ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ጥቂት ቁሬይሾች በመዲና ላይ ያሉት አይሁዳዊያን ይህንን ቀን ይጾሙ ነበር። ይህ ቀን የኢሥራዒል ልጆች ከፈርዖን ነጻ የወጡበት ቀን ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 13 ሐዲስ 162
ኢብኑ ዐባሥ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ *”የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ወደ መዲና በመጡ ጊዜ አይሁዳውያን የዓሹራን ቀን ሲጾሙ አጤኑ፤ አይሁዳውያን ስለዚያ ቀንም ይጠይቁና፦ “አላህ ለሙሳ እና ለኢሥራዒል ልጆች በፈርዖን ላይ ድል የሰጠበት ነው” ብለው ይመልሱ ነበር። ነቢዩም”ﷺ”፦ “ከእናንተ ይልቅ እኛ ለሙሳ ቅርብ ነን” አሉ፤ ይህ ቀን እንዲጾም አዘዙን*። عَنِ ابْنِ، عَبَّاسٍ – رضى الله عنهما – قَالَ قَدِمَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْمَدِينَةَ فَوَجَدَ الْيَهُودَ يَصُومُونَ يَوْمَ عَاشُورَاءَ فَسُئِلُوا عَنْ ذَلِكَ فَقَالُوا هَذَا الْيَوْمُ الَّذِي أَظْهَرَ اللَّهُ فِيهِ مُوسَى وَبَنِي إِسْرَائِيلَ عَلَى فِرْعَوْنَ فَنَحْنُ نَصُومُهُ تَعْظِيمًا لَهُ ‏.‏ فَقَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ نَحْنُ أَوْلَى بِمُوسَى مِنْكُمْ ‏”‏ ‏.‏ فَأَمَرَ بِصَوْمِهِ

ሚሽነሪዎች በኢሥላም ያሉትን ሕግና ሥርዓት በመጽሐፋቸው መኖሩን ይጠይቃሉ፤ ከሌለ ለምን የለም? ብለው ይጠይቃሉ፤ ካለ ደግሞ ያው ተኮረጀ ይላሉ። ግን የሚገርመው ነገር ስለ ዓሹራ ቀን መጽሐፋቸው ላይ እያለ እንደማያነቡት ነው፦
ዘሌዋውያን 23፥34 ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ *በዚህ በሰባተኛው ወር ከአሥራ አምስተኛው ቀን ጀምሮ ሰባት ቀን ለእግዚአብሔር የዳስ በዓል ይሆናል*።
ዘሌዋውያን 23፥42-43 ሰባት ቀን በዳሶች ውስጥ ትቀመጣላችሁ፤ *ከግብፅ ምድር ባወጣኋቸው ጊዜ የእስራኤልን ልጆች በዳስ ውስጥ እንዳስቀመጥኋቸው የልጅ ልጆቻችሁ ያውቁ ዘንድ፥ በእስራኤል ያሉት የአገር ልጆች ሁሉ በዳስ ውስጥ ይቀመጡ*፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።

“ከግብፅ ምድር ባወጣኋቸው ጊዜ” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ ያ ወር በዕብራውያን አቆጣጠር ሰባተኛው ወር ሲሆን በእኛ ሙሐረም ነው፤ የሚያጅበው በዚህ ወር በዐሥረኛው ቀን እንዲጾሙ መታዘዙ ነው፦
ዘኍልቍ 29፥7 ከዚህም *ከሰባተኛው ወር በአሥረኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ፤ ሰውነታችሁን አስጨንቁት*፤ ከሥራ ሁሉ ምንም አታድርጉ።
ዘሌዋውያን 16፥30 *በሰባተኛው ወር ከወሩም በአስረኛው ቀን ራሳችሁን አስጨንቋት*፥ የአገር ልጅም በእናንተ መካከል የተቀመጠም እንግዳ ሥራን ሁሉ አትሥሩበት፤

“እራሳችሁን አስጨንቋት” ለሚለው ቃል የገባው “ወኢንኒተም” וְעִנִּיתֶ֖ם ሲሆን በኢንግሊሽ ትርጉም እና የተለያዩ ማብራሪያዎች ጾምን ታሳቢ እና ዋቢ ያደረገ እንደሆነ ገልጸዋል፤ አይሁዳውያን ይህንን ቀን እንደሚጾሙ እሙንና ቅቡል ነው። እኛም ነቢያችን”ﷺ” የሰጡንን ነገር ሁሉ እንድንይዝ አምላካችን አላህ በተከበረው ቃሉ ነግሮናል፦
59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡ وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

ስለዚህ በዚህ ቀን መጾሙ ሙስተሃብ ነው፤ በዚህ ቀን መጾሙ ያለው ትሩፋት የአላህ መልዕክተኛ”ﷺ” ተጠይቀው “ያለፈውን አንድ አመት ወንጀል ያስምራል” ብለዋል፦
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 7, ሐዲስ 1810
አቢ ቀታዳህ እንዳስተላለፉት፦ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ *”የዓሹራእ ቀን መጾም ያለፈውን አንድ ዓመት ወንጀል ከአላህ ያስተሰርያል”*። عَنْ أَبِي قَتَادَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ “‏ صِيَامُ يَوْمِ عَاشُورَاءَ إِنِّي أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሦስቱ መልእክተኞች

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

40፥78 *ከአንተ በፊትም መልክተኞችን በእርግጥ ልከናል፡፡ ከእነርሱ በአንተ ላይ የተረክንልህ አለ፥ ከእነርሱም በአንተ ላይ ያልተረክነው አለ*፡፡ وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلًا مِّن قَبْلِكَ مِنْهُم مَّن قَصَصْنَا عَلَيْكَ وَمِنْهُم مَّن لَّمْ نَقْصُصْ عَلَيْكَ

አምላካችን አላህ ከነቢያችን”ﷺ” በፊት መልእክተኞች ልኳል። ከእነርሱ ውስጥ በነቢያችን”ﷺ” ላይ ስማቸው የተተረኩ አሉ፥ ከእነርሱም ውስጥ ስማቸው ያልተተረኩ አሉ፦
40፥78 *ከአንተ በፊትም መልክተኞችን በእርግጥ ልከናል፡፡ ከእነርሱ በአንተ ላይ የተረክንልህ አለ፥ ከእነርሱም በአንተ ላይ ያልተረክነው አለ*፡፡ وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلًا مِّن قَبْلِكَ مِنْهُم مَّن قَصَصْنَا عَلَيْكَ وَمِنْهُم مَّن لَّمْ نَقْصُصْ عَلَيْكَ

ስማቸው ካልተተረኩት መልእክተኞች መካከል ሦስት መልእክተኞች ወደ አንዲት ከተማ ልኳል፦
36፥13 *ለእነርሱም የከተማይቱን ሰዎች ምሳሌ መልክተኞቹ በመጧት ጊዜ የኾነውን ግለጽላቸው*፡፡ وَٱضْرِبْ لَهُم مَّثَلًا أَصْحَٰبَ ٱلْقَرْيَةِ إِذْ جَآءَهَا ٱلْمُرْسَلُونَ
36፥14 *ወደ እነርሱ ሁለትን ሰዎች በላክን እና ባስተባበሉዋቸው ጊዜ በሶስተኛም በአበረታን እና "እኛ ወደ እናንተ መልክተኞች ነን" ባሏቸው ጊዜ የኾነውን ምሳሌ ግለጽላቸው*፡፡ إِذْ أَرْسَلْنَآ إِلَيْهِمُ ٱثْنَيْنِ فَكَذَّبُوهُمَا فَعَزَّزْنَا بِثَالِثٍۢ فَقَالُوٓا۟ إِنَّآ إِلَيْكُم مُّرْسَلُونَ

ታላቁ ሙፈሢር ኢሥማኢል ኢብኑ ከሲር በተፍሢራቸው ላይ ስለ እነዚህ ሦስት መልእክተኞች ማንነት በነቢብ እና በነሲብ የተተረከውን አስቀምጠዋል፦
አት-ተፍሢል ኢብኑ ከሲር ሱረቱ ያሲን 36፥13-14
*"ለእነርሱም የከተማይቱን ሰዎች ምሳሌ መልክተኞቹ በመጧት ጊዜ የኾነውን ግለጽላቸው" ኢብኑ ኢሥሓቅ ከከዕብ አል-አሕባር፣ ከወህብ ኢብኑ ሙነቢህ በተላለፈው ኢብኑ ዐባሥን መሠረት አድርጎ በዘገበው፦ "ያቺ ከተማይቱ አንጧኪያህ ናት፥ በእርሷም አንጢሕሥ የሚባል ንጉሥ ጣዖት የሚያመልክ የአንጢሕሥ ልጅ፣ የአንጢሕሥ ልጅ ነበረ። አላህ ወደ እርሱ ሦስት መልእክተኞችን ላከ፥ እነርሱም፦ ሷዲቅ፣ ሷዱቅ እና ሻሉም ናቸው። እርሱም በእነርሱ አስተባበለ።
ቡረይዳህ ኢብኑል ሑሰይብ ከዒክረማህ፣ ከቀደታህ እና ከአዝ-ዙህሪይ እንዳገኘው ያቺ ከተማይቱ አንጧኪያህ ናት ብሏል"*።

*"ከተማይቱ አንጧኪያህ ስለመሆኗ እና ከዚህ በታች የምንመለከተውን ትረካ ዐበይት ኢማሞች በታሪኩ ማብራሪያ እርግጠኛ አይደሉም። ኢንሻላህ ተዓላ "ወደ እነርሱ ሁለትን ሰዎች በላክን እና ባስተባበሉዋቸው ጊዜ በሶስተኛም በአበረታን እና እኛ ወደ እናንተ መልክተኞች ነን ባሏቸው ጊዜ የኾነውን ምሳሌ ግለጽላቸው" ሸዕይብ አል-ጀባኢይ ከወሕብ ኢብኑ ሡለይማን፣ ኢብኑ ጁረይጅ አለ ብሎ እንደተናገረው፦ "የመጀመሪያዎቹ ሁለት መልእክተኞች ስም ሸሙን እና ዩሐና ናቸው፥ ሦስተኛው ቡሉስ ነው። ከተማይቱ አንጧኪያህ ናት"*።
( مثلا أصحاب القرية إذ جاءها المرسلون ) .
قال ابن إسحاق - فيما بلغه عن ابن عباس ، وكعب الأحبار ، ووهب بن منبه - : إنها مدينة أنطاكية ، وكان بها ملك يقال له : أنطيخس بن أنطيخس بن أنطيخس ، وكان يعبد الأصنام ، فبعث الله إليه ثلاثة من الرسل ، وهم : صادق وصدوق وشلوم ، فكذبهم .
وهكذا روي عن بريدة بن الحصيب ، وعكرمة ، وقتادة ، والزهري : أنها أنطاكية .

وقد استشكل بعض الأئمة كونها أنطاكية ، بما سنذكره بعد تمام القصة ، إن شاء الله تعالى .
وقوله : ( إذ أرسلنا إليهم اثنين فكذبوهما ) أي : بادروهما بالتكذيب ، ( فعززنا بثالث ) أي : قويناهما وشددنا أزرهما برسول ثالث .
قال ابن جريج ، عن وهب بن سليمان ، عن شعيب الجبائي قال : كان اسم الرسولين الأولين شمعون ويوحنا ، واسم الثالث بولص ، والقرية أنطاكية .

ከላይ እንደተገለጸው የእነዚህ ሦስት መልእክተኞች ስም እና የከተማይቱ ስም በቁርኣን ላይ አልተገለጸም። ግን በተፍሢሩ ላይ ሁለት ዘገባዎች ተቀምጠዋል።
የመጀመሪያው ዘገባ ሦስት መልእክተኞች ሷዲቅ፣ ሷዱቅ እና ሻሉም የተባሉት ትረካ የተፋሰስ ወይም የላይዮሽ ትረካ”vertical narration” ሲሆን ከታች ትውልድ ወደ ላይ ትውልድ ሲወርድና ሲወራረድ ኢብኑ ኢሥሓቅ ከከዕብ አል-አሕባር፣ ከዕብ አል-አሕባር ደግሞ ከወህብ ኢብኑ ሙነቢህ፣ ወህብ ኢብኑ ሙነቢህ ደግሞ ከኢብኑ ዐባሥ የተገኘ ትረካ ነው፦
ኢብኑ ዐባሥ
|
ወህብ ኢብኑ ሙነቢህ
|
ከዕብ አል-አሕባር
|
ኢብኑ ኢሥሓቅ
ይህ የላይዮሽ ዘገባ ሙተሲል ነው። “ሙተሲል” مُتَّصِل ማለት ሰንሰለት የተቀበለበት “አያያዥ ማንነት” ነው። “ኢሥናድ” اِسْنَاد ማለት “ትርክት” ማለት ነው፥ ትረካው የሚተላለፍበት ሰንሰለት ደግሞ “ሠነድ” سَنَد ሲባል የሚያስተላልፈው “ተራኪ” ደግሞ “ሙሥነድ” مُسْنَد ይባላል። ኢሥናዱ፦ "አላህ ወደ እርሱ ሦስት መልእክተኞችን ላከ፥ እነርሱም፦ ሷዲቅ፣ ሷዱቅ እና ሻሉም ናቸው" የሚል ነው፥ ሠነዱ ከዕብ አል-አሕባር እና ወህብ ኢብኑ ሙነቢህ ሲሆን ሙሥነድ ደግሞ ኢብኑ ዐባሥ ነው። ኢብኑ ዐባሥ ደግሞ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” ሶሓቢይ ነው። ስለዚህ የኢብኑ ኢሥሓቅ ዘገባ አስተማማኝ ነው።
አንጢሕሥ በታሪክ ሦስተኛ አንጥያኮስ የተባለው ንጉሥ አንጥያኮስ ኤጴፋኔዎስ ሲሆን አያቱ ሁለተኝ አንጥያኮስ ቴኦስ፥ ቅድመ-አያቱ አንደኛው አንጥያኮስ ሶተር ይባላሉ። ይህ ንጉሥ በ 175 ቅድመ-ልደት ንግሥናን ጨብጧል፥ ዚየስ ኦሊምፒየስ የተባለውን ጣዖት በማምለክና የአሳማ ስጋ መስዋዕት በመሰዋቱ ይታወቃል። አንጧኪያህ በታሪክ አንጾኪያ የሚለው "አናጽ" ከምትባለው የጦርነት አምላክ ወይም "አንጥያኮስ" ከተባለው የነገሥታቱ ስም እንደመጣ ይነገራል። እንደ ኢብኑ ዐባሥ ትርክት አላህ ወደ እነርሱ ሦስት መልእክተኞችን ልኳል።
ሁለተኛው ዘገባ ሦስት መልእክተኞች ሸሙን፣ ዩሐና እና ቡሉስ የተባሉት ትረካ የአግድም ወይም የጎንዮሽ ትረካ”horizontal narration” ሲሆን በአንድ ትውልድ ሸዕይብ አል-ጀባኢይ ከወሕብ ኢብኑ ሡለይማን፥ ወሕብ ኢብኑ ሡለይማን ደግሞ ከኢብኑ ጁረይጅ የተገኘ ትረካ ነው፦
ሸዕይብ አል-ጀባኢይ – ወሕብ ኢብኑ ሡለይማን – ኢብኑ ጁረይጅ
ኢብኑ ጁረይጅ ከሦስተኛው ትውልድ ታቢዑ አት-ታቢዒን ከሚባሉት ነው።
ብዙ ጊዜ "ኢሥራኢሊያት" إِسْرَائِيلِيَّات ማለትም "የአይሁድ እና የክርስትና ትረካ" ያስተላልፋል። አባቱ ጁረይጅ ሲሆን የሮማ ክርስቲያን የነበረ፥ ስሙም ግሪጎሪ ነበር። የእርሱ ዘገባ ከሁለተኛ ትውልድ ከታቢዒይ እና ከመጀመሪያ ትውልድ ከሶሓቢይ የመጣ ኢሥናድ የለም። ሠነድ እና ሙሥነድ የሌለው ኢሥናድ ሙዐለቅ ነው፥ “ሙአለቅ” مُعَلَّق ማለት በሙሐዲስ እና በሙሥነድ መካከል ምንም አይነት ተራኪና ትረካ ሳይኖር ሲቀር “ሙዐለቅ” ይባላል። "ሙሐዲስ" مُحَدِيث ማለት "ዘጋቢ" ማለት ነው። ስለዚህ ከሸዕይብ አል-ጀባኢይ የተገኘው ዘገባ ደካማ ስለሆነ ውድቅ ነው።
ሲቀጥል ሸሙን ስምዖን ጴጥሮስ፣ ዩሐና ዮሐንስ እና ቡሉስ ጳውሎስ ከሆኑ እነዚህ ሦስት ሰዎች በዒሣ እና በነቢያችን"ﷺ" መካከል ያሉ ናቸው፥ በዒሣ እና በነቢያችን"ﷺ" መካከል ደግሞ ምንም ነቢይ የለም፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 43, ሐዲስ 190
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ከሰዎች ሁሉ ይልቅ ለዒሣ የመርየም ልጅ በዚህ ዓለም በመጨረሻይቱ ዓለም ቅርብ ነኝ። እነርሱም፦ "ይህ እንዴት ይሆናል? የአላህ መልእክተኛም፦ ሆይ!" አሉ። እርሳቸው፦ "ነቢያት ወንድማማቾች ናቸው፣ እናቶቻቸው ይለያያሉ፣ ነገር ግን ሃይማኖታቸው አንድ ነው። በእኔ እና በእርሱ መካከል አንድም ነቢይ የለም" አሉ"*። قَالَ هَذَا مَا حَدَّثَنَا أَبُو هُرَيْرَةَ، عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَذَكَرَ أَحَادِيثَ مِنْهَا وَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ أَنَا أَوْلَى النَّاسِ بِعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ فِي الأُولَى وَالآخِرَةِ ‏"‏.‏ قَالُوا كَيْفَ يَا رَسُولَ اللَّهِ قَالَ ‏"‏ الأَنْبِيَاءُ إِخْوَةٌ مِنْ عَلاَّتٍ وَأُمَّهَاتُهُمْ شَتَّى وَدِينُهُمْ وَاحِدٌ فَلَيْسَ بَيْنَنَا نَبِيٌّ ‏

