TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
218 files
4.4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጎጆብሪጅ #ጤናባለሙያዎች

➡️ " ውላችን ይቋረጥ ፣ #ገንዘባችንም_ይመለስልን ብለው የፈረሙ 4,000 ቆጣቢዎች አሉ " - የቤት እጣ ቆጣቢዎች

➡️ " ከጤና ሚኒስቴር፣ ከዳሽን ባንክ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ስላለን ተመካክረን መልስ እንሰጣለን " - ጎጆ ብሪጂ

ከ7 ሺህ 500 በላይ ለሚሆኑ #የጤና_ባለሙያዎች ቤት ገንብቶ ለማስረከብ ከጤና ሚኒስቴር እንዲሁም ከዳሽን ባንክ የሦስትዮሽ ውል የፈረመው ጎጆ ብሪጂ ሀውሲንግ ፦
➡️እጣውን በወቅቱ እያወጣ ባለመሆኑ፣
➡️እጣ የወጣላቸውም ግንባታ ባለመጀመሩ፣ 4,000 ቆጣቢዎች ገንዘባቸው እንዲመለስ ቢጠይቁም እንዳልተመለሰላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

አሁንም ቢሆን ገንዘቡ እንዲመለስላቸው ጠይቀዋል።

የቆጣቢዎቹ ኮሚቴ በጉዳዩ ዙሪያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፥ " በየሶስት ወሩ ለማውጣት እጣው ሳይሰጥ 2 ዙር አልፏል። ለምን ? ተብለው ሲጠየቁ ' #የመሬት_አስተዳደር_ችግር_ስላለብን_ነው ' እያሉ እስካሁን ቆዩ " ብሏል።

" ውላችን ይቋረጥ ፤ ገንዘባችንም ይመለስልን ብለው የፈረሙ 4,000 የቤት ቆጣቢዎች አሉ " ሲል የገለጸው ኮሚቴው በደብዳቤ ጭምር ቢጠይቅም መፍትሄ እንዳልተሰጠው አስረድቷል።

ለተነሳው የቤቶች እጣ መዘግየት ቅሬታ በ ' ጎጆ ብሪጅ ሃውሲንግ ' በኩል ምላሽ እንዲሰጡን የተጠየቁት አቶ አልማው ጋሪ ፤ " የገጠመን ችግር በአደረጃጀት ላይ #መዘግየቶች ስለነበሩ ነው " ብለዋል።

" የሚያደራጀው የአዲስ አበባ ህብረት ሥራ ኮሚሽን የሚባለው ነው " ያሉት አቶ አልማው፣ " ሌላ ሳይት ላይ በተፈጠረ ክስ ትንሽ ሥራው ስለቆመ እስኪ ውጤቱን እንየው የሚል ሀሳብ ተነስቶ ስለነበረ የመዘግየት ጉዳይ አጋጥሟል " ነው ያሉት።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ የቤት ቆጣቢዎቹ ከጠየቁ ለምን ገንዘባቸውን አልመለሳችሁም ? ሲል ላቀረበው ጥያቄ ፣ " ውሉ የሚያስቀምጣቸው ብዙ ነገሮች አሉ። ይህን ደግሞ ለብቻችን ሳይሆን ከጤና ሚኒስቴርም ከዳሽን ባንክም ጋር የመግባቢያ ሰነድ ስላለን ተመካክረን መልስ እንሰጣለን " ብለዋል።

" የመጀመሪያው እጣ ማውጣት ተደርሶ ወደ 300 ሰዎች እጣ የደረሳቸው አሉ። እነርሱን ለማደራጀት በሂደት ላይ ነው ያለነው " ያሉት አቶ አልማው " አንዳንዶች ደግሞ ቅሬታ አላቸው እየመጡ ይጠይቃሉ " ሲሉ ተናግረዋል።

" የቅሬታ አቅራቢዎቹን ጉዳይም ባለፈው ሳምንት ጤና ሚኒስቴር የተቋማት ተወካዮች በተገኙበት ውይይት ተደርጎ አቀረቡ አቅጣጫ ተቀምጧል። ምናልባት በዚህ ሳምንት አንድ ደረጃ ላይ ይደርሳል " ብለዋል።

#TikvahEthinpiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
311😡119😢61😱48🙏45🕊42🤔32😭32👏30🥰14
TIKVAH-ETHIOPIA
" በ10 ሺህ ብር ዋስ ከእስር ተፈተዋል " - ቤተሰቦች ከቀናት በፊት ከሰሞነኛዉ የጤና ባለሙያዎች እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እና ከአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ተወስደዉ ታስረዉ የነበሩ 3 ዶክተሮች በ10 ሺህ ብር ዋስ ከእስር መፈታታቸዉን ቤተሰቦቻቸዉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል። " ባሳለፍነዉ ዐርብ ዕለት ' ለስብሰባ ትፈለጋላችሁ ' ተብለዉ በተወሰዱበት ነዉ እንዲታሰሩ የተደረገዉ…
🔈#የጤና_ባለሙያዎች

የጤና ባለሙያዎች ከዚህ ቀደም እስከ ግንቦት 3/2017 ዓ/ም ድረስ ለጠየቁት ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጣቸው ያ ካልሆነ በከፊል ስራ ለማቆም እንደሚገደዱ በጻፉት ደብዳቤ አሳውቀው ነበር።

በዚህም ዛሬ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ባሉ የጤና ተቋማት ወደ ስራ ያልገቡ እንዳሉ ይህም በመሆኑ ተቋማቱ ወደ ስራ እንዲመለሱ ማስጠንቀቂያ ሲለጥፉ እንደነበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

" ጥያቄዎቻችን ምላሽ አልተሰጣቸውም " በማለት ስራ ያልገቡ ባለሙያዎች እስከ ግንቦት 9 ይቆያል ያሉት ከፊል የስራ ማቆም እንቅስቃሴ ፦
- የአዋቂ የድንገተኛ ህክምና ክፍል
- የህፃናት ድንገተኛ ክፍል
- ከድንገተኛ ክፍል ጋር ተያይዘው የሚሰጡ አገልግሎቶች እነዚህም የድንገተኛ ክፍል መድሃኒት ቤት እና ላቦራቶሪ
- የማዋለጃ ክፍል
- ፅኑ ህሙማን ክፍል (የጨቅላ እና የአዋቂዎች)
- የድንገተኛ ቀዶ ህክምና ክፍል የሚሰሩትን አይመለከትም ሲሉ ተናግረዋል።

" ከግንቦት 10 በኃለ ግን ምላሽ ካልተሰጠን ሙሉ በሙሉ እናቆማለን " ሲሉም ገልጸዋል።

" የእኛ እንቅስቃሴ አንዳችም የፖለቲካ ሆነ ከፖለቲከኞች ጋር የሚያይዘ አይደለም። ታዋቂም ሰዎች ሆኑ ማንኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ የሚያራምዱ ሰዎችም እጃቸውን እንዲያነሱ ደጋግመን አሳስበናል። ሀገራችንን ህዝባችንን እንወዳለን ሰላምም እንድትሆን ነው የምንፈልገው ነገር ግን ዓመታት ያለፋቸው ጥያቄዎች መልስ ይሰጥባቸው ፤ ሁሌ ሽንገላና ማታለያ ይቁም " ብለዋል።

ጤና ባለሙያዎቹ ፥ " ያሉብን ዘርፈ ብዙ ችግሮች በግልጽ ይታወቃሉ መፍትሄው ላይ ቁጭ ብለን እንነጋገርባቸውና ቁርጥ ያለ ዘላቂ መፍትሄ ይሰጠን። ቢመረን ፤ ኑሮውም ከአቅማችን በላይ ቢሆንብን ፣ ቤተሰብ ማስተዳደር ቀርቶ ጭራሽ ሸክም ወደመሆን በመሸጋገራችን ፤ ድካማችንን እንቅፍል ማጣታችንን የሚመጥን ነገር ሳናገኝ በመቅረታችን ነው እጅጉንም ቢከፋን ቢመረን ነው ወደዚህ እንቅስቃሴ የገባነው እንጂ ለማንም የፖለቲካ አጀንዳ ማራመጃ ለዩትዩብና ሚዲያ መነገጃ ለመሆን አይደለም። በእኛ ስም ፖለቲካ ለሚነግዱትም ተውን በለን ነገራቸዋል " ሲሉ አክለዋል።

ጤና ባለሙያዎቹ " ያሉብንን ችግሮች በይፋ ደጋግመን ጠይቀን ምላሽ ለመስጠት እስካሁን ድረስ ብቅ ያለ አካል የለም " ሲሉ ተናግረው አሁንም ጥያቄዎቻችንን በድጋሚ እናቀርባለን ሲሉ ገልጸዋል።

