሆን በነጠላ "ጃሚዕ" جَامِع ሲሆን ደግሞ "ብዙ" ማለት ነው። "ከሊም" كَلِم ወይም "ከሊማት" كَلِمَات ማለት "ቃላት" ማለት ሲሆን በነጠላ "ከሊማህ" كَلِمَة ሲሆን ደግሞ "ቃል" ማለት ነው። "ጀዋሚዓል ከሊም" ማለት "አንድ ቃል ሆኖ ብዛት ቃላት ያለው ትርጉም" ማለት ነው። ይህንን ከተረዳን ዘንዳ ሰለ አል-ሑሩፉል ሙቀጧዓት ሙሉ ትርጉም የሚያውቀው አላህ ብቻ ነው፥ ነገር ግን መጠነኛ ዕውቀት ከቀደምት ሠለፍ ተገኝቷል።
"አል-ሑሩፉል ሙቀጧዓት" الْحُرُوف الْمُقَطَّعَات ማለት "አጽርዖተ-ፊደላት" ወይም "አጫጭር ፊደላት" ማለት ነው። በቁርኣን ከ 114 ምዕራፎች ውስጥ በ 29 ምዕራፎች መግቢያ ላይ ስላሉ "ፈዋቲሕ" فَوَاتِح ማለትም "ከፋች" ይባላሉ። እነዚህም ሐርፎች 14 ናቸው፥ እነርሱም "አሊፍ" أ "ላም" ل "ሚም" م "ሯ" ر "ኑን" ن ወዘተ ናቸው። እነዚህ ሐርፎች ለምሳሌ "አሊፍ" أ የሚለው ሐርፍ "አና" أَنَا ለሚለው ቃል ምጻረ-ቃል ነው፣ "ላም" ل የሚለው ሐርፍ "አሏህ" الله ለሚለው ቃል ምጻረ-ቃል ነው፣ "ሚም" م የሚለው ሐርፍ "ዐሊም" عَلِيم ለሚለው ቃል ምጻረ-ቃል ነው፣ "ሯ" ر የሚለው ሐርፍ "በሲር" بَصِير ለሚለው ቃል ምጻረ-ቃል ነው፣ "ኑን" ن የሚለው ሐርፍ "ሑት" حُوت ለሚለው ቃል ተለዋዋጭ ነው። ይህ በወፍ በረር ለቅምሻ ያክል ነው፥ እስቲ አንዳንድ ናሙናዎችን በመጠኑ እንይ፦
29፥1 *"አሊፍ ላም ሚም"* الم
ከላይ በተቀመጠው መሠረት "አሊፍ ላም ሚም" الم ማለት "አና አሏሁ ዐሊም" أَنَا اللَّهُ عَلِيم ማለት ነው፥ ትርጉሙም "እኔ አላህ ዐዋቂ ነኝ" ማለት ነው። ይህንን ኢብኑ ዐባሥ ሲያስቀምጠው እንዲህ ይላል፦
ተፍሢሩል ኢብኑ ዐባሥ 29፥1 "ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *"የላቀው አላህ ንግግር ስለ አሊፍ ላም ሚም ማለት "እኔ አላህ ነኝ፥ ዐውቃለው" ማለት ነው"*። عن ابن عباس في قوله تعالى : " الۤـمۤ " ، أي : أنا الله أعلم
ሌላ ናሙና፦

ከላይ በተቀመጠው መሠረት "አሊፍ ላም ሯ" الر ማለት "አና አሏሁ በሲር" أَنَا اللَّهُ بَصِير ማለት ነው፥ ትርጉሙም "እኔ አላህ ተመልካች ነኝ" ማለት ነው። ይህንን ኢብኑ ዐባሥ ሲያስቀምጠው እንዲህ ይላል፦
ተፍሢሩል ኢብኑ ዐባሥ 10፥1 "ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *"የላቀው አላህ ንግግር ስለ አሊፍ ላም ሯ ማለት "እኔ አላህ ነኝ፥ ዐያለው" ማለት ነው"*። عن ابن عباس في قوله تعالى : " الر " ، أي : أنا الله أرى

68፥1 *"ኑን"* በብርእ እምላለሁ በዚያም መልአኮች በሚጽፉት፡፡ ن ۚ وَالْقَلَمِ وَمَا يَسْطُرُونَ
እዚህ ሱራህ ላይ ስለ የዓሣው ባለቤት ስለ ዩኑስ ስለሚናገር ይህ መግቢያ "ኑን" ይላል፦
68፥48 ለጌታህም ፍርድ ታገሥ! በመበሳጨትና ባለ መታገሥ *"እንደ ዓሣው ባለቤትም"* አትኹን፡፡ እርሱ በጭንቀት የተመላ ኾኖ ጌታውን በተጣራ ጊዜ፡፡ فَاصْبِرْ لِحُكْمِ رَبِّكَ وَلَا تَكُن كَصَاحِبِ الْحُوتِ إِذْ نَادَىٰ وَهُوَ مَكْظُومٌ
እዚህ አንቀጽ ላይ "ዓሣ" ለሚለው ቃል የገባው "ሑት" حُوت ሲሆን በሌላ ሱራህ ላይ "ዓሣ" ለማለት የገባው "ኑን" نُّون ነው፦
21፥87 *"የዓሳውንም ባለቤት ተቆጥቶ በኼደ ጊዜ አስታውስ"*፡፡ وَذَا النُّونِ إِذ ذَّهَبَ مُغَاضِبًا
ስለ አስራ አራቱም ሐርፎች ለመናገር ሰፊ ጊዜና ቦታ ይፈልጋል፥ ግን ለማሟሻ ያክል ይህ በቂ ነው። ይህ ትርጓሜ ከኢብኑ ዐባሥ የተገኘ ሪዋያህ ነው፥ ይህንን ትርጓሜ አምላካችን አላህ ያስተማረው ትርጓሜ ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 171
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ያዙኛና እንዲህ አሉ፦ *"አላህ ሆይ! ጥበብን እና የመጽሐፉ ትርጉም አስተምረው"*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ ضَمَّنِي رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ إِلَيْهِ وَقَالَ " اللَّهُمَّ عَلِّمْهُ الْحِكْمَةَ وَتَأْوِيلَ الْكِتَابِ
"ትርጉም" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ተእዊል" تَأْوِيل ነው። "ሙሕከማት" مُّحْكَمَات ማለት "ግልጽ"clear" ማለት ነው፥ የመጽሐፉ መሠረት የሆኑት የኢሥላም እና የኢማን መሠረት ግልጾች አናቅጽ ናቸው። "ሙተሻቢያት" مُتَشَابِهَات ማለት "ምሳሌአዊ"allegorical" ማለት ነው፥ ምሳሌአዊ አናቅጽን ትርጉም አላህ እና በዕውቀትም የጠለቁት እንጂ ሌላ ማንም ዐያውቀውም፦
3፥7 *"እርሱ ያ በአንተ ላይ መጽሐፉን ያወረደ ነው፡፡ ከእርሱ ከመጽሐፉ ግልጽ የኾኑ አንቀጾች አሉ፡፡ እነርሱ የመጽሐፉ መሠረቶች ናቸው፡፡ ሌሎችም ምሳሌአዊ አንቀጾች አሉ፡፡ እነዚያማ በልቦቻቸው ውስጥ ጥመት ያለባቸው ሰዎች ማሳሳትን ለመፈለግ እና ትርጉሙን ለመፈለግ ከእርሱ ሙተሻቢውን ይከታተላሉ፡፡ ፍቺውን አላህ እና በዕውቀትም የጠለቁት ብቻ እንጅ ሌላ አያውቀውም፡፡ እነርሱም፦ «በእርሱ አምነናል፤ ሁሉም ከጌታችን ዘንድ ነው» ይላሉ፡፡ የአእምሮ ባለቤቶችም እንጅ ሌላው አይገሰጽም"*፡፡ هُوَ الَّذِي أَنزَلَ عَلَيْكَ الْكِتَابَ مِنْهُ آيَاتٌ مُّحْكَمَاتٌ هُنَّ أُمُّ الْكِتَابِ وَأُخَرُ مُتَشَابِهَاتٌ ۖ فَأَمَّا الَّذِينَ فِي قُلُوبِهِمْ زَيْغٌ فَيَتَّبِعُونَ مَا تَشَابَهَ مِنْهُ ابْتِغَاءَ الْفِتْنَةِ وَابْتِغَاءَ تَأْوِيلِهِ ۗ وَمَا يَعْلَمُ تَأْوِيلَهُ إِلَّا اللَّهُ ۗ وَالرَّاسِخُونَ فِي الْعِلْمِ يَقُولُونَ آمَنَّا بِهِ كُلٌّ مِّنْ عِندِ رَبِّنَا ۗ وَمَا يَذَّكَّرُ إِلَّا أُولُو الْأَلْبَابِ
ከላይ ያቀረብኩት ከዐረቢኛው ጋር ተቀራራቢ ትርጉም ያለውን የሻኪር ትርጉም"translation" ነው። ይህ አተረጓጎም የቁርኣንን መሠረትና ውቅር፣ ዋልታና ማገር፣ ጥልቀትና ስፋት፣ ድርና ማግ በቅጡ በማወቅ የጠለቁት ያውቁታል። ስለ አል-ሑሩፉል ሙቀጧዓት እሳቤ በግርድፉና በሌጣው ለመጨበጥ እንጂ ደርዝና ፈርጅ ባለው መልኩ ለማሳወቅ እንዳልሆነ አንባቢ ግምት ውስጥ ያስገባልኝ።

የፍጥረት በኵር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
3፥47 *፡-ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፤ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል አላት*፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ
በ 325 ድህረ-ልደት በኒቂያ ጉባኤ በአትናቴዎስ እና በአርዮስ መካከል ውይይት ከተደረገ በኃላ የአርዮስ ተከታዮች ከዐበይት የሥላሴያውያን መሪዎች ግዝት እና ግዞት ደርሶባቸዋል፤ የአርዮስ እሳቤ ባዕዳና እንግዳ ኢያም ያረጀና ያፈጀ እሳቤ ሳይሆን ጳውሎሳዊ እሳቤ ነው፤ በግሪክ ኮይኔ “ፕሮቶኮስ” πρωτότοκος ማለት “በኵር” “ቀዳማይ” “መጀመሪያ” ማለት ነው፦
ቆላስይስ 1፥15 እርሱም የማይታይ አምላክ መልክ እና *”የፍጥረት ሁሉ በኵር ነው”*። who is the image of the invisible God, the firstborn of all creation; (English Revised Version)
ግሪክ፦ πρωτότοκος πάσης κτίσεως
“ፓሰስ” πάσης ማለት “ሁሉ” ማለት ነው፤ “የፍጥረት ሁሉ በኵር” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርት፤ “ክቲሶስ” κτίσεως ማለት “ፍጥረት” ማለት ነው። “ፍጡር” በነጠላ “ፍጥረት” በብዜት ነው፤ የፍጥረት ሁሉ በኵር ማለት መጀመሪያ የተፈጠረ ማለት ነው። ይህንን ናሙና ለመረዳት አንድ ተመሳሳይ ሰዋስው እንይ፦
ራእይ 1፥5 ከታመነውም ምስክር *”የሙታንም በኵር”* and from Jesus Christ, who is the faithful witness, the firstborn of the dead, (English Revised Version)
ግሪክ፦ πρωτότοκος τῶν νεκρῶν
“ኔክሮን” νεκρῶν ማለት “ሙታን” ማለት ነው። “ሙት” በነጠላ “ሙታን” በብዜት ነው፤ የሙታን በኵር ማለት መጀመሪያ የተነሳ ማለት ከሆነ የፍጥረት በኩር ማለት መጀመሪያ የተፈጠረ ማለት ካልሆነ ምን ማለት ነው? እንቀጥል፦
1 ቆሮንቶስ 15፥20 አሁን ግን *”ክርስቶስ ላንቀላፉት በኵር ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል”*።
ግሪክ፦ Νυνὶ δὲ Χριστὸς ἐγήγερται ἐκ νεκρῶν, ἀπαρχὴ τῶν κεκοιμημένων.
