ወቅታዊ መራር ቀልድ...
#ሽንኩርት
"ድሮ ሲላጥ ነበር የሚያስለቅሰው ዘንድሮ ስትገዛው ነው..."
√ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲሰራጭ የተገኘ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሽንኩርት
"ድሮ ሲላጥ ነበር የሚያስለቅሰው ዘንድሮ ስትገዛው ነው..."
√ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲሰራጭ የተገኘ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሽንኩርት
በቤንች ሸኮ ዞን የደቡብ ቤንች ወረዳ ገበሬዎች ለሚያመርቱት የሽንኩርት ምርት የገበያ ትስስር እንዲፈጠርላቸው እየጠየቁ ይገኛሉ።
በተለያየ ጊዜ ሽንኩርት በሀገሪቱ ያሉ ገበያዎች ላይ ከዋጋዉ መናር ባለፈ የአቅርቦት ችግሩም ጎልቶ ሲነሳ ይታያል።
በቤንች ሸኮ ዞን የተመረተው የሽንኩርት ምርት ግን የሚያነሳዉ አጥቶ ሊበላሽ መሆኑ ገበሬዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተናግረዋል።
ዞኑ በኩታ ገጠም አሰተራረስ ስልት ከፍተኛ ስራ ሲሰራ ዉጤታማ ከሆኑ ወረዳዎች መካከል አንዱ ሲሆን የደቡብ ቤንች ወረዳ ደግሞ ግንባር ቀደም ነው።
ይሁንና የገበያ ትስስር አለመኖሩ ሽንኩርቱ ከማሳ ሳይነሳ ይቆይ ዘንድ ምክንያት ሆኗል።
በመሆኑም የወረዳዉ ገበሬዎች ሽንኩርቱ ከመበላሸቱ በፊት የሚመለከተዉ አካል ለኛም ሆነ በሀገር ደረጃ ፋይዳ ያለውን ሸንኩርት እንዲነሳ እንዲያደግ ጥሪ አቅርበዋል።
በዚህ አመት በሰሩት ጠንካራ ስራ በሄክታር 1200 ኩንታል ሽንኩርት መገኘቱንና ባጠቃላይ 1622 ሄክታር መሬት በምርት መሸፈናቸዉን ገልጸዋል።
የገበያ ትስስሩን በተመለከተ በተደጋጋሚ መጠየቃቸዉን የሚገልጹት ገበሬዎቹ በዚህ ምክኒያት ችግር ላይ መዉደቃቸዉን ያነሳሉ።
የደቡብ ቤንች ወረዳ አስተዳደር በበኩሉ የዞንና የክልል የንግድ ማህበራት እንዲሁም በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ያሉ ነጋዴዎች ፣ በተማሪ ምገባ ፕሮግራም የሚሳተፉ ትምህርትቤቶችና የከተማ መስተዳድሮች የሰንደይ ማርኬቶች ሽንኩርቱን በማንሳት ገበሬዉን በማገዝ ራሳቸዉም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ጥሪዉን ያስተላለፉት የወረዳዉ ም/ አስተዳዳሪ አቶ ብርሀኑ ተስፋዬ እንደገለጹት ባካባቢዉ ካሁን በፊት ባልነበረ መልኩ ከፍተኛ የሽንኩርት ምርት መመረቱን ጠቅሰዉ ለገበሬዉ የንግድ ትሰስር ለመፍጠር አየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።
መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የቲክቫህ ቤተሰብ ሀዋሳ አባል ነው።
@tikvahethiopia

👍709❤77😱24😢23🕊18👏15👎10🥰7🙏3