TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ዝቅተኛ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ዩኒቨርሲቲዎች እኩል በጀት የሚመደብበት አሰራር አይኖርም " - ትምህርት ሚኒስቴር

ከዚህ በኃላ ዝቅተኛ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ዩኒቨርሲቲዎች እኩል በጀት የሚመደብበት አሰራር እንደሚቀር የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደብላቸው በጀት ባስመዘገቡት ውጤት ልክ እንደሚሆን ሚኒስትሩ ይፋ አድርገዋል።

ይህን ይፋ ያደረጉት ከሰሞኑን በትምህርት ዘርፉ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በተቀናጀ መልኩ ማሻሻል የሚያስችል ስምምነት ትምህርት ሚኒስቴር እና 47 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የቦርድ ሰብሳቢዎችና የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች በተፈራረሙበት ወቅት ነው።

ሚኒስትሩ ፤ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን በመሰረታዊነት ለመቀየር የትምህርት ጥራትን ማስጠበቅ ወሳኝ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች የተጣለባቸውን ሃላፊነት በብቃትና በጥራት እንዲፈፅሙ በተለይ ሙስናን ማጥፋት ግዴታ መሆኑን ፕ/ር ብርሃኑ አሳስበዋል።

" ሙስና የትውልድ ጸር በመሆኑ ለትውልዱ አርዓያ የሚሆን ዩኒቨርሲቲ መፍጠር ይገባል " ብለዋል። #ኤፍኤምሲ

@tikvahethiopia
👏573😡101🤔8075😱25😢13🕊13😭13
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" በነገው ዕለት አንድ ቡድን ወደ ስፍራው ያቀናል " - አምባሳደር ነብያት ጌታቸው

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ ፤ በማይናማር ታግተው የነበሩ 246 ዜጎችን በቀጣይ ሳምንት ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን ነው አሳውቀዋል።

" በማይናማር በከፍተኛ ችግር ውስጥ ያሉ ዜጎችን ለማስወጣት በቶኪዮ እና በኒውዴሊ ባሉ ኤምባሲዎች በኩል ሥራዎች እየተሠሩ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" አሁን ላይ 246 ኢትዮጵያዊያን ከማይናማር ወጥተው ወደ ታይላንድ ደርሰዋል " ሲሉ ጠቅሰዋል።

" እነሱን ለመርዳትና የማጣራት ሥራ ለመሥራት በነገው ዕለት አንድ ቡድን ወደ ስፍራው ያቀናል " ብለዋል።

በተመሳሳይ በመካከለኛው ምስራቅ በችግር ውስጥ ያሉ ዜጎችን ለማስወጣት የሚደረገው ጥረት ቀጣይነት እንዳለውም ጠቁመዋል።
#ኤፍኤምሲ

@tikvahethiopia
🙏863161🕊64😭53😡49👏31😁24🥰23😢16😱14🤔12
አንጋፋው የማሲንቆና በገና ተጫዋች ድምጻዊና የሙዚቃ መምህር አለማየሁ ፋንታ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

ግጥምና ዜማ በመድረስ ክራር ፣ በገና እና ማሲንቂ በመጫወት የሚታወቁት አለማየሁ ፋንታ ፤ ለበርካታ ዓመታት በያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት በመምህርነት አገልግለዋል፡፡

በተለየ የማሲንቆ አጨዋወታቸው የሚታወቁ ሲሆን፤ በዓለም ዙሪያ የኢትዮጵያን ባህል ማስተዋወቅ ችለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ባወጣው የሀዘን መግለጫ ፤ ለኢትዮጵያ የሙዚቃ ማህበረሰብና ለመላው ሕዝብ ከባድ ሀዘን ነው ብሏል፡፡

በነገው ዕለት የአስክሬን ሽኝት መርሐ-ግብር ተደርጎ ስርዓተ ቀብራቸው ፒያሳ በሚገኘው በገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ከቀኑ በ9 ሰዓት የፈጸማል።

#ኤፍኤምሲ

@tikvahethiopia
😭1.16K🕊12077😢60🙏34😁26😱4👏3
TIKVAH-ETHIOPIA
ሻዕቢያ ? ➡️ " በፕሪቶሪያ ስምምነት አኩርፎ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የተጣላ ኃይል ጋር ተሰልፈህ የኢትዮጵያን መንግሥት ማስወገድ የሚቻልበት እድል ካለ ብለህ መንቀዥቀዥ በጣም አደገኛ ነው !! " - አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፦ " ትግራይ ውስጥ በሚፈጠር ትርምስ እናተርፋለን የሚሉ ብዙ ወገኖች አሉ። የኤርትራ መንግሥት አንዱ እንደሆነ አውቃለሁ። …
#Tigray

ዛሬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ በኢትዮጵያ ከሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ጋር ውይይት አካሂዷል።

በመድረኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ እንዲሁም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ተገኝተው ነበር።

ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ሰፋ ያለ ማብራሪያን መስጠታቸው ታውቋል።

ምን ተባለ?

