TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ATTENTION🚨

ከዛሬ ግንቦት 6 / 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት የኩፍኝ ክትባት ይሰጣል።

ወላጆች ልጆቻችሁን አስከትቡ።

ኩፍኝ ምንድነው ?

የኩፍኝ በሽታ የኩፍኝ ቫይረስ በሚባል ረቂቅ ተህዋስ የሚከሰትና በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው የሚዛመት የበሽታ ዓይነት ነው፡፡ የኩፍኝ በሽታ ለብዙ ህጻናት ህመም፣ የአካል ጉዳትና ሞት ምክንያት ከሆኑት በሽታዎች አንዱ ነው፡፡

የበሽታው መተላለፊያ መንገዶች ምንድናቸው ?

➡️ ኩፍኝ በሽታ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው የኩፍኝ በሽታ ከተያዘው ሰው አፍንጫና ጉሮሮ በሚወጡ ፈሳሽና ጠብታዎች ንክኪና በትንፋሽ አማካኝነት ነው፡፡

➡️ የኩፍኝ በሽታ አምጭ ተህዋስ ወይም ቫይረስ በኩፍኝ ከተያዘዉ ሰዉ በከፍተኛ ሁኔታ የመሰራጨት አቅም የሚኖረው የበሽታው ምልክቶች መታየት በሚጀምርበት ወቅት ነው፡፡

➡️ አንድ በኩፍኝ የተያዘ ሰው በአብዛኛው ጊዜ ቫይረሱ ወደ ሰውነቱ ከገባ በኋላ የሽፍታ ምልክቶች በሰውነቱ ከመውጣቱ ከ4 ቀናት በፊት እንዲሁም ሽፍታዎቹ ከወጡ በኋላ እስከ 4 ቀን ድረስ ባለው ጊዜ በሽታውን ወደ ሌሎች ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ ያስተላልፋል፡፡

➡️ ህጻናት በሚሰባሰቡበት ቦታ ማለትም በትምህርት ቤቶች፣ በጤና ተቋማት እና በሌሎችም ቦታዎች በሽታው በቀላሉ ሊዛመት ይችላል፡፡

የበሽታው ዋና ዋና ምልክቶች ምንድናቸው ?

- ከፍተኛ ትኩሳት፣
- ከራስ ፀጉር ጀምሮ ወደ ሌሎች የሰውነት፣ ክፍሎች የሚዛመት ሽፍታ፣
- የአይን መደፍረስ ወይም መቅላት፣
- ከአፍንጫ የሚወጣ ፈሳሽ መብዛት፣
- የአይን እንባ ማዘል፣
- ሳል እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

ስላ ኩፍኝ መከላከያ ክትባት ፦ የኩፍኝ መከላከያ ክትባት ህፃናት ከተወለዱ በ9 እና በ15 ወር ዕድሜያቸው በመደበኛው የክትባት አገልግሎት ይሰጣል፡፡

በተጨማሪም የኩፍኝ ክትባት የህፃናትን በሽታ የመከላከል አቅም ለማዳበር በተለያዩ ጊዜያት በዘመቻ ይሰጣል፡፡

የኩፍኝ በሽታን በዘላቂነት መከላከል የሚቻለው ህፃናትን በመደበኛ የክትባት መርሐግብር እና በዘመቻ መልክ የሚሰጠውን የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባትን ማስከተብ ሲቻል ነው፡፡

ልጅዎትን ያስከትቡ !!
#ኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
😡235150🙏34🤔25🥰9🕊8😭8😢1
#ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ውስጥ በውጭ ምንዛሪ መገበያየት ይቻላል ? የብሔራዊ ባንክ መመሪያ በትክክል ምን ይላል ?

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ ባለፈው አመት 2016 ሐምሌ ወር ላይ የውጭ ምንዛሬ ግብይት በነፃ ገበያ እንዲመራ ከወሰነ በኋላ፣ አብሮ ይፋ በተደረገው መመሪያ በውጭ ምንዛሪ ግብይት ላይ አንዳንድ ማሻሻዎችን ማድረጉን አስታውቋል፡፡

በመመሪያው ላይ የተዘረዘሩትን ተግባራት መሰረት በማድረግም፣ ከህብረተሰቡ በኩል ኢትዮጵያ ውስጥ በውጭ ምንዛሪ መገበያየት ይቻላል ወይ ? የሚል ጥያቄ ይነሳል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ይህን በሚመለከት የባንክ ባለሙያዎች ማብራሪያ ጠይቋል፡፡

በዚህ ጉዳይ ዙርያ ማብራሪያቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት የብሔራዊ ባንክ ባለሙያ ምን አሉ ?

" ኢትዮጵያ ውስጥ ከተፈቀደላቸው ሰዎች ውጪ፣ በውጭ ምንዛሪ መገበያየት አይፈቀድም፡፡ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በውጭ ምንዛሪ ወይም ዶላር መገበያየት አይችልም፡፡

ግብይትን በዶላር የሚፈፅሙ ሰዎች፣ የተፈቀደላቸው ብቻ ናቸው፡፡ እነዚህም ዶላር ይዘው ከውጭ የሚመጡ ቱሪስቶች፣ ዲያስፖራዎች እና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ከውጭ ሲመጡ እስከ 10 ሺህ ዶላር ይዘው እንዲገቡ ስለሚፈቀድላቸው፣ በጉምሩክ አስመዝግበው ባስገቡት ዶላር መገበያየት ይችላሉ፡፡  "

አገልግሎት ሰጭዎችስ በዶላር ማስከፈል ይችላሉ ?

" እነዚህ ሰዎች በዶላር መገበያየት የሚችሉት፣ አገልግሎታቸውን በውጭ ምንዛሪ እንዲሸጡ ከተፈቀደላቸው ተቋማት ብቻ ነው፡፡

ለምሳሌ ነጋዴዎችና አገልግሎት ሰጭዎች፣ ማለትም ሆቴሎችና አስጎብኝዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ለሰጡት አገልግሎተት በዶላር ክፍያ መቀበል እንዲችሉ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ያላቸው ናቸው፡፡ ኢትዮጵያዊ ሆኖ፣ በዶላር ግብይት መፈፀም አይችልም፣ ከተፈቀደላቸው ተቋማትም ቢሆን፡፡

እኔ ኢትዮጵያዊ ሆኜ በዶላር እንዲያስከፍል ወደ ተፈቀደለት ሆቴል ሄጄ በዶላር መጠቀም አልችልም፡፡ ዲያስፖራ ከሆነንክ ግን፣ የሆነ ሆቴል ሔደህ ለተሰጠህ አገልግሎት በዶላር መክፈል ትችላለህ፡፡ ሆቴል ደግሞ ለሰጠው አገልግሎት በዶላር የማስከፈል ፈቃድ ያለው መሆን ይጠበቅበታል፡፡ ከፋዩም፣ አስከፋዩም (ተጠቃሚውና አገልግሎት ሰጪው) በዶላር ለመገበያየት የተፈቀደላቸው ወይም እውቅና የተሰጣቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡

ከአንድ የባንክ ሒሳብ ወደ ሌላ የባንክ ሒሳብ ዶላር ማስተላለፍ ይቻላል ?

