TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
መቐለ ዩኒቨርሲቲ👆

የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት በግቢው ውስጥ ደም እየለገሱ ይገኛሉ!! #መቐለ_ዩኒቨርሲቲ #Mekelle_University

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአንድ እናት ልጆች ነን መስመር አይለየን...
የአንድ ቤት ልጆች ነን መስመር አይለየን...

#መቐለ_ዩኒቨርሲቲ የሰላም አምባሳደር!
#ፍቅር #ተስፋ #አንድነት #መቐለ_ዩኒቨርሲቲ
ኦቦ #በቀለ_ገርባ ~~ #መቐለ_ዩኒቨርሲቲ

የፌደራል ሥርዓት አወቃቀር #ለቋንቋዎች እድገት መሠረት ከመጣሉ ባለፈ ኅብረተሰቡም ባደገበት ቋንቋ የመንግሥት አገልግሎት ለማግኘት እንደሚያስችለው የቋንቋ ምሁሩና ፖለቲከኛው አቶ #በቀለ_ገርባ ገለጹ። "የኢዮጵያ ቋንቋዎችና ጠቀሜታዎች" በሚል የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ያዘጋጀው መድረክ ዛሬ ተካሂዷል።

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/Mekelle-07-25
የTIKVAH-ETH #የStopHateSpeech ሀገር አቀፍ ዘመቻዎች/በዩኒቨርሲቲ ደረጃ/ና በየተለያዩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ውስጥ የተደረጉ ጉብኝቶችን ለመከታተል #የዩትዩብ ቻናላችንን ይጎብኙ!

#ሀረማያ #ጅማ #ወልቂጤ #ሀዋሳ #ወላይታ_ሶዶ #አርባምንጭ #መቐለ #ዋቻሞ #ወሎ #ደብረብርሃን #ወልዲያ

Watch ""የአንድ እናት ልጆች ነን" በመቐለ ዩኒቨርሲቲ #TIKVAH_ETHIOPIA" on YouTube
https://youtu.be/qjyt56okb3U
#መቐለ_ዩኒቨርሲቲ

በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ እና በዘንድሮው ዓመት ለምረቃ የሚበቁ ተማሪዎች ምንም አይነት ችግር ሳይገጥማቸው መቆየታቸውን ተናግረው ሆኖም ግን ለከፍተኛ ርሃብ እና የውሃ ጥም ተዳርገው መቆየታቸውንና በአሁኑ ሰዓት የመከላከያ ሰራዊቱ ድጋፍ እያደረገላቸው ይገኛል።

በአሁን ሰዓት ተማሪዎቹ ምንም አይነት ምግብ የሚያዘጋጁ ሰራተኞች በቅጥር ግቢው ባለመኖራቸው ምክንያት እየተቸገሩ መሆናቸውን በመግለፅ መንግስት እና የሚመለከታቸው አካላት በጉዳዩ ላይ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጣቸውም በአፅንኦት ጠይቀዋል።

መረጃውን የላከልን በራያ ግንባር የሚገኘው ሃምሳ አለቃ አበበ ሰማኝ ነው።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#መቐለ_ዩኒቨርሲቲ

ሀምሳ ሁለት (52) ተማሪዎችና አንድ መምህር ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ ኩሓ ካምፓስ በመውጣት በመኪና ወደ አባላ ከተማ (አፋር) መጓዛቸውንና ከዚያም ከአባላ ወደ አፍዴራ ሲጓዙ 'ስልሳ ስድስት' የሚባል የፍተሻ ጣቢያ ላይ ላይ በአፋር ክልል ፖሊስ አግኝቶ ተማሪ መሆናቸው ካረጋገጠ በኋላ ዛሬ ከሰዐት ለሠመራ ዩኒቨርሲቲ ማስረከቡን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ሰምቷል።

በመጀመሪያ 19 ተማሪዎች እና አንድ መምህር በሠመራ ዩኒቨርሲቲ ድጋፍ ዛሬ ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸው የተነገረ ሲሆን ቀሪ 33ቱን የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ነገ ጠዋት ተማሪዎቹን በባስ አሽኛኝት እንደሚያደረግላቸው የህዝብ ግንኙነት ባለሙያው ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አረጋግጠዋል።

ተማሪዎቹ በጉዟቸው ወቅይ ምንም የተለየ ችግር ባይገጥማቸውም ፤ ምግብ ባለማግኘታቸው አስከፊ ግዜ እንዳሳለፉ አልደበቁም። ከ52ቱ ተማሪዎች አንድ ሴት ተማሪ ያለች ሲሆኑ አብዛኛዎች የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ናቸው።

በተማሪዎቹ ጉዳይ አስተያየት የጠየቅነው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር "አዲስ ነገር ሲኖር ጠቅለል አርገን" እናሳውቃለን ብሏል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መረጃዎች በ @tikvahuniversity በስፋት ማግኘት ይቻላል።

https://tttttt.me/joinchat/RYD_4tbNBwRoKR2h

@tikvahethiopia