TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Hawassa

" . . . ማንም አካል በመንግስት ንብረት የግል ፍላጎቱን ማራመድ አይችልም ፤ እንዲህ አይነት ፍላጎት ያለዉ አካል ስልጣኑን ለቆ ፍላጎቱን ማሳካት ይችላል " - የሲዳማ ክልል የሰላምና ጸጥታ ጉዳይ ቢሮ

" ጉዳዩ በውስጣዊ አሰራር ህግና ደንብ መሰረት ተይዞ በሂደት ላይ ነው። " - የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ

" ... ለጊዜዉ በሌለሁበት ከስራ እንድታገድ ወስነዉብኛል። ነገር ሁሉ ለበጎ ነው ብዬ እየጠበኩ ነው። " - ኢኒስፔክተር ተስፋዬ

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ መነጋገሪያ ሆነው የሰነበቱት የሀዋሳ ከተማ ትራፊክ ፖሊስ ማስተባበሪያ ኃላፊዉ ኢንስፔክተር ተሰፋዬ ደምሴ ላልተወሰነ ጊዜ ከስራ ታግደዋል።

ይህ በተመለከት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ኢንስፔክተር ተስፋዬን እና ጉዳዩ ይመለከታቸው ያላቸውን አካላት ለማነጋገር ጥረት አድግጓል።

ከሰሞኑ የሲዳማ ክልል የጸጥታ አካላት ያደረጉትን ስብሰባ ተከትሎ በተለቀቀዉ አንድ ተንቀሳቃሽ ምስል ፤ ኢንስፔክተር ተስፋዬ ነጻና ገለልተኛ ሁኖ ማህበረሰቡን የሚያገለግለዉን የፖሊስ ንብረት በግላቸዉ ለሚከተሉት ሀይማኖታዊ አገልግሎት በማዋላቸዉ ምክኒያት ላልተወሰነ ጊዜ ከስራ መታገዳቸዉ ይገልጻል።

በወቅቱ ስብሰባዉን የመሩት የክልሉ የሰላምና ጸጥታ ጉዳይ ኃላፊዉ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ ባስተላለፉት መልእክት ፤ ማንም አካል በመንግስት ንብረት የግል ፍላጎቱን ማራመድ እንደማይችልና እንዲህ አይነት ፍላጎት ያለዉ አካል ስልጣኑን ለቆ ፍላጎቱን ማሳካት እንደሚችል ገልጸዋል።

በጉዳዩ ላይ ከቲክቫህ ኢትዮጰያ ተጨማሪ ማብራሪያ የተጠየቀዉ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ በበኩሉ ጉዳዩ በዉስጣዊ አሰራር ህግና ደንባቸዉ መሰረት ተይዞ በሂደት ላይ ያለ መሆኑን አሳውቋል።

ይሁንና ከሰሞኑ በነበረዉ ስብሰባ ወቅት የተነሳዉን የኢንስፔክተር ተስፋዬን ከስራ መታገድ በተመለከተ ለጊዜዉ ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ኢንስፔክተር ተስፋዬ ደምሴ ስለሁኔታው ምን ምላሽ እንዳላቸው በስልክ ጠይቋቸው " ኢየሱስ ይመጣል የሚለዉን መልእክት ባስተላለፍኩበት ወቅት እንዳያችሁት በተፈጠረዉ ሁኔታ ከስራ ታግጃለሁ ፤ ለጊዜዉ በሌለሁበት ከስራ እንድታገድ ወስነዉብኛል። " ብለዋል።

" ነገር ሁሉ ለበጎ ነዉ ብዬ እየጠበኩ ነው እግዚያብሄር መልካም ነዉ " ሲሉ አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

@tikvahethiopia
1.11K👏454😡208😭93🙏78😢37🕊36😱25🥰24