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ፦

" ራሱን ነጥሎ የወጣው የህወሓት አንጃ የፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ ለሙሉ እንዳይተገበር እንቅፋት ሆኗል።

በተጨማሪም ምርጫ ቦርድ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሄድ የሰጠውን መመሪያ አልተቀበለም።

የፌደራል መንግስት የፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ ለሙሉ እንዲተገበር እየሰራ ሲሆን መንግስት የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ በጥሞና እየተከታተለ ነው።

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም በክልሉ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት አስፈላጊውን እገዛ ሊያደርግ ይገባል " ብለዋል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፦

" ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ራሱን ነጥሎ የወጣው የህወሓት አንጃ የጊዜያዊ አስተዳደሩ የዕለት ተለት ተግባራት ላይ እክል እየፈጠረ መጥቷል።

ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እና የፌደራል መንግሥት በክልሉ ዘላቂ ሰላም ግንባታ ያላቸውን ሚና አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል " ብለዋል።
#ኤፍኤምሲ

@tikvahethiopia
😁308🕊152101😡37👏27😭25🤔15🙏10😱6😢6🥰4
" የባህር በር ጥያቄን ማንሳት ነውርነቱ አቁሟል " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ኢትዮጵያ ለቀይ ባህር ስትል ኤርትራን የመውረር ፍላጎት እንደሌላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

" የኢትዮጵያ ፍላጎት እንነጋገር፣ ሰጥቶ በመቀበል መርህ፣ ህዝቦች በሚጠቀሙበት መርህ እንወያይ የሚል ነው " ብለዋል።

" የኤርትራ ህዝብ የሚያስፈልገው ልማት ነው፣ ተባብረን መልማትና መስራት እንጂ አንዱ አንዱን መውጋት የእኛ እቅድ አይደለም " ነው ያሉት፡፡

" ኢትዮጵያ ላይ ማንም ሀገር ወረራ ሊፈጽም እና ከጀመርነው ህልም ሊያስቆመን ይችላል የሚል ስጋት የለብንም " ብለዋል፡፡

" በቂ ዝግጅት ስላለን ማንም አያስቆመንም፣ ዝግጅት የምናደርገውም ጦርነትን ለማስቆም ነው " ሲሉ አክለዋል፡፡

" የባህር በር ጥያቄን ማንሳት ነውርነቱ አቁሟል " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አቋምም በዓለም ላይ ትልቅ ሀገር ሆኖ የባህር በር የሌለው የለም ስለሆነም በሰጥቶ መቀበል መርህ ሊሆን ይገባል የሚል ነው " ሲሉ ገልጸዋል፡፡

" የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ አጀንዳ ለመስጠት የመጣ ሳይሆን ባለፉት ዓመታት ትኩረት የተሰጠው እና በመደመር መጽሐፍ ላይ የተካተተም ነው " ብለዋል፡፡
#ኤፍኤምሲ

@tikvahethiopia
962😡375👏93🙏47🕊26🤔16🥰15😭14😢9💔8😱4
ፎቶ ፦ የ2017 ዓ/ም ጸሎተ ሐሙስ ሥነ ሥርዓት በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሲከናወን።

#ኤፍኤምሲ #ሰላምካቶሊክቲቪ

@tikvahethiopia
🥰409😡168104🙏54🤔38🕊9😱6😢5👏4
ፎቶ ፦ የ2017 ዓ/ም ጸሎተ ሐሙስ ሥነ ሥርዓት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሲከናወን።

#ኤፍኤምሲ #EOTCTV

@tikvahethiopia
3.93K🙏300😡111🥰83🕊68🤔24💔24👏22😢10😱5😭4
" እስካሁን የ6 ሰዎች ህይወት አልፏል። የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል " - ፖሊስ

ዛሬ ከቀኑ 7 ሠዓት 30 ከሙከጡሪ ወደ ጂዳ ሲጓዝ የነበረ በተለምዶ አይሱዚ ቅጥቅጥ መለስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ከለሚ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ ከነበረ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨታቸው ከባድ የትራፊክ አደጋ መድረሱን ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል።

አደጋው የደረሰው በኦሮሚያ ክልል፤ በሰሜን ሸዋ ዞን ዋጫሌ ወረዳ ሙከጡሪ ከተማ አቅራቢያ መቼላ ቀበሌ ቄሌምቶ ላይ ነው።

እስከ አሁን የ6 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

ከሟቾች በተጨማሪ 21 ሰዎች ላይ ከባድ እንዲሁም በሌሎች 17 ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱ የዞነ ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ ክፍል ኃላፊ ም/ ኢንስፔክተር ታከለ ቶሌራ ተናግረዋል፡፡

የአደጋ ከባድ በመሆኑ የሟቾች ቁጥር አሁን ካለው ሊጨምር እንደሚችል ተጠቁሟል።
#ኤፍኤምሲ

@tikvahethiopia
😭85685😢70🕊51🙏27💔25😱18🤔7😡6👏2🥰1
#ሰሌዳ

በኢትዮጵያ የተሽከርካሪ ሰሌዳ (ታርጋ) ለውጥ ለማድረግ የሚያስችል መመሪያ ጸድቋል።

መመሪያው የተሸከርካሪ የመለያ ቁጥር ሰሌዳ ዓይነቶችና ምልክቶች መወሰኛ እና የአገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 1050/2017 ነው።

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አማካሪ ከድልማግስት ኢብራሂም፤ " የሰሌዳ ለውጡ ዋና ምክንያት ኢትዮጵያ የተቀበለቻቸውን ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ታሳቢ ያደረገ ሰሌዳ እንዲኖር ለማስቻል ነው " ብለዋል።

ከዚህ ቀደም በነበረው የተሽከርካሪ መለያ ቁጥር ሰሌዳ ፦
- የአመራረት እና አሰረጫጨት ችግር፣
- የአወጋገድ ችግር፣
- የአሰራር ክፍተት፣
- የሀብት ብክነት፣
- በሲስተም የተደገፈ ስራ አለመኖር ችግር እንደነበር ጠቁመዋል።

ከዚህ በፊት ከነበረው አሰራር ጋር ተያይዞ የዕለት የተላላፊ እና የቋሚ መለያ ቁጥር ሰሌዳ አገልግሎት አሰጣጥ ለፎርጅሪ ለብልሹ አሰራር ለበርከታ ወንጀሎች የተጋለጠ በመሆኑ ይህ መመሪያ ችግሩን ይቀርፋል ሲሉ አስረድተዋል።

" መመሪያው በመላ ሀገሪቱ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፤ በተመዘገቡና ለምዝገባ በሚቀርቡ ተሽከርካሪዎች፣ በተሽከርካሪ አምራች /አስመጪ/ገጣጣሚ ድርጅቶች፣ በተሽከርካሪ መዝጋቢ አካላት እንዲሁም በኢትዮጵያ በሚገኙ እና አህጉር አቀፍ ተቋማት እና በግለሰቦች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል " ብለዋል።

የተሽከርካሪ መለያ ቁጥር ሰሌዳ ዓይነቶች እና ምልክቶች ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን መሰረት በማድረግ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ የመለያ ቁጥር ሰሌዳ አገልግሎት ይዘት በዓይነት እና በመጠን ወጥ እንዲሆን ለማድረግ፣ የመለያ ቁጥር ሰሌዳ ምርት ስርጭት አወጋገድ የተሸከርካሪ መረጃ አያያዝ ቁጥጥሩ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድርግ የመመሪያው ዓላማ መሆኑ ተብራርቷል፡፡ #ኤፍኤምሲ

@tikvahethiopia
😡447370👏118🤔69🙏44😢28😭24🕊23🥰16😱16💔7
TIKVAH-ETHIOPIA
የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል። የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና መቼ ይሰጣል ? ➡️ በወረቀት ፈተናቸውን የሚወስዱ ተፈታኞች ፦ ሰኔ 23 ፣ ሰኔ 24 እና ሰኔ 25/2017 ዓ/ም ➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ1ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሰኔ 23 ፣ ሰኔ 24 እና ሰኔ 25/2017 ዓ/ም ➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ2ኛ ዙር…
#NationalExam

በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና 608 ሺህ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ/ም የሚሰጠው አገር አቀፍ ፈተና ላይ 608 ሺህ ተማሪዎች ይቀመጣሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

ፈተናው በወረቀት እና በበየነ መረብ ይሰጣል።

ፈተናውን በወረቀት የሚወስዱ ተማሪዎች እንደ ቀደሙት ዓመታት ሁሉ ሙሉ በሙሉ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ገብተው ይወስዳሉ።

ፈተናውን በበይነ መረብ የሚወስዱት ደግሞ ፦
- በዩኒቨርሲቲዎች፣
- በመንግስት እና በግል ትምህርት ቤቶች፣
- በጤና እና መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆች
- በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ውስጥ ባሉ ኮምፒዩተሮች ይፈተናሉ። ተማሪዎቹ ግቢ ማደር ሳይጠበቅባቸው ከቤታቸው እየተመላለሱ ነው ፈተናውን የሚወስዱት።

በበይነ መረብ የሚሰጠው ፈተና በሁለት ዙር ሲሆን ይህም የሆነው በበይነ መረብ የመፈተን አቅምን እና የተፈታኝ ተማሪዎችን ቁጥር ለመጨመር እንዲሁም ያለውን የመሰረተ ልማት አቅም ለማሳደግ እንደሆነ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለኤፍ ኤም ሲ በሰጠው ቃል አስረድቷል።

#Ethiopia #NationalExam #Grade12 #ኤፍኤምሲ

@tikvahethiopia
🤔351196😡117😭93🙏76👏37🕊32💔32🥰22😢10😱7