TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የግንቦት 2015 ዓ.ም የርክበ ካህናት ጉባኤ ባለ 10 ነጥብ መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል። ዛሬ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ሰጥቷል። ቅዱስ ሲኖዶስ ምን አለ ? ምልዓተ ጉባኤው ለቤተ ክርስቲያኗ አንድነት፣ ለሐዋርያዊ ተልእኮ መስፋፋት እና መንፈሳዊ ዕድገት ትኩረት በመስጠት ለቤተ ክርስቲያናን እና ለሀገር ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን ማሳለፉን አሳውቋል።…
#ሰላም
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ ግጭቶች እና አለመግባባቶች በውይይት ይፈቱ ዘንድ የሰላም ጥሪ አቀረበች።
ይህን ጥሪ ያቀረበችው የ2015 ዓ/ም የግንቦት ርክበ ካህናት ጉባኤ መጠናቀቁን ተከትሎ ትላንት በሰጠችው መግለጫ ነው።
ቤተክርስቲያኗ በሀገራችን በአንዳንድ ቦታዎች የሚታዩትን አላስፈላጊ ግጭቶች የዜጐች መፈናቀል፣ ስደት ተወግዶ ሁሉም ዜጋ በሀገሩ በእኩልነት፣ በሰላምና በፍቅር ተከባብሮ በአንድነት እንዲኖር፤ ለማድረግ ግጭቶችና አለመግባባቶች በውይይት እንዲፈቱ የሰላም ጥሪ አስተላልፋለች።
ከዚህ በተጨማሪ ፤ ቤተክርስቲያኗ በመላው ዓለም ጦርነት ባለባቸው ሀገራት ሁሉ ሰላም እና ዕርቅ እንዲሰፍን ተመኝታለች።
@tikvahethiopia

👍891❤104👎62🕊49🙏30🥰9😱3😢2