ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.3K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ነጥብ አንድ
“ሲታመን ይከዳል”
አምላካችን አላህ አማና ሲጣልብን አማናችን መወጣት እንዳለብን እንዲህ ይነግረናል፦
4፥58 *አላህ አደራዎችን ወደ ባለቤቶቻቸው እንድታደርሱ ያዛችኋል*፡፡ በሰዎችም መካከል በፈረዳችሁ ጊዜ በትክክል እንድትፈርዱ ያዛችኋል፡፡ አላህ በርሱ የሚገሥጻችሁ ነገር ምን ያምር! አላህ ሰሚ ተመልካች ነው፡፡ إِنَّ اللَّهَ يَأْمُرُكُمْ أَن تُؤَدُّوا الْأَمَانَاتِ إِلَىٰ أَهْلِهَا وَإِذَا حَكَمْتُم بَيْنَ النَّاسِ أَن تَحْكُمُوا بِالْعَدْلِ ۚ إِنَّ اللَّهَ نِعِمَّا يَعِظُكُم بِهِ ۗ إِنَّ اللَّهَ كَانَ سَمِيعًا بَصِيرًا
8፥27 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህንና መልክተኛውን አትክዱ፡፡ *አደራዎቻችሁንም እናንተ እያወቃችሁ አትክዱ*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَخُونُوا اللَّهَ وَالرَّسُولَ وَتَخُونُوا أَمَانَاتِكُمْ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ
23፥8 *እነዚያም እነርሱ ለአደራዎቻቸው እና ለቃል ኪዳናቸው ጠባቂዎች*፡፡ وَالَّذِينَ هُمْ لِأَمَانَاتِهِمْ وَعَهْدِهِمْ رَاعُونَ
70፥32 *እነዚያም እነርሱ አደራዎቻቸውን እና ቃል ኪዳናቸውን ጠባቂዎች የኾኑት*፡፡ وَالَّذِينَ هُمْ لِأَمَانَاتِهِمْ وَعَهْدِهِمْ رَاعُونَ

ነጥብ ሁለት
“ሲናገር ይዋሻል”
ሙስሊም ከዋሸ ቀኑ ተበላሸ ይላል ያገሬ ሰው፤ አንድ ሙናፊቅ “ተላላ” “አባይ” “ቀላማጅ” “ዋሾ” “በጥራቃ” “ውሸታም” “ሐሰተኛ” “ወሽከታ” ነው፤ አምላካችን አላህ፦ “ሐሰትንም ቃል ራቁ” “ትክክለኛንም ንግግር ተናገሩ” ብሎ ያዘናል፦
22፥30 ከጣዖታትም ርክሰት ተጠንቀቁ፡፡ *ሐሰትንም ቃል ራቁ*፡፡ فَاجْتَنِبُوا الرِّجْسَ مِنَ الْأَوْثَانِ وَاجْتَنِبُوا قَوْلَ الزُّورِ
33፥70 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ *ትክክለኛንም ንግግር ተናገሩ*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَقُولُوا قَوْلًا سَدِيدًا

ነጥብ ሦስት
“ቃል ገብቶ ያፈርሳል”
ቃል ገብቶ ማፍረስ ከመሃላ አይተናነስም፤ አምላካችን አላህ፦ “በቃል ኪዳኖች ሙሉ” ይለናል፦
5፥1 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *በቃል ኪዳኖች ሙሉ*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَوْفُوا بِالْعُقُودِ ۚ
23፥8 *እነዚያም እነርሱ ለአደራዎቻቸው እና ለቃል ኪዳናቸው ጠባቂዎች*፡፡ وَالَّذِينَ هُمْ لِأَمَانَاتِهِمْ وَعَهْدِهِمْ رَاعُونَ
70፥32 *እነዚያም እነርሱ አደራዎቻቸውን እና ቃል ኪዳናቸውን ጠባቂዎች የኾኑት*፡፡ وَالَّذِينَ هُمْ لِأَمَانَاتِهِمْ وَعَهْدِهِمْ رَاعُونَ
17፥34 የየቲምንም ገንዘብ የብርታቱን ጊዜ እስኪደርስ ድረስ በዚያች እርሷ መልካም በኾነች ኹኔታ እንጂ አትቅረቡ፡፡ *በኪዳናችሁም ሙሉ፤ ኪዳን የሚጠየቁበት ነውና*፡፡ وَلَا تَقْرَبُوا مَالَ الْيَتِيمِ إِلَّا بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ حَتَّىٰ يَبْلُغَ أَشُدَّهُ ۚ وَأَوْفُوا بِالْعَهْدِ ۖ إِنَّ الْعَهْدَ كَانَ مَسْئُولًا

ነገር ግን ይህ ምልክት የሚታይበት ሁሉ ሙናፊቅ ላይሆን ይችላል፤ ግን መናፍቅ የሚያሰኘው ጉዳይ ነብያችን”ﷺ” እንዲህ ይነግሩናል፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 116
ዐብዱላህ ኢብኑ ዐምር”ረ.ዐ.” እንደነገረን የአላህ መልክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፡- *“አራት ነገሮች ያሉበት ሰው ግልጽ መናፍቅ ሆኗል፤ ከአራቱ ውስጥ አንዱ ያለበት ሰው ደግሞ እስኪተወው ድረስ ከኑፋቄ ከፊሉ ጠባይ አለበት ማለት ነው፤ አራቱ ነገሮች፡- ሲታመን ይከዳል፣ ሲናገር ይዋሻል፣ ቃል ገብቶ ያፈርሳል፣ ሲሟገት ያስተባብላል*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ أَرْبَعٌ مَنْ كُنَّ فِيهِ كَانَ مُنَافِقًا خَالِصًا وَمَنْ كَانَتْ فِيهِ خَلَّةٌ مِنْهُنَّ كَانَتْ فِيهِ خَلَّةٌ مِنْ نِفَاقٍ حَتَّى يَدَعَهَا إِذَا حَدَّثَ كَذَبَ وَإِذَا عَاهَدَ غَدَرَ وَإِذَا وَعَدَ أَخْلَفَ وَإِذَا خَاصَمَ فَجَرَ ‏”‏ ‏

ነጥብ አራት
“ሲሟገት ያስተባብላል”
መናፍቃን የአላህ አንቀጾች ግልጾች ኾነው በእነርሱ ላይ በተነበቡላቸው ጊዜ መከራከር ይወዳሉ፦
45፥25 *አንቀጾቻችንም ግልጾች ኾነው በእነርሱ ላይ በተነበቡላቸው ጊዜ ክርክራቸው* «እውነተኞች እንደ ኾናችሁ አባቶቻችንን አምጡ» *ማለት እንጅ ሌላ አልነበረም*፡፡ وَإِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ آيَاتُنَا بَيِّنَاتٍ مَّا كَانَ حُجَّتَهُمْ إِلَّا أَن قَالُوا ائْتُوا بِآبَائِنَا إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ
10፥95 *ከእነዚያም የአላህን አንቀጾች ከአስተባበሉት አትሁን፡፡ ከከሳሪዎቹ ትሆናለህና*፡፡ وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ الَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِ اللَّهِ فَتَكُونَ مِنَ الْخَاسِرِينَ
4፥107 *ከነዚያም እራሳቸውን ከሚበድሉት ላይ አትከራከር*፤ አላህ ከዳተኛ ኀጢአተኛ የሆነን ሰው አይወድምና። وَلَا تُجَادِلْ عَنِ الَّذِينَ يَخْتَانُونَ أَنفُسَهُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ خَوَّانًا أَثِيمًا
ነጥብ አምስት
“በጥቂት አለመብቃቃት”
በጥቂት መብቃቃትን የአማኞች ባህርይ ነው፤ በጥቂት አለመብቃቃት የመናፍቃን ባህርይ ነው፦
ኢማም ቡኻሪይ: መጽሐፍ 70, ሐዲስ 22
አቢ ዑመር”ረ.ዐ.” እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“ሙዕሚን በአንድ አንጀት ይመገባል፤ ካፊር ወይም ሙናፊቅ በሰባት አንጀት ይመገባል*። عَنِ ابْنِ عُمَرَ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ إِنَّ الْمُؤْمِنَ يَأْكُلُ فِي مِعًى وَاحِدٍ، وَإِنَّ الْكَافِرَ ـ أَوِ الْمُنَافِقَ فَلاَ أَدْرِي أَيَّهُمَا قَالَ عُبَيْدُ اللَّهِ ـ يَأْكُلُ فِي سَبْعَةِ أَمْعَاءٍ ‏”‌‏.

ሙዕሚን በአንድ አንጀት ይመገባል ማለት ሲበላ በቢሥሚላህ ስለሚጀምር በረካ አለው፣ ያጣቅመዋል እና ይብቃቃል ማለት እንጅ አንድ ነው አንጀቱ ማለት አይደለም። በተጨማሪም ካፊር ወይም ሙናፊቅ በሰባት አንጀት ይመገባል ማለት በቢሥሚላህ ስለማይጀምር በረካ የለውም፣ አያጣቅመውም እና አይብቃቃም ማለት እንጅ ሰባት ነው አንጀቱ ማለት አይደለም። ይህ “መዕነዊይ” ማለትም “ፍካሬአዊ” አነጋገር እንጂ “ሒስሲይ” ማለትም “እማሬአዊ” አይደለም።

ነጥብ ስድስት
“ቁርአንን የሚቀራ ሙናፊቅ”
ቁርአንን የሚቀራ ሙናፊቅ ልክ እንደ አሪቲ ነው፤ ሽታው ያውዳል ጣዕሙ ግን ይመራል፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 6 , ሐዲስ 288,
ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ *“ቁርአንን የሚቀራ አማኝ ምሳሌው ልክ “እንደ” ትርንጎ ነው፤ ሽታው ጥሩ ነው ጣዕሙም ጥሩ ነው። ቁርአንን የማይቀራ አማኝ ደግሞ ልክ እንደ ተምር ነው፤ ሽታ የለውም ጣዕም ግን አለው። ቁርአንን የሚቀራ ሙናፊቅ አምሳያው ልክ እንደ አሪቲ ነው፤ ሽታው ያውዳል ጣዕሙ ግን ይመራል። ቁርአንን የማይቀራ ሙናፊቅ ደግሞ ልክ እንደ እንቧይ ነው ሽታ የለውም፤ ጣዕሙም መራራ ነው”* عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ الْمُؤْمِنُ الَّذِي يَقْرَأُ الْقُرْآنَ وَيَعْمَلُ بِهِ كَالأُتْرُجَّةِ، طَعْمُهَا طَيِّبٌ وَرِيحُهَا طَيِّبٌ، وَالْمُؤْمِنُ الَّذِي لاَ يَقْرَأُ الْقُرْآنَ وَيَعْمَلُ بِهِ كَالتَّمْرَةِ، طَعْمُهَا طَيِّبٌ وَلاَ رِيحَ لَهَا، وَمَثَلُ الْمُنَافِقِ الَّذِي يَقْرَأُ الْقُرْآنَ كَالرَّيْحَانَةِ، رِيحُهَا طَيِّبٌ وَطَعْمُهَا مُرٌّ، وَمَثَلُ الْمُنَافِقِ الَّذِي لاَ يَقْرَأُ الْقُرْآنَ كَالْحَنْظَلَةِ، طَعْمُهَا مُرٌّ ـ أَوْ خَبِيثٌ ـ وَرِيحُهَا مُرٌّ ‏”

ኒፋቅ በሁለት ይከፈላል፤ አንደኛው ኒፋቁል አስገር ሲሆን ይህ ባህርይ ያለበት ሙናፊቅ ባይሰኝም ግን ከላይ የተዘረዘሩት የታመኑት ጊዜ መካድ፣ ሲናገሩ መዋሸት፣ ቃል ገብቶ ማፍረስ፣ ቀጠሮን ማዛባት፣ ሲከራከር ማስተባበል ናቸው።
ሁለተኛው ኒፋቁል አክበር ሲሆን ይህ ሰው ሙናፊቅ ይባላል፤ የትልቁ ኒፋቅ ምልክቶች የአላህን መልእክተኛ ማስተባበል፣ የተቀበሉትን መልእክት በከፊሉ ማስተባበል፣ እሳቸውን መጥላት፣ መልእክታቸውን መጥላት፣ በኢስላም ዝቅ ማለት መደሰት፣ የኢስላም የበላይነትን መጥላት ናቸው ወዘተ ናቸው። ሙናፊቅ ማለት የሚችለው አላህ ብቻ ነው። ምክንያቱም ኒፋቅ ልብ ላይ ያለ በሽታ ነው፦
4፥63 *እነዚህ እነዚያ አላህ በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅባቸው ናቸው፤ እነርሱንም ተዋቸው፤ ገሥጻቸውም፤ ለእነርሱም በራሳቸው ውስጥ ስሜት ያለውን ቃል ተናገራቸው*። ﺃُﻭﻟَﺌِﻚَ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻳَﻌْﻠَﻢُ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻣَﺎ ﻓِﻲ ﻗُﻠُﻮﺑِﻬِﻢْ ﻓَﺄَﻋْﺮِﺽْ ﻋَﻨْﻬُﻢْ ﻭَﻋِﻈْﻬُﻢْ ﻭَﻗُﻞْ ﻟَﻬُﻢْ ﻓِﻲ ﺃَﻧْﻔُﺴِﻬِﻢْ ﻗَﻮْﻟًﺎ ﺑَﻠِﻴﻐًﺎ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﻨﺴﺎﺀ
3፥118 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *ከእናንተ ሌላ ምስጢረኛን አትያዙ፤ ማበላሸትን አይገቱላችሁም፤ ጉዳታችሁን ይወዳሉ፥ ጥላቻይቱ ከአፎቻቸዉ በእርግጥ ተገለጸች። ልቦቻቸዉም የሚደብቁት ይበልጥ ትልቅ ነዉ*። ልብ የምታደርጉ እንደሆናችሁ ለእናንተ ማብራራያዎችን በእርግጥ ገለጽን። يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا بِطَانَةً مِّن دُونِكُمْ لَا يَأْلُونَكُمْ خَبَالًا وَدُّوا مَا عَنِتُّمْ قَدْ بَدَتِ الْبَغْضَاءُ مِنْ أَفْوَاهِهِمْ وَمَا تُخْفِي صُدُورُهُمْ أَكْبَرُ ۚ قَدْ بَيَّنَّا لَكُمُ الْآيَاتِ ۖ إِن كُنتُمْ تَعْقِلُونَ

አላህ የቀልብ በሽታ ከሆነው ከኒፋቅ ይጠብቀን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ግዝረተ-ኢየሱስ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

21፥22 *የዐርሹ ጌታ አላህም ከሚሉት ሁሉ ጠራ*። فَسُبْحَانَ اللَّهِ رَبِّ الْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ

ፈጣሪ ጾታ የለውም። ሴትም ወንድም አይደለም፥ የሴትም የወንድም ሩካቤ ስጋ የለውም። ከዚህ በተቃራኒ ግን ኢየሱስ ጾታ አለው ወንድ ነው፦
ሉቃስ 1፥31 እነሆም፥ ትፀንሻለሽ *"ወንድ"* ልጅም *ትወልጃለሽ*፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ።

ጾታው ወንድ ስለሆነ የወንድ ሩካቤ ስጋ አለው፥ ይህ ሩካቤ ስጋ"sex organ" ሽንት ለመሽናት እና ከሴት ጋር ተራክቦ"intercourse" ለማድረግ ያገለግላል። ወንድ ሩካቤ ስጋው ላይ ያለውን ሸለፈት በስምንተኛ ቀን ይገረዛል፦
ዘፍጥረት 17፥12 *የስምንት ቀን ልጅ ይገረዝ*፤ በቤት የተወለደ ወይም ከዘራችሁ ያይደለ በብርም ከእንግዳ ሰው የተገዛ፥ ወንድ ሁሉ በትውልዳችሁ ይገረዝ።

