TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
216 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ዋግኽምራ📍

በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ህወሓት በሚቆጣጠረው አበርጌሌ በተፈጠረው የመድሃኒትና ምግብ እጥረት ሳቢያ ከሃምሌ ወር አንስቶ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 120 መድረሱ ተገልጿል።

ወረዳው ከሟቾቹ ውስጥ ብዛት ያላቸው ህፃናት እና አዛውንት እንደሆኑ፤ አብዛኞቹ ተጓዳኝ የጤና ችግር እንደነበረባቸው ነገር ግን የሞታቸው ምክንያት የመድሃኒት እጥረት መሆኑ አሳውቋል።

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አለሙ ክፍሌ ሲናገሩ፥ "ከ70 ሺ ህዝብ በላይ ነው አበርጌሌ የሚኖረው፤ አበርጌሌ ማለት ከትግራይ በሜትር ልዩነት የምንኖር ማህበረሰቦች ነን።

እዛ ያለው ማህበረሰብ አሁን በረሃብ እየሞተ ነው ያለው። ከ120 በላይ ሰው በረሃብ እና በመድሃኒት እጦት ሞቷል።

በአብዛኛው የሞቱት ሽማግሌዎች የነበሩ እና ከ50 በላይ እድሜ ያላቸው መንቀሳቀስ የማይችሉ በረሃብ እና በእድሜም ትንሽ ከፍ ያሉ ናቸው አንዳንዶቹ የግፊት መድሃኒት ይጠቀሙ የነበሩ ናቸው። አንዳንዶቹ የኤች አይቪ መድሃኒት የሚጠቀሙ ነበሩ።

ከዛ በዘለለ የተጠቁብን ህፃናቶች ናቸው በወባ እና በተለያዩ በሽታዎች ህክምና እና መድሃኒት የሚባል ስለሌለ ህፃናቶች ናቸው የሞቱት " ብለዋል።

አካባቢው በህወሓት ቁጥጥር ስር ከዋለ እንዴት የሟቾች ቁጥር ተረጋገጠ ? ለሚለውም ሲመልሱ፦

" አንደኛ ቤተሰቦቻችን ናቸው፣ አብዝሃኛው በየቀበሌው ያሉ ሰዎችም እዚህ ስለሚመጡ በተፈናቃይ መልኩ መረጃ ይሰጡናል።

በየቀኑም መረጃ የሚሰጡን ሰዎች አሉ እዛ ሆነው። በየቀኑ ምን እንደተፈጠረ ምን እንደሆነ ዝርዝር መረጃ የሚሰጡን አሉ።

እዛው አበርጌሌ ውስጥ አንዳንድ ቀበሌዎች ኔትዎርክ የሚሰራባቸው አሉ፤ ስልክ ስለሚሰራ በየቀኑ መረጃ እናገኛለን ይሄን በጣም እርግጠኛ ነኝ። " ሲሉ መልሰዋል።

telegra.ph/VOA-04-06

@tikvahethiopia
👍329😢246👎23😱139👏8
#ዋግኽምራ📍

ጦርነት ክፉኛ ከጎዳቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች አንዱ የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ነው።

በእዚህ አካባቢ ያሉ ወገኖች ለከፋ ችግር ተጋልጠው ሜዳ ላይ መውደቃቸው እና አስፈላጊው ድጋፍ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ጥሪ ሲቀርብ እንደነበር ይታወሳል።

ምንም እንኳን በቂ ባይሆንም የተለያዩ ድጋፎች ሲደረጉ ተስተውሏል።

ዛሬ ከዋግ ኽምራ ኮሚኒኬሽን በተገኘ መረጃ የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በጦርነት ሳቢያ ከቤታቸው ተፈናቅለው በሰቆጣ መጠለያ ለሚገኙ የዋግ ተፈናቃዮች 1.3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የስንዴ (300 ኩንታል) ድጋፍ አድርጓል።

ዩኒቨርሲቲው በችግር ላይ ለወደቁት ወገኖች አስፈላጊውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አሳውቋል።

በተጨማሪ በዞኑ የተለያዩ ምርምሮችን ተግባራዊ በማድረግ የህብረትሰቡን ችግር ለመፍታት የበኩሉን እንደሚወጣ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahethiopia
👍335😢35👎2011👏5🥰2
#ዋግኽምራ 📍

የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በፋሲካ ዋዜማ በአማራ ክልል ፤ ዋግ ኽምራ ዞን የሰቆጣ ከተማ ማእከላዊ እዝ እና ማህበረሰቡን መጎብኘታቸውን ፅ/ቤታቸው አስታውቋል።

ዶ/ር ዐቢይ ፤ ከማህበረሰቡ አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት የአገው ሕዝብን የኪነ-ህንፃ ልህቀት እና ፍልስፍናዊ መሰረት አድንቀው እነዚህን እሴቶች የመጠቀም እና ፈተናዎችን ለማሸነፍ አንድነትን ማስጠበቅ ያለውን ጠቀሜታ አመልክተዋል ተብሏል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአካባቢው የሚስተዋለውን የግጭት ሁኔታ አንስተውም ሰላምን ማስፈን የሰላማዊ ወኪል ለመሆን ወስኖ በቁርጠኝነት የሰላም እሴቶችን መገንባትን ይጠይቃል ማለታቸውን የጠ/ሚ ፅ/ቤት መረጃ ያመለክታል።

ዋግኽምራ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በዜጎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ፣ እንግልት እና ስቃይ የደረሰበት አካባቢ ሲሆን አሁንም ድረስ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተፈናቅለው ይገኘሉ።

