TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba

" በ3 ወራት ውስጥ 943 ፍቺዎች እንዲሁም 53 ውሳኔ የተሰጠባቸው ጉዲፈቻዎች ምዝገባ ተከናውኗል !! "

የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከፌደራል የመጀመርያ ፍርድ ቤት ጋር  የፍቺ እና ጉዲፈቻ ውሳኔዎችን መዝግቦ በአንድ መስኮት አገልግሎት ለመስጠት የጋራ ስምምነት ፈጽመው እየሰሩ ሲሆን ላለፉት 3 ወራት ውስጥ የተሰሩ ስራዎችን አፈፃፀም በጋራ ገምግመዋል።

በዚህም ወቅት በቀረበ ሰነድ 996 ተገልጋዮች በ3 ወራት የኩነት ምዝገባ አገልግሎቱን በፍርድ ቤቶች በአንድ መስኮት ማግኘታቸው ተመላክቷል።

ከዚህም ውስጥ ውሳኔ ያገኙ 943
#ፍቺዎች እንዲሁም 53 ውሳኔ የተሰጠባቸው #ጉዲፈቻዎች በወቅቱ ምዝገባ በማድረግ በአንድ ማዕከል በፍ/ቤቶች አገልግሎት መሰጠቱ ተመላክቷል።

Via
https://tttttt.me/addisvaitalpress/9155

@tikvahethiopia
😭36472😱28🤔26🕊16💔14👏12🥰11😢9🙏4
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ 1,735 የንግድ ቤቶች ለጨረታ ቀረቡ።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በተለያዩ ክ/ከተሞች ተገንብተው በተጠናቀዉ የ40/60 የጋራ ህንጻዎች ላይ የሚገኙ 1,735 የንግድ ቤቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ለማስተላለፍ እንደሚፈልግ አሳውቋል።

ኮርፖሬሽኑ ለጨረታ ያቀረባቸውን የ40/60 ንግድ ቤቶች ተወዳድሮ መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከሚያዝያ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 21 የሥራ ቀናት (ቅዳሜን ሙሉ ቀን ጨምሮ) ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ምሽት 11:30 ድረስ በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 1000.00 / አንድ ሺህ በመክፈል መግዛት ይችላል ተብሏል።

የጨረታ ሰነድ የሚሸጥባቸው ስፍራዎች የት ናቸው ?

- ቂርቆስ ክ/ከተማ አስተዳደር ፅ/ቤት (ባምቢስ አካባቢ)
- የካ ክ/ከተማ አስተዳደር ፅ/ቤት (መገናኛ)
- አራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ፅ/ቤት (አራት ኪሎ)
- አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ፅ/ቤት (ቃሊቲ መናኸሪያ ፊት ለፊት)
- አ/አ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ቅ/ጽ/ቤት (40/60 በሻሌ ሳይት ብሎክ 13)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
🤔168118😭33🙏25😱24😡19👏17🕊14🥰12💔10😢6