ኢየሱስም ስምንት ቀን ሲሞላው ተገርዟል፥ በማህጸን ከመረገዙ ማለትም ከመጸነሱ በፊት ስም እንደወጣለት ስሙ ኢየሱስ ተብሎ ተጠራ፦
ሉቃስ 2፥21 *"ሊገርዙት ስምንት ቀን በሞላ ጊዜ፥ በማኅፀን ሳይጸነስ በመልአኩ እንደ ተባለ፥ ስሙ ኢየሱስ ተብሎ ተጠራ"*።
ሮሜ 15፥9 *"ክርስቶስ ስለ እግዚአብሔር እውነት የመገረዝ አገልጋይ ሆነ"* እላለሁ።

ይህ የተገረዘውን ሕጻን በጌታ ፊት ያቆሙት ዘንድ ዮሴፍና ማርያም ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት፦
ሉቃስ 2፥24 *"እንደ ሙሴም ሕግ የመንጻታቸው ወራት በተፈጸመ ጊዜ፥ በጌታ ሕግ፦ የእናቱን ማኅፀን የሚከፍት ወንድ ሁሉ ለጌታ የተቀደሰ ይባላል ተብሎ እንደ ተጻፈ *"በጌታ ፊት ሊያቆሙት፥ በጌታም ሕግ፦ ሁለት ዋሊያ ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች እንደ ተባለ፥ መሥዋዕት ሊያቀርቡ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት"*።

አስቡት ፈጣሪ ጾታ ኖሮት፣ ወንድ ሆኖ፣ ተገርዞ፣ በጌታ ፊት ሊያቆሙት ሲወስዱት። አያችሁ የሁሉ ጌታ እና ሕጻኑ ሁለት የለያዩ ኑባሬ እንደሆኑ?
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ጥር 6 ቀን በዓመት አንዴ "ግዝረተ ኢየሱስ" ተብሎ የተገዘረበትን ዓመታዊ ክብረ በዓል ትዘክራለች። "ግዝረት" ማለት የግዕዝ ቃል ሲሆን "ግርዘት"circumcision" ማለት ነው። ይህ ተቆርጦ የተገዘረው ሸለፈት ስጋ አምላክ ነው፥ ይመለካል፦
ሃይማኖተ-አበው ዘቄርሎስ 78፥31
ቄርሎስም አለ፦
“ወዓዲ ንቤ እስመ ሥጋሁ ለእግዚእነ ክርስቶስ አምላክ ውእቱ”

ትርጉም፦
“ዳግመኛ የጌታችን የክርስቶስ ስጋ አምላክ እንደሆነ እንናገራለን”

"የክርስቶስ ስጋ አምላክ እንደሆነ እንናገራለን" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። ያ የተገዘው ሸለፈት ስጋ አምላክ ከነበረ ዛሬ የት ይገኛል? አሁን ተሸልቶ አፈር ሆኖ ታመልኩታላችሁን? የዐርሹ ጌታ አላህም ከሚሉት ሁሉ ጠራ፦
21፥22 *የዐርሹ ጌታ አላህም ከሚሉት ሁሉ ጠራ*። فَسُبْحَانَ اللَّهِ رَبِّ الْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ውይይት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

16:125 ወደ ጌታህ መንገድ *በብልሃትና በመልካም ግሣጼ በለዘብታ ቃል ጥራ”፤ በዚያችም እርሷ መልካም በሆነችው “ዘዴ ተከራከራቸው”*፤ ٱدْعُ إِلَىٰ سَبِيلِ رَبِّكَ بِٱلْحِكْمَةِ وَٱلْمَوْعِظَةِ ٱلْحَسَنَةِ ۖ وَجَٰدِلْهُم بِٱلَّتِى هِىَ أَحْسَنُ ۚ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعْلَمُ بِمَن ضَلَّ عَن سَبِيلِهِۦ ۖ وَهُوَ أَعْلَمُ بِٱلْمُهْتَدِينَ

"ውይይት" በተቃናቃኝ እና በአቀንቃኝ አሊያም በአውንታዊ እና በአሉታዊ አመለካከት ባላቸው ሰዎች መካከል የሚደረግ ሙግት ብቻ ሳይሆን ችግር ሲመጣ የመጣው ችግር ለማንበብ፣ ለመረዳት፣ ለመፍታት አይነተኛ ቁልፍ ነው፤ ማንኛውም ውይይት አላህ ይሰማዋል፣ ያውቀዋል፣ የቂያማ ቀን በቀኝና በግራ ያሉት መላእክትም ውይይታችንን ጽፈውት ያስጠይቀናል፦
9፥78 አላህ ምስጢራቸውን እና *ውይይታቸውን የሚያውቅ መኾኑን* አላህም ሩቆችን ሁሉ በጣም ዐዋቂ መኾኑን አያውቁምን? أَلَمْ يَعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ يَعْلَمُ سِرَّهُمْ وَنَجْوَىٰهُمْ وَأَنَّ ٱللَّهَ عَلَّٰمُ ٱلْغُيُوبِ
43፥80 ወይም እኛ ምስጢራቸውን እና *ውይይታቸውን የማንሰማ መኾናችንን ያስባሉን? አይደለም፤ መልክተኞቻችንም እነርሱ ዘንድ ይጽፋሉ*፡፡ أَمْ يَحْسَبُونَ أَنَّا لَا نَسْمَعُ سِرَّهُمْ وَنَجْوَىٰهُم ۚ بَلَىٰ وَرُسُلُنَا لَدَيْهِمْ يَكْتُبُونَ

ስለዚህ ውይይት ለአላህ ውዴታ ተብሎ የሚቀርብ የማስተማሪያ ጥበብ እንጂ የሌላውን ሰው ሃሳብና ስሜት ለማብጠልጠል፣ ለማጠልሸት፣ ለማበሻቀጥ፣ ለማነወር፣ ተብሎ የሚደረግ ንትርክ ወይም እሰጣገባ አይደለም። ለውይይት ምህዳር የሚሆኑ ቅድመ-ሁኔታ እስቲ ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
"ሥነ-እውነት"
የሥነ-እውነት ጥናት"metaphysics" ምሁራን እንደሚያትቱት እውነት አንድ ሲሆን ሁለት ገፅታዎች አሉት፤ አንዱ "ውሳጣዊ እውነታ"subjective truth" ሲሆን ለምሳሌ እኔ አሳ መብላት እወዳለው ብል፤ ሌላ ሰው አልወድም ብንል ሁለታችንም ትክክል ነን፤ ይህ "ውሳጣዊ እውነታ" ይባላል፤ ሁለተኛው ደግሞ "ውጫዊ እውነታ"objective truth" ሲሆን ለምሳሌ ቢጫ ቀለም በየትኛውም ቋንቋ ስሙ ይቀያየር እንጂ ቢጫ ቀይ፣ አረንጓዴ፣ ነጭ አይደለም፤ ይህ "ውጫዊ እውነታ" ይባላል፤ አንድ ሰው ይህንን እውነታ ሲቃረን ዕውቀት ጎድሎት በመሃይምነት እንዳለ ያሳብቅበታል። አምላካችን አላህ ከሰዎች ጋር ባለን መስተጋብር፦ "ትክክለኛውንም ንግግር” ተናገሩ" "ሐሰትንም ቃል ራቁ" ይለናል፦
33:70 እላንተ ያመናችሁ ሆይ አላህን ፍሩ፤ *ትክክለኛውንም ንግግር” ተናገሩ*። يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَقُولُوا۟ قَوْلًۭا سَدِيدًۭا
22፥30 ከጣዖታትም ርክሰት ተጠንቀቁ፡፡ *ሐሰትንም ቃል ራቁ*፡፡ فَٱجْتَنِبُوا۟ ٱلرِّجْسَ مِنَ ٱلْأَوْثَٰنِ وَٱجْتَنِبُوا۟ قَوْلَ ٱلزُّورِ

እውነትን ለመግለጥ ሃሰትን ለማጋለጥ እውነቱ ምንድን ነው? ሃሰቱ ምንድን ነው? ብሎ መሞገት እንጂ እውነተኛው ማን ነው? ሃሰተኛው ማነው? ካልክ ሰውዬው ወደ ግትረኛነት ወይም ወደ መበሻሸቅ ይሄዳል፤ ስለዚህ ውይይት ለማድረግ ሃቅ መያዝ አይነተኛ ሚና ነው፤ አንድ ሰው እውነተኛ ለመሆን ማስረጃ ማቅረብ አለበት፤ ሁሌም ማስረጃ ከያዙ እውነተኞች ጋር መሆን አለብን፦
2፥111 *እውነተኞች እንደኾናችሁ ማስረጃችሁን አምጡ* በላቸው፡፡ قُلْ هَاتُوا۟ بُرْهَٰنَكُمْ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
9፥119 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፤ *ከእውነተኞቹም ጋር ኹኑ*፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَكُونُوا۟ مَعَ ٱلصَّٰدِقِينَ

የተሟላ ማስረጃ ማለት ደግሞ ከአላህ የሚመጣው የአላህ ንግግር ነው፦
6፥149 *የተሟላው ማስረጃ የአላህ ነው*፡፡ በሻም ኖሮ ሁላችሁንም ባቀናችሁ ነበር» *በላቸው*፡፡ قُلْ فَلِلَّهِ ٱلْحُجَّةُ ٱلْبَٰلِغَةُ ۖ فَلَوْ شَآءَ لَهَدَىٰكُمْ أَجْمَعِينَ
45፥6 *እነዚህ በአንተ ላይ በእውነት የምናነባቸው ሲኾኑ የአላህ ማስረጃዎች ናቸው፡፡ ከአላህና ከማስረጃዎቹም ወዲያ በየትኛው ንግግር ያምናሉ*? تِلْكَ ءَايَٰتُ ٱللَّهِ نَتْلُوهَا عَلَيْكَ بِٱلْحَقِّ ۖ فَبِأَىِّ حَدِيثٍۭ بَعْدَ ٱللَّهِ وَءَايَٰتِهِۦ يُؤْمِنُونَ
ነጥብ ሁለት
"ሥነ-ዕውቀት"
"የሥነ-ዕውቀት ጥናት"epistemology" ምሁራን ዕውቀት በሁለት ይከፍሉታል፤ አንዱ "ውሳጣዊ ዕውቀት"Rational knowledge" ሲሆን ለምሳሌ ከውስጥ የሚመጣ እሳቤ፣ ፈጠራ፣ መፍትሔ ወዘተ "ውሳጣዊ እውነታ" ይባላል፤ ሁለተኛው ደግሞ "ውጫዊ ዕውቀት"Irational knowledge" ሲሆን ለምሳሌ ልምድ፣ ተሞርኮ፣ ሰርቶ ማሳያ ወዘተ "ውጫዊ ዕውቀት" ይባላል፤ ዕውቀት ለብዙ ነገር ማስረጃ ነው፤ እውነተኛ ሰው በዕውቀት ይናገራል፤ ያለ ዕውቀት አንድን እምነት መከተል ያስጠይቃል፦
6፥143 *እውነተኞች እንደሆናችሁ በዕውቀት ንገሩኝ* በላቸው፡፡ نَبِّـُٔونِى بِعِلْمٍ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
17፥36 *ለአንተም በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር አትከተል*፡፡ መስሚያ፣ ማያም፣ ልብም እነዚህ ሁሉ ባለቤታቸው ከእነርሱ ተጠያቂ ነውና፡፡ وَلَا تَقْفُ مَا لَيْسَ لَكَ بِهِۦ عِلْمٌ ۚ إِنَّ ٱلسَّمْعَ وَٱلْبَصَرَ وَٱلْفُؤَادَ كُلُّ أُو۟لَٰٓئِكَ كَانَ عَنْهُ مَسْـُٔولًۭا

አንድ ነገረኛ ወሬን ቢያመጣልን በስሕተት ላይ ሆነን ሕዝቦችን እንዳንጎዳ እና በሠራነው ነገር ላይ ተጸጻቾች እንዳንሆን በዕውቀት በተደገፈ ማስረጃ ማረጋገጥ አለብን፦
49:6 እላንተ ያመናችሁ ሆይ ነገረኛ *ወሬን ቢያመጣላችሁ” በስሕተት ላይ ሆናችሁ “ሕዝቦችን እንዳትጎዱ” እና በሠራችሁት ነገር ላይ “ተጸጻቾች” እንዳትሆኑ ”አረጋግጡ”*። يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِن جَآءَكُمْ فَاسِقٌۢ بِنَبَإٍۢ فَتَبَيَّنُوٓا۟ أَن تُصِيبُوا۟ قَوْمًۢا بِجَهَٰلَةٍۢ فَتُصْبِحُوا۟ عَلَىٰ مَا فَعَلْتُمْ نَٰدِمِينَ

ዕውቀት ከሰው ልጅ አዕምሮ ሲመጣ "ዐቅል" عقل ሲባል ወሕይ ሆኖ ወደ ነብያት ሲመጣ ደግሞ "ነቅል" نفل ይባላል፤ ለምሳሌ ቁርአን ከዕውቀት ጋርም የተዘረዘረ መጽሐፍ ነው፤ ነብያችን"ﷺ" የማያውቁት እና ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቃቸው አላህ ነው፦
7፥52 *ከዕውቀት ጋርም የዘረዘርነው የኾነን መጽሐፍ ለሚያምኑ ሕዝቦች መምሪያና እዝነት ሲኾን በእርግጥ አመጣንላቸው*፡፡ وَلَقَدْ جِئْنَٰهُم بِكِتَٰبٍۢ فَصَّلْنَٰهُ عَلَىٰ عِلْمٍ هُدًۭى وَرَحْمَةًۭ لِّقَوْمٍۢ يُؤْمِنُونَ
4፥114 *አላህም በአንተ ላይ መጽሐፍንና ጥበብን አወረደ፤ የማታውቀውንም ሁሉ ዐሳወቀህ*፡፡ የአላህም ችሮታ በአንተ ላይ ታላቅ ነው፡፡ وَأَنزَلَ ٱللَّهُ عَلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْحِكْمَةَ وَعَلَّمَكَ مَا لَمْ تَكُن تَعْلَمُ ۚ وَكَانَ فَضْلُ ٱللَّهِ عَلَيْكَ عَظِيمًۭا
55፥1-2 *አል-ረሕማን ቁርኣንን አሳወቀ*፡፡ ٱلرَّحْمَٰنُ عَلَّمَ ٱلْقُرْءَانَ
96፥5 *ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን*፡፡ عَلَّمَ ٱلْإِنسَٰنَ مَا لَمْ يَعْلَمْ

ነጥብ ሶስት
"ሥነ-አመክንዮ"
"የሥነ-አመክንዮ"Logic" ምሁራን "ሙግት"argument" በሁለት ይከፍሉታል፤ አንዱ "ስሙር ሙግት"valid argument" ሲሆን ይህ ሙግት በእማኝነትና በአስረጂነት ጠቅሶና አጣቅሶ መሟገት ነው፤ በትክክለኛው የአስተላለፍ ስልትና አወቃቀር ስለተዋቀረ የራሱ የሆነ መንደርደሪ፣ የሙግት ነጥብ"premise"፣ መደምደሚያ ያለው ነው፤ ዕውቀት ላይ የተመሰረተ ማስረጃ በአጽንኦትና በአንክሮት ለማዳመጥ ጥልና ጥንፍፍ ያለ መረዳት ነው፤ ይህን ሙግት አምላካችን አላህ መልካም ክርክር ይለዋል፤ ይህ ዘዴ ርቱዕ አካሄድ"optimistic approach" ነው፦
16:125 ወደ ጌታህ መንገድ *በብልሃትና በመልካም ግሣጼ በለዘብታ ቃል ጥራ”፤ በዚያችም እርሷ መልካም በሆነችው “ዘዴ ተከራከራቸው”*፤ ٱدْعُ إِلَىٰ سَبِيلِ رَبِّكَ بِٱلْحِكْمَةِ وَٱلْمَوْعِظَةِ ٱلْحَسَنَةِ ۖ وَجَٰدِلْهُم بِٱلَّتِى هِىَ أَحْسَنُ ۚ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعْلَمُ بِمَن ضَلَّ عَن سَبِيلِهِۦ ۖ وَهُوَ أَعْلَمُ بِٱلْمُهْتَدِينَ
29፥46 የመጽሐፉን ባለቤቶችም በዚያች እርሷ *መልካም በኾነችው ክርክር እንጂ አትከራከሩ*፡፡ ከእነርሱ እነዚያን የበደሉትን ሲቀር፡፡ በሉም «በዚያ ወደኛ በተወረደው ወደናንተም በተወረደው አመንን፡፡ አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው፡፡ እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን፡፡» وَلَا تُجَٰدِلُوٓا۟ أَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ إِلَّا بِٱلَّتِى هِىَ أَحْسَنُ إِلَّا ٱلَّذِينَ ظَلَمُوا۟ مِنْهُمْ ۖ وَقُولُوٓا۟ ءَامَنَّا بِٱلَّذِىٓ أُنزِلَ إِلَيْنَا وَأُنزِلَ إِلَيْكُمْ وَإِلَٰهُنَا وَإِلَٰهُكُمْ وَٰحِدٌۭ وَنَحْنُ لَهُۥ مُسْلِمُونَ