" ለጤና ሚኒስቴር ያቀረብናቸው ጥያቄዎቻችን ፦

1. የኢትዮጽያ ጤና ሚኒስቴር ዘመኑን በማይዋጅ አሰራር እየበዘበዘን ነው። የደመወዝ ክፍያን ከምስራቅ አፍሪቃ ሃገራት ተሞክሮ በመነሳት በአማካይ 1000$ (አንድ ሺ ዶላር) በወር ክፍያ ይጀምርልን። የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) በሚያስቀምጠው ምክረ ሃሳብ መሰረት የስራ ሰዓት 45 ሰዓት በሳምንት ይገደብ ከዛ በላይ ለሆነውም ተመጣጣኝ የትርፍ ሰዓት ክፍያ ይፈጸም።

2. ጤና ሚኒስቴር ለእኛ ለባለሙያዎቹ ተገቢውን የሆነ የቤት ኪራይ ፣ የተጋላጭነት እንዲሁም የማበረታቻ አበል ላይ አስቸኳይ ማስተካከያ ያድረግልን። በሥራ ላይ ሳሉ በበሽታ ለተጠቁ ባለሙያዎች ደግሞ ተጨማሪ ካሳ ይስጥልን።

3. እንደማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ በመታወቂያችን የነጻ ትራስፖርት ተጠቃሚ እንሁን አልያም ገበያውን ያማከለ የትራንስፖርት አበል ይታሰብልን። እንዲሁም ባለሙያው ከቀረጥ ነፃ መኪና አስገብቶ እንዲገለገል ጤና ሚኒስቴር መንግስትን ይጠይቅልን።

4. የትርፍ ሰዐት ክፍያ በሁሉም ጤና ተቋማት ላይ ህግን መሰረት አድርጎ በተመሳሳይ ይሰራ፤ ጊዜውን ጠብቆም ይከፈለን። ክፍያ ከዓመት በላይ በማዘግየት ጤና ባለሞያውን የሚበድሉ ተቋማት ላይ አስቸኳይ እርምጃ ይወሰድ።

5. መብታችንን እንዲሁም የሰራንበትን ዋጋ እንዳንጠይቅ በማሰር፣ በማሰቃየት፣ በማሸማቀቅ እና በማስፈራራት ከህግ አግባብ ውጪ በሆነ መልኩ ባለሙያን ለእንግልት እየዳረጉ ያሉ የጤና ተቋማት እና የመንግስት ሃላፊዎች ላይ ምርመራ ተካሂዶ ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰደ ጤና ሚኒስቴር ኃላፊነቱን ይወጣልን።

6. ጤና ሚኒስቴር ለሁሉም የጤና ባለሙያዎች እና ቤተሰቦቻችን በሁሉም የመንግስትም ሆነ የግል የጤና ተቋማት ላይ የነፃ ሕክምና አገልግሎት ያስጀምር። ውጪ ሄደው መታከም ላለባቸው ባለሙያዎችም ግማሽ ወጪ ይሸፍን የኑሮ ግሽበትን ያማከለ ድጋፍ ያድርግልን።

7. ባለሙያዎች በሚስሩበት አካባቢ የቤት ወይም የማህበር መስርያ ቦታ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አልያም በረጅም ግዜ ክፍያ ቤት የሚገዙበትን መንገድ ይመቻች።

8. ሚኒስቴሩ በስራ ቦታቸን ላይ ሰላማዊ መስተጋብር እና ደህንነቱ የተጠበቀ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲሁም የስራ አካባቢ እንዲፈጠር፣ በምንም መልኩ አግባብነት የሌለውን የጤና ባለሙያዎች ሞትንም እምርሮ ይታገልም መመርያም አውጥቶ ተፈፃሚነቱን ይከታተል።

9. የህክምና እውቀቱ ሆነ ሙያው በሌላቸው የሚዲያ ሰዎች በባለሙያው ላይ በሚነሱ አሉባልታና የሐሰት ክሶች ምክንያት ማህበረሰባችን በጤና ባለሙያ ላይ ያለውን እምነት እንዲሸረሸር ተደርጓል። እንዲህ ያለውን ግድየለሽ ተግባር የሚፈፅሙና ማስረጃ የሌለው የሐሰት ዜና የሚያሰራጩ ሰዎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ይደረግ።

10. እኛ ባለሙያዎች ለአለምአቀፍ ገበያ ብቁነታችንን የምናረጋግጥበት ዓለም አቀፍ የፈተና ማዕከላት / USMLE EXAM CENTER, NCLEX EXAM CENTER, PLAB, DHA, AMC / ከዓመት በፊት ቃል በተገባልን መሰረት ጤና ሚኒስቴር በሀገር ውስጥ ያቋቋምልን።

