TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሞስኮ

የሩስያ ፖሊስ በዋና ከተማዋ ተቃውሞ የወጡ ከአንድ ሺ በላይ ሰልፈኞችን ማሰሩ ተሰማ። ሩስያ ለምርጫ መወዳደደር የሚያበቃቸውን ፊርማ አላሰባሰቡም ስትል ተቃዋሚ ተወዳዳሪዎችን ከምርጫው ማገዷ ይታወቃል፡፡ ይህን ተከትሎም በሞስኮ ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ነዋሪ ለተቃውሞ ሰልፍ መውጣቱን ቢቢሲ አስነብቧል፡፡

ነገሩ ያልጣመው የሩስያ ፖሊሲም ተቃዋሚ ሰልፈኞችን አንዲበተኑ አድርጓል ይላል ዘገባው፡፡ ለምን ይታገዳሉ ሲሉ ሰልፍ ከወጡት መካከልም ፖሊስ ከአንድ ሺ በላይ ማሰሩንም ቢቢሲ ጨምሮ አስነብቧል፡፡ ተፎካካሪዎቹ ለምርጫ የማያበቃቸውን ፊርማ ስላልሰበሰቡ ሳይሆን ፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ሲባል ነው ክምርጫው እንዲወጡ የተደረገው ሲሉ ሰልፈኞቹ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡

ሰልፉን ለመበተን ፖሊስ የሄደበት መንገድ በጣም አደገኛ አገሪቱን ወደ ችግር የሚወስዳት እንደሆነ የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል፡፡ ሩስያ እኤአ መስከረም ስምንት 2019 የምታካሂደውን ምርጫ ተከትሎ ጥቂት ከምርጫው የታገዱ ተቃዋሚ ተወዳዳሪዎችን ማሰሯ ታውቋል፡፡ እስካሁንም 30 ተፎካካሪዎች በቂ ፊርማ ባለማሰባሰባቸው ከምርጫው ታግደዋል ይላል የቢቢሲ ዘገባ፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#RUSSIA

ሩሲያ በአንድ ቀን ብቻ 9,623 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ። አብዛኞቹ በዋና ከተማዋ #ሞስኮ የሚኖሩ ናቸው። ይህ ቁጥር ወረርሽኙ ሩሲያ ከደረሰ በኋላ ከተመዘገቡት ሁሉ ከፍተኛው ነው።

በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓታት 57 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። በመላ አገሪቱ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 1,222 ማሻቀቡን ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የተቋቋመው ኮሚቴ አስታውቋል።

የሞስኮ ከተማ ከንቲባ የሆኑት ሰርጌይ ሶብያኒን የከተማው ነዋሪዎች ራሳቸውን በመኖሪያ ቤታቸው ለይተው እንዲያቆዩ ተማፅነዋል።

በኮሮና ቫይረስ በጽኑ የታመሙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን የተናገሩት ከንቲባው እጅግ የከፋ ደረጃ አለመድረሱን ገልጸዋል። ሁኔታው ከከፋ በሞስኮ ከተማ ለመንቀሳቀስ የሚሰጥ ፈቃድ ሊቀነስ እንደሚችልም ከንቲባው ገልጸዋል።

በሞስኮ ከተማ ነዋሪዎች ከመንግሥት ልዩ ፈቃድ ካላገኙ በቀር ከቤታቸው መውጣት የሚችሉት ዕቃ ለመሸመት፣ ውሾቻቸውን ለማንሸራሸር እና ቆሻሻ ለመጣል ብቻ ነው።

#DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopi