TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.61K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ📸ርሑስ #ኣሸንዳ 2011 ዓ/ም #ETHIOPIA
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን አደረሰን!

Eden Gebreselassie, Trhas Tareke and Rahel Haile - #Ashenda | #ኣሸንዳ #ETHIOPIA #TIGRAY

ኢትዮጵያ ድንቅ ባህል ያላት ሀገር ናት!

ኢትዮጵያን መውደድ የሚገለፀው እርስ በእርስ በመከባበር ነው ፤ ህዝቦቿን በማፍቀር ነው ፤ ባህሎቿን በመንከባከብ ለመጪው ትውልድ በማስተላለፍ ነው !! ሁላችንም ሀገራችን ባሏት ተነግረው በማያልቁ ድንቅ ባህሎች እና ትውፊቶች #ልንኮራ ይገባናል። አሁን ያለነው ትውልድም ኢትዮጵያንና ባህሎቿን ሳንበርዝ ለመጭው ትውልድ የማውረስ ኃላፊነት አለብን።

እንኳን አደረሰን!

#14MB

@tsegabwolde @tikvahethiopia
1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን አደረሰን!

Eden Gebreselassie, Trhas Tareke and Rahel Haile - #Ashenda | #ኣሸንዳ #ETHIOPIA #TIGRAY

ኢትዮጵያን መውደድ የሚገለፀው እርስ በእርስ በመከባበር ነው ፤ ህዝቦቿን በማፍቀር ነው ፤ ባህሎቿን በመንከባከብ ለመጪው ትውልድ በማስተላለፍ ነው !! ሁላችንም ሀገራችን ባሏት ተነግረው በማያልቁ ድንቅ ባህሎች እና ትውፊቶች #ልንኮራ ይገባናል። አሁን ያለነው ትውልድም ኢትዮጵያንና ባህሎቿን ሳንበርዝ ለመጭው ትውልድ የማውረስ ኃላፊነት አለብን።

እንኳን አደረሰን!
#14MB
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኣሸንዳ

የዘንድሮው የኣሸንዳ በዓል " ለሰላም ፣ ለመዳንና ለመልሶ ግንባታ " በሚል በትግራይ እንዲሁም ከትግራይ ውጭ ባሉ አካባቢዎች ላይ ይከበራል።

ከትግራይ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በተገኘው መረጃ በዓሉ በቅድሚያ የሚከበረው በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ስር በሚገኙ ነፃ በሆኑ አካባቢዎች ሲሆን በመቀጠል አዲስ አበባ ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች ይከበራል።

ነሐሴ 16 በአዲስ አበባ ከተማ በዓሉ እንዲከበር እንቅስቃሴ ሲደረጉ የነበሩ ሌሎች አካላት እንደነበሩ የጠቆመው ቢሮው በመናበብ ችግር የተፈጠረ መሆኑ መግባባት ላይ በመደረሱ በዓሉ ነሐሴ 16 አዲስ አበባ ላይ እንደማይከበር አሳውቋል።

የዘንድሩው በዓል የሚከበረው የትግራይን አሁናዊ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ ትውፊት እና ክብሩን በጠበቀ መልኩ ሲሆን ትግራይ ላይ ከተከበረ በኃላ በአዲስ አበባ እንደሚከበር ተገልጿል።

አዲስ አበባ ላይ ለሚከበረው በዓል አቅጣጫ ተቅምጦ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑንና ከከተማው አስተዳደር እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ንግግር እየተደረገ ስለመሆኑ የትግራይ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ አሳውቋል።

ባለፉት ዓመታት አስከፊው ጦርነት ምክንያት በዓሉ በሚፈለገው ልክ ሳይከበር ቀርቷል።

ዘንድሮ ያለውን ሰላም ተከትሎ በርካታ ሰዎች ከተለያዩ የኢትዮጵያ እና የዓለም ክፍሎች ለዚሁ በዓል ትግራይ ይገኛሉ ፤ በክልሉ የተዳከመው የቱሪስት እንቅስቃሴም መነቃቃት ያሳያል ተብሎ ይጠበቃል።

የኣሸንዳ በዓል ፍቅር ፣ ይቅር ባይነትና መልካም ተግባቦት በተግባር የሚንጸባረቅበት በዓል ሲሆን የበዓሉ ይዘት በዋናነት ህብረተሰቡ ውስጥ ያሉ መልካም ተግባቦቶች፣ ፍቅርንና ይቅር ባይነት ላይ ያነጣጠረ ነው።

በዓሉ የሌሎች ሃሳቦች፣ ጭፈራዎችና ትእይንቶች እንዲታዩ የሚጋብዝ ከመሆኑ ባለፈ የሃይማኖትና የብሔር ልዩነት አይንፀባረቅበትም።

በዚህ በዓል ላይ ህብረትን የሚሰብኩ ፣ መድልዎን የሚጠየፉ እና ለሰው ክብርን የሚያጎናጽፉ መልዕክቶች ይተላለፉበታል።

@tikvahethiopia
👍964👎261172🕊49🥰11👏10🙏4😱3😢3