ሁለተኛው ሙግት ደግሞ "ስሁት ሙግት"Invalid argument" ሲሆን ይህ ሙግት ያለ ዕውቀትና ያለ መረጃ እውርር ድንብር የሆነ ፀለምተኛ ሙግት ነው፤ ሰው ሱሪ በአንገቴ ካለ ዓይን ያስፈጠጠ እውነት ዓይኔን ግንባር ያርገው ብሎ የጨባራ ለቅሶ ውስጥ እርርና ምርር ብሎ የሚንጨረጨረውና የሚንተከተከው በዚህ ሙግት ነው፤ ይህ አካሄድ ኢርቱዕ አካሄድ"pessimistic approach" ነው፦
22፥8 *ከሰዎችም ውስጥ ያለ ዕውቀት፣ ያለ ማስረጃም፣ ያለ አብራሪ መጽሐፍም በአላህ ጉዳይ የሚከራከር ሰው አለ*፡፡ وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يُجَٰدِلُ فِى ٱللَّهِ بِغَيْرِ عِلْمٍۢ وَلَا هُدًۭى وَلَا كِتَٰبٍۢ مُّنِيرٍۢ

በድርቅና ያለ ዕውቀት፣ ያለ ማስረጃም፣ ያለ አብራሪ መጽሐፍም የሚከራከርን ሰው መሃይምነት ስላጠቃው መሃይማን በክፉ ሲያነጋግሩን በሰላም ውይይቱን መተው ነው፤ ምክንያቱም ወደ ብሽሽቅ ስለሚያስገባ ነው፤ ብሽሽቅ ውስጥ መልካም የሆነችውን ቃል ስለማንናገር ሰይጣን በመካከላቸው ያበላሻልና፦
7:199 “ገርን ጠባይ ያዝ”፤ በመልካምም እዘዝ “መሃይማንን” الْجَاهِلِينَ ተዋቸው። خُذِ ٱلْعَفْوَ وَأْمُرْ بِٱلْعُرْفِ وَأَعْرِضْ عَنِ ٱلْجَٰهِلِينَ
25:63 የአልረሕማንም ባሮች እነዚያ በምድር ላይ “በዝግታ የሚኼዱት”፣ “መሃይማን” الْجَاهِلُونَ በክፉ ባነጋገሩዋቸው ጊዜ፣ “ሰላም” የሚሉት ናቸው። وَعِبَادُ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلَّذِينَ يَمْشُونَ عَلَى ٱلْأَرْضِ هَوْنًۭا وَإِذَا خَاطَبَهُمُ ٱلْجَٰهِلُونَ قَالُوا۟ سَلَٰمًۭا
17:53 ለባሮቼም በላቸው፦ ያችን እርሷ “መልካም የሆነችውን ቃል ይናገሩ”፤ ሰይጣን በመካከላቸው ያበላሻልና፤ ሰይጣን ለሰው ግልጽ ጠላት ነውና። وَقُل لِّعِبَادِى يَقُولُوا۟ ٱلَّتِى هِىَ أَحْسَنُ ۚ إِنَّ ٱلشَّيْطَٰنَ يَنزَغُ بَيْنَهُمْ ۚ إِنَّ ٱلشَّيْطَٰنَ كَانَ لِلْإِنسَٰنِ عَدُوًّۭا مُّبِينًۭا

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አሐዳዊያን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፤

21፥108 «ያ ወደ እኔ የሚወረደው፦ *”አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው”* ማለት ነው፤ ታዲያ እናንተ ፍጹም “ታዛዦች” ናችሁን?» *በላቸው*፡፡ قُلْ إِنَّمَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّسْلِمُونَ

በሥነ-መለኮት ጥናት ክርስትና፣ አይሁድ እና እስልምና አሐዳዊ ሃይማኖት"monotheistic Religion" ተብለው ይመደባሉ፤ ክርስቲያን፣ አይሁዳውያን እና ሙስሊም አሐዳውያን"Monotheism" ይባላሉ፤ ምክንያቱም ፈጣሪ በህላዌ ማለትም በምንነት አንድ ኑባሬ ነው ብለው ስለሚያምኑ ነው።

ነገር ግን የክርስትና አሐዳውያን በሥስት ዋና ዋና ክፍል ይከፈላሉ፤ እነርሱም፦
1ኛ አሓዳውያን“Unitarian” ሲሆኑ፤ “uni” ማለት "አንድ" ማለት ሲሆን ለእነርሱ አምላክ በምንነት እና በማንነት አንድ ስለሆነ አምላካቸውን “mono-une God” ይሉታል፤ እነዚህ የመጀመሪያ መቶ ክፍለ-ዘመን የኢየሱስ ቀዳማይ ተከታዮች ነበሩ።
2ኛ ደግሞ ክሌታውያ“Binitarian” ይባላል፤ “Bini” ማለት "ሁለት" ማለት ሲሆን ለእነርሱ አምላክ በምንነት አንድ ሲሆን በማንነት ደግሞ ሁለቱ አብና ወልድ ናቸው፤ አምላካቸውን “Bini-une God” ይሉት ነበር፤ ይህ ትምህርት ሁለተኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ላይ የዳበረ ትምህርት ነው።
3ኛ ሥላሴአዊያን“Trinitarian” ይባላሉ፤ “Tri” ማለት "ሶስት" ማለት ነው፤ ለእነርሱ አምላክ በምንነት አንድ ሲሆን በማንነት ሶስት ስለሆነ አምላካቸው “Tri-une God” ይባላል፤ ይህ በአራተኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ላይ የዳበረ ትምህርት ነው።

እንግዲህ አምላካችን አላህ ቁርአንን በነብያችን”ﷺ" ላይ ሲያወርድ የኢየሱስ ቀዳማይ ተከታዮች ትምህርት የያዙ ዩኒታሪያን በጥቂትም ቢሆኑ ነበሩ፤ አምላካችን አላህ እኛ እንዲህ እንድል አዞናል፦
3፥64 የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! *በእኛ እና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ*፡፡ እርሷም *አላህን እንጅ ሌላን ላናመልክ፣ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው፤ በላቸው*፡፡ እምቢ ቢሉም፡- *እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው*፡፡ قُلْ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ تَعَالَوْا إِلَىٰ كَلِمَةٍ سَوَاءٍ بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمْ أَلَّا نَعْبُدَ إِلَّا اللَّهَ وَلَا نُشْرِكَ بِهِ شَيْئًا وَلَا يَتَّخِذَ بَعْضُنَا بَعْضًا أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ ۚ فَإِن تَوَلَّوْا فَقُولُوا اشْهَدُوا بِأَنَّا مُسْلِمُونَ

የተውሒድ እሳቤ በእኛ እና በመጽሐፉ ባለቤቶች መካከል ትክክል የኾነች የጋራ ቃል ናት፤ ይህንን ጥሪ ያስተባበሉትን "እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክሩ" እንላቸዋለን፤ ነገር ግን ጥቂት ቀጥተኛ አሐዳዊያን በእነርሱ ላይ ቁርአን በሚነበብላቸውም ጊዜ «በእርሱ አምነናል፡፡ እርሱ ከጌታችን የኾነ እውነት ነው፤ እኛ ከእርሱ በፊት ሙስሊሞች ነበርን» ይላሉ፦
28፥52 እነዚያ ከእርሱ በፊት መጽሐፍን የሰጠናቸው እነርሱ *በእርሱ ያምናሉ*፡፡ الَّذِينَ آتَيْنَاهُمُ الْكِتَابَ مِن قَبْلِهِ هُم بِهِ يُؤْمِنُونَ
28፥53 በእነርሱ ላይ በሚነበብላቸውም ጊዜ «በእርሱ አምነናል፡፡ እርሱ ከጌታችን የኾነ እውነት ነው፡፡ *እኛ ከእርሱ በፊት ሙስሊሞች ነበርን*» ይላሉ፡፡ وَإِذَا يُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ قَالُوا آمَنَّا بِهِ إِنَّهُ الْحَقُّ مِن رَّبِّنَا إِنَّا كُنَّا مِن قَبْلِهِ مُسْلِمِينَ

ልብ አድርግ "እኛ ከእርሱ ማለትም ከቁርአን መውረድ በፊት ሙስሊም ነበርን" ማለታቸው ምክንያታዊ ነው፤ ሙስሊም” مُسْلِم ትርጉሙ “አቢድ” عَابِدُ ማለትም “አምላኪ” አሊያም “ቃኒት” قَانِتِ ማለትም “ታዛዥ” ማለት ነው፦
21፥108 «ያ ወደ እኔ የሚወረደው፦ *”አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው”* ማለት ነው፤ ታዲያ እናንተ ፍጹም “ታዛዦች” ናችሁን?» *በላቸው*፡፡ قُلْ إِنَّمَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّسْلِمُونَ

ወደ ነብያችን የሚወርደው ቁርአን "አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው” የሚል የተውሒድ ትምህርት ነው፤ አሁንም "ታዛዦች” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሙስሊሙን” مُّسْلِمُونَ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል፤ ከመጽሐፉ ሰዎች ቁርአንን ተገቢ ንባቡን ያነቡታል፤ እነዚያ በእርሱ ያምናሉ፤ በእነርሱ ላይ በተነበበ ጊዜ ሰጋጆች ኾነው በሸንጎበቶቻቸው ላይ ይወድቃሉ፤ "ጌታችን ጥራት ይገባው! እነሆ የጌታችን ተስፋ ተፈጻሚ ነው" ይላሉ፦
2፥121 እነዚያ መጽሐፉን የሰጠናቸው ተገቢ ንባቡን ያነቡታል፡፡ *እነዚያ በእርሱ ያምናሉ፤ በእርሱም የሚክዱ እነዚያ እነርሱ ከሳሪዎቹ ናቸው*፡፡ الَّذِينَ آتَيْنَاهُمُ الْكِتَابَ يَتْلُونَهُ حَقَّ تِلَاوَتِهِ أُولَـٰئِكَ يُؤْمِنُونَ بِهِ ۗ وَمَن يَكْفُرْ بِهِ فَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْخَاسِرُونَ
17፥106 *ቁርኣንንም በሰዎች ላይ በዝግታ ላይ ኾነህ ታነበው ዘንድ ከፋፈልነው፡፡ ቀስ በቀስ ማውረድንም አወረድነው*፡፡ وَقُرْءَانًۭا فَرَقْنَٰهُ لِتَقْرَأَهُۥ عَلَى ٱلنَّاسِ عَلَىٰ مُكْثٍۢ وَنَزَّلْنَٰهُ تَنزِيلًۭا
17፥107 *«በእርሱ እመኑ ወይም አትመኑ»* በላቸው፤ እነዚያ ከእርሱ በፊት ዕውቀትን የተሰጡት *በእነርሱ ላይ በተነበበ ጊዜ ሰጋጆች ኾነው በሸንጎበቶቻቸው ላይ ይወድቃሉ*፤ قُلْ ءَامِنُوا۟ بِهِۦٓ أَوْ لَا تُؤْمِنُوٓا۟ ۚ إِنَّ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْعِلْمَ مِن قَبْلِهِۦٓ إِذَا يُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ يَخِرُّونَ لِلْأَذْقَانِ سُجَّدًۭا
17፥108 *ይላሉም «ጌታችን ጥራት ይገባው! እነሆ የጌታችን ተስፋ ተፈጻሚ ነው፡፡»* وَيَقُولُونَ سُبْحَٰنَ رَبِّنَآ إِن كَانَ وَعْدُ رَبِّنَا لَمَفْعُولًۭا
3:113 *የመጽሐፉ ሰዎች ሁሉ እኩል አይደሉም፤ ከመጽሐፉ ሰዎች ቀጥ ያሉ በሌሊት ሰዓቶች እነርሱ የሚሰግዱ ኾነው የአላህን አንቀጾች የሚያነቡ ሕዝቦች አሉ*፡፡ لَيْسُوا۟ سَوَآءًۗ مِّنْ أَهْلِ ٱلْكِتَٰبِ أُمَّةٌ قَآئِمَةٌ يَتْلُونَ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ ءَانَآءَ ٱلَّيْلِ وَهُمْ يَسْجُدُونَ
ከመጽሐፉ ሰዎች በእርሱ በቁርአን የሚክዱ እነዚያ እነርሱ ከሳሪዎቹ ናቸው፤ የመጽሐፉ ሰዎች ሁሉ እኩል አይደሉም፤ አብዛኛዎቻቸም አመጸኞች ናቸው፤ እነዚያ ከመጽሐፉ ሰዎች የካዱት በገሀነም እሳት ውስጥ ናቸው፤ በውስጧ ዘውታሪዎች ሲኾኑ እነዚያ እነርሱ ከፍጥረት ሁሉ ክፉ ናቸው፦
5፥59 «የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በአላህ እና ወደ እኛ በተወረደው በፊትም በተወረደው ለማመናችን *አብዛኞቻችሁም አመጸኞች ለመኾናችሁ* እንጅ ሌላን ነገር ከእኛ ትጠላላችሁን» በላቸው፡፡ قُلْ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ هَلْ تَنقِمُونَ مِنَّا إِلَّا أَنْ آمَنَّا بِاللَّهِ وَمَا أُنزِلَ إِلَيْنَا وَمَا أُنزِلَ مِن قَبْلُ وَأَنَّ أَكْثَرَكُمْ فَاسِقُونَ
98:6 *እነዚያ ከመጽሐፉ ሰዎች የካዱት*፣ አጋሪዎቹም *በገሀነም እሳት ውስጥ ናቸው*፤ በውስጧ ዘውታሪዎች ሲኾኑ እነዚያ እነርሱ ከፍጥረት ሁሉ ክፉ ናቸው፡፡ إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ مِنْ أَهْلِ ٱلْكِتَٰبِ وَٱلْمُشْرِكِينَ فِى نَارِ جَهَنَّمَ خَٰلِدِينَ فِيهَآۚ أُو۟لَٰٓئِكَ هُمْ شَرُّ ٱلْبَرِيَّةِ

ምክንያቱም ከመጽሐፋ ሰዎች አብዛኛውን በሃይማኖታቸው ወሰን በማለፍ በአላህም ምንነት ላይ "ሦስት ነው" በማለት ቀጥፈዋል፤ አላህ በአንድ ምንነቱ ላይ ሦስት ማንነት የሌለበት አንድ አምላክ ብቻ ነው፦
4፥171 እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! *በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፡፡ በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ።….. « ሦስት ነው» አትበሉም وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ተከልከሉ፤ ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው*፡፡ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا تَغْلُوا۟ فِى دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ إِلَّا ٱلْحَقَّ ۚ إِنَّمَا ٱلْمَسِيحُ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ ٱللَّهِ وَكَلِمَتُهُۥٓ أَلْقَىٰهَآ إِلَىٰ مَرْيَمَ وَرُوحٌۭ مِّنْهُ ۖ فَـَٔامِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦ ۖ وَلَا تَقُولُوا۟ ثَلَٰثَةٌ ۚ ٱنتَهُوا۟ خَيْرًۭا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا ٱللَّهُ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ

ከመጽሐፉን ባለቤቶችንም እነዚያን በአላህ ላይ በማጋራት የበደሉትን ሲቀሩ ለእነርሱ "በዚያ ወደ እኛ በተወረደው ወደ እናንተም በተወረደው አመንን፤ አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው፡፡ እኛም ለእርሱ ለአንድ አምላክ ሙስሊሞች ነን" እንላለን፦
29፥46 የመጽሐፉን ባለቤቶችንም በዚያች እርሷ መልካም በኾነችው ክርክር እንጂ አትከራከሩ፡፡ *ከእነርሱ እነዚያን የበደሉትን ሲቀር*፡፡ በሉም *«በዚያ ወደ እኛ በተወረደው ወደ እናንተም በተወረደው አመንን፡፡ አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው፡፡ እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን*፡፡» وَلَا تُجَادِلُوا أَهْلَ الْكِتَابِ إِلَّا بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ إِلَّا الَّذِينَ ظَلَمُوا مِنْهُمْ ۖ وَقُولُوا آمَنَّا بِالَّذِي أُنزِلَ إِلَيْنَا وَأُنزِلَ إِلَيْكُمْ وَإِلَـٰهُنَا وَإِلَـٰهُكُمْ وَاحِدٌ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ

ይህ መጣጥፍ የዩኒታሪያንን ተከታዮችን ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ሀፍረተ ቢስነት ሲገን.pdf
1.3 MB
ከሰሞኑ ስለኩረጃ በማውራት ሲንቀበቀቡ የምናያቸው የፕሮቴስታንት ተርጓሚዎች ሲፈተሹ ..
___

@yahya5
ኢየሱስ ይመለካልን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

5፥117 «በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል፦ *ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ* ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ

“ዒባዳ” عبادة የሚለው ቃል “ዓበደ عَبَدَ “አመለከ” ከሚል ግስ የተገኘ ሲሆን “አምልኮ” ማለት ነው፤ አምልኮ የሚገባው አንዱ አምላክ አላህ ብቻ ነው፤ አላህ ዒሳን በል ብሎ ያዘዘው ቃል፦ “ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ” ማለትን ነው፦
5፥117 «በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል፦ *ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ* ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ

ነገር ግን በተቃራኒው ክርስቲያኖች ኢየሱስን በቀጥታ ያመልካሉ፤ “አምልኮ” የሚለው ቃል በእብራይስጥ “አቫድ” עָבַד ሲሆን በግሪክ ደግሞ “ላትሬኦ” λατρεύω ነው፤ ይህም ለአንዱ አምላክ ብቻ በሙሉ ሁለንተና የሚቀርብ ልመና፣ ስእለት፣ማጎብደድ፣ መተናነስ፣ ስግደት፣ መገዛት ፣ አገልግሎት Adoration ነው። ኢየሱስ፦ አምልኩኝ ያለበት፣ ሀዋርያት እና ነብያት፦ ኢየሱስን አምልኩ ያለበት እና ሰዎች ኢየሱስን ያመለኩበት አንድ አንቀጽ የለም። ነገር ግን ኢየሱስ የሚመለክ መሆኑን የሚጠቁሙ ጥቅሶች አሉ ይላሉ፤ እውን ይህ ጥቅስ ኢየሱስ ይመለካል ይላልን? እስቲ ጥቅሱን እንየው፦
ዳንኤል 7፥13-14 በሌሊት ራእይ አየሁ፤ እነሆም፥ “የሰው ልጅ የሚመስል” ከሰማይ ደመናት ጋር መጣ በዘመናት ወደ ሸመገለውም ደረሰ፤ ወደ ፊቱም አቀረቡት። ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ “ይገዙለት” δουλεύσουσιν ዘንድ ግዛትና ክብር መንግሥትም “ተሰጠው”፤ ግዛቱም የማያልፍ የዘላለም ግዛት ነው፥ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው።

ነጥብ አንድ
“የሰው ልጅ የሚመስል”
ዳንኤል በራእይ አራትም ታላላቅ አራዊት ከባሕር ሲወጡ አየ፤ እነዚህ አራቱ ታላላቅ አራዊት ከምድር የሚነሡ አራት ነገሥታት ናቸው፤ በራእይ ያየው “የሰው ልጅ የሚመስል” ደግሞ “የልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ” ነው፦
ዳንኤል 7፥27 መንግሥትም ግዛትም ከሰማይም ሁሉ በታች ያሉ የመንግሥታት ታላቅነት *”ለልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ”* ይሰጣል፤ መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ነው፥ ግዛቶችም ሁሉ “ይገዙለታል* δουλεύσουσι ይታዘዙለትማል።
ዳንኤል 7፥18 ነገር ግን *”የልዑሉ ቅዱሳን”* መንግሥቱን ይወስዳሉ፥ እስከ ዘላለም ዓለምም መንግሥቱን ይወርሳሉ።
ዳንኤል 7፥22 *”በዘመናት የሸመገለው እስኪመጣ ድረስ፥ ፍርድም ለልዑሉ ቅዱሳን እስኪሰጥ ድረስ”*፥ ቅዱሳኑም መንግሥቱን የሚወስዱበት ዘመን እስኪመጣ ድረስ አሸነፋቸውም።
ዘጸአት 19፥6 *”እናንተም የካህናት መንግሥት የተቀደሰም ሕዝብ ትሆኑልኛላችሁ”*። ለእስራኤል ልጆች የምትነግራቸው ቃል ይህ ነው።

የአይሁድ ኮሜንቴርይ፦ “የሰው ልጅ የሚመስል” የተባለው ዐውዱ ላይ የእስራኤል ሕዝብ ነው” ብለው የፈሠሩት። ዐውዱ ላይ የሰው ልጅ የሚመስል የልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ መሆኑን ፍትንው አርጎ ከዘጋ በኃላ ሌላ ትርጉም እንዳንሰጥ “የነገሩም ፍጻሜ እስከዚህ ድረስ ነው” በማለት ይቋጫል፦
ዳንኤል 7፥28 የነገሩም ፍጻሜ እስከዚህ ድረስ ነው።
ነጥብ ሁለት
“ተሰጠው”
ሙግቱን ጠበብ አድርገነው ዳንኤል ላይ “የሰው ልጅ የሚመስል” የተባለው ኢየሱስ ነው ቢባል እንኳን አሁንም ፍጡር ከመሆን የዘለለ ማንነት የለውም። ምክንያቱም በሃረጉ ውስጥ “ተሰጠው” የሚል ሃይለ-ቃል አለ፤ ሰጪው ደግሞ “በዘመናት የሸመገለው” አብ ነው፤ አንዱ አምላክ ለኢየሱስ የአባቱን ዙፋን ሰጥቶታል፦
ማቴዎስ 28፥18 ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ *ሥልጣን ሁሉ* በሰማይና በምድር *ተሰጠኝ*።
ሉቃስ 10፥22 *ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል*፥
ሉቃስ 1፥32 እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ *ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል*፤

ሰው እና የሰው ልጅ የተባለው ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ተለይቶ ፍጡር ነው፤ ታዲያ ይልቁንስ *ብስብስ የሆነ ሰው፥ ትልም የሆነ የሰው ልጅ በእግዚአብሔር ፊት ምንኛ ያንስ?
ዮሐንስ 13:31 ከወጣም በኋላ ኢየሱስ እንዲ አለ። *አሁን የሰው ልጅ ከበረ እግዚእብሔርም ሰለ እርሱ ከበረ*፤
ኢዮብ 25፥6 ይልቁንስ *ብስብስ የሆነ ሰው፥ ትልም የሆነ የሰው ልጅ ምንኛ ያንስ*!

የሰው ልጅ የሚመስል የሚባለው ኢየሱስ ነው ብንል እንኳን ኢየሱስ የሚመስለው አለ የሰው ልጅ የሚመስል ተብሏልና፤ ሰውን ይመስላል፤ ነገር ግን ነገር ግን ያ የሚመለከው አንዱ አምላክ የሚመስለው አለን? የለም፦
ኢዮብ 23:13 *እርሱ ግን ብቻውን ነው፤ እርሱንስ የሚመስለው ማን ነው?*

ነጥብ ሶስት
“ይገዙለት”
“ይገዙለት” ተብሎ በግሪክ ሰፕቱጀንት”LXX” ላይ የሰፈረው ቃል “ዱልኦስ” δοῦλος ነው፦
ዳንኤል 7፥14 ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ “ይገዙለት” δουλεύσουσιν ዘንድ ግዛትና ክብር መንግሥትም “ተሰጠው”፤ ግዛቱም የማያልፍ የዘላለም ግዛት ነው፥ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው።

“ይገዙለት” ተብሎ መገዛት የተገባው የሰው ልጅ የሚስመለው የልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ እንደሆነ ዐውዱ ላይ ፍንትውና ቁልጭ ብሎ ተቀምጧል፦
ዳንኤል 7፥27 መንግሥትም ግዛትም ከሰማይም ሁሉ በታች ያሉ የመንግሥታት ታላቅነት “ለልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ” ይሰጣል፤ መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ነው፥ ግዛቶችም ሁሉ “ይገዙለታል* δουλεύσουσι ይታዘዙለትማል።

አይ የሰው ልጅ የሚመስል የተባለው ኢየሱስ ነው፤ “ይገዙለት” ማለት “ያመልኩት” ዘንድ ማለት ነው ብላችሁ ከፈሰራችሁት የማትወጡት ገደል ውስጥ ትገባላችሁ፤ እንግዲያውስ የሚመለኩ አበዛዛቸው፦
ኢየሩሳሌም፦
ኢሳይያስ 60:12 ለአንቺም “የማይገዛ” δουλεύσουσί ሕዝብና መንግሥት ይጠፋል፥ እነዚያ አሕዛብም ፈጽመው ይጠፋሉ።

ያዕቆብ፦
ዘፍጥረት 25፥23 እግዚአብሔርም አላት፦ ሁለት ወገኖች በማኅፀንሽ ናቸው፥ ሁለቱም ሕዝብ ከሆድሽ ይከፈላሉ፤ ሕዝብም ከሕዝብ ይበረታል፤ ታላቁም ለታናሹ “ይገዛል” δουλεύσει ።
ዘፍጥረት 27፥29 አሕዛብ “ይገዙልህ” δουλευσάτωσάν ሕዝብም ይስገዱልህ፤
ሮሜ 8፥12 ለእርስዋ፦ ታላቁ ለታናሹ “ይገዛል” δουλεύσει ተባለላት።

“እርስ በእርስ”፦
ገላትያ 5፥13 ነገር ግን በፍቅር እርስ በእርሳችሁ “አገልግሉ” δουλεύετε ። KJV

ልብ አድርጉ ሁሉም ጋር መገዛት ተብሎ በግሪኩ ኮይኔ የቀረቡት ቃላት አንድ አይነት ነው።

በተለይ የክርስትና የዐቂዳህ መጽሐፍ የሆነው ሃይማኖተ-አበው ስጋ ፍጡር ነው ይሉን እና ተመልሰው አምላክ ነው ይላሉ፦
ሃይማኖተ-አበው ዘመጠሊጎን 44፥3
ዘመጠሊጎን አለ፦ “ወለሊሁ ሐነፀ ሥጋሁ ውስጠ ከርሠ ድንግል ወኢተሳተፎ መኑሂ በፈጢረ ሥጋሁ አላ ለሊሁ ባሕቲቱ ፈጠሮ”
ትርጉም፦ ” እርሱ ሥጋውን በድንግል ማሕፀን ፈጠረ፤ ሥጋውን በመፍጠር ማንም አጋዥ አልሆነውም፤ እርሱ እራሱ ፈጠረው እንጂ”
ሃይማኖተ-አበው ዘቄርሎስ 78፥31
ቄርሎስም አለ፦ “ወዓዲ ንቤ እስመ ሥጋሁ ለእግዚእነ ክርስቶስ አምላክ ውእቱ”
ትርጉም፦ ” ዳግመኛ የጌታችን የክርስቶስ ስጋ አምላክ እንደሆነ እንናገራለን”

ይህንን ህሊና ይቀበለዋል? ስጋው ምግብ ሲበላ የሚበላው ምግብ ሰውነት ሲሆን ይመለካልን? ሲከሳ ወይም ያ ምግብ ከሰውነት ሲወጣ አይመለክምን? ደሙ ስጋ ውስጥ እያለ የሚመለክ ሲፈስ የማይመለክ ነውን? ይህንን ውስብስብ ትምህርት እንኳን ልታስረዱን ይቅርና ለራሳችሁ አልገባችሁም። ኢየሱስ መመለክ የሚገባው እርሱ ሳይሆን የእርሱ አምላክ እንደሆነ በግልፅ ተናግሯል፦
ማቴዎስ 4፥10 ያን ጊዜ ኢየሱስ፦ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ *እርሱንም ብቻ አምልክ* λατρεύσεις ተብሎ ተጽፎአልና አለው።

አንድ ነጠላ ማንነት”person” ብቻ የሚመለክ መሆኑን ለማሳየት “እርሱ” የሚለው ነጠላ ተሳቢ-ተውላጠ ስም እና “ብቻ” በሚል ገላጭ”adjective” የሚመለከው ለኢየሱስ ንግስና የሰጠው ጌታ አምላክ ብቻ መሆኑን ያሳያል፤ ይህ ጌታም አምላክ አንድ ጌታ ነው፤ ይህ አንድ ጌታ ለእስራላልውያን የመረጠውን ኢየሱስን የላከ ነው፦
ሉቃስ 1፥32 እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ *ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል*፤
ማርቆስ 12፥29 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ፦ እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ *ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው*፥
ሐዋ ሥራ 3፥20 እንግዲህ *ከጌታ ፊት* የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ *የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ*፥ ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ጥንታዊ ስም አሏህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

20፥14 *«እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና አምልከኝ*፡፡ ሶላትንም በእርሷ እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡ إِنَّنِىٓ أَنَا ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدْنِى وَأَقِمِ ٱلصَّلَوٰةَ لِذِكْرِىٓ

“አሏህ” ٱللَّه የሚለው ስም 2699 ጊዜ በቁርአን የመጣ ሲሆን ትርጉሙ “የሚመለክ” ወይም “አምልኮ የሚገባው” ማለት ነው፦
Lane’s Arabic-English Lexicon by Edward William Lane (London: Willams & Norgate 1863)
አላህ ኢስሙል ዛት ማለትም የህላዌው ስም ነው፥ አምላካችን አላህ ጥንትም ሙሳን ሲያናግር የነበረው የሙሳ አምላክ አላህ እራሱ ነው፤ አላህ ለሙሳ፦ “እኔ አላህ እኔ ነኝ፥ ያለ እኔ አምላክ የለምና አምልከኝ” ብሎታል፦
20፥14 *«እኔ አላህ እኔ ነኝ፥ ያለ እኔ አምላክ የለምና አምልከኝ*፡፡ ሶላትንም በእርሷ እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡ إِنَّنِىٓ أَنَا ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدْنِى وَأَقِمِ ٱلصَّلَوٰةَ لِذِكْرِىٓ

አላህ ለሙሳ፦ “እኔ አላህ እኔ ነኝ፥ ያለ እኔ አምላክ የለምና አምልከኝ” ብሎ ከማለቱ በፊት «ሙሳ ሆይ» በማለት ጠርቶታል፦
20፥11 በመጣም ጊዜ «ሙሳ ሆይ» በማለት *”ተጠራ*፡፡ فَلَمَّآ أَتَىٰهَا نُودِىَ يَٰمُوسَىٰٓ