ስለዚህ በኢየሱስ እና በነቢያችን"ﷺ" መካከል ያሉት ስምዖን ጴጥሮስ፣ ዮሐንስ እና ጳውሎስ ነቢይ ካልነበሩ ከሸዕይብ አል-ጀባኢይ የተገኘው ዘገባ ሙድጠሪብ ነው፥ “ሙድጠሪብ” مُضْطَرِب ማለት አንድ ዘገባ የተቃረኑ የዘገባ ሰነድ ሲኖረው ወይንም ዘገባው የተቃረነ መትን ሲኖረው “ሙድጠሪብ” ይባላል። ሢሰልስ ኢብኑ ከሲር፦ "ከዚህ በታች የምንመለከተውን ትረካ ዐበይት ኢማሞች በታሪኩ ማብራሪያ እርግጠኛ አይደሉም" ብሎ አስተማማኝ ትርክት እንዳልሆነ አበክሮና አዘክሮ አስቀምጧል። ሚሽነሪዎች ጳውሎስን በኢሥላም ውስጥ ለማስገባት እና "የአላህ መልእክተኛ ነው! ተቀበሉት" ለማለት ያቀረቡት ስሁት ሙግት ለዛሬ አልተሳካም። እዛው መንደራችሁ አቧራ አስነሱ እንጂ እዚህ እኛ ጋር ቅቤ ጥበሱልኝ፥ ዕጣን አጭሱልኝ፣ በሞቀበት ጣዱኝ የምትሉት ነገር በስሙር ሙግት ድባቅ ይገባል። "አምልጦኝና አዳልጦኝ ነው" ብትሉ ውልፍጥና ዝልፍጥ አንልም።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አንዲት ከተማ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

26፥208 *"አንዲትንም ከተማ ለእርሷ አስጠንቃቂዎች ያሏት እና ያስተባበለች ኾና እንጅ አላጠፋንም"*፡፡ وَمَا أَهْلَكْنَا مِن قَرْيَةٍ إِلَّا لَهَا مُنذِرُونَ

አምላካችም አላህ ለአንዲት ከተማ መልእክተኛ ልኮ መልእክቱን ከማስተባበሏ በፊት ማንንም አይቀጣም፥ ለእርሷ አስጠንቃቂ መልእክተኛ ከመጣላት በኃላ ያንን መልእክት ስታስተባብል ትጠፋለች፦
17፥15 *መልእክተኛንም እስከምንልክ ድረስ የምንቀጣ አይደለንም*፡፡ وَمَا كُنَّا مُعَذِّبِينَ حَتَّىٰ نَبْعَثَ رَسُولًا
26፥208 *"አንዲትንም ከተማ ለእርሷ አስጠንቃቂዎች ያሏት እና ያስተባበለች ኾና እንጅ አላጠፋንም"*፡፡ وَمَا أَهْلَكْنَا مِن قَرْيَةٍ إِلَّا لَهَا مُنذِرُونَ

አንዲት ከተማ ስትበድል አላህ በበደሏ ለማጥፋት ሲፈልግ ቅድሚያ መልእክተኛ ልኮ፥ ከዚያ በመልእክተኛው የተላለፈውን ትእዛዝ ሲያምጹ ያቺ ያመጸችውን ከተማ ቅጣቱ ይፈጸምባታል፥ ማጥፋትንም ያጠፋታል፦
17፥16 *"ከተማንም ለማጥፋት በፈለግን ጊዜ ነዋሪዎችዋን "እናዛለን"፡፡ በውስጧም ያምጻሉ፡፡ በእርሷም ላይ ቃሉ ቅጣቱ ይፈጸምባታል፡፡ ማጥፋትንም እናጠፋታለን"*፡፡ وَإِذَا أَرَدْنَا أَن نُّهْلِكَ قَرْيَةً أَمَرْنَا مُتْرَفِيهَا فَفَسَقُوا فِيهَا فَحَقَّ عَلَيْهَا الْقَوْلُ فَدَمَّرْنَاهَا تَدْمِيرًا

"እናዛለን" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። ይህንን ትእዛዝ በመልእክተኞቹ አንደበት ነዋሪዎችን እንዲታዘዙ ያዛል፥ ነዋሪዎች በእርሱ ሲያምጹ ያጠፋል፦
ተፍሢሩል ጀላለይን 17፥16
*"ከተማንም ለማጥፋት በፈለግን ጊዜ ነዋሪዎችዋን እናዛለን" በመልእክተኞቻችን አንደበት ነዋሪዎችን እንዲታዘዙ እናዛለን፥ "በውስጧም ያምጻሉ" ወጥተው በትእዛዛችን ላይ ያምጻሉ። "በእርሷም ላይ ቃሉ ቅጣቱ ይፈጸምባታል" በቅጣት ይፈጸምባታም፥ "ማጥፋትንም እናጠፋታለን" ሕዝቡን እና አበላሾችን በጥፋት እናጠፋታለን"*። { وَإِذآ أَرَدْنَا أَن نُّهْلِكَ قَرْيَةً أَمَرْنَآ مُتْرَفِيهَا } مُنَعمِّيها بمعنى رؤسائها بالطاعة على لسان رسلنا { فَفَسَقُواْ فِيهَا } فخرجوا عن أمرنا { فَحَقَّ عَلَيْهَا ٱلْقَوْلُ } بالعذاب { فَدَمَّرْنَٰهَا تَدْمِيرًا } أهلكناها بإهلاك أهلها وتخريبها.

ይህ የሚያዘውን ትእዛዝ ያመጸች መጥፎንም ቅጣት የቀጣት ብዙ ናት፥ በማንኛይቱም ከተማ ውስጥ አስጠንቃቂ መልእክተኛ ሲላክ ነዋሪዎችዋ፦ "እኛ አባቶቻችንን በሃይማኖት ላይ አገኘን፥ እኛም በፈለጎቻቸው ላይ ተከታዮች ነን" ይሉ ነበር፦
65፥8 *ከከተማም ከጌታዋ ትዕዛዝ እና ከመልክተኞቹም ያመጸች፣ ብርቱንም ቁጥጥር የተቆጣጠርናት፣ መጥፎንም ቅጣት የቀጣናት ብዙ ናት*፡፡ وَكَأَيِّن مِّن قَرْيَةٍ عَتَتْ عَنْ أَمْرِ رَبِّهَا وَرُسُلِهِ فَحَاسَبْنَاهَا حِسَابًا شَدِيدًا وَعَذَّبْنَاهَا عَذَابًا نُّكْرًا
43፥23 ነገሩ እንደዚሁም ነው፡፡ *ከበፊትህ በማንኛይቱም ከተማ ውስጥ አስጠንቃቂን አላክንም፤ ነዋሪዎችዋ እኛ አባቶቻችንን በሃይማኖት ላይ አገኘን፤ እኛም በፈለጎቻቸው ላይ ተከታዮች ነን ያሉ ቢኾኑ እንጅ*፡፡ وَكَذَٰلِكَ مَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ فِي قَرْيَةٍ مِّن نَّذِيرٍ إِلَّا قَالَ مُتْرَفُوهَا إِنَّا وَجَدْنَا آبَاءَنَا عَلَىٰ أُمَّةٍ وَإِنَّا عَلَىٰ آثَارِهِم مُّقْتَدُونَ

17፥16 እና 43፥23 ላይ "ሙትረፊን" مُتْرَفِين ማለት "ነዋሪዎች" ማለት ነው። የከተማ ነዋሪዎችዋ አስጠንቃቂ ሲላክላቸው፥ አስጠንቃቂ መልእክተኛ በተላከበት ትእዛዝ ከሓዲዎች ይሆናሉ፥ አላህ ማንኛይቱንም ከተማ ለእርሷ የተወሰነ መጽሐፍ ያላት ሆና፥ የአላህ አንቀጽ በእነርሱ ላይ የሚያነብ መልክተኛን ከላከ በኃላ ያንን ትእዛዝ ሲያስተባብሉ ያጠፋል፦
34፥34 *"በከተማም አስጠንቃቂን አላክንም፥ "ነዋሪዎችዋ" «እኛ በዚያ በእርሱ በተላካችሁበት ከሓዲዎች ነን» ያሉ ቢኾኑ እንጂ*"፡፡ وَمَا أَرْسَلْنَا فِي قَرْيَةٍ مِّن نَّذِيرٍ إِلَّا قَالَ مُتْرَفُوهَا إِنَّا بِمَا أُرْسِلْتُم بِهِ كَافِرُونَ
15፥4 *"ማንኛይቱንም ከተማ ለእርሷ የተወሰነ መጽሐፍ ያላት ኾና እንጂ አላጠፋንም"*፡፡ وَمَا أَهْلَكْنَا مِن قَرْيَةٍ إِلَّا وَلَهَا كِتَابٌ مَّعْلُومٌ
28፥59 *"ጌታህም ከተሞችን በዋናዋ ውስጥ አንቀጾቻችንን በእነርሱ ላይ የሚያነብ መልክተኛን እስከሚልክ ድረስ አጥፊ አልነበረም፡፡ ከተሞችንም ባለቤቶቿ በዳዮች ሆነው እንጅ አጥፊዎች አልነበርንም"*፡፡ وَمَا كَانَ رَبُّكَ مُهْلِكَ الْقُرَىٰ حَتَّىٰ يَبْعَثَ فِي أُمِّهَا رَسُولًا يَتْلُو عَلَيْهِمْ آيَاتِنَا ۚ وَمَا كُنَّا مُهْلِكِي الْقُرَىٰ إِلَّا وَأَهْلُهَا ظَالِمُونَ

ስለዚህ "እናዛለን" የሚለው ትእዛዝ መጽሐፉን ወይም አንቀጹን ነው እንጂ "እንዲያምጹ እናዛለን" ማለት በፍጹም አይደለም፥ ለማንሸዋረር አትሞክሩ። የቁርኣን አናቅጽ ነቅሶና ወቅሶ ለማውጣት እና እርሾና ጌሾ ጨምሮ ለማብኳትና ለማስከር ብትዳዱም በኢሥላም ዐቅብተ-እምነት ትጥቅና ስንቅ ይዘን መሞገትና መሟገት እንደሚቻል ምንጨታዊ ሙግታችን ጉልህ ማሳያ ነው።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ከሺርክ በስተጀርባ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

36፥60 *"የአደም ልጆች ሆይ! ሰይጣንን አታምልኩ! እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና በማለት ወደ እናንተ አላዘዝኩምን?* أَلَمْ أَعْهَدْ إِلَيْكُمْ يَا بَنِي آدَمَ أَن لَّا تَعْبُدُوا الشَّيْطَانَ ۖ إِنَّهُ لَكُمْ عَدُوٌّ مُّبِينٌ

“ዒባዳህ” عِبَادَة የሚለው ቃል “ዓበደ عَبَدَ ማለትም “አመለከ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “አምልኮ” ማለት ነው። ዒባዳህ በሦስት ይከፈላል፥ እርሱም፦
1ኛ. "ዒባደቱል ቀልቢያ" عِبَادَة قَلْبِيَّة ማለት "የኃልዮ አምልኮ” ማለት ነው፥ "ቀልብ" قَلْب ማለት "ኃልዮ" ወይም "ልብ" ማለት ነው።
2ኛ. "ዒባደቱል ቀውልያ” عِبَادَة قَوْلِيَّة ማለት "የነቢብ አምልኮ" ማለት ነው፥ "ቀውል" قَوْل ማለት "ነቢብ" ወይም "አንደበት" ማለት ነው።
3ኛ. "ዒባደቱል ዐመልያ" عِبَادَة عَمَلِيَّة ማለት "የገቢር አምልኮ" ማለት ነው፥ "ዐመል" عَمَل ማለት "ገቢር" ወይም "ድርጊት" ማለት ነው።

"ዱዓ" ደግሞ በቀውል ከሚከናወን ዒባዳህ አንዱ ነው፥ “ዱዓእ” دُعَآء የሚለው ቃል "ደዓ" دَعَا ማለትም "ለመነ" "ጠራ" "ጸለየ" "ተማጸነ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ልመና" "ጥሪ" "ጸሎት" "ተማጽንዖ" ማለት ነው። ዱዓእ የአንድ አምላክ የአላህ ሐቅና ገንዘብ ነው፦
2፥186 *”ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ “እኔ ቅርብ ነኝ፥ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ*”፡፡ ስለዚህ ለእኔ ይታዘዙ፤ በእኔም ይመኑ፤ እነርሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡ وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِي عَنِّي فَإِنِّي قَرِيبٌ ۖ أُجِيبُ دَعْوَةَ الدَّاعِ إِذَا دَعَانِ ۖ فَلْيَسْتَجِيبُوا لِي وَلْيُؤْمِنُوا بِي لَعَلَّهُمْ يَرْشُدُونَ
40፥60 ጌታችሁም አለ *«ለምኑኝ እቀበላችኋለሁና፡፡ እነዚያ እኔን ከማምለክ የሚኮሩት ተዋራጆች ኾነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ"*፡፡ وَقَالَ رَبُّكُمُ ادْعُونِي أَسْتَجِبْ لَكُمْ ۚ إِنَّ الَّذِينَ يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِي سَيَدْخُلُونَ جَهَنَّمَ دَاخِرِينَ
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 34, ሐዲስ 2
አን-ኑዕማን ኢብኑ በሺር እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" አሉ፦ *"ዱዓእ ዒባዳህ ነው፥ ከዚያም፦ "ጌታችሁም አለ *«ለምኑኝ እቀበላችኋለሁና" የሚለውን አንቀጽ ቀሩ"*። عَنِ النُّعْمَانِ بْنِ بَشِيرٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏"‏ إِنَّ الدُّعَاءَ هُوَ الْعِبَادَةُ ‏"‏ ‏.‏ ثُمَّ قَرَأَ ‏{وَقَالَ رَبُّكُمُ ادْعُونِي أَسْتَجِبْ لَكُمْ}‏

ዱዓእ አምልኮ ከሆነ አምልኮ የአላህ ብቻ ሐቅ እና የባሕርይው ገንዘቡ ነው፥ አላህ ወደ እርሱ ዱዓእ ለሚያደርጉት ቅርብ ነው፥ አላህ መለኮት ነው። መለኮት በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፣ ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፣ ሁሉን ሰሚ ነው፣ ሁሉን ተመልካች ነው፣ በነገሩ ሁሉ ላይ ተቆጣጣሪ ነው፦
29፥20 አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው”*። إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
65፥11 *”አላህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው”*፡፡ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ
58፥1 *”አላህ ሰሚ ተመልካች ነው”*፡፡ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ بَصِير
2፥110 *”አላህ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው”*፡፡ إِنَّ اللَّهَ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ
4፥86 *አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ተቆጣጣሪ ነውና*፡፡ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ حَسِيبًا