" የውጭ ምንዛሪ ማስተላለፍን (ትራንስፈርን) በተመለከተ፣ ከአንድ የዶላር ሒሳብ ኢትዮጵያ ውስጥ ላለ ሌላ የዶላር ሒሳብ የውጭ ምንዛሪ ማስተላለፍ አይቻልም፡፡ ለምን ዓላማ ነው የሚተላለፈው ? የሚለው ይታያል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ዕቃ ገዝተህ በዶላር ልክፈል ብትል፣ አንተም በዶላር የመክፈል መብት የለህም፣ ሻጩም በዶላር ክፍያ የመቀበል ፈቃድ የለውም፣ ስለዚህ አይቻልም፡፡

ነገር ግን የዶላር አካውንት ኖሮህ፣ ከውጪ ሀገር እቃ ብትገዛ፣ ለእሱ በዶላር የመክፈል መብት አለህ፡፡ በቀጥታ ለእቃ ሻጩ ነው ዶላሩ የሚተለላለፈው፡፡ ውጭ ሀገር እቃ ወደገዛህበት መደብር ትራንስፈር ይደረጋል/ይተላለፋል፡፡ መረጃ አቅርበህ፣ ባንኩ ያንን መረጃ አይቶ አሳማኝ ሆኖ ካገኘው ይህንን ያደርግልሀል፡፡ ከራስህ ዶላር መፅሐፉን ለሸጠልህ ነጋዴ በቀጥታ ማስተላለፍ ይቻላል፡፡ ዋናው ነገር ለምን አላማ ነው የምታስተላልፈው የሚለው ነው፡፡ "

ኢትዮጵያ ውስጥ በውጭ ምንዛሪ ግብይት መቼ ሊጀመር ይችላል ?

" በውጭ ምንዛሪ ግብይት መቼም አይጀመርም፡፡ በየትም ሀገር በውጭ ምንዛሪ ግብይት አይደረግም፡፡ እንደዛ ከሆነ፣ የሚነግርህ ትርጉም የሀገርህን ብር አታምነውም ማለት ነው፡፡ ኢኮኖሚዋ ችግር ላይ የወደቀባት ዚምባብዌ እንኳን ያንን አላደረገችም፡፡

የውጭ ምንዛሪ ፍሰትን ለመጨመር፣ ኤክስፖርትን ለማበረታታት፣ የምታደርጋቸው ማስተካከያዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ከዛ ውጪ፣ ዜጎችህን በዶላር ተገበያዩ ልትል አትችልም፡፡

ለምሳሌ፣ ሪልስቴቶች ወይም አለምአቀፍ ት/ቤቶች የዋጋ እና የክፍያ ተመንን በዶላር ሲያወጡ ይታያል፡፡ ይህ ችግር የለውም፡፡ ክፍያው ሲፈፀም ግን በኢትዮጵያ ብር ነው የምትከፍለው፡፡ "

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቀጣይ ፦
- ለውጭ ጉዞ ዶላር/የውጭ ምንዛሪ እንዴት ነው የሚሰጠው ?
- የባንኮች ቪዛ ካርዶች እንዴት ነው የምንጠቀምባቸው ?
- የባንኮች ቪዛ ካርዶች በሀገር ውስጥ የምንጠቀምበት ዕድል አለ ?
- የዶላር አካውንት/የውጭ ምንዛሪ የባንክ ሒሳብ ለመክፈት ቅድመ ሁኔታ አለ ? በሚሉ ጥያቄዎች ላይ የባለሙያ ማብራሪያ ያቀርባል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
2404👏104🙏66😡52😭49🤔34🥰15🕊15😢14😱10💔4
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ውስጥ በውጭ ምንዛሪ መገበያየት ይቻላል ? የብሔራዊ ባንክ መመሪያ በትክክል ምን ይላል ? የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ ባለፈው አመት 2016 ሐምሌ ወር ላይ የውጭ ምንዛሬ ግብይት በነፃ ገበያ እንዲመራ ከወሰነ በኋላ፣ አብሮ ይፋ በተደረገው መመሪያ በውጭ ምንዛሪ ግብይት ላይ አንዳንድ ማሻሻዎችን ማድረጉን አስታውቋል፡፡ በመመሪያው ላይ የተዘረዘሩትን ተግባራት መሰረት በማድረግም፣ ከህብረተሰቡ…
#ኢትዮጵያ

" የዶላር ባንክ ሒሳብ ለመክፈት የዶላር ምንጭህ መታወቅ አለበት፡፡ ከዚሁ በጥቁር ገበያ እየለቃቀምክ ማስገባት አትችልም፡፡ ይህ ህገወጥ ነው " - የባንክ ባለሙያ

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ከብሔራዊ ባንክ ባለሙያ ጋር ፦
- ኢትዮጵያ ውስጥ በውጭ ምንዛሬ መገበያያት ይቻላል ወይ ?
- አገልግሎት ሰጪዎች በዶላር ማስከፈል ይችላሉ ?
- ከአንድ የባንክ ሒሳብ ወደሌላ የባንክ ሒሳብ ዶላር ማስተላለፍ ይቻላል ?
- ኢትዮጵያ ውስጥ በውጭ ምንዛሪ ግብይት መቼ ሊጀመር ይችላል ?

የሚሉ ጥያቄዎችን በማንሳት ማብራሪያ ማቅረቡ ይታወሳል።

ለዛሬ ደሞ ከኚሁ ባለሙያ እንዲሁም ከአንድ ሌላ የባንክ ባለሙያ ጋር የተለያዩ ማብራሪያ የሚፈልጉ ጥያቄዎችን በማንሳት ያዘጋጀውን ማብራሪያ ያቀርባል።

ለውጭ ጉዞ ዶላር/የውጭ ምንዛሪ እንዴት ነው የሚሰጠው ?

