TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ላለፉት አመታት የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽንን በሃላፊነት ሲመሩ የቆዩት ብ/ጄኔራል #ክንፈ_ዳኘውና የኢንሳ ዳይሬክተር ብ/ጄኔራል ተ/ብርሃን ወ/አረጋይ ትናንት ምሽት በቁጥጥር ስር ውለዋል። ሱዳን ድንበር አካባቢ የተያዙት ሁለቱ #ተጠርጣሪ ግለሰቦች ዛሬ ከሰአት ወደ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ተሰምቷል።

ምንጭ፦ አሀዱ ሬድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጋምቤላ ነዋሪዎች ጥንቃቄ አድርጉ‼️

በጋምቤላ ከተማ #ሀሰተኛ የብር ኖቶችን ሲያዘዋውር ደርሸበታለሁ ያለውን አንድ #ተጠርጣሪ ግለሰብ #በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ።

በከተማውና አካባቢው የሀሰተኛ የብር ኖት ዝውውር #እየተበራከተ በመምጣቱ ህብረተሰቡ #ጥንቃቄ እንዲያደርግ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የጋምቤላ ከተማ ኦፔኖ ቅርንጫፍ አሳስቧል።

በጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀልና የፎረንሲክ ምርመራ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር #ቱት_ኑዑት ለኢዜአ እንደገለጹት ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ሊውል የቻለው የልብስ ግብይት ያካሄደባቸው ባለሱቆች የሰጣቸው የብር ኖት ሀሰተኛ መሆኑን ከተረዱ በኋላ በሰጡት ጥቆማ መሰረት ነው።

ፖሊስ ባካሄደው የማጣራት ስራ ግለሰቡ ለባሱቆች ከሰጣቸው 20 ሺህ ሀሰተኛ ባለ መቶ የብር ኖት በተጨማሪ አንድ ካርቶን ሀሰተኛ የብር ኖት ወደ ወረዳዎች እንደተሰራጨ መረጃ ማግኘቱን ተናግረዋል።

በወረዳዎች የተሰራጨውን ሀሰተኛ የብር ኖት ለመያዝም ፖሊስ አስፈላጊውን ክትትል እያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።

”በአሁኑ ወቅት በቁጥጥር ስር በዋለው ግልሰብ ላይ  የምርመራና የማጣራት ስራ እየተከናወን እንደሚገኝ ጠቁመው ሂደቱ እንደተጠናቀቀም ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት የሚላክ ይሆናል “ብለዋል።

በኢትዮጰያ ንግድ ባንክ የጋምቤላ ከተማ ኦፔኖ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ግሩም አበራ በበኩላቸው  በጋምቤላ ከተማና አካባቢው በርካታ ሀሰተኛ የብር ኖት ስርጭት  እንዳለ ምልክቶች ስለሚያሳይ ህብረተሰቡ  በግብይት ወቅት ጥንቃቄ ሊያደረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በቅርቡ በአንድ ደንበኛ ወደ ባንኩ ሊገባ ከመጣ 90 ሺህ ባለ መቶ የብር ኖት ውስጥ 20 ሺህው  ሀሰተኛ የብር ኖት ሆኖ መገኘቱንና ጉዳዩንም ለፖሊስ በማሳወቅ እንዲያዝ መደረጉን ገልጸዋል።

ከአሁን በፊት ይገኝ የነበረው የሀሰተኛ የብር ኖት አንድና ሁለት ብቻ እንደነበር ያስታወሱት ስራ አስኪያጁ በተወሰነ ብር መካከል ብቻ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሀሰተኛ የብር ኖት መገኘቱ በርካታ ስራጭት መኖሩን እንደሚያሳይ ተናግረዋል።

ህብረተሰቡ ግብይት በሚያደርግበት ወቅት በተለይም በብር ኖቶች ላይ ያለውን የዘንግ ምልክቱን በማየት መጠቀም እንዳለበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢ.ዜ.አ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከ33 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር በቦሌ ኤርፖርት በኩል ወደ ዱባይ ልታስወጣ የነበረች #ተጠርጣሪ ተያዘች፡፡ግለሰቧ 33 ሺህ 250 የአሜሪካ ዶላርና 6 ሺህ 500 የሳውዲ ሪያል በቦሌ ኤርፖርት በኩል ወደ ዱባይ ልታስወጣ እያለች ነው በቁጥጥር ሥር የዋለችው፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀዋሳ

በሐዋሳ ለግርግሩ ተጠያቂ የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆናቸው ተገለፀ። አሁንም ከሁከቱ ጋር በተያያዘ #ተጠርጣሪ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየተሰራ ነው፤ በከተማይቱ የተፈጥረውን ግጭትና ሁከት ለመቆጣጠር ተችሏል ሲሉ የደቡብ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ተጠባባቂ ቢሮ ሃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ ለBBC ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia