TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጥንቃቄ #አዲስአበባ

ከመገናኛ ወደ ላምበረት በሚወስደው መንገድ እስራኤል ኤምባሲ አካባቢ የመሬት መንሸራተት በመከሰቱ ምክንያት መገናኛ አካባቢ ጭምር መንገድ ስለተዘጋ በዚህ አካባቢ የሚጓዙ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገድ እንዲጠቀሙ እና እግረኞችም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን የጥንቃቄ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

(የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን)

@tikvahethiopia
👍1.33K😱508163😢121🙏78👎38🕊35🥰19
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba #Exam ለአዲስ አበባ አስተዳደር አመራሮች ፣ ባለሞያዎች / ሠራተኞች የተሰጠውን የቴክኒክ እና ባህሪ ብቃት ፈተና የማለፊያ ነጥብ አምጥተው ያለፉ #የክዋኔ_ክህሎት ስልጠና ይሰጣቸዋል ተብሏል። የማለፊያ ነጥብ ማምጣት ሳይችሉ ቀርተው #ያላለፉት ደግሞ #የአቅም_ግንባታ_ስልጠና እንደሚሰጣቸው ተጠቁሟል። በተጨማሪ የማለፊያ ውጤት ያላመጡት ዝቅ ብለው እንደሚመደቡ ፤ አሁን ላይ #ስንብት…
#አዲስአበባ

ዛሬ 3,854 የመንግሥት ሰራተኞች ፈተና ተቀምጠዋል።

ዛሬ ለባህሪና ብቃት ምዘና ፈተና የተቀመጡት ፦
- የአዲስ አበባ መሬት ይዞታ ቢሮ፣
- የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ
- የከንቲባ ፅ/ቤት (ማለትም የ3 ተቋማት) ዳይሬክተሮች፣ ቡድን መሪዎች፣ ሰራተኞች እና ባለሙያዎች ናቸው።

ፈተናው በአዲስ አበባ ዩኒቪርስቲ በ6 ኪሎ ካምፓስ ውስጥ እየተሰጠ ይገኛል።

ከዚህ ቀደም 15,151 የአስተዳደሩ አመራሮች፣ ሠራተኞች / ባለሞያዎች (የ13 ተቋማት) የቴክኒክና ባህሪ ብቃት ፈተና መውሰዳቸውና ውጤቱም ይፋ መደረጉ ይታወሳል።

ፈተናውን ከወሰዱ 4,213 አመራሮች ያለፉት 1,422 መሆናቸው እንዲሁም ፈተናውን ከወሰዱ 10,257 ባለሞያዎች / ሠራተኞች ያለፉት 5,095 መሆናቸው መገለፁ አይዘነጋም።

የማለፊያ ነጥብ አምጥተው ላለፉ የክዋኔ ክህሎት ስልጠና እንደሚሰጥ ፤ የማለፊያ ነጥብ ማምጣት ሳይችሉ ቀርተው ያላለፉት ደግሞ የአቅም ግንባታ ስልጠና እንደሚሰጣቸው መነገሩ ይታወቃል።

በተጨማሪ ፤ የማለፊያ ውጤት ያላመጡት ዝቅ ብለው እንደሚመደቡ ፤ አሁን ላይ #ስንብት የሚባል ነገር እንደሌለ ፤ ስንብት የሚፈፀመው መጨርሻ ላይ ሁሉ ነገር ከተጠናቀቀና ሌላ አማራጭ ከጠፋ ብቻ መሆኑን የከተማው አስተዳደር ማሳወቁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
😢335227😡139🙏70😭66🕊24😱22🥰20👏2