" ለጉዞ ከሆነ ከራስህ ዶላር አካውንት ወይም ዶላር አካውንትም ባይኖርህ ከባንኮች ወይም ከተፈቀደላቸው የውጭ ምንዛሪ ሱቆች በግዢ እስከ 10 ሺህ ዶላር ይዘህ መውጣት ትችላለህ፡፡ ለዚህ ግን ማሳየት ያሉብህ ማስረጃዎች ይኖራሉ፣ የጉዞ ሰነዶች ማለት ነው፣ ለምሳሌ ቪዛ እና የአየር ቲኬት የመሳሰሉት፡፡ "

የባንኮች ቪዛ ካርዶች እንዴት ነው የምንጠቀምባቸው ?

" የንግድ ባንኮች ቪዛ/ማስተር ካርዶች ሁለት አላማ አላቸው፡፡

አንደኛው፣ ዳያስፖራዎች ከካርዳቸው በቀጥታ ወደ ሀገር ቤት በቀላሉ ዶላር እንዲልኩ ያስችላቸዋል፡፡ አሜሪካ ያለው ዳያስፖራ የአሜሪካ ባንክ ካርድ ይኖረዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ተቀባይ ደግሞ የንግድ ባንክ ማስተር ካርድ ይኖረዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ላለው ተቀባይ በካርዱ በቀላሉ ዶላር ሊያስተላልፍለት ይችላል፡፡ ተቀባዩ ደግሞ ከውጭ ዶላር ሊላክልኝ ስለሆነ የዶላር አካውንት ክፈቱልኝ ይላል፡፡ ከዛም ላኪው ከካርዱ በቀጥታ ወደ ተቀባዩ አካውንት ዶላር ያስተላልፍለታል፡፡

ሁለተኛው ጠቀሜታ፣ ከዚህ ወደ ውጭ ስትወጣ እስከ 10 ሺህ ዶላር መውሰድ ትችላለህ፡፡ ይህን በካሽ ከሚሰጡህ ይልቅ በካርድ ቢሰጡህ ይሻላል የሚል ነው፡፡ ስለዚህ ከባንክ ወደ ውጭ ይዘህ ለመውጣት የተፈቀደልህ ዶላር ማስተር ካርዱ ላይ ይጫናል ማለት ነው፡፡ ከዛም ካርዱን ይዘህ በመውጣት እንደ ኤቲኤም ትጠቀምበታለህ፡፡ "

ማስተር ካርዱን በውጭ ሀገራት ብቻ ነው የምንጠቀምበት ?

ስለዚህ ጉዳይ ያብራሩልን ማንነቴ አይጠቀስ ያሉን ሁለተኛ የባንክ ባለሙያ ፥ ቪዛ ካርዱ የሚጠቅመው ዶላር ይዞ ለመውጣት እና እዛው እንደ ኤቲኤም ለመጠቀም ነው ብለዋል፡፡

ካርዱ ላይ የሚጫነው ዶላር/የውጭ ምንዛሪ በባንክ የተፈቀደ ብቻ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
ካርዱን ስላወጣህና አካውንትህ ውስጥ ዶላር ስላለህ ብቻ ካርዱ ላይ አይጫንም፡፡ አሳማኝ በሆነ ምክንያት የውጭ ጉዞ መኖሩ ከተረጋገጠ በኋላ ይዘህ እንድትወጣ የተፈቀደልህን ዶላር ካርዱ ላይ ይጭኑልሃል፡፡

ከውጭ ሀገር ከተመልስክ በኋላ፣ ካርድህ ውስጥ የተጫነውን ዶላር ካልጨረስከው ያልተጠቀምክበት ዶላር ካርዱ ውስጥ ካለ እዚህ ሀገር ካለ ኤቲኤም ማሽን ልታወጣው ትችላለህ፡፡ ግን ኤቲኤም ማሽኑ ዘርዝሮ ነው በብር የሚሰጥህ በዶላር አይሰጥህም፡፡

ለሀገር ውስጥ ግብይት ልትጠቀምበት አትችልም፡፡ ምክንያትም ቪዛ ካርድ የሚጠይቅ ግብይት የለም እዚህ ሀገር፡፡ ነገር ግን ካርድህ ውስጥ ያለውን ዶላር (ያልተጠቀምክበትን) ለውጭ ግብይት ልትጠቀምበት ትችላለህ፡፡ የካርድ ቁጥርህን በመናገር የፈለከውን ክፍያ ትፈፅምበታለህ፡፡ ለምሳሌ የቪዛ ክፍያ የሚጠይቁ ኤምባሲዎች አሉ ' በዶላር ክፈል ' ይሉሀል፡፡ ቪዛ ካርድ ካለህ (ቀድሞ ዶላር የተጫነበት) የካርድ ቁጥሩን ትነግራቸውና ከዛ መቀነስ ይችላሉ፡፡  "

የባንኮች ቪዛ ካርዶች በሀገር ውስጥ የምንጠቀምበት ዕድል አለ ?

" ቪዛ ካርዶቹ ብርም ሊጫንባቸው ይችላል፡፡ ንግድ ባንኮች ካርዶቹን ከዶላር በተጨማሪ ብርም ከጫኑባቸው እዚህ እንደ ኤቲኤም ልትጠቀምባቸው ትችላለህ፡፡ እንደዛ የሚያደርጉ ባንኮች አሉ፡፡

ለምሳሌ ፦ አንዳንድ ባንኮች በቪዛ ካርዳችሁ መጥታችሁ በፖስ ማሽን ተጠቀሙ የሚል ማስታወቂያ ሲያስነግሩ እንሰማለን፡፡ ይህ ማለት ቪዛ ካርዳቸው ከዶላር በተጨማሪ ብርም ተጭኖበታል ማለት ነው፡፡ ሁለቱንም አገልግሎት እንዲሰጥ ይደረጋል ቪዛ ካርዱ፡፡

ፖስ ማሽኑ እና ኤቲኤም ማሽኑ ቪዛ ካርዶችን ያነብባል፡፡ ይህ ግን እንደ ባንኩ ምርጫ ይወሰናል፡፡ ሁለቱንም እንዲያገለግል (ዱዋል ማለት ነው ብርም ዶላርም እንዲጫንበት) ሊያደርግ ይችላል ወይም ለውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ብቻ እንዲሆን ሊያደርግ ይችላል።

ቪዛ ካርዱ ዱዋል (ለሁለቱም የሚያገለግል) ካልሆነ ግን አንዴ ከተጠቀምክበት በኋላ ከጥቅም ውጪ ነው የሚሆነው፡፡ ሁሌም ወደ ውጭ አትመላለስም፡፡ "

የዶላር አካውንት/የውጭ ምንዛሪ የባንክ ሒሳብ ለመክፈት ቅድመ ሁኔታ አለ ?