11. በሁሉም ጤና ተቋማት ላይ የሚታየው የአመራር ምርጫ በሹመት መሆኑ ከጤናው ዘርፍ የማይጠበቅ በመሆኑ ይሄ አሰራር አስቀርታቹ በእውቀት እና በውድድር እንዲሆን አድርጉት ፤ አሰራሩንም አዘምኑት።

12. የህክምና ዘርፍ ከሲቪል ሰርቪስ ማዕቀፍ እንዲወጣ በማድረግ ውስናችሁ አሳውቁን ፤ እራሱን ችሎ በቦርድ እንዲተዳደር ኃላፊነታችሁን ተወጡልን።

የሚሉ ናቸው " ብለዋል።

ጤና ሚኒስቴር ለተጠየቁት ለእነዚህ ግልጽ የሆኑ ጥያቄዎች ዙሪያ ጥምጥም መሄድ ሳያስፈልገው 1... 2 ... 3 እያለ በግልጽ ይመልሳቸው ሲሉ አክለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎቹ ላነሷቸው ጥያቄዎች ከጤና ሚኒስቴር በኩል ማብራሪያ ካገኘ ይዞ ይቀርባል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
1.67K👏421🙏57🤔23😡23😢22🥰13🕊13😭12💔6😱5
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
🔈 #የጤና_ባለሙያዎች

ደሴ በሚገኘው ቦሩ ሜዳ አጠቃላይ ሆስፒታል  ከታሰሩ የጤና ባለሙያዎች መካከል 3ቱ እስካሁን አለመለቀቃቸው የስራ ባልደረቦቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለፁ።

ከ3 ቀን በፊት መፈክሮችን በመያዝ በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ ቅሬታቸውን ለማሰማት ከወጡት ከ10 በላይ የሚሆኑ ጤና ባለሙያዎች በፀጥታ ሀይሎች ተወስደው የነበረ ሲሆን ሌሎቹ ሲለቀቁ 3ቱ ግን እስካሁን አልተለቀቁም ሲሉ የስራ ባልደረቦቻቸው ተናግረዋል።

" የታሰሩት ባለሙያዎች እንደ ማንኛውም ሀኪም ያለውን ቅሬታ በሰላማዊ መንገድ ያቀረቡ እንጂ ምንም አይነት የፖለቲካ ተሳትፎ የሌላቸው ናቸው " ሲሉ ነው የገለጹት።

" በትላንትናው እለት እነሱን ለማስለቀቅ ሁሉም ሀኪም በስራ ገበታው ላይ ቢውልም  ሀኪሞቹ ግን ሊለቀቁ ባለመቻሉ ዛሬ አብዛኛው ሀኪም የስራ ማቆም አድማውን ቀጥሏል " ሲሉ አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ሀኪም ተናግረዋል።

በሌላ በኩል፥ ማዕከላዊ ጎንደር ዞን በሚገኘው የአብርሃ ጅራ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎች  በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ ብዛት ያለው የፀጥታ ሀይል በመኖሩ እንዲሁም ማስፈራሪያም በመሰጠቱ በፍርሃት በስራ ገበታቸው ላይ እንደሚገኙ ተናገረዋል።

በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ከድንገተኛ ፣ ህፃናት ቀዶ ህክምና እና ተኝተው የሚታከሙ ህመምተኞችን ከሚከታተሉ ሀኪሞች ውጭ ሌሎች በከፊል የስራ ማቆም አድማ ላይ እንደሆኑ ለመረዳት ተችሏል።

በተያያዘ መረጃ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎችም ላይ " ለዓመታት የጠየቅናቸውን ጥያቄዎች አሁንም በዝርዝር ገልጸን ያቀረብናቸውን ጥያቄዎች የሚመለስ አልተገኘም " በሚል ዛሬም በስራ ገበታቸው ላይ ያልተገኙ የጤና ባለሙያዎች አሉ።

ከዚህ የጤና ባለሙያዎች እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘም ለእስር የተዳረጉ እንዳሉ ለመረዳትም ተችሏል።

ሆስፒታሎችም በስራ ገበታቸው ላይ ያልተገኙ የጤና ባለሙያዎች ወደ ስራቸው እንዲመለሱ የሚያስጠነቅቁ ማስታወቂያዎችን እያወጡ ናቸው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyBahirDar
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😢500😡11270🙏18💔17🕊15😭11🥰4🤔4