TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba

" በ3 ወራት ውስጥ 943 ፍቺዎች እንዲሁም 53 ውሳኔ የተሰጠባቸው ጉዲፈቻዎች ምዝገባ ተከናውኗል !! "

የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከፌደራል የመጀመርያ ፍርድ ቤት ጋር  የፍቺ እና ጉዲፈቻ ውሳኔዎችን መዝግቦ በአንድ መስኮት አገልግሎት ለመስጠት የጋራ ስምምነት ፈጽመው እየሰሩ ሲሆን ላለፉት 3 ወራት ውስጥ የተሰሩ ስራዎችን አፈፃፀም በጋራ ገምግመዋል።

በዚህም ወቅት በቀረበ ሰነድ 996 ተገልጋዮች በ3 ወራት የኩነት ምዝገባ አገልግሎቱን በፍርድ ቤቶች በአንድ መስኮት ማግኘታቸው ተመላክቷል።

ከዚህም ውስጥ ውሳኔ ያገኙ 943
#ፍቺዎች እንዲሁም 53 ውሳኔ የተሰጠባቸው #ጉዲፈቻዎች በወቅቱ ምዝገባ በማድረግ በአንድ ማዕከል በፍ/ቤቶች አገልግሎት መሰጠቱ ተመላክቷል።

Via
https://tttttt.me/addisvaitalpress/9155

@tikvahethiopia
😭36472😱28🤔26🕊16💔14👏12🥰11😢9🙏4