" የዶላር ባንክ ሒሳብ ለመክፈት፣ የዶላር ምንጭህ መታወቅ አለበት፡፡ ከዚሁ በጥቁር ገበያ እየለቃቀምክ ማስገባት አትችልም፡፡ ይህ ህገወጥ ነው፡፡ ከውጭ የሚገባልህ የደመወዝ ወይም የስጦታ አለያም የክፍያ ዶላር እንዳለህ ማስረዳትና ለዚያ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅብሀል፡፡

በካሽ ይዘህ ስትሔድ ደግሞ ከውጭ ያስገባኸው ዶላር ስለመሆኑ፣ በጉምሩክ በህጋዊነት የገባ መሆኑን የሚያሳይ ሰነድ ማቅረብ አለብህ፡፡ ምክንያቱም ከውጭ ስትገባ አስመዝግበህ ነው እስከ 10 ሺህ ዶላር ድረስ ይዘህ የምትገባው፡፡ ስለሆነም የዶላር የባንክ ሒሳብ/ዶላር አካውንት ለመክፈት ቅድመ ሁኔታው፣ የዶላር ምንጭህን ማሳወቅ ነው፡፡ "

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
6294😡141🙏52😭26🤔19👏17🕊13😱10💔10😢8🥰7
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ኢትዮጵያ #ረቂቅአዋጅ

የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ መሬትን በሊዝ በባለቤትነት መያዝ የሚያስችላቸው የአዋጅ ረቂቅ ነገ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይቀርባል።

የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ የማይንቀሳቀስ ንብረት " ባለቤት ' ወይም  " ባለይዞታ " የሚሆኑበትን አግባብ ለመደንገግ የወጣው ይህ " የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሚሆኑበት " ወይም " ለመኖሪያ ቤት ግንባታ የሚውል መሬት የሚያገኙበትን " ህጋዊ አሰራር ለመዘርጋት ነው።

ረቂቅ አዋጁ ምን ይላል ?

- ኢትዮጵያዊ ዜግነት የሌላቸው ግለሰቦች በኢትዮጵያ መሬትን፣ የመኖሪያ ቤትን ወይም ተያያዥ ግንባታዎችን በባለቤትነት ለመያዝ፤ ቢያንስ 150 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ሊመድቡ እንደሚገባ ይደነግጋል።

- በውጭ ዜጋ " በሊዝ ባለይዞታነት " ወይም " ባለቤትነት " የሚያዝ መሬት ወይም የመኖሪያ ቤት፤ " የማይንቀሳቀስ ንብረት " ተደርጎ ይወሰዳል። " ሊዝ "  ማለት " አግባብነት ባለው ህግ መሰረት በጊዜ በተገደበ ውል ለመኖሪያ ቤት ግንባታ ዓላማ የሚውል የከተማ ወይም የገጠር መሬት የሚገኝበት የመሬት ይዞታ ስሪት " ነው።

- ማንኛውም የውጭ ዜጋ በኢትዮጵያ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት ወይም ባለይዞታ ሊሆን የሚችለው በአዋጁ የተዘረዘሩ ቅደመ ሁኔታዎችን ሲያሟላ ነው።

እነዚህም ፦
° የውጭ ዜጋው ስም፣ ዜግነት እና ሌሎችን ማንነትን የሚገልጹ ህጋዊ ሰነዶችን ማቅረብ አለበት።
° የውጭ ዜጋው የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለመብት ለመሆን የሚያስፈልግ አነስተኛ የገንዘብ መጠን ለማሟላት የሚያስችል በቂ አቅም ያለው መሆን አለበት።
° ማንኛውም የውጭ ዜጋ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት ለመሆን፤ የሊዝ ዋጋውን ጨምሮ ለአንድ የመኖሪያ ቤት ግንባታ ሙሉ ዋጋ ወይም ለመኖሪያ ቤት ግዢ የሚመድበው አነስተኛ የገንዘብ መጠን ከ150 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ያነሰ ሊሆን አይችልም።
° የውጭ ዜጋው የወንጀል ሪከርድ የሌለበት መሆን ይገባዋል።

እነዚህን መስፈርቶች የሚያሟላ አንድ የውጭ ዜጋ ከከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የሚሰጥ ፈቃድ ሊያገኝ ይገባዋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ " የፈቃድ ይሰጠኝ " ማመልከቻ ላቀረበ የውጭ ዜጋ፤ አስፈላጊውን ምርመራ በማድረግ በ15 ቀናት ውስጥ ውሳኔ መስጠት ይጠበቅበታል።

- የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ከውጭ ዜጎች የሚጠበቀውን የአነስተኛ ገንዘብ መጠን ከፍ ወይም ዝቅ የሚያደርግ የእያንዳንዱን የሊዝ ቦታ ወይም ቤት ስፋት እንዲሁም የሊዝ ይዞታዎችን ወይም ቤቶችን አጠቃላይ ቁጥር የሚወስን መመሪያ የማውጣት ስልጣን በአዋጅ ረቂቁ ተሰጥቶታል። መመሪያውን የሚያወጣው፤ የቤቶች ገበያ ወቅታዊ ሁኔታን፣ የከተሞች የማይንቀሳቀስ ንብረት አማካይ ዋጋን፣ የውጭ ዜጎች በቤቶች ገበያ ያላቸውን የተሳትፎ መጠን እና የአዋጁን ዓላማ ለማሳካት የሚረዱ ሌሎች ምክንያቶችን መሰረት በማድረግ ነው።

- የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያ፤ የተወሰኑ ሀገራት ዜጎችን ወይም ዜግነት የሌላቸው የውጭ ሀገር ሰዎችን በኢትዮጵያ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት ወይም ባለይዞታ እንዳይሆኑ #ሊከልክል ይችላል።

