#አክሱም #Axum
በጣሊያን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር የተመራ ልዑካን ቡድን #የአክሱም_ሀውልትን ጎበኘ። ለስራ ጉብኝት ኢትዮጵያ የሚገኘው በጣሊያን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒትሯ አማንኤላ የተመራው ቡድን የአክሱም ሀውልት ጎብኝቷል፡፡ በጉብኝቱ ወቅት በቅርሱ ላይ እየታየ ያለውን ችግር በባለሞያዎቹም ገለፃ ተደርጎላቸዋል።
የልዑካን ቡድን አባላቱ ቅርሱ የተደቀነበትን ችግር በአስቸኳይ ለመንግስታቸው በማሳወቅ ቅርሱ ጥገና የሚደረግበትን መንገድ እናመቻቻለን ብለዋል፡፡ በቀጣይ ሁለት ሳምንታት ዉስጥም ባለሞያዎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚላኩም ተናግረዋል።
ልዑካን ቡድኑ በቅርሱ በአካል የተመለከቱትን ችግር ለመንግስታቸው አቅርበው ምላሽ እንደሚያገኙ እምነት እንዳለቸው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስተር የባህል ዘርፍ ሚኒትር ዴኤታ ክብርት ቡዝነሽ መሰረት ተናግረዋል።
ቅርሱ በዋናነት የከርስ ምድርና የገፀ ምድር ውሃ መጠን መጨመር ምክንያት በሀውልቱ ስር ያለውን አፈር የመሸርሸር አደጋ በማጋጠሙ ሀውልቱ ላይ የመዝመም አደጋ እንዲከሰት አድርጓል ተብሏል፡፡
ምንጭ፡- የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#አክሱም
በአክሱም ከተማ ከነሀሴ 24 ቀን ጀምሮ የሚከበረውን የዓይኒዋሪ/አሸንዳ በዓል ምክንያት በማድረግ ባዛርና ዓውደርእይ ዛሬ ተከፈተ። በትግራይ ክልል የአሸንዳ በዓል በየዓመቱ ከነሀሴ 16 ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት እንደሚከበረው ሁሉ የዓይኒዋሪ በዓል ደግሞ ከነሀሴ 24 ቀን ጀምሮ በአክሱምና አካባቢው በተመሳሳይ መልኩ ይከበራል።
Via #ENA

በአክሱም ከተማ በአንድ ነጋዴ ቤት በሕገ ወጥ መንገድ የተደበቀ 250 ጄሪካን የምግብ ዘይት በቁጥጥር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ። በአክሱም ከተማ በአንድ ነጋዴ ቤት በሕገ ወጥ መንገድ የተደበቀ 250 ጀሪካን የምግብ ዘይት በቁጥጥር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ። የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ኪሮስ አየለ እንዳሉት ግለሰቡና ዘይቱ የተያዘው ጄሪካኖች በቁጥጥር ሥር የዋሉት በኅብረተሰብ ጥቆማ ነው።
Via ENA

የትግራይ ክልል የንግድ፣ ኢንዱስቱሪና ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አብርሃም ተከስተ በዛሬው የሆቴል በምረቃ ወቅት የተናገሩት፦
"እያደገ የመጣውን ኢንቨስትመንት ፍሰት ለማስተናገድ የሚያስችል የአሰራርና አደረጃጀት ሪፎርም እየተከሄደ ነው። አለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎች መከፈት ለቱሪዝም ፍሰትና እድገት የላቀ አስተዋጽኦ አላቸው። በአክሱም ከተማ ዛሬ የተመረቀው ሆቴል ለክልሉ ብሎም ለሀገሪቱ ቱሪዝም ፍሰት መጨመርና እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ ይኖረዋል።"
#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#መቐለ #ራያ #አክሱም #ዓዲግራት
ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ስድስት አባላት ያሉት የባለሙያዎች ቡድን ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ በማቅናት ምልከታ ሊያደርግ ነው፡፡
በግጭቱ ምክንያት ሥራ ያቋረጡትን አክሱም፣ ራያ፣ አዲግራት እና መቐለ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ አገልግሎት ለመመለስ ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል።
እስካሁን ባለው ሁኔታ አክሱም እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ዳግም ወደ አገልግሎት በሚመለሱበት ሁኔታ ላይ ንግግር መጀመሩን በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደር እና መሰረተ ልማት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ለፋና ተናግረዋል።
በቀጣይም ከመቐለ እና አዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ግንኙነት እንደሚጀመር ኃላፊው አመላክተዋል፡፡
በአክሱም ከተማ የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ ተከትሎ፤ ስድስት አባላት ያሉት የባለሙያዎች ቡድን ከሰኞ ጀምሮ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ዋናውን ግቢ ጨምሮ አድዋ እና ሽረ ግቢዎችን በስፍራው በመገኘት ምልከታ ያደርጋል ብለዋል፡፡
ቡድኑ ተቋማቱ በሰው ኃይል፣ በመሰረተ ልማት፣ በቤተ ሙከራ፣ በኔትወርክ፣ በመኝታና መማሪያ ክፍሎች፣ በማስተማሪያ ሆስፒታል፣ በቤተ መጻሕፍት እና ሌሎች አገልግሎቶች ዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ሥራውን ለማስጀመር የሚያስችለውን ሁኔታ ይመለከታል፡፡ #FBC
@tikvahuniversity

👍669🕊646👎84❤82🙏51😱22🥰21😢20