ጥንቃቄ‼️
በአዲስ አበባ በአቃቂና አዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች #የኮሌራ_ወረርሽኝ ምልክት ታይቷል፡፡ በአማራ ክልልም በአጣዳፊ ተቅማጥና አተት ወረርሽኝ 14 ሰዎች እንደሞቱ ሪፖርተር የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትን ጠቅሶ አስነብቧል፡፡ በክልሉ ጠቅላላው 190 ሰዎችም በበሽታው እንደተያዙም ተረጋግጧል፡፡ 111ዱ በሰሜን ጎንደር ዞን በጠለምት ወረዳ ሕክምና እያገኙ ነው፡፡ በበየዳ ወረዳ፣ በዋግህምራ ዞን አበርጌሌ ወረዳም በበሽታው የተያዙ አሉ፡፡ በኦሮሚያ ክልል ጭሮና ኦዳ ቡልቱ ወረዳዎችም በበርካታ ሰዎች ላይ የበሽታው ምልክት ታይቷል፡፡ በደቡብ ክልልም መለኮዛ ወረዳ 2 ሰዎች ሞተዋል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia

የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ጥንቃቄ አድርጉ!
በሀዋሳ ከተማ #የኮሌራ በሽታ በመከሰቱ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የክልሉ ጤና ቢሮ አሳሰበ። የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ቀድራላ አህመድ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት በከተማዋ ምልክቱ ከታየባቸው 56 ሰዎች ውስጥ አራቱ በኮሌራ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በከተማዋ አዳሬ እና በሀዋሳ አጠቃላይ ሆስፒታሎች ጊዜያዊ የህክምና ማዕከላት መቋቋማቸውን እንዲሁም በአዳሬ ጤና ጣቢያ በቋሚነት ህሙማን የሚስተናገዱበት ልዩ ስፍራ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።
በሽታው በንጽህና ጉድለት ምክንያት እንደሚመጣና በቀላሉ ተላላፊ በመሆኑ ህብረተሰቡ ያልበሰሉ ምግቦችን ከመመገብና ንጽህናው ያልተጠበቀ ውሀ ከመጠቀም እንዲቆጠብ አሳስበዋል። ለመጠጥ የሚጠቀመውን ውሀ #አፍልቶ በማቀዝቀዝ አልያም በማከሚያ ዘዴ እንዲጠቀም የማይቆም #ተቅማጥና #ትውከት ሲገጥመውም በፍጥነት ወደ ህክምና ተቋም እንዲሄድም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
Via ኢዜአ

#SNNPRS
በደቡብ ክልል ወባና ኮሌራ የመሳሰሉ በሽታዎች ወደ ወረርሽን ደረጃ እንዳይሸጋገሩ ህብረተሰቡ ተገቢውን የመከላከል ስራ እንዲያከናውን የክልሉ ጤና ቢሮ አሳሰበ።
የክልሉ ጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ አቅናው ካውዛ በሀዋሳ እየተካሄደ ባለው የሴክተር መስሪያ ቤቱ ጉባኤ ላይ እንደተናገሩት የአካባቢ ቁጥጥር ስራው እየተዳከመ በመምጣቱ የወባ በሽታን ሙሉ በሙሉ ማስወገድ እየተቻለ ከነአካቴው ወደ ወረርሽኝነት የማደግ ምልክቶች እየታዩ ነው።
በተለይ አመራሩ ህብረተሰቡን በማሳተፍ ሲያከናውነው የነበረው የመከላከል ስራ እየተዳከመ በመምጣቱ በክልሉ መዲና ሀዋሳ ጭምር በሽታው በወረርሽኝ ደረጃ እየታየ መሆኑን አስረድተዋል።
ከወባ በተጨማሪ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች #የኮሌራ በሽታ መከሰቱን ገልፀው በሽታው የህዘቡ የጤና ችግር ሆኖ እንዳይቀጥል በሽታው በተከሰቱባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ባለሙያዎችና አመራሮች ጠንካራ የክትትልና የቁጥጥር ስራ መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።