TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ፌደራል ፖሊስ⬇️

የህዝቡን #ደህንነት እና #ሰላም ለመጠበቅ ሲል መንግስት አስፈላጊውን #እርምጃ እንደሚወስድ የፌደራል ፖሊስ ገለፀ።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ከሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው ላይ የመንግስት ትእግስት #ገደብ እንዳለው በመግለፅ #ጉልበተኞችን እንደማይታገስ አስታውቀዋል።

አሁን ላይ እየተስተዋሉ ያሉት #ሁከቶች #በሁለት የፖለቲካ ድርጅቶች ስም የተቀነባበሩ መሆናቸውን ኮሚሽነር ጀነራሉ ጠቁመዋል።

ባለፉት ሦስት ቀናት በቡራዩና አካባቢው ብዛት ያላቸው ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን በመጠቆም፥ በተለያዩ ቦታዎች ተዘርፈው የነበሩ ንብረቶችን የማሰባሰብ ስራ መሰራቱንም ነው ያስታወቁት።

በአጠቃላይም በቡራዩ ከ300 አስከ 400 የሚደርሱ ተጠርጣሪዎች ሲያዙ በአዲስ አበባ ደግሞ ከ300 በላይ ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ #ገንዘብ ተከፍሏቸው ብሄርን ከብሄር ለማጋጨት እንዲሁም ብሄርን መሰረት ያደረጉ ስድቦችንም ጭምር በማሰራጨት #የተጠረጠሩ ግለሰቦች መያዛቸውንም አንስተዋል።

ይህ ድርጊት #በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባና በአርባ ምንጭ መታየቱን ጠቅሰዋል።

ኮሚሽነሩ በቡራዩና አካባቢው የተፈፀመውን ግድያ ለማውገዝ በርካታ ሰላማዊ ሰው መውጣቱን ጠቅሰው #የተወሰኑ ቡድኖች ግን አዝሚሚያቸው ሌላ ነበር ብለዋል።

ከእነዚህ የተወሰኑ ግለሰቦች መካከልም #ቦምብ ይዘው የነበሩ በህብረተሰቡ ትብብር መያዛቸውን ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በፒያሳና በመርካቶ #ለዝርፊያ የሚቃጡ ግለሰቦች እንደነበሩ ነው የጠቀሱት።

የተወሰኑት የጸጥታ ኃይሎች ደግሞ ጠብመንጃ ለመንጠቅ ሙከራ ያደረጉ ሲሆን በዚህም ከጸጥታ ኃይሉ ጋር #ግብግብ ገጥመው ነበር ብለዋል።

ይህንንም ተከትሎ የአምስት ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን፥ ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች መቁሰላቸውን ገልጸዋል።

በአጠቃላይ ይህ ግርግር ሆን ተብሎ የተጀመረውን ለውጥ #እንዳይሳካ #ታስቦበት የተከናወነ መሆኑን ነው ያነሱት።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update "...ጉባኤተኛው ገና ያላፀደቀውና በተለይም የድርጅቱ ሊቀመንበር ጓድ ደመቀ መኮነን በክብር #ይሰናበቱ አይሰናበቱ የሚለው በጉባኤተኛው ሰፊ ክርክር እየተካሄደበት ያልተጠናቀቀ በመሆኑ ገና #ውሳኔ ላይ አልተደረሰም፡፡ ጉባኤው #በዛሬው ውሎ በእንጥልጥል ያደሩ በክብር በትምህርትና በአንባሰደርነት ለማእከላዊ ኮሚቴነት በማይወዳደሩ አመራሮች ዙሪያ
የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህም በተጨማሪ አዲስ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላትንና የድርጅቱን ስራአስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን የድርጅቱን ሊቀመንበርና ም/ሊቀመንበር እንዲሁም የኦዲትና ቁጥጥር ኮሚሽን አመራር አካላትን ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡"

ምንጭ፦ANDM CC office
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ የአስተዳደር መዋቅር‼️

3 ዞኖችና 44 ተጨማሪ ወረዳዎች የተካተቱበት አዲስ የአስተዳደር መዋቅር ረቂቅ አዋጅ ለደቡብ ክልል ምክር ቤት ቀረበ።

ረቂቅ አዋጁ የደቡብ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ ባለው 8ተኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ነው #በዛሬው እለት የቀረበው።

አዲሱ ረቂቅ አወቃቀር የመንግስት አገልግሎትን ለወረዳ ማዕከላት ቅርብ ለማድረግ የሚያግዝ መሆኑ ታምኖበታል።

በአዲሱ የአስተዳደር እርከን መሠረት፣ ካሁን በፊት ልዩ ወረዳ የነበረው ሀላባ ወደ ዞንነት ሲያድግ ዌራ ዙሪያ፣ ድጆ ዌራና ድጆ የተባሉ ወረዳዎች እና ቁልቶ ከተማ አስተዳደር ይኖሩታል።

ጋሞ ጎፋ ዞን #ለሁለት ተከፍሎ ጋሞ እና ጎፋ ዞኖች እንዲዋቀር በረቂቅ አዋጁ ላይ ቀርቧል።

በረቂቅ አዋጁ መሰረት ጎፋ ዞን በስሩ ስምንት ወረዳዎች የሚኖሩት ሲሆን፥ ወረዳዎቹም ዲምባ ጎፋ፣ ገዜ ጎፋ፣ ዛላ፣ ኡባ ደብረ ፀሐይ፣ ኦይዳ፣ ሳውላ ከተማ፣ መለኮዛና ጋዳ ወረዳዎች እና ቡልቂ ከተማ በዞኑ አስተዳደር ተዋቅረዋል።

ለብቻው እንደ አዲስ የሚዋቀረው ጋሞ ዞን ደግሞ 13 ወረዳዎች የሚኖሩት ሲሆን፥ አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ፣ አርባ ምንጭ ከተማ፣ ደራማሎ፣ ቁጫ፣ ዲታ፣ ካምባ፣ ምዕራብ አባያ፣ ጨንቻ፣ ቦንኬ፣ ሰሜን ቦንኬ፣ ጋርዳ ማርታ፣ ቦረዳ እና ምዕራብ ቁጫ የተባሉ ወረዳዎችን ያቀፈ ይሆናል።

በረቂቅ አዋጁ ከሰገን ሕዝቦች ዞን ወጥቶ በዞንነት እንዲደራጅ የውሳኔ ሀሳብ የቀረበበት ኮንሶ ዞን ደግሞ፣ በስሩ ካራት ከተማ አስተዳደር፣ ካራት ዙሪያ፣ ሰገን ዙሪያና ከና የሚሉ የወረዳ መዋቅሮች ተካተዋል።

በክልሉ ነባር ዞን አስተዳደሮች ተጨማሪ አዲስ የወረዳ አስተዳደር እርከኖች እንዲቋቋሙ በረቂቅ አዋጁ ላይ ቀርቧል።

በሰገን አካባቢ ሕዝቦች ዞን አስተዳደር የሚገኙ የቡርጂ፣ አማሮ፣ ዴራሼና አሌ ወረዳ አደረጃጀት በቀጣይ ከሕዝብ ጋር ያለው ውይይት ሲጠናቀቅ የክልል ምክር ቤቱ በሚሰጠው ውክልና መሠረት በመስተዳድር ምክር ቤት እንደሚወሰን ተገልጿል።

በቤንች ማጂ ዞን የተጨማሪ የአዲስ የዞንና የወረዳ አደረጃጀት ጥያቄ በቀጣይ ከሕዝብ ጋር ያለው ውይይት እንደተጠናቀቀ ይወሰናል ተብሏል።

ከቀድሞ የጋሞ ጎፋ ዞን አስተዳደር የቀረበው የኤዞ ወረዳ መሆን ጥያቄ እና በከንባታ ዞን የቀረበው የአዲሎ ወረዳ ጥያቄም በተመሳሳይ የክልል ምክር ቤቱ በሚሰጠው ውክልና መሠረት በመስተዳድር ምክር ቤት እንደሚወሰን ተገልጿል።

የደቡብ ክልል ምክር ቤት በዛሬው ውሎውም በረቂቅ አዋጁ ላይ ውይይት ሲያደርግ የዋለ ሲሆን፥ በነገው እለትም ውይይት ከተደረገበት በኋላ አዲሱ የመዋቅር አደረጃጀት ረቂቅ አዋጅ እንደሚጸድቅ ይጠበቃል።

ምክ ቤቱ በተጨማሪ በእስካሁን ቆይታው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በመወያየት የተለያዩ ውሳኔዎችን ያስተላለፈ ሲሆን የተለያዩ አዋጆችንም አፅድቋል፡፡

ከነዚህም መካከል የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ፣ የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ፣ የጠቅላይ አቃቤ ህግን ለማቋቋም የወጣ አዋጅና ሌሎችም አዋጆች በምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ ጸድቋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ🔝

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐቢይ_አሕመድ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ #በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ በተካሄደው የአፍሪካ መሪዎች ከፍተኛ የምክክር ስብሰባ ላይ ተሳትፈዋል፡፡

via epa
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የትራፊክ አደጋ...

#አርባምንጭ

በአርባምንጭ ከተማ #በዛሬው_ዕለት በደረሰ #የትራፊክ_አደጋ የሰው ህይወት ማለፉ ተሰምቷል።

Via Gamo Zone Administration public Relation office

•ወገኖቼ መነጋገር አለብን! እንደወጣን እየቀረን ነው! በየቦታው በየከተማው በትራፊክ አደጋ ብዙ ዜጎቻችን እያለቁ ነው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ #በአርክቴክቸር የትምህርት ዘርፍ ያስተማራቸውን ተማሪዎች #በዛሬው ዕለት #አስመርቋል

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ሙስጠፌ ተሸለሙ!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን #በዛሬው ዕለት ለሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ መሐመድና ለባልደረቦቻቸው ሽልማት አበርክታለች።

ዛሬ በጅግጅጋ በተካሄደው የኦሮሞና የሶማሌ የህዝብ ለህዝብ መድረክ ላይ የተገኙት የቤተክርስቲያኗ አባቶች ለአቶ ሙስጠፋና ለባልደረቦቻቸው የቤተክርስቲያኗን የክብር ካባ ሸልመዋቸዋል።

ቤተክርስቲያኗ ለአቶ ሙስጠፋና ለባልደረቦቻቸው ሽልማቱን ያበረከተችው በተለይ አዲሱ የክልሉ አስተዳደር ለሰላም ላላው ቁርጠኝነት እውቅና ለመስጠት እንደሆነ በቤተክርስቲያኗ የሶማሌ ክልል ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ መቃሪዎስ ገልጸዋል።

ባለፈው ዓመት በጂግጂጋና አካባቢው በተነሳው ረብሻ በርካታ አብያተ ክርስቲያንና የሃይማኖት አባቶች ጉዳት እንደደረሰባቸው ይታወሳል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia