TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#የመውጫፈተና የከፍተኛ ትምህርት ቅድመ ምረቃ መርሃ ግብር ተማሪዎች መውጫ ፈተና ከሰኔ 2 እስከ 10/ 2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል። ተፈታኞች ለፈተና ሲመጡ ብሄራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) መያዝ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል፡፡ የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) " የ2017 የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና ከሰኔ 2 እስከ ሰኔ 10 /2017 ዓ.ም.…
#ExitExam  #Fayda

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ለመውሰድ ዕጩ ተመራቂዎች የፋይዳ መታወቂያ / ብሔራዊ መታወቂያ ሊኖራቸው እንደሚገባ መገለጹ ይታወሳል።

ተፈታኞች በፈተና ወቅት ይዞ መገኘት የሚጠበቅባቸው የፋይዳ መታወቂያ አማራጮችን በተመለከተ የብሔራዊ መታወቂያ አገልግሎት ጽ/ቤት አጭር ማብራሪያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥቷል።

ተፈታኞች የትኞቹን የፋይዳ መታወቂያ አማራጮች መያዝ ይችላሉ ?

- በኢትዮ ቴሌኮም ወይም የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት አማካኝነት የታተሙ የፋይዳ መታወቂያዎችን፤

- ከ "Fayda ID" ሞባይል መተግበሪያ ፣ ከቴሌብር ሱፐር አፕ፣ እንዲሁም ሲቢኢ ብር ሞባይል መተግበሪያ ላይ #QR_ኮድ በማውረድ እና በወረቀት በማሳተም መያዝ ይችላሉ።

የማይፈቀደው ወይም የማይቻለው የቱ ነው ?

📵 ዲጂታል ኮፒ (በስልክ ይዞ መገኘት) አይቻልም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የፈተና ሥርዓቱ ከፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ጋር የተያያዘ መሆኑን ያረጋገጠ ሲሆን ተማሪዎች ከዲጂታል ኮፒ (ከስልክ) ውጪ ሌሎች የፋይዳ መታወቂያ አማራጮችን ይዞ በፈተናው ላይ መገኘት እንደሚችሉ አረጋግጧል።

የፋይዳ ቁጥር ከጠፋብዎ ወይም ካልደረስዎ *9779# ላይ በመደወል በድጋሚ ማስላክ ይችላሉ።

ፎቶ ፦ ተማሪዎች ሊይዙት የሚገባቸው የፋይዳ መታወቂያ አማራጮች ማሳያዎች

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
1.11K😡191😭57🙏52🤔27🕊18👏14🥰12😢10😱6💔5