- ለውጭ ዜጎች የተገደቡ ልዩ ቦታዎች እና የድንበር አካባቢዎችም እንዲሁ በሚያወጣ መመሪያ ይወሰናሉ።

- በውጭ ዜጎች ላይ የተጣሉ ሌሎች ገደቦችም አሉ።
° ማንኛውም የውጭ ዜጋ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት ወይም ባለይዞታ ለመሆን ከሀገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋም ወይም ምንጭ ገንዘብ መበደር ወይም ካፒታል ማሰባሰብ አይችልም።
° የውጭ ዜጎች ይህን ጉዳይ ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ የሊዝ፣ የቤት ግዢ፣ የግንባታ ፈቃድ ወይም ተያያዥ የመንግስታዊ አገልግሎት ክፍያዎችን መክፈል ያለባቸው በኢትዮጵያ ተቀባይነት ባለው የውጭ ምንዛሬ ብቻ ነው።
° ማንኛውም የውጭ ዜጋ በመንግስት ቀጥተኛ ድጎማ ለዜጎች በሚሰሩ የጋራ መኖሪያ ህንጻዎች ውስጥ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት መሆን አይችልም። ይህ ገደብ በግል እና በመንግስት አጋርነት ወይም በተመሳሳይ የቤቶች ልማት ማዕቀፍ በፌደራል ወይም በክልል መንግስታት የሚገነቡ መኖሪያ ቤቶችን አያካትትም። ለውጭ ዜጎች የተቀመጠው ገደብ በእነዚህ አካላት አማካኝነት ለትርፍ ዓላማ ተገንብተው ለሽያጭ የሚቀርቡ ቤቶች ላይ ተፈጻሚ አይሆንም።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገጽ ነው።

@tikvahethiopia
😡1.28K209😭88🤔72💔41🙏32👏21🕊18😢17😱10🥰7
#ኢትዮጵያ

በመንግሥት ብቻ ሲሰጥ የነበረው የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎት የግል ዘርፍን ጨምሮ ሌሎች አካላት እንዲሳተፉ የሚያስችለው ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መተላለፉን የሚኒስትሮች ምክር ቤት አስታወቀ።

በሀገሪቱ ባለፉት ዓመታት የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎት በመንግሥት ብቻ ሲሰጥ መቆየቱን ያስታወሰው ምክር ቤቱ፣ ከዘርፉ እያደገ ከመጣው ፍላጎት አንፃር መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን፣ የግል ዘርፉን፣ የሕብረት ሥራ ማሕበራትንና የሙያ ማሕበራትን ማሳተፍ የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝቧል።

ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ በሙሉ ድምጽ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 45ኛ መደበኛ ስብሰባው በበርካታ ጉዳዮች ላይ ከተወያየ በኋላ ውሳኔ ያሳለፈው ምክርቤቱ የስርዓተ ምህዳር አገልግሎት ክፍያ ረቂቅ አዋጅን በተጨማሪነት ለፓርላማው እንዲተላለፍ መወሰኑ ካፒታል ለመረዳት ተችሏል። #CAPITAL

@tikvahethiopia
😡23089👏29🤔19🥰11🕊10💔7😭2😢1🙏1
🇪🇹#ኢትዮጵያ

" ኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘትን ጉዳይ የብሔራዊ ጥቅም አንዱ አካል አድርጋ እየሰራችበት ነው።

ከቀጠናው ሀገራት ጋር ትብብር በመፍጠር ተጠቃሚነቷን ለማረጋገጥ ጥረት እያደረገች ነው።

በጂኦግራፊያዊ አቀማመጣችን፣ በሕዝብ ብዛታችንና በታሪካችን የባህር በር ማግኘት ይገባናል።

ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያለ ምንም ክፍፍል እና ልዩነት በመተባበር የተጀመረውን የባህር በር አጀንዳ ወደ ፊት ማስኬድ አለበት።

ሰላማዊ በሆነ መንገድ ምላሽ እንዲያገኝ
ኢትዮጵያ እየሰራችበት የሚገኘው የባህር በር ጥያቄ ቅቡልነት ያለው ነው። " - የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ቀነአ ያደታ (ዶ/ር)

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
1.06K😡376👏112🕊54🤔44😭24🥰19😱15💔14😢7🙏1
TIKVAH-ETHIOPIA
#Mpox #Ethiopia “ በሞያሌ በMpox የተያዙት ሦስት ሰዎች ናቸው፡፡ በጅማ ዞንም ተገኝቷል። ሁለት የተያዙ አሉ፡፡ በአጠቃላይ በኦሮሚያ አምስት ኬዞች ናቸው የተገኙት ” - የክልሉ ጤና ቢሮ በሞያሌ ከተያዙት በተጨማሪ በጅማ ዞንም ሁለት ሰዎች በዝንጀሮ ፈንጣጣ/Mpox መያዛቸውን፣ በአጠቃላይ በክልሉ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ብዛት አምስት መድረሱን የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።…
#ኢትዮጵያ

በMpox በሽታ የመጀመሪያው ሞት መመዝገቡን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በኢትዮጵያ የMpox (የዝንጀሮ ፈንጣጣ) መገኘቱ ከተገለጸ በኃላ በዛሬው ዕለት የመጀመሪያው ሞት መመዝገቡን ሚኒስቴሩ ይፋ አድርጓል።

እስካሁን 15 የላብራቶሪ ምርመራ ተካሂዶ 6 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን የ1 ሰው ህይወት አልፏል ተብሏል።

ከቀናት በፊት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የMpox ኬዝ በሞያሌ ከተማ መገኘቱ ይፋ መደረጉ ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
😭1.61K425😱189🙏80😢58💔49🕊34😡26👏24🤔23🥰11
#ኢትዮጵያ 🇪🇹 #ምርጫ

" በቀጣዩ ምርጫ በፋይዳ የዲጂታል መታወቂያ የታገዘ የመራጮች ምዝገባ እናደርጋለን " - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ በዛሬው ዕለት በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ቅድመ-ዝግጅትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫው ላይ ሰብሳቢዋ በቀጣዩ ምርጫ ኢትዮጵያ የዲጂታል መታወቂያን በተግባር ለማዋል መታቀዱን አንስተዋል።

በዚህም የመራጮች ምዝገባ በከፊል እንዲሁም የእጩዎች ምዝገባ ሙሉ ለሙሉ በዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) እንደሚከናወን ገልጸዋል።

ይህንንም ለማስቻል ከዚህ ቀደም የነበረው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 ላይ ማሻሻያ ተደርጎበት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መላኩን አስረድተዋል።

ፋይዳ የዲጂታል መታወቂያ በምን መልኩ ነው በቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ተግባራዊ የሚደረገው ?

የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላትወርቅ ፋይዳ መታወቂያ በተሻሻለው አዋጁ ማንነትን የሚገልጽ ሆኖ ተካቷል ብለዋል።

" ምርጫው በፋይዳ ብቻ ነው አይደለም። ፋይዳ አንድ ሰው አንድ ነው የሚለውን ይለይልናል በዛ የታገዘ የመራጮች ምዝገባ እናደርጋለን። ያ የሌለው ደግሞ ከዚህ ቀደም በነበረው ሥርዓት የሚመዘገቡበት ሁኔታ ይኖራል። መራጮች የፋይዳ መታወቂያ ስለሌላቸው ከምዝገባ አይከለከሉም " ሲሉ ነው ያስረዱት።

ወደ ዲጂታል ምዝገባ ስለሚቀየረው የእጩዎች ምዝገባ ምን አሉ ?

