TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
218 files
4.4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ትግራይን ዳግም ወደ ጦርነት የሚያስገባ ተጨባጭ ስጋት አለ ? " ይሄ የአንድ ድርጅት ጉዳይ ነው። ወደ ጦርነት የሚያስገባ ምንም ነገር የለም " - አቶ አማኑኤል አሰፋ በሊቀ - መንበሩ ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የ14ኛው የህወሓት ጉባኤ ቃል አቀባይ አማኑኤል አሰፋ ፤ አሁን ባለው ሁኔታ ወደ ጦርነት የሚያስገባ ነገር የለም ብለዋል። አቶ አማኑኤል ፥ " በአንድ አዳራሽ ውስጥ ገብቶ…
#TPLF

በሊቀመንበሩ ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የተመራው የህወሓት ጉባኤ አቶ ጌታቸው ረዳን ከምክትል ሊቀመንበርነት አነሳ።

ዶ/ር ደብረጽዮን በድጋሚ ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸው ተነግሯል።

በአቶ ጌታቸው ረዳ ምትክ አቶ አማኑኤል አሰፋ ምክትል ሊመንበር ሆነው ተመርጠዋል።

ሌሎች የስራ አስፈጻሚና የማእከላይ ኮሚቴ ሆነው የተመረጡ የድርጅቱ አባላት ከላይ ስማቸው ተያይዟል።

ምርጫ ቦርድ ከጉባኤው ቀደም ብሎ የቦርዱን አሰራር ያልተከተለ ጠቅላላ ጉባኤ እና በጉባኤው የሚተላለፉ ማንኛውም ውሳኔዎች ተቀባይነት እንደማይኖረው አሳውቆ ነበር።

@tikvahethiopia
🤔1.68K👏391330😡280🕊151🙏82😢70😭68😱50🥰38
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF በሊቀመንበሩ ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የተመራው የህወሓት ጉባኤ አቶ ጌታቸው ረዳን ከምክትል ሊቀመንበርነት አነሳ። ዶ/ር ደብረጽዮን በድጋሚ ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸው ተነግሯል። በአቶ ጌታቸው ረዳ ምትክ አቶ አማኑኤል አሰፋ ምክትል ሊመንበር ሆነው ተመርጠዋል። ሌሎች የስራ አስፈጻሚና የማእከላይ ኮሚቴ ሆነው የተመረጡ የድርጅቱ አባላት ከላይ ስማቸው ተያይዟል። ምርጫ ቦርድ ከጉባኤው ቀደም…
#TPLF

በሊቀ-መንበር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በተመራውና ለ7 ቀናት በቆየው የህወሓት 14ኛው ጉባኤ አዳዲስ የቁጥጥር ኮሚሽን አባላት ተመርጠዋል።

የኮሚሽኑ ሊቀመንበር እና ጉባኤውን ሲቃወሙ የቆዩትን አቶ ተኽለብርሃን ኣርኣያ ተነስተው አቶ ገብረ ካሕሳይ ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል።

አሁን ከሊቀመንበር ቦታቸው ተነስተው በአቶ ገብረ የተተኩት አቶ ተኽለብርሃን ይመሩት የነበረው የቁጥጥር ኮሚሽን ፤ የቁጥጥር ኮሚሽን ፥ " ጤናማ ያልሆነ ሂደት ውጤታማና መልካም ጉባኤ መፍጠር ስለማይችል የሚያስከትለው አደጋ የከፋ ነው " በማለት ከጉባኤው ራሱን ማግለሉን ይታወሳል።

በሌላ በኩል ፥ በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የተመራው የህወሓት ጉባኤ ፤ በጉባኤው ላይ ያልተሳተፉ አባላትን አግዷል።

" ጉባኤው እንዳይካሄድ እንቅፋት ፈጥሯል " ያለውን ቡድን ነው ያገደው።

ያታገዱት አባላት ጥያቄቸውን በጹሁፍ የሚያቀርቡ ከሆነ ወደ አባልነታቸው ሊመለሱ ይችላሉ ብሏል።

ቀደም ብሎ የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ ያሉበት 14 የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ጉባኤውን እንደማይሳተፉ ማሳወቃቸው ፤ የቁጥጥር ኮሚሽን አባላትም ራሳቸውን ማግለላቸው ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
🤔196138😡42👏40🕊35😭12🥰6😱5🙏5😢4
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF በሊቀመንበሩ ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የተመራው የህወሓት ጉባኤ አቶ ጌታቸው ረዳን ከምክትል ሊቀመንበርነት አነሳ። ዶ/ር ደብረጽዮን በድጋሚ ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸው ተነግሯል። በአቶ ጌታቸው ረዳ ምትክ አቶ አማኑኤል አሰፋ ምክትል ሊመንበር ሆነው ተመርጠዋል። ሌሎች የስራ አስፈጻሚና የማእከላይ ኮሚቴ ሆነው የተመረጡ የድርጅቱ አባላት ከላይ ስማቸው ተያይዟል። ምርጫ ቦርድ ከጉባኤው ቀደም…
#TPLF #Tigray