@tikvahethiopia
👎467👍32211😢11🥰10😱7👏4
TIKVAH-ETHIOPIA
እርዳታ ለሚፈልጉ ወገኖች ምን ያህል ድጋፍ እየተደረገ ነው ? በኦሮሚያ ክልል በወለጋ ዞን፦ - ኪረሙ፤ - ሁሙሩ እና አጋምሳ፣ - ቤጊ፤ - ጊዳሚ፤ - ቆንዳላ፤ - ሆሮ ሊሙ በተሰኙ ቦታዎች፣ በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር፣ ዋግኽምራ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደር እንዲሁም በትግራይና በአፋር ክልሎች የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ ዜጎች ለከፍተኛ ረሃብ መጋለጣቸው፣ በሰዎችና በእንስሳት ላይ ሕልፈተ ሕይወት መድረሱ…
#አማራ #ዋግኽምራ

" ሰው ሁሉ ግራ ተጋብቶ የሚበላውንም አጥቶ ነው ያለው፤ ታይቶም ተሰምቶ የማይታወቅ በጣም የሚዘገንን ድርቅ ነው ያጋጠመን  " - የዋግኽምራ ምሽሃ ቀበሌ ነዋሪ

በአማራ ክልል፣ ዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ፤ ሰሀላ ሰየትም ወረዳ ውስጥ ስላለው አስከፊ የድርቅ ሁኔታ በተደጋጋሚ መነገሩ ይታወሳል።

በአካባቢው ስለሚገኙ ዜጎች ሁኔታ ፣ የሰብዓዊ ድጋፍ ጉዳይ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተደጋጋሚ መልዕክቶችን ማጋራቱም ይታወሳል።

አሁንም ችግሩ በከፋ ሁኔታ ላይ ሲሆን በርካታ ወገኖች በድርቁ ችግር ውስጥ ይገኛሉ። ወደ ሚሊዮን የሚጠጉ እንስሳትም መኖ ፍለጋ ወደ አጎራባች ወረዳዎች ተሰደዋል።

በዚሁ አካባቢ ስላለው አስከፊ የድርቅ ሁኔታ ከሰሞኑን ቃላቸውን ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ የሰጡ ወገኖች " ቀጣይ ኑሯችን ተስፋም የለው " ብለዋል።

አርሶ አደር ደሴ ፈንቴ ፤ የምሸሃ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ ባለፈው ክረምት በቀበሌው ምንም አይነት ዝናብ ባለመጣሉ እርሳቸውም ሆኑ ከብቶቻቸው የሚበሉት እንደሌላቸው ተናግረዋል።

በድርቁ ምክንያት የጎረቤቶቻቸው ህይወት እንዳለፈም የገለፁት አርሶ አደሩ ፤ የቤት እንስሳቶቻቸው በመሞታቸው ቀጣይ ኑሯቸው ተስፋ እንደሌለው ስጋታቸውን ገልጸዋል።

ሌላው የ01 ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ነጋሽ ጎበዙ ፤ " 2015 ለ2016 ምንም አይነት ሳርም ሆነ ሌላ ነገር ያልበቀለበት ፤ ታይቶም ተሰምቶ የማይታወቅ በጣም የሚዘገንን ድርቅ ነው ያጋጠመን። ሰው ሁሉ ግራ ተጋብቶ የሚበላው አጥቶ እስሳቱንም ትቶ፣ ሰውም በየቦታው እየሞተ፣ እንስሳቱም እየሞቱ በጣም የከፋ ሁኔታ ላይ ነው ደርሰን ያለነው። በጣም በጣም አስከፊ ነው። " ብለዋል።

እሳቸው የነበራቸው በርካታ ከብቶች እና ፍየሎች በረሃብ ሞተውባቸው እንዳለቁ ተናግረው ፤ " የከብቱስ ይሁን እሳሳት ናቸውና እጅግ የሚያሳዝነው የሰዎች ህይወት እያለፈ መሆኑ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

በዚህ ሳምንት እሳቸው ባሉበት አካባቢ 2 ህፃናት እና 3 አዛውንቶች በአጠቃላይ 5 ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ ተናግረዋል።

ከሰሞኑን በዋግኽምራ ድርቅ ያስከተለውን ጉዳት ከመንግስታዊና 18 ከሚደርሱ መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት የተውጣጣ የባለሞያዎች ቡድን በአካል ተገኝቶ ጥናት ማድረጉ ተነግሯል።

በዚህም ጥናት በሰው እና እስሳት ሞት ላይ ዳሰሳ ተደርጓል።

ምንም እንኳን የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ለድርቅ ተጎጂዎች በሚል የዕለት እርዳታ እንደላከ ቢያሳውቅም የዋግኽምራ አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ድጋፉ በቂ እንዳልሆነ አሳውቋል።

ያለው ችግር የእንስሳት መኖ እጥረት፣ የሰዎች ሰብዓዊ ድጋፍ እጥረት ...ሌሎችም ዘርፈ ብዙ ችግሮች እንደሆነ የገለፀው ፅ/ቤቱ " የክልሉ መንግስት 600 ኩንታል ስንዴ፣ ፌዴራል መንግስት 675 ኩንታል ስንዴ አቅርበዋል፣ ረጂ ድርጅቶች 42 ሚሊዮን ብር የሚሆን በካሽ የሚከፈል አቅርበዋል። አሁን ላይ ለአንድ ወር የሚሆን 25,834 አካባቢ ሰዎችን ሊያግዝ የሚችል ድጋፍ አግኝተናል ይህ ግን ካለው ችግር አንፃር በቂ አይደለም " ብሏል።

ተጨማሪ ድጋፍ ካልተደረገ ተጨማሪ ጥፋት ሊደርስ ይችላል ሲልም ፅ/ቤቱ መግለፁን ቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
😢1.46K😭444155🙏76🕊63😱27😡25👏22🥰8