TIKVAH-ETHIOPIA
" ገዳዮች ለፍርድ መቅረብ አለባቸው " ከሰሞኑን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ያሳለፈው አዲስ አደረጃጀት በጉጂ ዞን በተለያዩ ቦታዎች ተቃውሞ እንደገጠመው የቲክቫህ አባላት ከየአካባቢው አሳውቀዋል። ትላንት ከዚህ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ በቦሬ ማቲ በፀጥታ ኃይሎች በተወሰደ የኃይል እርምጃ የሰው ህይወት ስለመጥፋቱ ተሰምቷል። አንድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል " መንግስት በሰላማዊ ተቃውሞ…
" ሠልፉ ያልተፈቀደ ነበር " - የቦሬ ሰላምና ፀጥታ ጽሕፈት ቤት
ትላንት በኦሮሚያ ክልል፣ ጉጂ ዞን ቦሬ ከተማ ከተቃውሞ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ 3 ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች መገደላቸው መግለፁ ይታወሳል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የቦሬ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽሕፈት ቤት ዛሬ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ በሰጠው ቃል ፤ ትላንት በከተማው ስለደረሰው ጉዳት ማረጋገጫ ሰጥቷል።
የፅህፈት ቤቱ ኃላፊ የሆኑት አቶ ተሾመ ቡሌ ትናንት በከተማው በተካሄደው ሠልፍ ጉዳት መድረሱን አረጋግጠው " ሠልፉ ያልተፈቀደ " እንደነበር ገልጸዋል።
ኃላፊው ፤ " አንዳንድ የሠልፉ ተሰታፊዎች በተቋማት ላይ #ድንጋይ በመወርወር እና ገበያ በመበተን ሁከት ለመፍጠር ሞክረዋል " ብለዋል።
" የፀጥታ አባላት የጉዳቱ መጠን ሳይሰፋ ለመቆጣጠር ችለዋል " ሲሉም ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።
Credit : #ዶቼቨለ_ሬድዮ
Photo : Social Media
@tikvahethiopia

👎828👍342😢37🤔12❤7🥰1😱1🕊1
#መቐለ
" የተለያዩ በደሎች እየደረሱብን ነው " ያሉ በትግራይ የሚገኙ የጦር ጉዳተኞች ዛሬ በመቐለ ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄዳቸውን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ከመቐለ ዘግቧል።
ፖሊስ ሰልፉ ለመበተን አስለቃሽ ጭስ ተኩሷል ተብሏል።
የጦር ጉዳተኛ ሰልፈኞቹ ከመቐለ ከተማ ወጣ ብሎ ከሚገኘው " መለስ ካምፓስ የጦር ጉዳተኞች ማእከል " በመነሳት እስከ የትግራይ ክልል አስተዳደር መሥርያ ቤት የተለያዩ መፈክሮች እያሰሙ ነበር የተጓዙት።
ሰልፍ የወጡት በአብዛኛው #ወጣቶች የጦር ጉዳተኞች ፦
- «እየደረሰብን ያለውን አስተዳደራዊ በደል ሕዝብ ይስማልን፣ ይወቅልን»
- «በኛ ስም ከሕዝብ የሚሰበሰብ መዋጮ እኛጋ እየደረሰ አይደለም፤ በተደጋጋሚ ጥያቄ ብናቀርብም ምላሽ አጥተናል»
- «በቂ ምግብና ውኃ እንኳን አጥተን የከፋ ሁኔታ ላይ ነን»
- «የታጋዮች ድምፅ ይሰማ»
- «ትኩረት ለጦር ጉዳተኞች»
- «ተክደናል» የሚሉና ሌሎች ብልሹ አሠራሮች የሚያወግዙ መፈክሮችን ያሰሙ እንደነበር ሬድዮ ጣቢያው ዘግቧል።
ሰልፈኞቹ " ድምፃችንን ለማሰማት ወደ ከተማ እንዳንገባ መቐለ ዩኒቨርስቲ አሪድ ካምፓስ አካባቢ አስለቃሽ ጭስ በመተኮስ ጭምር እንድንበተን ሙከራ ተደርጓል " ሲሉም ተናግረዋል።
ዶቼ ቨለ ሬድዮ ፤ የጦር ጉዳተኞቹ ሰልፍ ከፍተኛ የቁጣ ስሜት ይታይበት ነበር ያለ ሲሆን ሁኔታው በሃይማኖት አባቶች ሸምጋይነት እንዲረጋጋ ተደርጓል ብሏል።
ሰልፈኞቹ የክልሉ አስተዳደር መ/ቤት በሆነው ደጀን ቢሮ በር ቆይታ የነበራቸው ሲሆን የሕወሓት ከፍተኛ አመራር አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ከሌሎች ወታደራዊ መሪዎች ጋር በችግሮቻቸው ዙርያ መወያየታቸውን ሬድዮ ጣቢያው ዘግቧል።
#ዶቼቨለ_ሬድዮ

👍926😢413❤106👎43🤔31🕊19🙏11😱9🥰7