ይህንን ጥሪ ጠርቶ ያነጋገረው እራሱ እንደሆነ በመጀመሪያ መደብ ለነቢያችን”ﷺ”፦ “ጠራነው፥ ያነጋገርነውም ሲኾን አቀረብነው” በማለት ሙሴን የጠራው እርሱ እንደሆነ ይናገራል፦
19፥51 በመጽሐፉ ውስጥ *ሙሳንም አውሳ*፡፡ እርሱ ምርጥ ነበርና፡፡ መልክተኛ ነቢይም ነበር፡፡ وَٱذْكُرْ فِى ٱلْكِتَٰبِ مُوسَىٰٓ ۚ إِنَّهُۥ كَانَ مُخْلَصًۭا وَكَانَ رَسُولًۭا نَّبِيًّۭا
19፥52 ከጡር ቀኝ ጎን በኩልም *ጠራነው፥ ያነጋገርነውም* ሲኾን አቀረብነው፡፡ وَنَٰدَيْنَٰهُ مِن جَانِبِ ٱلطُّورِ ٱلْأَيْمَنِ وَقَرَّبْنَٰهُ نَجِيًّۭا

አምላካችን አላህ ለሙሳ "አላህ" ነኝ ብሎ እራሱ ማስተዋወቁ ካየን ዘንድ ለሙሳ እና ከእርሱ በኃላ ላሉት ነቢያት ያወረደው ወሕይ ሥረ-መሠረቱ በዘመናችን ስለሌለ በትክክል አሁን በአህሉል ኪታብ እጅ ያሉት ጋር አላህ የሚለውን ስም በግልጽ ማግኘት አልተቻለም። ነገር ግን "አላህ" የሚለውን ስም በእነርሱ ቅሪት ውስጥ ስለመኖሩ ፍንጭ የሚሰጡ አናቅጽ በፓሌዎ ዕብራይስጥ አነባነብ አለ። ፓሌዎ ዕብራይስጥ ማለት ከማሶሬት ዕብራይስጥ በፊት የነበረ እና ነቢያቱ ሲጠቀሙበት የነበረ ዕብራይስጥ ነው። ማሶሬት የሚባለው እደ-ክታብ በ 875 ድኅረ-ልደት"AD" ከመዘጋጀቱ በፊት ማሶሬት የሚባሉ የአይሁድ ግሩፕ ዕብራይስጥን ከዐረማይክ ጋር እየደባለቁ የጥንቱን የፓሌዎ ዕብራይስጥ በርዘውታል። "ማሶሬት" מֶסֹרֶת ማለት ቋንቋዊ ፍቺው "እስራት" ማለት ሲሆን ሃይማኖታዊ ፍቺው "ትውፊት" ማለት ነው።

በፓሌዎ ዕብራይስጥ "አ-ለ-ሀ" אלוה "አሌፍ-ላሜድ-ሃ" ነው።
"አሌፍ" א ሲነበብ "አ" እንጂ "ኤ" አይደለም።
"ላ" לו ሲነበብ "ላ" እንጂ "ሎ" አይደለም።
"ሀ" ה ሲነበብ "ሀ" ነው ግን የመጨረሻ ፊደል ላይ በሳድስ "ህ" ተብሎ ይሰክናል።
በፓሌዎ ዕብራይስጥ ሲነበብ "አ-ላ-ህ" ይሆናል።
በፓሌዎ ዕብራይስጥ ውስጥ "ኤ" የምትባል ኃምስ እና "ኦ" የምትባል ሳብዕ አናባቢ የለም። ስለዚህ "ኤ" እና "ሎ" የሚባለውም የማሶሬት ጭማሬ ነው።
ግዕዝ ሰባት አናባቢ አሉት፥ እነርሱም፦
ግእዝ "አ" ካዕብ "ኡ" ሣልስ "ኢ" ራብዕ "ኣ" ኃምስ "ኤ" ሳድስ "እ" እና ሳብዕ "ኦ" ናቸው።

በፓሌዎ ዕብራይስጥ ግን የዘር መነሻ ግእዝ "አ" ነው። የዘር ግንድ ራብዕ "ኣ" ነው። የዘር መዳረሻ ሳድስ "እ" ነው።
ይህንን ከተረዳን "አላህ" אלוה የሚለው ቃል በዕብራይስጡ ባይብል ውስጥ በቅሪት አለ፦
ኢዮብ 3፥4 ያ ቀን ጨለማ ይሁን፤ "አላህ" אֱל֣וֹהַּ ከላይ አይመልከተው፥ ብርሃንም አይብራበት።
ኢዮብ 5 ፥17 እነሆ፥ "አላህ" אֱל֣וֹהַּ የሚገሥጸው ሰው ምስጉን ነው፤ ስለዚህ ሁሉን የሚችለውን የአምላክን ተግሣጽ አትናቅ።
መዝሙር 139፥19 "አላህ" אֱל֣וֹהַּ ሆይ! አንተ ኃጢአተኞችን የምትገድል ከሆንህስ፥ የደም ሰዎች ሆይ፥ ከእኔ ፈቀቅ በሉ።
ታዲያ "አላህ" እኮ ማዕረግ ሆኖ እንጂ ስም ሆኖ አልመጣም የሚሉ ተከራካሪዎች አይጠፉም። ይህንን ለመረዳት ቅድሚያ ስለ ስም እንረዳ፦
ኤርምያስ 51፥57 መሳፍንቶችዋንና ጥበበኞችዋንም፥ አለቆችዋንና ሹማምቶችዋን ኃያላኖችዋንም አሰክራለሁ፥ ለዘላለምም አንቀላፍተው አይነቁም፥ ይላል *"ስሙ የሠራዊት ያህዌህ"* የተባለው ንጉሥ። וְהִשְׁכַּרְתִּי שָׂרֶיהָ וַחֲכָמֶיהָ פַּחוֹתֶיהָ וּסְגָנֶיהָ, וְגִבּוֹרֶיהָ, וְיָשְׁנוּ שְׁנַת-עוֹלָם, וְלֹא יָקִיצוּ: נְאֻם-הַמֶּלֶךְ--יְהוָה צְבָאוֹת, שְׁמוֹ.

እዚህ አንቀጽ ላይ "ያህዌህ ጸባዖት ሴሙ" אֱלֹהֵי-צְבָאוֹת, שְׁמוֹ ማለት "ስሙ የሠራዊት ያህዌህ ነው" ተብሏል። በተመሳሳይ ሰዋሰው "አላህ ጸባዖት ሴሙ" אֱלֹהֵי-צְבָאוֹת, שְׁמוֹ ማለት "ስሙ የሠራዊት አላህ ነው" ተብሏል፦
አሞጽ 5፥27 ስለዚህ ከደማስቆ ወደዚያ አስማርካችኋለሁ፥ ይላል ያህዌህ *"ስሙ የሠራዊት አላህ ነው"*። וְהִגְלֵיתִי אֶתְכֶם, מֵהָלְאָה לְדַמָּשֶׂק: אָמַר יְהוָה אֱלֹהֵי-צְבָאוֹת, שְׁמוֹ

"የሰራዊት አላህ" የሚለው "የሰራዊት ያህዌህ" በሚለው ተለዋዋጭ ሆኖ መጥቷል። ብሉይ ኪዳን ለመበረዝ ተጠያቂዎቹ የማሶሬት ቡድን ናቸው። "አሏህ" በዕብራይስ ቁርኣን ላይ “ላሜድን” ל ተሽዲድ ስናደርገው “አሏህ” אללה‌‎ ሲሆን ከውስጡ ሁለት “ላሜድ” ל ነው፥ አንዱን ላሜድ ማሶሬቶች ቀንሰው "አላህ" אלוה አድርገው ከዚያም ሲያነቡ አጣመው "ኤሎሃ" ብለው አዛብተውታል። አሏህ የሚለው ስም ነቢያችን"ﷺ" ነብይ ሆነ ከመላካቸው በፊትና ቁርኣን ከመውረዱ በፊት በሴመቲክ ዳራ ደግሞ ከሁሉ በላይ የሆነው አንዱ አምላክ ሲጠራበት የነበረ ስም እንደነበር የተለያየ መድብለ-ዕውቀቶች"Encycolopedias" ሆኑ ታሪካዊ ፍሰቶች ያትታሉ፦
1. የሃይማኖት መድብለ-ዕውቀት 1987: “አላህ የሚለው ስም ስረ-መሰረት የጋራ በሆኑ በተለያዩ ጥንታዊ የሴም ቋንቋዎች ይገኛል” ገጽ 27.
Encycolopedia of religion 1987: “the orgin of Allah is found in a root common to various ancient semetic languages” p27.
2. የክርስትና መድብለ-ዕውቀት 2001: “ ቅድመ-ቁርኣን ዐረብ ተናጋሪ ክርስቲያንና አይሁድ እንዲሁ አላህ ለታላቁ አምላክ ይጠቀሙበት ነበር” ገጽ 101.
Encyclopedia of Christianity 2001: “before Quran Arabic-speaking Christians and Jews also refer to supreme God as Allāh” page 101.
3. የኢሥላም መድብለ-ዕውቀት 1913: “ዐረቦች ቅድመ-ነቢዩ ሙሃመድ በነበሩት ዘመናት አላህ የሚባል ታላቅ አምላክ ያመልኩ ነበር” ገጽ 302.
Encyclopedia of Islam 1913: “Before prophet Muhammad Arabian was worshiping supreme God who is Allah” page 302.
4. የብሪታኒካ መድብለ-ዕውቀት 1996: “ቅድመ-ቁርኣን በነበሩት ዐረቢያን መጽሐፍት ውስጥ አላህ የሚለው ቃል ይገኛል” ገጽ 106.
Encyclopedia of britannica 1996: “Before Quran The word Allah was in the Arabic books” page 106.

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ያህዌህ እና መሢሑ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

5፥75 የመርየም ልጅ አልመሲሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُل

“አል-መሢሕ” الْمَسِيح የሚለው የዐረቢኛው ቃል “መሠሓ” مسح ማለትም “አበሰ” አሸ” “ቀባ” ከሚል ሥርወ-ግንድ የተገኘ ሲሆን “የቀባ” አሊያም “የተቀባ” ወይንም “የሚያብስ” አሊያም “የታበሰ” ወይንም “የሚያሽ” አሊያም “የሚታሽ” የሚል ፍቺ አለው፤ ዒሣ ኢብኑ መርየም በሽተኞችን፣ ህሙማንን እና ሙታንን በማበስ፣ በማሸት እና በመቀባት ከበሽታቸው በአላህ ፈቃድ ያሽራቸው ስለነበረ እና በአላህ የተሾመ(የተቀባ) ነቢይ ስለሆነ “አል-መሢሕ” ተብሏል። አምላካችን አላህ በተከበረው ቃሉ በዘጠኝ አንቀፆች 11 ጊዜ ኢየሱስ መሢሕ መሆኑን ነግሮናል። ይህ መሢሕ አስተምረው ካለፉት መልእክተኞች አንዱ የአላህ ባሪያ ነው፦
5፥75 የመርየም ልጅ አልመሲሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُل
4፥172 *"አልመሲሕ ለአላህ ባሪያ ከመኾን ፈጽሞ አይጠየፍም"*፡፡ لَّن يَسْتَنكِفَ الْمَسِيحُ أَن يَكُونَ عَبْدًا لِّلَّهِ

"መሺአሕ" מָשִׁיחַ‎ የሚለው የዕብራይስጥ ቃል "መሸሕ" מָשַׁח ማለትም "ቀባ" "አሸ" "ዳሰሰ" ከሚል ስርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "የተቀባ"anointed one" ማለት ነው። ይህም ቃል በብሉይ ኪዳን ላይ ለተለያየ ካህን፣ ንጉሥ እና ነቢይ አገልግሎት ላይ ውሏል። ነገር ግን ቃል የተገባለት መሢሕ በትንቢት የተነገረለት ንጉሥና ነቢይ ነው፦
ዘፍጥረት 49፥10 በትረ መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም፥ የገዥም ዘንግ ከእግሮቹ መካከል፥ *"ገዥ የሆነው እስኪመጣ ድረስ"*፤ የአሕዛብ መታዘዝም ለእርሱ ይሆናል።

"ገዥ የሆነው እስኪመጣ ድረስ" የሚለው ይሰመርበት። "ገዢ" ተብሎ የተቀመጠው የዕብራይስጥ ቃል "ሺሎሕ" שִׁיל֔וֹ ሲሆን "ሕጋዊ መብት ያለው ገዢ" ማለት ነው። ይህ ወደፊት የሚመጣው መሢሕ ከአንዱ አምላክ ከያህዌህ በማንነት ሆነ በምንነት ይለያል፦
ዘዳግም 6፥4 እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ *አምላካችን ያህዌህ አንድ ያህዌህ ነው*። שְׁמַע, יִשְׂרָאֵל: יְהוָה אֱלֹהֵינוּ, יְהוָה אֶחָד.
መዝሙር 2፥2 የምድር ነገሥታት ተነሡ፥ አለቆችም *”በያህዌህ” יְהֹוָה እና "በመሢሑ" ላይ እንዲህ ሲሉ ተማከሩ”*።

ያህዌህ አንድ ነው፥ በያህዌህ እና በመሢሑ መካከል "እና" የሚለው መስተጻምር መግባቱ በራሱ ያህዌህ እና መሢሑ ሁለት ማንነትና ምንነት መሆናቸውን ቁልጭ እና ፍንትው አድርጎ ያሳያል፥ የሚመጣው መሢሑ ያህዌህ ሳይሆን የያህዌህ መሢሕ ነው። ያህዌህ ቀቢ መሢሑ ተቀቢ ነው፥ መሢሑ የያህዌህ ባሪያ ነው፦
ሕዝቅኤል 37፥24 *"ባሪያዬም ዳዊት ንጉሥ ይሆናቸዋል፤ ለሁሉም አንድ እረኛ ይሆንላቸዋል"* ፤ በፍርዴም ይሄዳሉ ትእዛዜንም ይጠብቃሉ ያደርጓትማል።
ሕዝቅኤል 37፥25 አባቶቻችሁም በኖሩበት ለባሪያዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት ምድር ይኖራሉ፤ እነርሱና ልጆቻቸው የልጅ ልጆቻቸውም ለዘላለም ይኖሩባታል፤ *"ባሪያዬም ዳዊት ለዘላለም አለቃ ይሆናቸዋል"*።

"ዳዊድ" דָּוִ֔ד ማለት "የተወደደ"beloved one" ማለት ነው። "ዶውድ" דּוֹדָ֑ ማለትም "ወዳጅ" ለሚለው ቃል ገላጭ ሆኖ እንደሚገባ ሁሉ ከዳዊት ቤት የሚመጣው መሢሕም "ዳዊድ" ተብሏል እንጂ የእሴይ ልጅ ዳዊት ይመጣል ማለት በፍጹም አይደለም። ይህ የተወደደ መሢሕ የያህዌህ ባሪያ ከያህዌህ "እና" በሚል መስተጻምር አሁንም ተለይቷል፦
ሆሴዕ 3፥5 ከዚያም በኋላ የእስራኤል ልጆች ተመልሰው *"አምላካቸውን እግዚአብሔርን እና ንጉሣቸውን ዳዊትን ይፈልጋሉ"*፤ በኋለኛውም ዘመን ፈርተው ወደ እግዚአብሔርና ወደ በረከቱ ይመጣሉ።
ኤርሚያስ 30፥9 *"ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር እና ለማስነሣላቸው ለንጉሣቸው ለዳዊትም ይገዛሉ"* እንጂ ሌሎች አሕዛብ እንደ ገና አይገዙአቸውም።

እንግዲህ በብሉይ የተተነበየለት የሚመጣው መሢሕ "ባሪያ" "አለቃ" "እረኛ" እና "ንጉሥ" እንጂ ፈጣሪ ያህዌህ በፍጹም አይደለም። ይህንን መሢሕ ግን "ፈጣሪ አላህ ነው" ብሎ ማለት ኩፍር ነው፦
5፥72 *"እነዚያ «አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ"*፡፡ لَقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
እውነት ማን ነው?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