“በኵር” የሚለው የግሪኩ ቃል “አፕ-አርኬ” ἀπαρχὴ ሲሆን የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ “አፓ” ἀπό ማለትም “ከ” እና “አርኬ” ἀρχή ማለትም “መጀመሪያ” ነው፤ ላንቀላፉት ሙታን “መጀመሪያ” ነው ማለት መጀመሪያ የተነሳ ማለት ከሆነ የእግዚአብሔር ፍጥረት መጀመሪያ ማለት መጀመሪያ የተፈጠረ ማለት ነው፦
ራእይ 3፥14 አሜን የሆነው፥ የታመነውና እውነተኛው ምስክር፥ *”የእግዚአብሔር ፍጥረት መጀመሪያ”* የነበረው እንዲህ ይላል፦ the beginning of the creation of God. (English Revised Version)
ግሪኩ፦ ἡ ἀρχὴ τῆς κτίσεως τοῦ θεοῦ:

የእግዚአብሔር ፍጥረት መጀመሪያ” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ “መጀመሪያ” ለሚለው የገባው ቃል ልክ እንደ የሙታን መጀመሪያ “አርኬ” ἀρχή መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። ሌላው የእንስሳ በኵር ማለት ከእንስሳ የመጀመሪያው እንስሳ ማለት ነው፦
ዘሌዋውያን 27፥26 ለእግዚአብሔር ግን የሚቀርበውን *”የእንስሳ በኵር”* ማንም ይቀድሰው ዘንድ አይቻለውም፤ በሬ ቢሆን ወይም በግ ለእግዚአብሔር ነው።
የእንስሳ በኵር ማለት ከእንስሳ የመጀመሪያው እንስሳ ማለት ከሆነ የፍጥረት በኵር ማለት ከፍጥረት የመጀመሪያው ፍጡር ማለት ነው፤ ፍጥረት የሚለው አዲስ ፍጥረትን ነው የሚያመለክተው ብንል ኢየሱስ የአዲስ ፍጥረት በኩር ነው፦
ሮሜ 8፥29 *ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ*፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤
2ኛ ቆሮንቶስ 5፥17 ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን *”አዲስ ፍጥረት ነው”*፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።
“ሁሉም አዲስ ሆኗል” የሚለዉ ይሰመርበት፤ “ሁሉ” አንጻራዊ ከሆነ “የፍጥረት “ሁሉ” መጀመሪያ” ማለት የአዲስ ፍጥረት ሁሉ መጀመሪያ ማለት ነው፤ ግን ፍጥረት የሚለው አጠቃላይ ፍጥረትን ያመለክታል ከተባለ የፍጥረት በኵር ማለት ከሁሉ አስቀድሞ የተፈጠረ ማለት ነው፦
ምሳሌ 8፥22 *እግዚአብሔር ከሁሉ በፊት ፈጠረኝ*፥ (1980 አዲስ ትርጉም)
ግዕዝ፦
ምሳሌ 8፥22 “ፈጠረኒ እግዚእ መቅድመ ተግባሩ”
ኢንግሊሽ፦
Proverbs 8፥22 “The LORD made me as he began his planning, (International Standard Version)
ዕብራይስጥ፦
ምሳሌ 8፥22 יְהוָה–קָנָנִי, רֵאשִׁית דַּרְכּוֹ: קֶדֶם מִפְעָלָיו מֵאָז.
ግሪክ ሰፕቱአጀንት፦
Proverbs 8፥22 κύριος ἔκτισέν με ἀρχὴν ὁδῶν αὐτοῦ εἰς ἔργα αὐτοῦ
በተለይ በግሪኩ ሰፕቱአጀንት”LXX” ላይ “ኪትዞ” ἔκτισέν ማለት “ፈጠረኝ” ማለት ነው፤ በተመሳሳይ ዕብራይስጡ “ቃናኒ” קָ֭נָנִי ማለት “አስገኘኝ” ማለት ነው።
በዚህም አለ በዚያ ኢየሱስ ፍጡር መሆኑ አርዮሳዊ ብቻ ሳይሆን ጳውሎሳዊ አሊያም ባይብላዊ እሳቤ ነው። አምላካችን አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፤ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል፤ ከተፈጠሩት አንዱ የመርየም ልጅ ዒሣ ነው፦

የአላህ ስሞች
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
17፥180 *ለአላህም መልካም ስሞች አሉት፥ ስትጠሩት በእርሷም ጥሩት"*። وَلِلَّهِ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَى فَادْعُوهُ بِهَا
"ኢሥም" اِسْم የሚለው ቃል "ሠማ" سَمَّى ማለትም "ጠራ" "ሰየመ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መጠሪያ" ወይም "ስም" ማለት ነው፥ የኢሥም ብዙ ቁጥር "አሥማእ" أَسْمَاء ነው። "ስም" የአንድ ማንነት ወይም ምንነት "መጠሪያ" ነው። "አሏህ" ٱللَّه የሚለው ስም "ኢሥሙል ዐለም" اِسْم العَلَم ማለትም "የተጸውዖ ስም"proper name" ነው፥ ትርጉሙ "አምልኮ የሚገባው” ማለት ነው። ይህ ስም ስም 2699 ጊዜ በቁርኣን ተወስቷል፥ ይህ ስም የፈጣሪ ማንነት ስም ነው፦
34፥24 *«ከሰማያትና ከምድር ዝናብንና በቃይን የሚሰጣችሁ ማነው?» በላቸው፡፡ «አላህ ነው፡፡ እኛ ወይም እናንተ በትክክለኛው መንገድ ላይ ወይም በግልጽ መሳሳት ውስጥ ነን» በላቸው"*፡፡ قُلْ مَن يَرْزُقُكُم مِّنَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ قُلِ اللَّهُ ۖ وَإِنَّا أَوْ إِيَّاكُمْ لَعَلَىٰ هُدًى أَوْ فِي ضَلَالٍ مُّبِينٍ
29፥61 *"ሰማያትን እና ምድርን የፈጠረ፥ ፀሐይን እና ጨረቃንም የገራ ማን እንደኾነ ብትጠይቃቸው «በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል"*፡፡ ታድያ እንዴት ይመለሳሉ፡፡ وَلَئِن سَأَلْتَهُم مَّنْ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَسَخَّرَ الشَّمْسَ وَالْقَمَرَ لَيَقُولُنَّ اللَّهُ ۖ فَأَنَّىٰ يُؤْفَكُونَ
"መን" مَّنْ ማለት "ማን" ማለት ሲሆን ማንነትን ያሳያል፥ የፈጠረ ማን ነው? ለሚለው ጥያቄ መልሱ "አሏህ" ነው ማለቱ ይህንን ያሳያል፥ "እኔ አላህ እኔ ነኝ" ይህንን ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው፦
