TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የታሰሩት የምክር ቤት አባላት የት ናቸው ? በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተያዙ የም/ቤት አባላት ታስረውበት ከነበረው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የማቆያ ቦታ እንደሌሉ እና ያሉበትን ቦታ ማወቅ እንዳልቻሉ ከጠበቆቻቸው አንዱ ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል ተናግረዋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እንዲሁም በምክር ቤቱ የመንግሥት ወጪ፣ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ…
#EHRC

አዋሽ አርባ ላይ ታስረው የሚገኙ አብዛኞቹ እስረኞች ለእስር የተዳረጉት #በብሔር ማንነታቸው ብቻ መሆኑን እንደሚያምኑ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለን ጨምሮ 5 የኮሚሽኑ ባለሙያዎች የሚገኙበት ቡድን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሠረት በቁጥጥር ሥር ውለው አዋሽ አርባ አካባቢ በሚገኘው የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕራብ ዕዝ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ ውስጥ ተይዘው የሚገኙትን ታሳሪዎች ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. ጎብኝቷል።

እነዚህ ታሳሪዎች ፦
- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ፣
- የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ዮሐንስ ቧያለው፣
- የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል የሆኑት ዶ/ር ካሳ ተሻገር፤
- ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው፣ ጋዜጠኛ አባይ ዘውዱ፣ እና ቴዎድሮስ ዘርፉ፤
- የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባል አቶ ስንታየሁ ቸኮል፣ አቶ በለጠ ጌትነት፤
- በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ በኃላፊነት ይሠሩ የነበሩት አቶ ከፋለ እሱባለውን ጨምሮ በአጠቃላይ 53 ወንድ እስረኞች ሲሆኑ ከአዲስ አበባ ከተማና ከአማራ ክልል የተለያዩ ቦታዎች በተለያየ ጊዜ ተይዘው ከነሐሴ 15 ቀን እስከ ነሐሴ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ ወደ አዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ የሚገኝ ጊዜያዊ / መደበኛ ያልሆነ ማቆያ ጣቢያ የተወሰዱ ናቸው፡፡

ኮሚሽኑ በተለመደው አሠራሩ መሠረት ታሳሪዎቹን ለብቻቸው አነጋግሯል፣ ቦታውን ጎብኝቷል እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸውን የፖሊስ ኃላፊዎች አነጋግሯል፡፡

የፖሊስ ኃላፊዎች ለኮሚሽኑ እንደገለጹት ፤ ታሳሪዎችን ወደዚህ ጊዜያዊ ማቆያ ጣቢያ ማምጣት ያስፈለገው አዲስ አበባ የሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ማቆያ ጣቢያ ላይ ከፍተኛ መጣበብ በመፈጠሩ መሆኑን ገልጸዋል።

ታሳሪዎች ምን አሉ ?

እጅግ አብዛኛዎቹ ታሳሪዎች ብሔራቸው #አማራ፣ እምነታቸው ኦርቶዶክስ ክርስቲያን መሆኑንና ለእስር የተዳረጉት ደግሞ #በብሔር ማንነታቸው ብቻ መሆኑን እንደሚያምኑ ገልጸዋል።

ከፊሎቹ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተያዙበትና ቤታቸው በተበረበረበት ወቅት በራሳቸውና በቤተሰብ አባል ላይ ድብደባ፣ ብሔር ተኮር ስድብ፣ ማጉላላት፣ ዛቻና ማስፈራራት እንደደረሰባቸው ሆኖም በፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ከሆነ በኋላ የተፈጸመ ድብደባ ወይም አካላዊ ጥቃት አለመኖሩን አመልክተዋል።

ከፊሎቹ በተለይም ከአማራ ክልል ተይዘው የመጡ ሰዎች ከተያዙበት ጊዜ ጀምሮ ቤተሰቦቻቸው የት እንዳሉ እንኳን እንደማያውቁ አስረድተዋል።

ታሳሪዎቹ የአዋሽ አርባ አካባቢ እጅግ ከፍተኛ ሙቀት ያለው በመሆኑና ከአካባቢው የአየር ጠባይ እንዲሁም ቦታው የወታደራዊ ካምፕ እንጂ መደበኛ የተጠርጣሪዎች ማቆያ ስፍራ ስላልሆነ ለጤንነታቸው፣ ለደኀንነታቸውና ለሕይወታቸው ሥጋት እንዳላቸው፣ አልባሳትን ጨምሮ ከቤተስብ የሚፈልጉትን አቅርቦት ለማግኘት እንዳልቻሉ፣ ከፊሎቹ በሥራቸውም ሆነ በግል ሕይወታቸው ፈጽሞ በፖለቲካ ነክ ጉዳይ ተሳትፎ እንደሌሉና እንዴት ለእስር እንደበቁ መገረማቸውንና መደንገጣቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ፤ ከፖሊስ ኃፊዎች ጋር ውይይት ያደረገ ሲሆን በእስር ወቅት ተፈጽመዋል ስለተባሉ የሥነ ምግባር ጥሰቶች ተገቢው ማጣራት እንዲደረግ፣ ታሳሪዎቹ ከቤተሰብ ለሚፈልጉት አቅርቦት አዲስ አበባ በሚገኘው የፖሊስ ቢሮ አማካኝነት እንዲመቻች፣ ከቤተስብ መገናኛ ስልክና ጉብኝት ለሚፈልጉም በአፋጣኝ እንደሚመቻች መግባባት ላይ ተደርሷል።

(ከኢሰመኮ የተላከልን መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
👍1.97K😢386👎248204🕊27🙏25👏21🥰11😱9