TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ደብረ ማርቆስ⬆️

ኢትዮጵያና ኤርትራ ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል ያሳለፉትን ኩርፊያ ይበቃል በማለት የሰላምና የወዳጅነት ስምምነት መፈረማቸውን ተከትሎ በርካታ በጎ ተግባራትን በመስማት ላይ እንገኛለን፡፡

ከወደ ደብረማርቆስ የተሰማው ጉዳይም የዚሁ አዲስ ጅምር አንዱ አካል ነው፡፡

የደብረማርቆስ ህዝብ ከዓመታት መለያየት በኋላ #ከኤርትራ የመጡ አብሮ አደጎቹን ተቀብሏል፡፡

ከ20 ዓመታት በፊት ኑሯቸውን በደብረ ማርቆስ ከተማ አድርገው ነበር፤ የወቅቱ አስከፊ የፖለቲካ ውሳኔ ግን በአካል እንጂ በመንፈስ ካልተለዩት ህዝብ ጋር ሳይፈልጉ ተገደው እንዲለዩ አደረጋቸው፡፡

ዛሬ ታሪክ ተቀይሯል መለያየት በአብሮነት፤ ጥላቻ #በፍቅር ድል ተነስተዋል፡፡

እናም አቶ ተስፋ ሚካኤል ግደይና አቶ መድሃኔ ግደይ ወደ ቀድሞ ከተማቸው ተመልሰዋል፡፡ ደብረ ማርቆስም የትናንት ልጆቿን የዛሬ እንግዶቿን እልል…! ብላ
ተቀብላለች፡፡

ከአቀባበሉ በኋላ ደግሞ የህዝቡን ቃል አክባሪነት እና ታማኝነት ያስመሰከረ አንድ አስገራሚ ዕውነታ ተገለጠ፡፡

ወደ ኤርትራ በሄዱበት ወቅት ትተውት የሄዱት ቤት ተጠብቆ ቆይቶላቸው ነበርና ህዝቡ ለባለቤቶቹ አስረክቧል፡፡

የኢትዮጵዊነት እሴትም በተግባር ታየ በተጨማሪም ህዝቡ ለኤርትራዊያኑ ወንድሞቹ የጋቢ ስጦታም አበርክቶላቸዋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia