ደቡብ ክልል‼️
በደቡብ ክልል ኢትዮጵያን ከኬንያ ጋር የሚያዋስነውን ድንበር በህገ ወጥ መንገድ ሊሻገሩ ነበር የተባሉ 25 ኤርትራውያንን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የክልሉ ፖሊስ አስታወቀ። ወጣቶቹ በኬንያ አቋርጠው #ኡጋንዳ የመግባት እቅድ እንደነበራቸው ፖሊስ ገልጿል።
ኤርትራውያኑ ሐሙስ ዕለት የተያዙት በክልሉ በደቡብ ኦሞ ዞን፤ ሐመር ወረዳ ውስጥ ቱርሚ በተባለች አነስተኛ የጠረፍ ከተማ ላይ መሆኑን የዞኑ ፖሊስ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር #ካሳ_ካውዛ ለDW ተናግረዋል፡፡ ኤርትራውያኑ በወጣትነት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ
መሆናቸውን ኃላፊው ገልጸዋል።
“የተያዙበት ምክንያት ባልተለመደ ሁኔታ ወደዚያ በህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ከደረሱ በኋላ ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ ወደ ጭነት መኪና ተዛውረው ሊጓዙ ሲሉ በፖሊስ ጥርጣሬ ተይዘዋል። ሲታዩ ያው በኬንያ በኩል ወደ ኡጋንዳ ካምፓላ መድረስ እንፈልጋለን የሚሉ ወጣቶች
ነበሩ። ወጣቶቹ እነርሱ እንደሚሉት የኤርትራ ዜጎች ነን ነው። በእጃቸው ላይ የያዙት አንዳንድ መታወቂያዎችም ከኤርትራ ትምህርት ቤት የተነሱ መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው። አሁን ወደ ዞናችን ፖሊስ መምሪያ አስመጥተን ወጣቶቹን በዚያው በዞናችን ፖሊስ መምሪያ ግቢ ውስጥ ይገኛሉ” ሲሉ የዞኑ የፖሊስ ኃላፊ ወጣቶቹ እንዴት ሊያዙ እንደቻሉ አስረድተዋል።
ዋና ኢንስፔክተር ካሳ ወጣቶቹን በተመለከተ በቀጣይነት ምን ማድረግ እንዳለባቸው ከክልሉ መንግስት ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የኤርትራ ኤምባሲ እስከአሁን በፖሊስ እጅ በሚገኙት ኤርትራዊያን ጉዳይ ላይ ያለው ነገር አለመኖሩን ተዘግቧል።
ምንጭ፦ DW አማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ፎቶ📸አቶ ገዱ፣ አቶ ለማና ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ #ኡጋንዳ
በውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሚመራውና የመከላከያ ሚኒስትር ክቡር አቶ ለማ መገርሳና እና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ የሚገኙበት የልዑካን ቡድን በዛሬው ዕለት ከክቡር የኡጋንዳ ፕሬዝዳንት የዎሪ ካጉታ ሙሲቪኒ ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይቱ ፕሬዝዳንት ሙሴቪኒ ኢትዮጵያና ኡጋንዳ ያላቸውን ታሪካዊ ግንኙነት በማስታወስ ይህ ግንኙነት ይበልጥ ሊጠናከር በሚችልበት ሁኔታ ላይ ጠንክሮ መስራት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡ በነገው ዕለት የሚከፈተው ሶስተኛው የኢትዮ-ዩጋንዳ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ሁለቱ አገሮች ግንኙነታቸው የበለጠ እንዲጠናከር ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል፡፡
Via የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

👍1
#ኡጋንዳ
የውጭ ጉዳይ እና የመከላከያ ሚንስትሮች #በኡጋንዳ ከሚኖሩ #ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያዩ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸውና የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ በኡጋንዳ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያይተዋል፡፡ ሚንስትሮቹ ከኢትዮጵያዊያኑ ጋር የተወያዩት በሀገሪቱ እየተካሄደ ባለው ለውጥ ዙሪያ ነው ተብሏል፡፡ ውይይቱ ከ3ኛው የኢትዮ ኡጋንዳ የሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለጎን የተካሄደ ነው።
Via #FBC

" ሁለቱም ወገኖች ሰላም፣ ጸጥታና የኢትዮጵያ መረጋጋት ምኞታቸው መሆኑን ገልፀውልኛል " - ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ
በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ የመንግስትን እና የህወሃትን አመራሮችን ማነጋገራቸውን ካስታወቁ በኋላ መግለጫ አውጥተዋል፡፡
ኦባሳንጆ ሁሉም ወገኖች ወታደራዊ ፍልሚያውን እንዲያቆሙ ጠይቀዋል፡፡
ከመንግስትም ሆነ ሽብርተኛ ተብሎ ከተፈረጀው ህወሃት በኩል የሰላም ፍላጎቶች መኖራቸውን የገለጹት ከፍተኛ ተወካዩ ‘የሰላም መንገዱ ምን ይሁን’ የሚለው ግን ልዩነታቸው እንደሆነ ጠቅሰዋል።
የአፍሪካ መሪዎችና ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ ሕብረቱ የጀመረውን የማሸማገል ጥረት እንዲደፉ እና ግጭቱን ሊያባብሱ ከሚችሉ ነገሮች እንዲቆጠብም ኦባሳንጆ ጥሪ አቅርበዋል።
ኦባሳንጆ፥ "ሆን ተብሎም ይሁን ባለማወቅ ግጭቱን የሚባብሱና ወደከፋ ደረጃ ከሚያደርሱ ንግግሮች መቆጠብ ያስፈልጋል" ብለዋል ።
ኦባሳንጆ፤ ውጊያው ከቆመ የንግግር ዕድል እንደሚኖር የገለጹ ሲሆን አሁን ባለው ሁኔታ ውጊያ እየተደረገ ግን ለመነጋጋር የሚመች እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡
ኦባሳንጆ ፥ የኦሮሚያ እና አማራ ክልል አመራሮችን ማግኘታቸውን በመግለጫቸው ላይ የገለፁ ሲሆን በቀጣይ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ የአፋር ክልል አመራሮችን እንደሚያገኙ አሳውቀዋል።
ኦባሳንጂ ይህ የማሸማገል ስራ እንዲሳካ ቁርጠኛ እንደሆኑ የገለጹ ሲሆን ፦
- #የኬንያ፣
- #ኡጋንዳ፣
- #ጅቡቲ፣
- #ደቡብ_ሱዳን፣
- #ሶማሊያ እና ሱዳን መሪዎችን ማግኘታቸውን አስታውቀዋል፡፡
ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አስማሚ ሁኔታ ይፈጠራል ብዬ አስባለሁ ያሉት ኦባሳንጆ ሁለቱም ወገኖች ሰላም፣ ጸጥታና የኢትዮጵያ መረጋጋት ምኞታቸው መሆኑን እንደገለጹላቸው አሳውቀዋል።
Credit : #Al_AIN
Pic : AU
@tikvahethiopia

👍4