31፥30 ይህ *አላህ እርሱ እውነት ከእርሱም ሌላ የሚግገዙት ውሸት በመሆኑ* እና አላህም እርሱ የበላይ ታላቅ በመሆኑ ነው፡፡ ذَٰلِكَ بِأَنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلْحَقُّ وَأَنَّ مَا يَدْعُونَ مِن دُونِهِ ٱلْبَٰطِلُ وَأَنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلْعَلِىُّ ٱلْكَبِيرُ

ሚሽነሪዎች የራሳቸው መጽሐፍ ላይ ስለ ኢየሱስ አምላክነት በቂ መረጃ መስጠት ሲያቅታቸው ወደ ቁርአኑ መጡና፦ "አላህ እውነት ነው፤ ከአላህ ውጪ እውነት የለም፤ ስለዚህ በወንጌል ላይ ደግሞ ኢየሱስ በዮሐንስ 14፥6 "እውነት" ተብሏልና ኢየሱስ አምላክ ነው" የሚል ስሙር ሙግት ያቀርባሉ፤ ይህ ሙግት ውሃ ያነሳል ወይ? እስቲ በአፅንዖትና በአንክሮት ይህንን ሙግት ድባቅ እናስገባው፦

ነጥብ አንድ
"እውነት በቁርአን"
"አል-ሐቅ" الْحَقَّ በቁርአን ከተጠቀሱት የአላህ ስሞች አንዱ ነው፤ "አል" الْ በስም ላይ መነሻ ቅጥያ ሆኖ ሲመጣ “ማዕሪፋህ” معرفة ማለትም “አመልካች መስተአምር”definite article” ብቻ ሳይሆን "እጅግ በጣም" የሚል ትርጉም ይኖረዋል፤ አላህ በእርግጥም "እጅግ በጣም እውነት" ነው፦
31፥30 ይህ *አላህ እርሱ እውነት ከእርሱም ሌላ የሚግገዙት ውሸት በመሆኑ* እና አላህም እርሱ የበላይ ታላቅ በመሆኑ ነው፡፡ ذَٰلِكَ بِأَنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلْحَقُّ وَأَنَّ مَا يَدْعُونَ مِن دُونِهِ ٱلْبَٰطِلُ وَأَنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلْعَلِىُّ ٱلْكَبِيرُ
22፥62 ይህ *አላህ እርሱ እውነት በመሆኑ ከእርሱም ሌላ የሚግገዙት ነገር እርሱ ፍጹም ውሸት በመሆኑ* አላህም እርሱ የሁሉ በላይ ታላቅ በመኾኑ ነው፡፡ ذَٰلِكَ بِأَنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلْحَقُّ وَأَنَّ مَا يَدْعُونَ مِن دُونِهِۦ هُوَ ٱلْبَٰطِلُ وَأَنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلْعَلِىُّ ٱلْكَبِيرُ
6፥62 ከዚያም *እውነተኛ ወደ ኾነው ጌታቸው ወደ አላህ* ይመለሳሉ፡፡ ንቁ! ፍርዱ ለእርሱ ብቻ ነው፡፡ እርሱም ከተቆጣጣሪዎች ሁሉ ይበልጥ ፈጣን ነው፡፡ ثُمَّ رُدُّوٓا۟ إِلَى ٱللَّهِ مَوْلَىٰهُمُ ٱلْحَقِّ ۚ أَلَا لَهُ ٱلْحُكْمُ وَهُوَ أَسْرَعُ ٱلْحَٰسِبِينَ

ከአላህ እውነተኛነት ጋር የሚነጻጸር እውነተኛ ነገር የለም፤ አላህ ፍፁም እውነት ሲሆን ፍጡራን ደግሞ አንጻራዊ እውነተኞች ናቸው፤ በእርግጥም አላህ እውነተኛው ንጉሥ፣ እውነተኛው ጌታ እና እውነተኛው አምላክ ነው፤ ከእርሱ ውጪ እውነተኛው ንጉሥ፣ እውነተኛው ጌታ እና እውነተኛው አምላክ የለም፦
20፥114 *እውነተኛው ንጉሥ* አላህም ከሓዲዎች ከሚሉት ላቀ፡፡ ወደ አንተ መወረዱም ከመፈጸሙ በፊት በማንበብ አትቸኩል፡፡ «ጌታዬ ሆይ! ዕውቀትንም ጨምርልኝ» በል፡፡ فَتَعَٰلَى ٱللَّهُ ٱلْمَلِكُ ٱلْحَقُّ ۗ وَلَا تَعْجَلْ بِٱلْقُرْءَانِ مِن قَبْلِ أَن يُقْضَىٰٓ إِلَيْكَ وَحْيُهُۥ ۖ وَقُل رَّبِّ زِدْنِى عِلْمًۭا
10፥32 እርሱ *እውነተኛ ጌታችሁ* አላህ ነው፡፡ ከእውነትም በኋላ ጥመት እንጂ ሌላ ምን አለ ከእውነት እንዴት ትዞራላችሁ? فَذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمُ ٱلْحَقُّ ۖ فَمَاذَا بَعْدَ ٱلْحَقِّ إِلَّا ٱلضَّلَٰلُ ۖ فَأَنَّىٰ تُصْرَفُونَ
28፥75 ከሕዝቦችም ሁሉ መስካሪን እናወጣለን፡፡ ያን ጊዜ *እውነተኛውም አምላክነት ለአላህ ብቻ መኾኑን ያውቃሉ*፡፡ ይቀጣጥፉት የነበሩትም ከእነርሱ ይጠፋቸዋል፡፡ وَنَزَعْنَا مِن كُلِّ أُمَّةٍۢ شَهِيدًۭا فَقُلْنَا هَاتُوا۟ بُرْهَٰنَكُمْ فَعَلِمُوٓا۟ أَنَّ ٱلْحَقَّ لِلَّهِ وَضَلَّ عَنْهُم مَّا كَانُوا۟ يَفْتَرُونَ

"ሐቅ" حَقَّ የተባሉት በቁርአን እንደየ አውዱ ለቁርአን እና ለመልክተኛው ይጠቀምበታል፤ ቁርአን ሐቅ ተብሏል፦
13፥1 አሊፍ ላም ሚም ራ ይህች አናቅጽ ከመጽሐፉ አንቀጾች ናት፡፡ ያም ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደው *እውነት* ነው፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያምኑም፡፡ الٓمٓر ۚ تِلْكَ ءَايَٰتُ ٱلْكِتَٰبِ ۗ وَٱلَّذِىٓ أُنزِلَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ ٱلْحَقُّ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يُؤْمِنُونَ

ነብያችን”ﷺ” ሐቅ ተብለዋል፦
3፥86 ከእምነታቸው እና *መልክተኛውም እውነት መኾኑን ከመሰከሩ* የተብራሩ አንቀጾችም ከመጡላቸው በኋላ የካዱን ሕዝቦች አላህ እንዴት ያቀናል! አላህ በዳዮችንም ሕዝቦች አያቀናም፡፡ كَيْفَ يَهْدِى ٱللَّهُ قَوْمًۭا كَفَرُوا۟ بَعْدَ إِيمَٰنِهِمْ وَشَهِدُوٓا۟ أَنَّ ٱلرَّسُولَ حَقٌّۭ وَجَآءَهُمُ ٱلْبَيِّنَٰتُ ۚ وَٱللَّهُ لَا يَهْدِى ٱلْقَوْمَ ٱلظَّٰلِمِينَ

"ሷዲቅ" صَادِق የሚለው ቃል "ሐቅ" حَقَّ ለሚለው ተለዋዋጭ ሲሆን "እውነተኛ" ማለት ነው፤ "እውነተኛ" የተባሉት ደግሞ መርየም እና ምእምናንም ጭምር ናቸው።
መርየም፦
5፥75 የመርየም ልጅ አልመሲሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ *እናቱም በጣም እውነተኛ ናት*፡፡ مَّا ٱلْمَسِيحُ ٱبْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌۭ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ ٱلرُّسُلُ وَأُمُّهُۥ صِدِّيقَةٌۭ
ምእምናን፦
49፥15 *ምእምናን* እነዚያ በአላህና በመልእከተኛው ያመኑት ከዚያም ያልተጠራጠሩት በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸውም በአላህ መንገድ የታገሉት ብቻ ናቸው፡፡ *እነዚያ እነሱ እውነተኞቹ ናቸው*፡፡ إِنَّمَا ٱلْمُؤْمِنُونَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ ثُمَّ لَمْ يَرْتَابُوا۟ وَجَٰهَدُوا۟ بِأَمْوَٰلِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ ۚ أُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلصَّٰدِقُونَ

ስለዚህ እውነት ወይም እውነተኛ የተባለ ሁሉ አምላክ ነው ብሎ ማለት ቂልነት ነው፤ "ኢየሱስ እውነት ነው" ከተባለ ነብያችን”ﷺ”፣ መርየም እና ምእምናን በተባሉበት ሒሳብና ስሌት እንጂ አላህ በተባለበት ቀመር አይደለም።
ነጥብ ሁለት
"እውነት በባይብል"
"እውነት" የሚለው ቃል በዕብራይስጥ ብሉይ ኪዳን "ኢመት" אֱמֶת ሲሆን በግሪክ አዲስ ኪዳን ደግሞ "አሌቴስ" ἀληθής ነው፤ ወደ ባይብሉ ከሄድን "እውነት" የፈጣሪ የእጆቹ ሥራ የሆነው የብስ ነው፦
መዝሙር 111፥7 *የእጆቹ ሥራ "እውነት" אֱמֶ֣ת እና ፍርድ ነው*፤
መዝሙር 95፥5 ባሕር የእርሱ ናት እርሱም አደረጋት፥ *የብስንም እጆቹ ሠሩአት*።

የብስ ማለትም ምድር እውነት ስለተባለ አምላክ ነውን? በተጨማሪ ሐናንያን እውነት ተብሏል፦
ነህምያ 7፥2 ወንድሜን አናኒንና የግንቡን አለቃ ሐናንያን በኢየሩሳሌም ላይ ሾምኋቸው፤ *እርሱም "እውነተኛ" אֱמֶ֔ת ከሌሎቹም ይልቅ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበረ*።
ትዕማር እውነት ተብላለች፦
ዘፍጥረት 38፥26 ይሁዳም አወቀ፦ ከእኔ ይልቅ እርስዋ *"እውነተኛ" צָֽדְקָ֣ה ሆነች*፤ ልጄን ሴሎምን አልሰጠኋትምና አለ። ደግሞም አላወቃትም።

አይ የብስ፣ ሐናንያን፣ ትዕማር እውነት የተባሉት በአንጻራዊ ነው ከተባለ ኢየሱስም እውነት የተባለው በአንጻራዊ ነው፤ ምክንያቱም ኢየሱስ የላከው እውነተኛ እንደሆነ ቃለ-ምስክርነቱን ሰጥቷልና፦
ዮሐንስ 7፥28 እንግዲህ ኢየሱስ በመቅደስ ሲያስተምር፦ እኔንም ታውቁኛላችሁ ከወዴትም እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ፤ እኔም በራሴ አልመጣሁም ነገር ግን እናንተ የማታውቁት *የላከኝ "እውነተኛ" ἀληθινὸς ነው*፤
ዮሐንስ 8፥26 ስለ እናንተ የምናገረው የምፈርደውም ብዙ ነገር አለኝ፤ ዳሩ ግን *የላከኝ "እውነተኛ" ἀληθής ነው* እኔም *ከእርሱ የሰማሁትን ይህን ለዓለም እናገራለሁ አላቸው*።

በእርግጥም ኢየሱስ በጴንጤናዊውም በጲላጦስ ዘንድ መልካሙን መታመን ታምኖ የላከው የአንድ አምላክ ታማኝ እና እውነተኛ ምስክር ነው፤ ፍፁም እውነት ለሆነው ለአንዱ አምላክ ሊመሰክር ተልኳል፦
ራእይ 3፥14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ አሜን የሆነው፥ *የታመነውና እውነተኛው ምስክር*፥ በእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ የነበረው እንዲህ ይላል፦
ዮሐንስ 18፥37 እኔ *ለ"እውነት" ἀλήθεια ልመሰክር ስለዚህ ተወልጃለሁ* ስለዚህም ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ *ከእውነት የሆነ ሁሉ ድምፄን ይሰማል* አለው።
1 ጢሞቴዎስ 6፥13 ሁሉን በሕይወት በሚጠብቅ በእግዚአብሔር ፊት፥ *በጴንጤናዊውም በጲላጦስ ዘንድ መልካሙን መታመን በመሰከረ* በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት አዝሃለሁ፤

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የሚያደርጉትን አያውቁምና

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

ኢማም ሙስሊም : መጽሐፍ 19, ሐዲስ 4417
አነሥ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ”
በሑድ ጦርነት የፊት ጥርሳቸው ተሰበረ፣ እራሳቸው ቆሰለ፤ ደም ከፊታቸው ይጠርጉ ነበር፤ እንዲህ አሉ፦ “ያ ህዝብ እንዴት ሊድን ይችላል ነብዩን እያቆሰለ እና ጥርሱን እየሰበረ ወደ አላህ ይፀልይለታል? በዚያን ጊዜ የላቀው እና ክቡሩ አላህ፦ 3፥128 “አላህ በእነርሱ ላይ ይቅርታ እስኪያደርግ ወይም እነርሱ በዳዮች ናቸውና እስኪቀጣቸው ድረስ ለአንተ ከነገሩ ምንም የለህም” የሚለውን አንቀጽ አወረደ። عَنْ أَنَسٍ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم كُسِرَتْ رَبَاعِيَتُهُ يَوْمَ أُحُدٍ وَشُجَّ فِي رَأْسِهِ فَجَعَلَ يَسْلُتُ الدَّمَ عَنْهُ وَيَقُولُ ‏”‏ كَيْفَ يُفْلِحُ قَوْمٌ شَجُّوا نَبِيَّهُمْ وَكَسَرُوا رَبَاعِيَتَهُ وَهُوَ يَدْعُوهُمْ إِلَى اللَّهِ ‏”‏ ‏.‏ فَأَنْزَلَ اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ ‏{‏ لَيْسَ لَكَ مِنَ الأَمْرِ شَىْءٌ‏}‏

ነብያችን”ﷺ” የጸለዩት ጸሎት ደግሞ ምን እንደሆነ ዐብደላህ ከእርሳቸው የሰማውን በሦስተኛ መደብ በሚቀጥለው ቁጥር እንዲህ ይነግረናል፦
ኢማም ሙስሊም : መጽሐፍ 19, ሐዲስ 4418
ለእኔ የአላህን መልእክተኛ”ﷺ” ስመለከት ታዩኝ የተናገሩትን ሰማዋቸው፦ ነብይ በህዝቡ ሲደበድቡት፣ ደም ከፊቱ ሲጠርግ፦ “ጌታዬ ሆይ ህዝቦቼን የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅርታ አድርግላቸው” አለ። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ كَأَنِّي أَنْظُرُ إِلَى رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَحْكِي نَبِيًّا مِنَ الأَنْبِيَاءِ ضَرَبَهُ قَوْمُهُ وَهُوَ يَمْسَحُ الدَّمَ عَنْ وَجْهِهِ وَيَقُولُ ‏ “‏ رَبِّ اغْفِرْ لِقَوْمِي فَإِنَّهُمْ لاَ يَعْلَمُونَ ‏”

አንዳንድ ቂል መሃይማን “ጌታዬ ሆይ ህዝቦቼን የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅርታ አድርግላቸው” የሚለውን ከዚህ ጥቅስ ጋር ለማዛመድ ሞክረዋል፦
ሉቃስ 23፥34 ኢየሱስም፦ *አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው* አለ።