ነገር ግን ሰዎች ከዚህ በተቃራኒው ወደ ፍጡራን ዱዓእ ያረጋሉ። ፍጡራን ሁሉን የማወቅ፣ የመስማት፣ የማየት፣ የመቆጣር ችሎታ ውስንነት አለባቸው፥ ስለዚህ ወደ እነርሱ የሚደረግ ዱዓእ አይመልሱም፦
7፥194 *"እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትጠሯቸው እንደ እናንተ አምላኪዎች ናቸው፥ እውነተኞችም እንደሆናችሁ ጥሩዋቸው እና ለእናንተ ይመልሱላችሁ አይችሉም"*። إِنَّ ٱلَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ عِبَادٌ أَمْثَالُكُمْ ۖ فَٱدْعُوهُمْ فَلْيَسْتَجِيبُوا۟ لَكُمْ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ ።

እነርሱ እንደ ማንኛውም ፈጣሪን አምላኪ አምላኪዎች ናቸው እንጂ ተመላኪዎች አይደሉም። በክርስትና ዱዓእ ከሚደረግላቸው ፍጡራን መካከል መላእክት ናቸው፥ አላህ የትንሳኤ ቀን መላእክትን፦ "እነዚህ እናንተን ያመልኩ ነበሩን? ብሎ ይጠይቃቸዋል፤ እነርሱም በፍጹም፦ "ይልቁንም ጂንን ያመልኩ ነበሩ" ብለው ይመልሳሉ፦
34፥40 *"ሁሉንም በሚሰበስባቸው እና ከዚያም ለመላእክቶቹ፦ «እነዚህ እናንተን ያመልኩ ነበሩን?» በሚላቸው ቀን የሚኾነውን አስታውስ*፡፡ وَيَوْمَ يَحْشُرُهُمْ جَمِيعًا ثُمَّ يَقُولُ لِلْمَلَائِكَةِ أَهَـٰؤُلَاءِ إِيَّاكُمْ كَانُوا يَعْبُدُونَ
34፥41 *መላእክቶቹም፦ «ጥራት ይገባህ "ከእነርሱ ይልቅ ረዳታችን አንተ ብቻ ነህ፥ እንደሚሉት አይደለም፥ ይልቁንም ጂንን ያመልኩ ነበሩ፡፡ አብዛኞቻቸው በእነርሱ አማኞች ናቸው» ይላሉ*፡፡ قَالُوا سُبْحَانَكَ أَنتَ وَلِيُّنَا مِن دُونِهِم ۖ بَلْ كَانُوا يَعْبُدُونَ الْجِنَّ ۖ أَكْثَرُهُم بِهِم مُّؤْمِنُونَ

ልብ አድርግ አድርግ ሰዎች ወደ መላእክት በዱዓእ ዒባዳህ ቢጠቀሙም ግን ያንን ዒባዳህ የሚቀበሉት ጂኒዎች ናቸው። እዚህ ዐውድ ላይ ጂን የተባሉት ሸያጢን ናቸው፥ አንድ ሰው ጣዖት ሲያመልክ ከጣዖቱ በስተኃላ አምልኮ የሚቀበለው ሸይጧን ነው፦
19፥42 *"ለአባቱ «አባቴ ሆይ! የማይሰማንና የማያይን ከአንተም ምንንም የማይጠቅምህን ጣዖት ለምን ታመልካለህን? ባለ ጊዜ አስታውስ"*። إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ يَا أَبَتِ لِمَ تَعْبُدُ مَا لَا يَسْمَعُ وَلَا يُبْصِرُ وَلَا يُغْنِي عَنكَ شَيْئًا
19፥44 *«አባቴ ሆይ! ሰይጣንን አታምልክ፡፡ ሰይጣን ለአልረሕማን አመጸኛ ነውና"*፡፡ يَا أَبَتِ لَا تَعْبُدِ الشَّيْطَانَ ۖ إِنَّ الشَّيْطَانَ كَانَ لِلرَّحْمَـٰنِ عَصِيًّا
የኢብራሂም አባት የማይሰማና የማያይ ጣዖት ሲለማመን ከዚያ በስተኃላ የሚመለከው ሸይጧን ስለነበር፦ "አባቴ ሆይ! ሰይጣንን አታምልክ" አለው። እንግዲህ አንድ ሰው ፍጡራንን ሲጠራ ከአላህ ሌላ እረዳት አድርጎ በአላህ ላይ የሚያሻርከው ኩፋሩል ጂን የሆኑትን ሸያጢንን ነው፦
6፥100 *"ለአላህም ተጋሪዎች የፈጠራቸውን ጂንዎችን አደረጉ"*፡፡ ወንዶች ልጆችንና ሴቶች ልጆችንም ያለ ዕውቀት ለእርሱ ቀጠፉ፡፡ አላህ ጥራት የተገባው ከሚሉት ነገር የላቀ ነው፡፡ وَجَعَلُوا لِلَّهِ شُرَكَاءَ الْجِنَّ وَخَلَقَهُمْ ۖ وَخَرَقُوا لَهُ بَنِينَ وَبَنَاتٍ بِغَيْرِ عِلْمٍ ۚ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَىٰ عَمَّا يَصِفُونَ
7፥30 ከፊሉን ወደ ቅን መንገድ መራ፡፡ ከፊሎቹም በእነሱ ላይ ጥመት ተረጋግጦባቸዋል፡፡ *እነርሱ ሰይጣናትን ከአላህ ሌላ ረዳቶች አድርገው ይዘዋልና"*፡፡ እነርሱም ቅኑን መንገድ የተመራን ነን ብለው ያስባሉ፡፡ فَرِيقًا هَدَىٰ وَفَرِيقًا حَقَّ عَلَيْهِمُ الضَّلَالَةُ ۗ إِنَّهُمُ اتَّخَذُوا الشَّيَاطِينَ أَوْلِيَاءَ مِن دُونِ اللَّهِ وَيَحْسَبُونَ أَنَّهُم مُّهْتَدُونَ

አላህ ሰዎችን በቀጥተኛው መንገድ በኢሥላም ላይ ፈጥሮ ሳለ ሸያጢን ግን ከዚህ ዲን በሺርክ ምክንያት ሰዎችን ያርቃሉ፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐግ 53, ሐዲስ 76
ዒያድ ኢብኑ ሒማር እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" ኹጥባህ በሚደረግበት ቀን እንዲህ አሉ፦ *"ለእናንተ ያስተማርኩት ጌታዬ ያዘዘኝ፥ እናንተ የማታውቁትን እርሱ ዛሬ ያሳወቀኝን። አላህም አለ፦ "እኔ የሰጠኃቸውንና ሕጋዊ የሆነላቸው ያ ሁሉ ንብረት ነው። እኔ ሁሉንም ባሮቼን በቀጥተኛው መንገድ ላይ ፈጠርኳቸው፥ ሸያጢን መጥተው ከዲናቸው አራቋቸው"*። عَنْ عِيَاضِ بْنِ حِمَارٍ الْمُجَاشِعِيِّ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ذَاتَ يَوْمٍ فِي خُطْبَتِهِ ‏"‏ أَلاَ إِنَّ رَبِّي أَمَرَنِي أَنْ أُعَلِّمَكُمْ مَا جَهِلْتُمْ مِمَّا عَلَّمَنِي يَوْمِي هَذَا كُلُّ مَالٍ نَحَلْتُهُ عَبْدًا حَلاَلٌ وَإِنِّي خَلَقْتُ عِبَادِي حُنَفَاءَ كُلَّهُمْ وَإِنَّهُمْ أَتَتْهُمُ الشَّيَاطِينُ فَاجْتَالَتْهُمْ عَنْ دِينِهِم

እዚህ ሐዲስ ላይ "ሁነፋእ" حُنَفَاءَ የሚለው ቃል "ሐኒፍ" حَنِيف ለሚለው ብዙ ቁጥር ነው፥ አላህ ሰዎችን በእርስዋ ላይ የፈጠረባትን ሃይማኖት “ሐኒፋ” حَنِيفًا ናት፦
30፥30 *”ፊትህንም ወደ ቀጥተኛ ሃይማኖት ቀጥ አድርግ፡፡ የአላህን ፍጥረት ያችን አላህ ሰዎችን በእርስዋ ላይ የፈጠረባትን ሃይማኖት ያዟት፡፡ የአላህን ፍጥረት መለወጥ የለም፡፡ ይህ ቀጥተኛ ሃይማኖት ነው”*፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም፡፡ فَأَقِمْ وَجْهَكَ لِلدِّينِ حَنِيفًا ۚ فِطْرَتَ اللَّهِ الَّتِي فَطَرَ النَّاسَ عَلَيْهَا ۚ لَا تَبْدِيلَ لِخَلْقِ اللَّهِ ۚ ذَٰلِكَ الدِّينُ الْقَيِّمُ وَلَـٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ቀጥተኛ” ለሚለው ቃል የገባው “ሐኒፋ” حَنِيفًا ሲሆን አላህ ሰዎችን ሁሉ የፈጠረበት ሃይማኖት ኢሥላም “ሐኒፋ” መሆኑን ያሳያል። አንድ ሰው ፍጡርን በዱዓእ ከጠራ ከዱዓእ በስተኃላ ሸይጧን አምልኮ ስለሚቀበል አምላካችን አላህ በትንሳኤ ቀን፦ "ሸይጧንን አታምልኩ" "አምልኩኝ" ብሎ አዞ እንደነበር ይናገራል፦
36፥60 *የአደም ልጆች ሆይ! ሰይጣንን አታምልኩ! እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና በማለት ወደ እናንተ አላዘዝኩምን?* أَلَمْ أَعْهَدْ إِلَيْكُمْ يَا بَنِي آدَمَ أَن لَّا تَعْبُدُوا الشَّيْطَانَ ۖ إِنَّهُ لَكُمْ عَدُوٌّ مُّبِينٌ
36፥61 *"አምልኩኝ! ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው፤ በማለትም አላዘዝኩምን?"*፡፡ وَأَنِ اعْبُدُونِي ۚ هَـٰذَا صِرَاطٌ مُّسْتَقِيمٌ

ሺርክ በአላህ ላይ ሌሎች ማንነትንና ምንነትን በአምልኮ ማሻረክ ነው፥ ከሺርክ በስተጀርባ ይህንን አምልኮ የሚቀበሉት ሸያጢን ናቸው። ክርስቲያኖች ሆይ! ሳታውቁ የመስማት፣ የማየት፣ የማወቅ፣ የመቆጣጠር ውስንነት ባሕርይ ያለባቸውን ፍጡራንን ስትለማመኑ፣ ስትማጸኑ፣ ስትጠሩ ከነበረ እንግዲያውስ ባለማወቅ ነውና የተውበት በር ሳይዘጋ ወደ ዲኑል ኢሥላም ኑ እና የመስማት፣ የማየት፣ የማወቅ፣ የመቆጣጠር ውስንነት ባሕርይ የሌለበትን ፈጣሪን አላህን በብቸኝነት አብረን እናምልክ። ወደ ፍጡራን ዱዓእ በማድረግ በአላህ ላይ በማሻረክ ለሸያጢን አምልኮ ከመስጠት አላህ ይጠብቀን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የፀሐይ መጥለቂያ

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

18፥86 *"ወደ ፀሐይ መግቢያም በደረሰ ጊዜ ጥቁር ጭቃ ባላት ምንጭ ውስጥ ስትጠልቅ አገኛት"*፡፡ حَتَّىٰ إِذَا بَلَغَ مَغْرِبَ الشَّمْسِ وَجَدَهَا تَغْرُبُ فِي عَيْنٍ حَمِئَةٍ

ቀኝና ግራ፣ ታችና ላይ፣ ፊትና ኃላ፣ ውስጥና ውጪ፣ እዚህና እዚያ አንጻራዊ እውነት እንጂ ፍጹማዊ እውነት አይደም፥ እነዚህን ስምንቱን አመላካች አንጻራዊ ነጥብ ይወስነዋል። እንዲሁ ምስራቅና ምዕራብ፣ ሰሜንና ደቡብ አንጻዊ እውነታ ናቸው፦
18፥86 *"ወደ ፀሐይ መግቢያም በደረሰ ጊዜ ጥቁር ጭቃ ባላት ምንጭ ውስጥ ስትጠልቅ አገኛት"*፡፡ حَتَّىٰ إِذَا بَلَغَ مَغْرِبَ الشَّمْسِ وَجَدَهَا تَغْرُبُ فِي عَيْنٍ حَمِئَةٍ

"መግሪብ" مَغْرِب የሚለው ቃል "ገረበ" غَرَبَ ማለትም "ገባ" "ጠለቀ" "ተሰወረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መግቢያ" "መጥለቂያ" "መሰወሪያ" ማለት ነው። ከመነሻው ፀሐይ በፍጹማዊ እውነታ መግቢያና መውጫ የላትም፥ ከእኛ እይታ አንጻር የምትገባ እና የምትወጣ ስለሚመስለን ነው። ይህንን ከተረዳን እዚህ አንቀጽ ላይ "ስትጠልቅ" ለሚለው ቃል የገባው "ተግሩቡ" تَغْرُبُ ሲሆን “አል-ሙዷሪዕ” ٱلْمُضَارِع ነው። ስለዚህ ፀሐይ የጠለቀችው ለዙል-ቀርነይን ሲያያት እንጂ ቃል በቃል ፀሐይ አትጠቅም፤ አትወጣም። "ሐሚአህ" حَمِئَة ማለት "ጥቁር ጭቃ" ማለት ሲሆን ዙል-ቀርነይን ባደረገው ጉዞ ሜድትራትንያን ባሕር ውስጥ ስትገባ ታየችው፥ "ወጀደ" وَجَدَ ማለት "አገኘ" ማለት ሲሆን ጥቁር ጭቃ ባላት ምንጭ ውስጥ ስትጠልቅ እንዳያት ሁሉ ሕዝቦች ላይ ስትወጣ አገኛት፦
18፥90 *"ወደ ፀሐይ መውጫ በደረሰም ጊዜ ለእነርሱ ከበታችዋ መከለያን ባላደረግንላቸው ሕዝቦች ላይ ስትወጣ አገኛት"*፡፡ حَتَّىٰ إِذَا بَلَغَ مَطْلِعَ الشَّمْسِ وَجَدَهَا تَطْلُعُ عَلَىٰ قَوْمٍ لَّمْ نَجْعَل لَّهُم مِّن دُونِهَا سِتْرًا

"መጥሊዕ" مَطْلِع የሚለው ቃል "ጠለዐ" طَلَعَ ማለትም "ወጣ" "ተገለጠ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መውጫ" "መገለጫ" ማለት ነው። አሁንም "አገኘ" ለሚለው የተጠቀመበት ቃል "ወጀደ" وَجَدَ እንደሆነ አስተውል። ስትወጣ ለእነርሱ ከበታችዋ መከለያን በተደረገላቸው ሕዝቦች ላይ አንጻራዊ ከሆነ እንግዲያውስ ጥቁር ጭቃ ባላት ምንጭ ውስጥ ስትጠልቅ ማየቱ አንጻራዊ ነው። መውጣቷ ላይ "ዐላ" عَلَىٰ የሚለው መስተዋድድ አንጻራዊነትን እንደሚሳይ ሁሉ መግባቷ ላይም "ፊ" فِي የሚለው መስተዋድድ አንጻራዊነትን ያሳያል። እዚህ አንቀጽ ላይ "ስትወጣ" ለሚለው ቃል የገባው "ተጥሉዑ" تَطْلُعُ ሲሆን “አል-ሙዷሪዕ” ٱلْمُضَارِع ነው። ስለዚህ ፀሐይ የወጣችው ለዙል-ቀርነይን ሲያያት እንጂ ቃል በቃል ፀሐይ እንደማትወጣ ሁሉ ቃል በቃልም አትገባም።
እዚህ ድረስ ከተግባባን ሁለት ናሙና ከባይብል እንይ፦
ኢያሱ 1፥1 እንዲህም ሆነ፤ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ከሞተ በኋላ *እግዚአብሔር የሙሴን አገልጋይ የነዌን ልጅ ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው*፦
ኢያሱ 1፥4 ከምድረ በዳው ከዚህም ከሊባኖስ ጀምሮ እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ድረስ የኬጥያውያን ምድር ሁሉ *"እስከ ፀሐይ መግቢያ እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ"* ዳርቻችሁ ይሆናል።

እዚህ አንቀጽ ላይ ታላቁ ባሕር የፀሐይ መግቢያ እንደሆነ ይናገራል። ታዲያ የፀሐይ መግቢያ ታላቁ ባሕር ነውን? አይ "ይህ የተናገረው ኢያሱ ነው" እንዳትሉ "እግዚአብሔር የሙሴን አገልጋይ የነዌን ልጅ ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው" በማለት ይህንን የሚናገረው እግዚአብሔር መሆኑን ዐውዱ አስረግጦና ረግጦ ያስረዳል። ይህ ታላቁ ባሕር የሜዲትራኒያን ባሕር ነው፥ ኢያሱ ከነበረበት ከምድረ በዳው ከሊባኖስ አንጻር የተነገረ እንጂ ቃል በቃል ፀሐይ ታላቁ ባሕር ውስጥ በፍጹም አትገባም" ከተባለ እንግዲያውስ ከላይ ያለውን የቁርኣን አንቀጽ በዚህ ልክና መልክ ተረዱት፦
1 ነገሥት 22፥36 *"በሠራዊቱም መካከል ፀሐይ ስትገባ"*፦ ንጉሡ ሞቶአልና እያንዳንዱ ወደ ከተማው፥ እያንዳንዱም ወደ አገሩ ይሂድ፡ የሚል ጩኸት ሆነ።

"በሠራዊቱም መካከል ፀሐይ ስትገባ" የሚለው ይሰመርበት። በሠራዊት መካከል ፀሐይ ቃል በቃል ትገባለችን? እረ ይህ የሰው እይታ እንጂ ነባራዊ እውነታ አይደለም" ካላችሁ እንግዲያውስ ከላይ ያለውን የቁርኣን አንቀጽ በዚህ ስሌትና ቀመር ተረዱት። ኢንሻአላህ ይቀጥላል....