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን ለመምራት ህወሓት " የራሱን ሰዎች መመደብ ይችላል " ሲሉ የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ተናገሩ።

አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመሩት ቡድን " አሁን ህወሓትን መወከል አይችልም ” ብለዋል።

ሊቀመንበሩ ፤ አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙበት ትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር " ህወሓትን ወክሎ ነው የገባው። አሁን ህወሓትን መወከል አይችልም " ሲሉ ተናግረዋል።

በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር " የህወሓት ሰዎች መመደብ አለባቸው " ብለው በጉዳዩ ላይ ጊዜያዊ አስተዳደሩን " ካቋቋሙ ወገኖች ጋር ውይይት ያስፈልጋል " ብለዋል።

በጊዜያዊ አስተዳደሩ ውስጥ ከህወሓት በተጨማሪ የትግ ራይ ሠራዊት፣ ምሁራን እና ተቃዋሚው ባይቶና ድርሻ አላቸው።

በጉዳዩ ዙሪያ ከፌድራሉ መንግስት ጋር ውይይት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ጠቁመው ፥ " እኛ ትግራይ ውስጥ ብቻ የምንጨርሰው አይደለም" ሲሉ ተናግረዋል።

ከሰሞኑን ህወሓት " የድርጅቱን አመራሮች የከፋፈለ ነው " የተባለለትን 14ኛ ጠቅላላ ጉባኤ አድርጎ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤልን በድጋሚ ሊቀመንበር አድርጎ መምረጡ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑትን አቶ ጌታቸው ረዳን በማንሳት አቶ አማኑኤል አሰፋን እንዲሁም ሌሎችንም አዳዲስ የማዕከላዊና የስራ አስፈጻሚዎችን መምረጡ ይታወቃል።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግን ቀደም ብሎ ጉባኤው ሳይጀመር የቦርዱን አሰራር ላልተከተለ ጉባኤ እና በጉባኤው ለሚተላለፉ ማንኛውም ውሳኔዎችና ለውጦች እውቅና እንደማይሰጥ በይፋ አሳውቋል።

#TPLF #EthiopiaInsider

@tikvahethiopia
😭388😡208201👏114🕊81🤔71😱26🥰25😢24🙏17
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የትግራይ ጊዜያዊ አስተደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የስልጣን ሽምሹር አደረጉ። ፕሬዜዳንቱ በህወሓት የፓሊት ቢሮ አባልዋ ወ/ሮ ሊያ ካሳ ምትክ ፀጋይ ገብረተኽለ ገ/ክርስቶስ የደቡባዊ ምስራቅ ዞን አስተዳዳሪ በማድረግ ሾመዋል። በአቶ ጌታቸው ረዳ ተፈርሞ ነሃሴ 14/2016 ዓ.ም የወጣው ደብዳቤ ፤ ፀጋይ ገብረተኽለ የዞኑ አስተዳዳሪ በመሆን የሚገባቸው ጥቅም ተጠብቆላቸው ሃላፊነቱን በአግባቡ…
#TPLF #Tigray

በእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ማንኛውም አይነት የስልጣን ሹምሽር አልቀበልም አለ።

በእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት " በማንኛው የሃላፊነት እርከን በራስ ፍላጎት የሚደረግ የስራ ምደባና ሹምሽር ተቀባይነት የለውም " ብሏል።

የእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ህወሓት ለሁሉም የዞንና የወረዳ የድርጅቱ ፅህፈት ጠቅሶ ባሰራጨው ደብዳቤ ፥ " ከሰርዓታዊና ተቋማዊ አሰራር ውጪ የሚካሄዱ የስራ ምደባዎች ኢህጋዊ ብቻ ሳይሆኑ ተጠያቂነትን ያስከትላሉ " ሲል አስጠንቅቋል።

የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ነሃሴ 17/2016 ዓ.ም በህወሓት የፓሊት ቢሮ አባልዋ ወ/ሮ ሊያ ካሳ ምትክ ፀጋይ ገብረተኽለ ገ/ክርስቶስ የደቡባዊ ምስራቅ ዞን አስተዳዳሪ በማድረግ መሾማቸው ዘግበናል።

ነሃሴ 18/2016 ዓ.ም የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ደግሞ በሰሜናዊ ምዕራብ ዋና አስተዳዳሪና በቅርቡ ህወሓት ባካሄደው ጉባኤ የፓሊት ቢሮ አባል ሆነው በተመረጡት ተክላይ ገ/መድህን ምትክ የክልሉ የስፓርት ኮሚሽን ኮምሽነር የነበሩት ተኽላይ ፍቓዱ ተሹመዋል።

ትግራይ ካሉዋት ሰባት የዞን አስተዳደሮች በአሁኑ ጊዜ ስድስቱ የእነ ዶ/ር ደብረፂዮን አካሄድ በሚቃወሙ የሚመሩ ሲሆኑ የመቐለ ከተማ ብቻ በቅርቡ  በተካሄደ ጉባኤ  የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ሆኖው በተመረጡት ይመራል። 

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
😡401226🕊103🤔78👏59🥰30😭20🙏19😢18😱7