TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ይሄ ' የአማራ አዋሳኝ ' የሚባለው ቀልድ መቆም ያለበት ነው " - አቶ ረዳዒ ኃለፎም

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ረዳዒ ሀለፎም ሰሞኑን ስለነበረው የተኩስ ልውውጥ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አቶ ረዳዒ ሀለፎም ምን አሉ ?

- ግጭቱ ራያ አላማጣ ሳይሆን ጨርጨር አካባቢ ነው። ይሄ የአማራ አዋሳኝ የሚባለው #ቀልድ ደግሞ መቆም ያለበት ነው።

- የትግራይ መሬት ነው ጨርጨር። ጨርጨር ትግራይ እንጂ አማራ ሆኖ አያውቅም። አሁንም አይደለም። እዚያው የአማራ ታጣቂዎች አሉ። እነዛ የአማራ ታጣቂዎች በእኛ ሚሊሻዎች ላይ የፈጸሙት ጥቃት ነው። የአጭር ጊዜ ተኩስ ልውውጥ ነበር ቁሟል አሁን ግጭቱ የለም።

* ጉዳዩን በተመለከተ ምን እየተሰራ እንደሆነ ለቀረበ ጥያቄ ፦ " በእኛ በኩል (በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደርም) ከላይ ከሚመለከታቸው የፌደራሉ መንግሥትም የተወሰነ ንግግር እየተደረበት ነው " ብለዋል።

* የመፍትሄ ሀሳብን በተመለከተ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለተነሳው ጥያቄ ፦

" የመጀመሪያው ነገር ሕገ መንግሥቱን ማክበር ነው። የአዋሳኝ ጉዳይ አይደለም መሀል ትግራይ ላይ ነው ችግሩ እየተፈጠረ ያለው። ወረው በኃይል ከያዙት መሬት ላይ ነው አሁን ደግሞ መልሰው ጥቃት እየፈጸሙ ያለት። ይሄ ትክክል አይደለም። ለማናችንም የሚጠቅም ነገር አይደለም።

መሆን ያለበት ጥያቄ ያለው አካልም በሕጉ መሠረት ካልሆነ በቀር የሆነ አጋጣሚ ተጠቅሞ ‘ጉልበት አለኝ፣ ይጠቅመኛል’ ብሎ ባሰበ ጊዜ የኃይል አማራጭ የሚወስድ ከሆነ፣ ቢያንስ የሕዝቦች ዘላቂ ወዳጅነትና መቀራረብ የሚያረጋግጥ አይደለም። ከዚህ መቆጠብ ነው ያለብን " ብለዋል።

- የፌደራል መንግሥት ሲቪሊያንን የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት ድሮም ቢሆን በውሉም በተመሳሳይ ፤ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖም ከመከላከያ ሰራዊት ውጪ ያሉ ታጣቂዎች ከትግራይ ክልል እንዲወጡ ውሉም ያስገድዳል። አለመውጣታቸውም ብቻ ሳይሆን በየትኛውም የአማራ ታጣቂዎች ባሉበት አካባቢ ሴቶች እየተደፈሩ ናቸው። ሰብዓዊ መብቶች እየተረገጡ ናቸው። ብዙ ጥፋቶች እየተፈጸሙ ናቸው። ስለዚህ ውሉን በአግባቡ ተግባሪዊ ማድረግና በቁጥጥር ሥር መስራት ከተቻለ ብቻ ነው ወደ ሰላም ማምራት የምንችለው።

- በአማራ ክልል እየተፈጸሙ ያሉት ትክክል ስላልሆኑ አደብ መያዝ ያስፈልጋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
የካቲት 8/2016 ዓ/ም
መቐለ

#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
😡1.38K755👏270🕊164😱47😭36🥰31😢30🙏22