TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
እንኳን ለ84ኛው የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች የድል በዓል (የድል ቀን) አደረሳችሁ ! ክብር ለጀግኖች አርበኞቻችን ይሁን🙏 @tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ🇪🇹

ዛሬ 84ኛው ዓመት የኢትዮጵያውያን አርበኞች የድል በዓል እየተከበረ ይገኛል።

የአርበኞች የድል በዓል ለምን ይከበራል ?


ጣሊያን የዓድዋን ድል ለመበቀል በሚል በጊዜው ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቤኒቶ ሙሶሎኒ አማካኝነት፥ ከ1928 እስከ 1933 ዓ.ም ድረስ ኢትዮጵያን ወራ ነበር።

በወቅቱ የነበሩት ኢትዮጵያውያንም ወራሪውን ሀይል ለአምስት ዓመታት በጽናት ታግለው 1933 ዓ.ም ድል ነስተውታል።

የወቅቱ አርበኞቻችን ለሀገራቸው ነጻነት የከፈሉትን መስዋዕትነት እና ያስገኙትን ድል ለማሰብ ነው በየአመቱ ሚያዚያ 27 የኢትዮጵያ አርበኞች የድል በዓል የሚከበረው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
እንኳን አደረሳችሁ !

ፎቶ ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ

@tikvahethiopia
1.45K👏159🕊48🥰46😡22🙏20😭20🤔19😱12😢10
#ATTENTION🚨

ከዛሬ ግንቦት 6 / 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት የኩፍኝ ክትባት ይሰጣል።

ወላጆች ልጆቻችሁን አስከትቡ።

ኩፍኝ ምንድነው ?

የኩፍኝ በሽታ የኩፍኝ ቫይረስ በሚባል ረቂቅ ተህዋስ የሚከሰትና በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው የሚዛመት የበሽታ ዓይነት ነው፡፡ የኩፍኝ በሽታ ለብዙ ህጻናት ህመም፣ የአካል ጉዳትና ሞት ምክንያት ከሆኑት በሽታዎች አንዱ ነው፡፡

የበሽታው መተላለፊያ መንገዶች ምንድናቸው ?

➡️ ኩፍኝ በሽታ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው የኩፍኝ በሽታ ከተያዘው ሰው አፍንጫና ጉሮሮ በሚወጡ ፈሳሽና ጠብታዎች ንክኪና በትንፋሽ አማካኝነት ነው፡፡

➡️ የኩፍኝ በሽታ አምጭ ተህዋስ ወይም ቫይረስ በኩፍኝ ከተያዘዉ ሰዉ በከፍተኛ ሁኔታ የመሰራጨት አቅም የሚኖረው የበሽታው ምልክቶች መታየት በሚጀምርበት ወቅት ነው፡፡

➡️ አንድ በኩፍኝ የተያዘ ሰው በአብዛኛው ጊዜ ቫይረሱ ወደ ሰውነቱ ከገባ በኋላ የሽፍታ ምልክቶች በሰውነቱ ከመውጣቱ ከ4 ቀናት በፊት እንዲሁም ሽፍታዎቹ ከወጡ በኋላ እስከ 4 ቀን ድረስ ባለው ጊዜ በሽታውን ወደ ሌሎች ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ ያስተላልፋል፡፡

➡️ ህጻናት በሚሰባሰቡበት ቦታ ማለትም በትምህርት ቤቶች፣ በጤና ተቋማት እና በሌሎችም ቦታዎች በሽታው በቀላሉ ሊዛመት ይችላል፡፡

የበሽታው ዋና ዋና ምልክቶች ምንድናቸው ?

- ከፍተኛ ትኩሳት፣
- ከራስ ፀጉር ጀምሮ ወደ ሌሎች የሰውነት፣ ክፍሎች የሚዛመት ሽፍታ፣
- የአይን መደፍረስ ወይም መቅላት፣
- ከአፍንጫ የሚወጣ ፈሳሽ መብዛት፣
- የአይን እንባ ማዘል፣
- ሳል እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

ስላ ኩፍኝ መከላከያ ክትባት ፦ የኩፍኝ መከላከያ ክትባት ህፃናት ከተወለዱ በ9 እና በ15 ወር ዕድሜያቸው በመደበኛው የክትባት አገልግሎት ይሰጣል፡፡

በተጨማሪም የኩፍኝ ክትባት የህፃናትን በሽታ የመከላከል አቅም ለማዳበር በተለያዩ ጊዜያት በዘመቻ ይሰጣል፡፡

የኩፍኝ በሽታን በዘላቂነት መከላከል የሚቻለው ህፃናትን በመደበኛ የክትባት መርሐግብር እና በዘመቻ መልክ የሚሰጠውን የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባትን ማስከተብ ሲቻል ነው፡፡

ልጅዎትን ያስከትቡ !!
#ኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
😡235150🙏34🤔25🥰9🕊8😭8😢1