TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NewsAlert ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረበ ኤሊያስ የታሰረው ቅዳሜ ማታ እንደሆነ ነው የተሰማው፤ ከታሳሪው ጋር ባለፉት 2 ቀናት የተያዙ 14 ተጠርጣሪዎችን ፖሊስ ዛሬ ጧት ፍርድ ቤት ባቀረባቸው ጊዜ #በሽብር ወንጀል እንደሚከሳቸው መግለጡን አዲስ ስታንዳርድ አስነብቧል፡፡ ችሎቱ ለሐምሌ 29 ቀጥሯል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት ከባለ ሥልጣናት ግድያ ጋር በተያያዘ ነው፡፡

Via #አዲስ_ስታንዳርድ/#wazema/
🗞ቀን ሃምሌ 1/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#COVID19

አሜሪካ ውስጥ ኮሮና ቫይረስ እናሰራጫለን ብለው ያስፈራሩ ሁለት ሰዎች #በሽብር ወንጀል ተከሰሱ።

አንደኛው ተከሳሽ የፍሎሪዳ ነዋሪ ሲሆን የቤት ውስጥ ጥቃት ፈፅሞ በቁጥጥር ሥር ሲውል ፖሊሶች ላይ ምራቁን ተፍቷል፤ ሆን ብሎም አስሏል ተብሎ ነው የተከሰሰው።

የ31 ዓመቱ ግለሰብ ፖሊስ ላይ ከተፋ በኋላ 'ኮሮና ቫይረስ አለብኝ' ሲል አሸብሯል ተብሏል። ሰውዬው ሲመረመር ነፃ መሆኑ ታውቋል።

ሌላኛው የቴክሳስ ነዋሪ ደግሞ በፌስቡክ ገፁ ለሆነ ሰው ከፍዬ መገበያያ ሥፍራ ውስጥ ኮሮና ቫይረስ እንዲስፋፋ አድርጊያለሁ ብሎ በመፃፉ ነው በቁጥጥር ሥር የዋለው።

የአሜሪካ ፍትህ ሚኒስቴር ኮሮና ቫይረስን 'ባዮሎጂካዊ መሣሪያ' ሲል ሰይሞታል። ቫይረሱን ተጠቅሞ ሕገ-ወጥ ድርጊት መፈፀም እስከ አምስት ዓመት ሊያስሳስር ይችላልም ተብሏል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
1