20፥14 *«እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና አምልከኝ*፡፡ ሶላትንም በእርሷ እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡ إِنَّنِىٓ أَنَا ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدْنِى وَأَقِمِ ٱلصَّلَوٰةَ لِذِكْرِىٓ
“አና” أَنَا ማለት “እኔ” ማለት ሲሆን አንድ ነጠላ ማንነትን የሚያሳይ ነጠላ ተውላጠ-ስም ነው፥ ይህ አንድ ማንነት አላህ ሲሆን ምንነቱ ደግሞ አምላክ ስለሆነ “ከእኔ ሌላ አምላክ የለም” በማለት ይናገራል፦
91፥5 *"በሰማይቱም በገነባትም"*። وَالسَّمَاءِ وَمَا بَنَاهَا
እዚህ አንቀጽ ላይ "ማ" مَا ማለትም "ምንድን" የሚለው "ኢሥሙል መውሱል" اِسْم المَوْصُول ማለትም "አንጻራዊ ተውላጠ-ስም" ሲሆን ምንነትን ያሳያል። አላህ ምንነቱን የሚገልጹ ከፍጡራኑ ጋር የማይመሳሰል “አሥማኡል ሑሥና” الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ ማለትም “መልካም ስሞች” አሉት፦

17፥110 *"አላህን ጥሩ ወይም አልረሕማንን ጥሩ፥ ማንኛውንም ብትጠሩ ለእርሱ መልካም ስሞች አሉትና በላቸው"* قُلِ ادْعُوا اللَّهَ أَوِ ادْعُوا الرَّحْمَنَ أَيًّا مَا تَدْعُوا فَلَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَى
20፥8 አላህ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ *”ለእርሱ መልካሞች የኾኑ ስሞች አሉት”*፡፡ اللَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ
29፥24 *"እርሱ አላህ ፈጣሪው ከኢምንት አስገኚው ቅርጽን አሳማሪው ነው፤ ለእርሱ መልካሞች ስሞች አሉት"*። هُوَ اللَّهُ الْخَالِقُ الْبَارِئُ الْمُصَوِّرُ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَى
አላህ ምንድን ነው? ተብሎ ሲጠየቅ ባሕርያቱ የተሰየሙበትን ስሞች በመጥራት “አል-ኻሊቅ” الْخَالِق “አስ-ሰመድ” الصَّمَد “አል-ገኒይ” الْغَنِيّ “አል-ለጢፍ” اللَّطِيف እያልን እንዘረዝራለን። በቁርኣን የተጠቀሱት እነዚህ የአላህ መልካም ስሞች ዘጠና ዘጠኝ ናቸው፥ እነርሱን እያፈዘ አላህን የሚጠራ መዳረሻው ጀነት ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 48, ሐዲስ 5
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"አላህ ዘጠና ዘጠኝ ስሞች አሉት፥ እነርሱን ያፈዘ ጀነት ገባ። አላህ አንድ ነው፥ አንድን ይወዳል"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ " لِلَّهِ تِسْعَةٌ وَتِسْعُونَ اسْمًا مَنْ حَفِظَهَا دَخَلَ الْجَنَّةَ وَإِنَّ اللَّهَ وِتْرٌ يُحِبُّ الْوِتْرَ

"የአላህ ስሞች ዘጠና ዘጠኝ ናቸው" ተብለው በቁጥር ስላልተወሰኑ "አላህ ዘጠና ዘጠኝ ስሞች አሉት" ተብሎ ተቀምጧል። ያ ማለት አላህ በቁርኣን ያልገለጻቸው ግን እርሱ ብቻ የሚያውቃቸው ስሞች እንዳሉት እሙንና ቅቡል ነው፦
ኢማም አሕመድ መጽሐፍ 5, ሐዲስ 267
ዐብደላህ ኢብን መስዑድ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "የአላህ መልክተኛም"ﷺ" አሉ፡- *"አንድ የአላህ ባሪያ ጭንቀትና ሃዘን ሲገጥመው፦ "አላህ ሆይ! እኔ ባሪያህ የባሪያህ ልጅ ነኝ፥ ማንነቴ በአንተ ቁጥጥር ሥር ነው። ውሳኔክ በእኔ ላይ ተፈጻሚ ነው፥ ፍርድህም ፍትሐዊ ነው። እኔም የአንተ በሆኑት ራስህን በሰየምክበት ስሞችክ ሁሉና በመጽሐፍህም ውስጥ በጠቀስከው፣ አንተ ዘንድም ብቻክን ባወቅከውና ከፍጡሮችህም ለማንኛውም ባላሳወከው ስሞችህ እለምንሀለሁ" አይልም አላህ ጭንቀቱንና ሃዘኑን ቢያስወግድለትና በምትኩም ደስታን ቢለግሰው እንጂ"*። عَنْ عَبْدِ اللهِ ابن مسعود رضي الله عنه، قَالَ : قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : " مَا قَالَ عَبْدٌ قَطُّ إِذَا أَصَابَهُ هَمٌّ وَحَزَنٌ : اللَّهُمَّ إِنِّي عَبْدُكَ ، وَابْنُ عَبْدِكَ ، ابْنُ أَمَتِكَ ، نَاصِيَتِي بِيَدِكَ ، مَاضٍ فِيَّ حُكْمُكَ ، عَدْلٌ فِيَّ قَضَاؤُكَ ، أَسْأَلُكَ بِكُلِّ اسْمٍ هُوَ لَكَ ، سَمَّيْتَ بِهِ نَفْسَكَ ، أَوْ أَنْزَلْتَهُ فِي كِتَابِكَ ، أَوْ عَلَّمْتَهُ أَحَدًا مِنْ خَلْقِكَ ، أَوِ اسْتَأْثَرْتَ بِهِ فِي عِلْمِ الْغَيْبِ عِنْدَكَ ،.... إِلاَّ أَذْهَبَ اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ هَمَّهُ ، وَأَبْدَلَهُ مَكَانَ حُزْنِهِ فَرَحًا
ነገር ግን በቁርኣን የተገለጹት ከፍጡራን ጋር የማይመሳሰሉ የአላህ ስሞች "ኢሥሙል መዕሪፍ" اِسْم اللمَعْرِف ይባላሉ፥ እነዚህን ስሞች በቋንቋችን ተርጉመን መሓሪው፣ አዛኙ፣ ንጉሡ፣ ይቅርባዩ ወዘተ እያልን መጥራት እንችላለን። በቁርኣን ከተጠቀሱት ከአላህ ዘጠና ዘጠኝ መልካም ስሞች መካከል ትልቁ ስም "አል-ኢሥሙል አዕዘም" ٱلْإِسْمُ ٱلْأَعْظَم ይባላል። ይህ ታላቁ ስሙ “አል-ሐዩል ቀዩም” الْحَيُّ الْقَيُّومُ ሲሆን ትርጉሙ “ሕያው አስተናባሪ" ማለት ነዉ፥ ይህ ታላቁ ስሙ በሦስት ሱራዎች በሱረቱል በቀራህ 2፥255 በሱረቱል አለ ዒምራን 3፥2 እና በሱረቱ አጥ-ጧሃ 20፥111 ውስጥ ይገኛል፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 34, ሐዲስ 30
ኪታቡል ዱዓእ ባብ 9
አል-ቃሢም እንደተረከው፦ *“የአላህ ታላቁ ስም በእርሱ አላህን ከጠሩት ጥሪውን ይመልሳል፥ ይህም በሦስት ሱራህ በአል-ቀራ፣ በአለ-ዒምራን እና አጥ-ጧሀ ውስጥ ይገኛል"*። عَنِ الْقَاسِمِ، قَالَ اسْمُ اللَّهِ الأَعْظَمُ الَّذِي إِذَا دُعِيَ بِهِ أَجَابَ فِي سُوَرٍ ثَلاَثٍ الْبَقَرَةِ وَآلِ عِمْرَانَ وَطَهَ
ታላቁ ሙፈሢር ኢብኑ ከሲር አያቱል ኩርሲይ ላይ ስለሚገኘው ታላቁ ስም እንዲህ ይላል፦
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 2፥255 "ኢማም አሕመድ በዘገበው ሐዲስ አሥማ ቢንት የዚድ ኢብኑ አሥ-ሠከን እንደተረከችው፦ *"የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ *"ሁለቱ አናቅጽ፦ 2፥255 "አላህ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ራሱን ቻይ ነው" እና 3፥1-2 "አሊፍ ላም ሚም አላህ ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፥ እርሱ ሕያው ሁሉን ነገር አስተናባሪ ነው" የሚሉት የአላህን ታላቁ ስም ይዘዋል"*። እንዲሁ በአቢ ዳውድ፣ በአት-ቲርሚዚይ፣ በኢብኑ ማጃህ እንደተዘገበው ሐሠን እና ሰሒሕ ናቸው።
በሌላ ዘገባ አቢ መርዱውያህ እንደዘገበው አቢ ኡማማህ"ረ.ዐ" እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" አሉ፦ *"የአላህ ታላቁ ስም በእርሱ አላህን ከጠሩት ጥሪውን ይመልሳል፥ ይህም በሦስት ሱራህ በአል-ቀራ፣ በአለ-ዒምራን እና አጥ-ጧሀ ውስጥ ይገኛል"*።
حديث آخر في اشتماله على اسم الله الأعظم : قال الإمام أحمد : حدثنا محمد بن بكر ، أخبرنا عبيد الله بن أبي زياد ، حدثنا شهر بن حوشب عن أسماء بنت يزيد بن السكن قالت : سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول في هاتين الآيتين ( الله لا إله إلا هو الحي القيوم ) و ( الم الله لا إله إلا هو الحي القيوم ) [ آل عمران : 1 ، " إن فيهما اسم الله الأعظم " .
وكذا رواه أبو داود عن مسدد ، والترمذي عن علي بن خشرم ، وابن ماجه عن أبي بكر بن أبي شيبة ، ثلاثتهم عن عيسى بن يونس عن عبيد الله بن أبي زياد به ، وقال الترمذي : حسن صحيح .
حديث آخر في معنى هذا عن أبي أمامة رضي الله عنه : قال ابن مردويه : أخبرنا عبد الرحمن بن نمير ، أخبرنا إسحاق بن إبراهيم بن إسماعيل ، أخبرنا هشام بن عمار ، أخبرنا الوليد بن مسلم ، أخبرنا عبد الله بن العلاء بن زيد : أنه سمع القاسم بن عبد الرحمن يحدث عن أبي أمامة يرفعه قال : " اسم الله الأعظم الذي إذا دعي به أجاب في ثلاث : سورة البقرة وآل عمران وطه "
አምላካችን አላህ በስሞቹ ዘክረነው ጀነት የምንገባ ያርገን! አሚን።

ኢየሱስ ይመለካልን?
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
5፥117 «በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል፦ *ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ* ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ
“ዒባዳ” عبادة የሚለው ቃል “ዓበደ عَبَدَ “አመለከ” ከሚል ግስ የተገኘ ሲሆን “አምልኮ” ማለት ነው፤ አምልኮ የሚገባው አንዱ አምላክ አላህ ብቻ ነው፤ አላህ ዒሳን በል ብሎ ያዘዘው ቃል፦ “ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ” ማለትን ነው፦

ነገር ግን በተቃራኒው ክርስቲያኖች ኢየሱስን በቀጥታ ያመልካሉ፤ “አምልኮ” የሚለው ቃል በእብራይስጥ “አቫድ” עָבַד ሲሆን በግሪክ ደግሞ “ላትሬኦ” λατρεύω ነው፤ ይህም ለአንዱ አምላክ ብቻ በሙሉ ሁለንተና የሚቀርብ ልመና፣ ስእለት፣ማጎብደድ፣ መተናነስ፣ ስግደት፣ መገዛት ፣ አገልግሎት Adoration ነው። ኢየሱስ፦ አምልኩኝ ያለበት፣ ሀዋርያት እና ነብያት፦ ኢየሱስን አምልኩ ያለበት እና ሰዎች ኢየሱስን ያመለኩበት አንድ አንቀጽ የለም። ነገር ግን ኢየሱስ የሚመለክ መሆኑን የሚጠቁሙ ጥቅሶች አሉ ይላሉ፤ እውን ይህ ጥቅስ ኢየሱስ ይመለካል ይላልን? እስቲ ጥቅሱን እንየው፦
ዳንኤል 7፥13-14 በሌሊት ራእይ አየሁ፤ እነሆም፥ “የሰው ልጅ የሚመስል” ከሰማይ ደመናት ጋር መጣ በዘመናት ወደ ሸመገለውም ደረሰ፤ ወደ ፊቱም አቀረቡት። ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ “ይገዙለት” δουλεύσουσιν ዘንድ ግዛትና ክብር መንግሥትም “ተሰጠው”፤ ግዛቱም የማያልፍ የዘላለም ግዛት ነው፥ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው።
ነጥብ አንድ
“የሰው ልጅ የሚመስል”