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የፀሐይ መጥለቂያ

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

36፥38 *ፀሐይም ለእርሷ ወደ ሆነው መርጊያ ትሮጣለች፡፡ ይህ የአሸናፊው የዐዋቂው አምላክ ውሳኔ ነው*፡፡ وَالشَّمْسُ تَجْرِي لِمُسْتَقَرٍّ لَّهَا ۚ ذَٰلِكَ تَقْدِيرُ الْعَزِيزِ الْعَلِيمِ

ሚሽነሪዎች ቁርኣንን ለመተቸት ሱሪ ባንገቴ ካሉ ሰነባበቱ፥ እኛ ደግሞ እግር እራስን እንደማያክ እናሳያቸዋለን። እስቲ የሚተቹበትን ሐዲሱን እንመልከት፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 32, ሐዲስ 34
አቢ ዘር እንደተረከው፦ "ፀሐይ ስትጠልቅ የአላህ መልክተኛ”ﷺ” በአህያ ላይ ተንቆናጠው ሳለ በአጠገባቸው ተቀምጬ ነበር። *"እርሳቸውም ፦"እርሷ ወደየት እንደምትገባ ታውቃለህን? አሉ። እኔም፦ "አላህ እና መልእክተኛው የበለጠ ያውቃሉ" አልኩኝ። እርሳቸውም፦ "በሞቀ ውኃ ምንጭ ውስጥ ትገባለች" አሉ"*። عَنْ أَبِي ذَرٍّ، قَالَ كُنْتُ رَدِيفَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَهُوَ عَلَى حِمَارٍ وَالشَّمْسُ عِنْدَ غُرُوبِهَا فَقَالَ ‏"‏ هَلْ تَدْرِي أَيْنَ تَغْرُبُ هَذِهِ ‏"‏ ‏.‏ قُلْتُ اللَّهُ وَرَسُولُهُ أَعْلَمُ ‏.‏ قَالَ ‏"‏ فَإِنَّهَا تَغْرُبُ فِي عَيْنِ حَامِيَة

እዚህ ሐዲስ ላይ "ሓሚያህ" حَامِيَةٍ ማለት "ሙቅ ውኃ" ማለት እንጂ ጥቁር ጭቃ ማለት አይደለም። "ጥቁር ጭቃ" ለማለት ከፈለጋችሁ "ሐሚአህ" حَمِئَة ነው። ሓሚያህ ከዐርሽ ሥር ያለ ውኃ ነው፦
11፥7 *"እርሱም ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ ነው፡፡ ዐርሹም በውሃ ላይ ነበር"*፡፡ وَهُوَ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ وَكَانَ عَرْشُهُ عَلَى الْمَاءِ
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 59, ሐዲስ 2
ዒምራም ኢብኑ ሑሰይን እንደተረከው፦ "ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *"በመጀመሪያ ምንም ነገር ሳይኖር አላህ ነበረ፣ ከዚያ ዙፋኑን በውኃ ላይ ነበረ፣ ከዚያ ሁሉን ነገር ጻፈ፣ ከዚያ ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ"*። عَنْ عِمْرَانَ بْنِ حُصَيْنٍ، قَالَ إِنِّي عِنْدَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم كَانَ اللَّهُ وَلَمْ يَكُنْ شَىْءٌ غَيْرُهُ، وَكَانَ عَرْشُهُ عَلَى الْمَاءِ، وَكَتَبَ فِي الذِّكْرِ كُلَّ شَىْءٍ، وَخَلَقَ السَّمَوَاتِ وَالأَرْضَ ‏

እዚህ ድረስ ከተግባባን "በሞቀ ውኃ ምንጭ ውስጥ ትገባለች" የሚለውን በኢማም ቡኻርይ ላይ "ከዐርሽ ሥር እስክትሰግድ ድረስ ትጓዛለች" ተብሎ በደንብ ተፈሥሯል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 4802
አቢ ዘር"ረ.ዐ" እንደተረከው፦ "አንድ ጊዜ ፀሐይ ስትጠልቅ ከነቢዩ”ﷺ” በመሥጂድ ሆኜ ሳለ፥ *"እርሳቸውም ፦"አቢ ዘር ሆይ! እርሷ ወደየት እንደምትገባ ታውቃለህን? አሉ። እኔም፦ "አላህ እና መልእክተኛው የበለጠ ያውቃሉ" አልኩኝ። እርሳቸውም፦ "ከዐርሽ ሥር እስክትሰግድ ድረስ ትጓዛለች፥ ይህ የአላህ ንግግር ነው፦ "ፀሐይም ለእርሷ ወደ ሆነው መርጊያ ትሮጣለች፡፡ ይህ የአሸናፊው የዐዋቂው አምላክ ውሳኔ ነው"*። عَنْ أَبِي ذَرٍّ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ كُنْتُ مَعَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم فِي الْمَسْجِدِ عِنْدَ غُرُوبِ الشَّمْسِ فَقَالَ ‏"‏ يَا أَبَا ذَرٍّ أَتَدْرِي أَيْنَ تَغْرُبُ الشَّمْسُ ‏"‌‏.‏ قُلْتُ اللَّهُ وَرَسُولُهُ أَعْلَمُ‏.‏ قَالَ ‏"‏ فَإِنَّهَا تَذْهَبُ حَتَّى تَسْجُدَ تَحْتَ الْعَرْشِ، فَذَلِكَ قَوْلُهُ تَعَالَى ‏{‏وَالشَّمْسُ تَجْرِي لِمُسْتَقَرٍّ لَهَا ذَلِكَ تَقْدِيرُ الْعَزِيزِ الْعَلِيمِ‏}‌‏"‏

የሥነ-ፈለክ ጥናት ታሪክን ወደ ኋላ መለስ ብለን ስንመለከት “ምድር የሥርዓተ-ፈለክ እምብርት”Geocentric” ናት" ተብሎ ይታመን ነበር። ነገር ግን በ1533 ድኅረ-ልደት ኒክላስ ኮፐርኒኮስ ምድር ሳትሆን ፀሐይ የሥርዓተ-ፈለክ እምብርት”Heliocentric” ናት" ብሎ ለመጀመሪያ ጊዜ ለዓለማችን አዲስ ጥናት አበረከተ። ያ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ፀሐይ ቋሚ እምብርት”stationary” እንጂ ትንቀሳቀሳለች ተብሎ አይታሰብም ነበር። ነገር ግን በ1783 ድኅረ-ልደት ዊሊያም ሃርቸል ፀሐይ በሰከንድ 16.5 ኪሎ ሜትር ትጓዛለች" ብሎ አዲስ ግኝት አመጣ፥ ይህ ጉዞ “ሶላር አፔክስ”solar apex” ይባላል። የምትሄድበትን ቦታ ምሁራን “local standard of rest”(LSR) አሊያም “Galactic Center” ይሉታል። ምሁራን ይህንን ጉዞዋን ሶላር አፔክስ ይበሉት እንጂ ከዐርሽ ሥር ወደላው ውኃ ልትጠልቅ እየተጓዘች እንደሆነ ከላይ ያለው ሐዲስ ያስረዳል። ይህ ከዐርሽ ሥር ያለው ውኃ ለእርሷ "መርጊያ" ተብሏል፦
36፥38 *ፀሐይም ለእርሷ ወደ ሆነው መርጊያ ትሮጣለች፡፡ ይህ የአሸናፊው የዐዋቂው አምላክ ውሳኔ ነው"*፡፡ وَالشَّمْسُ تَجْرِي لِمُسْتَقَرٍّ لَّهَا ۚ ذَٰلِكَ تَقْدِيرُ الْعَزِيزِ الْعَلِيمِ
በመቀጠል ከሄደችበት ስትመለስ የሚኖራት የጊዜ ፍጥነት በሰከንድ 19.7 ኪሎ ሜትር ነው" ተብሎ በዊሊያም ሃርቸል ተዘክሯል። ይህም ምልሰት “ሶላር አንታፔክስ”solar antapex” ይባላል። ከጠለቀችበት ተመልሳ ስትወጣ ቂያማህ ይቆማል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 59, ሐዲስ 10
አቢ ዘር"ረ.ዐ" እንደተረከው፦ "ነቢዩም”ﷺ” እኔን፦ *"ፀሐይ ወደየት እንደምትገባ ታውቃለህን? አሉ። እኔም፦ "አላህ እና መልእክተኛው የበለጠ ያውቃሉ" አልኩኝ። እርሳቸውም፦ "ከዐርሽ ሥር እስክትሰግድ ድረስ ትጓዛለች፥ ተመልሳ እንድትወጣ ትጠይቃለች"*። عَنْ أَبِي ذَرٍّ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم لأَبِي ذَرٍّ حِينَ غَرَبَتِ الشَّمْسُ ‏"‏ تَدْرِي أَيْنَ تَذْهَبُ ‏"‌‏.‏ قُلْتُ اللَّهُ وَرَسُولُهُ أَعْلَمُ‏.‏ قَالَ ‏"‏ فَإِنَّهَا تَذْهَبُ حَتَّى تَسْجُدَ تَحْتَ الْعَرْشِ، فَتَسْتَأْذِنَ فَيُؤْذَنَ لَهَا،
ሙሥነድ አሕመድ 21459
አቢ ዘር እንደተረከው፦ "አንድ ቀን ፀሐይ ስትጠልቅ ኮርቻ ወይም ድብዳብ ባለው አህያ ላይ ነቢዩ”ﷺ” ተቀምጠው ሳለ በአጠገባቸው ነበርኩኝ። *"እርሳቸውም ለእኔ፦ "አቢ ዘር ሆይ! ፀሐይ ወደየት እንደምትገባ ታውቃለህን? አሉ። እኔም፦ "አላህ እና መልእክተኛው የበለጠ ያውቃሉ" አልኩኝ። እርሳቸውም፦ "በሞቀ ውኃ ምንጭ ለጌታዋ በዐርሽ ሥር እስክትሰግድ ትገባለች" አሉ። በምትወጣበት ጊዜ አላህ እንድትወጣና እንድትገባ ይፈቅላታል፥ ግን ይዘጋላል። እርሷም፦ "ጌታ ሆይ! ለመጒዝ ረጅም ርቀት አለኝ" ትላለች። አላህም፦ "በጠለቅሽበት ውጪ" ይላታል። 6፥158 "አማኝ ያልኾነችን ነፍስ እምነትዋ ወይም በእምነትዋ ጊዜ በጎ ያልሠራችን ነፍስ ጸጸትዋ አይጠቅማትም"*።
عَنْ أَبِي ذَرٍّ قَالَ : كُنْتُ مَعَ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ عَلَى حِمَارٍ وَعَلَيْهِ بَرْذَعَةٌ أَوْ قَطِيفَةٌ. قَالَ : وَذَلِكَ عِنْدَ غُرُوبِ الشَّمْسِ. فَقَالَ لِي : " يَا أَبَا ذَرٍّ، هَلْ تَدْرِي أَيْنَ تَغِيبُ هَذِهِ ؟ ". قَالَ : قُلْتُ : اللَّهُ وَرَسُولُهُ أَعْلَمُ. قَالَ : " فَإِنَّهَا تَغْرُبُ فِي عَيْنٍ حَامِيَةٍ،تَنْطَلِقُ حَتَّى تَخِرَّ لِرَبِّهَا سَاجِدَةً تَحْتَ الْعَرْشِ، فَإِذَا حَانَ خُرُوجُهَا أَذِنَ اللَّهُ لَهَا فَتَخْرُجُ فَتَطْلُعُ، فَإِذَا أَرَادَ أَنْ يُطْلِعَهَا مِنْ حَيْثُ تَغْرُبُ حَبَسَهَا، فَتَقُولُ : يَا رَبِّ، إِنَّ مَسِيرِي بَعِيدٌ. فَيَقُولُ لَهَا : اطْلُعِي مِنْ حَيْثُ غِبْتِ." فَذَلِكَ حِينَ لَا يَنْفَعُ نَفْسًا إِيمَانُهَا ".
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 4635
አቢ ሁረይራህ"ረ.ዐ" እንደተረከው፦ "የአላህ መልክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"ፀሐይ በጠለቀበት እስክትወጣ ድረስ ሰአቲቱ(ትንሳኤ) አትቆምም"*። حَدَّثَنَا أَبُو هُرَيْرَةَ، رضى الله عنه قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لاَ تَقُومُ السَّاعَةُ حَتَّى تَطْلُعَ الشَّمْسُ مِنْ مَغْرِبِهَا،

የሚያጅበው ሁሉም ስለ ፀሐይ መጥለቅ በተዘገቡት ሐዲስ ላይ ተራኪው አቢ ዘር ነው። ስለዚህ በሐዲሳቱ ላይ የተጠቀሱት የፀሐይ በዐርሽ ሥር ካለው ውኃ መጥለቅ እና ዙልቀርነይን በጥቁር ጭቃ ስትጠልቅ ካያት ጋር ምንም አይነት ተዛምዶ የለውም። "ነቢያችሁ"ﷺ" ፀሐይ የምትጠልቀው ጥቁር ጭቃ ውስጥ ነው ብለዋል" ያላችሁት ቅጥፈት ተጋልጧል። አላህ ሂዳያህ ይስጣቸው፥ ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አወዛጋቢው ዶክትሪን

ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ የማን ባሪያ ነው?
ክርስቲያኑ፦ "የእግዚአብሔር ባሪያ ነው።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ እራሱ የራሱ ባሪያ ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "ኖ! የአብ ባሪያ እንጂ የራሱ ባሪያ አይደለም።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ አብ ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አይደለም።
ሙሥሊሙ፦ "አብ ማን ነው?
ክርስቲያኑ፦ "እግዚአብሔር ነው።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ እግዚአብሔር ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አዎ! በትክክል።

ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ የማን ነቢይ ነው?
ክርስቲያኑ፦ "የእግዚአብሔር ነቢይ ነው።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ እራሱ የራሱ ነቢይ ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "ኖ! የአብ ነቢይ እንጂ የራሱ ነቢይ አይደለም።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ አብ ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አይደለም።
ሙሥሊሙ፦ "አብ ማን ነው?
ክርስቲያኑ፦ "እግዚአብሔር ነው።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ እግዚአብሔር ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አዎ! በትክክል።

ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስን የላከው ማን ነው?
ክርስቲያኑ፦ "እግዚአብሔር።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ እራሱ በራሱ ላከው?
ክርስቲያኑ፦ "ኖ! አብ ነው የላከው እንጂ ራሱን በራሱ አላከውም።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ አብ ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አይደለም።
ሙሥሊሙ፦ "አብ ማን ነው?
ክርስቲያኑ፦ "እግዚአብሔር ነው።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ እግዚአብሔር ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አዎ! በትክክል።

ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ ሰውነቱ ፍጡር ነው?
ክርስቲያኑ፦ "አዎ!
ሙሥሊሙ፦ "ማን ፈጠረው?
ክርስቲያኑ፦ "እግዚአብሔር።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ እራሱ በራሱ ፈጠረው?
ክርስቲያኑ፦ "ኖ! አብ ነው የፈጠረው እንጂ ራሱ እራሱን አልፈጠረውም።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ አብ ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አይደለም።
ሙሥሊሙ፦ "አብ ማን ነው?
ክርስቲያኑ፦ "እግዚአብሔር ነው።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ እግዚአብሔር ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አዎ! በትክክል።

ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ ሲጸልይና ሲሰግድ የነበረው ወደ ማን ነው?
ክርስቲያኑ፦ "ወደ እግዚአብሔር።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ ሲጸልይና ሲሰግድ የነበረው ወደ ራሱ ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "ኖ! ወደ አብ ነው ሲጸልይና ሲሰግድ የነበረው እንጂ ወደ ራሱ አይደለም።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ አብ ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አይደለም።
ሙሥሊሙ፦ "አብ ማን ነው?
ክርስቲያኑ፦ "እግዚአብሔር ነው።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ እግዚአብሔር ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አዎ! በትክክል።

ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ አምላክ አለው?
ክርስቲያኑ፦ "አዎ!
ሙሥሊሙ፦ "አምላኩ ማን ነው?
ክርስቲያኑ፦ "እግዚአብሔር!
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ ራሱ የራሱ አምላክ ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "ኖ! አምላኩ አብ ነው እንጂ ራሱ የራሱ አምላክ አይደለም።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ አብ ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አይደለም።
ሙሥሊሙ፦ "አብ ማን ነው?
ክርስቲያኑ፦ "እግዚአብሔር ነው።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ እግዚአብሔር ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አዎ! በትክክል።

የዚህ ዶክትሪን መልስ ኅሊና ይቀበለዋልን? መልስ ለኅሊና።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ንብ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

16፥68 *"ጌታህም ወደ ንብ እንዲህ ሲል አስታወቀ፦ ”ከተራራዎች፣ ከዛፍም፣ ሰዎች ከሚሠሩትም ቀፎ ቤቶችን ያዢ”*፡፡ وَأَوْحَىٰ رَبُّكَ إِلَى النَّحْلِ أَنِ اتَّخِذِي مِنَ الْجِبَالِ بُيُوتًا وَمِنَ الشَّجَرِ وَمِمَّا يَعْرِشُونَ

ንብ በራሪ ነፍስ”insect” ናት፤ ከሦስት አፅቂዎች የምትመደብ ስትሆን ልክ እንደ ጉንዳን ካሉ “Hymenoptera” ቤተሰብ ትመደባለች፤ ይህቺ በራሪ ነፍስ በማር እና በሰም ምርቷ ትታወቃለች። በምድራችን ላይ ከ20,000 በላይ የታወቁ የንብ ዝርያዎች ሲኖሩ እነዚህም በዘጠኝ ታዋቂ ቤተሰቦች ተከፋፍለዋል፥ ምን አለፋን ከተጠቀሰው ቁጥር በላይ ዝርያዎች ሊኖሯቸውም ይችላል። ንብ የራሷን ቤቶች የምትሰራው ከተራራዎች፣ ከዛፍም፣ ሰዎች ከሚሠሩትም ቀፎ ነው፥ ይህንን ሥርዓት ያሳወቃት ንድፍ አውጪው አምላካችን አላህ ነው፦
16፥68 *ጌታህም ወደ ንብ* እንዲህ ሲል አስታወቀ፦ *”ከተራራዎች፣ ከዛፍም፣ ሰዎች ከሚሠሩትም ቀፎ ቤቶችን ያዢ”*፡፡ وَأَوْحَىٰ رَبُّكَ إِلَى النَّحْلِ أَنِ اتَّخِذِي مِنَ الْجِبَالِ بُيُوتًا وَمِنَ الشَّجَرِ وَمِمَّا يَعْرِشُونَ

ንብ አበባዎች ባሉበት ሁሉ ትገኛለች፥ የንብ አካላቷ በሦስት ክፍል ይከፈላል፦
በአንደኛው ክፍል የምታሸትበት፣ የምትዳስስበት፤ የምትሰግበት፣ በግንባሯ በስተቀኝና በስተግራ ሁለት ቀጫጭን ነገሮች እንደ ቀንድ የሆኑ አሏት፤ ደግሞ በዚህ በገጿ ላይ ሁለት ትልልቅ ጠፍጣፋ ዓይኖች በግራና በቀኝ ሆነው ለማየት የሚያስችሏት በሌሎች ትንንሽ ዓይኖች የተሞሉ አሏት።
በሁለተኛው ክፍል የአካሏ ክፍል ፀጉራሞች የሆኑ በአበባ ውስጥ ያለውን ኔክታር ማለትም ፈሳሽ ነገር ስትመጥ የአበባ ዱቄት የምታመጣባቸው ስድስት እግሮች፣ ሁለት ወፈር ያሉ ክንፎችና ሌሎች ሁለት ሳሳ ያሉ ክንፎች በጠንካሮች ሥር የሆኑ አሏት።
በሦስተኛው የአካላት ክፍሏ እንደ አንጓ ክርክር ያላቸው መተንፈሻዎች የምትነድፍበትና የተበላሸውን የምታስወጣበት አሏት። ከፍራፍሬ ከሚገኘው የአበባ ዱቄት ምግቧን ትብላለች፤ ይህንን የተፈጥሮ ሥርአት የነደፈላት አምላካችን አላህ ነው፦
16፥69 *«ከዚያም “ከ”ፍሬዎች ሁሉ ብይ*፡፡ ثُمَّ كُلِي مِن كُلِّ الثَّمَرَات

“ፍሬዎች” በሚለው ቃል ላይ “ሚን” مِن ማለትም “ከ” የሚል መስተዋድድ መነሻ ቅጥያ ሆኖ መግባቱ ከፍሬዎች ሁሉ መካከል መብላቷን ያሳያል እንጂ ፍሬዎችን ሁሉ መብላቷን አያሳይም። ንብ ወለላን ቱቦ በመሰለው ምላሷ ከፍራፍሬ ከሚገኘው የአበባ ዱቄት”nectar” ቅሥም አውላ እየቀሰመች በሆዷ ውስጥ ባለ የማር ቋት ውስጥ ታጠራቅማለች፤ አምላካችን አላህ፦ “ከሆዶችዋ መልኮቹ የተለያዩ መጠጥ ይወጣል” የሚለው ይህንኑ ነው፤ ከዚያም ተሸክማ ወደ ወደ ቀፎዋ ትወስደዋለች፤ ቀጥሎም ፈሳሽ የአበባ ወለላውን ወደ ሌሎች ንቦች ታዘዋውረዋለች፤ ወለላውን በአፏ ውስጥ ካሉት እጢዎች ከሚመነጭ ኢንዛይም ጋር እያዋሐደች ለአንድ ሰዓት ከግማሽ ያህል ታላምጠዋለች፤ ከዚያም ከሰም በተሠሩ ባለ ስድስት ማዕዘን ክፍሎች ውስጥ ታስቀምጥና እርጥበቱ እንዲተን በክንፎቿ ታራግባለች፤ የውኃው መጠን ከ18 በመቶ በታች ሲሆን ክፍሎቹን በሰም በስሱ ትሸፍነዋለች፤ በዚህ መልኩ የተሸፈነ ማር ሳይበላሽ ለዘመናት ሊቆይ ይችላል። ይህ ማር ምግብ ከመሆኑም ባሻገር በቫይታሚን ቢ፣ በተለያዩ ማዕድናት እና አንቲኦክሲደንትስ በተባሉ ንጥረ ነገሮች የበለጸገ ስለሆኑ መድኃኒት ነው፤ ማር ቁስልን፣ የተቃጠለ የአካል ክፍልን፣ የዓይን ቆዳ መሸብሸብን እና በቆዳ ላይ የሚወጣ ቁስልን ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ የጤና ችግሮችን ለማከም ዛሬ አገልግሎት ላይ ይውላል፤ ንብ በአበባ ፈሳሹ ላይ ኢንዛይም ስለምትረጭ ማር ለስለስ ያለ የፀረ ባክቴሪያነትና አንቲባዮቲክነት ባሕርይ እንዳለው ጥናቶች ይጠቁማሉ። ይህንን ያገራላት አምላካችን አላህ ነው፤ በማር ውስጥ ለሰዎች መድኃኒት እና ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምር አለበት፦
16፥69 *የጌታሽንም መንገዶች ላንቺ የተገሩ ሲኾኑ ግቢ፡፡» ከሆዶችዋ መልኮቹ የተለያዩ መጠጥ ይወጣል፡፡ በእርሱ ውስጥ ለሰዎች መድኃኒት አለበት፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምር አለበት*፡፡ فَاسْلُكِي سُبُلَ رَبِّكِ ذُلُلًا ۚ يَخْرُجُ مِن بُطُونِهَا شَرَابٌ مُّخْتَلِفٌ أَلْوَانُهُ فِيهِ شِفَاءٌ لِّلنَّاسِ ۗ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
መላእክት እንዴት ዐወቁ?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

49፥18 *”አላህ የሰማያትን እና የምድርን ሩቅ ሚስጥር ያውቃል”*። إِنَّ ٱللَّهَ يَعْلَمُ غَيْبَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ

“አል-ገይብ” ٱلْغَيْب ማለት “የሩቅ ሚስጥር” ማለት ሲሆን ከሩቅ ሚስጥራት መካከል “አል-ገይቡል ሙሥተቅበል” ٱلْغَيْب ٱلْمُسْتَقْبَل ማለት “መጻእያት የሩቅ ሚስጥር” ነው፦
49፥18 *”አላህ የሰማያትን እና የምድርን ሩቅ ሚስጥር ያውቃል”*። إِنَّ ٱللَّهَ يَعْلَمُ غَيْبَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ

ሰው ከመፈጠሩ በፊት ምን እንደሚያደርግ አላህ ቀድሞውኑ ያውቀዋል። ሰው ከሚያደርጋቸው መካከል በምድር ውስጥ ማጥፋት እና ደም ማፍሰስ ነው፦
26፥152 *«የእነዚያን በምድር ውስጥ የሚያጠፉትን እና የማያበጁትን፡፡»* الَّذِينَ يُفْسِدُونَ فِي الْأَرْضِ وَلَا يُصْلِحُونَ
2፥84 *"ደሞቻችሁን አታፍስሱ ነፍሶቻችሁንም ከፊላችሁን ከአገሮቻችሁ አታውጡ የምንል ስንኾን የጠበቀ ቃል ኪዳናችሁን በያዝንባችሁ ጊዜ አስታውሱ"*፡፡ وَإِذْ أَخَذْنَا مِيثَاقَكُمْ لَا تَسْفِكُونَ دِمَاءَكُمْ وَلَا تُخْرِجُونَ أَنفُسَكُم مِّن دِيَارِكُمْ

ሰው በምድር ውስጥ እንደሚያጠፋ እና ደም እንደሚያፈስ ከመፈጠሩ በፊት መላእክት ያውቁ ነበር፦
2፥30 *ጌታህ ለመላእክት፡- «እኔ በምድር ላይ ምትክን አድራጊ ነኝ፤» ባለ ጊዜ የኾነውን አስታውስ። እነርሱም «እኛ ከማመስገን ጋር የምናጠራህ፥ ለአንተም የምንቀድስ ስንኾን በእርሷ ውስጥ የሚያጠፋን እና ደሞችንም የሚያፈስን ታደርጋለህን?» አሉ፡፡ አላህም «እኔ የማታውቁትን ነገር አውቃለሁ» አላቸው*፡፡ وَإِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي جَاعِلٌ فِي الْأَرْضِ خَلِيفَةً ۖ قَالُوا أَتَجْعَلُ فِيهَا مَن يُفْسِدُ فِيهَا وَيَسْفِكُ الدِّمَاءَ وَنَحْنُ نُسَبِّحُ بِحَمْدِكَ وَنُقَدِّسُ لَكَ ۖ قَالَ إِنِّي أَعْلَمُ مَا لَا تَعْلَمُون

አላህ ለመላእክት፡- "እኔ በምድር ላይ ምትክን አድራጊ ነኝ" ሲል፥ እነርሱም፦ "በእርሷ ውስጥ የሚያጠፋን እና ደሞችንም የሚያፈስን ታደርጋለህን? አሉት። ይህንን እንዴት ዐወቁ? ለሚለው ጥያቄ መልሱ አላህ ዐሳውቋቸው ነው፦
2፥32 *«ጥራት ይገባህ፤ ካሳወከን ነገር በስተቀር ለእኛ ዕውቀት የለንም፡፡ አንተ ዐዋቂው ጥበበኛው አንተ ብቻ ነህና» አሉ*፡፡ قَالُوا سُبْحَانَكَ لَا عِلْمَ لَنَا إِلَّا مَا عَلَّمْتَنَا ۖ إِنَّكَ أَنتَ الْعَلِيمُ الْحَكِيمُ

"ካሳወከን ነገር በስተቀር ለእኛ ዕውቀት የለንም" ካሉ አላህ ካሳወቃቸው ውጪ በራሳቸው ዕውቀት ከሌላቸው ሰው በምድር ውስጥ እንደሚያጠፋ እና ደም እንደሚያፈስ ከመፈጠሩ በፊት አላህ ዐሳውቋቸዋል። እንዲገባችሁ ከባይብል ሁለት ጥቅሶችን እንመልከት፦
ዘፍጥረት 16፥11-12 *"የእግዚአብሔር መልአክም አላት፦ እነሆ አንቺ ፀንሰሻል፥ ወንድ ልጅንም ትወልጃለሽ፤ ስሙንም እስማኤል ብለሽ ትጠሪዋለሽ፥ እግዚአብሔር መቸገርሽን ሰምቶአልና። እርሱም የበዳ አህያን የሚመስል ሰው ይሆናል፥ እጁ በሁሉ ላይ ይሆናል፥ የሁሉም እጅ ደግሞ በእርሱ ላይ ይሆናል፤ እርሱም በወንድሞቹ ሁሉ ፊት ይኖራል*።

መልአኩ እስማኤል ከመፀነሱ በፊት መልአኩ አጋር እንደምትፀንስ፥ ወንድ ልጅንም እንደምትወልድ፤ ስሙንም እስማኤል ብላ እንደምትጠራው። እስማኤል የበዳ አህያን የሚመስል ሰው እንደሚሆን፥ እጁ በሁሉ ላይ እንደሚሆን፥ የሁሉም እጅ ደግሞ በእርሱ ላይ እንደሚሆን፤ እርሱም በወንድሞቹ ሁሉ ፊት እንደሚኖር በምን ዐወቀ? እንዴ! "እግዚአብሔር ለመልአኩ ቀድሞውኑ ዐሳውቋቸው እንጂ መላእክት የቀደመ ዕውቀት በራሳቸው የላቸውም" ከሆነ መልሱ እንግዲያውስ ከላይ ያለውንም እሳቤ በዚህ ስሌት መረዳት ይቻላል፦
መሣፍንት 13፥5 *እነሆ ትፀንሻለሽ፥ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ልጁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናልና በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፤ እርሱም እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ማዳን ይጀምራል*።

መልአኩ ሳምሶን ከመፀነሱ በፊት መልአኩ የማኑሄ ሚስት እንደምትፀንስ፥ ወንድ ልጅንም እንደምትወልድ። ሳምሶን ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ እንደሚሆን፥ በራሱ ላይ ምላጭ እንደማይደርስበት። ሳምሶን እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ማዳን እንደሚጀምር በምን ዐወቀ? እንዴ! "እግዚአብሔር ለመልአኩ ቀድሞውኑ ዐሳውቋቸው እንጂ መላእክት የቀደመ ዕውቀት በራሳቸው የላቸውም" ከሆነ መልሱ እንግዲያውስ ከላይ ያለውንም እሳቤ በዚህ ሒሳብ መረዳት ይቻላል። ተግባባን አይደል? አዎ! ግን ለመላእክትን ቀድሞ መናገሩ ለምን አስፈለገ? ይህ የአላህ ምርጫ ነው። እሩቅ ሳንሄድ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም፦
አሞጽ 3፥7 *"በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም"*።

