TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" የትግራይ ህዝብ ከሰጠኝ እውቅናና ክብር በላይ የምመኘው የክብርና የምስጋና መድረክ የለም " - አቶ ጌታቸው ረዳ የጠቅላይ ሚንስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ በአዲሱ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) የቀረበላቸው የክብርና የምስጋና የሽኝት መድረክ ውድቅ አደረጉ። አቶ ጌታቸው ረዳ ሚያዝያ 3/2017 ዓ.ም የጠቅላይ ሚንስትሩ የምስራቅ…
" ጌታቸው ላይ መፈንቅለ መንግስት ፈፅሜ ከሆነ በገለልተኛ አካል ይጣራ " - ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ ጀነራል) " አውራ እምባ ታይምስ " ከተባለ ሚድያ ጋር ቃለ መጠይቅ አድርገው ነበር።

በዚህም ወቅት በትግራይ ተካሂደዋል ተብሎ ተደጋግሞ ስለሚነገረው የመፈንቅለ መንግስት ጉዳይ  ተጠይቀው መልሰዋል። 

በቀድሞ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የህወሓት ሃይል ባለፈው  ባወጣው መግለጫ " በትግራይ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት በማካሄድ ስልጣን ከተያዘ 40 ቀናት ተቆጠረዋል " ብሎ ነበር።

ይኸው ኃይል " የአቶ ጌታቸው አስተዳደር ህገ-ወጥ ተግባሩ ተጋግሎ ወደ ተባባሰ ግጭት እንዳያመራ ስልጣን ጭምር ለሰላም ሲል አሳልፎ ሰጥቷል " የሚል አገላለፅም ተጠቅሞ ነበር።

ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) ፥ " ጌታቸው ረዳ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አካል ሆኖ በተቋቋመው ጊዚያዊ አስተዳደር ወደ ኃላፊነት የመጡ ናቸው " ያሉ ሲሆን " ወደ ሃላፊነት መጋቢት 2015 ዓ.ም ነው የመጡት። የጊዚያዊ አስተዳደሩ ቆይታ ሁለት ዓመት መሆኑ ይታወቃል። እንዲያ ሆኖም 6 ወር ሊራዘም ይችላል። ይሁን እንጂ የነበረው ጊዚያዊ አስተዳደር ለ6 ወራት ለማራዘም የሚያስገደድ በቂ ምክንያት አልተገኘም " ብለዋል።

" መጋቢት 2015 ዓ.ም ወደ ሃላፊነት የመጡት አቶ ጌታቸው መጋቢት 2017 ዓ.ም የሁለት ዓመት ቆይታቸውን ጨርሰዋል " ሲሉ አስረድተዋል።

" አሁን የተደረገው በፓርላማ በፀደቀ አዋጅ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ለአንድ ዓመት ማራዘም ነው።  በተራዘመው የጊዚያዊ አስተዳደሩ ዕድሜ የነበረው ፕሬዜዳንት ሊቀጥል ላይቀጥል ይችላል። አጋጣሚ ሆኖ አቶ ጌታቸው በሃላፊነት አልቀጠለም " ሲሉ ገልጸዋል።

" እኔ እንደ አዲስ በተራዘመው ጊዚያዊ አስተዳደር ወደ ሃላፊነት መጥቻለው። በትግራይ የሃላፊነት ጊዜው ጨርሶ ከሃላፊነት የወረደ እንጂ የተካሄደ መፈንቅለ መንግስት የለም። መፈንቅለ መንግስት አልተካሄደም ብቻ ሳይሆን ወደዛ የሚወሰድ ምክንያትም አልነበረም " ብለዋል።

" ያን ያህል ጉዳዩ አሳሳቢ ሆኖ መፈንቅለ መንግስት ተካሂደዋል ? ወይስ አልተካሂደም የሚል ክርክርና እሰጣ ገባ ካለ ለሦስተኛ ወገን እድል እንስጥ። የሚያጣራ አካል ይኑር። ምናልባት እኔ ይህንን ጉዳይ የሚያጣራ አካል ላቋቁም ብል ተአማኒነትና ተቀባይነት ላይኖረው ስለሚችል ሦስተኛ አካል የሆነ ኮሚቴ ቢያጣራው እላለው " ሲሉ መልሰዋል።

" በጌታቸው ላይ መፈንቅለ መንግስት ፈፅሜ ከሆነ በገለልተኛ አካል ይጣራ " ሲሉም አክለዋል።

#Tigray

@tikvahethiopia
🤔18692🕊47😡35👏28😭18🙏12🥰6😢6💔5😱3
TIKVAH-ETHIOPIA
" ከብልጽግና ጋር ልክ እንደሌሎቹ በአገር ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ተባብሮ ለመሥራት ይችላል እንጂ የሚያገናኘው ነገር የለም፤ ገለልተኛ እና ነጻ ፓርቲ ነው " - የቀድሞ የህወሓት አመራር በጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ከህወሓት የተከፈለው ቡድን አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ለማቋቋም በሂደት ላይ መሆኑን ከአመራሮቹ መካከል አንዱ ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት…
#Tigray

" የትግራይ የፖለቲካ ቀውስ ወደ ባሰ ሁኔታ በማምራት አሸናፊና ተሸናፊ ሳይኖረው ትግራይንና ህዝብዋ ወደ ከፋ ሁኔታ እየመራ ነው " ሲል የትግራይ ስቪል ማህበራት ጥምረት ስጋቱ ገለፀ፡፡

ጥምረቱ ባወጣው መግለጫ " የትግራይ የፖለቲካ ምህዳር በመበላሸቱ ምክንያት በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ የሚኖር ትግራዋይ አንደነት ላይ ሳንካ ፈጥሯል " ብሏል።

" በጣም የከፋ ፖለቲካዊና ጠባብ አስተሳሰብ አንሰራፍቷል " በማለት ስጋቱ የገለፀው ጥምረቱ ፣ " አሁንም ሁነኛው መፍትሄ ሁሉን አቀፍ አሳታፊ ውይይት በማካሄድ ልዩነት በሰለጠነ መንገድ መፍታት ነው መፍትሄው " ሲል ገልጿል።

የጋራ መግባባት ላይ እንዲደረስ የሚያግዝና የሚያስችል ብሄራዊ ውይይት በአሰቸኳይ እንዲጀመር  " በድጋሜ ጥሪ አቀርባለሁ " ብሏል።

" በአዲሱ ጊዚያዊ አስተዳደር የተቋቋመው ካቢኔ አቃፊና አሳታፊ አይደለም " ሲል የተቸው ጥምረቱ ፣ " አወቃቀሩ ያለውን ፖለቲካዊ ቀውስ የሚያባብስ በመሆኑ ተዋፅኦው ከአሁኑ መታረም አለበት " ሲል አሳስቧል።

" በነባሩ ጊዚያዊ አስተዳደር የተቋቋመው ጊዚያዊ ምክር ቤት አዲሱ ጊዚያዊ አስተዳደር እንዲያስቀጥለውና ፣ የህዝብንና የአገር በጀት በታለመለት ስራ ላይ እንዲውል የመቆጣጠር ስልጣኑ እንዲወጣ ይፈቅድለት " ብሏል።

የትግራይ ሲቪል ማሕበራት ጥምረት ከ120 በላይ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ማህበራት ያቀፈ ፣ የቆይታ ጊዜው ባጠናቀቀው በፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በተመራው ጊዚያዊ አስተዳደር በተቋቋመው ጊዚያዊ ምክር ቤት ውክልና ያለው መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
249😭71🕊57😢29🙏23😡16🤔12🥰9😱9💔3👏1
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የትግራይ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዜዳንት እና ምክትል ፕሬዜዳንት በጋራ የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ አስገቡ። ስራ መልቀቂያውን ያስገቡት ፤ " በፍትህ እና የዳኝነት ሰርዓቱ ለውጥ ለማምጣት ያሰብናቸው ፣ ያቀድናቸው የጀመርናቸው ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎች ለማሳካት የሚያስችል ሁኔታ ማግኘት ስላልቻልን ነው " ብለዋል። ሰኞ ሰኔ 17/2016 ዓ.ም የተፃፈው የስራ መልቀቅያ ደብዳቤ በበርካታ የማህበራዊ…
#Tigray

የከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዜዳንቱና ምክትላቸው ከሃላፊነታቸው ተሰናበቱ።

የትግራይ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዜዳንት ፀጋይ ብርሃነ ገ/ተኽለ እና ምክትላቸው ገብረኣምላኽ የዕብዮ ከስራ ገበታቸው ተሰናብተዋል።

በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) ፊርማ ግንቦት 5/2017 ዓ.ም የተፃፈው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው ፥ ፕሬዜዳንቱና ምክትላቸው የስራ መልቀቅያ እንዲሰጣቸው  በጠየቁትና ባመለከቱት መሰረት ከምስጋና ጭምር ስንብት ተሰጥቶዋቸዋል።

