TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
እንኳን አደረሳችሁ!

ህዝቡ #አንድነቱን በማጠናከር ለየትኛውም ፈተና ሳይንበረከክ ለስኬት ሊሰራ እንደሚገባ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ። አቶ ሽመልስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አዲሱን አመት በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፥ በ2012 ዓ.ም ለተሻለ ተጠቃሚነት ይሰራል ብለዋል። በ2011 ዓ.ም የተገኙ ስኬቶችን በማጠናከርም ለ2012 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም ህብረተሰቡ የድርሻውን ሊወጣ ይገባልም ነው ያሉት።

በቀጣዩ በጀት አመትም መንግስት ህዝቡን የተሻለ ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰራም አንስተዋል። አዲሱ አመት ስኬታማ ስራዎች የሚሰሩበት፣ ሰላም የሚረጋገጥበት፣ የህግ የበላይነት ለማስከበር የሚሰራበት፣ ህዝቡን ከድህነት ለማውጣት የተጀመሩ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን የምናስቀጥልበት እና ስራ አጥ ዜጎች የተሻለ ስራ የሚያገኙበት እንደሚሆንም ተናግረዋል። በፖለቲካው ዘርፍም በ2011 ዓ.ም የታዩ መልካም ስራዎችን በማስቀጠል ስኬታማ ስራዎች እንደሚሰሩም ገልጸዋል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍1