TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ‼️

በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ሰኞ ምሽት ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች የተማሪዎችን ማደሪያዎች መብራት ካጠፉ በኋላ በተቀሰቀሰ ኹከት ስድስት ተማሪዎች ቆሰሉ። የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር በኹከቱ የሞቱ ተማሪዎች አለመኖራቸውን ጉዳት የደረሰባቸውም ሕክምና ማግኘታቸውን አረጋግጧል። የመማር ማስተማር ሒደቱ ግን ዛሬም እንደተቋረጠ ነው።

በሀገሪቱ ከሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አንፃራዊ በሆነ ሰላም የዘንድሮውን አመት የመማር ማስተማር ስራ ሲያከናውን የቆየው የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ከትናንት ምሽት ጀምሮ በጊቢው በተፈጠረ ሁከት ሰላማዊ ድባቡን ጠፍቷል፡፡ መደበኛ የመማር ማስተማር ስራውም በበተፈጠረው ሁከት ሳቢያ ተቋርጧል፡፡  

የዩኒቨርሲቲው አለም አቀፍና የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ዶ/ር #አለማየሁ_ዘውዴ ትናንት ምሽት ያልታወቁ አካላት በተማሪዎች መኖርያ አካባቢዎች መብራቶች በማጥፋት ባደረጉት እንቅስቃሴ ሁከቱ መፈጠሩን ተናግረዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው ትናንት ምሽት በተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ በሰው ህይወት ላይ ጉዳት ደርሷል በሚል በአንዳንድ ተማሪዎችና የአካባቢው ማህበረሰብ የሚነገረው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን የጠቆሙት ሀላፊው በተማሪዎች ላይ ከባድ የሚባል ጉዳት አለመድረሱን አስረድተዋል ፡፡

ዶ/ር አለማየሁ "ያልታወቁ" በሚል ለተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ መነሻ ያሏቸው አካላት በዩኒቨርሲቲው የሚገኙ ወይም ከዚያ ውጭ የመጡ ስለምሆናቸው ለተነሣው ጥያቄ በፀጥታ አካላት ምርመራ እየተካሄደበት ከመሆኑ ውጭእስካሁን የታወቀ ነገር አለመኖሩን ተናግረዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ስራው እንደተቋረጠ ነው፡፡ ሁከቱን በመሸሽ ግቢውን ጥለው የወጡ ተማሪዎችም ብዙ ናቸው፡፡

የዩኒቨርሲቲው አመራሮቸ፣ የተማሪ ተወካዮችና የአስተዳደሩ ከፍተና የስራ ሀላፊዎች ጋር እየተካሄደ ባለው ውይይት የተቋረጠው ት/ት #በአፋጣኝ ከነገው ዕለት ጀምሮ እንዲጀመር ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ሀላፊው ጠቅሰዋል፡፡

አንዳንድ ወገኖች እንደሚገልፁት በዩኒቨርሲቲው የተፈጠረው ሁከት እና ብጥብጥ #ብሄርን መሰረት ያደረገ ገፅታን የተላበሰ ነው፡፡

ምንጭ፦ DW የአማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የድሬዳዋ ወጣቶች‼️

የዓመታት የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎቻቸው #በአፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው በድሬደዋ ወጣቶች ባካሄዱት ሰልፍ ጠየቁ፡፡

ወጣቶቹ በተለያዩ የከተማው አስተዳደር አካባቢዎች በመዘዋወር ባካሄዱት ሰልፍ ጥያቄያቸውን ባሰሟቸው መፈክሮች  አስተጋብተዋል፡፡

በዚህም ድሬዳዋ ሁሉም ብሔሮችና ብሔረሰቦች በፍቅር በአንድነትና በእኩልነት የሚኖሩባትን መሆኗን ጠቅሰው አብዛኛውን ወጣትና ህዝብ ያገለለ የመንግስት መዋቅርና አሰራር ሊፈርስ እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡

በተግባር ላይ ያለው የፖለቲካ የስልጣን ክፍፍልና አሰራር የአብዛኛውን ህዝብና ወጣት ከልማት ተጠቃሚነት ያገለለ መሆኑን ወጣቶቹ ገልጸዋል፡፡

መዋቅሩ ወጣቱን ለከፋ የመልካም አስተዳደር ችግር የዳረገው በመሆኑ በፍጥነት እንዲቀየር ጠይቀዋል፡፡

በሰልፉ የተካፈለው ወጣት ሰለሞን መክብብ  በሰጠው አስተያየት የአስተዳደሩ ከንቲባ ወጣቶችን ለማናገር የያዙትን ቀጠሮ መሰረዛቸው በወጣቶቹ ዘንድ ቁጣ መቀስቀሱን ተናግራል፡፡

”እኛ ሁሉም ወጣቶች የሚሳተፉበት ውይይት ነው የምንፈልገው ፤ የወጣቶች ወኪል እየተባለ አዳራሽ የሚሰበሰበው እኛን ስለማይወክሉ የውክልና ውይይት አንፈልግም” ብሏል፡፡

”አንድም ባለስልጣን ቀርቦ #ያናገረን የለም፤ ከተማዋ መሪ የላትም፤ የፌደራል መንግስት በአስቸኳይ ጣልቃ ገብቶ ለጥያቄዎቻችን ምላሽ እንዲሰጠን እንፈልጋለን”  ያለው ደግሞ ሌላው የሰልፉ ተካፋይ ወጣት ሲሳይ አየለ ነው፡፡ በሁሉም  መስክ አድሏዊነት የሌለው ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እንዲኖር ጠይቋል፡፡

የኢዜአ ሪፖርተር በከተማው ተዘዋውሮ እንደተመለከተው ዛሬ በከተማ የተካሄደው ሰልፍ ካለፉት ሁለት ቀናት የበለጠ  አብዛኛውን የከተማው  አካባቢ ያዳረሰ ነው። በነበረው ግርግር በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱንና አገልግሎት መሰጪዎች መሰተጓጎላቸውን ተመልክቷል፡፡

በጤና ጣቢያዎችና በድል ጮራ ሆስፒታል የኢዜአ ሪፖርተር ባደረገው ቅኝት የተጎዱ ሰዎች ህክምና አግኝተው ሲመለሱ አይቷል፡፡

#የመከላከያ_ሠራዊት አባላት የወጣቶቹ ቁጣ  በሰላማዊ መንገድ ለማብረድና ለማረጋጋት ያደረጉት ጥረት በሰልፍ አድራጊዎችና በሌላም ህብረተሰብ ዘንድ በአዎንታዊ ጎኑ ድጋፍ አግኝቷል፡፡

በአሁን ሰዓት ሰራዊቱ በድንጋይ የተዘጉትን መንገዶች በማጽዳት ለተሸከርከሪዎች ክፍት እንዲሆኑ በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአቋም መግለጫ ደብዳቤ ልካያለሁ #በአፋጣኝ ውሳኔ ይሰጠኝ ሲል ጠይቋል።

ክለቡ የላከው ልኬያለሁ የሚለው ደብዳቤ👇
https://telegra.ph/FasilKenema-07-10
#DrAbrhamBelay

ዶክተር አብርሃም በላይ በዓዲግራት እና ውቅሮ ከተሞች የመብራት አገልግሎት በሁለት ቀናት ውስጥ እንደሚጀምር አሳወቁ።

ዶ/ር ኣብርሃም ይህን ያሳወቁት በዓዲግራት ከተማ ከአገር ሽማግሌዎች ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት እንደሆና ኢዜአ ገልጿል።

በውይይቱ ላይ የአገር ሽማግሌዎች ተቋርጦ የቆየው በተለይ የመብራት ፣ ቴሌኮም እና የውሃ አቅርቦት #በአፋጣኝ ወደ አገልግሎት እንዲመለስ ጠይቀዋል።

ዶ/ር አብርሃም መብራት በሁለት ቀን ውስጥ እንደሚጀመር ገልፀው ሌሎች መሰረተ ልማቶችን መልሶ የመገንባት ስራ በመከናወን ላይ መሆኑን አብራርተዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
1