ከዚህ ቀደም በምርጫ ክልል ደረጃ የሚሰጠው የእጩዎች ምዝገባ ተቀይሮ ሙሉ ለሙሉ እጩዎች ካሉበት ሆነው ራሳቸውን የሚመዘግቡበት ሥርዓት መዘጋጀቱን ገልጸዋል። ይህም ይወጣ የነበረውን ከፍተኛ ወጪ ያስቀራል ነው ያሉት።

ከዚህ በተጨማሪም የምርጫ አስፈጻሚዎችም በተመሳሳይ መልኩ ኦላይን የሚመዘገቡበት እንዲሁም፤ ኦላይን ፈተና ወስደው ወደ ሥራ የሚገቡበት እንዲሁም ስለመገኘታቸው ሁሉ ማረጋገጫ የሚሰጥ ሥርዓት መበጀቱንም ነው ሰብሳቢዋ ያነሱት።

ክፍያን በተመለከተም ከዚህ ቀደም የነበሩ ክፍያ አልተፈጸመልንም የሚሉ ሰፊ ቅሬታዎችን ሊቀርፍ በሚችልና በፍጥነት ሊከፈልበት የሚችል ሥርዓት ተዘርግቷል ብለዋል።

" ፓርቲዎች አባሎቻቸውንም የሚመዘግቡበት ሶፍትዌር በማዘጋጀት ላይ ነን " ሲሉም የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላትወርቅ ተናግረዋል።

ሁሉም ሶፍትዌሮች በራስ አቅም የተሰሩ መሆናቸውን ፤ ይህም በግዢ ቢሆን ኖሮ ብዙ ገንዘብ ይወጣ እንደነበር ገልጸዋል።

ቦርዱ በሰጠው መግለጫ  በሚቀጥለው ምርጫ በስፋት የቴክኖሎጂ ውጤቶችን እንደሚጠቀም አስረድቷል።

በተጨማሪ ከ50 ሺህ በላይ የሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎችን " XY Coordinates " የመመዝገብ ስራ እየተሰራ መሆኑን የገለጸው ቦርዱ እስካሁን 12 ሺህ የምርጫ ጣቢያዎችን መመዝገባቸውን ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
531😡216🤔102😭38🙏25🕊10👏7😱5🥰2💔2
#ኢትዮጵያ

ለእንጀራ፣ ለዳቦ እና ለተለያዩ የሸቀጥ እቃዎች መጠቅለያነት የሚውለውን የአንድ ብሩን ፕላስቲክ ይዞ መገኘት ከ2,000 እስከ 5,000 ብር የሚያስቀጣው አዋጅ ጸደቀ፡

ማንኛውም ሰው አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል የፕላስቲክ ከረጢት ይዞ ከተገኘ ከ2,000 እስከ 5,000 ብር የሚያስቀጣው አዋጅ ፤ " ዜጎችን በማያውቁት ጉዳይ ለቅጣት የሚዳርግ ነው " የሚል ትችት ከምክር ቤት አባላት ቀርቦበታል፡፡

የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ የጸደቀው የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ አዋጅ ፤ ማንኛውም ሰው አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል የፕላስቲክ ከረጢት ይዞ ከተገኝ ከ2,000 እስከ 5,000 ብር እንዲቀጣ ይደነግጋል፡፡

ያመረተ ወይም ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባ፣ ለገበያ ያቀረበ ወይም የሸጠ፣ ለንግድ ዓላማ ያከማቸ ወይም ይዞ የተገኘ ከ50,000 ብር በማያንስና ከ200,000 ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ እና ከ5 ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት  እንዲቀጣ አዋጁ ያዝዛል፡፡

የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አወቀ አምዛዬ (ዶ/ር) የአዋጁን ይዘት በንባብ ከቀረቡ በኃላ የም/ቤት አባላት ጥያቄ አቅርበዋል።

የምክር ቤት አባሉ አለሙ ጎንፋ (ዶ/ር) ህዝባችን በፕላስቲክ እቃ ይዞ ወደ ቤቱ ከገባ ይጣለው ? ወይስ መልሶ ለአካባቢ ጥበቃ ያስረክበው ? የሚል ጥያቄ ጠይቀዋል።

አክለው የምናመርተው የፕላስቲክ ውጤት ዳግም እንድንጠቀምበት የሚያደርግ ቢሆን አይሻልም ወይ ? ምክንያቱም 10 ጊዜ የምጠቀምበትን ፕላስቲክ አንድ ጊዜ ብቻ ተጠቀም ማለት ተገቢ አይደለም፣ አዋጁ ፕላስቲኩን ከተጠቀምኩበት ወዲያ የት ማስቀመጥ እንዳለበት አላስቀመጠም ብለዋል፡፡

አዋጁ ይዞ የተገኝ እንዲቀጣ ይደነግጋል ህዝባችን የዚህ ግንዛቤ ይኖረዋል ወይ ? የትኛው ፕላስቲክ እንደሆነ የመለየት ግንዛቤስ አለው ወይ ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ሌላ አንድ የምክር ቤት አባል በበኩላቸው ማንኛውም ሰው ፕላስቲክ ይዞ ከተገኘ ከሁለት እስከ አምስት ሺህ ብር እንዲቀጣ ይደነግጋል፤ ይህ ከእኛ ነባራዊ ሁኔታ ጋር  እንዴት ታየ ? በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ያለው የማህበረሰብ ክፍል ሊጠቀመው ስለሚችል ጫና አይፈጥርም ወይ ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ለጥያቄዎቹ ምላሽ የሰጡት የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ  አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አወቀ አምዛዬ(ዶ/ር) ለአንድ ጊዜ ብቻ አገልግሎት ላይ የሚውሉ ፌስታሎችን ዝቅተኛው የማህበረሰብ ክፍልም ስለሚጠቀማቸው ቅጣቱ ያን ግንዛቤ ውስጥ ያስገባ ነው ብለዋል፡፡

" ለምሳሌ አንዲት አሮጊት ወይም ሽማግሌ የሁለት ብር ዳቦ ወይም የአስር ብር ስኳር ገዝተው ሲሄዱ 5 ሺህ ብር ክፍሉ ቢባሉ ላይኖራቸው ስለሚችል ቅጣቱ ከ5 ሺህ ወደ 2 ሺህ ዝቅ እንዲል ተደርጓል ይህም የህብረተሰቡን የመክፈልም አቅም ከግንዛቤ ያስገባ ነው " ሲሉ አስረድተዋል፡፡

" የፕላስቲክ ከረጢቶች ከቅጣቱ በላይ ሀገርን የሚጎዱ ናቸው እስከ መቶ ዓመት ድረስም አይበሰብሱም " ያሉት ምክትል ሰብሳቢው፤ " ከዚህ አንጻር ቅጣቱ ሃያም ሰላሰም ሺህ ቢሆን ሀገርን ለማትረፍ ነው " ብለዋል፡፡

ለህዝቡ ግንዛቤ ለመስጠትም ከመጪው ሃሙስ ጀምሮ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ይካሄዳል ሲሉ አወቀ አምዛዬ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

አዋጁ የፕላስቲክ ጫማዎችን፣ የውሃ ኮዳዎችን እና ወፍራም የፕላስቲክ ውጤቶችን አይጨምርም ተብሏል።

አዋጁ ማንኛውም ሰው ከመኖሪያ ቤቱ ድንበር አንስቶ ከሃያ ሜትር በላይ አካባቢውን የማጽዳት ግዴታንም ያስቀምጣል፡፡

አዋጁ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

#ShegerFM101.2

@tikvahethiopia
😡4.19K1.88K🤔237😭157👏99😢66💔50😱46🕊34🥰27🙏21
#ኢትዮጵያ🇪🇹

ኢትዮጵያ የCFA የምስራቅ አፍሪካ ቻርተርን ተቀላቀለች።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ተዋናዮችን እውቅና (Certification) የሚሰጠው ሲ.ኤፍ.ኤ (CFA) በኢትዮጵያ የፈተና ማዕከል መስጠት የሚያስችለውን ስምምነት አድርጓል።

ከዚህ ቀደም ይህንን ሰርተፊኬት ለማግኘት የሚሰጠውን ፈተና ናይሮቢ ወይም ሌሎች ቻርተሮች ወደ ሚገኙበት መሄድ ይጠበቅባቸው የነበረ ሲሆን ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ቻርተርን መቀላቀሏን ተከትሎ በአዲስ አበባ የመፈተኛ ማዕከል ይኖራል ተብሏል።

በምሥራቅ አፍሪካ ይሄን ሰርተፊኬት ያገኙ ባለሞያዎች ቁጥር ከ600 ቢልቅም በኢትዮጵያ ግን ሰርተፊኬቱን ያገኙት ባለሞያዎች ቁጥር 11 ብቻ ናቸው።

በዚህ መርሐግብር የተገኙት የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሀና ተኸልኩ በዘርፉ ከፍተኛ የሆነ የክክሎትና እውቀት ክፍተት መኖሩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

በCFA እና መሰል ተቋማት የሚሰጡት ትምህርቶችና ሰርተፊኬቶች ክህሎት፤ እውቀት እና ዲሲፕሊን አብሮ የያዙ በመሆኑ ለገቢያው ጠቃሚ እንዲሁም ዓለም አቀፍ እና ወጥ የሆነ የእውቀት ደረጃ እንዲኖር እንደሚያግዝ አስረድተዋል።

በዘርፉ ያለው የሰው ኃይል እና እውቀት ክፍተት ምን ያህል ነው ? ምንስ እየተሰራ ነው? ስንል የጠየቅናቸው ዋና ዳይሬክተሯ " ሰፊ ክፍተት አለ " ሲሉ አመላክተዋል።

ዋና ዳይሬክተሯ በዝርዝር ምን አሉ ?

" የፋይናንስ እና አኮኖሚ ዘርፉን፤ ካፒታል ማርኬትን እንዲሁም በካፒታል ማርኬት ያሉ ህጎችና ደንቦችን ከመረዳት እና የሚፈጠሩ ችግሮችን በአግባቡ የማስተዳደር (Risk management) ላይ ሰፊ ክፍተት አለ።

አሁን ላይ ከfsd ጋር በመተባበር በዘርፉ የሚያስፈልገው የሰው ኃይል አቅም (Human Capital Strategy ) እየሰራን እንገኛለን ወደ መጠናቀቁ ላይ ይገኛል። ይሄ ሲጠናቀቅ ያለው ክፍተት ምንድን ነው፤ የትኞቹ ተቋማት መካፈል አለባቸው የሚለውን ይመልሳል።

ከዚህ በተጨማሪ፤ ባለሥልጣኑ የካፒታል ማርኬት ስልጠና ተቋም እያቋቋመ ነው። አሁን ላይ ከፍ ያለ የስልጠና ማኑዋል በማዘጋጀት ላይ እንገኛለን ይሄ ሲጠናቀቅ ፕሮግራሙን በይፋ አስተዋውቀን ወደ ስልጠና እንገባለ።

CFA ወደ ሀገር ውስጥ የማምጣቱም ሂደት የጥረቱ አካል ነው "
ሲሉ ገልጸዋል።

የዩኤን ዲ ፒ ፋይናንሻል ላብ አማካኝነት በኢትዮጵያ ለሚገኙ የዘርፉ ባለሞያዎች ስፖንሰር ሺፕ እንደሚሰጥም ተገልጿል።

ይህ ስኮላርሺፕ እነማንን ይመለከታል ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዩ ኤን ዲፒ ፋይናንሻል ላብ ዳይሬክተር የሆኑትን ዳግማዊት ሽፈራውን ጠይቋል።

ዳይሬክተሯ በምላሻቸውም፥ ይህ ስኮላርሺፕ በዘርፉ ልምድ ላላቸው የሚሰጥ እንደሆነ የገለጹ ሲሆን፥ ለምን ያህል ሰዎች እንዲሁም የብሩን መጠን ከመግለጽ ግን ተቆጥበዋል።

" በጣም ትጋት የሚፈልግ ነው ። ፈተናውን የማለፍ ምጣኔው 49 በመቶ ነው [Level 3] ለዚህ ደግሞ የውጤቱ መጠን ከፍ ያለ እንዲሆን ልምድ ላላቸው ሰዎች እድሉን እንሰጣለን " ሲሉ ነው ያስረዱን።

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሀና ተኸልኩ ባንኮች፤ ኢንሹራንሶች፤ የመንግስት ተቋማት እንዲሁም የዘርፉ ተዋናዮች ለሰራተኞቻቸው ይህን መሰል ሥልጠና እንዲያመቻቹ ጥሪ አቅርበዋል።

የCFA ሰርተፊኬት ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ገቢያውን ለመቀላቀል የሚረዳ ነው ሲባል ኢትዮጵያ ካፒታል ማርኬትን ማስተዋወቋን ተከትሎ ፍላጎቱ እንደሚጨምር ይታመናል።

