TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#አዲስ_አበባ አዲስ አበባ ውስጥ የቀጠለው ዝርፊያና ጥቃት ! ከሰሞኑን የኤሌክትሮኒክ ትራንስፖርት የሚሰጡ ወገኖች ላይ እየደረሰ ስላለው ወንጀል መረጃ መለዋወጣችን አይዘነጋም። ጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠው ማመልከታችንም የሚታወስ ነው። ለማስታወስ ፦ 👉 አንድ የቤተሰባችን አባል ራሱንና ቤተሰቡን ለማስተዳደር የሚሰራበትን መኪና ዘራፊዎች በስለት አስፈራርተውት እንደዘረፉት : t.me/tikvaheth…
#ፍትሕ

በአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክሮኒክ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት እና ዝርፊያ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል።

ባለፉት ሳምንታት ብቻ 3 በዚሁ አገልግሎት ላይ በተሰማሩ አገልግሎት ሰጪዎች ላይ ዝርፊያን ጨምሮ ጥቃት ተፈፅሟል (በቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ብቻ ሪፖርት የተደረገ) ።

ትላንት ግን ከዝርፊያም ባለፈ የሰው ህይወት ተቀጥፏል።

በዚህ ዘርፍ የሚሰሩ ወገኖች ጉዳዩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ መሆኑን በመግለፅ መንግስት ትኩረት እንዲሰጥ እያሳሰቡ ይገኛሉ።

ወንጀለኞችም ለፍርድ እንዲቀርቡ እየጠየቁ ናቸው።

የኤሌክሮኒክ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ትላንትና በግፍ የተገደለውን ሳልሀዲን ሀሰን ፍትህ እንዲያገኝ ዛሬ ተሰብሰው ጠይቀዋል።

ትላንት ሳልሃዲን አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ ገርጂ 24 ኤርትራ ቆንፅላ ፅ/ቤት አካባቢ ተገድሎ መገኘቱ ይታወቃል።

ይህን ተከትሎ ነው ፍትህ እንዲገኝ የኤሌክትሮኒክ ትራንስፖርት አገልግሎት ሠጪዎች ድምፃቸውን ያሰሙት ፤ ቤተሰቦቹንም ሄደው አፅናንተዋል።

በስራቸው ላይ እያሉ እየተፈፀመ ያለው ጥቃት እና አስተማማኝ ደህንነት እጦት እየተባባሰ መምጣቱን የሚገልፁት አገልግሎት ሰጪዎቹ መንግስት ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

Photo Credit : Solomon Muchie (DW)

@tikvahethiopia
😢745👍91🙏48😱2421🥰11
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ፍትሕ_ሚኒስቴር

የሁለት ህፃናትን ህይወት በአሰቃቂ ሁኔታ ያጠፋችው ህይወት መኮንን በዛሬው ችሎት ዐቃቤ ህግ በሞት እንድትቀጣ ካለ በኃላ ፦

- ከዚህ ቀደም ወንጀል ፈፅሜ የማላውቅ፣
- ወንጀሉን የፈጸምኩት ከእውቀት ማነስና ያልተማርኩ በመሆኔ መሆኑ፣
- እጄን ለፖሊስ አምኜ የሰጠው በመሆኔ ከግምት ገብቶ ቅጣቱ ይቅለልልኝ በማለት የቅጣት ማቅለያዎችን ከመንግስት በተመደበላት የተከላካይ ጠበቃ አማካኝነት  የጠየቀች ቢሆንም የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት ተከሳሿ ያቀረበችውን ማቅለያዋን #አልተቀበለውም፡፡

ፍርድ ቤቱ ሌሎች አጥፊዎችን ያስጠነቅቃል በማለት ተከሳሿ #በሞት እንድትቀጣ ሲል ወስኖባታል፡፡

@tikvahethiopia
👍6.5K😢772👎649🙏289249😱205🕊199
አዲሱ ዓመት 2016 ፦

- ሀዘን ፣ የዜጎችን ሞት ፣ ሰቆቃ ፣ ረሃብ ፣ የእርስ በእርስ መገዳደልና መጠፋፋት የማንሰማበት፤

- ለተበደሉት ፣ ለተገፉት ዜጎች ሁሉ #ፍትሕ የሚገኝበት፤

- ምስኪን እናቶች፣ ህፃናት ፣ አረጋውያን ምንም በማያውቁት ፖለቲካ የማይሰቃዩበት ፤ ወጣቶችም ነፍሳቸውን የማይነጠቁበት፤

- ዘውትር ጭንቀት ለሆነብን የኑሮ ውድነት መፍትሄ የሚያገኝበት፤

- ዜጎች ወጥተው ለመግባት የማይሳቀቁበት፤

- ወጥተን የማንቀርበት፤

- በአጠቃላይ ሀገራችን ከጫፍ እስከጫፍ ሰላም እና ተስፋ የሚነግስበት ዓመት እንዲሆን እንመኛለን።

የአዲስ ዓመት በዓልን ስናከበር ችግር ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን በማሰብ ፣ የሚወዱትን ከአጠገባቸው የተነጠቁ ወገኖችን በማፅናናት ፣ የታመሙትን በመጠየቅ ፣ ፈጣሪ ለሀገራችን አስተማማኝ የሆነ ሰላምን እንዲሰጠን በመማፀን ይሆን ዘንድ አደራ እንላለን።

መልካም አዲስ ዓመት !