ዳንኤል በራእይ አራትም ታላላቅ አራዊት ከባሕር ሲወጡ አየ፤ እነዚህ አራቱ ታላላቅ አራዊት ከምድር የሚነሡ አራት ነገሥታት ናቸው፤ በራእይ ያየው “የሰው ልጅ የሚመስል” ደግሞ “የልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ” ነው፦
ዳንኤል 7፥27 መንግሥትም ግዛትም ከሰማይም ሁሉ በታች ያሉ የመንግሥታት ታላቅነት *”ለልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ”* ይሰጣል፤ መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ነው፥ ግዛቶችም ሁሉ “ይገዙለታል* δουλεύσουσι ይታዘዙለትማል።
ዳንኤል 7፥18 ነገር ግን *”የልዑሉ ቅዱሳን”* መንግሥቱን ይወስዳሉ፥ እስከ ዘላለም ዓለምም መንግሥቱን ይወርሳሉ።
ዳንኤል 7፥22 *”በዘመናት የሸመገለው እስኪመጣ ድረስ፥ ፍርድም ለልዑሉ ቅዱሳን እስኪሰጥ ድረስ”*፥ ቅዱሳኑም መንግሥቱን የሚወስዱበት ዘመን እስኪመጣ ድረስ አሸነፋቸውም።
ዘጸአት 19፥6 *”እናንተም የካህናት መንግሥት የተቀደሰም ሕዝብ ትሆኑልኛላችሁ”*። ለእስራኤል ልጆች የምትነግራቸው ቃል ይህ ነው።
የአይሁድ ኮሜንቴርይ፦ “የሰው ልጅ የሚመስል” የተባለው ዐውዱ ላይ የእስራኤል ሕዝብ ነው” ብለው የፈሠሩት። ዐውዱ ላይ የሰው ልጅ የሚመስል የልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ መሆኑን ፍትንው አርጎ ከዘጋ በኃላ ሌላ ትርጉም እንዳንሰጥ “የነገሩም ፍጻሜ እስከዚህ ድረስ ነው” በማለት ይቋጫል፦
ዳንኤል 7፥28 የነገሩም ፍጻሜ እስከዚህ ድረስ ነው።
ነጥብ ሁለት
“ተሰጠው”
ሙግቱን ጠበብ አድርገነው ዳንኤል ላይ “የሰው ልጅ የሚመስል” የተባለው ኢየሱስ ነው ቢባል እንኳን አሁንም ፍጡር ከመሆን የዘለለ ማንነት የለውም። ምክንያቱም በሃረጉ ውስጥ “ተሰጠው” የሚል ሃይለ-ቃል አለ፤ ሰጪው ደግሞ “በዘመናት የሸመገለው” አብ ነው፤ አንዱ አምላክ ለኢየሱስ የአባቱን ዙፋን ሰጥቶታል፦
ማቴዎስ 28፥18 ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ *ሥልጣን ሁሉ* በሰማይና በምድር *ተሰጠኝ*።
ሉቃስ 10፥22 *ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል*፥
ሉቃስ 1፥32 እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ *ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል*፤
ሰው እና የሰው ልጅ የተባለው ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ተለይቶ ፍጡር ነው፤ ታዲያ ይልቁንስ *ብስብስ የሆነ ሰው፥ ትልም የሆነ የሰው ልጅ በእግዚአብሔር ፊት ምንኛ ያንስ?
ዮሐንስ 13:31 ከወጣም በኋላ ኢየሱስ እንዲ አለ። *አሁን የሰው ልጅ ከበረ እግዚእብሔርም ሰለ እርሱ ከበረ*፤
ኢዮብ 25፥6 ይልቁንስ *ብስብስ የሆነ ሰው፥ ትልም የሆነ የሰው ልጅ ምንኛ ያንስ*!
የሰው ልጅ የሚመስል የሚባለው ኢየሱስ ነው ብንል እንኳን ኢየሱስ የሚመስለው አለ የሰው ልጅ የሚመስል ተብሏልና፤ ሰውን ይመስላል፤ ነገር ግን ነገር ግን ያ የሚመለከው አንዱ አምላክ የሚመስለው አለን? የለም፦
ኢዮብ 23:13 *እርሱ ግን ብቻውን ነው፤ እርሱንስ የሚመስለው ማን ነው?*

“ይገዙለት”
“ይገዙለት” ተብሎ በግሪክ ሰፕቱጀንት”LXX” ላይ የሰፈረው ቃል “ዱልኦስ” δοῦλος ነው፦
ዳንኤል 7፥14 ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ “ይገዙለት” δουλεύσουσιν ዘንድ ግዛትና ክብር መንግሥትም “ተሰጠው”፤ ግዛቱም የማያልፍ የዘላለም ግዛት ነው፥ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው።
“ይገዙለት” ተብሎ መገዛት የተገባው የሰው ልጅ የሚስመለው የልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ እንደሆነ ዐውዱ ላይ ፍንትውና ቁልጭ ብሎ ተቀምጧል፦
ዳንኤል 7፥27 መንግሥትም ግዛትም ከሰማይም ሁሉ በታች ያሉ የመንግሥታት ታላቅነት “ለልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ” ይሰጣል፤ መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ነው፥ ግዛቶችም ሁሉ “ይገዙለታል* δουλεύσουσι ይታዘዙለትማል።
አይ የሰው ልጅ የሚመስል የተባለው ኢየሱስ ነው፤ “ይገዙለት” ማለት “ያመልኩት” ዘንድ ማለት ነው ብላችሁ ከፈሰራችሁት የማትወጡት ገደል ውስጥ ትገባላችሁ፤ እንግዲያውስ የሚመለኩ አበዛዛቸው፦
ኢየሩሳሌም፦
ኢሳይያስ 60:12 ለአንቺም “የማይገዛ” δουλεύσουσί ሕዝብና መንግሥት ይጠፋል፥ እነዚያ አሕዛብም ፈጽመው ይጠፋሉ።
ያዕቆብ፦
ዘፍጥረት 25፥23 እግዚአብሔርም አላት፦ ሁለት ወገኖች በማኅፀንሽ ናቸው፥ ሁለቱም ሕዝብ ከሆድሽ ይከፈላሉ፤ ሕዝብም ከሕዝብ ይበረታል፤ ታላቁም ለታናሹ “ይገዛል” δουλεύσει ።
ዘፍጥረት 27፥29 አሕዛብ “ይገዙልህ” δουλευσάτωσάν ሕዝብም ይስገዱልህ፤
ሮሜ 8፥12 ለእርስዋ፦ ታላቁ ለታናሹ “ይገዛል” δουλεύσει ተባለላት።
“እርስ በእርስ”፦
ገላትያ 5፥13 ነገር ግን በፍቅር እርስ በእርሳችሁ “አገልግሉ” δουλεύετε ። KJV
ልብ አድርጉ ሁሉም ጋር መገዛት ተብሎ በግሪኩ ኮይኔ የቀረቡት ቃላት አንድ አይነት ነው።
በተለይ የክርስትና የዐቂዳህ መጽሐፍ የሆነው ሃይማኖተ-አበው ስጋ ፍጡር ነው ይሉን እና ተመልሰው አምላክ ነው ይላሉ፦
ሃይማኖተ-አበው ዘመጠሊጎን 44፥3
ዘመጠሊጎን አለ፦ “ወለሊሁ ሐነፀ ሥጋሁ ውስጠ ከርሠ ድንግል ወኢተሳተፎ መኑሂ በፈጢረ ሥጋሁ አላ ለሊሁ ባሕቲቱ ፈጠሮ”
ትርጉም፦ ” እርሱ ሥጋውን በድንግል ማሕፀን ፈጠረ፤ ሥጋውን በመፍጠር ማንም አጋዥ አልሆነውም፤ እርሱ እራሱ ፈጠረው እንጂ”