በዚህም ፕሬዜዳንቱና ምክትላቸው ከዛሬ ግንቦት 6/2017 ዓ.ም ጀምሮ ከስራ መሰናበታቸው የተፃፈላቸው ደብዳቤ ያመለክታል።

ፕሬዜዳንቱ እና ምክትላቸው የቀድሞ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ወደ ስልጣን መምጣታቸው ተከትሎ ወደ ሃላፊነት የመጡ ሲሆን ከአንዴም ሁለቴ ጊዜ ስራ ለመልቀቅ ጠይቀው ሳይሳካላቸው ቀርቷል።

የስራ መልቀቅያ እንዲያስገቡ እንደ ምክንያት ከጠቀሱዋቸው ችግሮች የጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራ አስፈፃሚ አካላት በህግ ልዕልና የሚያሳዩት ያልተገባ ጣልቃ ገብነት መሆኑን ከዚህ ቀደም መግለጻቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃ ማድረጉ ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
276🕊73🤔35🙏32😭27👏21🥰7😢6💔6😡5
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ህወሓትን ከፖለቲካ ፓርቲነት ከሰረዘው በኃላ በማህበራዊ ሚዲያ ተለያዩ ያልተረጋገጡ መረጃዎች እየተዘዋወሩ ይገኛሉ።

ከነዚህ መረጃዎች መካከል " የፌዴራል ፖሊስ በገፍ ወደ ትግራይ እየገባ ነው " በአንዳንዶቹ ገጾች ደግሞ " ሁኔታዎች ጥሩ አይደሉም " የሚሉ ይጠቀሳሉ።

እነዚህ ያልተረጋገጡ መረጃዎች እየተሰራጩ ያሉት የፌዴራል ፖሊስን የድሮ ፎቶዎችን ጭምር በማያያዝ እንደሆነ ለመታዘብ ተችሏል።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል ከህወሓት መሰረዝ በኃላ ምን አዲስ ነገር ተፈጠረ ? ሲል በተለይ በመቐለና አካባቢው ያለውን ሁኔታ ተዘዋውሮ ዳሷል።

በዚህም የህወሓት መሰረዝን ተከትሎ እስከ አሁን ወደ ትግራይ በይፋ በገፍ የገባ የፌደራል ፓሊስ እንደሌለ ገልጿል።

በመቐለ ፣ አክሱም ፣ እንዳስላሰ-ሽረ ከተሞች ያሉ የአውሮፕላን ማረፍያዎች እንደ ቀድሞው በፌደራል ፓሊስ ጥበቃ ስር ናቸው።

ከዚህ ውጭ ግን ምንም አዲስ ነገር ፤ ምንም አዲስ እንቅስቃሴም የለም። እንዲህ ባለ ሁኔታ ነው " የፌዴራል የጸጥታ ኃይል በገፍ እየተባ ነው " ተብሎ የሚወራው።

በሌላ በኩል ፤ ህወሓት እስካሁኗ ሰዓትና ደቂቃ ስለመሰረዙ አስመልክቶ የሰጠው መግለጫ ወይም አስተያየት የለም።

በአጠቃላይ ትናንት ይፋ ከሆነው የመሰረዝ መግለጫ ተከትሎ የተፈጠረ አዲስ ነገር የሌለ ሲሆን የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል በክልሉ ያለውን ሁኔታ እየተከታተል ያቀርባል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
🕊40488🙏77😡34🤔32👏13😢11🥰8😭7💔3
TIKVAH-ETHIOPIA
" እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ እስካሁን የታገስኩት ይበቃኛል " - አቶ ጌታቸው ረዳ በትግራይ ያለው ህገወጥ የወርቅ ንግድ  ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኃላ የጀመረ ሳይሆን በጦርነቱ ጊዜም ሳይቀር ሲሰራ የነበረ እንደሆነ የቀድሞው የጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እና የአሁኑ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ይፋ አደረጉ። አቶ ጌታቸው፤ "ብዙ ሰው የወርቅ ንግድ የፕሪቶሪያ ስምምነት…
#Tigray

" ሚንስትር ጌታቸው ረዳ የፓለቲካ አቋማቸው እንደተጠበቀ ተመልሰው ቢመጡ በቂ ጥበቃ እንደሚደረግላቸው ልናረጋግጥላቸው እንወዳለን " - የትግራይ የሰላምና የፀጥታ ቢሮ

የትግራይ የሰላምና የፀጥታ ቢሮ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ሰሞኑን ፋና ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው የተናገሯቸውን ንግግሮች " ነጭ ውሸት ነው " በሚል ተቃወመ።

ቢሮው ባወጣው መግለጫ " የትግራይ ህዝብ እንኳን በትግሉ አስተዋፅኦ የነበረውን ታጋይ ተኮሶ ለገድል ይቅርና ሊያጠቃ የመጣ የጠላት ወታደር ማርኮ ስርዓት አስተምሮ ምህረት የሚሰጥ ልባም ነው " ብሏል።

በትግራይ ጦርነት ውቅት ጉልህ ሚና የነበራቸው አቶ ጌታቸው ረዳ በጦርነቱ ወቅት አንዳንድ  የወታደር አመራሮች እራሳቸው ብዙ ኪሎ ሜትሮች ርቀው " ወደኃላ ለምን ሸሻችሁ " በሚል ተዋጊዎችን መግደላቸውን ይፋ አድርገው ነበር።

ቢሮው " ሚንስትር አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ የጦር መኮንኖችን ስም የማጥፋትና የመወንጀል ብቃትና ሞራል የለውም " ሲል አብጠልጥሏል።

ሌላው አቶ ጌታቸው አንዳንድ መኮንኖች በግላጭ በተለያዩ የዝርፊያ ተግባራት ላይ መሰማራታቸውን ተናግረው ነበር።

ቢሮው ግን " በጦርነቱ የተቃጠሉና የወደሙ የጦር መሳሪዎች በራሱ ስልጣን ስርዓት ባልተከተለ መንገድ እንዲነሱና እንዲሰረቁ ያዘዘው ራሱ ጌታቸው ነው " ብሏል።

" ጌታቸው ሚድያዎች በመጠቀም ራሱ የፈፀመውን ጀነራሎቻችን እንደሰረቁትና እንደመዘበሩት አድርጎ የሚያወራው የብረታ ብረት ስርቆትና ምዝበራ ዋነኛ አላማው የሰራዊቱን አንድነት መበተን መሆኑ ለማንም ግልፅ ነው " ሲል በመግለጫው አስፍሯል።

አቶ ጌታቸው በክልሉ እያሉ ከታቀደባቸው ግድያም ማምለጥ እንደቻሉ አንስተው ነበር።

ቢሮው " ' የሰራዊት አመራር ሊገድሉኝ አቅደው ለጥቂት ከሞት አመለጥኩኝ ' የሚል በሚድያ የታጀበ ስም የማጥፋት ዘመቻ በስፋት ተስፋፍቷል " ያለ ሲሆን " ይህ ከእውነት የራቀ የፈጠራ ውሸት ነው " ሲል ወድቅ አድርጎታል።

ከዚህ ባለፈ " ጌታቸው አሰላለፉ ቀይሮ ብልፅግና ሆኗል " ያለው የሰላምና ፀጥታ ቢሮው " ፓለቲካዊ አቋሙ እንደተጠበቀ ተመልሶ ቢመጣ በቂ ጥበቃ እንደሚደረግለት ልናረጋግጥለት እንወዳለን " ብሏል።

" በትግራይ ህዝብ ትግል ብዙ ውሸታሞችና ከሃዲዎች ታይተዋል ቢሆንም የጌታቸውን ጥግ አይደርሱም " ሲል ገልጾ " መላው ሰራዊትና የትግራይ ህዝብ የጌታቸው መረጃ ነጭ ውሸት እንዳትደናገሩ " ሲል አሳስቧል።

ቢሮው የፌደራል መንግስትም ይህን መሰል የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የሚፃረር " ስም የማጥፋት ዘመቻ " በማረም የበኩሉ አስተዋፅኦ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።

ከሰሞኑን አቶ ጌታቸው ረዳ በሰጡት ቃል እንደነ ጄነራል ምግበ፣ ኮሎኔል ተወልደ፣ ጄነራል ሃይለስላሴ አይነት አመራሮች በወረቅ ዘረፋ ላይ እንደተሰማሩ ተናግረው ነበር።

በጦርነት ወቅት ሳይቀር ከፍተኛ ዝርፊያ ላይ የነበሩ መኮንኖች እንደነበሩም ይፋ አደርገው ነበር።

ከሻዕቢያ ጋር የሚገናኙ ሰዎችም መኖራቸውን ጨምሮ ሌሎችም በርካታ ያልተሰሙ ጉዳዮችን በይፋ አውጥተው ከፍተኛ መናገሪያ ሆኗል።

አቶ ጌታቸው ረዳ በትግራይ ፖለቲካ እንዲሁም በህወሓት ውስጥ በአመራርነት ትልቅ ስም ያላቸው በትግራይ ጦርነት ወቅትም እስከመጨረሻው የሰላም ስምምነት ከፊት የነበሩ ብዙ ጉዳዮችን እንደሚያውቁ የሚታመንባቸው ፖለቲከኛ ናቸው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
🤔420185😡54👏34🕊31😱12🥰8💔8😭8😢5🙏1
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray

ዛሬ በመቐለ ማእከላይ ፍርድ ቤት ምንድን ነው የተከሰተው ? 