የሚያጅበው ግን ይህንን ንግግር እንኳን ኢየሱስ ሊናገረው ይቅርና የሉቃስ ወንጌል ላይ ባሉት የግሪክ እደ-ክታባት ላይ ሽታው የለም። ይህንን የአዲስ ኪዳን ለዘብተኛ ምሁር ዶክተር ሄርማን እና ጽንፈኛ ምሁር ጀምስ ኃይት ተናግረዋል። NIV የግርጌ ማስታወሻ ላይም፦ “Luke 23፥34 some early manuscripts do not have this sentence” በማለት እርማችሁን እንድታወጡ አርድቷችኃል፦
https://youtu.be/eWiY32bb2K8


ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ውሸት ሲጋለጥ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

17፥81 በልም *«እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና፡፡»* وَقُلْ جَآءَ ٱلْحَقُّ وَزَهَقَ ٱلْبَٰطِلُ ۚ إِنَّ ٱلْبَٰطِلَ كَانَ زَهُوقًۭا

ሰው የሚዋሸት ከሁለት ነገር አንጻር ነው፥ አንዱ ባለማወቅ ሲሆን ሁለተኛው ሆን ብሎ ህሊናውን በመሸጥ ነው። እውነት ሲገለጥ ውሸት ይጋለጣል፥ እውነት ሲመጣ ውሸት ሁልጊዜ መቋቋው አይችልም። ውሸት በእውነት ፊት እሳት የነካው ሰም፣ ጸሐይ ያየው ቅቤ፣ ነፋስ የጎበኘው አቧራ ይሆናል። እውነትን በውሸት ላይ ስትጥለው ያፈራርሰዋል፥ ምክንያቱም ውሸትም መነሻም መድረሻም የለውምና እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነው፦
21፥18 በእርግጥ *እውነትን በውሸት ላይ እንጥላለን፡፡ አንጎሉን ያፈርሰዋልም፡፡ ወዲያውም እርሱ ጠፊ ነው፡፡ ለእናንተም ከዚያ ከምትመጥኑት ነገር ብርቱ ቅጣት አላችሁ፤ ወዮላችሁ*፡፡ بَلْ نَقْذِفُ بِٱلْحَقِّ عَلَى ٱلْبَٰطِلِ فَيَدْمَغُهُۥ فَإِذَا هُوَ زَاهِقٌۭ ۚ وَلَكُمُ ٱلْوَيْلُ مِمَّا تَصِفُونَ
34፥49 *«እውነቱ መጣ፤ ውሸትም መነሻም መድረሻም የለውም ተወገደ*» በላቸው፡፡ قُلْ جَآءَ ٱلْحَقُّ وَمَا يُبْدِئُ ٱلْبَٰطِلُ وَمَا يُعِيدُ

ይህንን ውሸት ለማጋለጥ እውነቱን እንግለጥ፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 63 ሐዲስ 75
ኑዐይም ኢብኑ ሐማድ እንደተረከው፤ ዐምር ኢብኑ መይሙን አለ፦ “በዘመነ-ድንቁርና ጊዜ ሴት ዝንጀሮ በብዙ ዝንጀሮዎች ተከባ አየው፤ ሕጋዊ ያልሆነ ተራክቦ አድርጋለች በሚል ምክንያት ሁሉም በድንጋይ ወገሯት፤ እኔም ከእነሱ ጋር ወገርኳት። حَدَّثَنَا نُعَيْمُ بْنُ حَمَّادٍ، حَدَّثَنَا هُشَيْمٌ، عَنْ حُصَيْنٍ، عَنْ عَمْرِو بْنِ مَيْمُونٍ، قَالَ رَأَيْتُ فِي الْجَاهِلِيَّةِ قِرْدَةً اجْتَمَعَ عَلَيْهَا قِرَدَةٌ قَدْ زَنَتْ، فَرَجَمُوهَا فَرَجَمْتُهَا مَعَهُمْ‏.‏

ቀጣፊዎች ይህንን ሐዲስ ይዘው፦ “ነብያችሁ”ﷺ” ዝንጅሮ ወግሯል” እያሉ ይቀጥፋሉ፤ ሲጀመር ይህንን ድርጊት አደረኩኝ እያለ ያለው ዐምር ኢብኑ መይሙን እንጂ ነብያችን”ﷺ” አይደሉም፤ ይህን የተናገሩት ነብያችን”ﷺ” ቢሆኑ ኖሮ ሐዲሱ በግልጽ “ቃለ ነብይ” ወይም “ቃለ ረሱል” ብሎ ይጀምር ነበር፤ የነብያችን”ﷺ ንግግር ሽታው እንኳን እዚህ ሐዲስ ላይ የለም።
ሲቀጥል ዐምር ኢብኑ መይሙን የተናገረው በዘመነ-ድንቁርና ጊዜ ማለትም ቁርአን ከመውረዱ በፊት የነበረውን የጨለማ ጊዜ በአውንታዊ ሳይሆን በአሉታዊ ለመግለፅ ነው።
እውነት ተገለጠ ውሸት ተጋለጠ፤ በልም እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነው፦
17፥81 በልም *«እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና፡፡»* وَقُلْ جَآءَ ٱلْحَقُّ وَزَهَقَ ٱلْبَٰطِلُ ۚ إِنَّ ٱلْبَٰطِلَ كَانَ زَهُوقًۭا

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የእስራኤል ሕዝብ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

3፥78 *ከእነሱም እርሱ ከመጽሐፉ ያይደለ ሲኾን ከመጽሐፉ መኾኑን እንድታስቡ በመጽሐፉ ምላሶቻቸውን የሚያጣምሙ ክፍሎች አሉ፡፡ እርሱ ከአላህ ዘንድ ያልኾነ ሲኾን «እርሱ ከአላህ ዘንድ ነውም» ይላሉ፡፡ እነርሱ የሚያውቁ ሲኾኑም በአላህ ላይ ውሸትን ይናገራሉ*፡፡ وَإِنَّ مِنْهُمْ لَفَرِيقًا يَلْوُونَ أَلْسِنَتَهُم بِالْكِتَابِ لِتَحْسَبُوهُ مِنَ الْكِتَابِ وَمَا هُوَ مِنَ الْكِتَابِ وَيَقُولُونَ هُوَ مِنْ عِندِ اللَّهِ وَمَا هُوَ مِنْ عِندِ اللَّهِ وَيَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ وَهُمْ يَعْلَمُونَ

ኢሳይያስ 53፥1-12 ዐውዱ የሚያወራው ስለ እስራኤል ሕዝብ ሆኖ ሳለ የክርስትናው ዓለም ግን ለኢየሱስ ስቃይ ነው በሚል እንደ ማስረጃ ይጠቀሙበታል። ነገር ግን የጥንት አይሁዳውያን እና የዘመኑ አይሁዳውያን እነዚህ ምዕራፍ "ስለ እስራኤል ሕዝብ የሚናገር ነው" ብለው ክፉኛ ይሞግታሉ። እስቲ ኢሳይያስ 53 ላይ ያሉትን አናቅጽ ጥርስና ምላሱን እየነቀስን እናስተንትን፦

አንቀጽ አንድ
የእግዚአብሔር ክንድ ተገልጦአል፦
ኢሳይያስ 53፥1የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል? *የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገልጦአል?*

የእግዚአብሔር ክንድ በአሕዛብ ሁሉ ፊት ተገልጦአል፦
ኢሳይያስ 52፥10 *"እግዚአብሔር የተቀደሰውን ክንዱን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ገልጦአል"*።

ያህዌህ ጥንት እስራኤላውያንን ከግብፃውያንም ባርነት በተዘረጋ ክንዱ ታድጓቸዋል፦
ዘጸአት6፥6 ስለዚህም ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በላቸው፦ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከግብፃውያንም ባርነት አወጣችኋለሁ፥ ከተገዥነታቸውም አድናችኋለሁ፤ *"በተዘረጋ ክንድ በታላቅ ፍርድም እታደጋችኋለሁ"*።
መዝሙር 77፥15 የያዕቆብንና የዮሴፍን ልጆች፥ *"ሕዝብህን በክንድህ አዳንሃቸው"*።

በተመሳሳይም የእግዚአብሔር ክንድ በአሕዛብ ሁሉ ፊት ተገልጦ ጥንት የእስራኤልን ሕዝብ እንደታደ በምርኮ ያሉትን እስራኤላውያን ይታደጋል፦
ኢሳይያስ 51፥9-10 *የእግዚአብሔር ክንድ ሆይ፥ ተነሥ፥ ተነሥ፥ ኃይልንም ልበስ በቀድሞው ወራትና በጥንቱ ዘመን በነበረው ትውልድ እንደ ሆነው ተነሥ። ረዓብን የቈራረጥህ ዘንዶውንም የወጋህ አንተ አይደለህምን?ባሕሩንና የታላቁን ጥልቅ ውኃ ያደረቅኸው፥ የዳኑትም ይሻገሩ ዘንድ ጠሊቁን ባሕር መንገድ ያደረግህ አንተ አይደለህምን?*
ኤርምያስ 21፥4-5 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ *የባቢሎንን ንጉሥ በቅጥርም ውጭ የከበቡአችሁን ከለዳውያንን የምትወጉበትን በእጃችሁ ያለውን ዕቃ ጦራችሁን እመልሰዋለሁ፥ እነዚያንም ወደዚህች ከተማ ውስጥ እሰበስባቸዋለሁ። እኔም በተዘረጋች እጅና "በብርቱ ክንድ"፥ በቍጣና በመዓት በታላቅም መቅሠፍት እወጋችኋለሁ*።

አንቀጽ ሁለት
እንደ ቡቃያ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል፦
ኢሳይያስ 53፥2 *በፊቱ እንደ ቡቃያ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል። መልክና ውበት የለውም፥ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም*።

ከደረቅ መሬት ከግብጽ እንደ ቡቃያ የበቀለው የእስራኤል ሕዝብ ነው፦
መዝሙር 80፥8-11 *ከግብጽ የወይን ግንድ አመጣህ፤ አሕዛብን አባረርህ እርስዋንም ተከልህ። በፊትዋም ስፍራን አዘጋጀህ፥ ሥሮችዋንም ተከልህ ምድርንም ሞላች። ጥላዋ ተራሮችን ከደነ፥ ጫፎችዋም እንደ እግዚአብሔር ዝግባ ሆኑ። ቅርንጫፎችዋንም እስከ ባሕር፥ ቡቃያዋንም እስከ ወንዙ ዘረጋች*።
ሕዝቅኤል 19፥13 *አሁንም በምድረ በዳ፥ በደረቅና በተጠማች መሬት ተተከለች*።

መልክና ውበት፣ ደም ግባት የለውም፦
ኢሳይያስ 53፥2 *መልክና ውበት የለውም፥ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም*።

የእስራኤል ሕዝብ ግን ፊቱ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ፥ መልኩም ከሰዎች ልጆች ይልቅ ተጐሳቍሎአልና፦
ኢሳይያስ 52፥14 *ፊቱ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ፥ መልኩም ከሰዎች ልጆች ይልቅ ተጐሳቍሎአልና*።
ኤርምያስ 46፥12 አሕዛብ *ጕስቍልናሽን ሰምተዋል*፥ ልቅሶሽም ምድርን ሞልቶአታል።
ሕዝቅኤል 7፥3 *ጕስቍልናሽንም ሁሉ አመጣብሻለሁ*።
ሕዝቅኤል 7፥8 *ጕስቍልናሽንም ሁሉ አመጣብሻለሁ*።
መዝሙር 44፥25 *ነፍሳችን በመሬት ላይ ተጐሳቍላለችና*፥ ሆዳችንም ወደ ምድር ተጣብቃለችና።

መሢሑ ግን በትንቢት ውበቱ ያምራል እንጂ ይጎሳቆላል የሚል አንቀጽ የለም፦
መዝሙር 45፥2 *ውበትህ ከሰው ልጆች ይልቅ ያምራል*፤ ሞገስ በከንፈሮችህ ፈሰሰ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘላለም ባረከህ።
3፤ ኃያል ሆይ፥ *በቍንጅናህና በውበትህ* ሰይፍህን በወገብህ ታጠቅ።

አንቀጽ ሦስት-አምስት
የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፦
ኢሳይያስ 53፥3 *የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም*።

የእስራኤል ሕዝብ ሰዎች የሚንቁት ሕዝብም የሚጠላው ባሪያ ነው፥ ደዌውን እና ቍስሉን ባየ ጊዜ ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ ወደ ንጉሡም ወደ ኢያሪም መልእክተኛን ላከ፤ እርሱ ግን ይፈውሳችሁ ዘንድ፥ ከቊስላችሁም ያድናችሁ ዘንድ አልቻለም፥ ይህ ሕዝብ ከሰውም የተጠላ ነበር፦
ኢሳይያስ 49፥7፤ የእስራኤል ታዳጊ ቅዱሱም፥ እግዚአብሔር፥ *ሰዎች ለሚንቁት ሕዝብም ለሚጠላው* ለገዥዎች ባሪያ እንዲህ ይላል፦ ስለ ታማኙ ስለ እግዚአብሔር ስለ መረጠህም ስለ እስራኤል ቅዱስ ነገሥታት አይተው ይነሣሉ፥ መሳፍንትም አይተው ይሰግዳሉ።
ሆሴዕ 5፥13 ኤፍሬምም *ደዌውን፥ ይሁዳም ቍስሉን* ባየ ጊዜ ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ ወደ ንጉሡም ወደ ኢያሪም መልእክተኛን ላከ፤ እርሱ ግን ይፈውሳችሁ ዘንድ፥ *ከቊስላችሁም ያድናችሁ ዘንድ አልቻለም*።
ኤርምያስ 30፥12 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ *ስብራትህ የማይፈወስ ቍስልህም ክፉ ነው*።
ኤርሚያስ 22፥23 አንቺ በሊባኖስ የምትቀመጪ፥ በዝግባ ዛፍም ውስጥ ጎጆሽን የምትሠሪ ሆይ፥ ምጥ እንደ ያዛት ሴት *"ሕማም በያዘሽ ጊዜ"* እንዴት ታጓሪያለሽ!
ኢሳያስ 60፥15 ከሰውም ማንም እስከማያልፍብሽ ድረስ የተተውሽና *የተጠላሽ ነበርሽ*።

አንቀጽ ስድስት-ሰባት
በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፦
ኢሳይያስ 53፥7 ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ *ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም*።

በሸላቶቹም ፊት ዝም ያለ የባዘነ በግ የእስራኤል ሕዝብ ነው፥ ሸላቶቹም መጀመሪያ የአሦር ንጉሥ በላው፥ በመጨረሻም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር አጥንቱን ቈረጠመው፦
ኤርምያስ 50፥17 *እስራኤል የባዘነ በግ ነው፤ አንበሶች አሳደዱት፤ መጀመሪያ የአሦር ንጉሥ በላው፥ በመጨረሻም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር አጥንቱን ቈረጠመው*።
መዝሙር 44፥22 ስለ አንተ ሁልጊዜም ተገድለናል፥ *እንደሚታረዱም በጎች ሆነናል*።

የእስራኤል ሕዝብ የደረሰበትን መከራ ለማሳየት የተሰጠ ፍካሬአዊ አነጋገር ነው፦
ኤርምያስ 30፥7 ወዮ! ያ ቀን ታላቅ ነውና፥ እርሱንም የሚመስል የለምና፤ *ያ የያዕቆብ መከራ ዘመን ነው*፥ ነገር ግን ከእርሱ ይድናል።
አንቀጽ ስምንት
በግዞት እና በፍርድ ተወሰደ፦
ኢሳይያስ 53፥8 በግዞት እና በፍርድ *"ተወሰደ" ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር "እርሱ" לָֽמוֹ እንደ ተወገደ* ከትውልዱ ማን አስተዋለ?