ሃይማኖተ-አበው ዘቄርሎስ 78፥31
ቄርሎስም አለ፦ “ወዓዲ ንቤ እስመ ሥጋሁ ለእግዚእነ ክርስቶስ አምላክ ውእቱ”
ትርጉም፦ ” ዳግመኛ የጌታችን የክርስቶስ ስጋ አምላክ እንደሆነ እንናገራለን”
ይህንን ህሊና ይቀበለዋል? ስጋው ምግብ ሲበላ የሚበላው ምግብ ሰውነት ሲሆን ይመለካልን? ሲከሳ ወይም ያ ምግብ ከሰውነት ሲወጣ አይመለክምን? ደሙ ስጋ ውስጥ እያለ የሚመለክ ሲፈስ የማይመለክ ነውን? ይህንን ውስብስብ ትምህርት እንኳን ልታስረዱን ይቅርና ለራሳችሁ አልገባችሁም። ኢየሱስ መመለክ የሚገባው እርሱ ሳይሆን የእርሱ አምላክ እንደሆነ በግልፅ ተናግሯል፦
ማቴዎስ 4፥10 ያን ጊዜ ኢየሱስ፦ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ *እርሱንም ብቻ አምልክ* λατρεύσεις ተብሎ ተጽፎአልና አለው።
አንድ ነጠላ ማንነት”person” ብቻ የሚመለክ መሆኑን ለማሳየት “እርሱ” የሚለው ነጠላ ተሳቢ-ተውላጠ ስም እና “ብቻ” በሚል ገላጭ”adjective” የሚመለከው ለኢየሱስ ንግስና የሰጠው ጌታ አምላክ ብቻ መሆኑን ያሳያል፤ ይህ ጌታም አምላክ አንድ ጌታ ነው፤ ይህ አንድ ጌታ ለእስራላልውያን የመረጠውን ኢየሱስን የላከ ነው፦

ማርቆስ 12፥29 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ፦ እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ *ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው*፥
ሐዋ ሥራ 3፥20 እንግዲህ *ከጌታ ፊት* የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ *የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ*፥ ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም።

ከሁሉ በላይ የሆነ አምላክ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
87፥1 *ከሁሉ በላይ የሆነዉን ጌታህን* ስም አሞግሥ። سَبِّحِ ٱسْمَ رَبِّكَ ٱلْأَعْلَى
በክርስትና ስልታዊ ሥነ-መለኮት”systematic theology” የአምላክ ሰው መሆን አስተምህሮት “ተሰግዎት”Incarnation” ሲባል፥ በአገራችን “ሚስጥረ-ስጋዌ” ይሉታል። “ስጋዌ” የሚለው ቃል “ስግው” ማለትም “ስጋ” ከሚለው የመጣ ነው፥ መለኮት በትስብእት ተገለጠ ብለው ድምዳሜ ላይ ያደረሳቸው የጳውሎስ ንግግር ነው። ለእኛ ለሙሥሊሞች ጳውሎስ የኢየሱስ ሐዋርያ ሳይሆን የግሪክንና የሮምን ዶክትሪን ከኢየሱስ ደክትሪን ጋር ለማስማማት የታገለ ጥሩ ፈላስፋ ነው። ነገር ግን ለክርስቲያኖች እንደ ነብይ ስለሚታይ የእርሱ ትምህርት ለሙሥሊም ማስረጃ ባይሆንም ለእነርሱ ግን መረጃ አድርገን እናቀርባለን። ብዙ ጊዜ ጳውሎስ ኢየሱስን ቁጭ የሚያደርገው ከአንዱ አምላክ ከአብ ነጥሎ ነው፥ ነገር ግን ክርስቲያኖች በተቃራኒው "ጳውሎስ ስለ ኢየሱስ አምላክነት ተናግሯል" ይላሉ። እዚህ ድምዳሜ ላይ አደረሰን ከሚሏቸው አናቅጽ መካከል አንዱን ጥቅስ በአጽንዖትና በአንክሮት እንመልከት፦
ሮሜ 9፥5 አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና፤ *"ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥ ከሁሉ በላይ የሆነ አምላክ እርሱ ለዘላለም የተባረከ ይሁን! አሜን*"። καὶ ἐξ ὁ Χριστὸς τὸ κατὰ σάρκα ὁ ὢν ἐπὶ πάντων Θεὸς εὐλογητὸς εἰς τοὺς αἰῶνας ἀμήν.
Whose are the fathers, and of whom as concerning the flesh Christ came. God, who is over all be blessed for ever. Amen.” Reivised standard version 1971 ,
ግሪኩ ላይ "ኤስቲን" ἐστιν ማለትም "ነው" የሚል ቃል የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጉም የግርጌ ማስታወሻ "ከሁሉ በላይ የሆነ አምላክ እርሱም ለዘላለም የተባረከ ይሁን" የሚል ፍቺ እንዳለው እሩቅ ሳንሄድ የዐማርኛ ምሁራን ይነግሩናል። በ 1971 ዕትም Reivised standard version "ይሁን"be" ብሎ አስቀጦጣታል "be blessed for ever"። "አሜን" የሚለው ቃል ለምስጋና የመጣ እስከሆነ ድረስ "ለዘላም የተባረከ ይሁን" ማለት ምስጋና ነው። ማነው ለዘላም የተባረከ ይሁን የተባለው? ስንል ለዘላም የተባረከ ይሁን የተባለው "ከሁሉ በላይ" የሆነ አምላክ ነው። እርሱም ከኢየሱስ እና ከመላው ፍጥረት ሁሉ በላይ የሆነው አብ ነው፦
ኤፌሶን 4፥6 *ከሁሉ በላይ የሚሆን πάντων በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ*።
ዮሐንስ 10፥29 *"የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ πάντων ይበልጣል"*።
ዮሐንስ 14፥28 የምትወዱኝስ ብትሆኑ *ከእኔ አብ ይበልጣልና* ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር።
ኢየሱስን የሚበልጠው አብ "ፓንቶን" πάντων ማለትም "ከሁሉ በላይ" ተብሏል። ልብ አድርግ "ክርስቶስ በሥጋ መጣ" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። በስጋ የመጣው አምላክ ሳይሆን ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ክርስቶስን ከዳዊት ዘር ያመጣው አምጪ አምላክ ነው፦
የሐዋርያት ሥራ 13፥23 *"ከዚህም ሰው ዘር "አምላክ" Θεὸς እንደ ተስፋው ቃል ለእስራኤል መድኃኒትን እርሱም ኢየሱስን አመጣ"*።