እንስት ዘውዱ ሃፍቱ ከሁለት ዓመት በፊት በግፍ ከተገደሉት ሴቶች አንድዋ ናት።

የሟችዋ ጉዳይ በፓሊስ ተጣርቶ መዝገቡ ወደ ፍርድ ደርሶ ለሁለት ዓመት ያህል ውሳኔ ሳያገኝ በይዋል ይደር ረጅም ጊዜ መውሰዱ የተበዳይዋ ቤተሰብና የፍትህ ፈላጊዎች ሁሉ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል።

ይህ በእንዲህ አንዳለ የመቐለ ማእከላይ ፍርድ ግንቦት 8 ቀን 2017 ዓ/ም ከሰዓት በፊት የመጨረሻው ውሳኔ ለመስጠት ችሎት ይቀመጣል።

ፍርድ ቤቱ በግድያ ወንጀሉ በተጠረጠሩት ላይ የመጨረሻ ያለውን የጥፋተኝነት የቅጣት ውሳኔ ይሰጣል።

ይህንን ተከትሎ ችሎቱ በሚከናወንበት አዳራሽ የነበሩት ብዛት ያላቸው የተጠርጣሪ ወገኖች ጠረጴዛ በመደብደብና የተለያዩ ድምፆች በማሰማት ረብሻ ይጀምራሉ።

ከረብሻ በዘለለ ዳኞቹን " እናንተም  እንደመስሳቹሃለን ፤ ቀናችሁን ጠብቁ " የሚሉ የስድብ ናዳና ዛቻ ያወርዳሉ።

በችሎት አዳራሹ በቂ የሆነ ስርዓት አስከባሪ ባለመኖሩና ዳኞቹ ሁኔታው ከአቅማቸው በላይ እና አስፈሪ በመሆኑ ምክንያት ውሳኔውን ሳይቋጩ ለግንቦት 18/2017 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ስጥተዋል።

የችሎት መድፈር ተግባሩ የማህበራዊ የትስስር ገፅ ሰፊ መነጋገሪ ሆኖዋል።

ጠበቃ ሚኪኤለ ፍስሃ የተባሉ የሟች ጠበቃ " በፍርሃት ስራዬን አላቋርጥም፤ የተበዳይን እንባ ለማበስ ነገም ዛሬም እሰራለሁ " ሲሉ በማህበራዊ ሚድያ የትሰስር ገጻቸው ላይ ሀሳባቸውን አስፍረዋል።

በርካቶች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የህግ ልዕልና እንዲከበር አገልግሎት በሚሰጠው ፍርድ ቤትና ዳኞች ላይ የተፈፀመ ድፍረት በምሬትና በቁጣ ሲያወግዙት ተስተውለዋል።

የመቐለ ማእከላይ ፍ/ቤት በያዝነው ሳምንት ብቻ የእንስት ዘውዱን ጨምሮ 4 በግፍ የተበደሉ ሴቶችን ጉዳይ መመልከቱን የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ከቦታው መረጃውን አድርሷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia 
😡1.71K😭412314😢102💔72🕊43🥰32🤔30👏28😱20🙏7
#Tigray

ሾልኮ የወጣው ሚስጥራዊው ሰነድ ምንድነው ?

" የጊዚያዊ  አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት በመሆናቸው ብቻ ያወቁትን ሚስጥር እሰከ መጨረሻ መጠበቅ ሲገባቸው ለርካሽ ገበያ አቅርበዋል " - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ፅ/ቤት

➡️ " ጥቂት ወንጀለኞችን ለማዳን ሲባል በህዝብ ስም መነገድ ይቁም " - አቶ ጌታቸው ረዳ


የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚንስትር አቶ ጌታቸው ረዳ በቅርቡ  ፋና ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው የተናገሯቸውን ንግግሮች አስመልክቶ የተቃውሞ መግለጫ አውጥተዋል።

በመግለጫው አቶ ጌታቸው ለፋና ቴሌቪዥን የሰጡትን ቃለመጠይቅ " የህግ ልዕልና ለማረጋገጥ ያለመ ሳይሆን የህዝቡን የትግል ታሪክና ቀጣይነት የሚያጎድፍና የሚያጨልም በቂም በቀል የታጨቀ ነው " ሲል ገልፆታል። 

" በስልጣን ቆይታቸው የታዩ ወድቀቶች ሙሉ በሙሉ ወደ ሌላ አካል ሲያላክኩና ከሳሽ ሲሆኑ ሰንብተዋል " ያለው ፅ/ቤቱ " ይህ ወደ ሚድያ ፕሮፓጋዳ የወረደ ሃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው " ብሏል።

የፅ/ቤቱ መግለጫ ፤ አቶ ጌታቸው ህገወጥ የሰዎች ዝውውር አስመልክቶ በብዙ ጥረት ተጠንቶ ወደ እጃቸው የገባ ኮፒ ያልተደረገ ሰነድ በወቅቱ ተጠያቂነት ሳያረጋግጡ ቀርተው አሁን በማህበራዊ ሚድያ እንዲሰራጭ አደርገዋል ሲል ይከሳል።

" ይህ ሃላፊነት የጎደለው ተግባር ሊያጠቋቸው የፈለጓቸው ግለሰቦች ላይ ብቻ  ያነጣጠረ ሳይሆን ፍትህና ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ የሚደረገው እንቅስቃሴ የሚጎዳ በጥናቱ ተሳትፎ የነበራቸውና አካላትና ቤተሰቦቻቸው ጭምር ለአደጋ የሚያጋልጥ የነውር ነውር ነው " ሲል በምሬት ወቅሷል።

" የጊዚያዊ  አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት በመሆናቸው ብቻ ያወቁትን ሚስጥር እንደ አንድ የህዝብ ብሄራዊ ጉዳይ እሰከ መጨረሻ መጠበቅ ሲገባቸው ለርካሽ ገበያ ማቅረባቸው ማንነታቸው ያሳየ ተግባር ነው " ሲል አቶ ጌታቸው ረዳን ወርፉዋቸዋል።

የፕሬዜዳንት ፅ/ቤቱን መግለጫ ተከትለው ወድያውኑ ምላሽ የሰጡት አቶ ጌታቸው ረዳ " የተጠናው ጥናት ተተንተርሶ ወደ እርምጃ እንደማይገባ ስላወቅኩኝ ወደ ሚመለከተው የበላይ አካል መረጃውን ልኬዋለሁ " ብለዋል።

ሚንስትሩ " በጥናት ሰነዱ መሰረት ህጋዊ እርምጃ ሊወሰድባቸው ከሚገባ ተጠያቂዎች እንዳንዶቹ ከአገር ወጥተዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ' ሰው መሸጥ (slave trading in modern parlance  ) ለትግራይ ህዝብ የማይመጥን ወንጀል ነው ' የሚል አገላለፅ በፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት በወጣው መግለጫ የለም " ያሉት አቶ ጌታቸው " ሰነዱ ግለሰቦችን ከማጥቃት ባለፈ የህግ ልዕልና እንዲረጋገጥ ያለመ ነው " ሲሉ አብራርተዋል።  

ሚንስትር አቶ ጌታቸው ረዳ " በጥናት ሰነዱ የተቀመጠው ሃቅ ነው ጥቂት ወንጀለኞች ለማዳን ሲባል በህዝብ ስም መነገድ ይቁም " ብለዋል።

ሚስጥራዊ ሰነዱ ምንድነው ?