በሰቆቃ በባቢሎን ከሕያዋን ምድር ከከነዓን ተግዘው ስለ ቀድሞ ሕዝብ ይህኛው ሕዝብ ተመተው እንደተወገዱ ከትውልዱ ማን አስተዋለ? ማንም። "እርሱ" ብለው የተረጎሙት ቃል "ላሞው" לָֽמוֹ ሲሆን ትርጉሙ "እነርሱ" ማለት ነው እንጂ "ሁ" ה֚וּא ማለትም "እርሱ" ማለት አይደለም፦
ኢሳይያስ 48፥21 በምድረ በዳ በኩል *"እነርሱን"* לָ֑מוֹ በመራቸው ጊዜ አልተጠሙም፤ ውኃንም ከዓለቱ ውስጥ አፈለቀላቸው፥ ዓለቱንም ሰነጠቀ ውኃውም ፈሰሰ።
መዝሙር 99፥7 በደመና ዓምድም ተናገራቸው፤ ምስክሩንና የሰጣቸውን ትእዛዝ *"እነርሱን"* לָ֑מוֹ ጠበቁ።

ስለዚህ ዐውዱ ላይ ያለው የህማም ሰው ሕዝብ ነው እንጂ አንድ ግለሰብ አይደለም። "ሉጋህ" לֻקַּ֥ח ማለት "ተወሰደ" ማለት ነው። ከከነዓን ወደ ባቢሎን ተማርኮ መወሰዱን ያሳያል። "ስለ ሕዝቤ ኃጢአት" የሚለው ይሰመርበት። ስለ ቀድሞ ሕዝብ ይህ አዲሱ ሕዝብ ወደ ባቢሎን ተወስዷል፦
ኢሳይያስ 52፥5 *"ሕዝቤ በከንቱ ተወስዶአልና? לֻקַּ֥ח አሁን ከዚህ ምን አለኝ? ይላል እግዚአብሔር"*።

"ተወስዷል" ለሚለው መጠይቅ ግስ የገባው ቃል ልክ ከላይ እንዳለው "ሉጋህ" לֻקַּ֥ח ነው። ይህም በምርኮ መወሰድን ያመለክታል፦
ሕዝቅኤል 17፥12 እነሆ፥ *"የባቢሎን ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፥ ንጉሥዋንና መኳንንቶችዋንም ማረከ፥ ወደ እርሱም ወደ ባቢሎን "ወሰዳቸው" וַיִּקַּ֤ח *።

አንቀጽ ዘጠኝ
ከክፉዎችም ጋር መቃብሩን አደረጉ፦
ኢሳይያስ 53፥9 *ከክፉዎችም ጋር መቃብሩን አደረጉ፥ ከባለጠጎችም ጋር በሞቱ፥ ሆኖም ግፍን አላደረገም ነበር፥ በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም ነበር*።

የእስራኤል ሕዝብ ከክፉዎችም ከባቢሎናውያን ጋር በመቃብር ሆነዋል፥ ይህም መቃብር ምርኮ ነው፦
ሕዝቅኤል 37፥12 ስለዚህ ትንቢት ተናገር እንዲህም በላቸው፦ አዶናይ ያህዌክ እንዲህ ይላል፦ *"ሕዝቤ ሆይ፥ እነሆ፥ መቃብራችሁን እከፍታለሁ፥ ከመቃብራችሁም አወጣችኋለሁ፥ ወደ እስራኤልም ምድር አገባችኋለሁ"*።

ምርኮውን መቃብር እንዳለው እናስተውል፥ ከምርኮ ወደ እስራኤልም ምድር ከሰባ ዓመት በኃላ ገብተዋል።
ግፍን አላደረገም ነበር፥ በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም ነበር፦
ኢሳይያስ 53፥9 *ግፍን አላደረገም ነበር፥ በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም ነበር*።

የእስራኤል ቅሬታ ግፍን አይሠሩም፥ ሐሰትንም አይናገሩም፥ በአፋቸውም ውስጥ ተንኰለኛ ምላስ አይገኝም፦
ሶፎንያስ 3፥13 *የእስራኤል ቅሬታ ኃጢአትን አይሠሩም፥ ሐሰትንም አይናገሩም፥ በአፋቸውም ውስጥ ተንኰለኛ ምላስ አይገኝም*።

አንቀጽ አስር
የእስራኤል ሕዝብ ሕይወቱን ለኃጢአት መስዋዕት አርጎ ሰጥቷል፦
ኢሳይያስ 53፥10 *እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል*።

ከታች፦ "አባቶቻችን ኃጢአትን ሠሩ ዛሬም የሉም፤ እኛም በደላቸውን ተሸከምን" የሚል ቃል አለ፥ ለእውነት መሞት መስዋዕትነት ነው። ጳውሎስ፦ "የእኔ ሕይወት ይሠዋልና" ብሏል፦
2 ጢሞቴዎስ 4፥6 *በመሥዋዕት እንደሚደረግ፥ የእኔ ሕይወት ይሠዋልና*፥ የምሄድበትም ጊዜ ደርሶአል።

የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ ነፍስ ነው፥ ይህ በምርኮ የተሰበረና የተዋረደ ነፍስ መሥዋዕት ነው፦
መዝሙር 51፥17 *የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፥ የተሰበርውንና የተዋረደውን ልብ እግዚአብሔር አይንቅም*።

የእስራኤል ሕዝብ ሕይወቱን በምርኮ መስዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፦
ኢሳይያስ 53፥10 *እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል*።

ዕድሜውም ይረዝማል ማለት "የሕዝቤ ዕድሜ እንደ ዛፍ ዕድሜ ይሆናል" ማለት ነው፥ ዘሩን ያያል ማለት "እነርሱ ከነልጆቻቸው የእግዚአብሔር ቡሩካን ዘር ናቸውና በከንቱ አይደክሙም ለጥፋትም አይወልዱም" ማለት ነው፦
ኢሳይያስ 65፥22-23 ሌላ እንዲቀመጥበት አይሠሩም፥ ሌላም እንዲበላው አይተከሉም፤ *የሕዝቤ ዕድሜ እንደ ዛፍ ዕድሜ ይሆናልና፥ እኔም የመረጥኋቸው በእጃቸው ሥራ ረጅም ዘመን ደስ ይላቸዋልና*። *እነርሱ ከነልጆቻቸው የእግዚአብሔር ቡሩካን ዘር ናቸውና በከንቱ አይደክሙም ለጥፋትም አይወልዱም*።
አንቀጽ አስራ አንድ
ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል፦
ኢሳይያስ 53፥11 *ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል*፥ ደስም ይለዋል።

ያህዌህ የእስራኤል ሕዝብ የቈሰለውን ቁስል በፈወሰ ዕለት ብርሃን ያያል ማለት የጨረቃ ብርሃን እንደ ፀሐይ ብርሃን፥ የፀሐይም ብርሃን እንደ ሰባት ቀን ብርሃን ሰባት እጥፍ ይሆናል ማለት ነው፥ ከምርኮ በኃላ ደስ ይላቸዋል፦
ኢሳይያስ 30፥26 *እግዚአብሔርም የሕዝቡን ስብራት በጠገነ ዕለት፥ መቅሰፍቱ የቈሰለውንም በፈወሰ ዕለት፥ የጨረቃ ብርሃን እንደ ፀሐይ ብርሃን፥ የፀሐይም ብርሃን እንደ ሰባት ቀን ብርሃን ሰባት እጥፍ ይሆናል*።
ኢሳይያስ 9፥3 *ሕዝብን አብዝተሃል፥ ደስታንም ጨምረህላቸዋል፤ በመከር ደስ እንደሚላቸው፥ *ሰዎችም ምርኮን ሲካፈሉ ደስ እንደሚላቸው በፊትህ ደስ ይላቸዋል*።

ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፦
ኢሳይያስ 53፥11 ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ *ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል*።

ባሪያዬ የተባለው የእስራኤል ሕዝብ ነው፥ የሚያጸድቀውም በእውቀት በማስተማር ነው፦
ኢሳይያስ 52፥13 *እነሆ፥ ባሪያዬ በማስተዋል ያደርጋል፤ ይከብራል ከፍ ከፍም ይላል፥ እጅግ ታላቅም ይሆናል*።
ኢሳይያስ 44፥21 *ያዕቆብ ሆይ፥ አንተም እስራኤል፥ ባሪያዬ ነህና ይህን አስብ፤ እኔ ሠርቼሃለሁ አንተም ባሪያዬ ነህ፤ እስራኤል ሆይ፥ በእኔ ዘንድ ያልተረሳ ትሆናለህ*።
ኢሳይያስ 49፥3 እርሱም፦ *"እስራኤል ሆይ፥ አንተ ባሪያዬ ነህ፤ በአንተም እከበራለሁ አለኝ"*።

ኃጢአታቸውን ይሸከማል፦
ኢሳይያስ 53፥11 ኃጢአታቸውን *ይሸከማል* יִסְבֹּֽל ።

"ወአዎኖታም" וַעֲוֺנֹתָ֖ם ማለት "ኃጢአታቸውን" ወይም "በደላቸውን" ማለት ነው። "ይስቦል" יִסְבֹּֽל ማለት "ይሽከማል" ማለት ነው። ይህ ይሸከማል የተባለው ደግሞ የእስራኤል ሕዝብ ነው፦
ሰቆቃው ኤርምያስ 5፥7 *"አባቶቻችን ኃጢአትን ሠሩ ዛሬም የሉም፤ እኛም በደላቸውን ተሸከምን" סָבָֽלְנוּ *።

"ሳባሌኑ" סָבָֽלְנוּ ማለት "ተሸከምን" ማለት ሲሆን ተሸካሚዎቹ በባቢሎን ምርኮ ያሉት ናቸው። "በደላቸውን" ለሚለው ቃል የገባው በተመሳሳይ "ወአዎኖቴም" עֲוֺנֹתֵיהֶ֥ם ነው። ሰቆቃ ማለት ስቃይ ማለት ነው፥ የእስራኤል ቅሬታ የእስራኤልንም ቤት ኃጢአት ተሸክሟል፦
ሕዝቅኤል 4፥4 *"አንተም በግራ ጐድንህ ተኛ የእስራኤልንም ቤት ኃጢአት አኑርባት፤ በምትተኛበትም ቀን ቍጥር ኃጢአታቸውን ትሸከማለህ"*።
4፥5 እኔም የኃጢአታቸውን ዓመታት ለአንተ የቀን ቍጥር እንዲሆንልህ ሦስት መቶ ዘጠና ቀን ሰጥቼሃለሁ፤ *"የእስራኤልንም ቤት ኃጢአት ትሸከማለህ"*።
ኢሳይያስ53፥6 እግዚአብሔርም *"የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ"*።

አንቀጽ አስራ ሁለት
ከኃያላን ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፦
ኢሳይያስ 53፥12 ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ *ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል*።

ኃያላን የተባሉት ከባቢሎን ምርኮ በኃላ የተነሱት ነገሥታት ናቸው፦
ዕዝራ 4፥20 *በኢየሩሳሌምም እጅግ ኃያላን ነገሥታት ነበሩ"*፥ በወንዝም ማዶ ያለውን አገር ሁሉ ይገዙ ነበር፤ ግብርንና ቀረጥን መጥንንም ይቀበሉ ነበር።

በትንቢቱ መሠረት የአምላክ ሕዝብ ከኃያላን ጋር ምርኮን ተከፋፍለዋል፦
ኢሳይያስ 9፥3 ሕዝብን አብዝተሃል፥ ደስታንም ጨምረህላቸዋል፤ በመከር ደስ እንደሚላቸው፥ *ሰዎችም ምርኮን ሲካፈሉ ደስ እንደሚላቸው በፊትህ ደስ ይላቸዋል*።

ስለ ዓመፀኞችም ማለደ፦
ኢሳይያስ 53፥12 ስለ ዓመፀኞችም *”ማለደ”*።

የማለዱት ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ የተበተኑት ናቸው፥ ላስማርክኋችሁ ከተማ ወደ እግዚአብሔር ማልደዋል፦
ሶፎንያስ 3፥10 ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ *የሚማልዱኝ*፥ የተበተኑት ሴቶች ልጆቼ፥ ቍርባኔን ያመጡልኛል።
ኤርምያስ 29፥7 በእርስዋ ሰላም ሰላም ይሆንላችኋልና ወደ እርስዋ ላስማርክኋችሁ ከተማ ሰላምን ፈልጉ፥ *"ስለ እርስዋም ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ"*።

ከላይ ከ 1-12 አናቅጽ ላይ ስለ እስራኤል ሕዝብ ሆኖ ሳለ ነገር ግን የአዲስ ኪዳን እደ-ክታባት አዘጋጆች ለኢየሱስ ስቃይ ትንቢት አድርገው መጠቀማቸው አያስገርምም። ምክንያቱም ይህ የተለመደ የማጣማም ሥራ ነው፥ ለምሳሌ ይህንን ጥቅስ እንመልከት፦
ሆሴዕ 11፥1-2 *እስራኤል ሕፃን በነበረ ጊዜ ወደድሁት፥ ልጄንም ከግብፅ ጠራሁት። አብዝቼ ብጠራቸው አጥብቀው ከፊቴ ራቁ፤ ለበኣሊምም ይሠዉ ነበር፥ ለተቀረጹ ምስሎችም ያጥኑ ነበር*።
ዘጸአት 4፥22 ፈርዖንንም፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ *እስራኤል የበኵር ልጄ ነው"*።

ልብ አድርግ ከግብፅ የተጠራው ልጅ አጥብቆ ከአምላክ ፊት የራቀ፤ ለበኣሊምም ይሠዋ የነበረ፥ ለተቀረጹ ምስሎችም ያጥን የነበረ የእስራኤል ሕዝብ ሆኖ ሳለ ግን የአዲስ ኪዳን እደ-ክታባት አዘጋጆች ለኢየሱስ ትንቢት ነው ይሉናል፦
ማቴዎስ 2፥14-15፤ እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን በሌሊት ያዘና *ከጌታ ዘንድ በነቢይ፦ "ልጄን ከግብፅ ጠራሁት" የተባለው እንዲፈጸም ወደ ግብፅ ሄደ"*፥ ሄሮድስም እስኪሞት ድረስ በዚያ ኖረ።

እውነት ኢየሱስ አጥብቆ ከአምላክ ፊት የራቀ፤ ለበኣሊም ይሠዋ የነበረ፥ ለተቀረጹ ምስሎችም ያጥን የነበረ ነውን? በዚህ ቴኦሎጅን እንዴት ቶኦሎጃይዝ ማድረግ ይቻላል? ይህ እኮ ትንቢት ነው፥ ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም፦
2 ጴጥሮስ 1፥20 ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ *በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም"*።

ብዙዎች ከመጽሐፉ ያይደለ ሲኾን ከመጽሐፉ መኾኑን እንድታስቡ በመጽሐፉ ምላሶቻቸውን የሚያጣምሙ ክፍሎች እንደዚህ አይነቶቹ ናቸው፦
3፥78 *ከእነሱም እርሱ ከመጽሐፉ ያይደለ ሲኾን ከመጽሐፉ መኾኑን እንድታስቡ በመጽሐፉ ምላሶቻቸውን የሚያጣምሙ ክፍሎች አሉ፡፡ እርሱ ከአላህ ዘንድ ያልኾነ ሲኾን «እርሱ ከአላህ ዘንድ ነውም» ይላሉ፡፡ እነርሱ የሚያውቁ ሲኾኑም በአላህ ላይ ውሸትን ይናገራሉ*፡፡ وَإِنَّ مِنْهُمْ لَفَرِيقًا يَلْوُونَ أَلْسِنَتَهُم بِالْكِتَابِ لِتَحْسَبُوهُ مِنَ الْكِتَابِ وَمَا هُوَ مِنَ الْكِتَابِ وَيَقُولُونَ هُوَ مِنْ عِندِ اللَّهِ وَمَا هُوَ مِنْ عِندِ اللَّهِ وَيَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ وَهُمْ يَعْلَمُونَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም