" Galatoomaa Tour "
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ እና የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጃዋር መሀመድ ወደ በሰኔ እና ሃምሌ ወር 2022 ወደ #ሰሜን_አሜሪካ እና #አውሮፓ እንደሚጓዙ ታውቋል።
አመራሮቹ ጉዟቸውን " Galatoomaa Tour " በሚል የሚያደርጉ ሲሆን በተለያዩ ከተሞች ከደጋፊዎቻቸው ጋር ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ጉዞውን በተመለከተ እስካሁን በሁለቱ ወራት የሚያዳርሷቸውን ከተሞች እና ቀናት ይፋ ከመሆን በዘለለ ለጊዜው በዝርዝር ይፋ የተደረገ መረጃ የለም።
@tikvahethiopia

👍1
#ዓለምአቀፍ
የጣሊያኗ " ላምፔዱሳ " ደሴት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀች።
አዋጁን ያወጀችው ባለፉት ሁለት ቀናት ከአፍሪካ የተነሱ ወደ 8,000 የሚጠጉ ስደተኞች ወደ ደሴቷ መድረሳቸውን ተከትሎ ነው።
ስድተኞች ከተለያዩ አፍሪካ ሀገራት ወደ ጣልያን እየገቡ የሚገኙት በጀልባ ለህይወታቸው እጅግ አስጊ በሆነ መንገድ ተጉዘው ነው ተብሏል።
አንድ ከጊኒ ተነስቶ ጣልያን የገባ ስደተኛ ፤ በሕይወት ተርፎ ጣልያን በመግባቱ ዕድለኛ እንደሆነ ተናግሯል።
ሀገሪቱ አሁን እየገቡ ያሉትን ስደተኞች ወደ ሌሎች የመቀበያ ቦታዎች ለማዘዋወር እየሰራች ነው ተብሏል።
የጣልያን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የትራንስፖርት ሚኒስትር ማትዮ ሳልቪኒ ፤ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ስደተኞች ጣልያን መድረሳቸውን " የጦርነት አነይት ድርጊትን " ይወክላል ብለዋል።
ሚኒስትሩ " ጣሊያንን ለማተራመስ ሆን ተብሎ የተነደፈ ስልት መሆኑን እርግጠኛ ነኝ " ያሉ ሲሆን ከዚህ ሴራ ጀርባ ማን እንዳለ ለመግለፅ አልወደዱም።
" ከዚህ በስተጀርባ አንድ እቅድ እንዳለ እርግጠኛ ነኝ " ያሉት ሚኒስትሩ " ከ100 በላይ ጀልባዎች በጥቂት ሰአታት ውስጥ መድረሳቸው ድንገተኛ ሳይሆን የተደራጀ የጦርነት አይነት ድርጊት ነው። " ብለዋል።
" ይህ የሚያመጣው ተፅእኖ በላምፔዱሳ ላይ ብቻ የሚያበቃ አይደለም ፤ ወደ ሮም፣ ሚላን፣ ቱሪን፣ ኔፕልስ፣ ፓሌርሞ ስለሚሄዱ አሳዛኝ መዘዞችን ያስከትላል። " ሲሉ ተናግረዋል።
ጣልያን ከፍተኛ የስደተኞችን ቁጥር የምታስተናግድ አውሮፓዊት ሀገር ስትሆን በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታየው ያለው ነገር ውጥረት መፍጠሩ ተገልጿል።
በላምፔዱሳ ያለው ከመደበኛ በላይ ሁኔታ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ አስገድዷል።
ባለፉት 2 ቀናት ብቻ 8,000 ከአፍሪካ የተነሱ ስደተኞችን የቀበለችው የጣልያኗ ደሴት ላምፔዱሳ አጠቃላይ የነዋሪዎቿ ብዛት 6000 ብቻ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ።
በሌላ በኩል ፤ የጀርመን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር በጣሊያን በኩል ወደ #አውሮፓ የገቡ አዲስ ስደተኞችን ለጊዜው መቀበል እንዳቆመ አስታውቋል።
ጀርመን እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው ጣልያን ባአውሮፓ ህብረት በኩል በስደተኞች ላይ የተደረሰውን ስምምነት ለማክበር ፈቃደኛ ባለመሆኗ ነው ተብሏል።
የጀርመን መገናኛ ብዙሀን እንደዘገቡት " ከፍተኛ የስደተኞች ጫና አለ " በሚል ምክንያት ጀርመን ከጣሊያን የሚገቡ አዲስ ስደተኞችን ላልተወሰነ ጊዜ መቀበል አቋርጣለች።
ፈረንሳይ በበኩሏ ወደ ግዛቷ ለመሻገር የሚሞክሩ ስደተኞች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱ ከጣሊያን ጋር በሚያዋስናት ድንበር ላይ የሚገኙ የፖሊስ እና የጦር ሃይሎች ጥበቃን በከፍተኛ ሁኔታ እንደምታጠናክር ይፋ አድርጋለች።
ቪድዮ ፦ ከማህበራዊ ሚዲያዎች የተገኘ

👍1.11K😢235❤158👎46😱41🕊29🙏15🥰6