ከሰሞኑን አንድ ሚስጥራዊ ሰነድ ሾልኮ ወጥቶ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል። በማህበራዊ ሚዲያዎችም በርካቶች እየተቀባበሉት ይገኛሉ።

ሚስጥራዊ ሰነዱ ፥ የህገወጥ የሰዎች ዝውውር (በብዛት ኤርትራውያን በህገ-ወጥ መንገድ ማዘዋወር የሚመለከት) እና ሌሎችም ጉዳዮች ላይ የተጠና ሰነድ ሲሆን በ4 ክፍሎች የተከፋፈሉ 69 ገፆች አሉት።

በሰነዱ በጥናት የተለዩ የወንጀል ተግባራት ፦
- ስልጣን ያለአግባብ በመጠቀም
- በወንጀል የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ በመያዝና በማዘዋወር (መኒ ላውንደሪንግ)
- ሰው ማፈንና መሰወር
- በህገወጥ መንገድ ሰዎችን ከአገር ወደ አገር ማዘዋወር
- የመንግስት ስራ ምቹ ባልሆነ መንገድ መምራት
- ሃላፊነት ባልተገባ መንገድ በመጠቀም
- ሙስና

መፈፀማቸውን ያረጋግጣል።

በሰነዱ በተጠቀሱ የወንጀል ተግባራት በሰራዊት አመራር ያሉ የነበሩ የጀነራል መዓርግ ካለቸው ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች እስከ ቀበሌ አመራር ያሉ አስተዳዳሪዎች ነጋዴዎችና ሌሎች የሚገኙባቸው 231 ተጠርጣሪዎች በስምና አድራሻቸው ተጠቅሷል።

ሰነዱ በህገ-ወጥ መንገድ የተዘዋወሩ ኤርትራውያን ስም የተዘዋወሩበት ቦታና ቀን ፣ ያረፉባቸው ሆቴሎች እንዲሁም ለህገወጥ ዝውውሩ ገንዘብ ገቢ ያደረጉባቸው የባንክ የሂሳብ ቁጥሮች ሰፍረዋል።

የጥናት ሰነዱ የሰው ማስረጃ ፣ የድምፅ ቅጂ፣ እንዲሁም በድብቅ የተቀረፀ ምስል ያካተተ እንደሆነ ይዘረዝራል።

በሰነዱ በቀንደኛ ተጠርጣሪነት ከተጠቀሱት ከፍተኛ መኮንኖች አንዱ የሆኑት ተወልደ ገ/ትንሳኤ (ዕምበብ) በቅርቡ ከአገር መውጣታቸው ሚንስትር አቶ ጌታቸው ረዳ በቅርቡ ከፋና ቴሌቪዥን በነበራቸው ቆይታ ጠቅሰዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
3😢733411🤔185👏141😡78🕊64😱49🙏49😭40💔31🥰28
#Tigray

" ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ሳይመለሱ በብርድ ንፋስና ዝናብ እየተፈራረቀባቸው ለአምስተኛ ክረምት  በስቃይ  እንዳይከርሙ ሰግተናል " - ሸኽ አደም ዓብደልቃድር

የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዜዳንት ሸኽ አደም ዓብደልቃድር " በትግራይ የሚታዩ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ተባብሰው ቀጥለዋል በዚህ ምክንያትም ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ሳይመለሱ በብርድ ንፋስና ዝናብ እየተፈራረቀባቸው ለአምስተኛ ክረምት  በስቃይ  እንዳይከርሙ ሰግተናል " ሲሉ ተናግረዋል።

ይህ ያሉት ዛሬ እየተከበረ በሚገኘው የ1446ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል የዒድ ሶላት ላይ ነው።

ፕሬዜዳንቱ ፥ መንግስት የተፈናቃዮች ስቃይ እንዲያበቃ ያለመ አመርቂ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ አለመሆኑ ጉዳዩ ተስፋ አስቆራጭ አድርጎታል ሲሉ ነቅፈዋል።

" መንግስት የተፈናቃዮች ችግር ከመፍታት የበለጠ ሌላ አንገብጋቢ ስራ ሊኖረው አይገባም " ያሉት ፕሬዜዳንት ሸኽ አደም " በዓሉ ሲከበር እነዚህ ወገኖች ማሰብ የአላህ ክብር ያጎናፅፋል " ብለዋል።  

ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እስኪመለሱ የሚደረግላቸው እገዛ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አደራ ብለዋል። 

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
764😡73🙏43😢41🕊38🤔5😭4🥰3
TIKVAH-ETHIOPIA
የፕሬዜዳንቱን ፅ/ቤት ጥሰው የገቡት ሰልፈኞች ! " የማይተገበሩ ቃሎች መስማት ሰልችቶናል ፤ ለ5ኛ ክረምት በመጠለያ አንከርምም ወደ ቄያችን መልሱን " ያሉ በትግራይ ጦርነት የተፈናቀሉና መቐለ መጠለያ የሚገኙ ዜጎች ዛሬ ሰልፍ ወጥተው ነበር። ሰልፈኞቹ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ  አስተዳደርና የፌደራል መንግስት ወደ ቄያቸው እንዲመልሱዋቸው ጠይቀዋል። ሰልፈኞቹ ጥያቄያቸው በፅሁፍና በድምፅ ወደ ጊዚያዊ አስተዳደር…
#Tigray

" 1.2 ሚሊዮን ህፃናት ወደ ትምህርት ገበታ አልተመለሱም፤ የጦርነቱ ጦስ ዛሬያችን ብቻ ሳይሆን ነገያችንም እያጨለመው ነው "  - የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ

የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ኪሮስ ጉዑሽ (ዶ/ር) የፕሪቶሪያ ሰላም ስምምነት ሙሉ ሆኖ ባለመተግበሩ 1.2 ሚሊዮን ህፃናት ወደ ትምህርት ገበታ እንዳልተመለሱ ገልጹ።

" የጦርነቱ ጦስ ዛሬያችን ብቻ ሳይሆን ነገያችንም እያጨለመው ነው " ብለዋል።

ኃላፊው ይህንን ያሉት " ይበቃል ! " በሚል መሪ ቃል ተፈናቃዮች ዛሬ በመቐለ ማካሄድ የጀመሩትን ሰላማዊ ሰልፍ በመደገፍ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ነው።

ተፈናቃዮቹ በሁለት ሳምንት ለሦስተኛ ጊዜ ፤ ለሦስት ቀናት የሚዘልቅ ሰላማዊ ሰልፎ ዛሬ ሰኔ 11/2017 ዓ.ም ሮማናት አደባባይ ማካሄድ ጀምረዋል።  
 
" ለ5ኛ ክረምት በመጠለያ መኖር ይብቃ " ያሉ ሲሆን የትግራይ ክልል ቀድሞ ወደነበረበት ቅርጽ ተመልሶ ግዛታዊ አንድነቱ እንዲከበር፣ የተፈናቃዮች ድምፅ እንዲሰማ፣ በተፈናቃዮች ስም የሚሰራው የፓለቲካ ቁማር እንዲቆምና ሌሎችም ጥሪዎች አቅርበዋል።

ሰላማዊ ሰልፉን ያዘጋጀው በተፈናቃዮች የተመሰረተው " ፅላል ማሕበረሰብ ምዕራብ ትግራይ " የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ማህበር እንደሆነ ተነግሯል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
447😢148😭37🕊25😡13🤔12👏11🙏11😱1
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray " 1.2 ሚሊዮን ህፃናት ወደ ትምህርት ገበታ አልተመለሱም፤ የጦርነቱ ጦስ ዛሬያችን ብቻ ሳይሆን ነገያችንም እያጨለመው ነው "  - የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ኪሮስ ጉዑሽ (ዶ/ር) የፕሪቶሪያ ሰላም ስምምነት ሙሉ ሆኖ ባለመተግበሩ 1.2 ሚሊዮን ህፃናት ወደ ትምህርት ገበታ እንዳልተመለሱ ገልጹ። " የጦርነቱ ጦስ ዛሬያችን ብቻ ሳይሆን ነገያችንም እያጨለመው…
#Tigray

" የተደፈረው ግዛትና ተፈናቃዮች በሰላማዊ መንገድ ለመመለስ የሚደረገው ሁሉን አይነት ጥረት ካልተሳካ  ዝም ብሎ የሚተው እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል " - አቶ አማኒኤል አሰፋ

በሺህዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች የተገኙበት ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ የሚጠይቅ " ይበቃል ! " በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ሰላማዊ ሰልፍ በመቐለ ተካሂደዋል።

ዛሬ ሰኔ 13/2017 ዓ.ም ለሦስተኛ ቀን የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ውሳኔ መሰረት የመንግስት ሠራተኞች ስራቸውን በማቆም የታደሙበት ነው። 

በሰልፉ ማጠቃለያ በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ የሚጠይቁ በርካታ መልእክቶች ተደምጠውበታል።

በሰልፉ መልእክት ያስተላለፉት የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት አቶ አማኒኤል አሰፋ " የተደፈረው ግዛትና ተፈናቃዮች በሰላማዊ መንገድ ለመመለስ የሚደረገው ሁሉን አይነት ጥረት ካልተሳካ  ዝም ብሎ የሚተው እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል " ብለዋል።

" ከተፈረመ ሦስት ዓመት ሊሞላ ወራት የቀሩት የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ተኩስ ከማቆም በዘለለ የተፈናቃዮች ደህንነት ማረጋገጥ አቅቶታል " ሲሉ ተደምጠዋል።