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
Tikvah Family

#ኢትዮጵያ2016

@tikvahethiopia
👍5.07K842🙏398🕊287👎114🥰62😢29😱26
#Ethiopia #ፍትሕ

በአሰቃቂ ሁኔታ ተደፍራ የተገደለችው የ7 ዓመቷ ህጻን ሔቨን ታሪክ የበርካቶችን ልብ የሰበረ ጉዳይ ሆኗል።

ይህ ድርጊት የተፈጸመው ከዛሬ #አንድ_ዓመት በፊት በባህርዳር ከተማ እንደሆነ ዛሬም ድረስ መሪር ሀዘን ውስጥ የምትገኘው እናት " ኢዮሃ " በተሰኘ የማህበራዊ ሚዲያ ላይ ቀርባ ተናግራለች።

ህጻን ሔቨን የተደፈረችው ተከራይተው ይኖሩበት በነበረ ግቢ አከራይ ነው።

የተደፈረችበት መንገድም ወደ ሽንት ቤት በምትሔድበት ጊዜ ጠብቆ ወደ ቤት በማስገባት ነው። እጅግ በጣም አሰቃቂም ነበር።

ህጻን ሔቨንን የደፈረው ወንጀለኛ በምትደፈርበት ወቅት አንገቷን አንቆ ፤ አፏን አፍኖ ድርጊቱን የፈጸመ ሲሆን ወድቃ የሞተች ለማስመሰል ደሟን አንጠባጥቦ በር ላይ ጥሏት መሄዱን እናት ታስረዳለች።

እናት ልጇን ብቻ አይደለም ያጣችው ፤ ፍትህ ስትጠይቅ ይህንን ግፍ ሰምተው እንዳልሰማ የሆኑ ጎረቤት እና ቤተሰቦች ፤ በጥቅም ወንጀለኛውን ነጻ ለማስወጣት የሰሩ ፤ እናትን ጭምር ተባብረው ለማጥፋት ረጅም ርቀት የተጓዙ ፤ ማስፈራሪያ ደርሷቸው ቃላቸውን ከመስጠት የጠፉ ሁሉ ለእናት ፈተና ሆነውባታል።

ይህም ሆኖ ጥቂት የሚባሉ (የሴቶች እና ህጻናት ወንጀል መሪማሪ ፖሊሷ፤ የሴቶችና ህጻናት ቢሮ) አንዳንዶቹ ማስፈራሪያ ጭምር እየደረሳቸው አግዘዋት ከብዙ መከራ በኋላ ድርጊቱን የፈጸመው ግለሰብ በ25 ዓመት ጽኑ እስራት ይፈረድበታል።

እናት ግን ዛሬም ትኩስ ሀዘን ላይ ነች።

ሥራ እየሰራች መኖር አልቻለችም።

ነገ ከእስር ሲለቀቅ እሷንም ጭምር ለመግደል እንደሚፈልግ ፤ ለዚህም ደግሞ ዳግም ሥራ ከጀመረችበት ቦታ ቤተሰቦቹ ተከታትለዋት ጥላ መውጣቷን እናት አስረድታለች።

ዛሬም እውነተኛ ፍትሕ አጥታ ትንከራተታለች።

ግፍ ላይ ግፍ !

በመሰረቱ በዚህች ምስኪን አንድ ፍሬ ፤ ክፉ ደግ በማታውቅ ህጻን ላይ አሰቃቂ የመድፈር እና ኃሏም ህይወቷን ያሳጣ የወንጀል ድርጊት የፈጸመ ሰው እንዴት 25 ዓመት ይፈረድበታል ? እውነት ይህ ማስተማሪያ ነው ? ወይስ ሌላ ነው ዓላማው ?

የሔቨን ታሪክ የብዙ ህጻናት ታሪክ ጭምር ነው።

ከዚህ በፊት ሴቶች፣ ህጻናት ጭምር ሲደፈሩ የሚተላለፉ የፍርድ ውሳኔዎች ህዝቡን እያስቆጣ መሆኑን አሳውቀን ነበር።

ዛሬም ፍትሕ ተጓድሏል። ፍትሕ ይስፈን።

ዛሬ አጋጣሚ ይህ ጉዳይ አደባባይ ወጣ እንጂ ስንቷ እናት ቤቷ ዘግያ እያለቀሰች ይሆን ? ስንት ሴቶች በግፍ ሰለባ ሆነው እያነቡ ይሆን ?

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
😭9.06K😡661327😢245🙏131🕊81😱33👏26🥰25🤔7