እግዚአብሔር ምንም ነገር ከማድረጉ በፊት ለነቢያቱ መናገሩ ችግር ከሌለው አላህ ሰውን ከመፍጠሩ በፊት ሰውን እንደሚፈጥር ለመላእክት መናገሩ ችግር የለውም። ምነው እግዚአብሔር ሰውን ከመፈጠሩ በፊት ለመላእክት "እንፍጠር" ብሏቸው የለ እንዴ? የባሰ ጉድ፦
ኩፋሌ 4፥4 *ፈጣሪያችን* እግዚአብሔር ለእኛ *እንዲህ አለን*፦ “ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ረዳት *”እንፍጠርለት”*።

“ፈጣሪያችን” የሚል ሃይለ-ቃል ይሰመርበት። "ፈጣሪያችን" ለእኛ "እንፍጠርለት" አለን እያለ ለሙሴ የሚተርክለት አንድ መልአክ ነው፦
ኩፋሌ 2፥4 *የፊቱ መልአክ በእግዚአብሔር ቃል ታዞ ሙሴን እንዲህ አለው*፦

በማለት እግዚአብሔር ለመላእክት እንፍጠርለት እንዳለ ይህ የኩፋሌ መጽሐፍ ይናገራል። የምጣዱ እያለ የዕንቅቡ ተንጣጣ። ቅቤ አንጣሪዋ እያለች ጎመን ቀንጣሿን ምች መታት።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዋቄፈና

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ *”እኔንም ብቻ አምልኩኝ”*፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ

አምላካችን አላህ መለኮት ነው፤ “መለኮት” ማለት ሁሉን ነገር የሚሰማ፣ ሁሉን ነገር የሚመለከት፣ ሁሉን ነገር የሚያውቅ፣ ሁሉን ነገር የፈጠረ፣ በሁሉን ነገር ላይ ቻይ ማለት ነው፤ እርሱ በእኔነት የሚናገር ነባቢና ሕያው መለኮት ነው፤ ብዙ አንቀጾች ላይ “አምልኩኝ” እያለ በመጀመሪያ መደብ ይናገራል፦
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ *”እኔንም ብቻ አምልኩኝ”*፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ
21፥92 ይህች አንዲት መንገድ ስትሆን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት፤ *”እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ”*፡፡ إِنَّ هَٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمْ أُمَّةًۭ وَٰحِدَةًۭ وَأَنَا۠ رَبُّكُمْ فَٱعْبُدُونِ
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ *”ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ”* በማለት ወደ እርሱ *”የምናወርድለት”* ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ
51፥56 *ጂኒን እና ሰውንም ሊያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም*፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

እኛ ሙስሊም አላህ ስናመልከው እርሱን እንዴት ማምለክ እንዳለብን በቅዱስ ቃሉ በቁርኣን ውስጥ እና በእርሱ ነቢይ ሐዲስ ውስጥ በተቀመጠልን መስፈርት ብቻ ነው። ይህንን ካወቅን ስለ ዋቄፈና ደግሞ በግርድፉና በሌጣው እንይ።

“ዋቄፈና” የሚለው ቃል “ዋቃ” ማለትም “አምላክ” ከሚለው ቃል የመጣ ሲሆን የእምነቱ ስም ነው፤ ይህንን እምነት የሚከተል ሰው ደግሞ “ዋቄፈታ” ይባላል፤ “ኢሬቻ” ማለት “ምስጋና” ወይም “አምልኮ” ማለት ሲሆን “ገልማ” ማለትም “ቤተ-አምልኮ” ውስጥ በጭፈራዎቹና በፌሽታዎች የሚከበር በዓል ነው፤ ኢሬቻን የምትለዋ ቃል የምትወክለው እርጥብ ሣር ወይም አበባ በማቅረብ “መሬሆ” ማለትም “መዝሙር” መዘመሩን ነው። ይህንን አምልኮ የሚፈጽሙ ምዕመናኑ “ሚሤንሣ” ሲባሉ እምነቱን የሚመሩት ካህናቱ “ቃሉ” ይባላሉ፤ ፓለቲካውን “ሲርነ ገዳ” ሲባል ፓለቲካውን የሚመሩት መሪዎች ደግሞ “አባ ገዳ” ይባላሉ።

ይህ እምነት አምልኮውን የሚፈጽመው በተራራ እና በሃይቅ ወዘተ ነው፤ “ቱሉ” ማለት “ተራራ” ማለት ሲሆን “ቱሉ ጩቋላ(የዝቋላ ተራራ) “ቱሉ ፊሪ” “ቱሉ ኤረር” እየተባለ ወደ ስምንት ተራሮች ላይ አምልኮ ይፈጸማል። “ሆረ” ማለት “ሃይቅ” ማለት ሲሆን “ሆረ አርሰዴ” “ሆረ ፊንፊኔ” “ሆረ ኪሎሌ” እየተባሉ ሰባቱ የዋቃ ሃይቆች ላይ አምልኮ ይፈጸማል፤ ይህ በዓል በአመት ሁለት ጊዜ ይከበራል።

ይህ እምነት ታሪካዊ ዳራው ከክርስቶስ ልደት በፊት በ3000 ቅድመ-ልደት እንደተጀመረ እና ጅምሩ የአንድ አምላክ አስተምህሮት እንደነበር ይገመታል ይነገራል። እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 2007 ድህረ-ልደት በተደረገው የሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ከኦሮሞ ሕዝብ ወደ 3.3 በመቶ የሚደርሰው ሕዝብ የዚህ እምነት ተከታይ ነበር፤ በአሁኑ ጊዜ ይሄ ቁጥር ወደ 3 በመቶ ዝቅ እንዳለ ይነገራል፤ አንዳንዶች ደግሞ፦ “አብዛኛው ዋቄፈናን ከእስልምና ጋር ወይንም ከክርስትና ጋር ቀይጦ ነው የሚያመልከው” ይላሉ፤ ይህ ስህተት ነው። ምክንያቱም የሚያመልኩት ዋቃ አንድም ቀን እንዴት መመለክ እንዳለበት አልነገራቸውም፥ ደግሞም “አይናገርምም” ይላሉ፤ እነርሱም ባወጡት ሰው ሰራሽ አምልኮ ያመልኩታል፤ ይህ ደግሞ ቢድዓ ነው፤ እዚህ አምልኮ ውስጥ ለወንዙ፣ ለተራራው፣ ለሃይቁ የሚደረገው የሁሉ አምላክነት”Pantheism” እሳቤ ሺርክ ነው፤ በዚህ አምልኮ ውስጥ ልመና፣ ምስጋና፣ ስለት፣ ስግደት የመሳሰሉት ይካሄዳሉ፤ ዛፍ ቅቤ በመቀባት መለማመን፣ ማመስገን፣ መሳል፣ መስገድ ባዕድ አምልኮ ካልሆነ ምንድን ነው? እንደውም “ቃሊቻ” የሚለው ቃል የተገኘው “ቃሉ” ከሚለው እንደሆነም ይነገራል፤ “ቃሉ” የተባሉት መሪዎች ከአጋንንት ጋር እየተነጋገሩ ሺርክ እንደሚያደርጉ የዚህ ባዕድ አምልኮ ነጻ የወጡ ሰዎች ይናገራሉ።
ነብያችን”ﷺ” የነገሩን ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻና ብቻ ናቸው፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው፦
ሡነን አቢ ዳዉድ : መጽሐፍ 2, ሐዲስ 745
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” መዲና ሲገቡ የመዲና ሠዎች የሚደሰቱባቸው ሁለት በዓላት እንዳሏቸው አወቁ። እርሳቸውም እነዚህ ሁለቱ ቀናት ምንድን ናቸው? በማለት ጠየቁ፤ ሰዎችም በጃሂሊያ ጊዜ እንጫወትባቸው የነበሩ በዓላት ናቸው አሏቸው። የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ *“አላህ ከእነርሱ የተሻሉ ሁለት ዒዶችን ሠጥቷችኋል፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓን። አሏቸው*። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَدِمَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْمَدِينَةَ وَلَهُمْ يَوْمَانِ يَلْعَبُونَ فِيهِمَا فَقَالَ ‏”‏ مَا هَذَانِ الْيَوْمَانِ ‏”‏ ‏.‏ قَالُوا كُنَّا نَلْعَبُ فِيهِمَا فِي الْجَاهِلِيَّةِ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّ اللَّهَ قَدْ أَبْدَلَكُمْ بِهِمَا خَيْرًا مِنْهُمَا يَوْمَ الأَضْحَى وَيَوْمَ الْفِطْرِ ‏”‏ ‏.‏
ጃሚዒ አት-ተርሚዲህ : መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏
ከእነዚህ ሁለት በዓል ውጪ ሌሎች በዓላት ተቀባይነት የላቸውም፤ ማንም ሰው አላህ እና መልእክተኛው ያልደነገጉትን ቢድዓን ያስተዋወቀ ያንን ፈለግ የተከተሉትን ሰዎች የሚያገኙትን ኀጢአት ከእነርሱ ላይ ሳይቀነስና ሳይጨመር ይሸከማል፤ ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓ ነው፤ ቢድዓ ሁሉ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ የእሳት ነው፦
ኢማም ቡኻርይ : መጽሐፍ 53, ሐዲስ 7
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ማንኛውም ሰው ከትእዛዛችን ያልሆነ አንድ ነገር ቢፈጥር ተቀባይነት የለውም”* عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ أَحْدَثَ فِي أَمْرِنَا هَذَا مَا لَيْسَ فِيهِ فَهُوَ رَدٌّ ‏”‌‏.‏
ሡነን ኢብኑ ማጃህ : መጽሐፍ 1, ሐዲስ 210
ከሲር ኢብኑብ ዐብደላህ እንደተረከው አባቱ ከአያቱ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰማው ያለው፦ “ማንኛውም ሰው የእኔን ሡናህ ሱናህ ያደረገ ከእኔ በኃላ የእኔን ፈለግ የሚከተሉትን ሰዎች የሚያገኙትን አጅር ከእነርሱ ላይ ሳይቀነስና ሳይጨመር ያገኛል፤
*ማንም ሰው አላህ እና መልእክተኛው ያልደነገጉትን ቢድዓን ያስተዋወቀ ያንን ፈለግ የተከተሉትን ሰዎች የሚያገኙትን ኀጢአት ከእነርሱ ላይ ሳይቀነስና ሳይጨመር ይሸከማል*። حَدَّثَنِي كَثِيرُ بْنُ عَبْدِ اللَّهِ، عَنْ أَبِيهِ، عَنْ جَدِّهِ، قَالَ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ يَقُولُ ‏ “‏ مَنْ أَحْيَا سُنَّةً مِنْ سُنَّتِي قَدْ أُمِيتَتْ بَعْدِي فَإِنَّ لَهُ مِنَ الأَجْرِ مِثْلَ أَجْرِ مَنْ عَمِلَ بِهَا مِنَ النَّاسِ لاَ يَنْقُصُ مِنْ أُجُورِ النَّاسِ شَيْئًا وَمَنِ ابْتَدَعَ بِدْعَةً لاَ يَرْضَاهَا اللَّهُ وَرَسُولُهُ فَإِنَّ عَلَيْهِ مِثْلَ إِثْمِ مَنْ عَمِلَ بِهَا مِنَ النَّاسِ لاَ يَنْقُصُ مِنْ آثَامِ النَّاسِ شَيْئًا ‏”‏ ‏.‏
ሡነን ነሣኢ : መጽሐፍ 19, ሐዲስ 23
ጃቢር ኢብኑ ዐብደላህ እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሑጥባቸው ላይ እንደተናገሩት፦ “አላህ የመራውን ማንም አያጠመውም፤ አላህ ያጠመመውን ማንም አያቀናውም። ከንግግር ሁሉ በላጩ የአላህ መጽሐፍ ነው፤ ከመመሪያ ሁሉ በላጩ የሙሐመድ መመሪያ ነው። *ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓ ነው፤ ቢድዓ ሁሉ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ የእሳት ነው*። عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ قَالَ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ فِي خُطْبَتِهِ يَحْمَدُ اللَّهَ وَيُثْنِي عَلَيْهِ بِمَا هُوَ أَهْلُهُ ثُمَّ يَقُولُ مَنْ يَهْدِهِ اللَّهُ فَلَا مُضِلَّ لَهُ وَمَنْ يُضْلِلْهُ فَلَا هَادِيَ لَهُ إِنَّ أَصْدَقَ الْحَدِيثِ كِتَابُ اللَّهِ وَأَحْسَنَ الْهَدْيِ هَدْيُ مُحَمَّدٍ وَشَرُّ الْأُمُورِ مُحْدَثَاتُهَا وَكُلُّ مُحْدَثَةٍ بِدْعَةٌ وَكُلُّ بِدْعَةٍ ضَلَالَةٌ وَكُلُّ ضَلَالَةٍ فِي النَّارِ

ስለዚህ እዚህ እምነት ውስጥ ያላችሁ ዋቄፈታዎች የነቢያት አምላክ የሆነውን አንዱን አምላክ አላህን በብቸኝነት እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው፤ ሙስሊሞች ሆናችሁ ይህንን በዓል ባለማወቅ የምታከብሩምና የምታመልኩ ካላችሁ በንስሃ ወደ አላህ ተመለሱ። አላህ ወደ እርሱ በመጸጸት ለሚመለሱት ይቅር ባይና አዛኝ ነው፦
2፥160 እነዚያ ከመደበቅ የተጸጸቱና ሥራቸውን ያሳመሩም የደበቁትን የገለጹም ብቻ ሲቀሩ፡፡ *እነዚህም በእነርሱ ላይ ጸጸታቸውን እቀበላለሁ፤ እኔም ጸጸትን በጣም ተቀባይ አዛኙ ነኝ*፡፡ إِلَّا الَّذِينَ تَابُوا وَأَصْلَحُوا وَبَيَّنُوا فَأُولَـٰئِكَ أَتُوبُ عَلَيْهِمْ ۚ وَأَنَا التَّوَّابُ الرَّحِيمُ

ስለ ዋቄፈና ዋቢ መጽሐፍት፦
1. Mulugeta Jaleta Gobenooromo; Indiginious Religion: Anthroplogical Understanding of Waaqeffanna-Nature Link, With Highlight on Livelihood in Guji Zone, Adola Redde and Girja Districts, A thesis submitted to the department of Social Anthropology, College of Social Science Addis Ababa University, June 2017,
2. Census (PDF), Ethiopia, 2007,
3. Workinesh Kelbessa, Traditional Oromo Attitudes towards the Environment, Social Science Research Report Series.