" የትግራይ ህዝብ ሉአላዊ ግዛቱ ተቀምቶ ፣ ከቄዩ ተፈናቅሎ ተሰዶ በማያቋርጥ መከራ ተዘፍቆ ይገኛል " ያሉት ምክትል ፕሬዜዳንቱ  " የፌደራል መንግስት በጦርነት ያላሳካው ድል በፕሪቶሪያ ውል ስምምነት ስም የተከፋፈለች ትግራይ እንድትኖር የዲሞግራፊ ለውጥ ለመቀየር እየተጠቀመበት ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

" የፌደራል መንግስት ለሰላም ዋጋ ሰጥቶ እንዲሰራ ደጋሜ ጥሪ እናቀርባለን " ያሉት አቶ አማኒኤል " የምዕራብ ትግራይ ተፈናቃዮች የኩርድ ህዝቦች ዕጣ ፈንታ እንዲደርሳቸው የሚፈቅድ ትክክለኛ ያልሆነ ተግባር መቆም አለበት " ሲሉ ተናግረዋል።

ዛሬ በመቐለ ሮማናት አደባባይ የሦስት ቀናት ማጠቃለያ ሰላማዊ ሰልፍ ፦
- የጊዚያዊ አስተዳደሩ የካቢኔ አባላት
- የሁሉም የሃይማኖት ተቋማት አመራርና ምእመናንና ምእመናት 
- የሚድያ ባለሙያዎች በሺዎች የሚቆጠሩ የመንግስት ሰራተኞች
- ተማሪዎች
- መምህራንና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች መገኘታቸው ተነግሯል።

የፌዴራል መንግሥት ሁሉም ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ ፅና ፍላጎ እንዳለው በተደጋጋሚ መግለጹ አይዘነጋም።

የቀድሞ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳም አሁን ላይ በትግራይ ትርምስ እንዲፈጠር እየሰራ ያለው የህወሓት አንጃ ተፈናቃዮችን ለፖለቲካ ፍጆታ በመጠቀም ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዳይመለሱ እየሰራ መሆኑን አስገንዝበው ነበር።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከትላንት በስቲያ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት የትግራይ ተፈናቃዮችን ጉዳይ አንስተው ነበር።

" የተፈናቀሉ ሰዎች መመለስ በሚመለከት 100% ዝግጁ ነን እኛ  100% ፤ ነበርን ነን ፤ ራያ እኮ መልሰናል ፤ ራያ ተመልሰዋል የተፈናቀሉ ሰዎች ወልቃይትም እንደዛ አይነት ፍላጎት ነው ያለን። ከጊዜያዊ መንግሥቱ ጋር እየተነጋገርን ነው በእኛ በኩል እነኚያ ዜጎች ለፖለቲካ ፍጆታ መጠቀሚያ ሳይሆኑ ቦታቸው ቢመለሱ ከማንም በላይ ኢትዮጵያ ታተርፋለች " ብለዋል።

" በእኛ በኩል አንዴ አይደለም 10 ጊዜ እቅድ ያወጣነው ፤ የትግራይ ጉዳይ ብዙ የማይገደን ፣ የማያሳስበን አይመሳላችሁ " ሲሉ ገልጸዋል።

" ያስጨነቀንን ጉዳይ በግልጽ እንድታውቁት ግን ትንሽ ዘመን ተቀይሯል የዛሬ 4 አመት 5 አመት የነበረን የውጊያ አቅም የነበረን ቴክኖሎጂ እና ዛሬ ትንሽ ይለያያል። በተቻለ መጠን maximum ውጊያ ብናስቀር ይሻላል ለምን ? እንደምታውቁት በባለፈው ውጊያ ያኔም ተናግሪያለሁ ከትግራይ ወጣቶች ከትግራይ እናቶች በላይ የተጎዳ ሰው የለም ፤ የሚያስገድሉ ሰዎች ይፎክራሉ አስገዳዮች ይፎክራሉ ሟቾች ግን ጉዳዩን ሳያውቁ ይጠፋሉ ያ እንዳይፈጠር ነው maximum ትዕግስት የምናደርገው " ብለዋል።

" ትግራይ ውስጥ ሊመጣ የሚገባው ልማት ፤ ሊሰራ የሚገባው ስራ በበቂ ተሰርቷል ብለን አናምንም እንጂ የሚደረጉ ሙከራዎች unconstitutional ልምምዶች እንዳሉ ስለማናውቅ አይደለም በደምብ ነው የምናየው " ሲሉ ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
1K😡103🕊64🤔30😭25😢12🥰11🙏9👏6😱6💔4
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray " የተደፈረው ግዛትና ተፈናቃዮች በሰላማዊ መንገድ ለመመለስ የሚደረገው ሁሉን አይነት ጥረት ካልተሳካ  ዝም ብሎ የሚተው እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል " - አቶ አማኒኤል አሰፋ በሺህዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች የተገኙበት ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ የሚጠይቅ " ይበቃል ! " በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ሰላማዊ ሰልፍ በመቐለ ተካሂደዋል። ዛሬ ሰኔ 13/2017 ዓ.ም ለሦስተኛ ቀን የተካሄደው…
#Tigray : " ከፓለቲካዊና ሰላማዊ ትግል ውጭ ያለው አማራጭ ተገደን እንጂ ፈቀድን የምንገባው እንዳልሆነ የዓለም ማህበረሰብ ሊገነዘበው ይገባል አሉ " የትግራይ ክልል ጊዚያዊ  አስተዳደር ፕሬዜዳንት።

ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) ዛሬ ሰኔ 15/2017 ዓ.ም በትግራይ ደረጃ ለ37ኛ ጊዜ የተከበረው የሰማእታት ቀን በማስመልከት መልእክት አስተላልፈዋል።

ፕሬዜዳንቱ በመልእክታቸው " የትግራይ ህዝብ ምርጫ ሰላም ነው ጦርነት ተገደን እንጂ ወደን የምንገባው እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል " ብለዋል። 

" የትግሉ ሰማእታት በዓመት አንድ ጊዜ የሚታወሱ ሳይሆን የተሰውለት ዓላማ እንዲፈፀም ህዝቡ በሁሉም መስክ ተጠቃሚ በማድረግ ህያው እንዲሆኑ መስራት ይገባል " ብለዋል።

" የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በሙሉነት እንዳይፈፀም በፌደራል መንግስት ያለው ዝቅተኛ ፍላጎት ፣ በትግራይ ፓለቲከኞች መካከል ያለው እርስ በርስ ያለመግባባት ምክንያቶች ናቸው " ሲሉ አክለዋል።

ዛሬ ሰኔ 15/2017 ዓ.ም በመቐለ የሀውልት ሰማእታት በተካሄደው ስነ-ስርዓት ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ(ሌ/ጀነራል)  ፣ የህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ፣ የሰማእታት ቤተሰቦችና ልሎች የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
626😡152🕊60🤔26😢15👏11😭11🙏9🥰5
#Tigray

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር አቶ ኣለም  ገ/ዋህድን በምክትል መአርግ የፕሬዜዳንት የፓለቲካዊ  ጉዳዮች አማካሪ አድርጎ ሾመ።

ሹመቱ በምርጫ ቦርድ የተሻረው ህወሓት በጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ ያለውን ቦታ እጅግ ከፍ አድርጎታል።

በጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ ያለው የተፎኳኳሪ ፓርቲዎች ቦታ ከ3 አይበልጥም።

ከሰኔ 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) በምክትል ፕሬዜዳንት መአርግ የፓለቲካዊ ጉዳዮች አማካሪ ተደርገው የተሾሙት ኣለም  ገ/ዋህድ ፥ ከጦርነቱ በፊት እስከ አምና 2016 ዓ.ም ነሀሴ ተካሂዶ ህገ-ወጥ ነው የተባለው የህወሓት ጉባኤ ድረስ የድርጅቱ የፓለቲካዊ ጉዳዮች ሃላፊ በመሆን ሰርተዋል።

በተጨማሪ ከጦርነቱ በፊትና በኋላ ከ5ቱ የህወሓት የፓሊት ቢሮ አባላት አንዱ በመሆን ሰርተዋል።

በተካሄደው ጉባኤ ደግሞ ከነበሩበት የሃላፊነት ቦታ ወርደው የህወሓት የማእከላይ ኮሚቴ አባል እንዲሆኑ 'የተገፉ' ናቸው ተብሎ ሲነገርባቸው ቆይተዋል።

ከያዝነው ወር ጀምሮ ደግሞ በጊዚያዊ አስተዳደሩ የከፍተኛ የሃላፊነት ቦታ ማግኘታቸውን ተከትሎ የደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት በሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ በሚመራው ካቢኔ ከፍተኛ ቁጥር የያዘ እንዲሆን አስችሎታል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
563😡105🕊36😭16👏14🤔12🙏7🥰6😢5😱4
TIKVAH-ETHIOPIA
" ጦርነት ከተጀመረ ከዚህ በፊት እንደምናቀው አይደለም ነገር ይበላሻል !! " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ በነበረው የህ/ተ/ም/ቤት ጉባኤን አንድ አባል " በትግራይ ክልል ዳግም ጦርንት እንዳይነሳ ስጋት አለ " በማለት በክልሉ ስላለው አሁናዊ የፖለቲካ እና የጸጥታ ሁኔታ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ማብራርያ እና ምላሽ ጠይቀዋል። " ህወሓት ለዳግም ግጭት ቅስቀሳ እያደረገ ነው "  በማለት " ከሰላም…
#Tigray

