#ኢትዮጵያ2016
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳሰት ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ የ2016 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓልን በማስመልከት ለመላው ምዕመናን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በዚህም መልዕክታቸው ላይ ፤ " አሁን #አገራችን ያለችበት ሁኔታ እጅግ አስቸጋሪና አሳሳቢ ሆኖ እናየዋለን፡፡ " ብለዋል።
" ምክንያቱም አገራችን በፈጠራት ፈጣሪዋ ምንም ሳታጣና ሳይጎድላት እኛ በእግዚአብሔር አርአያና አምሳል የተፈጠርነው ምድራውያን ሰዎች እርስ በርሳችን በመገፋፋትና በመጋጨት ያለማቋረጥ መጠፋፋትንና መገዳደልን የምናስተናግድ ሆነናል፡፡ " ሲሉ ገልጸዋል።
ሁሉም ባለድርሻ አካላት በሁሉም መስክ በአስተዋይነትና በጥበብ ነባራዊውን የጥፋት ሁኔታ ከባለፈው የስቃይ ጊዜ በመማር የሁሉንም የአገሪቱ ሕዝቦች ድምጽ በመስማት የወንድማማቾችን ግጭት በሕዝቦች ውይይት፣ በዕርቅና በሰላም ብሎም በእውነትና በመቻቻል መንፈስ ነገሮችን በማሰከንና የአብሮነትና የሰላም ጉዞ በእዲስ ዓመት እንዲመጣልን አጥብቀን እንመኛለን ብለዋል።
ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ፤ " ዜጎች በሰላምና በደስታ በልማትና በሥራ እንዲተጉና እንዲሳተፉ ታዳጊዎች ልጆቻችንም በተስፋና በፍቅር የሚያድጉባት አገር እንድትኖረን መልካም መሠረት ለመጣል እንድንተጋ ሁሉንም በእጽንዖት እንጠይቃለን " ብለዋል።
(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia

👍404❤86👎33🕊9😱8🥰6🙏3