TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ቅዱስ ፓትርያርኩ የመሩት የሰላም ልዑክ የዛሬ ውሎ ምን ይመስል ነበር ?

- ቀደም ብሎ በወጣ መርሀ ግብር በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የተመራው የሰላም ልዑክ መቐለ አሉላ አባነጋ ኤርፖርት ሲደርስ በምዕመናን፣ ዘማርያን፣ በክልሉ ሃይማኖት አባቶች አቀባበል ይደረግለታል ቢባልም በስፍራው ከትግራይ አባቶች ፣ ዘማርያን የተገኘ አልነበረም። የተገኙት የመንግስት አመራሮች ነበሩ።

- በመቀጠል እዛው መቐለ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የተመራ ፀሎት ይከናወናል ተብሎ የነበረ ቢሆንም ምዕመናን፣ ካህናት ፣ የትግራይ አባቶች አልተገኙም ነበር። ቅዱስነታቸው እና የመሩት ልዑክ የቤተክርስቲያኑ በር የዘግቶባቸው በር ላይ ፀሎት አድርሰው ለመውጣት ተገደዋል።

- በፕላንቴ ሆቴል በተካሄደ ስነስርዓት ልዑኩ የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በዚህ ስነስርዓት ላይ የትግራይ አባቶች #አልተገኙም። ተገኝተው የነበሩት የክልሉ መንግስት አመራሮች ነበሩ።

- ልዑኩ በመቀጠል በመቐለ 70 ካሬ ተፈናቃዮችን የተመለከተ ሲሆን በዚህ ወቅትም " ቅዱስ ሲኖዶሱ ለበዳዮች ወግንዋል " በማለት ተፈናቃዮች በድምፅና በፅሁፍ ተቋውሞ ማሰማታቸውን ለማወቅ ተችሏል።

- ከመቐለ 70 ካሬ የተፈናቃዮች መልከታ በኃላ የሰላም ልዑኩ ከትግራይ ብፁአን አበውና የኦርቶዶክሳዊ ቤተክርስተያን አመራሮች ጋር ይገናኛል ውይይትም ያደርጋል የሚል መርሀ ግብር ተይዞ የነበረ ቢሆንም ይህም አልተደረገም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በትግራይ ያሉ ብፁዓን አባቶች ከጥዋት አንስቶ በነበሩ መርሀግብሮች ላይ ለምን አልተሳተፉም ? የሚለውን ለመጠየቅ ጥረት ቢያደርግም አልተሳካም።

@tikvahethiopia
😢821👍591👎11892🕊18🥰11🙏11😱8