" በትግራይ በኩል የሚከፈት ጦርነት የለም ፤ ከሌላው ወገን የሚተኮስ ጥይት እንዳይኖር ጥንቃቄ ያሻል " - የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት

" በትግራይ በኩል የሚከፈት ጦርነት የለም ፤ ከሌላው ወገን በተሳሳተ ውሳኔ  ትግራይ የሚተኮስ ጥይት እንዳይኖር ጥንቃቄ ያሻል " ሲሉ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) ተናገሩ።

ፕሬዜዳንቱ " ሁሉም ነገር በሰላማዊ መንገድ ይፈታል ብለን ስለምናምን በትግራይ በኩል የሚጀመር ትንኮሳ እና ጦርነት አይኖርም " ብለዋል። 

" በክልሉ ደቡባዊ ዞን ያለው ችግር የመላው ትግራይ እንጂ የአከባቢው ብቻ አይደለም " ያሉት ፕሬዜዳንት ታደሰ " ጊዚያዊ አስተዳደሩ በዞኑ ካለው አስተዳደር በመነጋገር በሰላማዊ መንገድ ይፈታዋል " ሲሉ ተናግረዋል ።

ራሱን " የትግራይ የሰላም ሃይል " በሎ ከሚጠራውና በዓፋር ክልል ሆኖ የትጥቅ ትግል ከሚያካሂደው ሃይል ጋር ያለውን ችግር " በሰላማዊ ውይይት ይፈታል " ያሉ ሲሆን " ከዚህ ውጪ ያለው አማራጭ ግን ህዝብን ለአደጋ የሚዳርግ ስለሆነ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል " ብለዋል።

" የትግራይ ሉአላዊነት ተደፍሮ ተፈናቃዮችና ስደተኞች ወደ ቄያቸው ባልተመለሱበት ሁኔታ ላይ ተሆኖም ችግሮች በሰላማዊ መንገድ የመንፍታት ጉዳይ አንደኛ አማራጫችን ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

" ተፈናቃዮችና ስደተኞች ወደ ቄያቸው መመለስ  ከሁሉም ስራዎቻችን ቅድምያ የምንሰጠው ነው ጉዳዩ ጊዜ በወሰደ ቁጥር የሰላም በር እንዳያጠብ የፌደራል መንግስት የበኩሉን ሃላፊነት በመወጣት ችግሩ እንዲፈታ ጥሪ እናቀርባለን " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
757🕊139😡22🥰19🤔17👏14💔10🙏9😱6😭3😢1
TIKVAH-ETHIOPIA
" ጦርነት ከተጀመረ ከዚህ በፊት እንደምናቀው አይደለም ነገር ይበላሻል !! " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ በነበረው የህ/ተ/ም/ቤት ጉባኤን አንድ አባል " በትግራይ ክልል ዳግም ጦርንት እንዳይነሳ ስጋት አለ " በማለት በክልሉ ስላለው አሁናዊ የፖለቲካ እና የጸጥታ ሁኔታ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ማብራርያ እና ምላሽ ጠይቀዋል። " ህወሓት ለዳግም ግጭት ቅስቀሳ እያደረገ ነው "  በማለት " ከሰላም…
#Tigray

ከሁሉም የሃይማኖት የቋማት የተወጣጡ እና በሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የተመሩ አባቶች መቐለ ከተማ ይገኛሉ።

የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን ከሁለት ሳምንት በፊት ባካሄደበት ወቅት የተገኙት የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) በትግራይ ክልል ለዳግም ግጭት ቅስቀሳ የሚያደርጉ አካላት ስለመኖራቸው ያመላከተ መላሽ መስጠታቸው ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ለተነሳላቸው ጥያቄ የሰጡት ምላሽ በፌደራሉ መንግስት እና ማንነታቸውን ባልጠቀሷቸው በክልሉ የሚንቀሳቀሱ አካላት መካከል መቃቃር ስለመኖሩ አመላካች ሆኗል።

ለጥያቄው በሰጡት ምላሽም " የሁሉም እምነት አባቶች እዚህ ተወካዮች አላችሁ፣ ሌላ ምንም ስራ የላችሁም በፍጥነት ትግራይ ወደ ግጭት፣ ወደ ጦርነት እንዳይገባ ስራችሁን አሁን ጀምሩ፣ ከተጀመረ ወዲያ ብትናገሩ ዋጋ የለውም " ብለው ነበር።

" ባለሃብቶች፣ ምሁራን፣ ኤምባሲዎች ውጊያ እንዳይጀመር አሁን ሚናችሁን ተወጡ ምክንያቱም ከተጀመረ ከዚህ በፊት እንደምናቀው አይደለም ነገር ይበላሻል " ማለታቸውም የሚታወስ ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትሩን መልእክት ተከትሎ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በማግስቱ ለአስቸኳይ ስብሰባ ተቀመጦ እንደነበር ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል።

በወቅቱ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ሃላፊ ፓስተር ይታገሱ ሃይለ ሚካኤል ተቋሙ እያደረገ ስላለው ተግባራዊ እንቅስቃሴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል " በቅርብ ጊዜ የሚደረጉ ነገሮች እንደሚኖሩ ተስፋ እናደርጋለን አሁን በውይይት ደረጃ ላይ ነው ያሉት ምን ይደረግ፣ እንዴት እናድርግ ውጤታማ የምንሆነው እንዴት ነው በሚለው ላይ መክረዋል በቅርብ ጊዜ ተግባራዊ የሆነ እንቅስቃሴ ውስጥ ይገባሉ " ብለው ነበር።

የስብሰባው አላማም የጠቅላይ ሚኒስትሩ መልእክት ነገሩን በአጽንዖት መያዝ እንደሚያስፈልግ ጠቋሚ በመሆኑ መሆኑን ፓስተር ይታገሱ አስታውቀዋል።

መደረግ ባለባቸው ጉዳዮች ላይ ተከታታይ ውይይት ያደረጉት አባቶች በዛሬው ዕለት ወደ መቀሌ አቅንተዋል።

በመቐለ የሚገኙት አባቶች በምን በምን ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ተጨማሪ መረጃ ከተቋሙ እንዳገኘን የምናጋራቹ ይሆናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

ፎቶ፦ ድምጺ ወያነ

@tikvahethiopia
676🕊149😡60🤔26🙏23😭11👏6😢5😱2🥰1
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ🇪🇹 የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ፥ " በአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች የሚደረግ ምክክርና እርቀ ሰላም ፍሬው ጣፋጭ ነው " አሉ። ትናንት ሀምሌ 10/2017 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ ያቀኑት የትግራይ የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሸማግሌዎች ዛሬ ሀምሌ 11/2017 ዓ.ም ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) መክረዋል። የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ…
#Tigray የትግራይ ክልል የኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ለመወያየት ወደ አዲስ አበባ መጥተዋል።

ጳጳሳቱ ባለፈው ሳምንት ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር ለመወያየት ጥያቄ አቅርበው ነበር።

ለጥያቄ አወንታዊ ምላሽ በማግኘታቸው ዛሬ ወደ አዲስ አበባ ሊጓዙ እንደቻሉ ተነግሯል።

ጳጳሳቱ ነገ ማክሰኞ ሀምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠቅላይ ሚንስትሩ ተገናኝተው እንደሚወያዩ ተናግረዋል።

ከቀናት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትግራይ የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሸማግሌዎች ተቀብለው ስለ መምከራቸው ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamliyMekelle

ፎቶ፦ ድምጺ ወያነ

@tikvahethiopia
562😡194🕊67😭39🤔37🙏15👏10😢3🥰1
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ ቅዳሜ በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን በሚገኙ 6 ወረዳዎች ካለፈው የቀጠለ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመሩትን ህወሓት የሚቃወም የተቋውሞ ሰልፍ ተካሂደዋል። የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ሃፍቱ ኪሮስ " ራሳችን በራሳችን የማስተዳደር መብት ተጎናፅፈናል የህወሓት ቡድን በሚመድብልን ምስሌነ አንተዳደርም አያም በል ! " ብለዋል። " የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት እናከብራለን ፤ ተፈናቃዮች…
#Tigray

በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን የጊዚያዊ አስተዳደሩ ትእዛዝ በሰጠው አድማ በታኝ ፓሊስ የተደገፈ የስልጣን ሹምሽር እየተካሄደ መሆኑ ተሰምቷል።

ከትናንት ሀምሌ 14/2017 ዓ.ም ጀምሮ ነው ከመቐለ ወደ ማይጨው ከተማ በተላከ የአድማ ብተና ፓሊስ ጥብቅ ቁጥጥር ስር የስልጣን ሹምሽር እየተካሄደ ያለው።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጄ) የስልጠን ሹም ሽሩ " ሰላማዊ ነው " ቢሉም የቀድሞ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ጨምሮ በርካቶች ድርጊቱ " በሀይል የሚደረግ ግጭት ቀሰቃሽ የስልጣን ንጥቂያ  " ብለውታል።

የዞኑ አስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳ በወርሃ መጋቢት 2017 ዓ.ም ከትግራይ ከወጡበት ጀምሮ የአመራር ለውጥ ያልተደረገበት አከባቢ ሆኖ ቆይቷል።

የዞኑ አስተዳደር አመራሮች ባለፉት ወራት ህወሓት እንደማይወክላቸው የሚገልፅ ሰፋፊ ህዝባዊ ህዝባዊ ሰልፎች ማካሄዳቸው መዘገባችን ይታወሳል።

ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) በደቡባዊ ዞን እየተደረገ ነው ስላሉት የስልጣን ሹምሽር ዛሬ ሀምሌ 15/2017  ዓ.ም ለሚድያ በሰጡት መግለጫ ምን አሉ ?

