TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ📸ርሑስ #ኣሸንዳ 2011 ዓ/ም #ETHIOPIA
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን አደረሰን!

Eden Gebreselassie, Trhas Tareke and Rahel Haile - #Ashenda | #ኣሸንዳ #ETHIOPIA #TIGRAY

ኢትዮጵያ ድንቅ ባህል ያላት ሀገር ናት!

ኢትዮጵያን መውደድ የሚገለፀው እርስ በእርስ በመከባበር ነው ፤ ህዝቦቿን በማፍቀር ነው ፤ ባህሎቿን በመንከባከብ ለመጪው ትውልድ በማስተላለፍ ነው !! ሁላችንም ሀገራችን ባሏት ተነግረው በማያልቁ ድንቅ ባህሎች እና ትውፊቶች #ልንኮራ ይገባናል። አሁን ያለነው ትውልድም ኢትዮጵያንና ባህሎቿን ሳንበርዝ ለመጭው ትውልድ የማውረስ ኃላፊነት አለብን።

እንኳን አደረሰን!

#14MB

@tsegabwolde @tikvahethiopia
1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን አደረሰን!

Eden Gebreselassie, Trhas Tareke and Rahel Haile - #Ashenda | #ኣሸንዳ #ETHIOPIA #TIGRAY

ኢትዮጵያን መውደድ የሚገለፀው እርስ በእርስ በመከባበር ነው ፤ ህዝቦቿን በማፍቀር ነው ፤ ባህሎቿን በመንከባከብ ለመጪው ትውልድ በማስተላለፍ ነው !! ሁላችንም ሀገራችን ባሏት ተነግረው በማያልቁ ድንቅ ባህሎች እና ትውፊቶች #ልንኮራ ይገባናል። አሁን ያለነው ትውልድም ኢትዮጵያንና ባህሎቿን ሳንበርዝ ለመጭው ትውልድ የማውረስ ኃላፊነት አለብን።

እንኳን አደረሰን!
#14MB
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኣሸንዳ

የዘንድሮው የኣሸንዳ በዓል " ለሰላም ፣ ለመዳንና ለመልሶ ግንባታ " በሚል በትግራይ እንዲሁም ከትግራይ ውጭ ባሉ አካባቢዎች ላይ ይከበራል።

ከትግራይ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በተገኘው መረጃ በዓሉ በቅድሚያ የሚከበረው በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ስር በሚገኙ ነፃ በሆኑ አካባቢዎች ሲሆን በመቀጠል አዲስ አበባ ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች ይከበራል።

ነሐሴ 16 በአዲስ አበባ ከተማ በዓሉ እንዲከበር እንቅስቃሴ ሲደረጉ የነበሩ ሌሎች አካላት እንደነበሩ የጠቆመው ቢሮው በመናበብ ችግር የተፈጠረ መሆኑ መግባባት ላይ በመደረሱ በዓሉ ነሐሴ 16 አዲስ አበባ ላይ እንደማይከበር አሳውቋል።

የዘንድሩው በዓል የሚከበረው የትግራይን አሁናዊ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ ትውፊት እና ክብሩን በጠበቀ መልኩ ሲሆን ትግራይ ላይ ከተከበረ በኃላ በአዲስ አበባ እንደሚከበር ተገልጿል።

አዲስ አበባ ላይ ለሚከበረው በዓል አቅጣጫ ተቅምጦ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑንና ከከተማው አስተዳደር እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ንግግር እየተደረገ ስለመሆኑ የትግራይ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ አሳውቋል።

ባለፉት ዓመታት አስከፊው ጦርነት ምክንያት በዓሉ በሚፈለገው ልክ ሳይከበር ቀርቷል።

ዘንድሮ ያለውን ሰላም ተከትሎ በርካታ ሰዎች ከተለያዩ የኢትዮጵያ እና የዓለም ክፍሎች ለዚሁ በዓል ትግራይ ይገኛሉ ፤ በክልሉ የተዳከመው የቱሪስት እንቅስቃሴም መነቃቃት ያሳያል ተብሎ ይጠበቃል።

የኣሸንዳ በዓል ፍቅር ፣ ይቅር ባይነትና መልካም ተግባቦት በተግባር የሚንጸባረቅበት በዓል ሲሆን የበዓሉ ይዘት በዋናነት ህብረተሰቡ ውስጥ ያሉ መልካም ተግባቦቶች፣ ፍቅርንና ይቅር ባይነት ላይ ያነጣጠረ ነው።

በዓሉ የሌሎች ሃሳቦች፣ ጭፈራዎችና ትእይንቶች እንዲታዩ የሚጋብዝ ከመሆኑ ባለፈ የሃይማኖትና የብሔር ልዩነት አይንፀባረቅበትም።

በዚህ በዓል ላይ ህብረትን የሚሰብኩ ፣ መድልዎን የሚጠየፉ እና ለሰው ክብርን የሚያጎናጽፉ መልዕክቶች ይተላለፉበታል።

@tikvahethiopia
👍964👎261172🕊49🥰11👏10🙏4😱3😢3
#ኣሸንዳ

" ኣሸንዳ ለሰላምና ለዳግመ ግንባታ " በሚል በመቐለ የውይይት መድረክ  ተካሂዷል።

በዚሁ መድረክ የተገኙት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜደንት ጌታቸው ረዳ ፤ " ባለፉት ሶስት የጦርነት አመታት የኣሸንዳ ባለቤት በሆኑ ሴት ልጃገረዶች እጅግ አስከፊ ፆታዊ ጥቃትና በደል መፈፀሙ መርሳት አይገባም " ሲሉ ተናግረዋል።

" የኣሸንዳ በዓል ስናከብር በአስከፊው ጦርነት ምክንያት በሴት አህቶቻችን የደረሰው በደል እንዳይረሳና አጥፊዎች በመጠየቅ የህገ የበላይነት ማረጋገጥ እንዲቻል በሚያወሱ መልእክቶች በመታጀብ ሊሆን ይገባል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ቱባ ባህሎቻችን ተውበን ስናከብር በጦርነቱ ምክንያት ጥቃት የደረሳቸው ሴቶች በማገዝ ፣ ከቄያቸው የተፈናቀሉ ወገኖች በማስታወስ ሊሆን ይገባል ያሉት " ፕረዚደንት ጌታቸው " የኣሸንዳ ልጆች በወረራ የተያዙ መሬቶች በሰላም ስምምነቱ መሰረት በሰላማዊ መንገድ እንዲመለሱ እየተደረገ ያለውን ትግል በመደገፍ በዓላቸው ማድመቅ አለባቸው " ብለዋል።

" ባለፉት ሶስት አመታት በተካሄደው ዘግናኝ ጦርነት ምክንያት በዓሉ በአደባባይ መከበር አልቻለም"  ያሉት  ደግሞ የክልሉ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር አፅብሃ ገ/እግዚአብሔር  ናቸው።

ዶ/ር አፅብሃ ፤ የአሸንዳ ክብሮችን በማጉላት በአሉ ለአንድነት ፣ ለልማት ፣ ለሰላምና ዴሞክራሲ ማጠናከሪያ ሊውል ይገባዋል።

በውይይት መድረኩ  " የአሸንዳ ክብሮች ከፍትህ ፤ ከተጠያቂነትና ከስነ-ልቦናዊ ማገገም አንፃር " በሚል ርእስ ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀረቡ ዶ/ር ትካቦ ገ/ስላሴ ደግሞ " በዓሉ ሴቶች ተውበው በዘፈንና ጭፈራ የሚያከብሩት የነፃነት መግለጫ ነው " ብለዋል።

" ኣሸንዳ በዓለም ከሚከበሩት የሴቶች የአደባባይ በዓላት የሚመደብ በራሳቸውና በሌላው ማህበረስብ የደስታ ስሜት የመፍጠር አቅምና አቀራርብ ያለው ነው " ያሉት ዶ/ር ትካቦ " በዓሉ ከመጤ ልምድ በመጠበቅ ለአገር ውስጥና ለውጭ ቱሪስቶች መስህብ ማዋል ይገባል " ብለዋል።

የበዓሉ ባለቤቶች የሆኑ ሴት ልጃገረዶች የታደሙበት የውይይት መድረኩ ፣ የመቐለ ዩኒቨርስቲ ፣ የባህልና ቱሪዝም ቢሮና የትግራይ ቴሌቪዥን በመተባበር እንዳዘጋጁት የቲክቫህ ሪፓርተር ከቦታው ዘግቧል።

@tikvahethiopia
👍629👎30678🥰11🙏10🕊9
#ኣሸንዳ #መቐለ

በመቐለ የኣሸንዳ በዓል ያለፀጥታ ችግር በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል።

ዘንድሮ የተገኘውን ሰላም ተከትሎ በርካታ ቁጥር ያለው ዜጋ በኣሸንዳ በዓል ላይ ለመካፈል ትግራይ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።

የመቐለ ከተማ ወንጀል መከላከል ኃላፊ ኮማንደር ሰለሞን በላይ ለትግራይ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ፤ የዘንድሮውን የኣሸንዳ በዓል ለማክበር ከተለያዩ የሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገራት የሚመጡ ታዳሚዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ እና ያለምንም የፀጥታ ስጋት በዓሉን እንዲያሳልፉ ዝግጅቶች ሁሉ መጠናቀቁን ገልጸዋል።

ኮማንደር ሰለሞን ፤ " የዘንድሮውን በዓል ለማክበር የሀገር እና የክልል ሁኔታን የሚመጥን እቅድ ተዘጋጅቷል ፤ ለበዓሉ የሚመጥን የፀጥታ አካላትም ዝግጅታቸውን ጨርሰው እየተጠባበቁ ይገኛሉ " ብለዋል።

በዓሉ ሲከበር የትግራይ ህዝብ በጦርነት ምክንያት የማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ስነልቦናዊ ቀውስ በደረሰበት ወቅት ቢሆንም የተገኘውን የሰላም ጭላንጭል በመጠቀም ባህላዊ ትውፊቱን ለማስቀጠል ሁሉም የበኩሉን ሚና እንዲጫወት ለክልሉ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethiopia
👍813👎200111🕊52🥰25😱6👏5