TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
218 files
4.4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢፍጧር

በኢትዮጵያ የታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጧር ለአራተኛ ጊዜ ነገ መጋቢት 18/2016 ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ የከናወናል።

የነገው ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መሪ ቃል " ኢፍጧራችን ለአንድነታችን " የሚል ነው።

ዓላማው በታላቁ የረመዳን ወር ሰዎችን በአንድነት በማሰባሰብ በጋራ ጾማቸውን እንዲያፈጥሩ በማስቻል የአብሮነትና የመተባበር መንፈስ ለማዳበር ነው ተብሏል።

በዚህ ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጧር የህዝበ ሙስሊሙ፦
- አንድነት የሚንፀባረቅበት ፣
- ያለው ለሌለው የሚያካፍልበት፣
- ወረሐ ረመዷን ከመሆኑ አንፃር የቁርአን ክብር በአደባባይ የሚልቅበት እንደሚሆን ተነግሯል።

ዝግጅቱ ሀላል ፕሮሞሽንና ከነጃሺ በጎ አድራጎት ድርጅት በጋራ በመሆን የተዘጋጀ ነው።

@tikvahethiopia
717😡437👏21🤔19🕊17🙏9😱7😢6😭3🥰1