TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ATTENTION

" በድርቅ እና ለረጅም ጊዜ በተከሰተ የፀጥታ ችግር ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ በርካት ሰዎች ለአደጋ ተጋልጠዋል " - የአማሮ ልዩ ወረዳ

• " ከምግብ እጥረት ጋር በተያያዘ ህፃናትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ለረሀብ፣ ለበሽታ እና ለሞት እየተዳረጉ ነው " - የቡርጂ ልዩ ወረዳ

በደቡብ ክልል አማሮ እና ቡርጂ ልዩ ወረዳዎች በተከሰተ ድርቅ ምክንያት ከ136 ሺህ በላይ ሰዎች አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ተገልጿል።

#አማሮ

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የአማሮ ልዩ ወረዳን ዋቢ አድርጎ ባሰራጨው መረጃ ፤ በልዩ ወረዳው ለረጅም ጊዜ ዝናብ ባለመጣሉ በ22 ቀበሌዎች ድርቅ ተከስቷል፡፡

በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በልዩ ወረዳው ከ96 ሺህ በላይ ሰዎች አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል።

በድርቁ ከ3 ሺህ 500 በላይ የቤት እንስሳት በድርቁ ምክንያት መሞታቸው ተገልጿል።

በልዩ ወረዳው የተከሰቱ የፀጥታ ችግሮች የህብረተሰቡን ተጋላጭነት እንዳባባሱት ልዩ ወረዳው አመልክቷል።

በድርቁ እና ለረጅም ጊዜ በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ በርካት ሰዎች ለአደጋ መጋለጣቸው ተገልጿል።

የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በተለያየ ጊዜ እርዳታ ቢያደርግም በልዩ ወረዳው ከከተከሰተው ጉዳት አንፃር ድጋፉ በቂ አለመሆኑን ልዩ ወረዳው አሳውቋል።

#ቡርጂ

የቡርጂ ሶያማ ልዩ ወረዳ በበኩሉ በልዩ ወረዳው በተከሰተው ድርቅ 83 ሺህ 528 ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው አሳውቋል።

በልዩ ወረዳው ከ30 ሺህ በላይ እንስሳት መሞታቸውም ተጠቁሟል።

ከምግብ እጥረት ጋር በተያያዘ ህፃናትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ለረሀብ፣ ለበሽታ እና ለሞት እየተዳረጉ መሆኑ ተገልጿል።

ከክልሉ መንግስት በተጫማሪ የአካባቢው ተወላጆች እና ግለሰቦች እርዳታ ቢያደርጉም በልዩ ወረዳው ከተከሰተው ድርቅ አንፃር የተጎዱ ዜጎችን ለመርዳት በቂ አለመሆኑ ተመላክቷል።

በድርቅ የተጎዱ ዜጎችን ለመርዳት እና መልሶ ለማቋቋም ረጂ ድርጅቶችን ጨምሮ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረታቸውን ወደ ልዩ ወረዳው እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

#ኮንሶ

በኮንሶ ዞን በተከሰተ ድርቅ ከ800 ሺህ በላይ ዜጎች ለአስቸኳይ ድጋፍ መዳረጋቸውን ዞኑ አሳውቋል።

ለተከታታይ 5 ዓመት የተከሰተው የዝናብ መዘግየት እና እጥረት ባስከተለው ድርቅ ለአስቸኳይ ድጋፍ የተዳረጉት 822 ሺ 526 ዜጎቻችን ናቸው።
 
የተከሰተው ድርቅ ዜጎች ላይ አስከፊ ጉዳት ከማድረሱ በፊት በችግር ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ ሊደረግ ይገባል ተብሏል።

Credit : #FBC #SRTA

@tikvahethiopia
👍350😢11710🕊8🙏7🥰3🤔1
#ATTENTION

በአማራ ክልል ፤ የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን አስተዳደር ጥብቅ ክልከላዎች ተጣሉ።

የኦሮሞ ዞን ኮማንድ ፖስት ምን ክልከላዎችን ጣለ ?

- የሰአት እላፊ ገደብ (ባጃጅ 1:00፤ የሰው እንደ አካባቢና እንደ ሚፈጠር ችግር ይወሰን ፆም በመሆኑ ተብሏል) ።

- ስምሪት ከተሰጠው ሃይል ውጭ ጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እንደማይቻል ተገልጿል።

- በማንኛውም ሆቴል መሳሪያ ይዞ መግባት የተከለከለ ሲሆን ፤ በሁሉም ሆቴሎች ፍተሻ እንዲጠናከር ታዟል።

- የፀጥታ ሃይሉን መጠርነፍና ለግዳጅ ዝግጁ ማድረግ ፖሊስና ሚሊሻ ፤ ከፌደራልና መከላከያ ጋር በቅንጅት መስራት አለባቸው ተብሏል።

- የኬላ ላይ ፍተሻ እንዲጠናከር ታዟል።

- የህዝብ ግንኙነት ስራ በተደጋጋሚ እንዲሰራ ታዟል ፤ በዋናነት በመስመር መዝጋት እየተጎዳ ያለው ህዝብ መሆኑ ተመላክቷል።

- ህብረተሰቡ በቀበሌ፣ በመንደር፣ በሰፈር፣ በኬላ፣ በተቋማት ጥበቃ ላይ ተደራጅቶ አካባቢውን የመጠበቅና ለሰላም ለሚከፈል ዋጋ ሃላፊነቱን እንዲወጣ ታዟል።

- የተሳሳተ መረጃ የሚነዙ፣ በአሉቧልታ ህዝብን የሚያሸብሩ፣ ወንጀለኞችን ለመንግስት አጋልጦ እንዲሰጥ ሁሉም በጥብቅ ተማምኖ መንቀሳቀስ አለበት ተብሏል።

- ፈጣን የመረጃ ልውውጥ እንዲደረግ ፤ በየደረጃው ያለው አመራርና ህዝቡ ከፀጥታ ማዋቅሩ ጋር መረጃ መለዋወጥ እንዳለበት ታዟል።

- የመንግስት ተቋማት፣ ባንኮችን ፣ የሀይማኖት ተቋማትን የጥበቃ ሁኔታን እንዲጠናከር ታዟል።

- የአካባቢውን ሁኔታና የዞኑን ክልከላ በማይጣረስ መንገድ ተጨማሪ ክለከላዎችን በወረዳና ከተማ አስተዳደር ኮ/ፖስት ማወጅ እንደሚቻል ተገልጿል።

መረጃው የኦሮሞ ዞን ኮማንድ ፖስት ነው።

@tikvahethiopia
👎1.23K👍77183🕊34😢13🥰8😱8🙏7