- ከዞኑ የአመራር ቦታ የሚነሱ ሀላፊዎች በክልል የሃላፊነት ቦታ ተዘጋጅቶላቸዋል።

- የስልጣን ሽምሹሩ እንዲተገበር የሚያሳልጥ ፓሊስ ወደ አከባቢው ተልኳል።

- በዞኑ የለውጥ አመራር ለማድረግ ያስፈለገበት ምክንያት ቀጣይ አደጋዎች ለማስቀረትና  የክልሉ የፀጥታ ችግር ለመፍታት በማለም ነው።

- መንግስት በዞኑ በግድ ማድረግ ያለበት ነው እያደረገ ያለው ስለሆነም ሂደቱ ማደናቀፍ አይቻልም።

- የአከባቢው ህዝብ ፣ ወጣቶች ፣ ሚልሻና ሌሎች ለውሳኔው ውጤታማነት ተባባሪ መሆን አለባቸው።

ሲሉ ተናግረዋል።

በትግራይ ደብባዊ ዞን እየተከናወነ ያለውን ጉዳይ" በዞኑ ህዝብ ላይ የተጫነ አስገዳጅ የስልጣን ንጥቂያ ነው " በማለት ብርቱ ትችት አዘል ፅሁፍ ካጋሩት በርካቶች አንዱ አቶ ጌታቸው ረዳ ናቸው።

አቶ ጌታቸው " ' ኃላቀር ቡድን ' ሲሉ የገለፁት የህወሓት አመራር በክልሉ ደቡብና ደብባዊ ዞኖች ወታደራዊ ዘመቻ በማካሄድ ሌላ ቀውስ እንዲፈጠር እየሰራ ነው " ሲሉ ከሰዋል።

በዚህ ምክንያት ለሚፈጠር ማንኛውም ጥፋት ' ኃላቀር ቡድን ' ሲሉ የገለፁት የህወሓት አመራር ፣ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮችና በተለይ ፕሬዜዳንቱና የጊዚያዊ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ተጠያቂ መሆናቸውን አስጠንቅቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamliyMekelle

@tikvahethiopia
672🤔60🕊42😢19😡17👏8😱5🙏5😭1
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትግራይ ያልመከነ ተተኳሽ ሶስት የአንድ ቤተሰብ አባላት ህይወት ቀጠፈ። ጥቅምት 21 /2017 ዓ.ም በትግራይ ማእከላይ ዞን አበረገለ ጭላ ወረዳ ስምረት ቀበሌ ገበሬ ማህበር ዘገልዋ መንደር ውስጥ ባልመከነ ተተኳሽ  ሶስት የአንድ ቤተሰብ አባላት ህይወታቸው ጠፍቷል። ህይወታቸው የጠፋው ባል እና ሚስት ከ5 ዓመት ልጃቸው ጋር ነው። የወረዳው ፓሊስ አከባቢው በትግራዩ ጦርነት ከባድ ውግያ የተካሄደበት…
#Tigray

ያልመከነ ተተኳሽ ፈንድቶ የሦሥት ህፃናት ህይወት ተቀጨ።

ሦሥቱ ወንድሟሟች የአንድ አባትና እናት ልጆች ናቸው።

አደጋው ሀሞሌ 18/2017 ዓ.ም በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ታሕታይ ቆራሮ ወረዳ ልዩ ስሙ ዓዲ መናብር ነው ያጋጠመው።

ህፃናቱ ለጨዋታ በተንቀሳቀሱበት መንደራቸው አጠገብ የሚገኘው ጫካ ውስጥ የወደቀ ሹል ድምቡልቡል ብረት ያገኛሉ።

የልጅ ነገር ሆኖባቸው ብረቱ በደንጋይ እየቀጠቀጡ ሳጫወቱ ፈንድቶባቸው ወድያውኑ ህይወታቸው አልፈዋል።

በትግራዩ ጦርነት ምክንያት በየቦታው ያሉ ያልመከኑ ተተኳሾት በሰውና እንስሳት ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ላይ መሆናቸው በተደጋጋሚ መረጃ ማካፈላችን ይታወሳል።

ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በትግራይ የተለያዪ ወረዳዎች የሚገኙ ያልመከኑ ተተኳሾች በማስወገድ ሰብአዊ ኃላፊነታቸው በመወጣት ላይ ቢገኙም ጦርነቱ ከተካሄደበት የቦታ የቆዳ ስፋት አንፃር በቂ እንዳልሆነ ይገለፃል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia            
😭1.84K511😢145💔110🕊41🙏19🥰9👏3
#Tigray 🇪🇹 #EthiopianNationalDialogue

መተማመን እንዲጎለብትና ዘርፈ ብዙ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ መፍታት እንዲቻል የፖለቲካ ውይይት ማካሄድ ወሳኝና አስፈላጊ እንደሆነ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን አሳወቀ።

የትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀኔራል ) በበኩላቸው የምክክር ኮሚሽኑ ዓላማና ጥረት ለዘላቂ ሰላም ያለውን አወንታዊ አስተዋፅኦ እንደሚገነዘቡ አረጋግጠዋል።

ዛሬ በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የፕሬዜዳንት ፅህፈት ለመጀመሪያ ጊዜ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ አመራሮች ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች ጋር የፊት ለፊት ግንኙነት አደርገዋል።

የምክክር ኮሚሽኑ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ፣ " አገራዊ ችግሮችና ቁርሾዎቻችን ከንግግርና ውይይት ውጪ ሌላ ፍቱን መድሀኒት የላቸውም " ብለዋል።

" አገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ህዝብን የሚያቃቃሩ ትርክቶች ነቅሶ በንግግርና ውይይት በመፍታታ ህዝባዊና አገራዊ መግባባትና መተማመን ፅኑ መሰረት እንዲይዝ አልሞ እየሰራ ነው " ብለዋል።

የአገራዊ የምክክር ኮሚሽኑን ዓላማው አስፈላጊነት በማመን የተናገሩት ፕሬዚዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጄነራል) " ከምክክሩ በፊት በፌደራል መንግስትና በትግራይ ክልል መካከል የሚካሄድ የፖለቲካ ውይይት መቅደም አለበት " ብለዋል።

" የትግራይ ህዝብና መንግስት መልሶ ወደ ግጭትና ጦርነት አዙሪት የመግባት ፍላጎት ፈፅሞ የለውም " ያሉት ፕሬዜዳንቱ ፤ የምክክር ኮሚሽኑ በክልሉ ለሚሰራቸው ስራዎች ራሳቸውንና ካቢኔያቸው ተባባሪ ለመሆን ያላቸው ቁርጠኝነት ማረጋገጣቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከፕሬዘዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘው መረጃ ያሳያል።

#Peace #Ethiopia

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
905🕊159😡49😭44🙏43🤔15😢13🥰9
TIKVAH-ETHIOPIA
#መቐለ “ ማስክ የለበሱ ታጣቂዎች ገብተው የጽሕፈት ቤታችንን ታፔላ ነቅለውታል ” - ስምረት ፓርቲ “ ማስክ የለበሱ ” ያላቸው ታጣቂዎች ትላንት ምሽት 4:00 የመቐለ ጽሕፈት ቤቱን ለመዝረፍ ሙከራ እንዳደረጉና “ ታፔላውን ነቅለው እንደሄዱ ” በነአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው አዲሱ ስምረት ፓርቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል፡፡ በጽሕፈት ቤታችሁ በኩል የተዘረፈ ንብረትና የደረሰ ውድመት አለ ? ስንል የጠየቅናቸው…
#Tigray

“ የክልሉም የፌደራሉም መንግስታት ሕግ ማስከበር አለባቸው ካልሆነ በስተቀር የከበደ የጦርነት አደጋ እየመጣብን ነው ” - ስምረት ፓርቲ

➡️ “ የኤርትራ ታጣቂዎች ከዚህ በፊት ይዘዋቸው የነበሩ ቦታዎችን እንደያዟቸው ናቸው፡፡ አዳዲስ የያዟቸው ቦታዎችም አሉ ! ”


“ አዲስ ጦርነት እንዳይከፈት ” በሚል የተፈጠረውን ስጋት ጨምሮ በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ በእነ አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ስምረት ፓርቲ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርጓል።

አሁን ባለው ሁኔታ ጦርነት እንዳይነሳ መሰጋቱን በመጥቀስ፤ ዳግም ጦርነት ተፈጥሮ ያላገገመው ህዝብ የገፈት ቀማሽ እንዳይሆን እንደ ፓርቲ ያላቸውን ምክረ ሃሳብ የጠየቅናቸው የፓርቲው አባል አቶ ጣዕመ ዓረዶም፣ “ ከሰላም ውጭ ሌላ አማራጭ የለንም ” ብለዋል።

“ ህዝቡ የሚፈልገው ሰላም ነው፡፡ ለዚያም ነው የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት የተፈረመው፤ የፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ ለሙሉ ተተግብሮ እንደ ክልልም እንደ ሀገርም ወደ ሰላም እንድንገባ እንጅ ተጨማሪ የጥፋት ጦርነት እንዲመጣ አንፈልግም ” ሲሉም ተናግረዋል።

ሁሉም ሰላማዊ አማራጭ እንዲከተል መክረው፣ “ የፌደራል መንግስትም ማድረግ ያለበትን የሕግ ማስከበር ሥራዎችም እስካሁን አላደረገም፤ የፌደራል ሕጎች ሲጣሱ የማየት፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳዳርም በተመሳሳይ ሕግ ያለማስከበር ችግሮች አሉ፡፡ ስለዚህ የክልሉም የፌደራሉም መንግስታት ሕግ ማስከበር አለባቸው ካልሆነ በስተቀር የከበደ የጦርነት አደጋ እየመጣብን ነው ” ሲሉም አሳስበዋል።

ይፈጠራል ተብሎ ለተሰጋው ጦርነት የፕሪቶሪያው ስምምነት አለመፈጸም እንደ ምክንያት ሆኖ በተደጋጋሚ ይጠቀሳል፣ ለመሆኑ ያልተፈጸመውና ለጦርነት ሰበብ የሚሆነው ጉዳይ በግልጽ ምንድን ነው ? ሲልም ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስምረት ፓርቲን ጠይቋል፡፡

አቶ ጣዕመ በምላሻቸው፣ “ አንደኛው የትግራይ የግዛት አንድነት በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት መመለስ፣ ተፈናቃዮችም መመለስ ነበረባቸው፡፡ ሁለተኛው የኢትዮጵያና የኤርትራን ቦርደር የፌደራሉ መንግስት መጠበቅ ነበረበት፤ ስላልተጠበቀ ነው የኤርትራ ታጣቂዎች እየገቡ እየፈነጩበት ያሉት ” ብለዋል፡፡

“ DDR መፈጸም ነበረበት፤ የተወሰነ ቢሰራም በበጀት እጥረት ተቋርጦ ሙሉ ለሙሉ አልተተገበረም፡፡ ሙሉ ለሙሉ ተተግብሮ ታጣቂዎች ወደ ሰላሙ መሄድ ነበረባቸው፤ ወደ ሰላም ስላልሄዱ ነው ታጣቂዎቹን እየተጠቀሙባቸው ያሉት ” ነው ያሉት።

የፓርቲው አባል፣ “ ለትግራይ የሚያስፈልጋት የጸጥታ ኃይል እንደማንኛውም ይደረጋል ግን አሁን ባለው ሁኔታ ወጣ ባለመንገድ መሄድ አልነበረበትም ” ብለዋል፡፡

የኤርትራ ታጣቂዎች የያዟቸው የትግራይ ግዛቶች አሉ? አሁንም ነዋሪው የጥቃት ስጋት አለበት ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ፣ “ አዎ፡፡ የኤርትራ ታጣቂዎች ከዚህ በፊት ይዘዋቸው የነበሩ ቦታዎችን እንደያዟቸው ናቸው፡፡ አዳዲስ የያዟቸው ቦታዎችም አሉ። ሴቶች ላይ በኃይል ጥቃት ይፈጽማሉ፤ ሰዎችን አፍነው አፍሰው ይወስዳሉ፤ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ላይ ንብረት ዘርፈው ይወስዳሉ ” ሲሉም ከሰዋል።

“ ይሄ ወደ ልኩ መግባት አለበት፡፡ ይህም የፌደራል መንግስቱ ኃላፊነት ነው” የፓርቲው አባል፣ “በኢሮብ፣ በዛላምበሳ፣ በባድሜ ገብተው ተጨማሪ ቦታዎችን ይዘዋል ” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEhiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
1.04K😡137🕊99🤔26💔22😭18😢13🥰12🙏1
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray “ የክልሉም የፌደራሉም መንግስታት ሕግ ማስከበር አለባቸው ካልሆነ በስተቀር የከበደ የጦርነት አደጋ እየመጣብን ነው ” - ስምረት ፓርቲ ➡️ “ የኤርትራ ታጣቂዎች ከዚህ በፊት ይዘዋቸው የነበሩ ቦታዎችን እንደያዟቸው ናቸው፡፡ አዳዲስ የያዟቸው ቦታዎችም አሉ ! ” “ አዲስ ጦርነት እንዳይከፈት ” በሚል የተፈጠረውን ስጋት ጨምሮ በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ በእነ አቶ…
#Tigray

" የስምረት ፓርቲ ታጣቂ  ሀይል በሰነዘረው ጥቃት አንድ ሰው ተገድሏል " - የትግራይ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ

➡️ " እኛ ታጣቂ ሰራዊት የለንም " - አቶ ጌታቸው ረዳ

    
ከሰሞኑን በአላማጣ ከተማ በአንድ ቤተሰብ አባላት ላይ የቦንብ ተፈጽሞ የሰው ህይወት አልፏል።

የትግራይ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ባወጣው መግለቻ " ጥቃቱን የፌደራል መንግስት አጣርቶ እርምጃ የመውሰድ ኃላፊነት አለበት " ብሏል።

ሀምሌ 21/2017 ዓ.ም ሌሊት በአላማጣ ከተማ ነዋሪ በሆኑት ባለሀብት ሰለሙን አያሌው መኖሪያ ቤት በታጣቂዎች በደረሰ የቦንብ ጦቃት ሁለት ልጆቻቸው ሞተው እሳቸውና ባለቤታቸው የሚገኙባቸው 3 ሰዎች በከባድ ቆስለው በህክምና ክትትል ስር ይገኛሉ።

ቢሮው፤ " ለጥቃቱ ከተማዋን በኮማንድ ፓስት ስር እያስተዳደረ ያለው የፌደራል መንግስት ኃላፊነት ይወስዳል " ብሏል።

" ስለሆነም የፌደራል መንግስት የጥቃቱ ፈፃሚዎች አጣርቶ ህግ ፊት ያቅርብ " ሲል ገልጿል።

በሌላ በኩል ሀምሌ 20/2017 ዓ.ም በደቡባዊ ምስራቅ ዞን የዓዲ ጉዶም ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ በወጡ የወጀራት ነዋሪዎች ላይ በተተኮሰ ጥይት አንድ ሰው መገደሉንና ተኳሹ ማን እንደሆነ እስከ አሁን እንደማይታወቅ ያመለከተው ቢሮው " እስከመጨረሻው አጣራለሁ " ብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ ቢሮው ሀምሌ 23/2017 ዓ.ም በዓፋር ክልል ይንቀሳቀሳል ያለው " የስምረት ፓርቲ ታጣቂ ሀይል " በእንደርታ ወረዳ ምላዛት ተብሎ በሚጠራ ቦታ ላይ በሚገኝ የትግራይ ኃይል ላይ በሰነዘረው ጥቃት አንድ አባል  ተሰውቷል ሲል ከሰዋል።

" ስምረት ፓርቲ በሽብር ተግባር እየተሳተፈ ነው " ሲል የገልጾ " በላያችን ላይ እየተወሰደ ባለው ትንኮሳ ትዕግስታችን ተሟጠዋል " ሲል አስጠንቅቋል።

የስምረት ዴምክራሲያዊ ፓርቲ መስራችና መሪ አቶ ጌታቸው ረዳ ለዚሁ ክስ በሰጡት ምላሽ  " በምስረታ ሂደት የሚገኘው ስምረት የፓለቲካ ፓርቲ ታጣቂ ሰራዊት የለውም " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
476🕊69😢28😡25🤔17💔12😭11👏8🙏4🥰3