"አመጣ" የሚለው ቃል ይሰመርበት። አምጪው አምላክ መጪው ኢየሱስ ከሆነ፥ ክርስቶስን በስጋ ያመጣው አምጪው "ከሁሉ በላይ የሆነ አምላክ ለዘላለም የተባረከ ይሁን" መልእክቱ ይህ ነው። "ለዘላለም የተባረከ" ደግሞ የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እና አምላክ ነው፦
2ኛ ቆሮንቶስ 11፥31 *"ለዘላም የተባረከ εὐλογητὸς εἰς τοὺς αἰῶνας ἀμήν የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት"* እንዳልዋሽ ያውቃል።
ጳውሎስ አይሁዳዊ ነው፥ የሚሞግተውም የአይሁድ ዳራ ይዞ ነው። "ቶዩስ አዩናስ" τοὺς αἰῶνας ማለት "ከዘላለም እስከ ዘላለም" ማለት ነው፦
መዝሙር 41፥13 *"ከዘላለም እስከ ዘላለም የእስራኤል አምላክ ያህዌህ ይባረክ"። አሜን አሜን*።
መዝሙር 106፥48 *"ከዘላለም እስከ ዘላለም የእስራኤል አምላክ ያህዌህ ይባረክ፤ ሕዝብም ሁሉ አሜን ይበል"*። ሃሌ ሉያ።
ከዘላለም እስከ ዘላለም የተባረከ የእስራኤል አምላክ ያህዌህ ከሆነ፥ እስራኤላውያን አምላካችን የሚሉት ያህዌህን ነው፥ አምላካችን የሚሉት ኢየሱስን ሳይሆን አባቱን እንደሆነ እራሱ ኢየሱስ ተናግሯል፦
ዘዳግም 6፥4 *እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን ያህዌህ አንድ ያህዌህ ነው"*።
ዮሐንስ 8፥54 *"እናንተ አምላካችን የምትሉት አባቴ ነው"*።
የሮሜ መልእክት ጸሐፊ ክርስቶስን ለአምላክ ተቀበላችሁት፣ አምላክ የክርስቶስ አባት ነው፣ የክርስቶስ ራስ አምላክ ነው፣ ክርስቶስ የአምላክ ነው፣ ክርስቶስ በአምላክ ፊት ይታያል ወዘተ እያለ ለማምታታት ተመልሶ ክርስቶስ አምላክ ነው አይልም፦
ሮሜ 15፥7 ስለዚህ *"ክርስቶስ ለአምላክ Θεὸς ክብር እንደ ተቀበላችሁ"* እንዲሁ እርስ በርሳችሁ ተቀባበሉ።
ሮሜ 15፥6 በአንድ ልብ ሆናችሁ በአንድ አፍ *"አምላክን Θεὸς፥ እርሱም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት"*፥ ታከብሩ ዘንድ፥
1ኛ ቆሮንቶስ 11፥3 ነገር ግን የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ፥ የሴትም ራስ ወንድ፥ የክርስቶስም ራስ አምላክ Θεὸς እንደ ሆነ ልታውቁ እወዳለሁ"*"*
1ኛ ቆሮንቶስ 3፥23 *"ሁሉ የእናንተ ነው፥ እናንተም የክርስቶስ ናችሁ ክርስቶስም የአምላክ Θεὸς ነው*።
ዕብራውያን 9፥24 *"ክርስቶስ በእጅ ወደ ተሰራች፥ የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደ ምትሆን ቅድስት አልገባምና፥ ነገር ግን በአምላክ Θεὸς *ፊት* ስለ እኛ አሁን ይታይ ዘንድ ወደ እርስዋ ወደ ሰማይ ገባ"*።
ክርስቶስ አምላክ ሳይሆን የአምላክ ነው። አምላክ ክርስቶስ ሳይሆን የክርስቶስ አባት እና ራስ ነው። አምላክ በአምላክ ፊት ከታየ ሁለት አምላክ ሊሆን ነው፥ ቅሉ ግን በአምላክ ፊት ስለ አማንያን የሚታየው ክርስቶስ ነው። "ክርስቶስ" ማለት እራሱ "የተቀባ" ማለት ነው፥ ቀቢ አምላክ ተቀቢ ሰው ነው፦
የሐዋርያት ሥራ 10፥38 *"አምላክ Θεὸς የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ አምላክ Θεὸς ከእርሱ ጋር ነበረና"*።

ክርስቶስ አምላክ ሳይሆን አምላክ የቀባው እና አምላክ ከእርሱ ጋር የነበረ ሰው ነው። አምላክ አምላክን ለመርዳት አብሮት ነበር ማለት መድበለ-አማልክት ይሆናል። አይ አምላክ በክርስቶስ ሆኖ የዕርቅ ሥራ ሠራ እንጂ አምላክ ክርስቶስ አይደለም፦
2ኛ ቆሮንቶስ 5፥19 *"አምላክ Θεὸς በክርስቶስ ሆኖ"* ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና።
"አምላክ በአምላክ ሆኖ" ትርጉም አይሰጥም፥ ሁለት አምላክ ይሆናል። "አንድ ሰው ከሌላ ሰው ጋር ነበረ" ብሎ ሁለቱም አንድ ሰው ሳይሆኑ ሁለት ሰዎች ናቸው።
ስለዚህ ጳውሎስ ለማለት የፈለገው "ክርስቶስን በስጋ ያመጣ ከሁሉ በላይ የሆነ አምላክ አብ ለዘላለም የተባረከ ይሁን! አሜን" የሚል ብቻ ነው። በኢሥላም ከሁሉ በላይ የሆነዉ ጌታ አምላክ አላህ ብቻ ነው፥ እነዚያ መሲሢሑን "አላህ ነው" ያሉ በእርግጥ ካዱ። ይህ በአላህ አምላክነትን ላይ ሰውን ማሻረክ ነው፥ እነሆ በአላህ ላይ የሚያጋራ ሰው አላህ በእርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም ስላደረገበት እና መኖሪያውም እሳት ስለሆነች መሲሢሑን "አላህ ነው" የምትሉ የተውበት በሩ ሳይዘጋ በተውበት ወደ አላህ ተመለሱ፦
87፥1 *ከሁሉ በላይ የሆነዉን ጌታህን* ስም አሞግሥ። سَبِّحِ ٱسْمَ رَبِّكَ ٱلْأَعْلَى
5፥72 *" «አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ አልመሲህም አለ፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን ተገዙ፡፡» እነሆ! በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፡፡ መኖሪያውም እሳት ናት፡፡ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም"*፡፡ لَقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ ۖ وَقَالَ الْمَسِيحُ يَا بَنِي إِسْرَائِيلَ اعْبُدُوا اللَّهَ رَبِّي وَرَبَّكُمْ ۖ إِنَّهُ مَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ اللَّهُ عَلَيْهِ الْجَنَّةَ وَمَأْوَاهُ النَّارُ ۖ وَمَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ أَنصَارٍ