TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Hawassa

" . . . ማንም አካል በመንግስት ንብረት የግል ፍላጎቱን ማራመድ አይችልም ፤ እንዲህ አይነት ፍላጎት ያለዉ አካል ስልጣኑን ለቆ ፍላጎቱን ማሳካት ይችላል " - የሲዳማ ክልል የሰላምና ጸጥታ ጉዳይ ቢሮ

" ጉዳዩ በውስጣዊ አሰራር ህግና ደንብ መሰረት ተይዞ በሂደት ላይ ነው። " - የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ

" ... ለጊዜዉ በሌለሁበት ከስራ እንድታገድ ወስነዉብኛል። ነገር ሁሉ ለበጎ ነው ብዬ እየጠበኩ ነው። " - ኢኒስፔክተር ተስፋዬ

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ መነጋገሪያ ሆነው የሰነበቱት የሀዋሳ ከተማ ትራፊክ ፖሊስ ማስተባበሪያ ኃላፊዉ ኢንስፔክተር ተሰፋዬ ደምሴ ላልተወሰነ ጊዜ ከስራ ታግደዋል።

ይህ በተመለከት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ኢንስፔክተር ተስፋዬን እና ጉዳዩ ይመለከታቸው ያላቸውን አካላት ለማነጋገር ጥረት አድግጓል።

ከሰሞኑ የሲዳማ ክልል የጸጥታ አካላት ያደረጉትን ስብሰባ ተከትሎ በተለቀቀዉ አንድ ተንቀሳቃሽ ምስል ፤ ኢንስፔክተር ተስፋዬ ነጻና ገለልተኛ ሁኖ ማህበረሰቡን የሚያገለግለዉን የፖሊስ ንብረት በግላቸዉ ለሚከተሉት ሀይማኖታዊ አገልግሎት በማዋላቸዉ ምክኒያት ላልተወሰነ ጊዜ ከስራ መታገዳቸዉ ይገልጻል።

በወቅቱ ስብሰባዉን የመሩት የክልሉ የሰላምና ጸጥታ ጉዳይ ኃላፊዉ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ ባስተላለፉት መልእክት ፤ ማንም አካል በመንግስት ንብረት የግል ፍላጎቱን ማራመድ እንደማይችልና እንዲህ አይነት ፍላጎት ያለዉ አካል ስልጣኑን ለቆ ፍላጎቱን ማሳካት እንደሚችል ገልጸዋል።

በጉዳዩ ላይ ከቲክቫህ ኢትዮጰያ ተጨማሪ ማብራሪያ የተጠየቀዉ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ በበኩሉ ጉዳዩ በዉስጣዊ አሰራር ህግና ደንባቸዉ መሰረት ተይዞ በሂደት ላይ ያለ መሆኑን አሳውቋል።

ይሁንና ከሰሞኑ በነበረዉ ስብሰባ ወቅት የተነሳዉን የኢንስፔክተር ተስፋዬን ከስራ መታገድ በተመለከተ ለጊዜዉ ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ኢንስፔክተር ተስፋዬ ደምሴ ስለሁኔታው ምን ምላሽ እንዳላቸው በስልክ ጠይቋቸው " ኢየሱስ ይመጣል የሚለዉን መልእክት ባስተላለፍኩበት ወቅት እንዳያችሁት በተፈጠረዉ ሁኔታ ከስራ ታግጃለሁ ፤ ለጊዜዉ በሌለሁበት ከስራ እንድታገድ ወስነዉብኛል። " ብለዋል።

" ነገር ሁሉ ለበጎ ነዉ ብዬ እየጠበኩ ነው እግዚያብሄር መልካም ነዉ " ሲሉ አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

@tikvahethiopia
1.11K👏454😡208😭93🙏78😢37🕊36😱25🥰24
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Hawassa

በፀጋ በላቸው ላይ የጠለፋና አስገድዶ መድፈር ወንጀል የተከሰሰው ኮንስታብል የኋላመብራት ወልደማርያም በ16 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል።

የህግ አማካሪና ጠበቃ እንዲሁም በፆታዊ ጉዳዮች ላይ የሚሰሩት አበባየሁ ጌታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ ውሳኔው የከተማውን ገፅታ የሚያበላሽ እንደሆነ ስለታሰበ ነው መፍትሄ ያገኘው ብለዋል።

አበባየሁ ጌታ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ምን አሉ ?

-  ሚዲያ ላይ ባለመውጣታቸው ብዙ ተሸፋፍነው የቀሩ የጠለፋ ወንጀሎች በከተማው አሉ።

-  ይህ ውጤት የተገኘው በተለያዩ መንገዶች በማህበራዊ ሚዲያው ላይ ከፍተኛ ትኩረት ስላገኘ ነው።

-  ጉዳዩ አነጋጋሪ የሆነው የከንቲባው የግል ጠባቂ ከመሆኑ፣ የመንግስትን ንብረት ተጠቅሞ በመሆኑ በከተማው ገፅታ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ስለነበረው ነው ይህ ጉዳይ እልባት ያገኘው።

-  ታህሳስ 04 ቀን 2016 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ተጠርጣሪው በተከሰሰባቸው ሁለት ወንጀሎች ማለትም በጠለፋ እና አስገድዶ መድፈር ጥፋተኛ ተብሏል።

- በመቀጠል ታህሳስ 08 ቀን 2016 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ላይ ከሁለቱም ወገኖች የቅጣት ማቅለያ እና ማክበጃ እንዲያቀርቡ ተደርጎ ነበር።

-  በዛሬው እለት ከተያዘበት ቀን ጀምሮ በ16 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ፍርድ ተሰጥቷል።

ባለሙያው በአጠቃላይ ፆታዊ ጥቃቶችን በተመለከተ ምን አሉ ?

* ወደሐዋሳ አካባቢ መሰል ችግሮችን በሽምግልና መፍታት እና ከባህል ጋር የማያያዝ አዝማሚያ አስቸጋሪ ነው። እንደዚህ አይነት ነገሮች በሽምግልና መፈታት የለባቸውም።

* የህግ አካላት በማህበራዊ ሚዲያ የማይጮኹ ጉዳዮችንም ትኩረት አለመስጠት እና ተባባሪ አለመሆንም መስተካከል ይገባዋል።

* በትምህርት፣ በስልጠና እና በመሰል አስተማሪ ቅጣቶች ለፆታዊ ጥቃቶች ትኩረት መስጠት ይገባል።

የዳሸን ባንክ ሰራተኛ እንዲሁም የአላሙራ ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆነችው ፀጋ በላቸው ፤ ግንቦት 15 ቀን 2015 ከስራ ስትወጣ በወቅቱ የከተማው ከንቲባ የግል ጠባቂ በነበረው ኮንስታብል የኃላመብራት ወ/ማርያም የተባለ ግለሰብ በመኪና ታግታ መወሰዷና አድራሻዋም ሳይታወቅ ለቀናት መቆየቱ የሚታወስ ነው።

የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በወቅቱ እንዳስታወቀው ተጠርጣሪው ከግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን ከፀጥታ ሀይል ለማምለጥ ሲል በሻፋሞ ጫካ ለጫካ ሲዘዋወር እንደነበረ እና ተጠርጣሪው ግለሰብ ወንጀሉን ለመፈጸም ሲጠቀምባቸው ከነበሩ አንድ ክላሽንኮቭ የጦር መሳሪያና ሽጉጥ ጋር  ህዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም. መያዙን የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታውቆ ነበር።

መረጃው ተዘጋጅቶ የተላከው በአዲስ አበባ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
👏522😡13698🙏31😭25🕊16😱10😢8🥰7