TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢትዮጵያ2017

እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሰን !

ፈጣሪ አዲሱን ዓመት ፦
- የሰላም
- የፍቅር
- የአንድነት
- ከተፈጥሮ ውጭ የሆነ የሰው ልጅ ሞት የማንሰማበት
- ደመ የማይፈስበት
- ሰው ታገተ፣ ተገደለ፣ ታፈነ የሚል ቅስምን ሰባሪ ዜና የማንሰማበት
- በመላ ሀገሪቱ ፍጹም እርጋታ ያለበት
- እናት የማታለቅስበት
- ሰው ወጥቶ ቀረ የማይባልበት
- ፍትሕ ለተነፈጉ ሁሉ ፍትህ የሚሰፍንበት
- ፍትሕ አጥተው የሚያነቡ ፍትሕ አግኝተው እንባቸው የሚታበስበት
- እየፈተነን ያለው የኑሮ ጫና መፍትሄ የሚያገኝበት
- በሰላም በነጻነት ያሻን ቦታ ወጥተን የምንገባበት
- በሁላችንም ዘንድ የማያስማሙን ጉዳዮች መፍትሄ የሚያገኙበት
- እርስ በእርስ ልክ እንደጠላት የማንተያይበት ፣ የማንሰዳደብበት
- እሮሮ፣ ስቃይ በደል የማንሰማበት
- ያዘንን ተስፋ የቆረጥን ፤ የምንጽናናበት ተስፋ የምናደርግበት
- ሰራተኞች ፣ ተማሪዎች ፍጹም የተሳካ ዓመት የሚያሳልፉበት
- ከምንም በላይ በሀገራችን የትኛውም ቦታ ሰላም ተረጋግጦ ፣ ስምምነት መጥቶ በሀገራችን ፍጹም ደስታ የምናገኝበት
- ሁሉም በአንድ መንፈስ ለእናት ሀገሩ " አለሁልሽ " ብሎ የሚቆምበት ያደርግል ዘንድ #ቲክቫህ_ኢትዮጵያ ይመኛል።

ፈጣሪ ምኞታችንን ያሳካልን !

መልካም አዲስ ዓመት !
ከዓመት ዓመት ያደረሰን ፈጣሪ ቀጣዩን እንድናይ ይርዳን !
ለሁላችሁም ረጅም እድሜን ከጤና ጋር እንመኛለን !

#TikvahEthiopiaFamily
#ቲክቫህኢትዮጵያቤተሰቦች

@tikvahethiopia
4.72K🙏1.26K🕊269👏154🥰116😡59😢51🤔49😭48😱28
TIKVAH-ETHIOPIA
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 ትምህርት ዘመን መደበኛ ትምህርት ነገ ሰኞ መስከረም 6 ቀን 2017 ዓ/ም እንደሚጀምር የከተማው ትምህርት ቢሮ ገልጿል። @tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ2017

ዛሬ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የ2017 የትምህርት ዘመን ተጀምሯል።

በመዲናችን አዲስ አበባ በሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ትምህርት ተጀምሯል።

በተለያዩ የክልል ከተሞችም የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተጀምሯል።

@tikvahethiopia
335😡91😭61👏42🕊32🙏25😢18🤔17😱12🥰8