TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
216 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አቶ ታገሰ ጫፎ ከሴናተር ጀምስ ኢንሆፎ ጋር ተወያዩ።

ትላንት ኢትዮጵያ (አ/አ) የገቡት ሴናተር ጀምስ ኢንሆፎ ከኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሠ ጫፎ ጋር ተወያይተዋል።

አፈ ጉባኤ አቶ ታገሠ ጫፎና የአሜሪካ ኮንግረሰ ሴናተር ጀምስ ኢንሆፎ በቀጠናዊና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል።

በውይይቱ አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ፦
- በህዳሴ ግድብ ፣
- በህግ ማስከበር ፣
- በሰብአዊ እርዳታ ተደራሽነት፣
- ከሱዳን ድንበር ማስከበር ሥራ ጋር ተያይዞ ያለበት ደረጃና እየተከናወኑ ያሉትን ተግባራት ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በተጨማሪ ኢትዮጵያ ሁለተኛውን ዙር የህዳሴ ግድብ የሙሌት ሥራ ለማከናወን በዝግጅት ላይ መሆኗን አብራርተዋል።

ሙሌቱ የተፋሰሱን ሃገራት ጥቅም በማይነካ መልኩ እንደሚፈፀምም ገልፀዋል፡፡

ከ "ህግ ማስከበር" ጋር ተያይዞ የተከሰቱ ችግሮችን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት እየተሠራ ነው ብለዋል። የሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ድጋፍ በመደረግ ላይ ነው ብለዋቸዋል።

ኢትዮጵያ ከሱዳን ድንበር ጋር ተያይዞ በየጊዜው የሚነሱ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ኢትዮጵያ ዝግጁ መሆኗን ለሴናተሩ ተናግረዋል፡፡

ሴናተር ጀምስ ኢንሆፍ ምን አሉ ?

በተደረገላቸው አቀባበል ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።

የተሰጠው ማብራሪያ በኢትዮጵያ ውሥጥ እየተደረገ ያለውን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ለመረዳት እንዳስቻላቸው ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በምታከናውናቸው ተግባራት ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውን ሴናተር ጀምስ አረጋግጠዋል፡፡ #FDRE_HoPR

@tikvahethiopia