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የመስቀል ቦታ ጽዳት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

5፥2 *"በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ፡፡ ግን በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና"*፡፡ وَتَعَاوَنُوا عَلَى الْبِرِّ وَالتَّقْوَىٰ ۖ وَلَا تَعَاوَنُوا عَلَى الْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

አምላካችን አላህ ከሰው ጋር በሚኖረን ማሕበራዊ ዘይቤ እንዴት መኗኗር እንዳለብን እንዲህ ይነግረናል፦
4፥36 *አላህንም አምልኩ፤ በእርሱም ምንንም አታጋሩ፡፡ በወላጆች፣ በቅርብ ዝምድና ባለቤትም፣ በየቲሞችም፣ በምስኪኖችም፣ በቅርብ ጎረቤትም፣ በሩቅ ጎረቤትም፣ በጎን ባልደረባም፣ በመንገደኛም፣ እጆቻችሁም ንብረት ባደረጓቸው መልካምን ሥሩ*፤ አላህ ኩራተኛ ጉረኛ የኾነን ሰው አይወድም፡፡ وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا ۖ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا وَبِذِي الْقُرْبَىٰ وَالْيَتَامَىٰ وَالْمَسَاكِينِ وَالْجَارِ ذِي الْقُرْبَىٰ وَالْجَارِ الْجُنُبِ وَالصَّاحِبِ بِالْجَنبِ وَابْنِ السَّبِيلِ وَمَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ مُخْتَالًا فَخُورًا
4፥135 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *በትክክል ፍትሕ ቀዋሚዎች በራሳችሁ ወይም በወላጆች እና በቅርብ ዘመዶች ላይ ቢኾንም እንኳ ለአላህ መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሀብታም ወይም ድኻ ቢኾን አላህ በእነርሱ ከእናንተ ይበልጥ ተገቢ ነው፡፡ እንዳታደሉም ዝንባሌን አትከተሉ፡፡ ብታጠምሙም ወይም መመስከርን ብትተው አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ بِالْقِسْطِ شُهَدَاءَ لِلَّهِ وَلَوْ عَلَىٰ أَنفُسِكُمْ أَوِ الْوَالِدَيْنِ وَالْأَقْرَبِينَ ۚ إِن يَكُنْ غَنِيًّا أَوْ فَقِيرًا فَاللَّهُ أَوْلَىٰ بِهِمَا ۖ فَلَا تَتَّبِعُوا الْهَوَىٰ أَن تَعْدِلُوا ۚ وَإِن تَلْوُوا أَوْ تُعْرِضُوا فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرًا

እዚህ አንቀጽ ላይ “ተዕዲሉ” تَعْدِلُوا የሚለው ቃል ይሰመርበት፤ ይህ ቃል የስም መደቡ “ዐድል” عَدْل ሲሆን “ፍትሕ” ማለት ነው፤ ፍትሕ ለአላህ ፍራቻ ተብሎ እና አላህ በምንሠራው ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው ተብሎ የሚደረግ ነው። ይህ ለአላህ ተብሎ የሚደረግ ፍትሕ ለአማንያን ብቻ ሳይሆን ለከሃድያንም ጭምር ነው፦
60፥8 *ከእነዚያ በሃይማኖት ካልተጋደሏችሁ፣ ከአገሮቻችሁም ካላወጡዋችሁ ከሓዲዎች መልካም ብትውሉላቸው እና ወደ እነርሱ ብታስተካክሉ አላህ አይከለክላችሁም፡፡ አላህ ትክክለኞችን ይወዳልና*፡፡ لَّا يَنْهَاكُمُ اللَّهُ عَنِ الَّذِينَ لَمْ يُقَاتِلُوكُمْ فِي الدِّينِ وَلَمْ يُخْرِجُوكُم مِّن دِيَارِكُمْ أَن تَبَرُّوهُمْ وَتُقْسِطُوا إِلَيْهِمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُقْسِطِينَ

ዲናችንን አክብረው ካልተጋደሉንና ካላሳደዱን ከሃድያን ጋር በዝምድና፣ በባልደረባ፣ በጉርብትና መልካም መዋዋል እና ማስተካከል ይቻላል። “ብታስተካክሉ” ለሚለው ቃል አሁንም የገባው “ቱቅሢጡ” َتُقْسِطُوا ሲሆን የስም መደቡ “ቂሥጥ” قِسْط ማለትም “ፍትሕ” ነው፤ ለአላህ ብለን ስናስተካክል “ሙቅሢጢን” مُقْسِطِين ማለትም “ፍትኸኞችን” “ትክክለኞች” “አስተካካዮች” እንሰኛለን፤ አላህ ሙቅሢጢንን ይወዳልና። በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም መረዳዳት ተፈቅዷል፦
49፥9 *በነገሩ ሁሉ አስተካክሉም፡፡ አላህ አስተካካዮችን ይወዳልና*፡፡ وَأَقْسِطُوا ۖ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُقْسِطِينَ
5፥2 *"በበጎ ነገር እና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ፡፡ ግን በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና"*፡፡ وَتَعَاوَنُوا عَلَى الْبِرِّ وَالتَّقْوَىٰ ۖ وَلَا تَعَاوَنُوا عَلَى الْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

"በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ" የሚለው ይሰመርበት። ወደ ኩፍርና ሺርክ ሊያስገባ የሚችለውን ሥራ ከሌላ እምነት ጋር መሥራት ከኢሥላም ያስወጣል፥ ይህ ወሰን ማለፍ ነው፦
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 15, ሐዲስ 311
ሰሙራህ ኢብኑ ጁንዱብ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እዲህ አሉ፦ *”ከሙሽሪክ ጋር ያበረ እና የተኗኗረ እርሱን(ሙሽሪኩን) ይመስላል”*። أَمَّا بَعْدُ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ جَامَعَ الْمُشْرِكَ وَسَكَنَ مَعَهُ فَإِنَّهُ مِثْلُهُ ‏
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 12, ሐዲስ 34
ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም አሉ፦ *”ከማንኛውም ሕዝብ ጋር የሚመሳሰል ከእነርሱ ነው”*። عَنِ ابْنِ عُمَرَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ تَشَبَّهَ بِقَوْمٍ فَهُوَ مِنْهُمْ
ስለዚህ የማይመለከተን ነገር ውስጥ ለመመሳሰል ለምሳሌ ቤተ ክርስቲያን ማጽዳት፣ የመስቀል ደመራ ቦታ ማጽዳት፣ የጥምቀት ቦታ ማጽዳት፥ ታቦት መሸኘት፣ በዓላቸውን ማክበር፣ መዝሙራቸውን መዘመር ከኢሥላም አጥር ያስወጣል። አንዳንድ ቂሎች፦ “ለመረዳዳት ነው” ይሉናል። በጋራ እሴት ማለትም በልማት፣ በጉርብትና፣ በአስኳላ ትምህርት፣ በሰብአዊነት ወዘተ… ልንረዳዳ እንችላለን፥ ነገር ግን በእምነት ጉዳይ እረዳቶች አድርገን ከያዝናቸው ከእነርሱ እንደ አንዱ ነን፦
4፥144 *”እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከምእምናን ሌላ ከሓዲዎችን ረዳቶች አድርጋችሁ አትያዙ*፤ ለአላህ በእናንተ ላይ ግልጽ ማስረጃዎችን ልታደርጉ ትፈልጋላችሁን? يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا الْكَافِرِينَ أَوْلِيَاءَ مِن دُونِ الْمُؤْمِنِينَ ۚ أَتُرِيدُونَ أَن تَجْعَلُوا لِلَّهِ عَلَيْكُمْ سُلْطَانًا مُّبِينًا
5፥51 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አይሁዶችንና ክርስቲያኖችን ረዳቶች አድርጋችሁ አትያዙ፡፡ ከፊላቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ ከእናንተም ውስጥ ረዳቶች የሚያደርጋቸው ሰው እርሱ ከእነርሱ ነው*፡፡ አላህ አመጸኞችን ሕዝቦች አያቀናም፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا الْيَهُودَ وَالنَّصَارَىٰ أَوْلِيَاءَ ۘ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَاءُ بَعْضٍ ۚ وَمَن يَتَوَلَّهُم مِّنكُمْ فَإِنَّهُ مِنْهُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الظَّالِمِينَ
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 24, ሐዲስ 2939
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”የሙሽሪክ እርዳታ አያስፈልገንም”* عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ إِنَّا لاَ نَسْتَعِينُ بِمُشْرِكٍ ‏

ምን ይሁን ብለን ነው ለመስቀል በዓል የምናጸዳው? መስቀል እኮ ስግደት እና ምስጋና ይቀበላል። መስቀል በሃውልት ድንጋይ፣ እንጨት፣ ወርቅ፣ ብር፣ ብረት፣ ነሐስ ወዘተ ነው። ይህ ግዑዝ ነገር ይሰገድለታል፥ ምስጋና ይቀርበለታል፤ ይህ በተግባር ሲሆን በጽሑፍ ደግሞ የዘወትር ፀሎት ላይ እንዲህ ይነበባል፦
ግዕዙ፦
“እሰግድ “ለ”መስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘተቀደሰ በደሙ ክቡር”
ትርጉም፦
“ዓለምን ለማዳን ሲል ኢየሱስ ክርስቶስ “ለ”ተሰቀለበት መስቀል እሰግዳለው”
ግዕዙ፦
“ስብሐት “ለ”መስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ በምህረቱ ይዘከረነ”
ትርጉም፦
” “ለ”ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ምስጋና ይገባዋል”

እንግዲህ ሄደክ ስታጸዳ እንዲያሻርኩ እያመቻቸክላቸው እንደሆነ አትርሳ። ይህንን ድርጊት መተባበር ሺርክ እይደለምን? መከባበር በዚህ ነው እንዴ? ሰዎቹን በሰውነታቸው እናከብራቸዋል እንጂ ለአምልኮታቸው ዕውቅና ሰጥቶ እሹሩሩ ማለት ምን የሚሉት ማሽቃበጥ ነው? መንግሥት ይሉንታ በማስያዝ በሃይማኖት ጣልቃ አይግባብን። ሙሥሊሙ የራሱ ለማጽዳት የሌላ እገዛ አይሻም። መሣጂዶችን እንዲያጸዱልን አንፈልግም። እኛም የእነርሱን ማጽዳት የለብንም፥ የራሳቸውን እራሳቸው ያጽዱ። ኡስታዞች፣ ዐሊሞች፣ መሻይኮች ምነው ዝምታውን መረጡዛ? በዝምታው ምእመኑን በእምነቱ እንዲሸማቀቅ እና እዲሳቀቅ እያረጋችሁት ነው። አብሮነት፣ መከባበር፣ የአገር ልማትና ግንባታ በዚህ አይለካም። አብሮነት፣ መከባበር፣ የአገር ልማትና ግንባታ እናመጣለን በሚል ሽፋን ኡማውን የዝቅተኝነት ስሜት በማከናነብ ከድጡ ወደ ማጡ አትክተቱት። ኢትዮጵያዊነት በመሆን እንጂ በመምሰል አይለካም። ምንም ሳይገባውና ሳያውቀው የሚሳተፈውን ሙሥሊም በትህትና የማስጠንቀቅ የሁላችንም ሃላፍትና ነው። ይህንን መልእክት ለሁሉም በማስተላለፍ ዲናዊ ግዴታዎን ይወጡ! አላህ ለሁላችንም ሂዳያ ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ተውባህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

2፥160 እነዚያ ከመደበቅ የተጸጸቱና ሥራቸውን ያሳመሩም የደበቁትን የገለጹም ብቻ ሲቀሩ፡፡ *”እነዚህም በእነርሱ ላይ ጸጸታቸውን እቀበላለሁ፤ እኔም ጸጸትን በጣም ተቀባይ አዛኙ ነኝ”*፡፡ إِلَّا الَّذِينَ تَابُوا وَأَصْلَحُوا وَبَيَّنُوا فَأُولَـٰئِكَ أَتُوبُ عَلَيْهِمْ ۚ وَأَنَا التَّوَّابُ الرَّحِيمُ

"ንስሐ" የሚለው የግዕዝ ቃል "ነስሐ" ማለትም "ተመለሰ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "በጸጸት መመለስ" ማለት ነው። “ተውባህ” تَوْبَة የሚለው ቃል "ታበ" تَابَ ማለትም "ተመለሰ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ከነበሩበት ስህተት በንስሐ ወደ አላህ መመለስ” ማለት ነው፥ አላህ ወደ እርሱ የሚመለሱት ንስሐን የሚቀበል ስለሆነ “አት-ተዋብ” التَّوَّاب ማለትም "ጸጸትን ተቀባይ" ነው። እርሱም፦ “እኔም ጸጸትን በጣም ተቀባይ አዛኙ ነኝ” ይላል፦
2፥160 እነዚያ ከመደበቅ የተጸጸቱና ሥራቸውን ያሳመሩም የደበቁትን የገለጹም ብቻ ሲቀሩ፡፡ *”እነዚህም በእነርሱ ላይ ጸጸታቸውን እቀበላለሁ፤ እኔም ጸጸትን በጣም ተቀባይ አዛኙ ነኝ”*፡፡ إِلَّا الَّذِينَ تَابُوا وَأَصْلَحُوا وَبَيَّنُوا فَأُولَـٰئِكَ أَتُوبُ عَلَيْهِمْ ۚ وَأَنَا التَّوَّابُ الرَّحِيمُ

ወደ አላህ በንስሐ የሚመለሱት ሰዎች ደግሞ “አት-ተዋቡን” التَّوَّابُون ይባላሉ። አላህ ከኃጢኣት ተመላሾችን ይወዳል፥ በመሳሳት አጥፍተን ወደ እርሱ ለምንመለስ መሓሪ ነው፦
2፥222 *"አላህ ከኃጢኣት ተመላሾችን ይወዳል፤ ተጥራሪዎችንም ይወዳል በላቸው"*፡፡ اللَّهَ يُحِبُّ التَّوَّابِينَ وَيُحِبُّ الْمُتَطَهِّرِينَ
4፥25 *"ጌታችሁ በነፍሶቻችሁ ውስጥ ያለውን ሁሉ አዋቂ ነው፡፡ ታዛዦችም ብትኾኑ በመሳሳትም ብታጠፉ እርሱ ለተመላሾች መሓሪ ነው"*፡፡ رَّبُّكُمْ أَعْلَمُ بِمَا فِي نُفُوسِكُمْ ۚ إِن تَكُونُوا صَالِحِينَ فَإِنَّهُ كَانَ لِلْأَوَّابِينَ غَفُورًا

ነቢያችን"ﷺ" በሐዲስ ላይ፦ "የአደም ልጆች ሁሉ ተሳሳች ናቸው፡፡ ከተሳሳቾቹ ሁሉ በላጩ ግን ከስህተታቸው በተውበት ተመላሾቹ ናቸው" ብለውናል፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 4392
አነሥ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”የአደም ልጆች ሁሉ ተሳሳች ናቸው፡፡ ከተሳሳቾቹ ሁሉ በላጩ ግን ከስህተታቸው በተውበት ተመላሾቹ ናቸው”*። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏:‏ ‏ “‏ كُلُّ بَنِي آدَمَ خَطَّاءٌ وَخَيْرُ الْخَطَّائِينَ التَّوَّابُونَ
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 50, ሐዲስ 13
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"በዚያ ነፍሴ በእጁ በኾነው በአላህ እምላለው! እናንተ ኃጢአትን ባታደርጉ ኖሮ፥ አላህ እናንተን ያስወግዳችሁ እና ኃጢአትን አድርገው ከዛም ይቅርታ ጠይቀው፣ አላህ ይቅር የሚላቸውን ሕዝብ ያመጣ ነበር"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ لَوْ لَمْ تُذْنِبُوا لَذَهَبَ اللَّهُ بِكُمْ وَلَجَاءَ بِقَوْمٍ يُذْنِبُونَ فَيَسْتَغْفِرُونَ اللَّهَ فَيَغْفِرُ لَهُمْ ‏"‏ ‏

እዚህ ሐዲስ ላይ "ለው" لَوْ ተለዋዋጭ ቃሉ "ኢን" إِن ነው፥ "ለው" ወይም "ኢን" በሰዋሰው አቀማመጥ "አርፉ አሽ-ሸርጥ" حَرْف الشَرْط ማለትም ሁኔታዊ መስተዋድድ"conditional particle" ነው። "ኖሮ" የሚለው አርፉ አሽ-ሸርጥ ከገባን "እናንተ ኃጢአትን ባታደርጉ ኖሮ" ማለት ኃጢአትን ታደርጋላችሁ፥ የአደም ልጆች ሁሉ ተሳሳች ናቸው። ከተሳሳቾቹ ሁሉ በላጩ ግን ከስህተታቸው በተውበት ተመላሾቹ ናቸው ማለት ነው። ይህንን ተመሳሳይ ሰዋስው ከቁርኣን እንመልከት፦
7፥143 ሙሳም ለቀጠሯችን በመጣና ጌታውም ባነጋገረው ጊዜ፡- *«ጌታዬ ሆይ! አሳየኝ ወደ አንተ እመለከታለሁና» አለ፡፡ አላህም፡- «በፍጹም አታየኝም ግን ወደ ተራራው ተመልከት፡፡ "በስፍራውም ቢረጋ በእርግጥ ታየኛለህ"» አለው፡፡ ጌታው ለተራራው በተገለጸ ጊዜ እንኩትኩት አደረገው፡፡ ሙሳም ጮሆ ወደቀ*፡፡ በአንሰራራም ጊዜ «ጥራት ይገባህ፡፡ ወደ አንተ ተመለስኩ፡፡ እኔም የምእምናን መጀመሪያ ነኝ» አለ፡፡ وَلَمَّا جَاءَ مُوسَىٰ لِمِيقَاتِنَا وَكَلَّمَهُ رَبُّهُ قَالَ رَبِّ أَرِنِي أَنظُرْ إِلَيْكَ ۚ قَالَ لَن تَرَانِي وَلَـٰكِنِ انظُرْ إِلَى الْجَبَلِ فَإِنِ اسْتَقَرَّ مَكَانَهُ فَسَوْفَ تَرَانِي ۚ فَلَمَّا تَجَلَّىٰ رَبُّهُ لِلْجَبَلِ جَعَلَهُ دَكًّا وَخَرَّ مُوسَىٰ صَعِقًا ۚ فَلَمَّا أَفَاقَ قَالَ سُبْحَانَكَ تُبْتُ إِلَيْكَ وَأَنَا أَوَّلُ الْمُؤْمِنِينَ

