TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#MoE

" የመውጫ ፈተናውን በተደጋጋሚ ወስዶ ማለፍ ያልቻለ ተማሪ ከዲግሪ በታች ባሉ ደረጃዎች ምዘና ወስዶ መቀጠል እንዲችል የሚያደርግ የብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ ነው " - ትምህርት ሚኒስቴር

250 ሺ ለሚጠጉ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በመጪው #ሐምሌ_ወር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ለሚመረቁ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እየተጠናቀቅ እንደሚገኝ በሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት ማሻሻያ ዴስክ ኃላፊ ሰይድ መሐመድ ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር የመውጫ ፈተናውን በተሳካ ሁኔታ ለመስጠት ከመንግሥት እና ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በቅርበት እየሠራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የመውጫ ፈተናውን ወስደው ማለፍ ያልቻሉ ተማሪዎች ደጋግመው መፈተን የሚችሉበት ዕድል መኖሩን ኃላፊው አመልክተዋል።

ፈተናውን በተደጋጋሚ ወስዶ ማለፍ ያልቻለ ተማሪ ከዲግሪ በታች ባሉ ደረጃዎች ምዘና ወስዶ መቀጠል እንዲችል የሚያደርግ የብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ በትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን በመዘጋጀት ላይ ይገኛል ብለዋል።

ይሁን እንጂ ተፈታኙ ለዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ዝግጁ ነኝ ብሎ ባሰበ ጊዜ ፈተናውን መውሰድና ማለፍ ከቻለ የዲግሪ ማረጋገጫ ማግኘት እንደሚችል ገልጸዋል።

የመውጫ ፈተናው በ #ኦንላይን እንደሚሰጥ ያመለከቱት ኃላፊው፤ ለዚህ ያመች ዘንድም የሶፍትዌር ማዘጋጀትን ጨምሮ ፈተናውን በስኬት መስጠት የሚያስችሉ ሥራዎች በመሠራት ላይ ናቸው ብለዋል።

ተማሪዎች ዋናውን ፈተና ከመፈተናቸው በፊት ሞዴል ፈተናዎች እንደሚወስዱ ጠቅሰዋል፡፡ 

#ኢፕድ

@tikvahuniversity @tikvahethiopia
👎913👍67963🤔29😱20😢10🙏8🕊8🥰5