ይንንን ሰርተፊኬሽን ለማግኘት ሦስት ደረጃዎች ሲኖሩት ለማጠናቀቅ ከ4100 ዶላር በላይ ይጠይቃል። ከዚህም በላይ 400 የጥናት ሰዓታት በየደረጃው ይፈልጋል ተብሎ ሲገለጽ ፈጣኑ የማጠናቀቂያ ጊዜ 2 ዓመት ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
576👏32🤔19😡17🥰9🙏8😢6🕊4😱3😭2
#ኢትዮጵያ

ወደፊት ለሚቋቋመው “ የአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ” ከመንግስት እና ከግል ተቋማት ሰራተኞች ደመወዝ መዋጮ እንዲሰበሰብ የሚያስገድደው የአዋጅ ድንጋጌ ተሰርዟል።

ዛሬ “የአደጋ ስጋት ስራ አመራር አዋጅ” በፓርላማ ፀድቋል።

ከመንግስት እና ከግል ተቋማት ሰራተኞች ደመወዝ መዋጮ እንዲሰበሰብ የሚያስገድደው የአዋጅ ድንጋጌ በሰራተኞች ላይ “ተደራራቢ ጫና እንዳያስከትል” በሚል ወጥቷል።

ባለፈው መጋቢት ወር መጀመሪያ ለተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ይኸው አዋጅ፤ የመንግስት እና የግል ተቋማት ከሚሰጧቸው 15 አይነት አገልግሎቶች “ለአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ” ገቢ እንዲሰበሰቡ የሚያስገድድ ድንጋጌ በውስጡ ይዞ ነበር።

መረጃው የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ነው።

@tikvahethiopia
549👏186🤔46😡39🙏29🕊14😭9🥰7💔7
#ኢትዮጵያ

የገቢ ግብር ምጣኔ ላይ ማሻሻያ ለማድረግ መንግስት ረቂቅ አዋጅ ማዘጋጀቱን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

ሬድዮ ጣቢያው ከገንዘብ ሚኒስቴር አገኘሁት ባለው መረጃ በደመወዝተኛው ሆነ በንግድ የገቢ ግብር ምጣኔ ላይ ማሻሻያዎችን የያዘ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቷል።

በመጭው ሰኞም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከባለሙያዎች ጋር ለመመካከር ጥሪ ማድረጉ ተሰምቷል።

የኢትዮጵያ ሰራተኞች ኮንፌዴሬሽንና ሌሎችም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለሙያዎች በተለይ ቋሚ ደመወዝተኛው የኑሮ ጫናውን ለመቋቋም እንዲችል የሚቆረጥበት የገቢ ግብር ትርጉም ባለው መልኩ እንዲሻሻልለት ሲጠይቁ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡

ኢትዮጵያን ከጎረቤት ሀገራት ጋር ሲነጻጸር ?

የኢትዮጵያ ብር እና የኬንያ ሽልንግ ከዶላር አንፃር የምንዛሪ ዋጋቸው እኩል ነው፡፡

በኢትዮጵያ  ከ600 ብር  ጀምሮ የሚያገኝ ደመወዝተኛ የገቢ ግብር ይቆረጥበታል፤ በኬንያ  ደግሞ የገቢ ግብር የሚቆረጠው ከ24,000 ብር ደመወዝተኛ ጀምሮ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ደመወዙ 10,900 ብርና ከዚያ በላይ የሆነ ተቀጣሪ 35 በመቶ የገቢ ግብር ሲቆረጥበት፤ በኬንያ ከ800,000 ብር ደመወዝተኛ ጀምሮ ነው 35 በመቶ የገቢ ግብር የሚቆረጥበት፡፡

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia
1.49K👏274😭213🙏96🤔80💔31😡27😱22🥰10🕊9😢6
TIKVAH-ETHIOPIA
" አዲሱ በጀት የኑሮ ውድነትንና የዋጋ ግሽበትን በሚያረጋጉ ስራዎች ላይ መዋል አለበት " - የኢኮኖሚ ባለሙያ ለቀጣዩ አመት 2018 በሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበው የሁለት ትሪሊዮን ብር በጀት ህዝቡን እያስጨነቁ ያሉትን የኑሮ ውድነትና የዋጋ ግሽበት ችግሮችን ለማረጋጋት መዋል እንዳለበት የኢኮኖሚ ባለሙያው ገለፁ፡፡ የኢኮኖሚ ባለሙያውና የፖሊሲ አማካሪው ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ በጉዳዩ ዙርያ…
#ኢትዮጵያ

ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የፌዴራል መንግሥት የ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት 1.93 ትሪሊዮን ብር እንደሆነ ገንዘብ ሚኒስቴር አሳውቋል።

1 ትሪሊዮን ብር ወይም 73 በመቶውን ከታክስ ገቢ ለማግኘት መታቀዱ ተሰምቷል።

የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት በሰጡት ማብራሪያ ከ2018 ረቂቅ በጀት ፦
➡️ 1.2 ትሪሊዮን ብር ለመደበኛ ወጪ፣
➡️ 415 ቢሊዮን ብር ለካፒታል ወጪ፣
➡️ 315 ቢሊዮን ብር ለክልል መንግስታት ድጋፍ
➡️ 14 ቢሊዮን ብር ለክልሎች የዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈፀሚያ ድጋፍ የሚውል እንደሆነ ገልጸዋል።

ከረቂቅ በጀቱ ፦
🔴 1 ትሪሊዮን ብር ወይም 73 በመቶውን ከታክስ ገቢ
🔴 236 ቢሊዮን ብር ከልማት አጋሮች ቀሪውን ደግሞ ከፕሮጀክቶች ድጋፍ እና ልዩ ልዩ ገቢዎች ለማግኘት መታቀዱን ተናግረዋል።

በረቂቅ በጀቱ ከጥቅል ሀገራዊ ምርት አንፃር ያልተጣራ የበጀት ጉድለት 2.2 በመቶ እንዲሁም የተጣራ የበጀት ጉድለት 1 በመቶ መሆኑንም የገንዘብ ሚኒስትሩ አስረድተዋል።

መንግስት የበጀት ጉድለቱን በቀጥታ ከብሔራዊ ባንክ ብድር በመውሰድ ሳይሆን በግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭ እንደሚሸፍን ፤ በ2018 በጀት ዓመት የ8.9 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት እንደሚጠበቅ መናገራቸው ብሔራዊ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

@tikvahethiopia
😭735635😡149🤔49🙏36😱18😢17🕊12💔10