"በስፍራውም ቢረጋ" ማለት "አይረጋም" ማለት ከሆነ "እናንተ ኃጢአትን ባታደርጉ ኖሮ" ማለት "እናንተ ኃጢአትን አለማድረግ አትችሉም" ማለት ነው። "በስፍራውም ቢረጋ በእርግጥ ታየኛለህ" ማለት "አይረጋም እንጂ ቢረጋ ታየኛለህ" ማለት እንደሆነ ሁሉ "እናንተ ኃጢአትን ባታደርጉ ኖሮ አላህ እናንተን ያስወግዳችሁ እና ኃጢአትን አድርገው ከዛም ይቅርታ ጠይቀው፣ አላህ ይቅር የሚላቸውን ሕዝብ ያመጣ ነበር" ማለት "እናንተ ኃጢአትን አለማድረግ አትችሉም እንጂ ብትችሉ ኃጢአትን አድርገው ከዛም ጌታቸውን ምሕረትን ጠይቀው፣ እሱም ይቅር የሚላቸውን ሕዝብ ያመጣ ነበር" ማለት ነው። " በእርግጥ ታየኛለህ" የሚለው ተራራው መርጋት እንደማይችል ግነት ሆኖ እንደመጣ ሁሉ "አላህ እናንተን ያስወግዳችሁ እና ኃጢአትን አድርገው ከዛም ይቅርታ ጠይቀው፣ አላህ ይቅር የሚላቸውን ሕዝብ ያመጣ ነበር" የሚለውም "እናንተ ኃጢአትን አለማድረግ አትችሉም" የሚለውን ለማሳየት የመጣ ግነታዊ ቃል ነው። ሌላ ናሙና፦
21፥22 *በሁለቱ በሰማያትና በምድር ውስጥ ከአላህ ሌላ አማልክት በነበሩ "ኖሮ" በተበላሹ ነበር"*፡፡ የዐርሹ ጌታ አላህም ከሚሉት ሁሉ ጠራ፡፡ لَوْ كَانَ فِيهِمَا آلِهَةٌ إِلَّا اللَّهُ لَفَسَدَتَا ۚ فَسُبْحَانَ اللَّهِ رَبِّ الْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ
እዚህ አንቀጽ ላይ "ለው" لَوْ የሚለው አርፉ አሽ-ሸርጥ "ኖሮ" የሚለው ለማመልከት የገባ ነው። "አማልክት በነበሩ ኖሮ" ማለት "አማልክት የሉም" ማለት እንደሆነ ሁሉ "እናንተ ኃጢአትን ባታደርጉ ኖሮ" ማለት "እናንተ ኃጢአትን አለማድረግ አትችሉም" ማለት ነው። ከፊሉ በከፊሉ ላይ በመላቅ ሊበላሹ የሚችሉት ከመነሻው አማልክት ቢኖሩ ኖሮ ነበር እንጂ ይበላሻሉ ማለት እንዳልሆነ ሁሉ ኃጢአትን አድርገው ከዛም ጌታቸውን ምሕረትን ጠይቀው፣ እሱም ይቅር የሚላቸውን ሕዝብ የሚያመጣው እናንተ ኃጢአትን የማታደርጉ ቢሆን ነበር ማለት ነው። የመጨረሻ ናሙና፦
43፥81 *«ለአልረሕማን ልጅ ቢኖረው እኔ ለልጁ የተገዢዎቹ መጀመሪያ ነኝ» በላቸው*፡፡ قُلْ إِن كَانَ لِلرَّحْمَـٰنِ وَلَدٌ فَأَنَا أَوَّلُ الْعَابِدِينَ

"ለአልረሕማን ልጅ ቢኖረው" ማለት "ለአልረሕማን ልጅ የለውም" ማለት እንደሆነ ሁሉ "እናንተ ኃጢአትን ባታደርጉ ኖሮ" ማለት "እናንተ ኃጢአትን አለማድረግ አትችሉም" ማለት ነው። እኔ ለልጁ ተገዢ መሆን የምችለው ከመነሻው ልጅ ቢኖረው ኖሮ ነበር እንጂ ለልጁ ተገዢ ነኝ ማለት እንዳልሆነ ሁሉ ኃጢአትን አድርገው ከዛም ጌታቸውን ምሕረትን ጠይቀው፣ እሱም ይቅር የሚላቸውን ሕዝብ የሚያመጣው እናንተ ኃጢአትን የማታደርጉ ቢሆን ነበር ማለት ነው። ስለዚህ የሐዲሱ መልእክት ያዘለው "እናንተ ኃጢአትን አለማድረግ ስለማትችሉ" ያላችሁ ምርጫ ተውበት አድርጉ! የአደም ልጆች ሁሉ ተሳሳች ናቸው፡፡ ከተሳሳቾቹ ሁሉ በላጩ ግን ከስህተታቸው በተውበት ተመላሾቹ ናቸው” የሚል ነው እንጂ "አላህ ሰዎች ኃጢአትን ካላደረጉ ይቅርባይነቱ ይቀርበታል" የሚል የሚሽነሪዎችን የቡና ወሬ አያሲዝም። ባይሆን እግዚአብሔር ሲያጠፋችሁ ሲያፈርሳችሁም ደስ ይለዋል፦
ዘዳግም28፥63 እግዚአብሔርም በጎ ያደርግላችሁ ዘንድ ያበዛችሁም ዘንድ ደስ ይለው እንደ ነበረ፥ እንዲሁ *እግዚአብሔር ሲያጠፋችሁ ሲያፈርሳችሁም ደስ ይለዋል"*።

ለነገሩ ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር የሆነውን ክፉን መንፈስ ይልካል፥ ይህም ክፉም መንፈስ ከእግዚአብሔር ጋር እተመካከረ ለእግዚአብሔር ያሳስትለታል። የሚሳሳተው ሰው እና የሚያሳስተው ክፉ መንፈስ ለእግዚአብሔር ናቸው፦
2ኛ ተሰሎንቄ 2፥12 ስለዚህም ምክንያት፥ በእውነት ያላመኑ ነገር ግን በዓመፅ ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ ፍርድን እንዲቀበሉ፥ *ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል*።
መሣፍንት 9፥23 *እግዚአብሔር በአቤሜሌክና በሴኬም ሰዎች መካከል ክፉን መንፈስ ሰደደ*፤
1ኛ ነገሥት 22 20-23 እግዚአብሔርም፦ ወጥቶ በሬማት ዘገለዓድ ይወድቅ ዘንድ *አክዓብን የሚያሳስት ማን ነው?* አለ። አንዱም እንዲህ ያለ ነገር፥ ሌላውም እንዲያ የለ ነገር ተናገረ። *መንፈስም ወጣ በእግዚአብሔርም ፊት ቆሞ፦ እኔ አሳስተዋለሁ አለ*። እግዚአብሔርም፦ በምን? አለው እርሱም፦ *ወጥቼ በነቢያቶቹ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ እሆናለሁ አለ*። እግዚአብሔርም፦ *ማሳሳትስ ታሳስተዋለህ፥ ይሆንልሃልም ውጣ፥ እንዲሁም አድርግ አለ*። አሁንም፦ እነሆ፥ እግዚአብሔር በእነዚህ *በነቢያትህ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ አድርጎአል*፤ እግዚአብሔርም በላይህ ክፉ ተናግሮብሃል።
ኢዮብ 12፥16 ኃይልና ጥበብ በእርሱ ዘንድ ናቸው፤ *የሚስተው እና የሚያስተው ለእርሱ ናቸው*።

ይህ ሁላ ባተሎና ዘባተሎ እሳቤ ባይብል ላይ እያለ ከላይ ያለው ሐዲስ ለመተቸት የሚያስችል የሞራል ብቃት፣ አቅም፣ ወኔም የላችሁም። አላህ ሂዳያ ይስጣችሁ፥ ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ክርስቲያን፦ "ፍጡሮቹ ፈጣሪን ገደሉት"
ሙሥሊም፦ "ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?
ክርስቲያን፦ "ፈጣሪ ሁሉን ቻይ ነው"
ሙሥሊም፦ ፈጣሪ ሁሉን ቻይ አመሆን ይችላልን?
ክርስቲያን፦ "ይህማ የፈጣሪ ባሕርይ አይደለም"
ሙሥሊም፦ ባይሆን በፍጡሮቹ ፈጣሪ መገደሉ ነው የእርሱ ባሕርይ የማይሆነው። እሺ ፈጣሪ ሲሞት እርሱ ያሞተው ማን ነው?
ክርስቲያን፦ "ሌላ አካል አለ፥ እርሱን ያሞተው እና ከሞት ያስነሳው"
ሙሥሊም፦ እርሱ ደግሞ ማን ነው?
ክርስቲያን፦ "አብ ይባላል"
ሙሥሊም፦ አብ ከወልድ ጋር በባሕርይ አንድ ነው ብላችሁ ታምናላችሁ፥ ወልድ ሲሞት ከአብ ባሕርይ ጋር አንድ የሆነው ባሕርይ ሞቷል ወይስ አልሞተም?
ክርስቲያን፦ "ሥላሴን እመራመራለው ብትል አይምሮህን ታጣዋለህ፥ እክዳለው ብትል ነፍስህን ታጣለህ"
ሙሥሊም፦ ይህ ነው መልሱ?
ክርስቲያን፦ "አዎ! እምነት ሞኝነት ነው"
ሙሥሊም፦ እሺ ይኹንልህ ግን አእምሮህ እረፍት የለውም። ፈጣሪ በፍጡሮቹ መገደሉ ሲገርመኝ፥ እርሱን ያሞተው ሌላ ፈጣሪ መኖሩ አስደመመኝ"።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሰኞ እና ሐሙስ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና። وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمْ عَنْهُ فَٱنتَهُوا۟ ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ

ሙሥሊም በሳምንት ውስጥ ሁለት ቀናት የሡናህ አፅዋማት ይፆማል፥ እነርሱም ሰኞ እና ሐሙስ ናቸው። ሰኞ የሚፆምበት አራት ምክንያት አሉ፥ እነርሱም፦
1ኛ ወደ ነቢያችን"ﷺ" ወሕይ የመጣበት ቀን ነው።
2ኛ. ነቢያችን"ﷺ" የተወለዱበት ቀን ነው።
3ኛ. ሥራዎች ወደ አላህ የሚቀርቡበት ቀን ነው።
4ኛ. አላህ ይቅር የሚልበት ቀን ነው፦
ኢማም ሙስሊም: መጽሐፍ 13, ሐዲስ 256
አቢ ቀታደህ አንሷሪይ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ *”የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሰኞ ቀን ስለሚጾምበት ተጠየቁ፥ እርሳቸውም፦ “የተወለድኩበት እና ወሕይ የወረደልኝ ቀን ነው” አሉ*። عَنْ أَبِي قَتَادَةَ الأَنْصَارِيِّ، رضى الله عنه أَنَّرَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم سُئِلَ عَنْ صَوْمِ الاِثْنَيْنِ فَقَالَ ‏ “‏ فِيهِ وُلِدْتُ وَفِيهِ أُنْزِلَ عَلَىَّ ‏”‏ ‏.‏
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 66
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ሥራዎች ሰኞ እና ሐሙስ ወደ አላህ ይቀርባሉ፥ ሥራዬ ፆመኛ ሆኜ እንዲቀርብልኝ እወዳለሁኝ"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ تُعْرَضُ الأَعْمَالُ يَوْمَ الاِثْنَيْنِ وَالْخَمِيسِ فَأُحِبُّ أَنْ يُعْرَضَ عَمَلِي وَأَنَا صَائِم
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 7, ሐዲስ 1812
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" ሰኞ እና ሐሙስ ይፆሙ ነበር። እንዲህም ተባለ፦ *"የአላህ መልክተኛ"ﷺ" ሆይ! ለምን ሰኞ እና ሐሙስ ይፆማሉ? እርሳቸውም፦ "ሰኞ እና ሐሙስ አላህ ሁሉንም ሙሥሊም ይቅር ይላል ከተቷቷዉት ሁለት በስተቀር። እርሳቸውም፦ "እነዚህ ሁለቱን እስኪስማሙ ድረስ ተዋቸው"*። عَنْ سُهَيْلِ بْنِ أَبِي صَالِحٍ، عَنْ أَبِيهِ، عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ النَّبِيَّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ كَانَ يَصُومُ الاِثْنَيْنِ وَالْخَمِيسَ ‏.‏ فَقِيلَ يَا رَسُولَ اللَّهِ إِنَّكَ تَصُومُ يَوْمَ الاِثْنَيْنِ وَالْخَمِيسِ فَقَالَ ‏ "‏ إِنَّ يَوْمَ الاِثْنَيْنِ وَالْخَمِيسِ يَغْفِرُ اللَّهُ فِيهِمَا لِكُلِّ مُسْلِمٍ إِلاَّ مُهْتَجِرَيْنِ يَقُولُ دَعْهُمَا حَتَّى يَصْطَلِحَا ‏"‏ ‏

ሐሙስ የሚፆምበት ምክንያት ሁለት ሲሆን እርሱ ከላይ ሐዲሱ ላይ እንደተገለጸው ሥራዎች ወደ አላህ የሚቀርቡበት እና አላህ ይቅር የሚልበት ቀን ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 45, ሐዲስ 43
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም እንዲህ አሉ፦ *"የጀነት ደጃፎች በአላህ ላይ ምንም ነገር ላላሻረከ ሁሉ ሰኞ ቀን እና ሐሙስ ቀን ይከፈታል፥ አንድ ሰው በውስጡ መራራነት በወንድሙ ላይ ካለበት በስተቀር"። እንዲህም ይባላል፦ "በሁለቱ መካከል ዕርቅ እስኪሆን ድረስ አጢኑ፣ በሁለቱ መካከል ዕርቅ እስኪሆን ድረስ አጢኑ፣ በሁለቱ መካከል ዕርቅ እስኪሆን ድረስ አጢኑ"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ تُفْتَحُ أَبْوَابُ الْجَنَّةِ يَوْمَ الاِثْنَيْنِ وَيَوْمَ الْخَمِيسِ فَيُغْفَرُ لِكُلِّ عَبْدٍ لاَ يُشْرِكُ بِاللَّهِ شَيْئًا إِلاَّ رَجُلاً كَانَتْ بَيْنَهُ وَبَيْنَ أَخِيهِ شَحْنَاءُ فَيُقَالُ أَنْظِرُوا هَذَيْنِ حَتَّى يَصْطَلِحَا أَنْظِرُوا هَذَيْنِ حَتَّى يَصْطَلِحَا أَنْظِرُوا هَذَيْنِ حَتَّى يَصْطَلِحَا

የጀነት ደጃፎች ሰኞ ቀን እና ሐሙስ ቀን ክፍት የሆነው ቂም ወይም ጥላቻ በሙሥሊም ወንድሙ ላይ በልቡ ላልቋጠረ ሙሥሊም ነው። ሰኞ እና ሐሙስ ሳምንታዊ መጠነ-ሰፊ የአምልኮ ጊዜ ለማመልከት እንጂ ሌላውን የአዘቦት ቀናት ሥራዎች አይቀርቡም ወይም አላህ ይቅር አይልም ማለትን አያሲዝም። እንግዲህ እነዚህን የሡናህ አፅዋማት እንድንፆም የተሰጠን ከመልእክተኛው ነው፦
59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና። وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمْ عَنْهُ فَٱنتَهُوا۟ ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 64
ዓኢሻህ እንደተረከችው፥ እንዲህ አለች፦ *"ነቢዩ"ﷺ" ሰኞ እና ሐሙስ ይፆሙ ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم يَتَحَرَّى صَوْمَ الاِثْنَيْنِ وَالْخَمِيسِ

ኢሥላም ሰው ሠራሽ ሕግና ሥርዓት ሳይሆን ዐቂደቱ አር-ረባንያህ ነው። ይህንን ስንል አርቲ ቡርቲና ቶራ ቦራ የሆነ ስሁትና መሪር የቡና ወሬ ይዘን ሳይሆን ቁርኣንና ሐዲስን ያማከለ ስሙርና ጥዑም ማስረጃ ይዘን ነው።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም