#ጀርመን
በፍራንክፈርት የስምንት አመት ልጅ ከነ አናቱ ወደ ባቡር ሐዲድ ገፍቶ በመጣል የተጠረጠረው ኤርትራዊ በጥምር ግድያ ወንጀል ክስ ሊመሰረትበት ነው፣ የ40 አመቱ ተጠርጣሪ ባለትዳርና የ3 ልጆች አባት ነው። ስዊትዘርላንድ ከገባ 13 አመታት አስቆጥሯል።
Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ከዓለም ዙሪያ ፦
➤ #ሳዑዲ_አረቢያ ፦ ሳዑዲ አረቢያ የሃጅ ተጓዦችን እየተቀበለች ትገኛለች። ከቀናት በፊት የመጀመሪያው የሃጅ ተጓዦች ቡድን ከኢንዶኔዥያ ወደ ሳዑዲ መግባቱ ይታወሳል። ዛሬ ባገኘነው መረጃ እስከ ትላንት እሁድ ድረስ ከተለያዩ ሀገራት ለሃጅ ጉዞ ሳዑዲ የገቡ ተጓዦች 955 ደርሰዋል። ሳዑዲ አረቢያ ዘንድሮ ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ 1 ሚሊዮን የሃጅ ተጓዦችን እንደምታስተናግድ ይታወቃል።
➤ #ጀርመን ፦ የጀርመኑ መኪና አምራች ኩባንያ መርሴዲስ-ቤንዝ 1 ሚሊዮን ገደማ አሮጌ መኪናዎችን ለጥገና ጠርቷል። ኩባንያው እኚህ መኪናዎች ፍሬናቸው ችግር አለባቸውና ጠግኜ ልመልስላችሁ ብሏል። ኩባንያው መኪኖቹ ከፍተኛ በሆነ ዝገት ምክንያት የፍሬን ሰርዓታቸው ተገቢውን ሥራ ላይሰራ ይችላል ብሏል። ጀርመን ያሉ 70 ሺህ መኪናዎችን ጨምሮ ከ993 ሺህ በላይ መኪናዎች መጠገን አለባቸው።
➤ #UK ፦ ዩናይትድ ኪንግደም ለመጀመርያ ጊዜ ኤም 270 የተባሉ ረዥም ርቀት ተወንጫፊ ሚሳኤሎችን ለዩክሬን ልትሰጥ ነው። እነዚህን እጅግ ዘመናዊ ሮኬት ማስወንጨፍያ መሣሪያዎች መቼ እና በምን ያህል መጠን ወደ ዩክሬን እንደምትልክ አልገለጸችም።
➤ #ሩስያ ፦ የሩስያ ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለአሜሪካ ማስጠንቀቂያ ልከዋል። ሀገሪቱ ለዩክሬን የጦር መሣሪያ ልገሳ እንድታቆም ያስጠነቀቁ ሲሆን ይህ የማይሆን ከሆነ ሩሲያ በዩክሬን የምታደርሰው ጥቃት መጠኑ እየሰፋ እንደሚመጣ ገልፀዋል። አሜሪካ ባለፈው ሳምንት ዘመናዊ ተወንጫፊ ሚሳኤል ሲስተምን ወደ ዩክሬን ልካለች። አሜሪካ መሣሪያውን ብትሰጥም ዩክሬን ይህን መሣሪያ ወደ ሩሲያ ግዛት እንዳትተኩስ አሳስባ ነው።
#ቢቢሲ #ሳዑዲጋዜቴ #ኤፒ
@tikvahethiopia

👍3
ከስራ ቦታ እንደወጡ ያልተመለሱት አቶ ኢብራሂም በያን !
በኦሮሚያ ክልል ሰበታ ከተማ፣ ቀበሌ 04 ነዋሪ እና የሐጂ መሐመድ ሪል ስቴት ምክትል ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ኢብራሂም በያን ሠይድ መጋቢት 29/2014 ከሥራ ቦታ እንደወጡ እስከአሁን አለመመለሳቸውን ፤ የት እንዳሉም እንደማይታወቅ ቤተሰቦቻቸው ገልጸዋል።
በወቅቱ አቶ ኢብራሂም ከሥራ ወጥተው ወደ መኖሪያ ቤታቸው በመመለስ ላይ እያሉ የስልክ ግንኙነት እንደነበራቸው የገለፁት ቤተሰቦቻቸው ከምሽቱ 3 ሰዓት አካባቢ ግን የስልክ ግንኙነቱ መቋረጡን፤ የስልክ ግንኙነቱ ሲቋረጥም በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ቦታው #ጀርመን_አደባባይ አካባቢ እንደነበሩን አታውሰዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የተለያዩ የፖሊስ ጣቢያዎች ፣ ትራፊክ ጽ/ቤቶች፣ ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች ጠይቀውም ምንም ፍንጭ ባለማግኘታቸው ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንዳመለከቱ የገለጹት የአቶ ኢብራሂም ወንድም አብዱልሀዲ በያን እና የቅርብ ቤተሰባቸው ሩቅያ ሀሰን በወቅቱ ጉዳዩን መዝግቦ መርማሪ በመመደብ ተከታትሎ እንደሚያሳውቋቸው ፖሊስ እንደተነገራቸው ገልጸዋል።
ቢሆንም ግን ከመጋቢት 29 ቀን 2014 እስከ ዛሬ ምንም አይነት መፍትሄ እንዳልተገኘ አስረድተዋል።
አቶ ኢብራሂም ለረጅም ጊዜያት በመጥፋታቸውና ያሉበት ቦታ ባለመታወቁ ቤተሰቦቻቸው በጭንቀት ውስጥ የሚገኙ ሲሆን አሁንም ፍለጋቸውን መቀጠላቸውን ገልፀዋል።
የኢብራሂም ቤተሰቦች አቶ ኢብራሂምን ያየ ወይንም ያሉበትን ቦታ የሚያውቅ በስልክ 0911149306፣ 0911616199 ፣ 0911438549 ላይ በመደወል እንዲያሳውቃቸው ተማፅነዋል።

👍383😢377🙏34😱15❤7🥰5👏4